Telegram Web Link
አንድ ሜምበርም ይሁን የ2022 እና ከዚያ በታች ግሩፕ የስጠኝን ሰው ካርድ እሸልማለሁ ማርያምን ወዲያውኑ እልካለሁኝ

ለመጠቆም
👇👇👇👇👇
@Notman11
🙏6
ምእመናን ሆይ

ሰንፔር ማለት ከወርቅ የበለጠ ነው።

እና ይሄ ሰንፔር ሳሩንም ቅጠሉንም የሚሰብ ነው ።

ድንግል ማርያምም ማትሰበው ፍጡር የለም

ጽጌረዳ ካለበት ንቦች ይከባሉ
እውነተኛይቱ ፅጌሬዳ ካለችበት መላእክት ይከባሉ ።
እግዚአብሔር በሷ ስላለ መላእክት በቤተልሔም ከተሙ

ኃጥዓን ይፈልጓታል ብታነፃን ብለው
ፃድቃን ይፈልጓታል ትምህክታቸው ናትና
መላእክት ይፈልጓታል የሃይማኖት መስታወታቸው ናትና

አይተውት ማያውቁትን እግዚአብሔር እኮ
ያሳየቻቸው ድንግል ማርያም ናት

የእመብርሃን በረከቷ ይደርብን🙏
9👍1
ምእመናን ሆይ

እግዚአብሔር አምላክ ቅድስት ድንግል ማርያምን መርጧታል
ታዲያ ከመረጣት ሲመርጡት ማይመረጥ አለ ብለው ይጠይቃሉ ?

ቆርጠው በትር ሲያደርጉት እምቢ ሚል በትር የለም ? ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ መረጣት እናቱ ሆነች ታዲያ እኛ ለምን እንሰግዳለን? ይላሉ።

መመረጥማ አለም ሁሉ ተመርጦ ነበር
ታዲያ መመረጡን አላበላሽም ?

ለምንኩስና ተመርጦ ምንኩስነውን ያበላሽ የለም ?
ለቅስና ተመርጦ ቅስናውን የጣለ የለም ?
ለትዳር ተመርጦ ትዳሩን ያበላሽ የለም ?
ለክርስትና ተመርጦ ለክህደት የሮጠ የለም ?
ለዝማሬ ተጠርቶ ለዘፈን የሮጠ የለም
?

ለእናትነት ተመርጣ እናትነቷን አፅንታ የኖረች
ቅድስት ድንግል ማርያም
❤️ ብቻ ናት።

መመረጧን ያፀናች ማለት ነው

የእመብርሃን በረከቷ አይለየን🙏
🙏54👍1
ምእመናን ሆይ

ማርያም❤️

ማለት የባህር ኮከብ ማለት ነው

የ ዛሬ መረከብ በኮምፖስ ነው እና አንመስልበትም
የድሮ መርከብ የንጋት ኮከብ እያዩ ነው ወደብ ሚደረሱበት

ያ የባህር ኮከብ ነው አቅጣጫ እየመራ ወደብ ሚያደርሳቸው
ያ የባህር ኮከብ ከወደብ ያደርሳቸዋል

ድንግል ማርያምም በኃጢአት ባህር የዘቀጠውን አለም ወደ እግዚአብሔር መርታ ታደርሰዋለችና የባህር ኮከብ ትባላለች

-በዝሙት ያሉትን( በዝሙት ውስጥ የዘቀጡትን)
ወደ ንፅህና ትመራቸዋለች

-ክርስቶስን የተራቡትን ወደ ሥጋ ወደሙ ትመራቸዋለች
-በሲኦል የማቀቁትን በቀዝቃዛ ውሃ ወደ ገነት ትመራቸዋለች

ስለዚህ

ድንግል ማርያም❤️

- የኃጢአት ማዕበል
- የመከራ ማዕበል በአዘቀተን ጊዜ
- ጎትታ የምታወጣን መራሒተ መንግስተ ሰማያት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም❤️ ስለሆነች

የባህር ኮከብ ትባላለች።

የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን🙏
👍6👏1
ምእመናን ሆይ

ቅዱስ ኤፍሬም እንዲህ ይላል

ፈጣሪዋ ነህና  ለድንግል እናትህ  ለጡቶቿ ወተትን ሰጠህ
ልጇ ነህና  ከሰጠሀት ወተት መልሰህ ጠባህ
ለደናግል ወተት አይሰጣቸውም
አንተ ግን  አምላኳ ስለሆንህ ወተት ሰጥታሀታል
ልጇ ስለሆነህ ደሞ ከሰጣሀት ወተት ጠባህ
ድንግል ለአንተ ለሁሉ መጋቢ የተወሶ ወተት ሰጠችህ
ሰማያትን በዘረጋው እጆችህ ጡቶቿን ጨበጥክ

ወላዲተ አምላክ ናት ክብር ምስጋና ይግባት🙏
6
ምእመናን ሆይ

ሰው እኮ ኑሮው እንደ አሳ ነበር

አሳ ሲዋኝ ድምፁን ሰምቶ የሚያወቅ አለ? የለም

የሰው ልጅ ም በሀጢአት ወድቆ ሳለ ፀሎቱ አይሰማም ነበረ።

ስለዚህ

ምዕራገ ፀሎት እመቤታችን ❤️ ስትወለድ ስትመጣ

ብሶታችን ተሰማልን
የወይኑ( የመርገሙ) አተላ ተጠረገ እና አዲስ ውኃ ተሾመብን
አዲስ ወይን ጣፈጠልን
አዲስ ወይን ተሰጠን

ጣዕመ ቢሱን አለም የለወጠችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ።


የእመቤታችን እረድኤት በረከት አይለየን 🙏
10
ቅዱስ አምብሮስ❤️

👉ጌታ የሰው ልጆች የእናቱን ንጽሕና ከሚጠራጠሩ ይልቅ የእርሱን መለኮታዊ ልደት ቢጠራጠሩ እንደሚሻል መረጠ፡፡

👉የድንግሊቱ ትሕትና አንዴት ጥልቅ አንደሆነ ያውቃል፡፡

👉የንጽሕናዋ ነገርም በቀላሉ እንዴት [በአይሁድ ዘንድ] ሊሰደብ እንደሚችል ያውቃል፡፡

👉 ስለዚህ የልደቱ ክብር በእናቱ መዋረድ ላይ አንዲገነባ አልፈለገም”
👍7
ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ እግዚእ ሐሤቶሙ ለመላእክት፡፡

የመላእክት ደስታቸው የሚሆን ጌታን የወለድሽው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ለሊሁ ዓለሞሙ ወለሊሁ ተድላሆሙ ወለሊሁ ሀገሮሙ እንዲል፡፡ አንድም ሥጋዌውን ተልከው ለነቢያት የሚነግሩ መላእክት ናቸው፡፡ ከዚህ የተነሣ ባጭር ቁመት በጠባብ ደረት ተወስኖ አይተውት ፤ ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ብለው አመስግነውት ፤ በጣዕም ላይ ጣዕም ፤ በጸጋ ላይ ጸጋ ተጨምሮላቸው ደስ ብሏቸዋልና አንድም የመላእክት ደስታቸው የምትሆኝ ጌታን የወለድሺው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ንጽሕናዋን ቅድስናዋን እያዩ ደስ ይላቸዋልና ሐሴቶሙ ለመላእክት አለ፡፡

ተፈሥሒ ኦ ድንግል ዜናሆሙ ለነቢያት፡፡

የነቢያት ዜና ትንቢታቸው ንጽሕት ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ኦ ድንግል አምሳል ወትንቢት ፤ ዘነቢያት እንዲል፡፡

ተፈሥሒ እስመ ረከብኪ ሞገሰ እግዚአብሔር ምስሌኪ፡፡

እግዚአብሔር ከነፍስሽ ነፍስ ፤ ከሥጋሽ ሥጋ ነሥቶ ካንቺ ጋር አንድ ባሕርይ ሆኗልና፡፡ ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ አንድም እግዚአብሔር በጸጋ ቢያድርብሽ ባለሟልነትን አግኝተሻልና ደስ ይበልሽ፡፡

ተፈሥሒ እስመ ተወከፍኪ ቃሎ ለመልአክ ፍሥሓ ኩሉ ዓለም፡፡

የሰው ሁሉ ደስታ የሚሆን የመልአኩን ቃል ፤ እንደ ኒቆዲሞስ ሳትከራከሪ እንደ ዘካሪያስ ሳትጠራጠሪ አምነሻልና ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡ ሰብአ ፊንቆን ተወክፍዎ ፤ ወእለሰ ተወክፍዎ ወሀቦሙ ሥልጣነ እንዲል ፍሥሐ ኩሉ ዓለም ያለውን ለመልአክ ቢቀጥሉ ምስጋናው ተፈሥሒ ተፈሥሒ እያለ ነውና ቃል ላለው ቢቀጽሉ ወነዋ ተወልደ ፍሥሐ ዘይከውን ፣ ለክሙ ለኩሉ ዓለም ይለዋልና፡፡

ተፈሥሒ ኦ ወላዲተ ፈጣሬ ኩሉ ዓለም።

ሃያውን ዓለም የፈጠረ ጌታን የወለድሽው ተፈሥሒ ደስ ይበልሽ፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

ሃያውን ዓለም ከፈጠረ ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን አይምዕሮውን
ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን::
2👍1
ምእመናን ሆይ

ቅድስት ድንግል ማርያም

የኖኅ የድኅነት ማደሪያ ፣
ሦስት ገዥዎች እነርሱም አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ በውስጧ የከተሙባት የአብርሃም ድንኳን ናት።

ቅድስት ድንግል ማርያም ከምድር እስከ ሰማይ ተዘርግታ የፍጥረቱ ሁሉ ንጉሥ የሚጠጋባት የያዕቆብ የእሳት መሰላል ናት።

ቅድስት ድንግል ማርያም እግዚአብሔር ከሰው ጋር ያደረባት የሙሴ የምስክር ድንኳን ናት።

ቅድስት ድንግል ማርያም የኢያሱ የምስክር ሐውልት (የማዕዘን ድንጋይ) ናት።

ቅድስት ድንግል ማርያም ያበበችና የፈራች ባለርስቶች ያወቋት የአሮን በትርና ማዲጋ ናት።

ቅድስት ድንግል ማርያም የሳሙኤል የረድኤት አለት ፣ በንጉሥ ቀኝ የምትቀመጥ የዳዊት ንግሥት ናት።

ቅድስት ድንግል ማርያም
በኪሩቤል ክንፎች የምትጋረድ የሰሎሞን መቅደስ ናት።

ቅድስት ድንግል ማርያም
የሕዝቅኤል የተዘጋች የምሥራቅ በር ደጅ ናት።

ደጅ :- ማለት የምሕረት መግቢያ ማለት ነው።
ምሥራቅ :- ማለት የፀሐይ መውጫ ማለት ነው። መግቢያዎቹም :- ኮከቦች ናቸው።
እነዚህም ኮከቦት:- የጻድቃን ነፍስ ናቸው።

ቅድስት ድንግል ማርያም የነፍስ ሁሉ ምግብ የሆነ የመንፈስ ቅዱስ አዝመራ በውስጧ ያለባት

የዮሴፍ የስንዴ መዝገብ ናት።

ቅድስት ድንግል ማርያም የኢሳይያስ የተጠማች ምድር ናት።


የእመብርሃን አማላጅነት❤️ ረድኤት በረከት አይለየን🙏
🙏5👏2
የእግዚአብሔር ቤተሰቦች

ሰው እኮ ኑሮው እንደ አሳ ነበር

አሳ ሲዋኝ ድምፁን ሰምቶ የሚያወቅ አለ? የለም

የሰው ልጅ ም በሀጢአት ወድቆ ሳለ ፀሎቱ አይሰማም ነበረ።

ስለዚህ

ምዕራገ ፀሎት እመቤታችን ❤️ ስትወለድ ስትመጣ

ብሶታችን ተሰማልን
የወይኑ( የመርገሙ) አተላ ተጠረገ እና አዲስ ውኃ ተሾመብን
አዲስ ወይን ጣፈጠልን
አዲስ ወይን ተሰጠን

ጣዕመ ቢሱን አለም የለወጠችው እመቤታችን ድንግል ማርያም ናት ።

የእመቤታችን እረድኤት በረከት አይለየን 🙏
12🙏1
የሲና ሐመልማል የሙሴ ፅላት
7
በእግዚአብሔር ስዕል  የተሳሉ
የተፃፈበሽ በኪዳን ሁሉ
ታላቋ መቅደስ ኪሩቤል የጋረዱሽ
ያለመለወጥ ንፅህት ማርያም ነሽ

ወደ ቀደመ ክብሩ ሊመለስ
የጠፋው አዳም መዳኛው ሲደርስ
ሰማይ ከምድር ዳግም ሊስማማ
ባንቺ ሰፈረ የውሉ ፊርማ (፪)
8👍1
ተወዳጆች

መሶበ ወርቅ

መሶበ ወርቅ በእመቤታችን ይመሠላል
መሶብ ህብስቱን መያዙ እመቤታችንጌታችንን በማህፀኗ መያዟ
ከዚያም አቅፉ ጡቶቿን እያጠባች ማሳደጓ ፤
መና ክርስቶስ የተገኘበት ምሳሌ ነው
🙏8
ተወዳጆች

የቅዱስ ያሬድ ምሥጋና

ድንግል ሆይ ድንቅ ለሚሰኘው የተዋሕዶ ምሥጢር
መድኃኔአለም ኢየሱስ ክርስቶስ ካንቺ በመወለዱ ፤
ሰማያት ተደሰቱ ምድርም ሐሤት አደረገች

የእመብርሃን ልመናዋ ክብሯ የልጇ ቸርነት አይለየን🙏
🙏8👍2
ተወዳጆች ሆይ

ሁሉ ቢተወን እመቤታችን ግን ታየናለች
እመቤታችን ማንንም ነው ምትሰማው ማትንቀው
የሰውን ችግር ታውቃለች እመቤታችን
ከልቤ ነው የምነግራችሁ

አሁን እናንተ የሚመሰላችሁ
አላውቅም ምን እንደሚመስላችሁ
ይሄ ትዕቢት ስለሆነ ማለት ነው

ብቻ ብዙዎቻችን ግን ሚመሰለን
እመቤታችን የሆኑ ሰዎችን ምትረዳቸው
እኛን ደሞ ማትረዳን ነው የሚመስለን

እንደው ለኛ ለኛ ማናሳዝናት
ይመስላችኋል አይደለም
የማንም ችግር ያሳዝናትል
የማንም ችግር እውነት ከልቤ ነው

ማንም ሰው ሳያይላችሁ
ቀድማ የምታይላችሁ እመቤታችን ናት

ይሔው ቃና ዘገሊላ ላይ
ሁሉም ሰው ከዚህ ቅዳ
ስጥ ለእንግዳ እያለ ይቆርጣል እንጂ

ማን ጠጅ ማለቁን አይቷል
እሷ እኳ ናት ጓዳቸውን ያየችላቸው

ማንም አልተረዳም ነበር
እርሱ ግን እያወቀ ትቶት ለምን
የእመቤታችን ክብር እንዲገለጥ

አምላክ ነው እሱ ያውቃል

ር ዕሰ ሊቃውንት አባገብረ ኪዳን❤️
10👍7
ተወዳጆች

እኔ

እመቤታችንን እንኳን በገሀድ አይተናት
እንደው በህልማችንም አይተን በሞትን
እንዴት ያለች ውብ ናት ፈጣሪ እንዴት አድርጎ ወደዳት
እንዴት ያለች መልከኛ ናት
መላእክት እኮ ሳስተውላታል

ለቅዱስ ሚካኤል እና ለቅዱስ ገብርኤል


ተመልከቱ አዳምን ፈጥሬ ማድነው በዚች ነው ብሎ
ከክንፋቸው ላይ ሳለላት
ስሎ ቢያሳያት ኧረ ቶሎ ፍጠርልን ኧረ ቶሎ ፍጠራት
ናፍቃናለች ለኛም እህት እንድትሆነን
በንፅህና እንድትመስል ቶሎ ፍጠርልን


ሚካኤል መልአክ በክንፉ ፆራ የተባለች ለዚህ ነው


በክነፉ ፁሮ ክንፋቸው ላይ ስሎ አሳይቷቸዋል
እና ገና ሳያገኟት ሳትወለድ ነበር ሚወዷት
በዚህ ዓለም ላይ የእመቤታችን ፍቅር
እንደ ውሃ የፈሰሰለት ሰው የታደለ ነው

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ለዚህ ነው

ፍቅርሽ እንደ ወይን እና ውሃ በልቤ ውስጥ ተቀላቅሏል
ወይን እና ውሃ ከተቀላቀለ በኋላ
ይሔ ወይን ነው ይሔ ውሃ ነው አይባልም


እኔን ከማርያም ፍቅር ለይቶ ማሳየት የሚችል የለም

እንዴት አድርጎ ቢወዳት ነው እናንተ
እንዴት አድርጌ ላመስግንሽ ይሆን ? አለ
ምን ላድርግ ? ፀጉሬ እንኳን
አፍ አውጥቶ በዚምርልሽ አይበቃሽ ይላታል
ዝም ብዬ ቡርክት ቡርክት ቡርክት እልሻለሁ ይላል።

ስሟ እግዚአብሔር እንዳመሰገነው የከበረ ይሁን ።

ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❤️
13🙏2🥰1
ተወዳጆች

↘️መኃልየ መኃልየ ዘሰሎሞን

መኃ 4፥12፦ <<እህቴ ሙሽራ
የተቆለፈ ገነት
የተዘጋ ምንጭ
የታተመም ፈሳሽ ናት

↘️አንድምታ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዘላለማዊ ድንግል ነች ሲል ነው ፣ ቅድመ ዓለም በእግዚአብሔር ታስባ የነበረች ኋላም በሃሳብና በሥራ ንጽህት ድንግል የሆነች ስለሆነ የተቆለፈ ገነት የተዘጋ ምንጭ የታተመም ፈሳሽ ናት ሲል ምሥጢር ነግሮናል

ረድኤቷ በረከቷ አይለየን
የፀሓይ ብርሃን በጠቢባን ጥበብ ይሰፈራል፤ የጨረቃም ውበት ይመጠናል፤ ሰማይና ምድር በአድማስ፣ ባሕርም በናጌብ ይወሰናል።

የእመቤታችንን ክብር ግን መመጠንና መወሰን ይቅርና ማን ሊመረምረው ይቻለዋል? 'ሊቁ መኑ ዘይክል ነቢበ ዕበይኪ” እንዳለ ገናንነትሽን ማን ይናገራል እያልን ስለ እሷ የተነገረውን ሁሉ በመደነቅ እናነባለን።

ሊቃውንቱ ለእመቤታችን ውዳሴ በመጽሐፍ የሚያኖሩት ለኀሊና ማቅኛ እንዲሆን ነው እንጅ ከዚያ በኋላስ ኅሊና አስቦ ወደማይደርስበት ጥልቅ ባሕረ ውዳሴ መግባት ነው።

የአበቦችን ውበት በምድረ በዳ፣ ከዋክብትን በሰማይ ላይ በጥበቡ የገለጠ አምላክ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምንም በሊቃውንት እንደበት ይገልጣታል።

ቅዱስ ኤፍሬምን አፈ በረከት ቅዱስ ዮሐንስን አፈ ወርቅ ያሰኛቸው የድንግል እመቤታችን ውዳሴ ነው።

እስከ ዕለተ ምጽእት የሚነሣው ትውልድ እንዲያመሰግናት በትንቢት የተነገረላት ሉቃ 1:48 ይፈጸም ዘንድ ዛሬ ባሉ የቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት እንደበትም በጉባኤ፣ በማኅሌት፣ በቤተ መቅደስ ትመሰገናለች።

ርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን እመቤታችን "ያስተበፅዑኒ ኩሉ ትውልድ” ብላ ከተናገረችላቸው አንዱ ናቸው። ለዚህም ምስክሬ ትምህርታቸው ነው።

በዐውደ ምሕረት "የምድር ጌጥ ይሏታል። በጉባኤ ቤት “ብርሃንኪ የዐቢ እምብርሃነ ፀሐይ” ይሏታል።

በበዐታቸው "ሰአሊ ለነ ቅድስት'' ይሏታል። ዛሬ ደግሞ ተነቦ የማይጠገብ ውዳሴዋን በመጽሐፍ አቅርበውልናል።

ይሄ መጽሐፍ በትውፊት የምናወርሰው፥ ነገር ግን እያየነው የተደረሰ አዲሱ አርጋኖን ነው።

ቅድመ ዓለም በአምላክ ኅሊና ከታሰበው ድኅረ ዓለም በነቢያት እስከተነገረው፣ በመላእክት ከተዘመረው በሐዋርያት እስከተሰበከው ሊጠቀስ የሚገባው ተጠቅሷል።

የእመቤታችን ነገር ሐረግ ነው፤ በነካነው ጊዜ ሁሉ ብሉያትን ሐዲሳትን ሊቃውንትን ያንቀሳቅሳል።

ርእሰ ሊቃውንት እንደ ሐረግ ሳቢ አንድ ጥቅስ በመዘዙ ጊዜ የመጻሕፍት ሁለንተናቸው ይንቀሳቀሳል።

ከብሉይ ኪዳን ጀምሮ በእግዚአብሔር መንፈስ የተጻፈ መጽሐፍ ሁሉ እመቤታችን የሌለችበት መጽሐፍ አይገኝም።

ይህን መጽሐፍ ባነበባችሁ ጊዜ ይህንን እውነት ትረዱታላችሁ። "አሐቲ ድንግል" አንድ መጽሐፍ ብቻ አደለም።

ትርጓሜ፤ ድርሳን፤ ምዕላድ፤ ውዳሴም ነው።

ሁልጊዜ የርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳንን ስብከት ስሰማ የምመኘው ይህንን መጽሐፍ ነበር።

አንዳንዴ ስብከት መሆኑን ረስቼ መጽሐፍ የሚያነቡልኝ ይመስለኝ ነበርና። እነሆ የተመኘሁት መጽሐፍ በብራና ተጠቅሎ በቤተ መጻሕፍት ተጥሎ አገኘነው። ከእኔ ጋራ የተወለደውን የመጻሕፍት ንጉሥ ታዩ ዘንድ ኑ!

ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የ፬ቱ ጉባኤያተ መጻሕፍት ምስክር መምህር
👍62
2025/10/27 03:24:30
Back to Top
HTML Embed Code: