Telegram Web Link
አንዴ የጫካ ንጉስ የሆነው አንበሳ ቀጪኔዎችን ሁሉ እንደሚበላ ተናገረና ወሬው ከ ዝሆን ጆሮ ደረሰ ዝሆኑም በሩጫ ይቀውጠው ጀመር በዚ መሐል ፍየል ታገኘውና ለምን እንደሚሮጥ ትጠይቀዋለች ዝሆንም ይልቅ ራስሽን አዲኚ እኔ ራሴን እያዳንኩ ነው አንበሳ  ቀጪኔዎችን በሙሉ እንደሚበላ ዝቷል ለዛ ነው የምሮጠው አለ ፍየሏም በመገረም ታዲያ አንተ ዝሆን እንጂ ቀጪኔ አይደለህ?  አለችው እሱም ባክሽ ዝሆን መሆኔን አቃለው ግን አንበሳ ቀጪኔዎቹ በሙሉ እንዲሰበስቡለት ውክልና የሰጠው ለ አህያ ነው
እኔ ደግሞ ውክልና የተሰጠውን አካል አላምንበትም ምክኒያቱም የተሳሳተ ውሳኔ ሊወስን ይችላልና

#ልብ በል የህይወትህን ውሳኔ በሌሎች አካል ላይ አታድርገው ምናልባት አንተ በማትፈልገው መንገድ ሊወስኑ ይችላሉና የሕይወት መንገድህን በራስህ እጆች ጀምር አለበለዚያ አጨራረሱ እንደምትፈልገው አይነት ላይሆንልህ ይችላልና!!

❤️መልካም ቀን❤️


@umeralfarukk
የሰሃባው ሐምዛ (ረ.ዓ) አፍቃሪ የቦረናው ሐምዛ!

አቡ ዳውድ ኡስማን

ከስር በምስሉ ላይ የምትመለከቱት ብዙዎቻችሁ የምታውቁት ወንድማችን ሐምዛ ቦረና(አዳነ) ነው፡፡ የቦረና ተወላጅ ነው፡፡

ሃምዛ የተወለደው የክርስትና እምነት ከሚከተሉ ወላጆቹ ነው፡፡ ወላጆቹ እና ቤተሰቦቹ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ከመሆናቸው በተጨማሪ ሃይማኖታቸውን አጥብቀው የሚከተሉ እና የቤተክርስቲያን ሰዎች ከሚባሉት የሚመደቡ ናቸው፡፡

ልጃቸውን ሃምዛን ሲያሳድጉትም ሃይማኖታዊ ትምህርት እንዲከታተል በማድረግ በክርስትና ሃይማኖት ጠንካራ እንዲሆንላቸው በማድረግ ነበር፡፡

ሐምዛ ያደገበት ማህበረብ ክርስቲያናዊ ሲሆን መፅሃፍቶችን የማንበብ እና ጥያቄዎችን የመጠየቅ ልምድ ነበረው፡፡ ይህ ልምድም እያደገ መጥቶ ከእምነቱ መፅሃፍቶች በተጨማሪ እስልምና መፅሃፍቶችንም ማንበብ በመጀመሩ ውስጡ የተለያዩ ጥያቄዎች በወቅቱ ፈጥረውበት ነበር፡፡ ውስጡ ለሚጠይቀው ጥያቄ አርኪ የሆነ ምላሽ ግን ሊያገኝ አልቻለም ነበር፡፡ እስልምናን እያነበበ በሄደ ቁጥር ለእልምና የነበረው ፍላጎት እየጨመረ ሄደ፡፡ በተለይ የሐምዛ(ረ.ዓ) የጀግንነት ታሪክ ባነበበ ቁጥር ፍላጎቱ ይበልጥ ተመነደገ፡፡

በአንድ ወቅት ውስጡ ለተፈጠረበት ጥያቄ ምላሽ የሚሰጠው ከሌለ እስልምናን ለመቀበል እንደሚገደድ ለወላጅ እናቱ አሳውቆ ነበር፡፡ ውስጡ ላይ ሲመላለስ ለነበሩ ጥያቄዎቹ አጥጋቢ ምላሽ ሊያገኝ ባለመቻሉ በራሱ ፈቃድ እስልምናን በመቀበል ወደ ተፈጥሯዊው እምነት ተመለሰ፡፡

ሃምዛ እስልምናን ከመቀበሉ በፊት ከነበረበት የተለያዪ ሱሶች ሙሉ ለሙሉ እራሱን ነፃ በማውጣት እጁን ለአላህ ሰጠ፡፡ ሃምዛ ካነበባቸው መፅሃፍቶች ውስጥ የሐምዛ(ረ.ዓ) የጀግንነት ባህሪ እና ሌሎች ሰሃቦች መስለማቸውን በወቅቱ በድብቅ ሲያደርጉ እሱ ግን በግላጭ መስለሙን ይፋ የማድረጉ ሁኔታ እጅግ ውስጡ ላይ ተፅእኖ አሳድሮበት ስለነበር የክርስትና ስሙንም በሚወደው እና በሚያደንቀው ሰሃብይ ስም ወደ ሐምዛ በራሱ ፈቃድ ሊቀይረው ችሏል፡፡

በነብዩ(ሰ.ዐ.ወ) ዘመን ሰዎች እስልምናን በመቀበላቸው ሲደርስበቸው የነበረውን መከራ እና ግፍ ቀድሞ አንብቦ ስለነበር እሱም እስልምናን ሲቀበል ከቤተሰቡ ጀምሮ ከማህበረሰቡ ሊከሰትበት የሚችለውን ውግዘት እና ጫና ቀድሞ ስለገባው እራሱን ለሚመጣበት ፈተና ቀድሞ አዘጋጅቶ ነበር፡፡፡

ወላጆቹ "ጠበል ተወስዶ የለከፈው ነገር እንዲለቀው ይደረግ "በማለት ቢያስቡም ሃምዛ ግን "ልቤ ሃቅን ፈልጋ እና ወዳ ተቀብላለች እንጂ የለከፈኝ ነገር የለም" በማለት ወደ እስልምና በመግባቱ ውስጣዊ ሰላም እና ደስታ እንዳገኘ ግልፅ ማድረጉን ቀጠለ፡፡

እስልምናን ከተቀበለ ወዲህ ለመጀመሪያ ቀን ይሰራበት ወደነበረው የመንግስት መስሪያ ቤት ሲሄድ ነጭ ጀለቢያውን በመልበስ ነበር፡፡ ይህን ያደረገውም የነብዩ አ(ሰ.ዓ.ወ) አጎት የነበረው ሐምዛ(ረ.ዓ) እስልምናን ሲቀበል በይፋ ማንም ሳይፈራ በግልፅ እንዳደረገው ሁሉ እሱም መስለሙን በድፍረት ማሳወቁ ነበር፡፡ በአካባቢው የሱ እስልምናን መቀበል አነጋጋሪ ከመሆኑም በተጨማሪ ወደ ክርስትና ለመመለስ አሻፈረኝ በማለቱ የተበሳጩበት ሰዎች ከስራ ሲወጣ ጠብቀው በድንጋይ ወገሩት፡፡ ደሙ እየፈሰሰ ነጭ ጀለቢያውን ወደ ቀይ ቢቀየርም በመፅሃፍ ያነበበው የሰሃቦች ስቃይ እየታወሰው የነሱ አይነት እድል እንደገጠመው ለራሱ በማሰብ ከማዘን እና ከመረበሽ ይልቅ ይበልጥ በእምነቱ መጠንከር እና በአቋሙ መፅናት እንዳለበት በደስታ ወሰነ፡፡

እስልምናን አልተውም በማለቱ ከቤተሰቡም ከአካባቢው ማህበረሰብም ተገለለ፡፡ በስራ ገበታውም መቀጠል ሳይችል ቀረ፡፡ ከቤት እንዲወጣ ተደርጎ ጫካ ቢቆይም እሱ ልቦናውን ለኢስላም በመከፈቱ እየደረሰበት ያለው መከራ ፅናትን እንጂ ምንም አልቀነሰበትም፡፡

የአካባቢው የተከበሩ ሽማግሌዎች እሱን ለመምከር እና ለመገሰፅ ከቤተሰቡም ከማህበረሰቡም ጋር እንዲታረቅ እምነቱን መለወጥ ግዴታ መሆኑን በመንገር እየተቆጡም እያባበሉም መከሩት፡፡ እሱ ግን ፈፅሞ እስልምናን በምንም ነገር እንደማይለውጠው፣ በእምነቱም እንደሚፀናና እና እምነቱን አክብረውለት እንዲቀበሉት እና በሰላም እና በፍቅር እንዲኖር ካልሆነ ግን ፈፅሞ ሃይማኖቱን እንደማይለውጥ በማስረዳት ሽማግሌዎቹን መልሷቸዋል፡፡

ወንድም ሐምዛ ብዙ ፈተናዎችን እያስተናገደ ጓደኞቹንም በመመክር እና ከነበሩበት ሱስ እንዲላቀቁ በማድረግ እስልምናን እንዲቀበሉ ሰፊ ጥረት በወቅቱ አድርጓል፡፡ ጫናው ሲበረታበትም የትውልድ ቄውን በመልቀቅ ወደ አዲስ አበባ ሊመጣ ችሏል፡፡

ኢስላማዊ እውቀትን ለመቅሰም ከነበረው ጉጉት አንፃር በአዲስ አበባ በርካታ አሊሞች እና ኡስታዞች ስለሚገኙ ያሰበው እንደሚሳካለት አስቦ ነበር፡፡ ሆኖም ወደ ኢስላም መምጣቱን እና በመስለሙም ብዙ ስቃይ አሳልፎ መምጣቱን ለቀረባቸው በወቅቱ ለነበሩ የመጅሊስ ሰዎች፣ ሼኾች እና ኡስታዞች ቢያሳውቅም ከተወሰኑት በስተቀር በጠበቀው መልኩ ዲኑን ሊያስተምረው እና ሊደግፈው የሚችል ሰው ሊያገኝ አልቻለም፡፡
ብዙ ጠብቆ ስለነበር ካገኛቸው ሰዎች ያገኘው ምላሽ ውስጡን ቢያደማውም እስልምናን የተቀበለው እራሱ አንብቦ እና መርምሮ በመሆኑ ኢስላም በአማኞቹ ሁኔታን የሚመዝንበት ሁኔታ ስላልነበር ይህም ሌላ የአላህ ፈተና እንጂ ሌላ አይደለም በሚል የራሱን ጥረት ለማድረግ ወስኖ ተንቀሳቅሷል፡፡

በአወልያ ሰለምቴ የሆኑ ሰዎችን በማሰባሰብ ዲን የመማማር ስራ እንዲሰራ ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡ ዲኑን ከመውደዱ የተነሳ ለሚገጥመው እንቅፋት ሁሉ ተስፋ ከመቁረጥ ይልቅ ይበልጥ በፅናት ለዲኑ መልፋት እንዳለበት ለራሱ ቃል ይገባ ነበር፡፡

የወንድም ሐምዛ ቦረና እስልምናን ከተቀበለ ወዲህ የገጠሙት ፈተናዎች በአላህ እርዳታ ቢሆን እንጂ ማንም የሚያልፋቸው አልነበሩም፡፡ ልቡን ወደ ኢስላም አላህ የመራለት ሰው በፈተናዎች አይወድቅምና እስከዛሬዋ ቀን ድረስ በእምነቱ ላይ እንደፀና ይገኛል፡፡

ሐምዛ ቦረና በአወልያ ጅማሮውን ያደረገው የህዝበ ሙስሊሙ ሰላማዊ ትግል መጀመሩን ተከትሎ ለስደት ተዳርጎ ቆይቷል፡፡ በስደት በነበረበት ሳኡዲ አረቢያም በቢቢኤን ራዲዬ የአማርኛ እና የኦሮምኛ ክፍል እንዲሁም ዳንዲሃቃ የተሰኘም የኦሮምኛ ቋንቋ ራዲዬ በማቋቋም ህዝበ ሙስሊሙ ሲያካሂድ የነበረውን ሰላማዊ ትግል ሙሉ ጊዜውን በመስጠት ከ7 አመታት በላይ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ለሰላማዊ ትግሉ አበርክቷል፡፡

የሙስሊሙ ትግል ፍፁም ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ለማንኛውም ሃይማኖት ተከታዬች የሙስሊሙ ትግል ስጋት እንዳልሆነ ፣ትግሉም ፍፁም ሰላማዊ እና የመብት ትግል ብቻ መሆኑን በሰፊው ሲሰብክ እና ሲያቀነቅን ቆይቷል፡፡

ከክርስትና እምነት ተከታይ ቤተሰብ በመወለዱ የሙስሊሙ ትግል ይበልጥ ለማንም ስጋት አለመሆኑን ጠንቅቆ ከመረዳቱም በላይ ሌሎችም ትግሉ ሃይማኖታዊ እንጂ ፈፅሞ ክርስቲያኖችም ሆኑ ሌሎችን ለመጉዳት እንዳልሆነ እና ስጋት እንደይገባቸው እውነታውን በማሳወቅ ትልቅ ስራ ሰርቷል፡፡

በስደት አለም በመኖሪያ ፈቃድ ጉዳይ ለእስር ከመዳረጉም በላይ ለረጅም አመታት ከሚኖርበት ክፍል ብዙ ወደ ውጪ ባለመውጣቱ የተነሳ ለደም ግፊት፣ለስኳር እና ለተዛማጅ በሽታዎች ተዳርጓል፡፡ እስከዛሬ ድረስ በዚህ ህመም እየተሰቃየ እና መድሃኒት እየወሰደ ይገኛል፡፡

ሐምዛ ቦረና በስደት አለም ከሚስቱን እና ከልጆቹ ተነጥሎ ለረጅም አመታት ሲኖር ለሃይማኖቱ መክፈል ካለበት መስዋትነት አንፃር ምንም እያበረከተ እንዳልሆነ በማሰብ ለኢስላም ጊዜውን ብቻ ሳይሆን ህይወቱንም ቢሰጥ ብቁ እንዳልሆነ ያም
ን ነበር፡፡

እስልምናን በመቀበሉ ወላጆቹ በወቅቱ ደስተኛ ያልነበሩ ቢሆንም ከጊዜ ቡኋላ ግን መብቱን አክብረውለት በስደት አለም ችግር ላይ ሲወድቅም የገዛ መሬታቸውን ሳይቀር ሽጠው ልጃቸውን ከችግሩ ለማገዝ ጥረት አድርገዋል፡፡ የሐይማኖት መቻቻልን እና መከባበርን በነሱ ቤተሰብ ውስጥ ለሌለው ትምሀርት ይሆን ዘንድም በተግባር አሳይተዋል፡፡

ባለፉት ሁለት አመታት በህዝቡ ትግል ህወሃት በበላይነት ይመራው የነበረው መንግስት ከፌደራል መንግስቱ ስልጣን ሲገፋ እና በሃገሪቱ ለውጦች ሲመጡ ወደ ሃገሩ እና ወደናፈቀው ቤተሰቡ ከስደት አለም ሊመለስ ችሏል፡፡

ወደ ሃገር ቤት ከተመለሰም ቡኋላ ለውጡን በማገዝ ደረጃ ያመነበትን ለማድረግ የተንቀሰቀሰ ሲሆን ወደ ፖለቲካው መስክ በመግባትም የተወለደበትን የኦሮሞ ማህበረሰብ መብት እና ጥያቄ ምላሽ ያገኝ ዘንድ በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የኦፌኮ አባል በመሆን ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡

ሐምዛ ያመነበትን ነገር በተፅእኖ እና በጫና የሚቀይር አይነት ሰው አይደለም፡፡

ሐምዛ ቦረና የአርቲስት ሃጫሉን ግድያ ተከትሎ በተቀሰቀሰው ረብሻ ሃይማኖትን ከሃይማኖት ለማጋጨት በማህበራዊ ሚዲያ ቅስቀሳ ሲያደርግ ነበር በሚል በኦቦ ጀዋር መሐመድ የክስ መዝገብ ተወንጅሎ በአሁኑ ወቅት በእስር ላይ ይገኛል፡፡

ቤተሰቡ የገዛ ወላጆቹ ሳይቀር የክርስትና እምነት ተከታይ ሆነው ሲያበቃ ሃይማኖታዊ ግጭት እንዲቀሰቀስ ጥሪ በማስተላለፍ ተጥርጥሯል በሚል ለእስር ተዳርጓል፡፡

ስለሐምዛ ከሁሉም በላይ ኢስላምን ተቀብሎ ከማህበረሰቡም ቀጥሎም ከሙስሊሙም በኩል ገጥሞት የነበረውን ፈተና ያለ አንዳች መፍረክረክ በፅናት በዲኑ ላይ ፀንቶ መቆየቱ ለብዙዎቻችን አስተማሪ ነው ብዬ ስላሰብኩኝ ያወኩትን ላካፍላችሁ ወደድኩኝ፡፡

እኔ ያወኩትን እውነታ መሰከርኩኝ! እስልምናዬን ብሎ ብዙ መስዋት ስለመክፈሉ የማናችንም ምስክርነት የማያሻው አረህማን ደግሞ ሃቁን ያውጣለት!

አላህ ሁሉም አዋቂ እና ቻይ በመሆኑ ከማናችንም በላይ ፍትሃዊው ጌታ እውነታውን ያውቀዋል እና አላህ ትክክለኛ ፍትህ ያስፍንለት:፡

◙○◙◙○◙◙○◙◙○۩
@umeralfarukk
ዱንያን ከሞትክ በኋላ ማየት ከፈለክ ሰዎች ከሞቱ በኋላ እያት። ሰዎች ሟች ወዳጆቻቸውን እንዴት እንደሚረሱ ስታስተውል ያን ጊዜ አንተንም እጅግ የሚወዱህ ሰዎች እንደሚረሱህ እርግጠኛ ትሆናለህ። ወይም በዱንያ ተጠምደው ላንተ ጊዜም ልብም ያጣሉ። ስለዚህ ህይወትህን በሙሉ ለአላህ አድርገው። እርሱ ብቻ ነው የማይረሳው። ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት አሳምር። የማይጠፋው ብቸኛ ጌታ እርሱው ነው።
መልካም ዜና

ቢላል ቲቪ እነሆ በሳተላይ ብቅ ብሏል

የሳተላይት ፍሪኩዌንሲው ከታች በምስል ላይ ማግኘት ትችላላችሁ

በቅርቡ የሙከራ ስርጭቱን ይጀምራል !
@umeralfarukk
"የኢትዮጵያ አምላክ ቅጣት"??

አቡ ዳውድ ኡስማን

በሱዳን የጎርፍ አደጋ በመከሰቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሱዳን መንግስት አወጀ ሲባል "ኢትዮጵያን የነካ ድሮም የኢትዮጵያ አምላክ ዝም አይልም እንዲህ ይቀጣዋል እያሉ ነው ደብተራዎች::
ባለፈውም በተመሳሳይ ስልጤ ላይ ጎርፍ አደጋ ሲከሰት ቅድስት አርሴማን ነክተው ስለነበር በጎርፍ እየተቀጡ ነው ሲሉንም ነበር:: አፋሮችስ ማንን ነክተው ይሆን እንበላቸው?

በነሱ እሳቤ መሰረት የነ ሱዳን የጎርፍ አደጋ ኢትዮጵያን ስለነኩ ቅጣት ነው ካሉን በኢትዮጵያ በአፋር፣ በደቡብ፣ በጋምቤላ፣ በኦሮሚያ፣በትግራይ ክልሎች የደረሱት የጎርፍ አደጋዎችስ የትኛዋን ኢትዮጵያ ነክተው ይሆን የተቀጡት? ወይስ እነዚህ ክልሎች ኢትዮጵያውያን አይደሉም?

የኢትዮጵያ አምላክ ከሌሎች ሃገራት አምላክ ይለያል ማለት ነው ከኢትዮጵያ ጋር ድርድር የተቀመጠን ሃገር ሁላ እየቀጣ ለኢትዮጵያ የሚያደላው(ወነዐዑዙቢላህ)?
@umeralfarukk
በዋሻው ምእራፍ፣በሰለዋት ደምቀን፤
ገላችንን ታጥበን፣ተውበን አሸብርቀን፤
ንፁህ ልብስ ለብሰን፣ከጌታችን ታርቀን፤
ሽቶውንም ነስነስ በፈገግታ ፈካ፤
የቀናቶች ንጉስ ጁመአ ነው ለካ።
<<መልካም ጁመአ>>
(ከውሰር)
ከለሊቱ ስምንት ሰአት አካባቢ የቤቴ በር በሀይል ተንኳኳ። ከእንቅልፌ
ባንኜ ተነሳሁ። በቀስታ ወደ በሩ ተጠጋሁና ከፈትኩ።
በር ላይ አንድ ወጣት ቆሟል አጎቱ ነበር የሞቱት። ቶሎ መቀበር እንዳለበት
ሀኪም ስለነገራቸው ተያይዘን ወደ ቤታቸው አመራን።
........ጀናዛውን ማጠብ ጀመርኩ በመሀል ግን የሚያስደነግጥ ሁኔታ
ተፈጠረ። የሰውነት ከለሩ መቀያየር ጀመረ። ፊቱ ጠቆረ አካሉ ከሰለ።
እንደምንም አጥበን ጨረስን። ወደመቃብር ስፍራም ይዘነው ሄድን።
የተቆፈረው ቀብር ውስጥ ገባሁ መሬቱን ጠራረኩና አፀዳሁት የለህዱንም
ስፋት ሞከርኩት። ወደ ውስጥ ጀናዛውን አስገባነው ምድር ሰውነቱን
እንደነካው ከመሬት ስር ትልቅ ትል ወጣና ሰውነቱ ላይ ተለጠፈ
አስወገድኩት ሆኖም ግን ሌላ ከመጀመርያው የተለቀ እባብ የመሰለ
በደረቱ የሚሳብ አስፈሪ እንሰሳ ሰውነቱ ላይ ተጠመጠመ። ነገሩ
ስላስደነገጠንና ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ትተነው ከቀብር ወጣን።
በስነስርዓት ሳይቀበር በላዩ ላይ አፈር ደፋንበት።
በህይወት ዘመኑ ምን አይነት ሰው እንደነበር ጠየቅን። ሰላትን ወቅቱን
ጠብቆ እንደማይሰግድ ከአንድ ዘመዱ ተነገረኝ ።
ሙሰልሰል ስትመለከቱና ፌስቡክ ላይ ተጥዳችሁ ሰላት የሚያመልጣችሁ፣
ኳስ እየተጫወታችሁ ሰላት የሚያልፋችሁ ሰዎች ሆይ !!! ስሙ
ይህን አይነት አሟሟት ነው የምትሹትን? !
በአላህ እምላለሁ ባጠፋሀቸው ጊዜያት የምትቆጭበት ቀን ይመጣል ።
ዱንያን ለቀህ ከመውጣትህ በፊት ለኸይር ነገር ተቻኮል
#ሼር በማድረግ ለወዳጅ ዘመድ አዳርሱ

@umeralfarukk
ዱዓ ስታደርግ አላህ ሆይ ጀነት አስገባኝ ብቻ አትበል! ተቀጥተውም ጀነት የሚገቡ አሉና:: ይልቁንም ያለ ሂሳብ ጀነት ከሚገቡት አድርገኝ ፣ከጀሃነም እሳትም ጠብቀኝ በል:: አላህ ያለ ሂሳብ ጀነት ከሚገቡት ያድርገን
ለ እኔ ከ አባይ ግድብ በላይ በማንነታቸው የ ሚገደሉ ሰዎች ሁኔታ ያስጨንቀኛል

.....ፖለቲካው ለላ ነገር ነው. .ነገር ግን እንዲህ በ አሰቃቂ እና በ ግፍ እሱንም በ አደባባይ የ ሚገደሉት ወንድምና እህቶች ደም ከ ሁሉም በላይ መቅደም ያለበት ጉዳይ ነው..
በ አሁን ሰዐት የ ሰው ልጅ ነፍስ እንደ ትንኝ እየተቆጠረ አደለም
ግን ለምን❗️❗️❗️
#ከ ትራምፕ ድንቁርና በላይ የ አብይ አህመድ ለ ነፍስ ዋጋ ያለው ንቀት ያበሽቀኛል
#ከሚፈሰው ዉሃ በላይ የሚፈሰው የ ህፃናት ደም በ እጅጉ ያሳስበኛል

#HUMANITY #BEFORE #GERD

የ ኡማው ጉዳይ ያገባናል የ ቴለግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
🍁 የጠዋት እና የማታ ዚክር የሚደረግበት ጊዜ።

🍁 ታላቁ አሊም ኢብን ኡሰይሚን(ረሂመሁላህ) እንዲህ ይላሉ :

🍁 የጠዋት ዚክር ጎህ ቀሚቀድበት ጊዜ አንስቶ ፀሀይ ከፍ እስከምትልበት (የዱሃ ሰላት የሚሰገድበት) ጊዜ ድረስ የሚደረግ ይሆናል።
🍁የማታ ዚክር ደግሞ ፀሀይ ወደ መግቢያዋ ከምትቃረብበት ጊዜ አንስቶ እስከ እኩለ ለሊት ይሆናል።
(فتاوى نور على الدرب شريط 374)

@umeralfarukk
🍁 ኢብን ኡሰይሚን ረሂመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡

🍁ወንድሜ ሆይ (ልብህን) ቀልብህን ሁልጊዜ ሃክማት ሁሌም እስክትፀዳ እጠባት።ልባችንን ማፅዳት በደምብ አስፈላጊ የሆነ ነገር ነውና።


🍁 ልባችንን እንዲያፀዳልን፣በንፁህ ልብ ከሚግገዙት እንደዚሁም መልእክተኛውንም(ሰ.ዐ.ወ) ከሚከተሉት አንዲያደርገን አላህን እለምነዋለሁ።

شرح رياض الصالحين ٦٣/١


@umeralafarukk
Audio
Umer Al-Faruk
Audio
❤️ ምርጥ ነሺዳ ❤️
ጋበዝኳችሁ☝️☝️☝️
"ኢማም ማሊክ እንዲህ ይላሉ: — "የተደላደለ ጥልቅ ዕውቀት ባለቤት ማለት አራት ነገሮችን የሰበሰበ ነው: —
❶ በነፍሱና በአላህ መካከል ፍርሀትን፤
❷ በነፍሱና በሰዎች መካከል ትህትናን፤
❸ በነፍሱና በዱንያ መሀል ዝህድናን፤
❹ በነፍሱና በነፍሱ መሀል ደግሞ ትግልን።"
:
ተፍሲር ሷዊይ ዐለል ጀላለይን
#ሴትየዋና_ጂኒው

አንድ ሰው ሚስቱ ጂኒ እንደያዘው ሰው ሲያደርጋት "ጂኒ ሳይዛት አይቀርም" ይልና እንዲቀራባት ወደ አንድ ሸህ ይዟት ይመጣል
ከተቀራባት በኋላ ጂኒው ለመውጣት ዝግጁ እንደሆነና ለመውጣት ግን አንድ መስፈርት እንዳለው ይናገራል
"ካለመስፈርት ነው መውጣት ያለብህ" በማለት ሸይኹ ያስተባብላሉ

ጂኒውም "እስቲ መስፈርቱን ስማኝ"

ሸይኹም "እሺ ተናገር"

ጂኒው "እወጣና ባሏ ውስጥ እገባለሁ"

ባልየው "ይህን ሲሰማ በድንጋጤ ብድግ ይልና
"በፍፁም አይሆንም" ይላል

ጂኒው "ለምን በሱ አካል ልገባ እንደፈለኩ ታቃለህ?"

ሸይኹ "ለምንድነው?"

ጂኒው "ሰላት አይሰግድም"

ሸይኹም ባልየውን "ጂኒው ባለው ትስማማለህ ወይ?" ብሎ ጠየቀው

ባል" ኧረ በፍፁም እንደማይስማማ ተናገረ

ሸይኹም ለጂኒው "ከሴቷ ውጣና ከቤታቸው አቅራቢያ ሁን ሰላት የማይሰግድ ከሆነ ግን ትገባበታለህ" የሚል ሀሳብ አቀረበለት

ጂኒው ተስማማ

ከጊዜያት በኃላ ሴቲቱ ሸይኹን ለማመስገን ደወለች

ሸይኹም ስለባሏ ሁኔታ ጠየቃት

ሚስትም "የመስጂድ በር የሚከፍተው እሱ ነው፡፡ አንዲት ሰላት አምልጣው አታቅም" አለች

የሚገርመው ሚስት ሲጀምርም ጂኒ አልያዛትም ነበረ ቧሏ ሰላት ስለማይሰግድ ጂኒ እንደያዘው ሰው መስላ ቧሏ ሰጋጅ እንዲሆን ከሸይኹ ጋ ተነጋግረው የፈጠሩት ዘዴ ነበረ
በዱንያም በአኺራም ለባሏ ቅጣትን የምትፈራለት ባሏን ከልቧ የምትወድ ምርጥ ሴት ማለት ይህች ሴት ናት
“የሚወድህ ጀነትን ይገዛለሀል"


@umeralfarukk
#ሐዲሥ 50/409

አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል። "የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ፦ "(ምድር) የዚያን ቀን ወሬዋን ታወራለች፡፡" የሚለውን አንቀጽ ሲያነቡ ፦ "ወሬዋ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁን?" በማለት ጠየቁ። "አላህና መልዕክተኛው ያውቃሉ" አሏቸው (ባልደረቦቻቸው)። "ወሬዋ እያንዳንዱ ሴት ወይም ወንድ ከጀርባዋ የሠራውን ማውራቷ ነው። በዚህ ቀን ይህን ይህን ሠርተሃል ትላለች። ወሬዋ ይህ ነው" አሉ። (ቲርሚዚ ዘግበውታል። ሐሰኑን ሶሒሕ ብለውታል።)

፨ ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ ለመልካም ሥራ መነሳሳትና ከኃጢአት መራቅ እንደሚገባ።
2/ አላህ ምድርን ማናገር መቻሉ የወሰን የለሽ ችሎታው አካል ነው።
አቡ ሁረይራ (ረ.ዐ) እንዳስተላለፊት የአሏህ መልዕክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል :- ሙስሊም በሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች አምስት ናቸው ፤ ሰላምታን መመለስ ፣በሽተኛን መጠየቅ፣ጀናዛን መሸኘት ፣ጥሪን(ግብዣን ማክበር) ፣ ላስነጠሰው በጎ ምኞትን መግለፅ።

" ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል"

በሌላ ዘገባ :-" ሙስሊም በሙስሊም ላይ ያሉት መብቶች ስድስት ናቸው :-ስታገኘው ሰላምታ አቅርብለት ፣ ሲጋብዝህ ግብዣውን ተቀበል፣ ካንተ ምክር ሲፈልግ ምክርህን ለግሰው ፣ ካስነጠሰውና ለአሏህ ምስጋና ካደረሰ በጎ ምኞትህን ግለፅለት፣ ሲታመም ጠይቀው፣ ሲሞት ተከተለው ( አስክሬኑን ወደ መቃብር ሸኝ")

@umeralfarukk
ሮበርት ሙጋቤ
"የአፍሪካ የትምህርት ስርአት አስገራሚ ውጤቶች አሉት። አንደኛ ደረጃ የሚይዙ ቀለሜ ገበዝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት አምጥተው ኢንጂነሪንግና ሜዲሰን እዲማሩ እድል ያገኛሉ። ሁለተኛ ደረጃ የሚይዙት ደግሞ ህግና ማኔጅመንት ተምረው አንደኛ ደረጃዎቹን ያስተዳድሯቸዋል።ዝቅ ብለው በ ሶስተኛ ደረጃ የሚገኙት ተማሪዎች ደግሞ ፖለቲካ ውስጥ ይገቡና አንደኛም ሁለተኛም ደረጃ ላይ ያሉትን ከላይ ሆነው ይቆጣጠራሉ። በትምህርት ወዳቂዎች ደግሞ ፖሊስና ወታደር ይሆናሉ እነዚህ ደግሞ ፖለቲከኞችን ይቆጣጠራሉ ደስ ያላላቸውን ፖለቲከኛ እስከ መግደል ድረስ ።

ከሁሉም ግን ምርጡ ጭራሽ ክላስም ሆነ ትምህርት ቤትም ገብቶ የማያውቀው ደግሞ ነብይና ጠንቋይ ይሆናል ይሄን ደግሞ ሁሉም ይከተሉታል 😂 😂 😂 😂


ለወዳጅ ዘመድዎ ሼር በማድረግ ይተባበሩን



@umeralfarukk
2024/06/16 01:44:51
Back to Top
HTML Embed Code: