Telegram Web Link
ጥቁር አዝሙድ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

59፥7 *መልክተኛውም የሰጣችሁን ማንኛውንም ነገር ያዙት! ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ*፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና። وَمَآ ءَاتَىٰكُمُ ٱلرَّسُولُ فَخُذُوهُ وَمَا نَهَىٰكُمْ عَنْهُ فَٱنتَهُوا۟ ۚ وَٱتَّقُوا۟ ٱللَّهَ ۖ إِنَّ ٱللَّهَ شَدِيدُ ٱلْعِقَابِ

ኢሥላም ዱር ሙሥሊሙ ሐሩር እንዲሆን ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና፥ ጠብ እርግፍ የሚሉት አግድም አደግ ዕውቀት ያላቸው ሚሽነሪዎች፦ “ነቢያችሁ"ﷺ"፦ *"በጥቁር አዝሙር ውስጥ ከሞት በስተቀር ከሁሉም በሽታ መድኃኒት ነው” ብለዋል፥ ስለዚህ ጥቁር አዝሙር ለኤች አይቪ ኤድስ፣ ለኮሮና ቫይረስ እና ለመሳሰሉት መድኃኒት እንዴት አልሆነም? እያሉ ይጠይቃሉ። እኛም ደግሞ ጥሬውን ከብስል ምርቱን ከእንክርዳር የሚለዩ ሊሒቃን፦ “ ነገርን ከሥሩ ውኃን ከጡሩ” እንደሚሉት ኢንሻሏህ ከሥሩ ጥናት በማድረግ መልስ እንሰጣለን፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 76, ሐዲስ 11
አቢ ሁራይራህ ሰምቶ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"በጥቁር አዝሙር ውስጥ ከሞት በስተቀር ከሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው"*። أَنَّ أَبَا هُرَيْرَةَ، أَخْبَرَهُمَا أَنَّهُ، سَمِعَ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ فِي الْحَبَّةِ السَّوْدَاءِ شِفَاءٌ مِنْ كُلِّ دَاءٍ إِلاَّ السَّامَ ‏"‌‏

፨ አንደኛ እዚህ ሐዲስ ላይ “ኩል” كُلٌّ ማለትም “ሁሉ” የሚለው ቃል ተቀምጧል። “ኩል” كُلٌّ በዐረቢኛ ሰዋስው ውስጥ ፍጹማዊ “Absolute” ሆኖ ሲመጣ “ኩሉል ሙጥለቅ” كُلٌّ ٱلْمُطْلَق ሲባል፥ በአንጻራዊ “Relative” ሆኖ ሲመጣ ደግሞ “ኩሉል ቀሪብ” كُلٌّ ٱلْقَرِيب‎ ይባላል። እዚህ ሐዲስ ላይ "ኩል" የሚለው ቃል ኩሉል ቀሪብ መሆኑን የምናውቀው "ኩል" በሚል ቃል መነሻ ላይ "ሚን" مِنْ ማለትም "ከ"from" የሚል መስተዋድድ መምጣቱ ነው፥ እስቲ ተመሳሳይ ሰዋስው እንመልከት፦
14፥34 "ከ"ለመናችሁትም ሁሉ የሰጣችሁ ነው፡፡ وَآتَاكُم مِّن كُلِّ مَا سَأَلْتُمُوهُ
13፥3 እርሱም ያ ምድርን የዘረጋ በእሷም ተራራዎችን እና ወንዞችን ያደረገ በውስጧም “ከ”ፍሬዎች ሁሉ ሁለት ሁለት ጥንዶችን ያደረገ ነው*፡፡ وَهُوَ الَّذِي مَدَّ الْأَرْضَ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَاسِيَ وَأَنْهَارًا ۖ وَمِن كُلِّ الثَّمَرَاتِ جَعَلَ فِيهَا زَوْجَيْنِ اثْنَيْنِ

"የለመናችሁትን ሁሉ የሰጣችሁ ነው" ሳይሆን "ከ"ለመናችሁት ሁሉ" ማለት ከፊልን ያሳያል፥ በተመሳሳይ "ፍሬዎች ሁሉ" ሳይሆን "ከ"ፍሬዎች ሁሉ " ማለት ከፊልን ያሳያል። በተመሳሳይም "ለሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው" ሳይሆን "ከ-ሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው" ማለት ከፊልን ያሳያል።

፨ ሁለተኛ ሐዲሱ ላይ "ኢላ" إِلَّا ማለትም "በቀር" የሚል ሐርፉል ሐስድ ይጠቀማል። "ሐርፉል ሐስድ" حَرْف الحَصْرْ ማለት "ግድባዊ መስተዋድድ"restriction particle" ማለት ሲሆን ይህም ሐስድ በሁለት ዋና ዋና ዐበይት ክፍሎች ይከፈላል፥ እርሱም አንደኛው “ሐስዱል ሙጥለቅ” حَصْرْ ٱلْمُطْلَق ማለትም “ፍጹማዊ ግድብ“Absolute restriction” ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ “ሐስዱል ቀሪብ” حَصْرْ ٱلْقَرِيب‎ ማለትም “አንጻራዊ ግድብ“Relative restriction” ነው። ይህንን ናሙና እንይ፦
26፥77 *”«እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር እርሱ ወዳጄ ነው”*፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ
46፥25 *"በጌታዋ ትዕዛዝ አንዳቹን ሁሉ ታጠፋለች፥ ከመኖሪያዎቻቸውም በስተቀር ምንም የማይታዩ ኾኑ፡፡ تُدَمِّرُ كُلَّ شَيْءٍ بِأَمْرِ رَبِّهَا فَأَصْبَحُوا لَا يُرَىٰ إِلَّا مَسَاكِنُهُمْ

ኢብራሂም፦ "የዓለማት ጌታ ሲቀር" ሲል ከአሏህ ውጪ ያሉ መላእክት፣ ነቢያት እና ምእመናን ጠላቶቼ ናቸው ማለት እንዳልሆነ ሁሉ፣ እንዲሁ ነፋስ ከመኖሪያዎቻቸው በቀር ሁሉን ታጠፋለች ሲባል መላእክት፣ ነቢያት እና ምእመናን ታጠፋለች ማለት እንዳልሆነ ሁሉ በተመሳሳይ "ከሞት በስተቀር ከሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው" ማለት "ሁሉ" የሚለው ቃል አንጻራዊ "በቀር" የሚለው ግድባዊ አነጋገር ነው። ስለዚህ ጥቁር አዝሙድ ለካንሰር እባጭ፣ ለስኳር በሽታ፣ ለተቅማጥ፣ ለደረቅ ሳል፣ ለጆሮ ህመም፣ ለዓይን ህመም፣ ለእይታ ችግር፣ ለፊት ፓራሊሲስ፣ ለጉንፋን፣ ለፍሉ፣ ለሐሞት ጠጠር፣ ለጉበት ጠጠር፣ ለሆድ ትላትል፣ ለሆድ ህመም፣ ለሪህ፣ ለጀርባ ህመም፣ ለአፍ ኢንፌክሽን ቫይረስ፣ ለጡንቻ ህመም፣ ለራስ ህመም፣ ለማይግሬን፣ ለማስታወስ ችሎታ ለፀጉር መሳሳት እረ ስንቱ ተዘርዝሮ ይለቅ? ለዚህ ሁሉ መድኃኒት ነው፥ ቅሉ ግን "ሁሉ" እና "በቀር" የሚለው "ኢሥቲስናእ” اِسْتِثْنَاء‏ ማለትም "ግድባዊ"exceptional" ሆኖ የመጣ ነው።

፨ ሦስተኛ "በጥቁር አዝሙር ውስጥ ከሞት በስተቀር ከሁሉም በሽታ መድኃኒት ነው" ስለተባለ ጥቁር አዝሙድን ዝም ብሎ መውሰድ ያድናል ማለት ሳይሆን እንዴት መቀመም እንዳለበት ጥናት እና ከአሏህ ዘንድ ጥበቡ ያስፈልጋል። ለምሳሌ የፋርማሲይ ምልክቱ የእባብ መርዝ ነው፥ የእባብ መርዝ ፕሮቲን ሲሆን ከእኛ ፕሮቲን ጋር በቀጥታ ስለማይመጣጠን ለእኛ መርዝ ነው። ቅሉ ግን የእባብ ፕሮቱኑ ለምሳሌ ለደም ግፊት አሁን ሥራ ላይ እየዋለ ካሉ መድኃኒቶች ዉስጥ "Angiotensin-converting enzyme (ACE) inhibitors" ከሚባሉት ዉስጥ የዚህ ACE I ግሩፕ አካል የሆነ እና "Prodrug" በመባል የሚታወቀው ''Captopril'' ምንጩ የእባብ መርዝ ነው፥ ታዲያ የእባብ መርዝ "ለደም ግፊት መድኃኒት ነው" ስለተባለ ያለ ጥናት እና ያለ ጥበብ እስቲ ምክረውና ምን እንደሚፈጠር መገመት አያዳግትም። በተመሳሳይም የጥቁር አዝሙር መድኃኒትነትን የሰው ልጅ ሙሉ ለሙሉ አልደረሰበት ማለት ለሁሉ ነገር መድኃኒት አይደለም ማለት አይደለም፥ የእባብ መርዝ አጠቃቀሙ የተነገረበት "ሢያቅ" سِيَاق ማለትም "ዐውድ"context" እንደሚወስነው ሁሉ የጥቁር አዝሙድ አጠቃቀም ዐውዱ ይወስነዋል። ለአንድ በሽታ መድኃኒት ለማግኘት አምላካችን አሏህ ዕውቀቱን እና ጥበቡ እንዲያገኙ ሲፈቅድ ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 39, ሐዲስ 95
ጃቢር እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ለሁሉም በሽታ መድኃኒት አለው፥ መድኃኒቱ በሽታውን ካገኘው በአሏህ አዘ ወጀል ፈቃድ ይፈውሳል"*። عَنْ جَابِرٍ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ "‏ لِكُلِّ دَاءٍ دَوَاءٌ فَإِذَا أُصِيبَ دَوَاءُ الدَّاءِ بَرَأَ بِإِذْنِ اللَّهِ عَزَّ وَجَلَّ

የጥቁር አዝሙር መድኃኒትነትን ከላይ በተዘረዘረው የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ ሙግት መረዳት በቀላሉ ይቻላል። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን! አሚን።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም
ነቢይነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

3፥79 *ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠው* እና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፡፡ مَا كَانَ لِبَشَرٍ أَن يُؤْتِيَهُ اللَّهُ الْكِتَابَ وَالْحُكْمَ وَالنُّبُوَّةَ ثُمَّ يَقُولَ لِلنَّاسِ كُونُوا عِبَادًا لِّي مِن دُونِ اللَّهِ

“ነቢይ” نَبِيّ የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “የሩቅ ወሬ አውሪ” ማለት ነው፥ አላህ የሚሰጠው "ነቢይነት" ደግሞ "ኑቡዋህ" نُبُوَّة ይባላል፦
3፥79 *ለማንም ሰው አላህ መጽሐፍንና ጥበብን ነቢይነትንም ሊሰጠው* እና ከዚያም ለሰዎች «ከአላህ ሌላ ለእኔ ባሮች ኾኑ» ሊል አይገባውም፡፡

ሙሉውን ያንብቡ
https://tiriyachen.org/ነቢይነት/
የነብያችን ጉብኝት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

መግቢያ
ብዙ ጊዜ ከሓዲዎች በጥላቻ የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህ ግን ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አፈልግም፤ ከዚያም ባሻገር ነብያችንን”ﷺ” በቅን መንገድ እና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርጋቸው ዘንድ የላከቸው ነው፦
9፥32-33 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፤ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም يُرِيدُونَ أَن يُطْفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفْوَٰهِهِمْ وَيَأْبَى ٱللَّهُ إِلَّآ أَن يُتِمَّ نُورَهُۥ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَٰفِرُونَ ፡፡
እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُونَ ፡፡

ነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶቻቸውን በመዞር በአንድ ሌሊት ይጎበኙ ነበር፤ ይህንን ጉብኝት ከሓዲያን በመገልበጥ መሳለቂያ አድርገው ብዙ ጊዜ እንደ በቀቀን ሲደጋግሙት ይደመጣል፤ ይህንን ገላባ ጥያቄ እስቲ እንመልከት፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 5 , ሐዲስ 36:
አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዓ.” እንደተረከው፦ የአላህ ነብይ”ﷺ” በአንድ ሌሊት ሚስቶቻቸውን “ይዞሩ” ነበር፤ ለእርሳቸው በዚያን ጊዜ ዘጠኝ ሚስቶች ነበሩ أَنَّ أَنَسَ بْنَ مَالِكٍ، حَدَّثَهُمْ أَنَّ نَبِيَّ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم كَانَ يَطُوفُ عَلَى نِسَائِهِ فِي اللَّيْلَةِ الْوَاحِدَةِ، وَلَهُ يَوْمَئِذٍ تِسْعُ نِسْوَةٍ‏.‏ ።

ይህ ዘገባ በኢማም ቡኻሪይ ውስጥ በተመሳሳይ አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዓ.” የተረከበት ብዙ ቦታ ሰፍሯል፤ ይህንን ዘገባ ጥልል እና ጥንፍፍ ባለ መልኩ እንየው፦

ነጥብ አንድ
“ጉብኝት”
አነሥ ኢብኑ ማሊክ”ረ.ዓ.” የተረከው፦ የአላህ ነብይ”ﷺ” በአንድ ሌሊት ሚስቶቻቸውን “ይዞሩ” ነበር” ብሎ ነው፤ “ይዞሩ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “የጡፉ” يَطُوفُ ሲሆን “ጣፈ” طَافَ ማለትም “ዞረ” ከሚለው ኢሽቲቃቀል ከቢር ወይንም “ጠዋፍ” طَواف ማለትም “ዙረት” ከሚለው ኢሽቲቃቅ አሰጊር የመጣ ነው፤ በምን ቀመርና ስሌት ነው “ዙረት” ሲተረጎም “ተራክቦ” የሚሆነው? አላህ በሐጅ ጊዜ ቤቴንም “ለሚዞሩት”፣ ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ”፣ በጥንታዊው ቤት “ይዙሩ” ብሎ የለ እንዴ? ያ ማለት ተራክቦ ያድርጉ ማለት ነው እንዴ? ይህ የሌለ ፉርሽ ኢሥነ-አመክንዮ ነው፦
2:125 ቤቱንም ለሰዎች መመለሻ እና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ አስታውስ፡፡ ከኢብራሂምም መቆሚያ መስገጃን አድርጉ፡፡ ወደ ኢብራሂምና ወደ ኢስማዒልም ቤቴን “ለዘዋሪዎቹ” እና ለተቀማጮቹም ለአጎንባሾች ሰጋጆቹም አጥሩ ስንል ቃል ኪዳን ያዝን وَإِذْ جَعَلْنَا ٱلْبَيْتَ مَثَابَةًۭ لِّلنَّاسِ وَأَمْنًۭا وَٱتَّخِذُوا۟ مِن مَّقَامِ إِبْرَٰهِـۧمَ مُصَلًّۭى ۖ وَعَهِدْنَآ إِلَىٰٓ إِبْرَٰهِـۧمَ وَإِسْمَٰعِيلَ أَن طَهِّرَا بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْعَٰكِفِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ ፡፡
22:26 ለኢብራሂምም የቤቱን ስፍራ መመለሻ ባደረግንለት ጊዜ፣ በኔ ምንንም አታጋራ፤ ቤቴንም “ለሚዞሩት” እና ለሚቆሙበት፣ ለሚያጎነብሱትና በግንባራቸውም ለሚደፉት ንጹሕ አድርግላቸው ባልነው ጊዜ አስታውስ وَإِذْ بَوَّأْنَا لِإِبْرَٰهِيمَ مَكَانَ ٱلْبَيْتِ أَن لَّا تُشْرِكْ بِى شَيْـًۭٔا وَطَهِّرْ بَيْتِىَ لِلطَّآئِفِينَ وَٱلْقَآئِمِينَ وَٱلرُّكَّعِ ٱلسُّجُودِ ።
22:29 ከዚያም ትርፍ አካላችቸንን እና ዕድፋቸውን ያስወግዱ፤ ስለቶቻቸውንም ይምሉ፤ በጥንታዊው ቤት “ይዙሩ” ثُمَّ لْيَقْضُوا۟ تَفَثَهُمْ وَلْيُوفُوا۟ نُذُورَهُمْ وَلْيَطَّوَّفُوا۟ بِٱلْبَيْتِ ٱلْعَتِيقِ ።

ስለዚህ ነብያችን”ﷺ” ይዞሩ የነበሩት ጉብኝት እንጂ ተራክቦ የሚል አልሰፈረም፤ ይጎበኙ ነበር ማለት ተራክቦ ነው ቢባልስ ችግሩ ምንድን ነው? አላህ የሰጣቸው ችሎታና ፀጋ ቢሆንስ? በክርስትናው አስተምህሮት ተራክቦ የኃጢአት ውጤት ነው ተብሎ የሚታመነው ኢስላም ጋር አይሰራም።
ምክንያቱም ተራክቦ ሰው የሚረካበትና አይኑን በአይኑ የሚያይበት የአብራኩ ክፋይ ነው፤ ለማንኛውም የሚቀጥለው ነጥብ “ይዞሩ” ነበር ሲባል ምን ማለት እንደሆነ ዓኢሻ”ረ.ዓ.” ትነግረናለች፦

ነጥብ ሁሉት
“መነካካት”
በቁርአን አገላለፅ “መነካካት” የሚለው በግልፅና በማያሻማ ተራክቦን ነው፤ ይህንን በቀላሉ ለመረዳት መርየም ለመላኩ የመለሰችው መልስ እና አላህ ስለ ሴቶች የተናገረውን ማየት ይቻላል፦
3፥46 ፡-ጌታዬ ሆይ! “ሰው ያልነካኝ ስኾን ለእኔ እንዴት ልጅ” ይኖረኛል?” አለች قَالَتْ رَبِّ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى وَلَدٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ ۖ ፡፡
19፥20 « ሰው “ያልነካኝ” ሆኜ አመንዝራም ሳልሆን ለእኔ እንዴት ልጅ ይኖረኛል?» አለች قَالَتْ أَنَّىٰ يَكُونُ لِى غُلَٰمٌۭ وَلَمْ يَمْسَسْنِى بَشَرٌۭ وَلَمْ أَكُ بَغِيًّۭا ፡፡
2፥236 ሴቶችን “ሳትነኳቸው” ወይም ለእነሱ መህርን ሳትወስኑላቸው ብትፈቷቸው በእናንተ ላይ ኃጢኣት የለባችሁም لَّا جُنَاحَ عَلَيْكُمْ إِن طَلَّقْتُمُ ٱلنِّسَآءَ مَا لَمْ تَمَسُّوهُنَّ أَوْ تَفْرِضُوا۟ لَهُنَّ فَرِيضَةًۭ ۚ ፡፡

“ሰው ያልነካኝ” እና “ሳትነኳቸው” የሚለው ቃል “ተራክቦን” ካመለከተ ይህንን ነጥብ ይዘን ዓኢሻ”ረ.ዓ.” እንደነገረችን እያንዳንዳቸው የነብያችን”ﷺ” ባልተቤቶቻቸው የየራሳቸው ቀናት እንዳላቸውና ግን በቀን ውስጥ ሁሉንም ሴቶች “ያለ ንክኪ” ማለትም ያለ ተራክቦ “ይዞሩ” እንደነበር ነው፦
ሱነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 12 , ሐዲስ 90:
ዓኢሻ”ረ.ዓ.” አለች፦ የእህቴ ልጅ ሆይ የአላህ መልእክተኛ”ﷺ” እኛ ጋር በሚቆይበት ጊዜ አንደኛችን ከሌላኛችን ጋር አያበላልጡም ነበር፤ ትንሽ ወቅት ሁላችንም ጋር “ይዞሩ” يَطُوفُ ነበር፤ ቀኑዋ የደረሰበት ሴት እስከሚደርስ እና እስከሚያድር ድረስ ሁላችንም ሴቶች ጋር “ያለ ንኪክይ” غَيْرِ مَسِيسٍ ይቀርቡን ነበር قَالَتْ عَائِشَةُ يَا ابْنَ أُخْتِي كَانَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم لاَ يُفَضِّلُ بَعْضَنَا عَلَى بَعْضٍ فِي الْقَسْمِ مِنْ مُكْثِهِ عِنْدَنَا وَكَانَ قَلَّ يَوْمٌ إِلاَّ وَهُوَ يَطُوفُ عَلَيْنَا جَمِيعًا فَيَدْنُو مِنْ كُلِّ امْرَأَةٍ مِنْ غَيْرِ مَسِيسٍ حَتَّى يَبْلُغَ إِلَى الَّتِي هُوَ يَوْمُهَا فَيَبِيتُ” ።
ምን ትፈልጋለህ? አንዱን አጠማለው ብትል በአንዱ ትያዛለህ፤ ሚሽነሪዎች የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ቢፈልጉም አላህ ብርሃኑን ገላጭ ነው፦
61፥8-9 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፤ አላህም ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን ገላጭ ነው يُرِيدُونَ لِيُطْفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفْوَٰهِهِمْ وَٱللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْكَٰفِرُونَ ፡፡
እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን በመምሪያ በእውነተኛው ሃይማኖትም ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ሊያደርገው የላከ ነው هُوَ ٱلَّذِىٓ أَرْسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلْهُدَىٰ وَدِينِ ٱلْحَقِّ لِيُظْهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّينِ كُلِّهِۦ وَلَوْ كَرِهَ ٱلْمُشْرِكُونَ ፡፡

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
የአላህ ባህርይ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 53, ሐዲስ 32
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ አላህ አዝዘ ወጀል አደምን ስልሳ ኩብ ቁመት አድርጎ በራሱ "መልክ" ፈጠረው። خَلَقَ اللَّهُ عَزَّ وَجَلَّ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا.
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 79, ሐዲስ 1
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ አላህ አደምን ስልሳ ኩብ ቁመት አድርጎ በራሱ "መልክ" ፈጠረው። خَلَقَ اللَّهُ آدَمَ عَلَى صُورَتِهِ، طُولُهُ سِتُّونَ ذِرَاعًا،

የቋንቋው ሊሂቃን "ሱራ" صورة ማለት "መልክ" image" ብለው ያስቀመጡት ሲሆን ይህም "መልክ" ባህርይ ለማመልከት እንደሚመጣ ይናገራሉ፦
ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 60 ሐዲስ 2
አቢ ሁረይራህ"ረ.አ." እንደተረከው የአላህ መልእክተኛ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ የመጀመሪያው ግሩፕ በሌሊት ሙሉ እንደሆነች በጨረቃ "#መልክ" صُورَةِ ሆኖ ወደ ጀነት ይገባሉ። إِنَّ أَوَّلَ زُمْرَةٍ يَدْخُلُونَ الْجَنَّةَ عَلَى صُورَةِ الْقَمَرِ لَيْلَةَ الْبَدْرِ،

በዚህ ሐዲስ ላይ መቼም የጨረቃ መልክ የጨረቃን ቅርፅና ክብደት ለማመልከት ነው ከተባለ የጨረቃ ቅርጷ 1958×1010 km3 እንዲሁ ክብደቷ 7.342×1022 kg ነው፤ ያ ማለት ሰው ጀነት የሚገባው በጨረቃ ቅርፅና ክብደት ነው ማለት ሳይሆን የጨረቃ ባህርይ የሆኑን ንፅህናዋን፣ ድምቀቷ እና ውበቷን ማለቱ ነው፤ እንግዲህ "ሱራ" صورة "መልክ" የአንድን ህላዌ ባህርይ ለማመልከት ከመጣ ይህም "መልክ" ማየት፣ መስማት፣ ማወቅ የሚባሉትን ባህርያት ያቅፋል፤ አላህ ሁሉን ነገር ተመልካች፣ ሁሉን ነገር ሰሚ እና ሁሉን ነገር አዋቂ ነው፤ አላህ አደምን ሲፈጥረው በባህርያቱ የሚያይበት አይን፣ የሚሰማበት ጆሮ እና የሚያውቅበት ልብ"አንጎል" ሰቶታል ማለት ነው፦
67:23 እርሱ ያ የፈጠራችሁ ለእናንተም "#መስሚያ" እና "#ማያዎችን" "#ልቦችንም" ያደረገላችሁ ነው፤ ጥቂትንም አታመሰግኑም በላቸው።
23፥78 እርሱም ያ "#መስሚያዎችንና" "#ማያዎችን" "#ልቦችንም" ለእናንተ የፈጠረላችሁ ነው፤ ጥቂትን እንጅ አታመሰግኑም፡፡

አላህ "የሚመስለው ምንም ነገር የለም" አላህ ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው፦
42:11"የሚመስለው" ምንም ነገር የለም፤ እርሱም "ሰሚው" "ተመልካቹ" ነው።

አላህ ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው እንደተባለ ሁሉ ሰውም ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው ተብሏል፦
76:2 እኛ ሰዉን፥ በሕግ ግዳጅ የምንሞክረዉ ስንሆን፥ ቅልቅሎች ከሆኑ የፍትወት ጠብታ ፈጠርነዉ፤ "ሰሚ" "ተመልካችም" አደረግነዉ።

ነገር ግን አላህ ሰሚ" እና "ተመልካች" ነው የተባለው ሰው ሰሚ" እና "ተመልካች" በተባለበት ሂሳብ አይደለም፤ ምክንያቱም አላህ ሁሉን ነገር ይሰማል ያያል፤ ይህ ባህርይ ጊዜና ቦታ አይገድበውም፤ ሰው ግን ያለ ብርሃን ማየት እና ያለ ድምፅ መስማት አይችልም፤ በተመሳሳይ አላህ ሁሉን አዋቂን ነው እውቀቱ በጊዜና በቦታ አይገደብም፤ ሰው ግን እውቀቱ ጊዜ እና ቦታ ይገድበዋል፦
58:6 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ አዋቂ ነው።
67:19 እርሱ በነገር ሁሉ ተመልካች ነው።
4:86 አላህ በነገሩ ሁሉ ላይ ተቆጣጣሪ ነውና።
39:62 እርሱም በነገሩ ሁሉ ላይ አስተናባሪ ነው።
33:27 አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው።

የሰው መስሚያ፣ ማያም፣ ልብም ከአላህ የሆኑ ፀጋ ሲሆኑ ከእንስሳ በተለየ መልኩ ይሰሩት በነበሩት ሁሉ ተጠያቂ ናቸው፦
17:36 ለአንተም በእርሱ ዕውቀት የሌለህን ነገር አትከተል፤ #መስሚያ#ማያም#ልብም፣ እነዚህ ሁሉ ባለቤታቸው ከእነርሱ #ተጠያቂ ነውና إِنَّ السَّمْعَ وَالْبَصَرَ وَالْفُؤَادَ كُلُّ أُولَٰئِكَ كَانَ عَنْهُ مَسْئُولًا ።
102:8 ከዚያም #ከጸጋዎቻችሁ النَّعِيمِ ሁሉ በዚያ ቀን #ትጠየቃላችሁ ثُمَّ لَتُسْأَلُنَّ يَوْمَئِذٍ عَنِ النَّعِيمِ ።
16:93 ትሠሩት ከነበራችሁትም ሁሉ በእርግጥ #ትጠየቃላችሁ" وَلَتُسْأَلُنَّ عَمَّا كُنْتُمْ تَعْمَلُونَ ።

የአላህ ዛት የራሱ ሲፋ አለው ማየት፣ መስማት፣ መናገር፣ ማወቅ እና እጅ ግን ከፍጡራን ማየት፣ መስማት፣ ማወቅ፣ መናገር እና እጅ ጋር አይመሳሰልም። ለምሳሌ የሰው እጅ ቀኝና ግራ ነው የአላህ እጆች ግን ቀኝ ናቸው፦
ኢማም ሙስሊም 33, ሐዲስ 21 ፍትኸኞች አላህ ዘንድ በብርሃን መንበሮች ላይ ከአር-ረህማን በስ-ተቀኝ በኩል ይሆናሉ፤ ሁለቱም እጆቹ #ቀኝ ናቸው። " ﺇِﻥَّ ﺍﻟْﻤُﻘْﺴِﻄِﻴﻦَ ﻋِﻨْﺪَ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻋَﻠَﻰ ﻣَﻨَﺎﺑِﺮَ ﻣِﻦْ ﻧُﻮﺭٍ ﻋَﻦْ ﻳَﻤِﻴﻦِ ﺍﻟﺮَّﺣْﻤَﻦِ ﻋَﺰَّ ﻭَﺟَﻞَّ ﻭَﻛِﻠْﺘَﺎ ﻳَﺪَﻳْﻪِ ﻳَﻤِﻴﻦٌ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﻌْﺪِﻟُﻮﻥَ ﻓِﻲ ﺣُﻜْﻤِﻬِﻢْ ﻭَﺃَﻫْﻠِﻴﻬِﻢْ ﻭَﻣَﺎ ﻭَﻟُﻮﺍ "

አላህ በራሱ ባህርይ ፈጠረው ማለት ለምሳሌ አላህ አደምን በእጁ ፈጥሮታል፦
38፥75 አላህም «ኢብሊስ ሆይ! *"በሁለት እጆቼ"* "ለፈጠርኩት" ከመስገድ ምን ከለከለህ? አሁን ኮራህን? ወይስ ከትዕቢተኞቹ ነበርክ?» አለው፡፡ قَالَ يَٰٓإِبْلِيسُ مَا مَنَعَكَ أَن تَسْجُدَ لِمَا خَلَقْتُ بِيَدَىَّ ۖ أَسْتَكْبَرْتَ أَمْ كُنتَ مِنَ ٱلْعَالِينَ
36፥71 እኛ *"እጆቻችን ከሠሩት"* ለእነርሱ እንስሳዎችን መፍጠራችንን አያውቁምን? እነርሱም ለእርሷ ባለ መብቶች ናቸው፡፡ أَوَلَمْ يَرَوْا۟ أَنَّا خَلَقْنَا لَهُم مِّمَّا عَمِلَتْ أَيْدِينَآ أَنْعَٰمًۭا فَهُمْ لَهَا مَٰلِكُونَ

እጅ የአላህ ባህርይ ነው፤ ኹን የሚለው ንግግሩ የራሱ ባህርይ ነው፤ በባህርይው አደምን ፈጥሮታል።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
ወሰላሙ አለይኩም
አሥራ ሁለቱ ነገዶች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

ሙሳም ለሕዝቦቹ ባለ ጊዜ አስታውስ፦«ሕዝቦቼ ሆይ የአላህን ጸጋ *በውስጣችሁ ነቢያትን ባደረገ* እና መንግሥትም ባደረጋችሁ ከዓለማትም ለአንድም ያልሰጠውን ችሮታ በሰጣችሁ ጊዜ በእናንተ ላይ ያደረገውን ጸጋ አስታውሱ፡፡»

وَإِذْ قَالَ مُوسَىٰ لِقَوْمِهِ يَا قَوْمِ اذْكُرُوا نِعْمَةَ اللَّهِ عَلَيْكُمْ إِذْ جَعَلَ فِيكُمْ أَنبِيَاءَ وَجَعَلَكُم مُّلُوكًا وَآتَاكُم مَّا لَمْ يُؤْتِ أَحَدًا مِّنَ الْعَالَمِينَ
ቁርኣን 5፥20

“ነቢይ” نبي የሚለው ቃል “ነበአ” نَبَّأَ ማለትም “አወራ” ወይም “ተናገረ” ከሚል ሥርወ-ቃል የተገኘ ሲሆን “አውሪ” ወይም “ነጋሪ” ማለት ነው፤ ይህንን እስቲ ከቁርአን እንመልከት፦ ..............

ማስፈንጠሪያውን ይንኩ እና ሙሉውን ያንብቡ

https://tiriyachen.org/አሥራ-ሁለቱ-ነገዶች/
ስድብ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

49፥11 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች አይሳለቁ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ እራሳችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰ أَن يَكُونُوا خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَاءٌ مِّن نِّسَاءٍ عَسَىٰ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّ ۖ وَلَا تَلْمِزُوا أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ ۖ بِئْسَ الِاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الْإِيمَانِ ۚ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

“በደል” ሦስት አይነት ነው፥ እርሱም፦ አላህን መበደል፣ እራስን መበደል እና ሰውን መበደል ነው። አላህን መበደል ሺርክ ሲሆን በዱንያ ያለ ተውበት የማይማር በአኺራ ግን የማይማረው በደል ነው፣ እራስን መበደል ቅጣት ተቀብሎ አላህ የሚምረው በደል ነው፣ ሰውን መበደል አላህ በፍጹም የማይተወው በደል ነው፦
ሶሒሑል ጃሚዕ 3961
አነሥ ኢብኑ ማሊክ"ረ.ዐ" እንዳስተላለፈው፦ "የአላህ መልክተኛም"ﷺ" እንዲህ አሉ፡- *"በደል ሦስት አይነት ነው፥ እርሱም፦ አላህ የማይምረው በደል፣ የሚምረው በደል እና የማይተወው በደል ነው። አላህ የማይምረው በደል የሆነው ሺርክ ነው፥ አላህም በቁርኣኑ፡- "ማጋራት ታላቅ በደል ነውና" ብሏል፡፡ የሚምረው በደል ደግሞ ሰዎች የአላህን ሕግጋት በመጣስ ኃጢአት ላይ ወድቀው ራሳቸውን የበደሉበት ነው፡፡ አላህ በፍጹም የማይተወው በደል ደግሞ ሰዎች ሌላውን ሰው መበደላቸውን ነው። አላህ በመሐከላቸው ትክክለኛውን ፍርድ እስኪፈርድ በሰው ሐቅ አይተዋቸውም"*። عَنْ أَنَسِ بْنِ مَالِكٍ رَضِيَ الله عَنْهُ، قَالَ: قَالَ رَسُولُ اللهِ صَلَّى الله عَلَيْهِ وَسَلَّمَ: «الظُّلْمُ ثَلاثَةٌ، فَظُلْمٌ لا يَغْفِرُهُ الله، وَظُلْمٌ يَغْفِرُهُ، وَظُلْمٌ لا يَتْرُكُهُ. فَأَمَّا الظُّلْمُ الَّذِي لا يَغْفِرُهُ الله فَالشِّرْكُ، قَالَ الله: إنَّ الشِّرْكَ لَظُلْمٌ عَظِيمٌ، وَأَمَّا الظُّلْمُ الَّذِي يَغْفِرُهُ فَظُلْمُ العِباَدِ أَنْفُسَهُمْ فِيمَا بَيْنَهُمْ وَبَيْنَ رَبِّهِمْ، وَأَمَّا الظُّلْمُ الَّذِي لا يَتْرُكُهُ الله فَظُلْمُ الْعِبَادِ بَعْضِهِمْ بَعْضًا حَتَّى يُدَبِّرُ لِبَعْضِهِمْ مِنْ بَعْضٍ

ሰውን መበደል ማንኛውም ሰው ሌላው ላይ የሚያደርሰው በደል ነው። ሰውን መበደል ማለት የሰው ሐቅ መንካት ነው፥ የሰው ሐቅ ተነክቶ የሚመለሰው በካሳ ወይም በይቅርታ ብቻ ነው። “ከፋራህ” كَفّارَة ማለት “ካሳ” መክፈል ማለት ሲሆን “ዐፉው” عَفُوّ ማለት ደግሞ “ይቅርታ” ማለት ነው። የበደልነውን ሰው በካሳ ወይም በይቅርታ ሐቁን ካልመለስን የትንሳኤ ቀን በአላህ ዘንድ ያስጠይቀናል። ሰውን መዝረፍ፣ ማማት፣ መስደብ፣ መማታት፣ መግደል ሰውን መበደል ነው። ዛሬ የምናየው ነጥብ ስለ ስድብ ነው፥ አምላካችን አላህ፦ "እራሳችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው" ይለናል፦
49፥11 *"እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ወንዶች ከወንዶች አይቀልዱ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ ሴቶችም ከሴቶች አይሳለቁ፡፡ ከእነርሱ የበለጡ ሊኾኑ ይከጀላልና፡፡ እራሳችሁንም አታነውሩ፡፡ በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ፡፡ ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ከፋ፡፡ ያልተጸጸተም ሰው እነዚያ እነርሱ በዳዮቹ ናቸው"*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا يَسْخَرْ قَوْمٌ مِّن قَوْمٍ عَسَىٰ أَن يَكُونُوا خَيْرًا مِّنْهُمْ وَلَا نِسَاءٌ مِّن نِّسَاءٍ عَسَىٰ أَن يَكُنَّ خَيْرًا مِّنْهُنَّ ۖ وَلَا تَلْمِزُوا أَنفُسَكُمْ وَلَا تَنَابَزُوا بِالْأَلْقَابِ ۖ بِئْسَ الِاسْمُ الْفُسُوقُ بَعْدَ الْإِيمَانِ ۚ وَمَن لَّمْ يَتُبْ فَأُولَـٰئِكَ هُمُ الظَّالِمُونَ

"ቀውም" قَوْم ማለት "ሕዝብ" ማለት ነው፥ አንደኛው ሕዝብ በሌላ ሕዝብ ላይ መቀለድ ሐራም ነው። ለምሳሌ የኦሮሞ ሕዝብ በአማራ ሕዝብ፥ የአማራ ሕዝብ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ማለት ነው። አንደኛዋ ሴት በሌላ ሴት ላይ መሳለቅ ሐራም ነው። ቀልድና ስላቅ የስድብ አይነቶች ናቸው። ቀልድ እና ፈገግ የሚያደርጉ ጭውውት በራሱ ችግር የለውም፥ ቅሉ ግን የሰው ሞራል፣ ስሜት እና ስብዕና ሊጎዳ የሚችል ቀልድ እና ስላቅ ክልክል ነው። "እራሳችሁን አታነውሩ" ማለት "እርስ በእርሳችሁ አትዘላለፉ" ማለት ነው፥ ትልቁ ነውር ስድብ ነው። በስድብ ሰው ማነወር ሐራም ነው፥ ማበሻቀጥ ሆነ ማብጠልጠል አሊያም መዝለፍና መዘርጠጥ የስድብ አይነት ነው። "አታነውሩ" ለሚለው ቃል የገባው "ላ ተልሚዙ" لَا تَلْمِزُو ሲሆን "አትዝለፉ" ማለት ነው፥ "ሉመዛህ" لُّمَزَة ማለት በራሱ "ዘላፊ" "ተሳዳቢ" "አነዋሪ" "ዘርጣጭ" ማለት ነው፦
104፥1 *"ለሃሜተኛ ለዘላፊ ሁሉ ወዮለት"*፡፡ وَيْلٌ لِّكُلِّ هُمَزَةٍ لُّمَزَةٍ
68፥11 *"ሰውን አነዋሪን እና በማሳበቅ ኼያጅን አትታዘዝ"*፡፡ هَمَّازٍ مَّشَّاءٍ بِنَمِيمٍ

"አልቃብ" أَلْقَٰب ማለት "እኩይ ስም" ማለት ነው፥ በዚህ የመበሻሸቂያ ስም መጠራራት ከእምነት በኋላ የማመጽ ስም ነው፡፡ "በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ" የሚለው አንቀጽ የወረደበት ምክንያት ይህ ነው፦
ጃምዒ አት-ቲርሚዚይ መጽሐፍ 47, ሐዲስ 3578
አቢ ጀቢራህ ኢብኑ አድ-ደሓክ እንደተረከው፦ *"አንድ ሰው ከመካከላችን በሁለት ወይም በሦስት ስም ይታወቃል፥ እርሱም ከሚጠላው በአንዱ ስም ተጠራ። ከዚያም፦ "በመጥፎ ስሞችም አትጠራሩ" የሚለው አንቀጽ ወረደ"*። يُحَدِّثُ عَنْ أَبِي جَبِيرَةَ بْنِ الضَّحَّاكِ، قَالَ كَانَ الرَّجُلُ مِنَّا يَكُونُ لَهُ الاِسْمَيْنِ وَالثَّلاَثَةَ فَيُدْعَى بِبَعْضِهَا فَعَسَى أَنْ يَكْرَهَ قَالَ فَنَزَلَتْ هَذِهِ الآيَةُ ‏(‏ وَلاَ تَنَابَزُوا بِالأَلْقَابِ ‏)‏ ‏.‏
"መጥፎ ስም" ማለት ሰውዬው ቢጠራበት ደስ የማይለው እና ስሜቱ የሚጎዳበት ስም ነው። በእኩይ ስም ሰውን የሚጠራ እና በዚህ ድርጊቱ ያልተጸጸተም ሰው በደለኛ ነው። ይህ ሥራው ዓመፅ ነው፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 2, ሐዲስ 41
ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ *"ሙሥሊምን መሳደብ ፉሡቅ ነው፥ መግደል ደግሞ ኩ*ፍ*ር ነው"*። فَقَالَ حَدَّثَنِي عَبْدُ اللَّهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ "‏ سِبَابُ الْمُسْلِمِ فُسُوقٌ، وَقِتَالُهُ كُفْرٌ

"ፉሡቅ" فُسُوق ወይም ፊሥቅ" فِسْق የሚለው ቃል "ፈሠቀ" فَسَقَ ማለትም "ዓመፀ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ዓመፅ" ማለት ነው። አምላካችን አላህ በቁርኣኑ "እራሳችሁን አታነውሩ" ሲለን፥ ነቢያችን"ﷺ" ደግሞ "ሙሥሊምን መሳደብ ፉሡቅ ነው" ብለውናል። እርስ በእርስ መዘላለፍ ከተጀመረ ቀጣዩ ደረጃ እርስ በእርስ መገዳደል ነው፦
4፥29 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ገንዘቦቻችሁን በመካከላችሁ ያለ አግባብ አትብሉ፡፡ ግን ከእናንተ በመዋደድ የኾነችውን ንግድ ብሉ፡፡ *”እራሳችሁንም አትግደሉ”*፡፡ አላህ ለእናንተ አዛኝ ነውና፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا لَا تَأْكُلُوا أَمْوَالَكُم بَيْنَكُم بِالْبَاطِلِ إِلَّا أَن تَكُونَ تِجَارَةً عَن تَرَاضٍ مِّنكُمْ ۚ وَلَا تَقْتُلُوا أَنفُسَكُمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ كَانَ بِكُمْ رَحِيمًا

"እራሳችሁንም አትግደሉ" ማለት "እርስ በእርሳችሁ አትገዳደሉ" ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከዓመፅ ወደ ክህደት ያመራል፥ ለዛ ነው ነቢያችን"ﷺ" "ሙሥሊምን መግደል ደግሞ ኩ*ፍ*ር ነው" ያሉት። በግል ደረጃ እንኳን እራስን ለመግደል መንስኤው እራስን ማነወር ነው። ሰው ራሱ ስለ ራሱ ጥሩ ካልተሰማው እራሱን ዝቅ አድርጎ ማነወር ይጀምራል፥ ይህ ሂደት ስር ሲሰድ እራስን ወደ መግደል እርምጃና ደረጃ ይደርሳል። ወደተነሳንበት ነጥብ ስንመለስ ስድብ ፈሳዱ ይህን ያክል አደገኛ ነው ማለት ነው፥ የራሳችን እምነት እንዳይሰደብ ከፈለግን የሌላውን እምነት መሳደብ የለብንም፦
6፥108 *"እነዚያንም ከአላህ ሌላ የሚገዙዋቸውን አትሳደቡ፡፡ ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሳደባሉና"*፡፡ وَلَا تَسُبُّوا الَّذِينَ يَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ فَيَسُبُّوا اللَّهَ عَدْوًا بِغَيْرِ عِلْمٍ

ጣዖታውያን ከአላህ ሌላ የሚጠሯቸውን ማንነት ሆነ ምንነት ከዘለፍን እነርሱም ድንበርን በማለፍ ያለዕውቀት አላህን ይሳደባሉና። የሌላውን እምነት መዝለፍ እራሱ የሌላ ሰው ሐቅ መንካት ስለሆነ በደል ነው። ስድብ አሳብን በተሻለ አሳብ ማሸነፍ ሲያቅተን የምንጠቀምበት ዱላ ነው። ይህ ጽርፈት ሥር ከሰደደ የመግደል ስሜት ይፈጥራል። አላህ ከጽርፈት ይጠብቀን፥ ለሁላችንም ሂዳያህ ይስጠን! አሚን።

✍️ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen
https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
ፍትሐዊነት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

"ዐድል" عَدْل የሚለው ቃል "ዐደለ" عَدَلَ ማለትም "አስተካከለ" ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ማስተካከል" "ፍርድ" "ፍትሕ" ማለት ነው፥ "ዐዲል" عَادِل‎ ማለት "ፍትሓዊ" ማለት ሲሆን "ተዕዲል" تَعْدِيل‎ ማለት ደግሞ "ፍትሐዊነት" ማለት ነው። አምላካችን አላህ በፍትሕ ያዛል፥ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፦
16፥90 *አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ እና ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል*፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُ بِالْعَدْلِ وَالْإِحْسَانِ وَإِيتَاءِ ذِي الْقُرْبَىٰ وَيَنْهَىٰ عَنِ الْفَحْشَاءِ وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ ۚ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ “ማስተካከል” ለሚለው ቃል የገባው “ዐድል” عَدْل መሆኑን አንባቢ ልብ ይለዋል። የፍትሕ ተቃራኒ ዙልም ነው፥ “ዙልም” ظُلْم የሚለው ቃል “ዞለመ” ظَلَمَ ማለትም “በደለ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “በደል” ማለት ነው። "ከሚጠላ ነገር ሁሉ" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። አላህ ዘንድ የሚጠላ ነገር ሺርክ፣ ኩፍር፣ ዘረኝነት፣ ጎጠኝነት፣ ብሔርተኝነት፣ ዘውገኝነት ነው። ይህንን እኩይ ነገር ከልባችን መጥላት ፍትሓዊነት ነው፦
ሪያዱ አስ-ሳሊሒን መጽሐፍ 1, ሐዲስ 184
አቢ ሠዒድ አል-ኹድሪይ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "የአላህ መልክተኛ"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻቸዋለሁ፦ *“ከእናንተ ውስጥ እኩይ ነገር ያየ በእጁ ይቀይረው፣ ካልቻለ በምላሱ ያውግዝ፣ ይህንንም ካልቻለ በልቡ ይጥላው። በልብ መጥላት ደካማው ኢማን ነው”*። عن أبي سعيد الخدري رضي الله عنه قال‏:‏ سمعت رسول الله صلى الله عليه وسلم يقول‏:‏ ‏ "‏من رأى الخد منكرًا فليغيره بيده ، فإن لم يستطع فبلسانه، فإن لم يستطع فبقلبه وذلك أضعف الإيمان

የአንድን ሰው ዘውግ፣ ብሔር፣ ዘር መጥላት በራሱ በደል ነው። ሰውን በቋንቋው፣ በዘሩ፣ በዘውጉ፣ በብሔሩ መጥላት የፍትሕ ተቃራኒ ነው፦
5፥8 *እናንተ ያመናችሁ ሆይ! ለአላህ ቀጥተኞች በትክክል መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሕዝቦችንም መጥላት ባለማስተካከል ላይ አይገፋፋችሁ፡፡ አስተካክሉ፡፡ እርሱ ማስተካከል ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህንም ፍሩ፡፡ አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ لِلَّهِ شُهَدَاءَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ۚ اعْدِلُوا هُوَ أَقْرَبُ لِلتَّقْوَىٰ ۖ وَاتَّقُوا اللَّهَ ۚ إِنَّ اللَّهَ خَبِيرٌ بِمَا تَعْمَلُونَ

አሁንም "አስተካክሉ" ለሚለው የገባው ቃል “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا መሆኑ ልብ በል። "ሕዝቦችን መጥላት" ወደ ፍትሕ አልባ ይገፋፋል፥ ፍትሕ ግን ለአላህ ፍራቻ በጣም የቀረበ ነው። በፍትሕ የሚጠላ ነገር ሁሉ ለአላህ ብሎ ጠልቶ መከልከል ከመበደል ይታደጋል። ፍትሕ ከራስ፣ ከወላጅ እና ከቅርብ ዘመድ በላይ ለአላህ ተብሎ የሚደረግ፣ ከዝንባሌ የጸዳ፣ ሀብታም ወይም ድኻ ሳይል፣ አላህ ውስጠ ዐዋቂ ነው ብሎ በትክክል መቆም ነው፦
4፥135 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *በትክክል ፍትሕ ቀዋሚዎች በራሳችሁ ወይም በወላጆች እና በቅርብ ዘመዶች ላይ ቢኾንም እንኳ ለአላህ መስካሪዎች ኹኑ፡፡ ሀብታም ወይም ድኻ ቢኾን አላህ በእነርሱ ከእናንተ ይበልጥ ተገቢ ነው፡፡ እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ፡፡ ብታጠምሙም ወይም መመስከርን ብትተው አላህ በምትሠሩት ሁሉ ውስጠ ዐዋቂ ነው*፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا كُونُوا قَوَّامِينَ بِالْقِسْطِ شُهَدَاءَ لِلَّهِ وَلَوْ عَلَىٰ أَنفُسِكُمْ أَوِ الْوَالِدَيْنِ وَالْأَقْرَبِينَ ۚ إِن يَكُنْ غَنِيًّا أَوْ فَقِيرًا فَاللَّهُ أَوْلَىٰ بِهِمَا ۖ فَلَا تَتَّبِعُوا الْهَوَىٰ أَن تَعْدِلُوا ۚ وَإِن تَلْوُوا أَوْ تُعْرِضُوا فَإِنَّ اللَّهَ كَانَ بِمَا تَعْمَلُونَ خَبِيرًا

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ “ተዕዲሉ” تَعْدِلُوا የሚለው ቃል ይሰመርበት። ማዳላት የሚመጣው ዝንባሌን ከመከተል ስለሆነ "እንዳታደሉም ዝንባሌን አትከተሉ" ብሎ ነግሯናል። “አህዋ” أَهْوَآء ማለትም “ዝንባሌ”inclination” ነው፤ አንድ ሙስሊም ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት። ዝንባሌ ደግሞ ከተከተሉት ሊመለክ የሚችል አደገኛ ጣዖት ነው፦
79፥40-41 በጌታው ፊት መቆምን የፈራ ሰውማ *ነፍሱንም ከዝንባሌዋ የከለከለ ገነት እርሷ በእርግጥ መኖሪያው ናት*፡፡ وَأَمَّا مَنْ خَافَ مَقَامَ رَبِّهِ وَنَهَى النَّفْسَ عَنِ الْهَوَىٰ فَإِنَّ الْجَنَّةَ هِيَ الْمَأْوَىٰ
25:43 *ዝንባሌውን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን?* أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

ማደላት ከዝንባሌ የሚመጣ ሲሆን ፍትሐዊነት ግን ለአላህ ተብሎ የሚደረግ የሥነ-ምግባር እሴት ነው። ይህ ፍትሓዊነት ለመላው የሰው ዘር ሁሉ በሰውነትን የምናደርገው ነው፦
60፥8 *ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ፣ ከአገሮቻችሁም ካላወጡዋችሁ ከሓዲዎች መልካም ብትውሉላቸው እና ወደ እነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና*፡፡ لَّا يَنْهَاكُمُ اللَّهُ عَنِ الَّذِينَ لَمْ يُقَاتِلُوكُمْ فِي الدِّينِ وَلَمْ يُخْرِجُوكُم مِّن دِيَارِكُمْ أَن تَبَرُّوهُمْ وَتُقْسِطُوا إِلَيْهِمْ ۚ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ
ዲናችንን አክብረው ካልተጋደሉንና ካላሳደዱን ማናቸውም ሕዝቦች ጋር በዝምድና፣ በባልደረባ፣ በጉርብትና መልካም መዋዋል እና ማስተካከል ይቻላል። “ብታስተካክሉ” ለሚለው ቃል የገባው “ቱቅሢጡ” َتُقْسِطُوا ሲሆን የስም መደቡ “ቂሥጥ” قِسْط ማለትም “ፍትሕ” ነው። ለአላህ ብለን ስናስተካክል “ሙቅሢጢን” مُقْسِطِين ማለትም “ፍትኸኞችን” “ትክክለኞች” “አስተካካዮች” እንባላለን። አላህ ሙቅሢጢንን ይወዳል፦
49፥9 *በነገሩ ሁሉ አስተካክሉም፡፡ አላህ አስተካካዮችን ይወዳልና*፡፡ وَأَقْسِطُوا ۖ إِنَّ اللَّهَ يُحِبُّ الْمُقْسِطِينَ

ለዘሩ፣ ለብሔሩ፣ ለፓለቲካው፣ ለዝንባሌው፣ ለስሜቱ ብሎ መውደድ እና መጥላት ኪሳራ አለው፥ በዱንያም በአኺራም ይጎዳል። ነገር ግን ለአላህ ብሎ መውደድ እና መጥላት ትርፍ አለው፥ በዱንያም በአኺራም ይጠቅማል፦
አቢ ዳውድ መጽሐፍ 42, ሐዲስ 86
አቢ ኡማማህ እንደተረከው፦ “የአላህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ *”ማንኛውም ሰው ለአላህ ብሎ የወደደ እና የጠላ፣ ለአላህ ብሎ የሰጠ እና የነፈገ የተሟላ ኢማን አለው”*። عَنْ أَبِي أُمَامَةَ، عَنْ رَسُولِ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم أَنَّهُ قَالَ ‏ “‏ مَنْ أَحَبَّ لِلَّهِ وَأَبْغَضَ لِلَّهِ وَأَعْطَى لِلَّهِ وَمَنَعَ لِلَّهِ فَقَدِ اسْتَكْمَلَ الإِيمَان

ለእዩልኝና ስሙልኝ ሳይሆን ለአላህ ብሎ መስጠት የተሟላ ኢማን ነው። የምንሰጠው ልግስና ለጥፋት ለምሳሌ ለሲጋራ፣ ለጫት፣ ለመጠጥ እንደሚውል ተረድተን ለአላህ ብሎ መንፈግ የተሟላ ኢማን ነው። ለአላህ ብሎ መውደድ እና መጥላት የተሟላ ኢማን ነው። ይህ አል-ወላእ ወል በራእ ነው። “ወላእ” وَلَاء ማለት “መውደድ” “መቅረብ” “መርዳት” ማለት ሲሆን አላህን፣ መልእክተኛው፣ እንዲሁም ዲነል ኢሥላምን እና ሙሥሊሞችን መወደድ፣ መቅረብ እና መርዳት ነው። “በራእ” بَراء‎ ማለት “መጥላት” “መራቅ” “መተው” ማለት ሲሆን ከአላህ ውጭ የሚመለኩ ጣዖታትን እና የአላህ ጠላቶችን ለአላህ ብሎ መጥላት፣ መራቅ እና መተው ነው። ከዚህ በተረፈ ዝንባሌን ተከትለው ለሰዎች የማያዝኑ አላህ ለእነርሱ አያዝንላቸውም፥ ሰዎችን በዱንያ ያለ ፍትሕ የሚቀጡ አላህ ይቀጣቸዋል፦
ኢማም ቡኻርይ መጽሐፍ 97 ሐዲስ 6
ጀሪር ኢብኑ ዐብደሏህ እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" አሉ፦ *"ለሰዎች የማያዝኑ አላህ ለእነርሱ አያዝንላቸውም"*። ظَبْيَانَ عَنْ جَرِيرِ بْنِ عَبْدِ اللَّهِ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ "‏ لاَ يَرْحَمُ اللَّهُ مَنْ لاَ يَرْحَمُ النَّاسَ
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 45 ሐዲስ 157
ዑርዋህ ኢብኑ ዙበይር እንደተረከው፦ "የአላህ መልእክተኛም"ﷺ" እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው፦ *"እነዚያ ሰዎችን በዱንያ ያለ ፍትሕ የሚቀጡ አላህ ይቀጣቸዋል"*። عَنْ عُرْوَةَ، بْنِ الزُّبَيْرِ فَقَالَ مَا هَذَا إِنِّي سَمِعْتُ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم يَقُولُ ‏ "‏ إِنَّ اللَّهَ يُعَذِّبُ الَّذِينَ يُعَذِّبُونَ النَّاسَ فِي الدُّنْيَا

ለሰዎች ማዘን ማለት በትክክል መመዘን፣ ተመዛኙንም አለማጉደል፣ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው ማድረስ በሰዎችም መካከል በፍትሕ መበየን ነው፦
55፥9 *"መመዘንንም በትክክል መዝኑ፡፡ ተመዛኙንም አታጉድሉ"*፡፡ وَأَقِيمُوا الْوَزْنَ بِالْقِسْطِ وَلَا تُخْسِرُوا الْمِيزَانَ
4፥58 *"አላህ አደራዎችን ወደ ባለቤቶቻቸው እንድታደርሱ ያዛችኋል፡፡ በሰዎችም መካከል በፈረዳችሁ ጊዜ በትክክል እንድትፈርዱ ያዛችኋል"*፡፡ አላህ በርሱ የሚገሥጻችሁ ነገር ምን ያምር! አላህ ሰሚ ተመልካች ነው፡፡ إِنَّ اللَّهَ يَأْمُرُكُمْ أَن تُؤَدُّوا الْأَمَانَاتِ إِلَىٰ أَهْلِهَا وَإِذَا حَكَمْتُم بَيْنَ النَّاسِ أَن تَحْكُمُوا بِالْعَدْلِ ۚ إِنَّ اللَّهَ نِعِمَّا يَعِظُكُم بِهِ ۗ إِنَّ اللَّهَ كَانَ سَمِيعًا بَصِيرًا
11፥85 «ሕዝቦቼም ሆይ! *"ስፍርንና ሚዛንን በትክክል ሙሉ፡፡ ሰዎችንም ምንም ነገራቸውን አታጉድሉባቸው፡፡ በምድርም ውስጥ አጥፊዎች ሆናችሁ አታበላሹ"*፡፡ وَيَا قَوْمِ أَوْفُوا الْمِكْيَالَ وَالْمِيزَانَ بِالْقِسْطِ ۖ وَلَا تَبْخَسُوا النَّاسَ أَشْيَاءَهُمْ وَلَا تَعْثَوْا فِي الْأَرْضِ مُفْسِدِين

አላህ ፍትሓዊ ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

✍️ከኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

የበለጠ ለማወቅ
ጥሪያችን Tiriyachen

ወሠላሙ ዐለይኩም
የመጽሐፉን ባለቤቶችን ጠይቁ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

21፥7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ የምናወርድላቸው የኾነን *"ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም"*፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች *"ጠይቁ"* وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًۭا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ ۖ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ ፡፡

ብዙ ሚሽነሪዎች ከላይ ያለውን አንቀፅ ሲመፃደቁበት ማየት የተለመደ ሆኗል፤ "እናንተ ሙስሊሞች እኛን ጠይቁ ተብላችኃል" እያሉ እንደበቀቀን ሲደጋግሙትም ይታያል፤ እልህ መርፌ ሊያስውጣቸው ከሚደርሱ መሃይማን ጋር ጊዜን፣ ጉልበትና እውቀትን ማባከን አግባብ አይደለም፤ ሳይገባቸው ስለሚናገሩ ሃሳባቸው ሲዝረከረክባቸው ማየት የተለመደ ነው፤ "ዱባና ቅል አበቃቀላቸው ለየቅል" ይላል ያገሬ ሰው፤ በየትኛው ቀመርና ስሌት ነው ሙስሊም እውቀት ፈልጎ ክርስቲያንን የሚጠይቀው? ይህንን ነጥብ በነጥብ ማየት አለብን፦

ነጥብ አንድ
"ተጠያቂዎች"
የመጽሐፉን ባለቤቶች የተባሉት ተጠያቂዎች ክርስቲያንና አይሁዳውያን እንደሆኑ እሙንና ቅቡል ነው፦
3፥71 የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! *"እውነቱን በውሸት ለምን "* እውነቱንም እናንተ የምታውቁ ስትኾኑ ለምን *"ትደብቃላችሁ"*? يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لِمَ تَلْبِسُونَ ٱلْحَقَّ بِٱلْبَٰطِلِ وَتَكْتُمُونَ ٱلْحَقَّ وَأَنتُمْ تَعْلَمُونَ ።
ትቀላቅላላችሁ5፥68 እናንተ የመጽሐፉ ባለቤቶች ሆይ! *"ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታችሁም ወደ እናንተ የተወረደውን"* እስከምታቆሙ ድረስ በምንም ላይ አይደላችሁም» በላቸው قُلْ يَٰٓأَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ لَسْتُمْ عَلَىٰ شَىْءٍ حَتَّىٰ تُقِيمُوا۟ ٱلتَّوْرَىٰةَ وَٱلْإِنجِيلَ وَمَآ أُنزِلَ إِلَيْكُم مِّن رَّبِّكُمْ ۗ وَلَيَزِيدَنَّ كَثِيرًۭا مِّنْهُم مَّآ أُنزِلَ إِلَيْكَ مِن رَّبِّكَ طُغْيَٰنًۭا وَكُفْرًۭا ۖ فَلَا تَأْسَ عَلَى ٱلْقَوْمِ ٱلْكَٰفِرِينَ ፡፡
29፥46 የመጽሐፉን ባለቤቶችም በዚያች እርሷ መልካም በኾነችው ክርክር እንጂ አትከራከሩ፡፡ ከእነርሱ እነዚያን የበደሉትን ሲቀር፡፡ በሉም *"በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው"* አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን وَلَا تُجَٰدِلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلْكِتَٰبِ إِلَّا بِٱلَّتِى هِىَ أَحْسَنُ إِلَّا ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ مِنْهُمْ ۖ وَقُولُوٓا۟ ءَامَنَّا بِٱلَّذِىٓ أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَٰهُنَا وَإِلَٰهُكُمْ وَٰحِدٌۭ وَنَحْنُ لَهُۥ مُسْلِمُونَ ፡፡

ነጥብ ሁለት
"ጠያቂዎች"
አላህ "ጠይቁ" ብሎ ያለው ማንን ነው የሚለውን ነጥብ ለመረዳት ቅድሚያ አውዱ መመልከት ግድ ይላል፤ አረብ ሙሽሪኪን፦ "ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ ነውን? በማለት። ተናገሩ፦
21፥3 ልቦቻቸው ዝንጉዎች ኾነው እነዚያም የበደሉት ሰዎች መንሾካሾክን ደበቁ፡፡ *"ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ ነውን?"* እናንተም የምታዩ ስትኾኑ *"ድግምትን ለመቀበል ትመጣላችሁን?"*» አሉ لَاهِيَةًۭ قُلُوبُهُمْ ۗ وَأَسَرُّوا۟ ٱلنَّجْوَى ٱلَّذِينَ ظَلَمُوا۟ هَلْ هَٰذَآ إِلَّا بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ ۖ أَفَتَأْتُونَ ٱلسِّحْرَ وَأَنتُمْ تُبْصِرُونَ ፡፡

አረብ ሙሽሪኪን፦ "ይህ ብጤያችሁ ሰው እንጅ ሌላ አይደለምና ይህ መልክተኛ ምግብን የሚበላ፣ በገበያዎችም የሚኼድ ሲኾን"* ምን አለው አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ እርሱ መልአክ አይወረድም ኖሯልን? አሉ፦
25፥7 ለእዚህም *"መልክተኛ ምግብን የሚበላ፣ በገበያዎችም የሚኼድ ሲኾን"* ምን አለው ከእርሱ ጋር *"አስጠንቃቂ ይኾን ዘንድ ወደ እርሱ መልአክ አይወረድም"* ኖሯልን? *"አሉ"* وَقَالُوا۟ مَالِ هَٰذَا ٱلرَّسُولِ يَأْكُلُ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشِى فِى ٱلْأَسْوَاقِ ۙ لَوْلَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مَلَكٌۭ فَيَكُونَ مَعَهُۥ نَذِيرًا ፡፡
25፥21 እነዚያም መገናኘታችንን የማይፈሩት፦ *"በእኛ ላይ ለምን መላእክት አልወረደም"*፡፡ ወይም ጌታችንን ለምን አናይም *"አሉ"*፡ በነፍሶቻቸው ውስጥ በእርግጥ ኮሩ፡፡ ታላቅንም አመጽ አመፁ وَقَالَ ٱلَّذِينَ لَا يَرْجُونَ لِقَآءَنَا لَوْلَآ أُنزِلَ عَلَيْنَا ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ أَوْ نَرَىٰ رَبَّنَا ۗ لَقَدِ ٱسْتَكْبَرُوا۟ فِىٓ أَنفُسِهِمْ وَعَتَوْ عُتُوًّۭا كَبِيرًۭا ፡፡

አላህም ከዚህ በፊት አስጠንቃቂ ይኾኑ ዘንድ ወህይ የምናወርድላቸው የኾነን ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም፤ ምግብን የማይበሉ አካልም አላደረግናቸውም፤ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ ብሎ ምላሽ ሰጠ፦
21፥7 ከአንተም በፊት ወደ እነርሱ የምናወርድላቸው የኾነን *"ሰዎችን እንጂ ሌላን አላክንም"*፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች *"ጠይቁ"* وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ إِلَّا رِجَالًۭا نُّوحِىٓ إِلَيْهِمْ ۖ فَسْـَٔلُوٓا۟ أَهْلَ ٱلذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ ፡፡
21፥8 *"ምግብን የማይበሉ አካልም አላደረግናቸውም*"፡፡ ዘውታሪዎችም አልነበሩም وَمَا جَعَلْنَٰهُمْ جَسَدًۭا لَّا يَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَمَا كَانُوا۟ خَٰلِدِينَ ፡፡
25፥20 ከአንተ በፊትም *"ከመልክተኞች እነርሱ በእርግጥ ምግብን የሚበሉ በገበያዎችም የሚኼዱ ኾነው በስተቀር አልላክንም"* وَمَآ أَرْسَلْنَا قَبْلَكَ مِنَ ٱلْمُرْسَلِينَ إِلَّآ إِنَّهُمْ لَيَأْكُلُونَ ٱلطَّعَامَ وَيَمْشُونَ فِى ٱلْأَسْوَاقِ ۗ وَجَعَلْنَا بَعْضَكُمْ لِبَعْضٍۢ فِتْنَةً أَتَصْبِرُونَ ۗ وَكَانَ رَبُّكَ بَصِيرًۭا ፡፡

አላህ ጠይቁ ያለው ጠያቂዎች አረብ ሙሽሪኮችን መሆኑን ካየን ጠይቁ የተባሉት ጥያቄ፦ "ከነብያችን በፊት ወህይ ሲወርድላቸው የነበሩት ሰዎች ወይስ መልአክ" የሚለውን ነው፤ አረብ ሙሽሪኮች ከእነርሱው ወደ ኾነ አንድ ሰው አላህ ወህይ ማውረዱ ድንቅ ስለሆነባቸው ያንን ወህይ ድግምት ነው፤ መልእክተኛውን ድግምተኛ ነው ብለው አስተባበሉ፦
10፥2 *"ሰዎችን አስጠንቅቅ"*፤ እነዚያንም ያመኑትን ለእነርሱ ከጌታቸው ዘንድ መልካም ምንዳ ያላቸው መኾኑን *"አብስር"*» በማለት *"ከእነርሱው"* ወደ ኾነ አንድ ሰው *"ራእይን ማውረዳችን ለሰዎች ድንቅ ኾነባቸውን"* ከሓዲዎቹ፡- «ይህ በእርግጥ ግልጽ ድግምተኛ ነው» *"አሉ"* أَكَانَ لِلنَّاسِ عَجَبًا أَنْ أَوْحَيْنَآ إِلَىٰ رَجُلٍۢ مِّنْهُمْ أَنْ أَنذِرِ ٱلنَّاسَ وَبَشِّرِ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ أَنَّ لَهُمْ
قَدَمَ صِدْقٍ عِندَ رَبِّهِمْ ۗ قَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ إِنَّ هَٰذَا لَسَٰحِرٌۭ مُّبِينٌ ፡፡
38፥4 *"ከእነርሱ የሆነ አስጠንቃቂም"* ስለ መጣላቸው ተደነቁ፡፡ ከሓዲዎቹም፦ *"ይህ ድግምተኛ ውሸታም ነው"*» *"አሉ"* وَعَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌۭ مِّنْهُمْ ۖ وَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا سَٰحِرٌۭ كَذَّابٌ ፡፡
50፥2 ይልቁንም *"ከእነርሱ"* ጎሳ የኾነ *"አስጠንቃቂ"* ስለ *"መጣላቸው"* ተደነቁ፡፡ *"ከሓዲዎቹም"* «ይህ አስደናቂ ነገር ነው» *"አሉ*" بَلْ عَجِبُوٓا۟ أَن جَآءَهُم مُّنذِرٌۭ مِّنْهُمْ فَقَالَ ٱلْكَٰفِرُونَ هَٰذَا شَىْءٌ عَجِيبٌ ፡፡

አላህም ነብያችንን፦ "ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም፤ ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ" በላቸው በማለት ተናግሯል፦
6:50 «ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም አላውቅም፡፡ *"ለእናንተም እኔ መልአክ ነኝ አልልም"*፡፡ ወደ እኔ *"የሚወርድልኝን"* እንጅ ሌላን አልከተልም» በላቸው قُل لَّآ أَقُولُ لَكُمْ عِندِى خَزَآئِنُ ٱللَّهِ وَلَآ أَعْلَمُ ٱلْغَيْبَ وَلَآ أَقُولُ لَكُمْ إِنِّى مَلَكٌ ۖ إِنْ أَتَّبِعُ إِلَّا مَا يُوحَىٰٓ إِلَىَّ ፡፡
18፥110 «እኔ አምላካችሁ አንድ አምላክ ብቻ ነው ማለት ወደ እኔ የሚወረድልኝ *"ቢጤያችሁ ሰው ብቻ ነኝ"*፡፡ የጌታውንም መገናኘት የሚፈልግ ሰው፤ መልካም ሥራን ይሥራ፡፡ በጌታውም መገዛት አንድንም አያጋራ» *"በላቸው"* قُلْ إِنَّمَآ أَنَا۠ بَشَرٌۭ مِّثْلُكُمْ يُوحَىٰٓ إِلَىَّ أَنَّمَآ إِلَٰهُكُمْ إِلَٰهٌۭ وَٰحِدٌۭ ۖ فَمَن كَانَ يَرْجُوا۟ لِقَآءَ رَبِّهِۦ فَلْيَعْمَلْ عَمَلًۭا صَٰلِحًۭا وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِۦٓ أَحَدًۢا ፡፡

ስለዚህ ቁርአን ላይ ሙስሊሞች በሁሉም ርእሰ ጉዳይ ላይ የመጽሓፉ ባለቤቶችን ጠይቁ ሳይሆን ያለው አረብ ሙሽሪኮችን ከእዚህ በፊት ግህደተ መለኮት ሲወርድላቸው የነበረው መልአክ ሳይሆን ሰዎች ነው፤ ይህንን የማታውቁ ከሆናችሁ የመጽሓፉ ባለቤቶችን ጠይቁ፤ ምክንያቱም አስጠንቃቂ ለምን ሰው ይሆናል የሚል ሙግት ያቀረቡት እነርሱ ናቸው እንጂ ሙስሊሙማ በነብያችን ነብይነት በቁርአን የአላህ ቃል መሆን ያምናል፤ ምን ብሎ ይጠይቃል? በተጨማሪም ከነብያችን በፊት በነበሩት መልእክተኞች ሰው መሆናቸውን ያምናል፦
2፥285 መልክተኛው ከጌታው ወደ እርሱ በተወረደው አመነ፤ ምእምኖቹም እንደዚሁ፤ ሁሉም በአላህ፣ በመላዕክቱም፣ በመጻሕፍቱም፣ *"በመልክተኞቹም ከመልክተኞቹ «በአንድም መካከል አንለይም» የሚሉ ሲኾኑ አመኑ"*፡፡ «ሰማን፤ ታዘዝንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ምሕረትህን (እንሻለን)፡፡ መመለሻም ወዳንተ ብቻ ነው» *"አሉም"* ءَامَنَ ٱلرَّسُولُ بِمَآ أُنزِلَ إِلَيْهِ مِن رَّبِّهِۦ وَٱلْمُؤْمِنُونَ ۚ كُلٌّ ءَامَنَ بِٱللَّهِ وَمَلَٰٓئِكَتِهِۦ وَكُتُبِهِۦ وَرُسُلِهِۦ لَا نُفَرِّقُ بَيْنَ أَحَدٍۢ مِّن رُّسُلِهِۦ ۚ وَقَالُوا۟ سَمِعْنَا وَأَطَعْنَا ۖ غُفْرَانَكَ رَبَّنَا وَإِلَيْكَ ٱلْمَصِيرُ ።

ኡሥታዝ ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

ለመከታተል :- ጥሪያችን Tiriyachen
Follow as ፦https://www.facebook.com/tiriyachen

ወሰላሙ አለይኩም
2025/07/08 01:56:16
Back to Top
HTML Embed Code: