Telegram Web Link
ባህርዳር

2012 ዓ.ም
@unstoppablecaption
ፍኖተ ፅድቅ

2012 ዓ.ም
@unstoppablecaption
ጎጃም, ባህርዳር


@unstoppablecaption
"Be calm like a calm lake, then you will look beautiful like a beautiful calm lake! "

@unstoppablecaption
Self -portrait
ባዶ እግሬን …
ባዶ ሆዴን … ባዶ እጄን
ራቁቴን
ከሰው ፊት መቆም ፈርቼ
ቤቴ ቀርቼ …
ተቆጠረብኝ ጊዜ
ተሰፈረብኝ እድሜ፡፡
ኋላ ….
‹‹ አትቀላቀልም እሷ
ራቁት ነው ልብሷ
ባይተዋረት ነው ነፍሷ …››
የሚል መዝሙር ሰምቼ
‹‹ ከ`ናት እንዳልተወለድኩ ጨሼ … ›› አይ ሰለሞን
እየፈራሁ መንገድ ወጣሁ፡፡
መንገዱ ላይ …
እርቃን የቆመ ውኃ ዐየሁ
ሕይወት ነካኝ
እውነት ለየሁ፡፡
(ከመዘምራኑ እንደ አንዳቸው ሆንኩ፡፡)
‹‹ አካሆኗ አይወግንም
ሰውነቷ ለሰው አይሆንም፡፡
ፍቅሯ እስካለመሆን ይዘልቃል
የተቀጠረችበት ማታ
ለድሆች እራት ይሆናል፡፡››
(ለክብሯ ግጥም እንዳዋጣ ተማጸንኳቸው)
‹‹ ሀዘንተኛ ነፍሴን
ገላ ከሚያጅባት
ጥላሽን ለብሳለሁ
እስከ ፀሐይ ግባት ››
(ጀማው ተቀበለ)
‹‹ስሟ የተጠራበት …
ዘምዘም ነው
ቁስል ይከላል
የሄደችበት ጎዳና
ወይ ላላ ወይ ላላ ››
እንባ ተናነቀኝ፡፡
(መንፈስ እንደ ጥላ ከእግሮቿ ስር ስር ይላል፡፡)
ለክብሯ ሎላ ግጥም …
‹‹ ካሁን በፊት ብሞት
ግድ እስከማይሰጠኝ
ሕይወት ካላት ሁሉ
ስቃ አቀበለጪኝ፡፡››
እንባዬን ማቆም አልቻልኩም፡፡ በሳግ ሌላ ግጥም አቀበልኩ …
‹‹ሕይወት የሌለው ላይረግጣት
ፍቅር ያልነካው ላያያት
የተሰወረች ሁለንታ
ምትሽኮረመም ቦታ ናት …››
መዘምራኑ አንድ አንድ እያሉ መበተን ጀመሩ፡፡ በቀሩት መዘምራን እየታጀብኩ ሌላ ግጥም …
‹‹ባንቺ የመጣ የሆንኩትን
ካበቦች ፊት ሸንጎ አቆምኩት
ምን አተረፍኩ?
አሄሄ! አሄሄ! ››
ብቻዬን ነኝ፡፡ መዘምራኑ ሁሉ ሄደዋል፡፡ እንደምንም … ሌላ ግጥም …
‹‹ ያለቀሰችበት እንደሆን
ጨለማም ይበሰብሳል
የተቆጣችው እንደሆን
ንፈራስም ያጎነብሳል
ሁሉ እንደየ አቅሙ
ከሁኔታሽ ጋር ይስማማል
ፈገግ ያልሽለት እንደሁ
የኔ ልብ ምን ይመልሳል? ››
ፈገግ አለች፡፡
ጩኸት!!!!
ድምጼ ከሕልሜ እስከውኔ ተሸገረ፡፡ when I open my sleepless eyes at dawn በእንባ ርሰዋል፡፡
ጥቁር ግጥም
እንዴት የሕልሜ ሀዘን
ጉንጬ ላይ እንባ ነቀሰ?
እንዴት በጊዜ ጉልበት
አላሎ ላላላ …
ኪዳን
ከአልጋዬ ላልወርድ፡፡ ከቤቴ ላልወጣ
( I am a stranger to myself … )

©Migbar Siraj
Self -portrait

Inspired by migbar siraj's poem
ባዶ እግሬን …
ባዶ ሆዴን … ባዶ እጄን
ራቁቴን
ከሰው ፊት መቆም ፈርቼ
ቤቴ ቀርቼ …
ተቆጠረብኝ ጊዜ
ተሰፈረብኝ እድሜ፡፡
ኋላ ….
2025/07/10 17:18:28
Back to Top
HTML Embed Code: