Telegram Web Link
ዩኒቨርሲቲዎች ከነገ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተፈታኞችን ዛሬ ተቀብለው ያጠናቅቃሉ፡፡

ተማሪዎች ከአርብ ሰኔ 20/2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደየተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ ቆይተዋል። በዛሬው ዕለትም ገለጻ ተሰጥቷቸዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም እንደሚሰጥ ይታወቃል። በወጣው መርሐግብር መሰረት ነገ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ይጀምራል፡፡

ምስል፦ የተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
ነገ ሰኔ 23/2017 ዓ.ም መሠጠት የሚጀምረውን ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ለገቡ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ (Orientation) ተሰጥቷል።

የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎቹ የዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው ሰላማዊና ስኬታማ የፈተና ግዚ እንዲኖራቸው የሚያግዛቸው ነው። በሆነ መንገድ በውጤት ያጠናቅቁ ዘንድ አጠር ያለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ሰኔ 22/2017 ዓ.ም ተሰጥቷቸዋል፡፡

ተፈታኞቹ በዩኒቨርሲቲዎቹ በሚኖራቸው ቆይታ ስለሚያገኙት አገልግሎቶች (ምግብ፣ መኝታ፣ ጤና...) እና ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች ግንዛቤ እንዲያገኙ ተደርጓል።

በተጨማሪም በፈተና ወቅት ስለሚከተሏቸው ህግና ደንቦች እንዲሁም ተያያዥ ስለሆኑ የፈተና ሂደቶችና አተገባበሮችን በሚመለከት ገለጻ ተሰጥቷቸዋል።

ምስል፦ ጎንደር፣ መቅደላ አምባ፣ ቦንጋ፣ ወልድያ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች

@tikvahuniversity
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦንላይን ለሚወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች አጠቃላይ ገለጻ (Orientation) ተሰጥቷል፡፡

ምስል፦ በአብሮህት ቤተ መፃሕፍት እና በአድዋ ሙዚየም የፈተና ማዕከላት ፈተና ለሚፈስዱ ተፈታኞች የተሰጠ ገለጻ

@tikvahuniversity
የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ለመፈተን ወደተቋሙ ለገቡ ተማሪዎች የግንዛቤ ማስጨበጪያ ሰጥቷል።

ተማሪዎቹ በተቋሙ በሚኖራቸው ቆይታ ማሟላት የሚገቧቸውን እና የሚያገኟቸውን አገልግሎቶች በተመለከተ ኦረንቴሽን ተሰጥቷል

በኢንስቲትዩቱ ከአራት ትምህርት ቤቶች የተመደቡ ከ800 በላይ ተማሪዎች እንደሚፈተኑ ተገልጿል።

@tikvahuniversity
#ESSLCE #Schedule

ነገ የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዙር የፈተና መርሐግብር

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

@tikvahuniversity
2025/06/30 01:11:40
Back to Top
HTML Embed Code: