ታላቁ ጦርነት
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።
53፥4 *እርሱ ንግግሩ የሚወረድ ወሕይ እንጅ ሌላ አይደለም*፡፡ إِنْ هُوَ إِلَّا وَحْيٌ يُوحَىٰ
አምላካችን አሏህ ነቢያችንን"ﷺ" ነቢይ አድርጎ ልኳል፥ ነቢያችን"ﷺ" የሩቅ ነገርን ሁሉ ከልብ ወለድ አይናገሩም። ስለ ሩቅ ነገር የሚናገሩት ንግግር የሚወርድ ወሕይ እንጂ ሌላ አይደለም፦
53፥3 *ከልብ ወለድም አይናገርም*፡፡ وَمَا يَنطِقُ عَنِ الْهَوَىٰ

በግሪክ ኮይኔ "አፓካሊፕስ" ἀποκάλυψις ማለት "የተደበቀን ነገር መግለጥ" ማለት ሲሆን አምላካችን አሏህ ለነቢያችንን"ﷺ" ካወረደው ጉዳይ አንዱ “አል-ገይቡል ሙሥተቅበል” ٱلْغَيْب ٱلْمُسْتَقْبَل ነው፥ ከነገሩን አል-ገይቡል ሙሥተቅበል መካከል ስለ መጨረሻው ቀን ምልክቶች ነው። ከንዑሳን የመጨረሻ ቀን ምልክቶች አንዱ "አል-መልሐመቱል ኩብራ" ነው፥ "አል-መልሐመቱል ኩብራ" الْمَلْحَمَة الكُبْرَى ማለት "ታላቁ ጦርነት" ወይም "አርማጌዶን" ማለት ነው። ሰዓቲቱ ሲቃረብ ዒልም በዓሊም ሞት ምክንያት ይወሰዳል፥ በጃሂል ጀህል ይስፋፋል። ብዙ አል-ሀርጅ ይሆናል፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 41, ሐዲስ 8
ዐብደሏህ ኢብኑ ዐምሪው ኢብኑል ዓሲ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በእርግጥ አሏህ ከሰዎች ዒልምን አይነጥቅም ግን ዓሊም ሳይኖር ሰዎች ጁሃልን እስኪጠይቁ እና ጁሃልም ያለ ዒልም እስኪስቱና እስኪያያሳስቱ ድረስ ዑለማእን በመውሰድ ዒልምን ቢነጥቅ እንጂ"*። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَمْرِو بْنِ الْعَاصِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " إِنَّ اللَّهَ لاَ يَقْبِضُ الْعِلْمَ انْتِزَاعًا يَنْتَزِعُهُ مِنَ النَّاسِ وَلَكِنْ يَقْبِضُ الْعِلْمَ بِقَبْضِ الْعُلَمَاءِ حَتَّى إِذَا لَمْ يَتْرُكْ عَالِمًا اتَّخَذَ النَّاسُ رُءُوسًا جُهَّالاً فَسُئِلُوا فَأَفْتَوْا بِغَيْرِ عِلْمٍ فَضَلُّوا وَأَضَلُّوا "
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 92, ሐዲስ 14
አቢ ሙሣ እንደተረከው፦ "ነቢዩም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሰዓቲቱ ሲቃረብ ጀህል ይስፋፋል፥ ዒልም ይወሰዳል። ብዙ አል-ሀርጅ ይሆናል፥ አል-ሀርጅ ማለት / #ግ/#ድ/#ያ ነው"*። عَنْ أَبِي مُوسَى قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم " إِنَّ بَيْنَ يَدَىِ السَّاعَةِ لأَيَّامًا يَنْزِلُ فِيهَا الْجَهْلُ، وَيُرْفَعُ فِيهَا الْعِلْمُ، وَيَكْثُرُ فِيهَا الْهَرْجُ، وَالْهَرْجُ الْقَتْلُ ".
"ዒልም" عِلْم ማለት "ዕውቀት" ማለት ሲሆን "ዓሊም" عَالِم ማለት ደግሞ "ዐዋቂ" ማለት ነው፥ የዐሊም ብዙ ቁጥር "ዑለማእ" عُلَمَاء ወይም "ዓሊሙን" عَالِمُون ነው። "ጀህል" جَهْل ማለት "መሃይምነት" ማለት ሲሆን "ጃሂል" جَاهِل ማለት ደግሞ "መሃይም" ማለት ነው፥ የጃሂል ብዙ ቁጥር "ጁሃል" جُهَّال ወይም "ጃሂሉን" جَاهِلُون ነው። ዛሬ በዓለም ዓቀፍ ደረጃ መጠነ ሰፊ የዑለማዎች ሞት የምናየው ይህንን ትንቢት አመላካች ይሆን? መሃይማኖች ሲስቱ እና ሲያስቱ የእርስ በእርስ እልቂት ይመጣል፥ "አል-ሀርጅ" الْهَرْج ማለት "የእርስ በእርስ እልቂት ወይም መገዳደል" ማለት ነው። ከዚያ ዓለም ዐቀፍ ይዘት ያለው ታላቁ ጦርነት ይመጣል፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 4
ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በይቱል መቅዲሥ ሲለመልም የስሪብ ፍርስራሽ ትሆናለች፣ የስሪብ ፍርስራሽ በሆነች ጊዜ ታላቁ ጦርነት ይመጣል፣ ታላቁ ጦርነት ሲመጣ ቁሥጦንጢኒያህ ድል ታረጋለች፣ ቁሥጦንጢኒያህ ድል ባደረገች ጊዜ አል-ደጃል ይመጣል"*። عَنْ مُعَاذِ بْنِ جَبَلٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم " عُمْرَانُ بَيْتِ الْمَقْدِسِ خَرَابُ يَثْرِبَ وَخَرَابُ يَثْرِبَ خُرُوجُ الْمَلْحَمَةِ وَخُرُوجُ الْمَلْحَمَةِ فَتْحُ قُسْطَنْطِينِيَّةَ وَفَتْحُ الْقُسْطَنْطِينِيَّةِ خُرُوجُ الدَّجَّالِ "
"የስሪብ" يَثْرِب የመዲና ጥንታዊ ስም ነው፥ የስሪብ ፍርስራሽ በሆነች ጊዜ ታላቁ ጦርነት ይመጣል። "ቁሥጦንጢኒያህ" قُسْطَنْطِينِيَّة ማለት "ቆስጠንጢኒያ"Constantinople" ማለት ነው፥ ቆስጠንጢኒያ ከ 306 – 337 ድኅረ-ልደት ሲገዛ በነበረው በሮሙ ቄሳር በቆስጠንጢኖስ ስም የተሰየመችው የአሁኗ ቱርክ ናት። በታላቁ ጦርነት የሙሥሊሙ መሰብሰቢያ ቦታ ከሻም ከተሞች አንዷ በሆነችው ዲመሽቅ ተብላ በምትጠራ ከተማ አቅራቢያ በጉጧህ ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 39, ሐዲስ 4298
አቢ አድ-ደርዳእ እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በታላቁ ጦርነት የሙሥሊሙ መሰብሰቢያ ቦታ ከሻም ከተሞች አንዷ በሆነችው ዲመሽቅ ተብላ በምትጠራ ከተማ አቅራቢያ በጉጧህ ነው"*። عَنْ أَبِي الدَّرْدَاءِ، أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ " إِنَّ فُسْطَاطَ الْمُسْلِمِينَ يَوْمَ الْمَلْحَمَةِ بِالْغُوطَةِ إِلَى جَانِبِ مَدِينَةٍ يُقَالُ لَهَا دِمَشْقُ مِنْ خَيْرِ مَدَائِنِ الشَّامِ "
"ዲመሽቅ" دِمَشْق ማለት "ደማስቆ" ማለት ነው፥ "ጉጧህ" غُوطَة የሻም ደቡብ ምዕራብ ክፍል ነው። አሏህ ነቢያችን"ﷺ" የተናገሩትን የሩቅ ነገር የምናስተውል እና የምናስተነትን ያድርገን! አሚን።
✍️ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen
ወሠላሙ ዐለይኩም

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.