ተወዳጆች ሆይ
ሹመትም አይኑራችሁ እውቀትም አይኑራችሁ
ጤናም አይኑራችሁ ሀብትም አይኑራችሁ
ማርያም ስላለችልን ብቻ ደስ ሊለን ይገባል።
እሷ ስላለችን ይበቃናል ።
የ አክል ሐይማኖት ዘአልቦ ጥልቀት ወእምነት
በ ቅድስት ድንግል ከመ ይዕቲ ወላዲተ አምላክ
✅ ዘአልቦ ጥልቀት አለ
ጥርጥር የሌለበት ሐይማኖት ለምንም ነገር ይበቃል።
ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ብሎ ማመን ለሁሉም ይበቃል
ለልብስ ይበቃል ክርስቶስን እንለብሳለን
ለምግብ ይበቃል የህይወት እንጀራ ልጇን እንበላለን።
ለጥበቃ ይበቃል መልካም እረኛ ልጅ አላትና በእሷ ይጠብቀናል ።
ስለዚህ ምንም የሚጎልብን ነገር የለም
ሰው ማርያምን ከወደደ የሚያጣው ነገር የለም ።
✅ መለመን ያለብን
የእናትህን ፍቅር ጨምርልን ብለን ነው
መፀለይ ካለብን እሷን ነው
በኃጢአት የመረረው ህይወታችን ሊጣፍጥ የሚችለው
ጥዕምተ ስም ማርያም በልቡናችን ያደረች እንደሆነ ነው
✅ እሷ ስታድርብን
መራራው ንቅል ንቅል ንቅል እያለ ይጠፋል
መራራውን ህይወታችን
መራራውን ኃጢአታችን
በእናቱ በጣፈጠው ሥሟ ነቅሎ ይጣልልን 🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
Share
👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/uraman4u12
https://www.tg-me.com/uraman4u12
https://www.tg-me.com/uraman4u12
ሹመትም አይኑራችሁ እውቀትም አይኑራችሁ
ጤናም አይኑራችሁ ሀብትም አይኑራችሁ
ማርያም ስላለችልን ብቻ ደስ ሊለን ይገባል።
እሷ ስላለችን ይበቃናል ።
የ አክል ሐይማኖት ዘአልቦ ጥልቀት ወእምነት
በ ቅድስት ድንግል ከመ ይዕቲ ወላዲተ አምላክ
✅ ዘአልቦ ጥልቀት አለ
ጥርጥር የሌለበት ሐይማኖት ለምንም ነገር ይበቃል።
ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ብሎ ማመን ለሁሉም ይበቃል
ለልብስ ይበቃል ክርስቶስን እንለብሳለን
ለምግብ ይበቃል የህይወት እንጀራ ልጇን እንበላለን።
ለጥበቃ ይበቃል መልካም እረኛ ልጅ አላትና በእሷ ይጠብቀናል ።
ስለዚህ ምንም የሚጎልብን ነገር የለም
ሰው ማርያምን ከወደደ የሚያጣው ነገር የለም ።
✅ መለመን ያለብን
የእናትህን ፍቅር ጨምርልን ብለን ነው
መፀለይ ካለብን እሷን ነው
በኃጢአት የመረረው ህይወታችን ሊጣፍጥ የሚችለው
ጥዕምተ ስም ማርያም በልቡናችን ያደረች እንደሆነ ነው
✅ እሷ ስታድርብን
መራራው ንቅል ንቅል ንቅል እያለ ይጠፋል
መራራውን ህይወታችን
መራራውን ኃጢአታችን
በእናቱ በጣፈጠው ሥሟ ነቅሎ ይጣልልን 🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
Share
👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/uraman4u12
https://www.tg-me.com/uraman4u12
https://www.tg-me.com/uraman4u12
❤5👍5
ድንግል ሆይ
የሚበላውን ያፈራሽልን የሚጠጣውን ያስገኘ ሽልን ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ኅብስት
በማመን ከርሱ ለሚቀበሉ
ሕይወትንና ደኅንነትን የሚሰጥ ነው ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ኅብስት
በማመን ከርሱ ለማይቀበሉ ሰዎች
የማይላመጥ ጽኑ ነው
ይኸውም ኃያል የሚሆን የአድማስ ደንጊያ ነው ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ጽዋ በማመን
ከርሱ ለሚጠጡ ሰዎች
ጥበብን የሚገልጽ ሕይወትንም የሚሰጥ ነው ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ጽዋ በማመን
ከርሱ ለማይጠጡ ሰዎች
የሚያሰክርና የሚያፍገመግም
የሚጥልና ኃጢአትን ስለሚያስተው ፈንታ
ኃጢአትን የሚጨምር ነው ።
አሁንም ላንተ ምስጋና ይገባሃል ።
ለመንግሥትህም ምስጋና ይገባል እያልን እናመስግነው
ከንጹሕ ዕጣን ጋራ ምስጋናን እናቀርብልሃለን ።
ቅዳሴ ማርያም❣️
የሚበላውን ያፈራሽልን የሚጠጣውን ያስገኘ ሽልን ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ኅብስት
በማመን ከርሱ ለሚቀበሉ
ሕይወትንና ደኅንነትን የሚሰጥ ነው ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ኅብስት
በማመን ከርሱ ለማይቀበሉ ሰዎች
የማይላመጥ ጽኑ ነው
ይኸውም ኃያል የሚሆን የአድማስ ደንጊያ ነው ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ጽዋ በማመን
ከርሱ ለሚጠጡ ሰዎች
ጥበብን የሚገልጽ ሕይወትንም የሚሰጥ ነው ።
✅ ወዮ ከአንቺ የተገኘ ጽዋ በማመን
ከርሱ ለማይጠጡ ሰዎች
የሚያሰክርና የሚያፍገመግም
የሚጥልና ኃጢአትን ስለሚያስተው ፈንታ
ኃጢአትን የሚጨምር ነው ።
አሁንም ላንተ ምስጋና ይገባሃል ።
ለመንግሥትህም ምስጋና ይገባል እያልን እናመስግነው
ከንጹሕ ዕጣን ጋራ ምስጋናን እናቀርብልሃለን ።
ቅዳሴ ማርያም❣️
👍5🙏4❤1
በዚህ አለም ላይ
ተወዳጆች ሆይ
የእመቤታችን ፍቅር❣️
እንደውሃ የፈሰሰለት ሰው የታደለ ነው።
✅ አባ ጊዮርጊስ ለዚህ ነው
ፍቅርሽ እንደ ወይን እና እንደ ውሃ በልቤ ውስጥ ተቀላቅሏል
ወይን እና ውሃ ከተቀላቀለ በኋላ
ይሄ ወይን ነው ይሄ ውሃ ነው ማለት አይቻልም
እኔን ከማርያም ፍቅር ለይቶ ማሳየት የሚችል የለም
እንዴት አድርጎ ቢወዳት ነው እናንተ
እንዴት አድርጌ ላመስግንሽ ይሆን አለ
✅ ምን ላድርግ ?
ፀጉሬ እንኳን አፍ አውጥቶ ቢዘምርልሽ አይበቃሽም ይላል
ስለዚህ ዝም ብየ ቡርክት ቡርክት ቡርክት እልሻለሁ ይላል።
አምላክ እናቴ ያላትን እኔ እናቴ ላልላት ነው እንዴ
ፈጣሪ እናቴ ካላት እኔማ ሎሌሽ ነኝ ብላት
ኧረ! እናትም የሆነችን በቸርነቷ ነው
✅ አንደኛ
የእግዚአብሔር ቸርነት ይገርማል
የእሱን እናት እኛም እናታችን ስንል
ለነገሩ ፈጣሪ ቅናት የለበት አይደል
እንጂማ የአምላክን እናት
እናቴ ማለትኮ እራሱ ትዕቢት እኮ ነው
ትዕቢት ነው አዛኘን
✅ ሁለተኛ ደግሞ
የሷም ደግነት
እኔ አንተን ልጄ ባልኩበት
ዘማያውያንን ሁሉ ልጄ አልልም አለማለቷ
የረከሱት ሁሉ እናቴ ማርያም አይሉኝም
እንዳይሉኝ ከልክላቸው አለማለቷ
የምድር ንግስት ብትሆን እኮ
ዞርበል ያንተ እናት አይደለሁም ትለን ነበር።
✅ እሷ ግን
ቸር እናት ስለሆነች
የመሀሪው እናት ፣ እርህርሂት ማርያም
የውሻ ያዘነች ስለሆነች እናታችን ስንላት አናፍርም
እናትነቷ ሲበዛብን እንጂ
የፈጣሪን እናት እናት እንድትሆነን የፈቀደልን እግዚአብሔር
ስሙ የተመሰገነ ይሁን አሜን አሜን አሜን 🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
ተወዳጆች ሆይ
የእመቤታችን ፍቅር❣️
እንደውሃ የፈሰሰለት ሰው የታደለ ነው።
✅ አባ ጊዮርጊስ ለዚህ ነው
ፍቅርሽ እንደ ወይን እና እንደ ውሃ በልቤ ውስጥ ተቀላቅሏል
ወይን እና ውሃ ከተቀላቀለ በኋላ
ይሄ ወይን ነው ይሄ ውሃ ነው ማለት አይቻልም
እኔን ከማርያም ፍቅር ለይቶ ማሳየት የሚችል የለም
እንዴት አድርጎ ቢወዳት ነው እናንተ
እንዴት አድርጌ ላመስግንሽ ይሆን አለ
✅ ምን ላድርግ ?
ፀጉሬ እንኳን አፍ አውጥቶ ቢዘምርልሽ አይበቃሽም ይላል
ስለዚህ ዝም ብየ ቡርክት ቡርክት ቡርክት እልሻለሁ ይላል።
አምላክ እናቴ ያላትን እኔ እናቴ ላልላት ነው እንዴ
ፈጣሪ እናቴ ካላት እኔማ ሎሌሽ ነኝ ብላት
ኧረ! እናትም የሆነችን በቸርነቷ ነው
✅ አንደኛ
የእግዚአብሔር ቸርነት ይገርማል
የእሱን እናት እኛም እናታችን ስንል
ለነገሩ ፈጣሪ ቅናት የለበት አይደል
እንጂማ የአምላክን እናት
እናቴ ማለትኮ እራሱ ትዕቢት እኮ ነው
ትዕቢት ነው አዛኘን
✅ ሁለተኛ ደግሞ
የሷም ደግነት
እኔ አንተን ልጄ ባልኩበት
ዘማያውያንን ሁሉ ልጄ አልልም አለማለቷ
የረከሱት ሁሉ እናቴ ማርያም አይሉኝም
እንዳይሉኝ ከልክላቸው አለማለቷ
የምድር ንግስት ብትሆን እኮ
ዞርበል ያንተ እናት አይደለሁም ትለን ነበር።
✅ እሷ ግን
ቸር እናት ስለሆነች
የመሀሪው እናት ፣ እርህርሂት ማርያም
የውሻ ያዘነች ስለሆነች እናታችን ስንላት አናፍርም
እናትነቷ ሲበዛብን እንጂ
የፈጣሪን እናት እናት እንድትሆነን የፈቀደልን እግዚአብሔር
ስሙ የተመሰገነ ይሁን አሜን አሜን አሜን 🙏
ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን❣️
👍5🙏5❤1
ተወዳጆች
የድንግል ማርያም እራስ ግን እግዚአብሔር ነው
ህሊናዋ ውስጥ ከእግዚአብሔር ውጭ አስባ አታውቅም
ስለዚህ ምን ትባላለች ? የእግዚአብሔር ከተማ ትባላለች
የድንግል ማርያም እራስ ግን እግዚአብሔር ነው
ህሊናዋ ውስጥ ከእግዚአብሔር ውጭ አስባ አታውቅም
ስለዚህ ምን ትባላለች ? የእግዚአብሔር ከተማ ትባላለች
❤11👍2
ተወዳጆች
አለም ሁሉ ተደምሮ
የአንዷን የፀጉሯን ዘላላ ያህል ክብር የለውም
የአንዷን የፀጉሯን ዘላላ
አሁን ስለ እመቤታችን ስለምኗ ትናገራላችሁ ?
ሰው ስለምኗ ይናገራል ?
ስለ እናትነቷ ቢናገር ድንግል ትሆንበታለች
ስለ ድንግልናዋ ቢናገር እናት ትሆንበታለች
እናትነቷን ብቻ ልናገር ቢል አይሆንለትም
አምላክን መውለድ እንደምን ያለ ነገር ነው
ይሄ እስከዛሬ ድረስ አይገባንም
ከገባንማ ነገሩም ቀላል ነው ማለት ነው ።
አለም ሁሉ ተደምሮ
የአንዷን የፀጉሯን ዘላላ ያህል ክብር የለውም
የአንዷን የፀጉሯን ዘላላ
አሁን ስለ እመቤታችን ስለምኗ ትናገራላችሁ ?
ሰው ስለምኗ ይናገራል ?
ስለ እናትነቷ ቢናገር ድንግል ትሆንበታለች
ስለ ድንግልናዋ ቢናገር እናት ትሆንበታለች
እናትነቷን ብቻ ልናገር ቢል አይሆንለትም
አምላክን መውለድ እንደምን ያለ ነገር ነው
ይሄ እስከዛሬ ድረስ አይገባንም
ከገባንማ ነገሩም ቀላል ነው ማለት ነው ።
🥰4❤2
እመብርሃን ሆይ
ሰወነቴም የወደደችው ነገር ቢኖር አንቺን እለምናለሁ፡፡ በመታመን የሻትሁትንና የተመኘሁትንም ባንቺ አገኛለሁ ።
መታመን ያድናል ሃይማኖትም ያስቀናል መታመን ያነጻል፡፡ ሃይማኖትም ያራቅቃል መታመን ተስፋ ያደርጋል ሃይማኖትም ይሰጣል፡፡ መታመን ይጀምራል ሃይማኖት ይፈጽማል፡፡
የ ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን🙏
ደስ ብሰኝ ባንቺ ደስ እሰኛለሁ፡፡ ባዝንም ባአንቺ እጽናናለሁ፡፡ መከራና ችግርም ቢያገኘኝ ወዳንቺ እጮሃለሁ፡፡ያመፀኛም ምላስ ቢያስከፋኝ ወዳንቺ ፊት እማለላለሁ፡፡ሰወነቴም የወደደችው ነገር ቢኖር አንቺን እለምናለሁ፡፡ በመታመን የሻትሁትንና የተመኘሁትንም ባንቺ አገኛለሁ ።
መታመን ያድናል ሃይማኖትም ያስቀናል መታመን ያነጻል፡፡ ሃይማኖትም ያራቅቃል መታመን ተስፋ ያደርጋል ሃይማኖትም ይሰጣል፡፡ መታመን ይጀምራል ሃይማኖት ይፈጽማል፡፡
የ ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን🙏
❤10🙏2👍1
የዓለም ሁሉ መመኪያ
ድንግል እናት ሆይ
ከሚያሰጥመው ካመፀኛ አፍ በደምም ከሰከረች ምላስ አድኝኝ፡፡
መንፈሳዊት መርከብ ሆይ ድንግልናዊት መፆር ሆይ
ከክፉ ዘመን መከራ አድኝኝ፡፡
የሁላችን መመኪያ የመድኃኒት ሽቱ ብልቃጥ ያለ ርኩሰት ሙሽራ ሆይ
ከቀን ወራሪ ከሌሊት ሰባሪ አድኝኝ፡፡
የእመብርሃን አማላጅነት አይለየን🙏
ድንግል እናት ሆይ
ከሚያሰጥመው ካመፀኛ አፍ በደምም ከሰከረች ምላስ አድኝኝ፡፡
መንፈሳዊት መርከብ ሆይ ድንግልናዊት መፆር ሆይ
ከክፉ ዘመን መከራ አድኝኝ፡፡
የሁላችን መመኪያ የመድኃኒት ሽቱ ብልቃጥ ያለ ርኩሰት ሙሽራ ሆይ
ከቀን ወራሪ ከሌሊት ሰባሪ አድኝኝ፡፡
የእመብርሃን አማላጅነት አይለየን🙏
🙏7❤1
"ድንግል ሆይ
አንገታቸውን እንደሚያገዝፉ እንደ ዕብራውያን ሴቶች ልጆች በዋዛ ያደግሽ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና በቤተ መቅደስ ኖርሽ እንጂ፤
ድንግል ሆይ
ምድራዊ ኅብስትን የተመገብሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የበሰለ ሰማያዊ ኅብስትን ነው እንጂ፤
ድንግል ሆይ
ምድራዊ መጠጥን የጠጣሽ አይደለም፤ ከሰማየ ሰማያት የተቀዳ ሰማያዊ መጠጥን ነው እንጂ፤
ድንግል ሆይ
ከአንቺ አስቀድሞ ከአንቺም በኋላ እንዳሉ ሴቶች መተዳደፍን የምታውቂ አይደለም፤ በንጽሕና በቅድስና ያጌጥሽ ነሽ እንጂ፤
ድንግል ሆይ
የሚያታልሉ ጐልማሶች ያረጋጉሽ አይደለም የሰማይ መላእክት ጐበኙሽ እንጂ እንደተነገረ ካህናትና የካህናት አለቆች አመሰገኑሽ እንጂ....."
(አባ ሕርያቆስ - ቅዳሴ ማርያም)

🙏7👍3
ድንግል ሆይ
አንቺ የተባረክሽ ዕፅ ነሽ የሕይወትና የደህነት ዕፅ ነሽ፤
በገነት ውስጥ ባለው ዕፅ ሕይወት ፈንታ
በዚህ ዓለም የሕይወት ዕፅ ሆነሽ፤
ፍሬሽም የሕይወት ፍሬ ነው::
በሚወዱት (በሚያውቁት) በዓለም ሰዎች ዘንድ የሚሽት
መልካም መዓዛ ያለው አበባ ካንቺ ታየ፡፡
ይኸውም ከርቤ፣ሚዓ፤ ስሊክ የተባሉ ሽቶች በልብሶችሽ ላይ አሉ፡፡ ብሎ በበገና ነቢዩ ዳዊት ትንቢት የተናገረልሽ ነው::
ቅድስት ሆይ ልጅሽ ይቅርታውን ያድለን ዘንድ ለምኝልን🙏

❤9👍2🙏1
ለሰው ልጆች ሁሉ ታላቅ ስጦታ የሆነውን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን እንድትወልድ ከሴቶች ሁሉ በላይ ተመረጠች።
ቅድስተ ቅዱሳን እናታችን፣ በአክብሮት ቴዎቶኮስ ተብላ ትጠራለች፣ አምላክ የተሸከመች፣ እንዲሁም ከፍ ያለ ክብር ያለው ፓናጊያ የሚል ስያሜ አግኝታለች።
"ፓናጊያ" የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ሁሉ-ቅዱስ" ወይም "እጅግ ቅዱስ" ማለት ነው። የሰው ልጆች አዳኝ ኢየሱስ ክርስቶስን የወለደች ቅድስተ ቅዱሳን እናታችን የአምላክ እናት በመሆን ወደር የለሽ ንጽህና እና ቅድስናን የሚያመለክት በመሆኑ የተሰጠ ስያሜ ነው። ቃሉ በእምነት ያላትን ከፍ ያለ ቦታ፣ ከቅዱሳን ሁሉ በላይ ያጎላል፣ እና በድነት ታሪክ ውስጥ ያላትን ልዩ ሚና ያጎላል። ቅድስተ ቅዱሳን እናታችንን በጥልቅ አክብሮት እናከብራታለን፣ እርሷን እንደ እምነት፣ ትህትና እና ታማኝነት የመጨረሻ አርአያ አድርገን እንገነዘባለን። "ፓናጊያ" በኦርቶዶክስ ውስጥ ማእከላዊ ቦታዋን ያንፀባርቃል, ከሁሉም ሴቶች መካከል በጣም የተባረከች እንደሆነች ያከብራታል.
☦

❤6👏4👍1
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ…!
"…ልዩ ከሆነች ድንግል ማርያም ይህ የአምላክ መወለድ ምን ይደንቅ? ቃልን ወሰነችው። ልደቱንም ዘር አልቀደመውም። በመወለዱም ድንግልናዋን አልለወጠም። ቃል ከአብ ያለ ድካም ወጣ። ከድንግልም ያለ ህማም ተወለደ። ሰብአሰገል ሰገዱለት። አምላክ ነውና ዕጣን አመጡለት። ንጉሥም ነውና ወርቅ አመጡለት። ስለኛ በፈቃዱ ለተቀበለው መዳኛችን ለሆነው ሞቱም ከርቤ አመጡለት። እርሱ ቸርና ሰውን ወዳጅ የሆነ አንድ እርሱ ብቻ ነው። ቅድስት ሆይ ለምኚልን።
"…ቤዛ ይስሐቅ በግዕ ከኅቱም ዕፀ ሳቤቅ እንደተገኘ፤ ለእስራኤልም በበረሀ ውስጥ ከኅቱም አለት ውኃ እንደ ፈለቀ፤ የተደነቀች የአሮን በትርም እንደለመለመችና እንደ አፈራች፤ በሶምሶንም እጅ ውስጥ ከአህያ መንጋጋ አጥንት ውኃ እንደ ፈሰሰ፤ እንዲሁ የጌታችን ልደት በኅቱም ድንግልና ሆነ። በዕፀ ጳጦስ ውስጥ እሳት እንደ ነደደች ዕፂቱም እንዳልተቃጠለች እንዲሁ የመለኮቱ እሳት ድንግልን አላቃጠላትም። ለእርሱም ከቸር አባቱ ከማሕየዊ መንፈስ ቅዱስ ጋር ጌትነት ክብር ምስጋና ሰጊድ ከርሱ ጋር በትክክልነት ይገባል ለዘላለሙ አሜን።
"…በዓለ ጌናን ስናከብር በኀዘን በመከራ፣ በጭንቅ፣ በራብና በጥም፣ በሰቀቀን፣ በስደት፣ በወኅኒ ቤት፣ በአልጋ ቁራኛ በደዌ ደኛ፣ በፅኑ ህመም ተይዘው፣ በየቤቱ፣ በየጎዳናው፣ በየሆስፒታሉና በፀበል ስፍራዎች ሁሉ ያሉትን፣ ከሞቀ ቤትና ንብረታቸው ተፈናቅለው በየጥሻው የወደቁትን በማሰብ፣ በመንከባከብ፣ በመጠየቅ፣ በመጎብኘትና ማዕድ በማጋራት ይሁን። ሀገራችን ኢትዮጵያንና ጎረቤቶቿን፣ መላውንም ዓለም ሁሉ ሰላማዊው ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ያድርግልን። አሜን።
"…እንኳን ለጌታችንና ለመድኃኒታችን ለአምላካችንና ለፈጣሪያችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰን‼

❤9👍5
ጸጋ ክብርን የተመላሽ ድንግል ሆይ
ከመግፋት ከመገፋት አድኝኝ፡፡
ቅድስና የተመላሽ ድንግል ሆይ
ከመበደል ሌላውንም ከመበደል አድኝኝ፡፡ ከደም አፍሳሽ አድኝኝ፡፡ እኔም ደግሞ የሌላውን ደም ከማፍሰስ ሠውሪኝ፡፡
የተድላ መፍሰሻ ድንግል ሆይ
ከሽንገላ አድኝኝ፡፡
ከሸንጋይም ደግሞ ሠውሪኝ፡፡
የምስጋና መፍሰሻ ድንግል ሆይ
ከሽሙጥ ከስድብ ከሚያስሽሟጥጥና
ከሚሰድብ ደግሞ ሠውሪኝ፡፡
የባለጸግነትና የክብር መፍሰሻ ድንግል ሆይ
ሰውን ከሰው ከማጣላት አድኝኝ፡፡ ሰውን ከሰው ከሚያጣላ ሐሰተኛ ደግሞ ሰውሪኝ
የሕይወት የመድኃኒት ምንጭ ሆይ
ከቂምና ከቅናት አድኝኝ
ከቂመኛ ከቀናተኛ ደግሞ አድኝኝ፡፡
የፈውስ መቅጃ የበረከት አዘቅት ድንግል ሆይ
ከፀብ ከክርክር አድኝኝ፡፡
ከሚጣላና ከሚከራከር አድኝኝ፡፡ እሳት የሚለብሱ ኪሩቤልና ሱራፌል
በመብረቅ ክንፍ የሚጋርዱሽ
የንጉሠ ነገሥት ማደሪያ የምትሆን የብርሃን ድንኳን ሆይ፡፡ በሕይወት በመድኃኒት ጋሻ ጋርጅኝ
ከአጋንንት ፍላፃ እንድድን፡፡

👍5
ድንግል ሆይ
ሐሰተኛ ከመሆን ሰውንም ከሰው ከማጣላት አድኝኝ፡፡
ዳዊት እንዲህ ብሏልና፡፡ ሐሰት የዓመፅ ሁሉ ራስ ነው፡፡
ድንግል ሆይ
ከመሰሰን ኃጢአት አድኝኝ በነገሥት መጽሐፍ እንዲህ የሚል ተጽፏልና፡፡ (መዝ ፳፯፣ ፲፪) (ዘፀአ ፳፣ ፲፮)ሴሰኝነት ታላቅ ኃጢአት ነውና፡፡
ድንግል ሆይ
ከነገረ ዘርቅ ዋዛ ፈዛዛውን ከንቱውንም ነገር ሁሉ ከመናገር ሠውሪኝ በወንጌል እንዲህ ይላልና ዋዛ ፈዛዛውን ከንቱውንም ነገር የሚናገር ሁሉ ኃጥእ ተብሎ ይፈረድበታል፡፡ ከነገርህም የተነሣ ትጸድቃለህና ከነገርህም የተነሣ ትኮነናለህ፡፡ (ዘፀአ ፳፣ ፲፬) (ማቴ ፲፪፣ ፴፯)
ድንግል ሆይ
ከሐዋርያት ትምህርት ከመውጣት ከማፋለስ አድኝኝ ልጅሽ እንዲህ ብሏቸዋልና እናንተን የሰማ እኔን የሰማ ነው፡፡ እናንተን እምቢ ያለ እኔን እምቢ ያለ ነው፡፡ የላከኝንም እምቢ አለ፡፡ (ማቴ ፲፣ ፵ ም ፲፰፣ ፭ ሉቃ ፲፣ ፲፮)
ጳውሎስ ደግሞ
እንዲህ አለ እናንተስ የኛን መንገድ ተከተሉ እኛም ካስተማርናቸሁ ትምህርት ሌላ ያስተማራችሁ ቢኖር የሰማይ መላክ ቢሆን ውጉዝ ይሁን፡፡ (ገላ ፩፣ ፰) ፲. ደግሞ እንዲህ አለ እኛ ካስተማርናችሁ ሌላ ትምህርት ብትማሩ የተወገዛችሁ ሁኑ፡፡ (ገላትያ ፩፣ ፱)
የቅድስት ድንግል ማርያም❣️ አማላጅነት አይለየን

👍4
ድንግል ሆይ
የኔ ምሕረት በልጅሽ ዘንድ ስላንቺ አይደነቅም
ስለ ስምሽም
የኔ ይቅር መባል በልጅሽ ዘንድ አይደነቅም
ስለ ጸሎትሽም
የኔን ኃጢአት ማቀለል በልጅሽ ዘንድ አይደነቅም፡፡
ስለ ልመናሽም
የኔን ዕዳ በደል ማቅለል በልጅሽ ዘንድ አይደነቅም
ባንቺ እታመናለሁ፡፡
በዚህ ዓለም
ከፀብ ከክርክር ከሞት ታድኝኝ ዘንድ
በሚመጣውም ዓለም
ማዕበል ሞገድ ከሚፈላው የእሳት ባሕር ታድኝኝ ዘንድ፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን❣️
የኔ ምሕረት በልጅሽ ዘንድ ስላንቺ አይደነቅም
ስለ ስምሽም
የኔ ይቅር መባል በልጅሽ ዘንድ አይደነቅም
ስለ ጸሎትሽም
የኔን ኃጢአት ማቀለል በልጅሽ ዘንድ አይደነቅም፡፡
ስለ ልመናሽም
የኔን ዕዳ በደል ማቅለል በልጅሽ ዘንድ አይደነቅም
ባንቺ እታመናለሁ፡፡
በዚህ ዓለም
ከፀብ ከክርክር ከሞት ታድኝኝ ዘንድ
በሚመጣውም ዓለም
ማዕበል ሞገድ ከሚፈላው የእሳት ባሕር ታድኝኝ ዘንድ፡፡
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት አይለየን❣️
🙏5❤3👍1