#WallagaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን ከ2 ሺህ በላይ ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ናቸው፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 13 በሦስተኛ ዲግሪ እና 22 በስፔሻሊቲ የተመረቁ ይገኙበታል።

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በጊምቢ እና በሻምቡ ካምፓሶች ያስተማራቸውን 536 ተማሪዎች ትናንት ማስመረቁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
Forwarded from HaHuJobs (HahuJobs)
በ 10 ሳምንታት ፣ ተፈላጊ ይሁኑ!

HaHuMuya ባዘጋጀው የክረምት ኮርስ በሳምንት 3ቀን ብቻ እየተማሩ በ2 ወር ከ15 ቀን ውስጥ የሰርተፊኬት ባለቤት ይሁኑ።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥራችን ይደውሉ +251988007773/75/05 ወይም በአድራሻችን መገናኛ ወደ ሾላ በሚወስደው መንገድ ግሬስ ሲቲ ሞል አጠገብ ሲሳይ ፕላዛ 3ኛ ፎቅ መምጣት ይችላሉ!

@hahujobs | @hahujobs_bot
HaHuJobs, ለሀገር ልጅ በሀገር ልጅ!


#HaHuJobs #HaHuMuya #summerclass #summercourse #skillup #trainings #skills #careergoals
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ያስተማራቸውን ተማሪዎች አስመርቋል።

ከ60 ዓመታት በላይ ዕድሜ በትምህርት ተቋምነት ያስቆጠረው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፤ በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ያሰለጠናቸውን ስድስት ምሁራን ሰሞኑን አስመርቋል። ከስድስቱ ተመራቂዎች አንድ ሴት ይገኙበታል።

በመስከረም 2014 ዓ.ም በአዲስ መልክ የተደራጀው ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፤ የመጀመሪያዎቹን የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የትምህርት ተመራቂዎች ዘንድሮ ማስመረቁም ተገልጿል።

@tikvahuniversity
የወሎ ዩኒቨርሲቲ የዋንጫ ተሸላሚዎች 👏

በ2017 ዓ.ም ከወሎ ዩኒቨርሲቲ የሰርጅካል ነርሲንግ ትምህርት ክፍል ተመራቂው ተማሪ ፋንታሁን ስመኘው ከአጠቃላይ ተመራቂዎች አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.959 በማምጣት የሜዳሊያ እና የዋንጫ ተሸላሚ ሆኗል።

የፐብሊክ ሄልዝ ትምህርት ክፍል ተመራቂዋ ተማሪ ያብስራ አማረ ከሴት ተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት (CGPA) 3.955 በማምጣት የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።

ወሎ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ከ1 ሺህ በላይ ተማሪዎች ማስመረቁ ይታወቃል።

@tikvahuniversity
Tikvah-University
Photo
በአዲስ አበባ ከተማ በ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች ውጤት ዛሬ መለቀቁ ይታወቃል።

ውጤት ኦንላይን ለመመልከት 👇
https://aa.ministry.et/#/resu

@tikvahuniversity
የፊታችን እሑድ ሰኔ 22/2017 ዓ.ም ጠዋት 02:00 በፒያሣ ካምፓስ የጋዜጠኝነት ስልጠና ተማሪዎች የመመረቂያ ፕሮጀክታቸውን የሚያቀርቡ ሲሆን፤ ጋዜጠኛ ዳዊት አለሙ እና ጋዜጠኛ ውቢት ያረጋል በመርሐግብሩ ላይ በመገኝት የጋዜጠኝነት ሕይወታቸውን እና ልምዳቸውን የሚያካፍሉ ይሆናል።

በመርሐግብሩ ላይ በመገኘት የተመራቂ ተማሪዎቻችንን የመመረቂያ ሥራዎች እንዲከታተሉ እንዲሁም ለጋዜጠኛ ዳዊት አለሙ እና ጋዜጠኛ ውቢት ያረጋል መጠየቅ የሚፈልጉትን በማንሳት በልምድ ልውውጡ ላይ እንዲካፈሉ ጋብዘንዎታል።

መግቢያ: በነፃ

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

የበለጠ ይጠብቁ ...
💥 ሴጅ ማሰልጠኛ ኢንስቲትዩት 💥

Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
በ15 ዩኒቨርሲቲዎች 109 መምህራን የውል ግዴታቸውን ሳይወጡ በመልቀቃቸው ከ40 ሚልዮን ብር በላይ ሀብት ባክኗል፡፡ - የፌዴራል ዋና ኦዲተ

የፌዴራል ዋና ኦዲተር የፌዴራል መስሪያ ቤቶች የ2016 በጀት ዓመት የኦዲት ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት እንደተገለፀው፤ ዩኒቨርሲቲዎች ለስልጠና የላኳቸውን ባለሙያዎች በውልና ግዴታ መሰረተ ተመልሰው አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አንፃር ከፍተኛ ክፍተት አለባቸው ተብሏል።

በዚህም በ15 ዩኒቨርሲቲዎች 109 መምህራን የውል ግዴታቸውን ሳይወጡ ዩኒቨርሲቲውን በመልቀቃቸው ከ40 ሚልየዮን ብር በላይ ሀብት ዋና ኦዲተር መሠረት ዳምጤ ተናግረዋል።

አርባ ምንጭ፣ መቐለ፣ አክሱም፣ ጂንካ እና ጅማ ዩኒቨርሲቲዎች ከፍተኛውን ድርሻ የያዙ ሲሆን፤ ተቋማቱ መምህራን በውል ግዴታ መሰረት አገልግሎት እንዲሰጡ ማድረግ ወይም ሀብቱን ተመላሽ ማድረግ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በሌላ በኩል ዋቸሞ፣ ባህርዳር፣ ሐረማያ እና ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲዎች ውዝፍ ተሰብሳቢ ሂሳብ የተገኘባቸው ሲሆን፤ ማስተካከያ እንዲያደርጉ ዋና ኦዲተሯ አሳስበዋል። #ኢፕድ

@tikvahuniversity
የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለቋሚ የሥራ ቅጥር መደቦች የቀን ሠራተኞችን በመቅጠር ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ክፍያ ፈፅመዋል ተባለ፡፡

የፌዴራል ዋና አዲተር የመንግሥት ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት የበጀት ኦዲት አፈጻጸም ሪፖርት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት እንደጠቀሰው፤ 12 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ሳይፈቀድላቸው ለቋሚ የሥራ መደቦች ላይ የቀን ሠራተኞችን ቀጥረው ተገኝተዋል ብሏል፡፡

ተቋማቱ በጠቅላላው 61,882,081 ብር ለቀን ሠራተኞች ክፍያ እንደፈጸሙ የገለጸው የፌዴራል ዋና አዲተር፤ ጅማ ዩኒቨርሲቲ 25,310,211 ብር፣ አምቦ ዩኒቨርሲቲ 10,938,834 ብር፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ 7,888,374 ብር፣ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ 5,170,600 ብር እና ዲላ ዩኒቨርሲቲ 4,414,974 ብር በመክፈል ዋነኞቹ እንደሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሰዋል፡፡ #ሪፖርተር

@tikvahuniversity
ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እና ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን ተማሪዎች ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ያስመርቃሉ።

በዕለቱ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ 17ኛ ባች፥ ቀብሪደሀር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ 5ኛ ባች ሰልጣኝ ተማሪዎቻቸውን ያስመርቃሉ።

@tikvahuniversity
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተፈታኞች ውጤትን ይፋ አድርጓል።

በአስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዳችሁ ተፈታኞች ውጤታችሁን ከታች ያለውን ሊንክ በመጫንና የመለያ ቁጥራችሁን በማስገባት መመልከት ትችላላችሁ።

ውጤት ለማየት 👇
https://www.geight.diresrms.org/View_Result/get_result

@tikvahuniversity
የሁለት ወር የክረምት ስልጠና!
(25% ቅናሽ ሊጠናቀቅ 2 ቀናት ብቻ ቀሩ)

የቴክኒካል ሥራዎች (Technical Skills) ስልጠና በፒያሣ እና በመገናኛ ካምፓስ ምዝገባ ላይ ነን።

ስልጠናዎቹ፦
👉 Building Electrical Installation, CCTV Camera Installation and Security Solutions
👉 Computer Maintenance, Networking, Office Machine Maintenance and Home Appliance
👉 Mobile Maintenance 
👉 Industrial Machine Installation and Maintenance

ስልጠናው ሰኔ 30/2017 ዓ.ም ይጀመራል።

☎️   0906777799 / 0906777755
አድራሻ
ቁ.1: ፒያሣ ቸርችል ጎዳና ኤልያና ሆቴል 2ኛ ፎቅ
ቁ.2: መገናኛ ታሜጋስ ህንፃ 2ኛ ፎቅ

Instagram: https://www.instagram.com/sage_training_institute/
Telegram: https://www.tg-me.com/sagetraininginstitute
TikTok: https://www.tiktok.com/@sage_training_institute
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/sage-training-institute
በሀረሪ ክልል በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዝግጅት ተደርጓል፡፡ - የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ

ባለፈው ዓመት እንደ ሀገር ከአዲስ አበባ ቀጥሎ በሀረሪ ክልል የተሻለ ውጤት ተመዝግቦ እንደነበር - የሀረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ አስታውሰዋል፡፡

ዘንድሮ ከአምናው የተሻለ ውጤት በክልሉ ለማስመዝገብ ዝግጅት መደረጉን የገለፁት ኃላፊው፤ ተማሪዎቹን ለማብቃት ከፍተኛ ባለሙያዎችን በመመደብ የማጠናከሪያ ትምህርትና የስነ-ልቦና ዝግጅት ሥራ ሲሰራ መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

በአጠቃላይ 2292 ተማሪዎች በክልሉ የ12ኛ ክፍል ፈተና የሚወስዱ ሲሆን፤ 1931 ተማሪዎች በኦንላይን እና ቀሪዎቹ 361 በወረቀት በስድስት የመፈተኛ ጣቢያዎች እንደሚፈተኑ ተገልጿል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
በአፋር ክልል 4893 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ - የአፋር ክልል ትምህርት ቢሮ

በክልሉ በ2017 ዓ.ም ለ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከሚቀመጡ ተማሪዎች መካከል፥ 4099 ተማሪዎች በወረቀት እና 794 ተማሪዎች ደግሞ በኦንላይን ፈተናቸውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ሁመድ አብደላ ተናግረዋል፡፡

በአጠቃላይ ከ44 ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በሠመራ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን ፈተና እንደሚወስዱ ኃላፊው ገልፀዋል፡፡

የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ለስነ-ልቦና የሚያዘጋጁ ተከታታይ ሞዴል ፈተናዎች በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱን አስታውሰዋል፡፡

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
በማዕከላዊ ኢትዮዽያ ክልል ከ35 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ይወስዳሉ፡፡ - የክልሉ ትምህርት ቢሮ

ከቀናት በኋላ መሠጠት የሚጀምረውን ፈተና በክልሉ በተሳካ ሁኔታ ለማከናወን በቂ ዝግጅት መደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፍቃዱ ተናግረዋል።

በክልሉ 35246 ተማሪዎች ሀገር አቀፍ ፈተናውን የሚወስዱ ሲሆን፤ 28035 ተማሪዎች በወረቀት እና 7211 ተማሪዎች በበየነ መረብ ፈተናውን እንደሚወስዱ ኃላፊው ገልፀዋል።

የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይሰጣል።

@tikvahuniversity
🌐 ቅመም ማይፋይ በአዲስ ዋጋ መጥቷል 🙌

💨⚡️ እስከ 7 ሰዓት የሚቆይ የባትሪ አቅም ያለውና አዳዲስ የቴክኖሎጂ ትሩፋቶችን ይዞ በአንዴ እስከ 8 ሰው የሚያስጠቅመውን ልዩ ቅመም MIFIን ገዝተን ፈጣን 4G ኢንተርኔት እንጠቀም!

🍰30 ቀን ከሚቆይ ነጻ 30ጊባ ዳታ ጉርሻ ጋር 😊

ከሳፋሪኮም ጋር አንድ ወደፊት⚡️

#SafaricomEthiopia
#MizanTepiUniversity

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራም በአራት መስኮች ትምህርት መስጠት ሊጀምር ነው፡፡

ዩኒቨርሲቲው የባለሙያ ክፍተት በሚታይባቸው አራት የህክምና መስኮች በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ ትምህርት ለመስጠት ዝግጅት መጀመሩን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ዋቆ ገዳ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በሚገኝበት አካባቢ በሚነገሩ ሦስት ቋንቋዎች ማለትም በቤንች ኖን፣ በሸኪኖኖ እና በሸኮ ኢድ ቋንቋዎች የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች እያስተማረ እንደሚገኝ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ በአሁኑ ወቅት በ54 የቅድመ-ምረቃ እና በ42 የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመማር ማስተማር ሥራውን እያከናወነ ይገኛል፡፡ #SRTA

@tikvahuniversity
#AAU

አንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 75ኛ የተማሪዎች ምርቃት ስነ-ስርዓት እና የተቋሙን የአልማዝ ኢዮቤልዩ በዓል የፊታችን ቅዳሜ ሰኔ 21/2017 ዓ.ም ያከብራል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያስተማሯቸውን 75ኛ ባች ተማሪዎች ያስመርቃል።

ዩኒቨርሲቲው ባለፉት 75 ዓመታት በትምህርት ልህቀት፣ በአመራር ልማት እንዲሁም በሀገር ግንባታ ያደረገው ዘላቂ እና ዘርፈ ብዙ አበርክቶ ይዘከራል ተብሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ከ75 ዓመታት በፊት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በመባል ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ፤ የፈጠራ፣ ምርምር እና የዕውቀት መፍለቂያ በመሆን በርካታ መሪዎች፣ ባለሙያዎች እና ምሁራንን አፍርቷል፡፡

@tikvahuniversity
2025/06/27 01:13:02
Back to Top
HTML Embed Code: