Telegram Web Link
 “Choose only one master—nature.”
🏞🌅🌄🗻🏔
Meerkat
🦚💚
“The soul is like a violin string: it makes music only when it is stretched.” 🧡
ቤት ስገባ ፀጥ ብሏል ሁሌም ደስ ሲለኝ እንደማደርገው ቫዮሊኔን አነሳሁ ገመዱን በገመዱ ስፍቅ ድምፅ አወጣች ያሳለፍኩትን ምሽት እያሰብኩ በስሜት መጫወት ጀመርኩ ለምን ያህል ግዜ እንደቆየሁ አላወቅኩም "ደስ ያለሽ ትመስያለሽ ምን ተገኘ"? አለኝ ቆሞ በተመስጦ ሲመለከተኝ ቆይቶ ነበር እያንዳንዱን የስሜቶቼን ለውጦች ያውቃቸዋል ግን ግዴለሽ ነው ።
"ምንም" አልኩ።
እሱን ማግባቴ ለረጅም አመት ልክ እንደሆነ አስብ ነበር ከሱ ሌላ ደስታ የማገኝ አይመስለኝም ነበር የዛሬው ድንገት ለውጤ እሱንም ሳያስደነግጠው አይቀርም
"ምሽትሽ እንዴት ነበር "አለኝ
"በጣም ጥሩ አልኩት "
"ከማን ጋር ነበርሽ ?"
"ከጓደኛዬ ጋር "
"ማን የሚባል ጓደኛሽ ?"
ለሌላ ጭቅጭቅ መንገድ መክፈት ስላልፈለኩ ያንን ደስታዬንም ላለማበላሸት ይሁን እኔንጃ "አታውቀውም።" ብዬ ለመጀመሪያ ግዜ ዋሸሁት
ፊቱ ሲለዋወጥ ታየኝ
"ግን ለምንድነው እንዲ የምንሆነው?" አለኝ
ትከሻዬን ወደ ላይ ከፍ አድርጌ የእኔንጃ አይነት ምልክት ሰጠሁት
"እናውራ" አለኝ
በውስጤ ብናወራም ምንም ለውጥ የሌለው ነገር እንደሆነ ባውቅም እሺ አልኩት
ማውራት ጀመረ ችግሮቼን መደርደር ጀመረ ብዙ ሰአት አወራ ሰለቸኝ አዎ ልክ ነህ ብዬ ብድግ ስል ጭኔ ላይ የነበረው ቫዮሊን ወደቀ አንዷ ገመድ ብጥስ አለች ውስጤ ከቆረጠበት ቆይቷል ልቤ ብዙ እድል ሰጥቶታል ማየት አልፈለገም የወደቀውን ቫዮሊን ከነ ተበጠሰው ገመድ ትቼው መኝታ ቤት ገባሁ ምሽቴን እንደገና ላስብ።
ጥዬው መሄድ ባላስብም ልቤ እንደሸፈተበት ሳስብ እጨነቃለሁ እሱን እያሰብኩ ድጋሚ ፈገግ ማለት አለመቻሌ ያሳዝነኛል ....
model: frehiwot
💙🌧🌂
Thank you for this beautiful story and posing for me
Frehiwot D.
2025/07/04 11:40:14
Back to Top
HTML Embed Code: