Telegram Web Link
መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ!!

በአቡ ሀይደር
በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩህሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ የተገባ ይሁን (አል-ፋቲሓ 2)፡፡ የአላህ ሰላምና ውዳሴ የሰው ዘር ታላቅ መሪ ለሆኑት ለነቢዩ ሙሐመድ (አል-አሕዛብ 56) ለመላው የአላህ መልክተኞች (አል-ሷፍፋት 181) የሐቅንም መንገድ በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን (ጣሀ 47)፡፡
" فَإِنْ كُنْتَ فِي شَكٍّ مِمَّا أَنْزَلْنَا إِلَيْكَ فَاسْأَلِ الَّذِينَ يَقْرَءُونَ الْكِتَابَ مِنْ قَبْلِكَ لَقَدْ جَاءَكَ الْحَقُّ مِنْ رَبِّكَ فَلَا تَكُونَنَّ مِنَ الْمُمْتَرِينَ " سورة يونس 94
"ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ፡፡ እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል፡፡ ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን፡፡" (ሱረቱ ዩኑስ 10፡94)፡፡
የዚህን አንቀጽ መልእክት በአግባቡ ለመረዳት ወገኖቻችን አልታደሉም፡፡ በተሳሳተ መንገድ ተረድተው መልክቱን ለነሱ ሊያደርጓትም ቋመጡ፡፡ በድፍረትም እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፡- በዚህ አንቀጽ መሠረት ቅዱስ ቁርኣን ለሙስሊሞች፡ በእምነታቸው ጥርጥር ከገባባቸው መጽሐፍ ቅዱስ አንባቢዎች ዘንድ ሄደው በመጠየቅ እውነቱን መረዳት እንደሚችሉ መጠቆሙን እንረዳለን!!፡፡
ውይ ስታሳዝኑ…. እኔ የምለው፡- እንደው ትክክለኛ ትርጉሙንና መልእክቱን ከማየታችን በፊት፡ እናንተ እንዳላችሁት የ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ›› አንባቢዎችን እንድንጠይቅ ከሆነ ቁርኣኑ የሚገፋፋን፡ ለምን ከናንተ በፊት የነበሩትን አይሁዶቹን አንጠይቅም? ለምን ወደናንተ መምጣት አስፈለገ? ወይስ ቅድሚያ ወደናንተ እንድንመጣ ፈልጋችሁ ነውን?
  ደግሞስ እናንተን ነው ቢባል እንኳ ማንን ነው የምንጠይቀው? ካቶሊክን?፣ ኦርቶዶክስን?፣ ፕሮቴስታንትን?፣ ኢየሱስ ብቻ (only jesus) የሚሉትን?፣ የይሆዋ ምስክሮችን (Jihovah witness)?.....? እኮ ማንን? እንጠይቃችሁ ዘንድ ንገሩና! በስም ከፋፍለን የጠራናችሁ፡ በመሐከላችሁ የእምነት ልዩነት መኖሩ የታወቀ ስለሆነ ነው፡፡ ደግሞስ በየትኛው ‹‹መጽሐፍ ቅዱስ›› መሰረት ላይ ሆናችሁ ነው የምትጠየቁት? 66ቱቨ ወይስ 73ቱ? ወይንስ 81ዱ? ደግሞስ የየትኛው ዓመት እትም? ምረጡልና!!
ወደ ሐቁ ስንመጣ ግን የቅዱስ ቁርኣኑ መልእክት በፍጹም ይህን አያረጋግጥም፡፡ እነሱ የተረዱትን ሀሳብ የሚገልጽ ነገር በቅርቡም ሆነ በሩቁ በቃሉ ውስጥ አይገኝም፡፡ እንዴት? የሚሉ ከሆነና፡ ቀጥተኛ ትርጉሙን መረዳት የሚሹ ከሆነ ማብራሪያውን ከልብ ይከታተሉ፡፡ እውነቱንም ለመረዳት አላህ ያግዘን፡፡ ልባችንንም ያስፋልን፡፡
1ኛ. ጥቅላዊ ማብራሪያ፡-
የአንቀጹ መልእክት፡- የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ነቢይነትና ወደሳቸው የሚወርድላቸው መለኮታዊ ራእይ (ቅዱስ ቁርኣን) ከአላህ ዘንድ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የሌለበት መሆኑን እና፡ በዚህ ጉዳይም ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንደማይጠራጠሩና፡ ‹‹ቢጠራጠሩ እንኳ›› ከሳቸው በፊት የነበሩትን የቀደምት መለኮታዊ መጽሐፍት ሊቃውንቶችን በመጠየቅ እውነተኝነታቸውን ማረጋገጥ እንደሚችሉ ነው፡፡ ምክንያቱም፡- የሳቸው ነቢይነትም ሆነ፡ የቅዱስ ቁርኣን አምላካዊ ቃልነት በመጽሐፎቹ ኦርጂናል ቅጂ ላይ እንደተጠቀሰ ሊቃውንቶቹ ያውቃሉና!!፡፡ ስለዚህም ‹‹እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በርግጥ መጥቶልሀል፡፡ በመሆኑም ከተጠራጣሪዎች አትሁን!›› በማለት፡ እቅጩን በመንገር ጉዳዩን ይደመድመዋል፡፡ አለቀ ደቀቀ፡፡ እውነቱ ያለው እዚሁ ነው፡፡ እዛ እውነት አለና ሂደህ ጠይቅ! የሚል ቃልም ሆነ ፊደል ማግኘት አይቻልም፡፡ ሊቃውንቶቹን ጠይቅ! የተባለው፡ እነሱን እንኳ ብትጠይቃቸው አንተን በሚገባ ያውቁሀል፡፡ ነቢይነትህንም ሆነ የሚወርድልህ ራእይ ከአላህ ዘንድ መሆኑን ይመሰክራሉ ነው፡፡ ይኸው የጌታ አላህ ምስክርነት፡-
"እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ወንዶች ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል፡፡ ከነሱም የተለዩ ክፍሎች እነርሱ የሚያወቁ ሲኾኑ እውነቱን በእርግጥ ይደብቃሉ፡፡" (ሱረቱል በቀራህ 2፡146)፡፡
"እነዚያ መጽሐፍን የሰጠናቸው ልጆቻቸውን እንደሚያውቁ (ሙሐመድን) ያውቁታል፡፡ እነዚያ ከእነርሱ ውስጥ ነፍሶቻቸውን ያከሰሩት እነርሱ አያምኑም፡፡" (ሱረቱል አንዓም 6፡20)፡፡
ይህ ነው እውነታው! ከዛ ውጪማ እውነቱን ለማወቅ ከፈለግህ፡ እነሱን ሄደህ ጠይቅ ለማለት ከሆነ፡ በዚያው አንቀጽ ውስጥ ‹‹እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል›› በማለት አስረግጦ መናገር ለምን አስፈለገው? የቃሉ መልእክት ግን፡- እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ብትጠይቃቸው የአንተን ነቢይነትም ሆነ የሚወርድልህን ራእይ (ቅዱስ ቁርኣን) ከአላህ ዘንድ የመጣ መሆኑን ይናገራሉ ነው፡፡ ደግሞም ሊቃውንቶቹ ለሐቅ ያደሩ፡ እውነቱ ሲነገራቸው አምነው የተቀበሉ፡ እንደ ዐብዱላህ ኢብኑ ሰላም (ረዲየላሁ ዐንሁ)፣ እንደ ዐብዱላህ ኢብኑ-ዐምር ኢብኑል-ዓስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) አይነቶቹን እንጂ፡ ለምድራዊ ጥቅማቸው ሲሉ እውነቱን በሀሰት የለወጡ፡ የመጽሐፉን ትክክለኛ መልእክት የደበቁና፡ በመጽሐፉ ላይ እጃቸውን ያስገቡትን አይደለም፡፡ እነዚህን ክፍሎችማ ሄዶ መጠየቅ ለጥመት እንጂ ለምሪት እንደማይጠቅም በሌላ አንቀጽ እንዲህ ይገልጸዋል፡-
"ከመጽሐፉ ባለቤቶች የሆኑ ጭፍሮች ነፍሶቻቸዉን እንጂ የማያሳስቱ ሲሆኑ ሊያሳስቱዋችሁ ተመኙ ግን አያውቁም" (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3፡69)፡፡
2ኛ. ዝርዝር ማብራሪያ፡-
መልእክቱ ይበልጥ ግልጽ እንዲሆንና፡ በአንቀጹ ላይም ሊተላለፍ የተፈለገው መልእክት፡ ወገኖቻችን ካሰቡትና ከቋመጡለት ነገር ጋር ምንም ግኑኝነት እንደሌለው ለማወቅ ይረዳ ዘንድ፡ በኃይለ ቃል እየከፈልን እንመልከተው፡፡
1ኛ. ‹‹ወደ አንተም ካወረድነው›› በሚለው ኃይለ ቃል ውስጥ፡ ከጌታ አላህ ዘንድ ወደ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) የወረደ መለኮታዊ ራእይ መኖሩን በቀላሉ እንረዳለን፡፡ ይህም ራእይ ‹‹ቅዱስ ቁርኣን›› ነው፡፡
"እኛ ቁርአንን ባንተ ላይ ማውረድን እኛው አወረድነው።" (ሱረቱ-ደህር (ኢንሳን) 76፡23)፡፡ ከዛም ይቀጥልና፡-
2ኛ. ‹‹በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን›› በማለት ደግሞ አንድን ነገር እንዲያደርጉ ማረጋገጫ ይሰጣል፡፡ ማረጋገጫው ምንድነው? የሚለውን ኋላ ላይ እንመለስበታለን፡፡ ‹‹በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን›› ማለት ግን፡ ነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) መጠራጠራቸውን የሚያመላክት አይደለም፡፡ ምክንያቱም ቃሉ የሚናገረው ‹‹በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን›› እያለ እንጂ፡ ‹‹በመጠራጠር ውስጥ ነህና›› እያለ አይደለም፡፡
‹ብትሆን› (if) የሚለው ቃል Conditional sentence ነው፡፡ ሊከሰትም ላይከሰትም የሚችል፡ በሁኔታዎች የሚወሰን አያያዥ (conjunction) የሆነ ቃል ነው፡፡

አጠቃላይ ሀሳቡ፡- ወደ ‹‹አንተ ካወረድነው መጽሐፍ (መለኮታዊ ራእይ) ብትጠራጠር እንኳ›› ለማለት ነው፡፡ ታዲያ ምን ይሁን? ከተባለም፡-
3ኛ. ‹‹እነዚያን ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ›› በማለት ማረጋገጫ ይሰጠናል፡፡ የመጽሐፉን አንባቢዎች ጠይቅ የሚለው ሀሳብ የሚያያዘው፡ ወደ አንተም ካወረድነው በመጠራጠር ውስጥ ብትሆን ከሚለው የቁርኣኑ ቃል ጋር እንጂ፡ እውነትን ከፈለግህ ከሚል የፈጠራ ወሬ ጋር አይደለም፡፡ ታዲያ ከየት አምጥታችሁ ነው፡ እውነቱን ከፈለጋችሁ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነቡትን ጠይቁ! ይላል ቁርኣናችሁ የምትሉን?
ከላይ በጥቅላዊ ማብራሪያው ላይ ለመግለጽ እንደሞከርኩት፡ የመጽሐፍቱን ሊቃውንቶች ብትጠይቃቸው እንኳ፡ በመጽሐፉ ውስጥ በኦርጂናል ይዘቱ የአንተ ነቢይነት እንደተነገረ ያውቃሉ፡ እነሱም ይመሰክራሉ እያለ ነው፡፡
ወገኖቻችን! ‹‹ከአንተ በፊት›› የሚለው ኃይለ ቃል የናንተን ምኞት ከንቱ አያስቀረውምን? ቅዱስ ቁርኣን እየተናገረ ያለው፡- ‹‹ከአንተ በፊት መጽሐፉን የሚያነቡትን ጠይቅ›› በማለት እንጂ፡ ከአንተ በኋላ የሚመጡትን ጠይቅ አላለም፡፡ አሁንስ ገባችሁ?
4ኛ. ‹‹እውነቱ ከጌታህ ዘንድ በእርግጥ መጥቶልሃል ከተጠራጣሪዎቹም አትሁን›› በማለት አንቀጹ በሚያምር አገላለጽ ተደመደመ፡፡ አላሁ አክበር! ወደሳቸው ይወርድ የነበረው መለኮታዊ ራእይ፡- እውነቱ እኔው ራሴ ነኝ! ካለ፡ ሌላ እውነት ፍለጋ እንዴት ይኬዳል? ስለዚህ እውነቱ እዚሁ ቁርኣን ውስጥ ነው ያለው፡፡ ‹‹ብትጠራጠር እንኳ እነሱን ጠይቅ›› ማለቱ፡ እውነትን ፍለጋ ወደነሱ ሂድ! ከማለት ጋር ምንም ግኑኝነት የለውም፡፡ ግኑኝነቱ፡ እነሱም ቢሆኑ ብትጠይቃቸው የአንተን ነቢይነት በሚገባ ስለሚያውቁ ይነግሩሀል ነው፡፡
5ኛ. የአላህ ነቢይም (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ይህ አንቀጽ በወረደላቸው ግዜ፡ የመጽሐፉን ሰዎች ሄደው አልጠየቁም፡፡ ባይሆን በተቃራኒው እንዲህ ነበር ያሉት፡-
‹‹ላ አሹክኩ ወላ አስአል›› ‹አልጠራጠርም አልጠይቅምም›፡፡ (ተፍሲሩ-ጠበሪይ፡ ጃሚዑል በያን ሱረቱ ዩኑስ 94 ቁጥር 17893-17894)፡፡
እኛም የነቢዩ ሙሐመድ (ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ተከታይ የሆንን ሙስሊሞች፡ እሳቸውን በመከተል አንጠይቅምም ደግሞም አንጠራጠርምም፡፡
6ኛ. ኢማሙል ቡኻሪይ በዘገቡት ሶሒሕ ሐዲሥ ላይ ደግሞ፡ እንዲህ የሚል ግሳፄ ተቀምጧል፡-
عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ عَبَّاسٍ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُمَا، قَالَ: " يَا مَعْشَرَ المُسْلِمِينَ، كَيْفَ تَسْأَلُونَ أَهْلَ الكِتَابِ، وَكِتَابُكُمُ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَى نَبِيِّهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ أَحْدَثُ الأَخْبَارِ بِاللَّهِ، تَقْرَءُونَهُ لَمْ يُشَبْ، وَقَدْ حَدَّثَكُمُ اللَّهُ أَنَّ أَهْلَ الكِتَابِ بَدَّلُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ وَغَيَّرُوا بِأَيْدِيهِمُ الكِتَابَ، فَقَالُوا: هُوَ مِنْ عِنْدِ اللَّهِ لِيَشْتَرُوا بِهِ ثَمَنًا قَلِيلًا، أَفَلاَ يَنْهَاكُمْ مَا جَاءَكُمْ مِنَ العِلْمِ عَنْ مُسَاءَلَتِهِمْ، وَلاَ وَاللَّهِ مَا رَأَيْنَا مِنْهُمْ رَجُلًا قَطُّ يَسْأَلُكُمْ عَنِ الَّذِي أُنْزِلَ عَلَيْكُمْ " رواه البخاري 2685.7522.7523
ዐብዱላህ ኢብኑ-ዐባስ (ረዲየላሁ ዐንሁማ) እንዲህ ይላል፡- "እናንተ ሙስሊሞች ሆይ!  በነቢዩ ላይ የተወረደላችሁ መጽሐፍ (ቁርኣን) ከአላህ ዘንድ የመጣ አዲስ (ያላረጀ) ሆኖ ሳለ፡ እናንተም ያልተበረዘና የሰው እጅ ያልገባበት ሆኖ እያነበባችሁት፡ የመጽሐፉን ሰዎች (አይሁዶችና ክርስቲያኖች) እንዴት ትጠይቃላችሁ? አላህም (በቁርኣኑ) የመጽሐፉ ሰዎች መጽሐፉን በእጃቸው እንደበረዙትና እንደቀየሩት፣ ከዛም የተበረዘውን ጥቂትን ምድራዊ ዋጋ ለመሸመት፡ ይህ ከአላህ ዘንድ የመጣ ነው እንዳሉ ነግሯቹኋል፡፡ እንግዲያውስ ወደናንተ የመጣላችሁ ዕውቀት እነሱን ከመጠየቅ አይከለክላችሁምን? በአላህ ይሁንብኝ! ከነሱ ውስጥ አንድም ሰው ወደናንተ ስለወረደው ሲጠይቁአችሁ በፍጹም አላየንም (ታዲያ እናንተ እነሱን እንዴት ትጠይቃላችሁ?)" (ቡኻሪይ 2685፣ 7522፣ 7523)፡፡
አዎ! ልንጠይቃቸውም አይገባም! ትክክለኛው ሀሳብ ይህ ነው ወላሁ አዕለም፡፡
"ጌታህ በመካከላቸው በትክክል ፍርዱ ይፈርዳል፤ እርሱም አሸናፊው ዐዋቂው ነው። በአላህም ላይ ተጠጋ፤ አንተ ግልጽ በሆነው እውነት ላይ ነህና።" (ሱረቱ-ነምል 27፡79)፡፡

✍🏻በኡሥታዝ አቡ ሀይደር

የበለጠ ለማንበብ➤➤
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
👍1
ወንድ እና ሴት | ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ | ጥሪያችን

🔗 https://youtu.be/4F8XXDrzbak

👆  አዲስ ቪድዮ በዩትዩብ ቻነላችን ላይ


መልካም ቆይታ ከጥሪያችን ጋር
‐‐‐
Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen
👍2
አምላኪዎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

21፥106 *በዚህ ቁርኣን ውስጥ ለአምላኪዎች ሕዝቦች በቂነት አለ*፡፡ إِنَّ فِي هَـٰذَا لَبَلَاغًا لِّقَوْمٍ عَابِدِينَ

አምላካችን አላህ ነባቤ መለኮት ማለትም ተናጋሪ አምላክ ነው፤ ብዙ አንቀጾች ላይ “አምልኩኝ” እያለ በመጀመሪያ መደብ ይናገራል፦
29፥56 እናንተ ያመናችሁ ባሮቼ ሆይ! ምድሬ በእርግጥ ሰፊ ናት፤ ብትቸገሩ ተሰደዱ፡፡ *”እኔንም ብቻ አምልኩኝ”*፡፡ يَٰعِبَادِىَ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّ أَرْضِى وَٰسِعَةٌۭ فَإِيَّٰىَ فَٱعْبُدُونِ
21፥92 ይህች አንዲት መንገድ ስትሆን በእርግጥ ሃይማኖታችሁ ናት፤ *”እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ”*፡፡ إِنَّ هَٰذِهِۦٓ أُمَّتُكُمْ أُمَّةًۭ وَٰحِدَةًۭ وَأَنَا۠ رَبُّكُمْ فَٱعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ *”ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ”* በማለት ወደ እርሱ *”የምናወርድለት”* ቢኾን እንጅ ከመልክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِىٓ إِلَيْهِ أَنَّهُۥ لَآ إِلَٰهَ إِلَّآ أَنَا۠ فَٱعْبُدُونِ
51፥56 *ጂኒን እና ሰውንም ሊያመልኩኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም*፡፡ وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ

እስቲ ስለ ጣዖት፣ ስለ አላህ እና ስለ አምልኮ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“ጣጉት”
ከአላህ ውጪ የሚደረግ ባዕድ አምልኮ “ጣጉት” لطَّاغُوتِ ማለትም “ጣዖት” ይባላል፤ ይህም ጣዖት በሁለት ይከፈላል፦ አንዱ “አውሳን” أَوْثَٰنሲሆን “አውሳን” ማለት ከድንጋይ ተቀርፀው አምልኮ የሚቀርብላቸው ናቸው፤ ሁለተኛው ደግሞ “አስናም” أَصْنَام ነው፤ “አስናም” ማለት ከእንጨት፣ ከብር፣ ከነሐስ፣ ከወርቅ ተሰርተው አምልኮ የሚቀርብላቸው ናቸው፤ አምላካችን አላህ ለነብያችንን”ﷺ”፦ “እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸውን እንዳላመል ተከልክያለሁ፤ የዓለማትን ጌታ እንዳመልክ ታዝዣለሁ” በል ብሏቸዋል፦
23፥66 «እኔ ከጌታዬ አስረጂዎች በመጡልኝ ጊዜ *እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸውን እንዳላመል ተከልክያለሁ፡፡ የዓለማትን ጌታ እንዳመልክ ታዝዣለሁ»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّي نُهِيتُ أَنْ أَعْبُدَ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَمَّا جَاءَنِيَ الْبَيِّنَاتُ مِن رَّبِّي وَأُمِرْتُ أَنْ أُسْلِمَ لِرَبِّ الْعَالَمِينَ
10፥104 «እናንተ ሰዎች ሆይ! ከእኔ ሃይማኖት በመጠራጠር ውስጥ ብትሆኑ *እነዚያን ከአላህ ሌላ የምታመልኳቸውን አላመልክም፡፡ ግን ያንን የሚያሞታችሁን አላህን አመልካለው*፡፡ ከምእምናን እንድሆንም ታዝዣለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ يَا أَيُّهَا النَّاسُ إِن كُنتُمْ فِي شَكٍّ مِّن دِينِي فَلَا أَعْبُدُ الَّذِينَ تَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ وَلَـٰكِنْ أَعْبُدُ اللَّهَ الَّذِي يَتَوَفَّاكُمْ ۖ وَأُمِرْتُ أَنْ أَكُونَ مِنَ الْمُؤْمِنِينَ

ነጥብ ሁለት
“አላህ”
ቁረይሾች የፈጠራቸውን አላህን ትተው ወደ ፈጣሪ ያቃርቡናል የሚሏቸውን ጣዖታት ያመልካሉ፤ ያንን ከአላህ ሌላ የሚያመልኩት ነቢያችን”ﷺ” አምላኪ አይደሉም፤ ነቢያችን”ﷺ” የሚያመልኩትን አላህ እነርሱም አምላኪዎች አይደሉም፦
109፥3 *«እናንተም እኔ የማመልከውን አምላኪዎች አይደላችሁም*፡፡ وَلَا أَنتُمْ عَابِدُونَ مَا أَعْبُدُ
109፥4 *«እኔም ያንን የምታመልኩትን አምላኪ አይደለሁም*፡፡ وَلَا أَنَا عَابِدٌ مَّا عَبَدتُّمْ

እነርሱም አላህ ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጥ፣ መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ፣ ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ፣ ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ፣ ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ፣ ፀሐይንና ጨረቃንም የፈጠረ መሆኑን ይመሰክራሉ፤ ምክንያቱም አላህ ከኢብራሂም በእነርሱ ውስጥ ይመለሱ ዘንድ በአንድ አምላክ ማመንን ቀሪ ቃልን ስላደረገ ነው፦
10፥31 *«ከሰማይና ከምድር ሲሳይን የሚሰጣችሁ ማን ነው? መስሚያዎችንና ማያዎችንስ የፈጠረ ማን ነው ከሙትም ሕያውን የሚያወጣ ከሕያውም ሙትን የሚያወጣስ ማን ነው ነገሩን ሁሉ የሚያስተናብርስ ማን ነው» በላቸው፡፡ «በእርግጥም አላህ ነው» ይሉሃል*፡፡ «ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን?» በላቸው፡፡ قُلْ مَن يَرْزُقُكُم مِّنَ ٱلسَّمَآءِ وَٱلْأَرْضِ أَمَّن يَمْلِكُ ٱلسَّمْعَ وَٱلْأَبْصَٰرَ وَمَن يُخْرِجُ ٱلْحَىَّ مِنَ ٱلْمَيِّتِ وَيُخْرِجُ ٱلْمَيِّتَ مِنَ ٱلْحَىِّ وَمَن يُدَبِّرُ ٱلْأَمْرَ ۚ فَسَيَقُولُونَ ٱللَّهُ ۚ فَقُلْ أَفَلَا تَتَّقُونَ
39፥38 *ሰማያትንና ምድርን የፈጠረ ማን እንደ ኾነ ብትጠይቃቸው «አላህ ነው» ይሉሃል*፡፡ «ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸውን ጣዖታት አያችሁን? ንገሩኝ አላህ በጉዳት ቢፈልገኝ እነርሱ ጉዳቱን ገላጮች ናቸውን? ወይስ በችሮታው ቢፈቅደኝ እነርሱ ችሮታውን አጋጆች ናቸውን?» በላቸው፡፡ وَلَئِن سَأَلْتَهُم مَّنْ خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ لَيَقُولُنَّ ٱللَّهُ ۚ قُلْ أَفَرَءَيْتُم مَّا تَدْعُونَ مِن دُونِ ٱللَّهِ إِنْ أَرَادَنِىَ ٱللَّهُ بِضُرٍّ هَلْ هُنَّ كَٰشِفَٰتُ ضُرِّهِۦٓ أَوْ أَرَادَنِى بِرَحْمَةٍ هَلْ هُنَّ مُمْسِكَٰتُ رَحْمَتِهِۦ
43፥28 *በዝርዮቹም ውስጥ ይመለሱ ዘንድ በአንድ አምላክ ማመንን ቀሪ ቃል አደረጋት*፡፡ وَجَعَلَهَا كَلِمَةًۢ بَاقِيَةًۭ فِى عَقِبِهِۦ لَعَلَّهُمْ يَرْجِعُونَ

አላህም፦ “ታዲያ ለምን ታጋራላችሁ አትፈሩትምን?” በላቸው በማለት ይናገራል፤ እነዚያም ከአላህ ሌላ የሚያመልኳቸው ምንንም አይፈጥሩም፤ እነርሱም ይፈጠራሉ፤ የሚያጋሩበት ምክንያት አላህ ዘንድ መቃረቢያ አማላጆቻችን ናቸው ብለው ስላሰቡ ነው፦
16፥20 *እነዚያም ከአላህ ሌላ የምትገዟቸው ምንንም አይፈጥሩም፡፡ እነርሱም ይፈጠራሉ*፤ وَالَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ لَا يَخْلُقُونَ شَيْئًا وَهُمْ يُخْلَقُونَ
46፥28 *እነዚያም መቃረቢያ ይኾኑ ዘንድ ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው የያዙዋቸው አይረዷቸውም ኖሯልን?* በእርግጥ ከእነርሱ ራቁ፡፡ ይህም ውሸታቸውና በልማድ ይቀጥፉት የነበሩት ነው፡፡ فَلَوْلَا نَصَرَهُمُ الَّذِينَ اتَّخَذُوا مِن دُونِ اللَّهِ قُرْبَانًا آلِهَةً ۖ بَلْ ضَلُّوا عَنْهُمْ ۚ وَذَٰلِكَ إِفْكُهُمْ وَمَا كَانُوا يَفْتَرُونَ
1
10፥18 *ከአላህም ሌላ የማይጎዳቸውን የማይጠቅማቸውንም ይግገዛሉ፡፡ «እነዚህም አላህ ዘንድ አማላጆቻችን ናቸው» ይላሉ*፡፡ وَيَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ مَا لَا يَضُرُّهُمْ وَلَا يَنفَعُهُمْ وَيَقُولُونَ هَـٰؤُلَاءِ شُفَعَاؤُنَا عِندَ اللَّهِ

ነጥብ ሦስት
“ዒባዳህ”
“ዒባዳህ” عبادة የሚለው ቃል “ዐበደ عَبَدَ “አመለከ” ከሚል ግስ የተገኘ ሲሆን “አምልኮ” ማለት ነው፤ በቁርኣን “ባሪያ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዐብድ” عَبْد ሲሆን በተመሳሳይ “ዐበደ” ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ዐቢድ” عَابِد ማለትም ”አምላኪ” “ተገዢ” ማለት ነው። ቁረይሾች ጉዳት ባገኛቸው ጊዜ የሚጠሩዋቸው አማልክት ይረሱና አላህ ይጠራሉ፤ አላህ ከጉዳት ባዳቸው ጊዜ ይተዉታል፤ እነዚያን ከእርሱ ሌላ አማልክት የሚሏቸውን ከእነርሱም ላይ ጉዳትን ማስወገድን ወደ ሌላ ማዞርንም አይችሉም፦
17፥67 *በባሕሩም ውስጥ ጉዳት ባገኛችሁ ጊዜ የምትጠሩዋቸው ሁሉ ከእርሱ ከአላህ በቀር ይጠፋሉ፡፡ ወደ የብስም በማድረስ ባዳናችሁ ጊዜ ትተዋላችሁ፡፡ ሰውም በጣም ከሓዲ ነው*፡፡ وَإِذَا مَسَّكُمُ ٱلضُّرُّ فِى ٱلْبَحْرِ ضَلَّ مَن تَدْعُونَ إِلَّآ إِيَّاهُ ۖ فَلَمَّا نَجَّىٰكُمْ إِلَى ٱلْبَرِّ أَعْرَضْتُمْ ۚ وَكَانَ ٱلْإِنسَٰنُ كَفُورًا
17፥56 *«እነዚያን ከእርሱ ሌላ አማልክት የምትሏቸውን ጥሩ፡፡ ከእናንተም ላይ ጉዳትን ማስወገድን ወደ ሌላ ማዞርንም አይችሉም» በላቸው*። قُلِ ادْعُوا الَّذِينَ زَعَمْتُم مِّن دُونِهِ فَلَا يَمْلِكُونَ كَشْفَ الضُّرِّ عَنكُمْ وَلَا تَحْوِيلًا

በሙስሊሙ እና በጣዖታውያን ያለው ልዩነት ይህ ነው፤ ጣዖታውያን የሚያመልኩት ጣዖቶቻቸውን ቢሆንም የእነርሱም የእኛም ጌታ አላህ ብቻ ነው፤ ግን አምልኮ ላይ ለእነርሱ የራሳቸው ሥራዎች ያላቸው ሲሆን እኛም የራሳችን ሥራ አለን፦
2፥139 *እርሱ አላህ ጌታችን እና ጌታችሁ ሲኾን ለእኛም ሥራችን ያለን ስንኾን ለእናንተም ሥራችሁ ያላችሁ ስትኾኑ* እኛም ለእርሱ ፍጹም ታዛዦች ስንኾን በአላህ ሃይማኖት ትከራከሩናላችሁን? በላቸው፡፡ قُلْ أَتُحَاجُّونَنَا فِي اللَّهِ وَهُوَ رَبُّنَا وَرَبُّكُمْ وَلَنَا أَعْمَالُنَا وَلَكُمْ أَعْمَالُكُمْ وَنَحْنُ لَهُ مُخْلِصُونَ

“ፍጹም ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙኽሊሱን” مُخْلِصُون ሲሆን “ሙኽሊሱን” ማለት “ኢኽላስ” إخلاص ያለው ሙስሊም ማለት ነው፤ “ኢኽላስ” ማለት ደግሞ ከእዩልይና ስሙልኝ እና ከሙገሳና ወቀሳ ነጻ ሆኖ ለአላህ ውዴታ ተብሎ የሚነየት መተናነስ፣ ማጎብደድ፣ ማሸርገድ እና ማጥራት ነው፤ “አምልኮ” አላህ ዘንድ ተቀባይነት የሚያገኝባቸው ሥስት ሸርጦች ኢማን፣ ኢኽላስ እና ኢቲባዕ ናቸው፤ አንዱ መስፈርት ከጎደለ ያ አምልኮ ተቀባይነት ስለሌለው አላህን አመለከ አይባልም። ሌላ አንቀጽ ሌላ “ፍጹም ታዛዦች” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ሙስሊሙን” مُّسْلِمُون ሲሆን አንዱን አምላክ ብቻ በብቸኝነት ማምለክን ያሳያል፦
21፥108 «ያ ወደ እኔ የሚወረደው፦ *አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ነው፤ ታዲያ እናንተ ፍጹም ታዛዦች ናችሁን»* በላቸው፡፡ قُلْ إِنَّمَا يُوحَىٰ إِلَيَّ أَنَّمَا إِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ ۖ فَهَلْ أَنتُم مُّسْلِمُونَ
22፥34 *አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ*፡፡ ለአላህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

“ታዘዙ” ለሚለው ቃል የመጣው “አሥሊሙ” أَسْلِمُوا ሲሆን “ሙስሊም” ማለት አንዱን አምላክ የሚታዘዝ ታዛዥ ማለት ነው። በቁርኣን ውስጥ አላህን በብቸኝነት ለሚያመልኩ አምላኪዎች በቂነት አለ፦
21፥106 *በዚህ ቁርኣን ውስጥ ለአምላኪዎች ሕዝቦች በቂነት አለ*፡፡ إِنَّ فِي هَـٰذَا لَبَلَاغًا لِّقَوْمٍ عَابِدِينَ
2፥138 የአላህን የተፈጥሮ መንክር ያዙ፡፡ በመንከርም ከአላህ ይበልጥ ያማረ ማነው? ማንም የለም፤ *እኛም ለእርሱ ብቻ አምላኪዎች ነን* በሉ፡፡ صِبْغَةَ اللَّهِ ۖ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّهِ صِبْغَةً ۖ وَنَحْنُ لَهُ عَابِدُونَ

የአላህን የተፈጥሮ መንክር ይዞ ለእርሱ ብቻ አምላኪዎች ከሆኑት ሙስሊሙን እና ሙኽሊሱን ያድርገን አሚን።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
1
ቂሰቱል ገራኒቅ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን "በቀጠፈ" ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

ዊሊያም ሙኢር በ 1819 AD ተወልዶ በ 1905 AD ያለፈ “ሙስተሽሪቅ” مستشرق ማለትም “የመካከለኛው ምስራቅ ጥንተ-ነገር አጥኚ”Orientalist” ሲሆን እርሱ ለመጀመሪያ ጊዜ በ 1858 AD በመጽሐፉ ሽፋን ላይ “ሰይጣናዊ አንቀፅ”Satanic Verse” ብሎ ጻፈ፤ በመቀጠል የእርሱን ፈለግ የተከተለው ሳልማን ሩሽዲ 1988 AD በመጽሐፉ ሽፋን ላይ “ሰይጣናዊ አንቀፅ” ብሎ ጻፈ፤ ይህ መጽሐፍ በምዕራባዊያና በሚሽነሪዎች እገዛ በዓለማችን ላይ ትልቅ የህትመት ሽፋን ተሰቶት ተሰራጭቶ ነበር፤ ሳልማን ሩሽዲን ብዙዎች ከሊቅ እስከ ደቂቅ እጹብ ድንቅ በማለት አሞካሽተውት ነበር፤ ቂሰቱል ገራኒክ በቅጡ በማይታወቅበት በዚያ ጊዜ አለማወቅን ተገን አድርጎ የተነሣው ይህ ሰው ብዥታው አላንዳች ከልካይ እንደ ተዛማጅ በሽታ በዓለማችም ላይ ተዛምቶ ነበር፤ ከመነሻው የብዙዎችን ልብ የሳበው ይህ መጽሐፍ ከእርሱ በኋላ ለመጡት መሰል የሚሽነሪዎች ትችት ትልቅ የማደላደል ሥራ ሠርቷል። “ሰይጣናዊ አንቀፅ” ከትችት የመነጨ ሲሆን ይህ ስያሜ በኢስላም ጽሑፎች ውስጥ የለም። “ሰይጣናዊ አንቀፅ” በኢስላማዊ ጥናት ውስጥ ግን “ቂሰቱል ገራኒቅ” قصة الغرانيق ይባላል፤ “ገራኒቅ” غرانيق ማለት “የውሃ ወፍ”crane” ማለት ነው።
“ቂሰቱል ገራኒቅ” ማለት ይህ ነው፦
“ቲልከል ገራኒቁል ዑልያ፤ ወኢንነ ሸፋዐተሁንነ ለቱርጃ” تِلْكَ الْغَرَانِيقُ الْعُلْيَ وَ إِنَّ شَفاَعَتَهُنَّ لَتُرْجَى.
‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው›These are the high-flying ones, verily their intercession is to be hoped for!

ይህንን ከማየታችን በፊት ሙሉ ታሪካዊ ዳራውን እንመልከት፤ የረመዷን ወር ነብያችን”ﷺ” ወደ ተከበረው የሐረም መስጊድ ሄዱ፤ ቁረይሾች ተሰባስበው ባሉበት በድንገት ከመካከላቸው ቆሙና ሱረቱል ነጅም የተሰኘውን የቁርዓን ክፍል አነበቡ፤ ይህንን ሱራ አንብበው ሲጨርሱ "ለአላህም ስገዱ አምልኩትም" አንቀፅ ስለነበር ሁሉም ሙስሊሞች ሰገዱ፤ ከኃላ ሲሰሙ የነበሩት ቁረይሾች አብረው ሰገዱ፦
53፥62 ለአላህም ስገዱ አምልኩትም فَٱسْجُدُوا۟ لِلَّهِ وَٱعْبُدُوا۟ ۩ ፡፡
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 17 , ሐዲስ 5:
ኢብኑ ዐባስ"ረ.ዓ." እንደተረከው፦ ነቢዩ”ﷺ” ሱረቱል ነጅምን በቀሩ ጊዜ ሰገድኩ፣ ከእርሳቸው ጋር ሙስሊሞች፣ ሙሽሪኮች፣ ጂኒዎችና ሰዎችም ሰገዱ عَنِ ابْنِ عَبَّاسٍ ـ رضى الله عنهما أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم سَجَدَ بِالنَّجْمِ وَسَجَدَ مَعَهُ الْمُسْلِمُونَ وَالْمُشْرِكُونَ وَالْجِنُّ وَالإِنْسُ‏.‏ ።

አረብ ሙሽሪኮች የሰገዱበት ምክንያት ""አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?"" የሚለውን አንቀጽ ነብያችን”ﷺ” ስላነበቡ እንደሆነ ሰሒህ የሆነው ሐዲስ ላይ ከላይ ተቀምጧል።
ይህ የመጀመሪያው እይታ ሲሆን ነገር ግን ሁለተኛው እይታ ከዚህ በኃላ ያለው ታሪክ ኢብኑ ሃጅር አል አስቃላኒ እና ሼኽ አልባኒ ደኢፍ ነው ብለው አስቀምጠውታል፤ ራዚም፦ "በሙናፊቃን የተቀጠፈ መውዱዕ ነው" ብሏል(ተፍሲሩል ራዚ 11/134)። በተጨማሪም ኢብኑ ከሲር ሲናገር ይህ ታሪክ ደኢፍ ነው ብሎ ከደኢፍ ሁለተኛውን ክፍል ሙርሰል እንደሆነና በእርሱ አስተሳሰብ ሳሒህ እንዳልሆነ ተናግሯል። ይህንን ደኢፍ ታሪክ ኢብኑ ሂሻም፣ አል-ፈይሩዝ አባዲ፣ ተፍሲሩል ጀላለይን እና ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ ዘግበውታል፤ እንደውም ኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ መግቢያው ላይ እንዲህ ይላል፦
"በዚህ መጽሐፍ ትረካ አንባቢ ተቃራኒ ወይም ተገቢ ሆኖ በሚያገኝበት ጊዜ ይህ የእኛ ባህርይ እንዳልሆነ ማወቅ አለበት፤ ነገር ግን ካለፉት ሰዎች ወደ እኛ የተላለፈ ትረካ ነው" (ታሪኩር ረሱል ወል ሙልክ ቅፅ 1, ገፅ 3)

ስለዚህ ከዚህ በታች ያለው የኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ ትረካ ደኢፍ የሆሃንበት አጋጣሚ አለ ማለት ነው፤ አንዳንድ ሙፈሲሪን መሰረት ያደረጉበትን የኢብኑ ጀሪር አጥ-ጣባሪ ትረካ እስቲ እንየው፦
"አላህ፦ "በኮከብ እምላለሁ በገባ ጊዜ፡፡ ባልደረባችሁ አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም፡፡ ከልብ ወለድም አይናገርም፡" የሚለውን አንቀጽ አወረደ፤ በመቀጠል፦
"አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?"
ይህንን በአነበቡ ጊዜ ሸይጣን ""በንባቡ ላይ""፦
"ቲልከል ገራኒቁል ዑልያ፤ ወኢንነ ሸፋዐተሁንነ ለቱርጃ" تِلْكَ الْغَرَانِيقُ الْعُلْيَ وَ إِنَّ شَفاَعَتَهُنَّ لَتُرْجَى.
‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው› የሚለውን ቃል ጣለ።
አላህም፦ "ከመልክተኛና ከነቢይም ከአንተ በፊት አንድንም አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ የሚጥል ቢሆን እንጅ፡፡ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል" የሚለውን አንቀፅ አወረደ።
(ታሪኩር ረሱል ወል ሙልክ ቅፅ 1, ገፅ 108)

"በንባቡ ላይ" ተብሎ የተቀመጠው ቃል "ፊ ዑምኒይየቲሂ" فِي أُمْنِيَّتِهِ ሲሆን በነብያችን”ﷺ” ንባብ ማለትም "አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?" ብለው ባሉ ጊዜ ጎን ለጎን ሸይጣን፦ ‹እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው› የሚለውን ቃል ጣለ። እንግዲህ ይህ ነው "ቂሰቱል ገራኒቅ" የሚባለው፤ ሙሽሪክ ከሃድያን ይህ ሱራ ሲነበብ «ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ፡፡ ታሸንፉም ዘንድ ሲነበብ በእርሱ ውሰጥ ተንጫጩ» አሉ፦
41፥26 እነዚያም የካዱት «ይህንን ቁርኣን አታዳምጡ፡፡ ታሸንፉም ዘንድ "ሲነበብ" በእርሱ ውሰጥ ተንጫጩ» አሉ وَقَالَ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ لَا تَسْمَعُوا۟ لِهَٰذَا ٱلْقُرْءَانِ وَٱلْغَوْا۟ فِيهِ لَعَلَّكُمْ تَغْلِبُونَ ፡፡

በዚህ ሰአት ከእውነት "በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ" ሆነው "አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?" የሚለው አንቀፅ ሲነበብ በሚንጫጩት ልብ ውስጥ ፈተና ሊያደርግ ሸይጣን ልብስብስን ቃልን ጣለ፤ ሁልጊዜ በእያንዳንዱ ነብይ ዘመን ነብዩ ባነበበ ጊዜ ሰይጣን ልቦቻቸውም ደረቆች በሆኑት ውስጥ ልብስብስን ቃልን ይጥላል፤ ይህን የሚያደርገው የቀጠፈውን እንዲቀጣጥፉ ነው፦
22፥53 ሰይጣን የሚጥለውን ነገር ለእነዚያ በልቦቻቸው ውስጥ በሽታ ላለባቸው ልቦቻቸውም ደረቆች ለሆኑት ፈተና ሊያደርግ ይጥላል፡፡ በዳዮችም ከእውነት "በራቀ ጭቅጭቅ ውስጥ" ናቸው لِّيَجْعَلَ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ فِتْنَةًۭ لِّلَّذِينَ فِى قُلُوبِهِم مَّرَضٌۭ وَٱلْقَاسِيَةِ قُلُوبُهُمْ ۗ وَإِنَّ ٱلظَّٰلِمِينَ لَفِى شِقَاقٍۭ بَعِيدٍۢ ፡፡
1
6:112-113 እንደዚሁም *ለነቢያት ሁሉ ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ጠላት አደረግን*፡፡ ከፊላቸው ወደ ከፊሉ ለማታለል *ልብስብስን ቃል ይጥላሉ*፡፡ ጌታህም በሻ ኖሮ ባልሠሩት ነበር፡፡ *ከቅጥፈታቸውም ጋር ተዋቸው*፡፡ *የሚጥሉትም ሊያታልሉ* እና የእነዚያም በመጨረሻይቱ ሕይወት የማያምኑት ሰዎች ልቦች ወደእርሱ እንዲያዘነብሉ እንዲወዱትም እነርሱ *ይቀጥፉ የነበሩትንም እንዲቀጣጥፉ* ነው፡፡
22፥52 ከመልክተኛና ከነቢይም ከአንተ በፊት አንድንም አላክንም ባነበበ ጊዜ ሰይጣን በንባቡ ላይ የሚጥል ቢሆን እንጅ፡፡ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል፡፡ አላህም ዐዋቂ ጥበበኛ ነው وَمَآ أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍۢ وَلَا نَبِىٍّ إِلَّآ إِذَا تَمَنَّىٰٓ أَلْقَى ٱلشَّيْطَٰنُ فِىٓ أُمْنِيَّتِهِۦ فَيَنسَخُ ٱللَّهُ مَا يُلْقِى ٱلشَّيْطَٰنُ ثُمَّ يُحْكِمُ ٱللَّهُ ءَايَٰتِهِۦ ۗ وَٱللَّهُ عَلِيمٌ حَكِيمٌۭ ፡፡

ይህ አንቀፅ ሙጅመል ማለትም ጥቅላዊ ነው፤ ምክንያቱም *"ከአንተ በፊት"* የሚለው ገለጻ ከነብያችን በፊት በነበሩት ነብያትና መልእክተኞችም ላይም ከሰውና ከጋኔን የኾኑን ሰይጣናት ለማታለል *ልብስብስን ቃል* ይጥላሉ፤ ወዲያውም አላህ ሰይጣን የሚጥለውን ያስወግዳል፡፡ ከዚያም አላህ አንቀጾቹን ያጠነክራል፤ ሸኹል ኢስላም ኢብኑ ተምያህ ይህንን እይታ ይጋራሉ። ነገር ግን በወቅቱ ነብያችን”ﷺ” "አል-ላትንና አል-ዑዛን አያችሁን? ሦስተኛይቱንም አነስተኛዋን መናትን?" የሚለው አንቀጽ በአሉታዊ መልኩ አንብበው ሲጨርሱ በንባቡ ላይ ሸይጣን፦ "እነዚህ የተከበሩ ናቸው ምልጃቸው ተቀባይነት ያገኘው ናቸው" የሚለውን ለሙሽሪኮች ሲያነብ ሙሽሪኮች ይህን ቃል ሲሰሙ፦ "ነቢዩ”ﷺ” አማልክቶቻችንን አወድሷል" ሲሉ ዋሹ፤ የዚህ ቅጥፈት ዜና ወደ ሐበሻ ከተሰደዱ ሰሐቦች ዘንድ ከእውነታው እጅግ በተለየና በራቀ መልኩ ተሰማ፤ አላህም ነብያችንን”ﷺ” "ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፡፡ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር" በማለት ይህ ቅጥፈት ለማስዋሸት ፈተና መሆኑን እና ቢዋሹ ወዳጆች አድርገው ይይዧቸው እንደነበር ተናገረ፦
17፥73 እነሆ ከዚያም ወደ አንተ ካወረድነው ሌላን በእኛ ላይ ትዋሽ ዘንድ ሊፈትኑህ በእርግጥ ተቃረቡ፡፡ ያን ጊዜም ወዳጅ አድርገው በያዙህ ነበር وَإِن كَادُوا۟ لَيَفْتِنُونَكَ عَنِ ٱلَّذِىٓ أَوْحَيْنَآ إِلَيْكَ لِتَفْتَرِىَ عَلَيْنَا غَيْرَهُۥ ۖ وَإِذًۭا لَّٱتَّخَذُوكَ خَلِيلًۭا ፡፡

ሙሽሪኮች ጠላት መሆናቸው በራሱ ከአላህ ቃል ሌላ ቃልን እንዳልተናገሩ በቂ ማስረጃ ነው፤ ምክንያቱም ነብያችንን”ﷺ” ወዳጅ አድርገው አለመያዛቸው ነው፤ በተጨማሪም በመቀጠል ከአላህ ውጪ ከሌላ ማንነት ሆነ ምንነት ከፊል ቃልን አምጥቶ ቢቀጥፉ የልብ ስራቸውን እንደሚቆርጥ በመናገር ከሌላ ህልውና ምንም እንዳላሉ መስክሮላቸዋል፤ ፦
69፥44-46 በእኛ ላይም ከፊልን ቃላት ያላልነውን "በቀጠፈ" ኖሮ وَلَوْ تَقَوَّلَ عَلَيْنَا بَعْضَ ٱلْأَقَاوِيلِ ፤ በኀይል በያዝነው ነበር لَأَخَذْنَا مِنْهُ بِٱلْيَمِينِ ፡፡ ከዚያም ከእርሱ የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ثُمَّ لَقَطَعْنَا مِنْهُ ٱلْوَتِينَ ፡፡

""የልቡን ሥር በቆረጥን ነበር ""ብሎ ማለት የቱን ያህል በግህደተ-መለኮት ቀልድ እንደሌለ የሚያሳይ ሃይለ-ቃል ነው። ከአላህ ወዲህ የትኛው ንግግር ማስረጃ ሊሆን ይችላል? ቁርአንን አላህ ነው ያወረደው፤ አላህ ከሰው ሆነ ከሸይጣን ቃላት ጠብቆታል፣ ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፦
15:9 እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
41:42 ከኋላውም ከፊቱም ውሸት አይመጣበትም፤ ጥበበኛ ምስጉን ከሆነውጌታ የተወረደ ነው።

በቂሰቱል ገራኒቅ ዋቢ ደርስ የዶክተር ሸኽ ያሲር ”ሀፊዘሁላህ” ሌክቸር እዚህ ይመልከቱ፦
https://youtu.be/wFq5ZnD6pFQ

መደምደሚያ
ይህንን የተመታ እና የተመምታታ ውሃ የማያነሳ ሙግት ሳልማን ሩሽዲ በ 1988 AD "ሰይጣናዊ አንቀፅ" የሚል መጽሐፉን ሲያራግቡ ከነበሩት መካከል ሚሽነሪዎች አንዶቹ ናቸው፤ እስቲ በዚህ ሂስ ባይብል ላይ ያለውን ዳዊት እንመልከተው፤ ይህን ሙግት የዳዊትን ነብይነት ለማስተባበል ሳይሆን እሾህክን በእሾክ እንዴት እንደሆነ ለማሳየት ነው፤ ዳዊት እስራኤልን ቁጠር ሳይባል ቆጥሮ ዳዊት በሰራው ስህተት እግዚአብሔር በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ልኮ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች በመቅሰፍት ገደለ፦
2ኛ ሳሙኤል 24.14 እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ቸነፈርን ሰደደ፤ ከእስራኤልም ሰባ ሺህ ሰዎች ወደቁ።

ይህ ስህተት የራሱ የዳዊት እንደሆነ አምኗል፣ ይቅርታም ጠይቋል፣ ከዚያም ባሻገር ይህ የእኔ ስህተት ነው ህዝቡን አትንካ ብሎ ጸለየ፣ ነገር ግን የዳዊት ልመናም አልሰራም፦
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥8 ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ይህን በማድረግ እጅግ በድያለሁ፤ አሁን ግን ታላቅ ስንፍና አድርጌአለሁና የባሪያህን ኃጢአት ታስወግድ ዘንድ እለምንሃለሁ አለው።
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥17 ዳዊትም እግዚአብሔርን፦ ሕዝቡ ይቈጠር ዘንድ ያዘዝሁ እኔ አይደለሁምን? የበደልሁና ክፉ የሠራሁ እኔ ነኝ፤ እነዚህ በጎች ግን ምን አድርገዋል? አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ እጅህ በእኔና በአባቴ ቤት ላይ ትሁን፥ ነገር ግን ይቀሠፍ ዘንድ በሕዝብህ ላይ አትሁን አለው።

ታዲያ ዳዊት ማን ቁጠር ብሎት ነው የቆጠረው? ስንል
ዳዊት እስራኤልን የቆጠረው ሰይጣን "ቁጠር" ብሎት ነው ይለናል፦
2ኛ ሳሙኤል 24.1 ደግሞም የእግዚአብሔር ቍጣ በእስራኤል ላይ ነደደ፥ ዳዊትንም፦ *ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር* ብሎ በላያቸው አስነሣው።

ሂድ፥ እስራኤልንና ይሁዳን ቍጠር ያለው ሰይጣን ነው፥ እርሱ የተባለው ህቡዕ ተውላጠ-ስም ሰይጣን መሆኑን ሌላ ጥቅስ ይነግረናል፦
1ኛ ዜና መዋዕል 21፥1 ሰይጣንም በእስራኤል ላይ ተነሣ፥ እስራኤልንም ይቈጥር ዘንድ ዳዊትን "አንቀሳቀሰው"።

"አንቀሳቀሰው" ብለው ያስቀመጡት የዕብራይስጡ ቃል "የሰት" תְּסִיתֵ֥נִי ሲሆን "ሱት" סוּת ማለትም "አሳሳተ" ከሚል ግስ የመጣ ነው ፣ ለሃሰተኛ ነብይ ማሳሳት "የስቲአከ" יְסִֽיתְךָ֡ ማለትም "ቢያስትህ" በሚል መጥቷል፦
ዘዳግም 13.6 አንተም አባቶችህም የማታውቋቸውን ሌሎች አማልክት እናምልክ ብሎ ቢያስትህ יְסִֽיתְךָ֡፥

ዳዊትም ከሰይጣን መልዕክት የተቀበለውን ለኢዮአብንና ለሕዝቡ አለቆች ቍጠሩ ብሎ አስተላልፏል፦
ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 21.8 ዳዊትም ኢዮአብንና የሕዝቡን አለቆች፦ ሂዱ፥ ከቤርሳቤህ ጀምሮ እስከ ዳን ድረስ እስራኤልን ቍጠሩ፥ ድምራቸውንም አውቅ ዘንድ አስታውቁኝ አላቸው።

አንዱ ይህንን ሙግት ሳቀርብለት ዳዊት ነብይ አይደለም ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ ሊክደኝ ሞክሯል፤ በባይብል የተብራራው ዳዊት የፈጣሪ ነብይ እንደሆነ ይናገራል፦
2፡29-30 ወንድሞች ሆይ፥ ስለ አባቶች አለቃ ስለ ዳዊት እንደ ሞተም እንደ ተቀበረም ለእናንተ በግልጥ እናገር ዘንድ ፍቀዱልኝ፤ መቃብሩም እስከ ዛሬ በእኛ ዘንድ ነው። *ነቢይ ስለ ሆነ*፥
1
አዎ ዳዊት ነብይ ነበረ ከተባለ፤ የነብይ መስፈርቱ ከፈጣሪ መልዕክት መቀበል ወይስ ከሰይጣን መልዕክት መቀበል ? ፍርዱን ለህሊና።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የሚለቀቁ ትምህርቶችን ለመከታተል
ጥሪያችን Tiriyachen
https://fb.me/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
1
ሙት ማስነሳት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ማርታ የሞተውን ወንድሟን አልአዛርን ኢየሱስ እግዚአብሔርን ለምኖ ከሞት እንደሚያስነሳላት ጠንቅቃ ታውቅ ነበር፤ ለዚህ ነው “አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም ነበር” ያለችው፦
ዮሐንስ 𝟏𝟏፥𝟐𝟏-𝟐𝟓 ማርታም ኢየሱስን። ጌታ ሆይ፥ “”አንተ በዚህ ኖረህ ብትሆን ወንድሜ ባልሞተም”” ነበር፤ አሁንም “”ከእግዚአብሔር የምትለምነውን ሁሉ እግዚአብሔር እንዲሰጥህ አውቃለሁ”” አለችው።

ኢየሱስ አብን ለምኖ ሰዎች እግዚአብሔር እንዳላከው እንዲያምኑበት የተሰጠው ስራ እንደሆነ መናገሩ ነው፦
ዮሐንስ 𝟏𝟏፥𝟒𝟏-𝟒𝟒 ድንጋዩንም አነሡት። ኢየሱስም ዓይኖቹን ወደ ላይ አንሥቶ። “አባት ሆይ፥ ስለ ሰማኸኝ አመሰግንሃለሁ፤ ሁልጊዜም እንድትሰማኝ” አወቅሁ፤ ነገር ግን “አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ ዘንድ” በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ። ይህንም ብሎ በታላቅ ድምፅ። አልዓዛር ሆይ፥ ወደ ውጭ ና ብሎ ጮኸ። የሞተውም እጆቹና እግሮቹ በመግነዝ እንደ ተገነዙ ወጣ፤ ፈቱም በጨርቅ እንደ ተጠመጠመ ነበር። ኢየሱስም። ፍቱትና ይሂድ ተዉት አላቸው።

ብሉይ ኪዳን ላይ የነበሩት ሁለት ነቢያት ኤልያስ እና ኤልሳዕ የሁለት ሴቶችን ልጆች በፀሎት ህይወት በመስጠት አስነስተዋል፦
𝟏. ኤልያስ
𝟏ኛ ነገሥት 𝟏𝟕፥𝟐𝟏-𝟐𝟑 በብላቴናውም ላይ ሦስት ጊዜ ተዘረጋበት፥ ወደ እግዚአብሔርም። አቤቱ አምላኬ ሆይ፥ የዚህ ብላቴና ነፍስ ወደ እርሱ ትመለስ ዘንድ እለምንሃለሁ ብሎ ጮኸ፤ እግዚአብሔርም “የኤልያስን ቃል ሰማ፤ የብላቴናው ነፍስ ወደ እርሱ ተመለሰች”፥ እርሱም ዳነ፤ ኤልያስም ብላቴናውን ይዞ ከሰገነቱ ወደ ቤት አወረደው፥ ኤልያስም። እነሆ፥ “ልጅሽ በሕይወት ይኖራል” ብሎ ለእናቱ ሰጣት።
𝟐. ኤልሳዕ
𝟏ኛ ነገሥት 𝟒፥𝟑𝟐-𝟑𝟒 ኤልሳዕም ወደ ቤት በገባ ጊዜ እነሆ፥ “ሕፃኑ ሞቶ” በአልጋው ላይ ተጋድሞ ነበር። ገብቶም በሩን ከሁለቱ በኋላ ዘጋ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ መጥቶም በሕፃኑ ላይ ተኛ፤ “አፉንም በአፉ፥ ዓይኑንም በዓይኑ፥ እጁንም በእጁ ላይ አድርጎ ተጋደመበት፤ የሕፃኑም ገላ ሞቀ”፤ ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ሕፃኑም ዓይኖቹን ከፈተ።

የዕብራውያን ጸሐፊ ይህንን ጉዳይ በማስታወስ በኤልያስ እና በኤልሳዕ ዘመን የነበሩት ሁለት ሴቶሽ ሙታን ልጆቻቸውን በትንሳኤ ተቀበሉ ይለናል፦
𝟏𝟏፥𝟑𝟓 ሴቶች ሙታናቸውን “በትንሣኤ” ተቀበሉ፤

ሰዎች ይደነቁ ዘንድ አብ ለኢየሱስ ሙታንን እንዲያነሣ ሕይወትም እንዲሰጥ አድርጎታል፤ ይህንን የአብን ስራ ኢየሱስ በአብ ስም ይሰራል፦
ዮሐንስ 𝟏𝟎፥𝟐𝟓 ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል። ነገርኋችሁ አታምኑምም “”እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ስለ እኔ ይመሰክራል””፤”
ዮሐንስ 𝟏𝟎:𝟑𝟕 እኔ “”የአባቴን ሥራ”” ባላደርግ አትመኑኝ፤”
በኢየሱስ ይህንን ስራ የሚሰራው አብ ነው፤ ኢየሱስ የሰራውን ስራ በእርሱ መልእክተኝነት ያመኑ ሰዎችም ኢየሱስ ከሰራው ስራ ሊሰሩ እንደሚችሉ እራሱ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 𝟏𝟒፥𝟏𝟎-𝟏𝟑 እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ አታምንምን? እኔ የምነግራችሁን ቃል ከራሴ አልናገረውም፤ ነገር ግን “”በእኔ የሚኖረው አብ እርሱ ሥራውን ይሠራል””፤ እኔ በአብ እንዳለሁ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ “ስለ ራሱ ስለ ሥራው”” እመኑኝ፤ እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ በእኔ የሚያምን “”እኔ የማደርገውን ሥራ እርሱ ደግሞ ያደርጋል፤ ከዚህም የሚበልጥ ያደርጋል””፥

በዚህ መሰረት ኢየሱስ ነብይነት ያመኑት ሃዋርያትም ኢየሱስ የሰራውን ስራ ማለትም ሰው ከሞት ማስነሳት ሰርተውቷል፦
ማቴዎስ 𝟏𝟎፥𝟖 “ድውዮችን ፈውሱ፤ “”ሙታንን አስነሡ””፤ ለምጻሞችን አንጹ፤ አጋንንትን አውጡ፤ በከንቱ ተቀበላችሁ፥ በከንቱ ስጡ።
የሐዋርያት ሥራ 𝟗:𝟒𝟎 ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ “”ሬሳውም”” ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ “”ተነሺ”” አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች።”

እንደ ባይብሉ ኢየሱስ ሙት አስነስቶ ህይወት መስጠት አብ ለኢየሱስ መልክተኛነት በስጦታ የሰጠው ስራ እንደሆነ ኢየሱስ ፍትንውና ቁልጭ ባለ መልኩ ተናግሯል፦
ዮሐንስ 𝟏𝟕:𝟒 እኔ ላደርገው “የሰጠኸኝን ሥራ” ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ፤
ዮሐንስ 𝟓:𝟑𝟔 እኔ ግን ከዮሐንስ ምስክር የሚበልጥ ምስክር አለኝ፤ አብ ልፈጽመው “የሰጠኝ ሥራ”፥ ይህ የማደርገው ሥራ፥ “”አብ እንደ “”ላከኝ” ስለ እኔ ይመሰክራልና””።
ዮሐንስ 𝟏𝟏፥𝟒𝟐 ሁልጊዜም እንድትሰማኝ አወቅሁ፤ ነገር ግን “”አንተ እንደ ላክኸኝ ያምኑ”” ዘንድ በዚህ ዙሪያ ስለ ቆሙት ሕዝብ ተናገርሁ አለ።

ኢየሱስ ሙት በማስነሳት ህይወት የሰጠው በላከው ፈቃድ እንጂ በራሱ ፈቃድ አይደለም፤ ከራሱማ ምንም ማድረግ አይችልም፤ የኢየሱስ ተአምራት፣ ድንቆች እና ምልክቶችም እግዚአብሔር በኢየሱስ በኩል ያደረገው ነው፤ በተጨማሪም የናዝሬቱ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር ለእስራኤል ሰዎች የተላከ ሰው መሆኑን አበክሮና አዘክሮ የሚያሳይ ነው፦
ዮሐንስ 𝟓:𝟑𝟎 “”እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም””፤ እንደ ሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፥ “”የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና”:።
የሐዋርያት ሥራ 𝟐:𝟐𝟐 “”የእስራኤል ሰዎች”” ሆይ፥ ይህን ቃል ስሙ፤ ራሳችሁ እንደምታውቁ፥ የናዝሬቱ ኢየሱስ እግዚአብሔር በመካከላችሁ “”በእርሱ”” በኩል ባደረገው “”ተአምራትና በድንቆች በምልክቶችም” ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ “”ሰው”” ነበረ፤”

በተለይ “ራሴ”My selF” የሚለው ድርብ ተውላጠ-ስም”REflexivE PRonoUn” ስጋን፣ አጥንት አሊያም ደምን ሳይሆን የሚያመለክተው ሙሉ ማንነትን ነው፤ ይህ ከሆነ ኢየሱስ በሙሉ ማንነቱ አብ ከሰጠው ስልጣን ውጪ ከራሱ ምንም ማድረግ አይችልም።

የዓለማቱ ጌታ አላህ ከፊሉን መልእክተኛ በከፊሉ ላይ በደረጃ አብልጧል፤ ለድንግል ማርያም ልጅ ለኢየሱስ ግልፅ የሆነ ታምራት ሰጥቶታል፦
𝟐፥𝟖𝟕 ሙሳንም መጽሐፍን በእርግጥ ሰጠነው፡፡ ከበኋላውም መልክትኞችን አስከታተልን፤ የመርየምን ልጅ ዒሳንም “ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው”፡፡
𝟐፥𝟐𝟓𝟑 እነዚህን መልክተኞች “”ከፊላቸውን በከፊሉ ላይ አበለጥን””፤ ከእነርሱ ውስጥ አላህ ያነጋገረው አልለ፡፤ “”ከፊሎቻቸውንም በደረጃዎች ከፍ አደረገ””፤ የመርየምን ልጅ ዒሳንም “”ግልጽ ታምራቶችን ሰጠነው””፡፡

አምላካችን አላህ ለነቢዩ ኢየሱስ ነብይነት ከሰጠው ታምራት አንዱ የሆነው ሙታንን በአላህ ፈቃድ ከሞት ማስነሳት እንደሆነ ኢየሱስ በተልእኮው ተናግሯል፦
𝟑፥𝟒𝟗 ወደ እስራኤልም ልጆች መልክተኛ ያደርገዋል፡፡ ይላልም፡- «እኔ ከጌታዬ ዘንድ “”በተዓምር”” ወደ እናንተ መጣሁ፡፡ እኔ ለናንተ ከጭቃ እንደ ወፍ ቅርፅ እፈጥራለሁ፡፡ በርሱም እተነፍስበታለሁ፡፡ በአላህም ፈቃድ ወፍ ይኾናል፡፡ “”በአላህም ፈቃድ”” ዕውር ኾኖ የተወለደን፣ ለምጸኛንም አድናለሁ፡፡ “”ሙታንንም አስነሳለሁ””፡፡
👍31
አላህም ለኢየሱስ ካደረገው ከውለታ አንዱ በአላህ ፈቃድ ሙታንን ከመቃብር ማስነሳት እንደሆነ ይናገራል፦
𝟓፥𝟏𝟏𝟎 አላህ በሚል ጊዜ አስታውስ፡- «የመርየም ልጅ ዒሳ ሆይ! በአንተና በእናትህ ላይ የዋልኩላችሁን ጸጋዬን አስታውስ፡፡ በሕፃንነትና በከፈኒሳነት ሰዎችን የምትናገር ስትኾን በቅዱስ መንፈስ ባበረታሁህ ጊዜ፤ ጽሕፈትንና ጥበብንም ተውራትንና ኢንጂልንም ባስተማርኩህ ጊዜ፣ ከጭቃም የወፍ ቅርጽ ብጤ በፈቃዴ በምትሠራና

በውስጧ በምትነፋ በፈቃዴም ወፍ በምትኾን ጊዜ፣ ዕውርም ኾኖ የተወለደንና ለምጻምንም በፈቃዴ በምታሽር ጊዜ፣ “”ሙታንንም በፈቃዴ ከመቃብራቸው በምታወጣ ጊዜ”፣ያደረግሁልህን ውለታ አስታውስ፡፡

“”በአላህም ፈቃድ”” ..””ሙታንንም አስነሳለሁ”” እና “”ሙታንንም በፈቃዴ ከመቃብራቸው በምታወጣ ጊዜ” የሚሉት ቃላት ይሰመርበት፤ ስለዚህ ኢየሱስ በአላህ ፈቃድ ሙት ማስነሳቱ ለእርሱ መልእክተኛነት ማስረጃ መሆኑን እንረዳለን እንጂ ጭራሽ ለአምላክነት ሸርጥ ነው ብሎ እንደ ደሊል መረጃ ማቅረብ እጅግ በጣም ሲበዛ ቂ*ል*ነ*ት ነው።

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
4👍1
ታላቁ ታምር

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

6:124 “ታምርም” በመጣላቸው ጊዜ፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ وَإِذَا جَآءَتْهُمْ ءَايَةٌۭ قَالُوا۟ لَن نُّؤْمِنَ حَتَّىٰ نُؤْتَىٰ مِثْلَ مَآ أُوتِىَ رُسُلُ ٱللَّهِ ۘ ٱللَّهُ أَعْلَمُ حَيْثُ يَجْعَلُ رِسَالَتَهُۥ ۗ سَيُصِيبُ ٱلَّذِينَ أَجْرَمُوا۟ صَغَارٌ عِندَ ٱللَّهِ وَعَذَابٌۭ شَدِيدٌۢ بِمَا كَانُوا۟ يَمْكُرُونَ ፡፡

መግቢያ
ቁርኣን ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ ከተሰጣቸው ተአምራት ውስጥ ታላቁ እና ዋነኛው ነው፣ የቁርኣን ተአምራዊነት ከቀደምት ነቢያት ተአምራት በሁለት መልኩ ይለያል፦
አንደኛ የቀደምት ነቢያት ተአምራት በአይን የሚታይ፣ በእጅ የሚዳሰስ ነው፣ ይህም ታምር ”ሒስሲይ” ይባላል፣ የቀደምት ነቢያት ተአምር ከነቢይነት ዘመናቸው ጋር ብቻ የተቆራኘ ነው፣ ከእነርሱ ሞት በኋላ ያበቃል፣ ይህም ታምር ”ወቅቲይ” ማለትም ጊዜአዊ ይሰኛል፡፡
ሁለተኛ ለነቢያችን ነቢይነት እንደ ማስረጃ የተሰጣቸው ቁርኣን ግን ህሊናን የሚያናግር፡ አእምሮን የሚቆጣጠርና ልብን የሚገዛ፣ በሚያስተላልፋቸው መልእክቱ ሰዎችን ለለውጥ የሚዳርግ ነው፣ ይህም ታምር ”መዕነዊይ” ይባላል፣ ቁርኣን ከነቢያችን ሞት በኋላ እንኳ ተአምራዊነቱ አላከተመም፣ እስከ ቂያማ ድረስ በነበረው ተአምራዊነቱ ይቀጥላል፤ በዚህም ”አበዲይ” ይሰኛል፡፡ እስቲ ይህንን ታላቅ ታምር በወረደበት ወቅት ሰዎች እንዴት እንዳስተባበሉት እንመልከት፦

ነጥብ አንድ
“የአላህ ታምራት”
ቁርአን በወረደ ጊዜ ሰዎች፦ “ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም” አሉ፤ አምላካችን አላህም፦ “አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው” በላቸው ብሎ መለሰ ሰጠ፦
6:37 *«ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም»* አሉ፡፡ *«አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው*፡፡ ግን አብዛኞቻቸው አያውቁም፡፡

አላህ ቁርኣንን ታምር አድርጎ ለነቢያችን ነቢይነት ማረጋገጫ ይሆን ዘንድ እንዳወረደው ይናገራል፦
3:108 ይህች በአንተ ላይ በእዉነት የምናነባት ስትሆን የአላህ *ታምራት* آيَاتُ ናት፤
45:6 እነዚህ፣ በአንተ ላይ በእውነት የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤ ከአላህና *ከታምራቶቹም* وَآيَاتِهِ ወዲያ በየትኛው ንግግር ያምናሉ?
2:252 እነዚህ በእውነት በአንተ ላይ የምናነባቸው ሲኾኑ *የአላህ ታምራት* آيَاتُ ናቸው፤
3:58 ይህ *ከታምራቶች”* الْآيَاتِ እና ጥበብን ከያዘዉ ተግሣጥ ሲሆን በአንተ ላይ እናነበዋለን።

አላህ የሚነበብ ሆኖ ቁርአን መወረዱ ታምር እንደሆነ እንደነገረን ሁሉ ነብያችንም ቁርአን ለእሳቸው ነብይነት ታምር እንደሆነ በአጽንኦትና በአንክሮት ነግረውናል፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 66 , ሐዲስ 3:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደተረከው፦ ነብዩ”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ማንኛውም ነብይ ህዝቦቹ ያምኑበት ዘንድ ታምር ተሰጠውታል፣ ነገር ግን ለእኔ የተሰጠኝ ታምር አላህ ወደ እኔ ያወረደው ወህይ ነው عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ النَّبِيُّ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ مَا مِنَ الأَنْبِيَاءِ نَبِيٌّ إِلاَّ أُعْطِيَ مَا مِثْلُهُ آمَنَ عَلَيْهِ الْبَشَرُ، وَإِنَّمَا كَانَ الَّذِي أُوتِيتُ وَحْيًا أَوْحَاهُ اللَّهُ إِلَىَّ فَأَرْجُو أَنْ أَكُونَ أَكْثَرَهُمْ تَابِعًا يَوْمَ الْقِيَامَةِ ‏” ።
ነጥብ ሁለት
“ማስተባበያ”
ሰዎች ቁርአን ታምር ሆኖ በመጣላቸው ጊዜ፡- “የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም” ወይም “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” ብለው ይህንን ታምር አስተባበሉ፦
6:124 *”ታምርም በመጣላቸው ጊዜ”*፡- «የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ እስክንሰጥ ድረስ በፍጹም አናምንም» አሉ፡፡
28:48 እውነቱም ከእኛ ዘንድ በመጣላቸው ጊዜ “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ ። ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን? አሉም “የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” ፤ አሉም “እኛ በሁለቱም ከሀዲዎች ነን”።

ለሙሳ የተሰጠው ግልጽ የሆኑን “ዘጠኝ ታምራቶች” ናቸው፦
17:101 ለሙሳም ግልጽ የሆኑን “ዘጠኝ ታምራቶች” በእርግጥ ሰጠነው፤

አላህ ታምር ብሎ “ዘጠኝ ታምራቶች” ቢያሳይም በወቅቱ ሙሳና ሃሩንን “የተረዳዱ ሁለት ድግምተኞች ናቸው” አሉ፤ ከዚህ ታምር ይልቅ “ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ ለአንተ በፍጹም አናምንልህም” አሉ፦
2:55 ሙሳ ሆይ አላህን በግልጽ እስከምናይልህ ድረስ በአንተ በፍጹም አናምንልህም ”

በወቅቱ የነበሩ ሰዎች ስለ ነብያችን፦ “ለሙሳ የተሰጠው ቢጤ አይሰጠውም ኖሯልን ” አሉ፤ አላህም፦ “ከዚህ በፊት ሙሳ በተሰጠው አልካዱምን?” በማለት ያ የተባለው ታምር ተመልሶ ቢመጣ አሁን ማስተባበላቸውን እንደማይቀር ተናግሯል።

ነጥብ ሶስት
“አስጠንቃቂ”
እነዚያም የካዱት፦ “በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?” ብለው የጠየቁት ታምር የአላህ መልክተኞች የተሰጡትን ብጤ አይነት ታምር ነው፤ ይህንን ታምር ነብያችን በራሳቸው ማምጣት አይችሉም፤ እርሳቸው አስጠንቃቂ እንጂ በፍላጎታቸው ታምር እውራጅ አይደሉም፤ ታምር አውራጅ አላህ ነው፤ ስለሆነም ቁርአን በእርሳቸው ላይ ታምር አድርጎ አውርዷል፦
13:7 እነዚያም የካዱት፦ “በእርሱ ላይ ከጌታው ታምር ለምን አልተወረደለትም?” ይላሉ፤ አንተ “አስጠንቃቂ” ብቻ ነህ ለሕዝብም ሁሉ መሪ አላቸው።
10:20 በእርሱ ላይም ከጌታው የሆነች ታምር ለምን አትወረድለትም ይላሉ፡፡ «ሩቅ ነገርም ሁሉ የአላህ ብቻ ነው፡፡ ተጠባበቁም፤ እኔ ከናንተ ጋር ከሚጠባበቁት ነኝና» በላቸው፡፡
6:37 «ከጌታውም በእርሱ ላይ ለምን ተዓምር አልተወረደም» አሉ፡፡ «አላህ ተአምርን በማውረድ ላይ ቻይ ነው» በላቸው፡፡

በእርግጥም አንድ መልእክተኛ ሲመጣ አላህ በፈቃዱ ከሚሰጠው ታምር በራሱ ሊያመጣ አይችል፦
13:38 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ እንጂ፥ ታምር ሊያመጣ አይገባውም*፤
40:78 ለማንኛውም *መልክተኛ በአላህ ፈቃድ ካልሆነ ታምርን ሊያመጣ አይገባውም*።

መደምደሚያ
በኢየሱስ ዘመንም ኢየሱስ ብዙ ታምር እያደረገ በዘመኑ የነበሩ ሰዎች የሚጠይቁት ታምር ግን ከሰማይ ነው፤ ኢየሱስም እነርሱን የጠየቁትን ታምር ከመፈፀም ይልቅ “ለዚህ ትውልድ *”ምልክት አይሰጠውም”* ብሎ መለሰ፦
ማርቆስ 8፥11-12 ፈሪሳውያንም ወጡና ሊፈትኑት *”ከሰማይ ምልክት”* ከእርሱ ፈልገው ከእርሱ ጋር ይከራከሩ ጀመር። በመንፈሱም እጅግ ቃተተና፦ ይህ ትውልድ ስለ ምን *”ምልክት”* ይፈልጋል? እውነት እላችኋለሁ፥ ለዚህ ትውልድ *”ምልክት አይሰጠውም”* አለ።
ማቴዎስ 16:4 ክፉና አመንዝራ ትውልድ *”ምልክት”* ይሻል፥ ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር *”ምልክት አይሰጠውም”*። *ትቶአቸውም ሄደ*።
👍1
ኢየሱስ፦ “ለዚህ ትውልድ ምልክት አይሰጠውም” ማለቱ ሰዎች የፈለጉት ከሰማይ ምልክት አላደርግም ማለት እንጂ ምልክት አለማድረግን አያሳይም፣ እነርሱ የፈለጉት ምልክት ከሰማይ ምልክት ነው፣ ነገር ግን ኢየሱስ እነርሱ ከጠየቁት ታምር በተቃራኒው ያደረገውን ታምር በፊታቸው ምንም ቢያደርግ በእርሱ አላመኑም፦
ዮሐንስ 12፥37-38 ነገር ግን ይህን ያህል *”ምልክት በፊታቸው ምንም ቢያደርግ”* ነቢዩ ኢሳይያስ፦ ጌታ ሆይ፥ ማን ምስክርነታችንን አመነ? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገለጠ? ብሎ የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ *”በእርሱ አላመኑም”*።

በተመሳሳይም በነቢያችን ዘመን የነበሩት ሰዎች ታምር ብለው የሚሉትና አላህ ታምር የሚለው ሁለት ለየቅል ነው፣ የቁርአንን ታላቅ ታምርነት በወቅቱ የነበሩት ሰዎች እነርሱ በሚፈልጉት መልኩ ባይመጣም ለሰው የሚበጅ ታምር ማምጣት የሚችለው አላህ ብቻ ነው፤ ከላይ የቀረበውን ነጥብ በኢየሱስ ታምር ማሳያነት በቀላሉ መረዳት ይቻላል። አላህ ታምር ሲመጣላቸው እነርሱ የሚፈልጉት ያንን ታምር ስላልሆነ ይሸሻሉ፦

36:46 ከጌታቸውም ታምራት ማንኛይቱም ታምር አትመጣላቸውም፤ ከእርሷ የሚሸሹ ቢሆኑ እንጂ። وَمَا تَأْتِيهِم مِّنْ ءَايَةٍۢ مِّنْ ءَايَٰتِ رَبِّهِمْ إِلَّا كَانُوا۟ عَنْهَا مُعْرِضِينَ

እነዚያን በአላህ ታምራት ያስተባበሉ እሳት ይገባሉ፦
4፥56 እነዚያን *በተአምራታችን ያስተባበሉትን በእርግጥ እሳትን እናገባቸዋለን*፡፡ إِنَّ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ بِـَٔايَٰتِنَا سَوْفَ نُصْلِيهِمْ نَارًۭا

ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

Follow us on:
https://fb.me/tiriyachen
https://www.tg-me.com/tiriyachen
https://tiriyachen.org
https://bit.ly/3eVixKv
https://www.tiktok.com/@tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም።
2025/07/11 22:08:06
Back to Top
HTML Embed Code: