Telegram Web Link
ዘንድሮ በኦንላይን ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች የይለፍ ቃላቸውን ከየት ማግኘት እንደሚችሉ በተደጋጋሚ ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲን እየጠየቁ ይገኛሉ፡፡

የተፈታኝ ተማሪዎች Username እና Password ከዚህ በፊት ለትምህርት ቢሮዎች መላኩን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

በመሆኑም እስካሁን Username እና Password ያላገኛችሁ ተፈታኞች፤ ከትምህርት ቤት አስተባባሪዎች ማግኘት ትችላላችሁ።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
ሠመራ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ለሚጀምረው ዓመታዊ የስነ-ጽሁፍ ውድድር 'ፈኒ ዶጊሳ' የምዝገባ ጊዜን እስከ ነገ ግንቦት 27/2016 ዓ.ም አራዝሟል፡፡

የመመዝገቢያ አማራጮች፦
የተቋሙ ተማሪዎች፣ መምህራን እና ሠራተኞች በዩኒቨርሲቲው የምርምርና ቴክኖሎጂ ሸግግር ም/ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ መመዝገብ የምትችሉ ሲሆን ከዩኒቨርሲቲው ውጭ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች በስልክ ቁ. 0953990560 ላይ ሙሉ ስም፣ የሥራ ዘርፍና ቦታ፣ የምትወዳደሩበትን ዘርፍና ይዘት በማካተት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት ወይም በሞባይሉ የቴሌግራም አካውንት በመላክ መመዝገብ ትችላላችሁ ተብሏል፡፡

@tikvahuniversity
ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የቢዝነስና ቴክኖሎጂ ማበልፀጊያ ማዕከል አስመርቋል፡፡

ማዕከሉ የሥራ ዕድል ፈጣሪዎች (ስታርታፖች) ስልጠና የሚያገኙበትና ሃሳባቸውን ወደ ንግድ የሚቀይሩበት ይሆናል ተብሏል፡፡

ማዕከሉ ለዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራን እና በድሬዳዋና አካባቢዋ ለሚገኙ ወጣቶች የሃሳብ ማበልፀጊያ ማዕከል ሆኖ እንደሚያገለግል ተገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 14 ስታርታፕ ቢዝነሶችን ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር ወደሥራ ለማስገባት እየሠራ እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ፈተና (DELF A1 & DELF A1) ሰኔ 1 እና 2/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

ፈተናው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ እና በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሴስ ትብብር የሚሰጥ ነው፡፡

ፈተናው የሚሰጠው በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ማራኪ ካምፓስ መሆኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አካዳሚ በቡና ጥራት ቁጥጥር እና ቅምሻ ስልጠና በቀን እና በማት መርሐግብሮች ምዝገባ እያከናወነ ይገኛል!

የማታ መርሐግብር የመጀመሪያ ባች ተማሪዎች ትምህርት ሰኔ 3/2016 ዓ.ም ይጀምራል።

ስልጠናው ከሦስት እስከ ሦስት ወር ከግማሽ ይሰጣል። ክፍያ፦ ብር 45,000

ይመዝገቡ!!

በተከታዩ ሊንክ ይመዝገቡ 👇

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSe9XBw_BXSv56zYBUUjdaDypd74CUlIn4NKPci3vZswfcPbrw/viewform?usp=sf_link

@tikvahuniversity
ይለማመዱ!

የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የኦንላይን የመፈተኛ ፕላትፎርም አጠቃቀምን ይለማመዱ!

ፕላትፎርሙን እንዴት መጠቀምና እንዴት ፈተናውን መውሰድ እንደሚቻል ለማሳየት በትምህርት ሚኒስቴር እና በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የተዘጋጀን የአራት ደቂቃ ገላጭ ቪዲዮ በተከታዩ ሊንክ በመግባት ይመልከቱ፡፡ ራስዎን ለፈተናው ያዘጋጁ!

ቪዲዮውን ይመልከቱ 👇
https://www.youtube.com/watch?v=PdAu-FI-Q5M


@tikvahuniversity
የተለያዩ የትምህርት ተቋማት ዘንድሮ በኦንላይን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለሚወስዱ ተማሪዎች ሞዴል ፈተና እየሰጡ ነው።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች ትናንት የሞዴል ፈተና በዩኒቨርሲቲው አፄ ቴዎድሮስ ግቢ ሰጥቷል።

ትምርት ቤቱ በተያዘው የትምህርት ዘመን በሶሻል እና በተፈጥሮ ሳይንስ በድምሩ 57 ተማሪዎችን ለአገር አቀፍ ፈተና እያዘጋጀ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ባለፉት ሁለት ዓመታት ለ12ኛ ክፍል ፈተና ያስቀመጧቸውን ተማሪዎች በሙሉ ካሳለፉ ጥቂት ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ ነው።

@tikvahuniversity
ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸው ስህተትን መቀነስን ጨምሮ በርካታ ጠቀሜታዎች እንዳሉት ትምህርት ሚኒስቴር ገለፀ።

የበይነ መረብ ፈተና ለስህተት በር አይከፍትም

የበይነ መረብ ፈተና አንድ ጥያቄ ሳይመልሱ ወደ ፈለጉት ጥያቄ በአንድ Click የመሔድ እንዲሁም ተመልሰው መስራት የሚፈልጉትን ጥያቄ Flag በማድረግ ተመልሶ የመስራት ዕድልን ይሰጣል።

ጊዜ ቆጣቢ ነው

በአንድ Click የፈተና ጥያቄን መልስ ለመስጠት ያስችላል። እንዲሁም ምን ያህል ደቂቃ እንደተጠቀሙ ከመፈተኛ ስክሪን ላይ ማየት ስለሚቻል ጊዜን በአግባቡ ለመጠቀም ያስችላል።

የተሻሻለ የመረጃ ቋት አለው

የበይነ መረብ ፈተናዎች በቂ የፈተና መረጃዎችን ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ በማከማቸት ለተፈታኞች አመጣጥኖ ያቀርባል፡፡

የተሰሩ ጥያቄዎችን መልስ በፍጥነት በራሱ ይልካል

በፈተና ወቅት ጥያቄዎቹን ሰርተው ሳያጠናቀቁ የተሰጠው ደቂቃ ካለቀ የሰሩትን በጠቅላላ በራሱ በፍጥነት ይልካል።

ፈጣን ግብረ መልስ ይሰጣል

በበይነ መረብ ፈተናዎች ሲሰጡ ውጤታቸው ከሌላው ጊዜ በተለየ ፈጥኖ የመታወቅ ዕድል ይሰጣል።

ተማሪዎች በቤታቸው እያደሩ እንዲፈተኑ ዕድል ይሰጣል

ትምህርት ቤቶች የተደራጀ የኮምፒውተር ቤተሙከራ ካላቸውና የመፈተኛ ክላስተር ለመሆን አስፈላጊውን መስፈርቶች ማሟላታቸው ከተረጋገጠ ተማሪዎች በተማሩበት ትምህርት ቤት ሆነው እንዲፈተኑ ዕድል ይፈጥራል። #MoE

@tikvahuniversity
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስ ገዝ የመሆን ሒደቱን ለማጠናቀቅ በቀጣይ አምስት ዓመታት 60 ቢሊዮን ብር እንደሚያስፈልገው ተገለፀ።

ዩኒቨርሲቲው የራስ ገዝነት መንገዱን ከጀመረ ስምንት ወራትን ያስቆጠረ ሲሆን፤ የሽግግር ሒደቱ ሁለት ዓመት ይፈጃል ተብሏል።

አሁን ላይ የፋይናንስ አቅርቦት እጥረት ለሽግግር ሒደቱ ችግር እንደሆነባቸው የሽግግር ሒደቱ እስከሚጠናቀቅ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት በመሆን እያገለገሉ ያሉት ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ለመሆን ለሚሠራቸው ሥራዎች በቀጣይ አምስት ዓመታት 60 ቢሊዮን ብር የሚያስፈልገው ሲሆን፤ ከመንግሥት እና ከተቋሙ ገቢ በሚቀጥሉት አምስት ዓመታት 25 ቢሊዮን ሊያገኝ እንደሚችል ገልፀዋል። የ 35 ቢልዮን ብር ክፍተት ሊፈጠር እንደሚችልም አስረድተዋል፡፡

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም ይሰጣል።

በተመሳሳይ የስድስተኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ፈተናዎቹን ለመስጠት በቂ ዝግጅት መደረጉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል ፈተናውን 86,671 ተማሪዎች እንዲሁም የስድስተኛ ክፍል ፈተናውን 86,217 ተማሪዎች እንደሚወስዱ በቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር ዲናኦል ጫላ ለኢዜአ ተናግረዋል፡፡

ከተፈቀዱ የፈተና ቁሳቁሶች ውጪ፣ ዲጂታል ሰዓትን ጨምሮ ማንኛውንም ኤሌክትሮኒክስ መገልገያዎችን ይዞ ወደ ፈተና መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡

@tikvahuniversity
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና ከፊታችን ሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ ይጠበቃል።

የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና ጊዜን የተመለከቱ በርካታ ጥያቄዎች ለቲክቫህ ደርሰዋል፡፡

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የተመለከተው ጊዚያዊ የሪሚዲያል ተማሪዎች የፈተና መርግብር፤ ፈተናው ከሰኔ 3-10/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ያሳያል።

በዚህም የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 3 እስከ 6/2016 ዓ.ም እንዲሁም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ከሰኔ 6-10/2016 ዓ.ም ፈተናቸውን እንደሚወስዱ ይጠበቃል። የፕሮግራም ለውጥ የሚኖር ከሆነ የምናሳውቃችሁ ይሆናል።

ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ብቻ የሚሰጥ ሲሆን፤ ተቋማቱ ስለፈተናው ገለፃ ለተፈታኞች መስጠት መጀመራቸውን ተመልክተናል።

ዘንድሮ 78 ሺህ የሪሚዲያል ተማሪዎች #ከባህርዳር_ዩኒቨርሲቲ ውጪ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን ከታህሳስ ወር ጀምሮ ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡

@tikvahuniversity
በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ ከፍለው ለመማር የማይችሉ ተማሪዎች የባንክ ብድር እንዲያገኙ የሚረዳ ሕጋዊ አሠራር እንዲመቻች ተጠየቀ፡፡

በ2015 ዓ.ም. ፀድቆ ወደ ሥራ የገባውና ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ የሚያደርገው አዋጅ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ከስምንት ወራት በፊት ወደ ሥራ ማስገባቱ ይታወቃል፡፡

በመጪዎቹ ሁለት ዓመታት ተጨማሪ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎችን ወደ ራስ ገዝነት ለማሸጋገር ዕቅድ ተይዞ እየተሠራ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ምንም እንኳ ተጠያቂነቱ ኖሮ በተወሰነ ደረጃ መንግሥት በገንዘብ የሚደግፋቸውም ቢሆኑም፣ ራሳቸውን በራሳቸው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት የፋይናንስ፣ የአስተዳደር፣ የአካዴሚክ፣ የሰው ሃብት እና መሰል ነፃነት አዋጁ ያጎናፅፏቸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ራስ ገዝ ሆኖ ሥራ በጀመረው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ከፍለው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ክፍያው በከፍተኛ መጠን እንደጨመረባቸው እየተናገሩ ነው፡፡

ወደፊት ራስ ገዝ የሚሆኑ ዘጠኝ ዩኒቨርሲቲዎች ወደ ሥራ ሲገቡ አሁን ያለው ሁኔታ ጥሩ ውጤት ያላቸው ተማሪዎች ከፍለው እንዳይማሩ ይገድባል የሚል ሥጋት እየተሰማ ነው፡፡

የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጀማል የሱፍ (ዶ/ር) በጉዳዩ ላይ ለሪፖርተር በሰጡት አስተያየት፣ ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ሲሆኑ ለተማሪዎች የሚሰጥ ብድር መመቻቸት ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ለሚ ጉታ (ዶ/ር) በተመሳሳይ፤ መንግሥት በውጭው ዓለም የተለመደውን ለተማሪዎች ብድር የሚቀርብበት አሠራር ሊያስብበት ይገባል ብለዋል፡፡

ሙሉውን ያንብቡ 👇
https://www.ethiopianreporter.com/130161/

@tikvahuniversity
#Update

በሰኔ 2016 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተናን በድጋሚ (Re-exam) ለመውሰድ ያመለከታችሁ በምዝገባ ወቅት የተላከላችሁን የቴሌ ብር የክፍያ ማረጋገጫ (Tele Birr Payment Transaction Code) በመጠቀም የመፈተኛ የይለፍ ቃል (Password) https://exam.ethernet.edu.et በኩል ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ የመውጫ ፈተና የምትፈተኑ ዕጩ ተመራቂዎች የይለፍ ቃል (Password) የምታገኙት ከምትማሩበት ተቋም ብቻ መሆኑ ተገልጿል፡፡

Note:

ማንኛውም የድጋሚ (Re-exam) ተፈታኝ በምዝገባ ወቅት ያልተሟሉ መረጃዎችን በሲስተሙ በኩል ማሟላት ይጠበቅበታል። ሁሉም ተፈታኞች ወደፊት በሚገለፀው ፕሮግራም መሰረት የሞዴል ፈተናን መውሰድ ይኖርባቸዋል ተብሏል።

@tikvahuniversity
ዛሬ ያበቃል!

በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (INSA) የተዘጋጀ "ብሔራዊ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ" ፕሮግራም (National Cyber Talent Challenge Program) የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

በሳይበር ደህንነትና ተያያዥ ዘርፎች ልዩ ተሰጥኦ እና ፍላጎት ያላችሁ ኢትዮጵያውያን በቻሌንጁ ላይ መሳተፍ የምትችሉ ሲሆን፤ Cyber Security, Cyber Development, Embedded Systems, and Aerospace የታለንት መስኮች ናቸው፡፡

ምዝገባው ዛሬ ግንቦት 30/2016 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡

ለመመዝገብ፦ https://talent.insa.gov.et

@tikvahuniversity
#BahirDarUniversity

ባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ጥሪ ሊያደርግ ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው በፀጥታ ችግርና ሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች በ2016 ዓ.ም አዲስ ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ ሳያደርግ ቆይቷል።

ረቡዕ ግንቦት 28/2016 ዓ.ም ውይይት ያደረገው የዩኒቨርሲቲው ሴኔት፣ በሰኔ ወር መጨረሻ ለተማሪዎቹ ጥሪ እንዲደረግ መወሰኑን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ ከተቋሙ ለማረጋገጥ ችሏል፡፡

በዚህም ከሐምሌ ወር አጋማሽ ጀምሮ ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን በዩኒቨርሲቲው በመገኘት መከታተል ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ሲያጠናቅቁ፣ ትምህርት ሚኒስቴር በልዩ ሁኔታ ፈተና እንደሚያዘጋጅላቸውም ታውቋል።

@tikvahuniversity
አነስተኛ ቢዝነሶችን ለማሳድግ ቆርጦ የተነሳው አዲሱ የGig-Innovate ፕሮግራም መመዝገቢያ ጊዜ ሊጠናቀቅ 3 ቀን ብቻ ቀረው!

ማመልከቻውን አጠናቀው ዛሬውኑ ያስገቡ!

የምታገኙት ድጋፍ፦

- የቢዝነስዎን ሂደቶች የሚያቃልል ቴክኖሎጂ
- ኳሊፋይድ ፈይናንሲንግ
- የፋይናንስ፣ የህግ አና የቢዝነስ አማካሪዎች

መመዝገቢያ ሊንክ 👇

http://mesirat.acceleratorapp.co/application/new?program=mesirat-entrepreneurs-application-form-project-X

#MesiratEthiopia #SmallBusiness #Grow #BusinessDevelopment
የ2016 ዓ.ም የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናዎች የጊዜ ሰሌዳ

በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 4 እና 5/2016 ዓ.ም እንዲሁም የስድስተኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 12 እስከ 14/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል።

በከተማዋ የስምንተኛ ክፍል ፈተናን 86,671 ተማሪዎች እንዲሁም የስድስተኛ ክፍል ፈተናን 86,217 ተማሪዎች እንደሚወስዱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ መግለፁ ይታወሳል፡፡

(የፈተናዎቹን የጊዜ ሰሌዳ ከላይ ይመልከቱ፡፡)

@tikvahuniversity
Tikvah-University
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሊመረቅ ነው። ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት በግንባታና ግብዓት በማሟላት ሒደት ላይ የቆየው ሆስፒታሉ፤ ሰኔ 01/2016 ዓ.ም ተመርቆ አገልግሎት መሥጠት ይጀምራል፡፡ ተቋሙ "አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል" በሚል ስያሜ እንዲጠራ መወሰኑም ታውቋል፡፡ ሆስፒታሉ 600 የህሙማን አልጋዎች…
የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የማስተማሪያ እና ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚመረቅበት ጊዜ ተራዝሟል፡፡

ሆስፒታሉ ነገ ሰኔ 1/2016 ዓ.ም እንደሚመረቅ ዩኒቨርሲቲው ገልፆ የነበረ ቢሆንም፤ "በሌሎች ክልላዊ የሥራ ጉዳዮች ምክንያት" የምረቃው ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ እንዲታደመ ለተጋበዙ አካላት ይቅርታ የጠየቀው ዩኒቨርሲቲው፤ በቀጣይ የሆስፒታሉ ምረቃ የሚከናወንበትን ጊዜ እንደሚያሳውቅ ገልጿል፡፡

@tikvahuniversity
2024/06/08 02:45:11
Back to Top
HTML Embed Code: