በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
"የእግዚአብሔርን ቃል የተናገሩአችሁን ዋኖቻችሁን አስቡ፥ የኑሮአቸውንም ፍሬ እየተመለከታችሁ #በእምነታቸው_ምሰሉአቸው። ኢየሱስ ክርስቶስ ትናንትና ዛሬ እስከ ለዘላለምም ያው ነው። ልዩ ልዩ ዓይነት በሆነ በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ.."
[ዕብ 13፡7-9]

"እውነታው ያለው በዓለም አቀፋዊቷ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እንጂ ሌላ በየትም አይደለም"
[ሄራንዮስ፡ Against heresies 3:4]
“..በቅብብሎሽ ውስጥ ከአባቶች የተቀበልነውን ትውፊት ለሁል ጊዜ አጥብቀን እንይዝ ዘንድ ይገባናል።"
[ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፡ On “Not Three Gods.” To Ablabius: par. 3]
@what_the_fathers_taught

ቫለንቲኑስ እና መርቅያኖስ የተባሉ ጥንታውያን ኖስቲክ መናፍቃን ነበሩ.. ከእነዚህና ከተከታዮቻቸው ጋር በተያያዘ በሰዓቱ የነበረው ሊቁ ቅዱስ ሄራንዮስ እንዲህ አለ፡
"የቫለንቲኑስ ተከታዮች ቫለንቲኑስ ከመምጣቱ በፊት አልነበሩም፤ እንዲሁም የመርቅያኖስ ተከታዮችም ከመርቅያኖስ በፊት አልነበሩም"
[against heresies 3:4:3] 120-180ዓም
ስለዚህም እንግዳ ትምህርታቸው በአባቶቻቸው በቫለንቲኑስ እና መርቅያኖስ መጀመሩን የሚያጠይቅ ንግግር ነው።
እኛም ይህንን ይዘን የዘንድሮዎችን ኖስቲኮች በተለይ ደግሞ "መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ" በሚለው ሃሳብ ሁሉም ስለሚስማሙ ይህንን ደግሞ ያገኙት ከማንም ሳይሆን ከሉተር ነውና እንዲህ ልንላቸው እንችላለን፡
"ከሉተር በፊት የሉተር ተከታዮች የሉም፤ ከካልቪንም በፊት የካልቪን ተከታዮች የሉም።"
ስለዚህም በሃዋርያት ሃዋርያውያን በክርስቶስ ክርስቲያን መባላቸው ቀርቶ በሉተር ሉትራን ይባሉ ዘንድ የግድ ነው።

#ማቴዎስ_ወንጌል 28፡19 "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም" ይላል አይልም..??
አንዳንድ ሰዎች ይህ ጥቅስ ተበርዟል ይላሉ.. በተለይ "ኦንሊ ጂሰስ" በመባል የሚታወቁት አካላት አውሳብዮስ የተባለ የታሪክ ጸሐፊን ንግግር በመያዝ ቃሉ የሚለው "በእኔ ስም አጥምቁ" እንጂ አሁን በመጽሐፍ ቅዱሳችን ባለው መልኩ "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም" አይልም ይሉናል። በእርግጥ እንደው "ኦንሊ ጂሰሶችስ" ለእምነታቸው መደገፊያ ብለው ይህንን ይላሉ እኔኮ በጣም የሚገርመኝ ከእነሱ ሰምተው ይህንኑ የሚደግሙት አንዳንድ ሙስሊሞች😭😭 አሁን እስቲ ጥምቀት በኢየሱስ ስም ቢሆን ከእስልምና ጋር ምን ያገናኘዋል..?? እንደው ሰው ያለው ነገር አይቅርብኝ አትበሉ..
ለማንኛውም እስቲ ይህንን ለመመለስ ከአውሳብዮስ በፊት የነበሩ አባቶችን ብቻ ከራሳቸው ከሃዋርያት ከተማሩ አባቶች ጀምረን ስለዚህ ቃል(ማቴዎስ 28፡19) የተናገሩትን እንመለከታለን፤ ከዛም ደግሞ በስተመጨረሻም ራሱን እነሱ የጠቀሱትን አውሳብዮስን እንደማስረጃነት እንጠቀመዋለን። ከዚያም ደግሞ ጥንታውያኑን እደ ክታባት(Manuscripts) ምን እንደሚሉ እንመለከታቸዋለን።
እኚህን ማስረጃዎች ስናስቀምጥ አስቀድመን ጽሑፋቸውን እናስቀምጥና ከሥር በየት ቦታ ላይ እንደተናገሩት እናስቀምጣለን..
👇👇👇👇👇👇
"ነቢያት እንዲህ ሲሉ ተናገሩ፡ 'ለእርሱ የሚጠብቀውን እስኪያገኝ ድረስ የአህዛብ ተስፋቸው እርሱ ነውና'(ዘፍ 49፡10) ይህም ያወጁት ቃል በወንጌል ውስጥ ጌታችን 'ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው' ባለ ጊዜ ተፈጸመ።"
[St Ignatius: to philadelphians, chap 9]
ሦስት አብ ወይም ሦስት ወልዶች ወይም ሦስት መንፈስ ቅዱሶች ያሉ አይደሉም ይልቁንም ጌታችን አህዛብን ደቀመዛሙርት ያደርጉ ዘንድ ሃዋርያትን ሲልክ 'በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ' ብሎ በማዘዝ ነው። ስለዚህም አንዱ አካል ሦስት ስም እንደኖረው አይደለም ወይም ደግሞ ሦስቱ አካላት ሥጋ ሆነው እንደመጡ አይደለም ይልቁንም እኩል ክብር ባላቸው በሦስቱ እንጂ።
[St Ignatius: to philipians, chap. 1]
"(ጌታ) እርሱም (ሃዋርያትን) እንዲህ አላቸው 'ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው'"
[St Irenaeus: against heresies 3:17:1]
"የጥምቀት ህግ ተደንግጓልና፤ ፎርሙላውም(እንዴት እንደምንጠመቅ) ተቀምጧልና፣ 'ሂዱ' አላቸው 'አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው'"
[tertulian: on baptism, chap 13]
"ጌታም ከትንሳኤው በኋላ ሃዋርያቱን ሲልክ በምን መልኩ ማጥመቅ እንዳለባቸው እንዲህ ሲል አስተማራቸው 'ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጠኝ፤ እንግዲህ ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው'"
[St Cyprian: epistle 72:5]
"እንዲህም ሲል ሃላፊነትን ሰጣቸው 'ሥልጣን ሁሉ በሰማይም በምድርም ተሰጠኝ፤ እንግዲህ ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው'"
[Lucius of Castra Gilba on The Seventh Council of Carthage under Cyprian]
"አምላክንና ጌታችን ኢየሱስ በራሱ አንደበት ደቀመዛሙርቱን እንዲህ ሲል አዘዛቸው 'ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ..'”
[Euchratius of Thena on The Seventh Council of Carthage under Cyprian]
"እኛ በእርግጥም የእውነት ህግ አለን ይህም ጌታ በመለኮታዊው ትእዛዙ ሃዋርያቱን 'ሂዱ አህዛብን ሁሉ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው' ያለው ነው።"
[Vincentius of Thibaris on The Seventh Council of Carthage under Cyprian]
አርጌንስ የማቴዎስ ወንጌል 28፡19ን ቀጥታ አሁን እኛ ጋር ባለው መልኩ ይጠቅሰዋል
[origen: Homilies on Genesis, hom. 13]
🔥ሰዎቻችን የሚጠቅሱትም አውሳብዮስ "በእኔ ስም አጥምቁ" በማለት እንደተናገረ አድርጎ የጻፈው መቼስ ከእነዚህ ሁሉ አባቶች ዘንድ ከነበረ መጽሐፍ ቅዱስ ለእሱ ለብቻው ሌላ ወርዶለት ሳይሆን "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጥምቁ" የሚለው መለኮታዊ ትእዛዝ የጌታችን የኢየሱስ ትእዛዝ ነውና "በእኔ ስም" ብሎ አውሳብዮስ መናገሩ.. ወይም ደግሞ አንዳንድ አባቶች "በኢየሱስ ስም" ቢሉ በኢየሱስ ትእዛዝ ለማለት እንጂ ሌላ አይደለም። ቃሉን ቀጥታ "በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም" በማለት ራሱ አውሳብዮስ ሲጠራው እንዲህ አለ፡
"ጌታችን ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን 'እንግዲህ ሂዱ አሕዛብን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችሁ አስተምሯቸው' በማለት እንዳዘዘ.."
[letter of Eusebius concerning the council of nicea, 3]
እደክታባቱስ ምን ይላሉ..??
ኮዴክስ ሳይናይቲከስ, ቫቲካነስ፣ አሌክሳንድሪያነስ እንዲሁም ሌሎችም ጥንታውያን የመጽሐፍ ቅዱስ እደክታባት ይህንን የሥላሴን የጥምቀት ፎርሙላ የያዙ ናቸው።
ማሳሰቢያ
- ኦንሊ ጂሰሶች እባካችሁን የማይመስል ነገር አታውሩ
- ሙስሊሞች እባካችሁን ሰው ያለው አይቅርብኝ አትበሉ

አባቶች በመስቀል ምልክት ስለማማተብ ምን አስተማሩ..??
ሃዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችንን ጨምሮ ጥንታውያን የሚባሉ አብያተ ክርስቲያናት ማለተም ካቶሊክ እንዲሁም የግሪክና የራሽያን ኦርቶዶክስ የመሳሰሉ ጥንታውያን ሁሉ በመስቀል ምልክት ሲያማትቡ ይታያል.. በክርስትና ስም ተከልለው በመስቀል ምልክት የማያማትቡት ያው ፕሮቴስታንቶች ብቻ ናቸው.. እስቲ ጥንታውያን አባቶች ስለዚህ ጉዳይ ምን ብለዋል የሚለውን የተወሰነ እንመልከት፡
ታድያ ግን የአባቶችን ምስክርነት ስናይ በመስቀል ምልክት ማማተብን አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት እንደው ከክርስቶስ ስራ ለይተው በማየት እንዳልሆነ ልንረሳ አይገባም.. ቤተ ክርስቲያን ስለ መስቀል ምልክት ስታስተምር ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን ያደረገው ሰይጣንንም የቀጠቀጠው በመስቀል ላይ ነውና መስቀል ለአጋንንት ውርደት ለክርስቲያኖች ክብር ሆኖ ቀርቷል.. ዛሬም ድረስ ይህ ምልክት አጋንንትን የሚያስደነግጥ እኛንም የሚያጽናና ነው። ከዚህ ከጌታ ሥራ ጋር ተያይዞ የክርስቶስ ሥራው ላመኑበት ዛሬም ድረስ በመስቀሉ በኩል ይሰራል የሚል ነው። ከዚህ ጋር ተያይዞ ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም እና አፍራት ሶርያዊው ከተናገረት እንነሳና በመስቀል ምልክት ማማተብ እንዳለብን ያስተማሩንን አባቶችን እንመለከታለን፡
✝️ "ሰይጣንን ድል በመንሣት በእርሱ(በመስቀል) እያዞራቸው በግልጥ አሳይቷቸዋልና(አሳፍሯቸዋልና) መስቀልን ባዩ ጊዜ በእርሱ ላይ የተሰቀለውን ያስታውሳሉ የእባቡንም አናት የቀጠቀጠውን እርሱን ይፈራሉ ስለዚህም #መስቀል_ለአማኞች_ምልክታቸው_ለአጋንንትም_አሸባሪያቸው_ነው።"
[ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፡ Catechetical Lecture 13፡ 36]
✝️ "ሙሴ መራራውን ውሃ በእንጨት አጣፈጠ፤ [የእኛ ክርስቶስ]ኢየሱስ ደግሞ መራራነታችንን በመስቀሉ ይህም በተሰቀለበት እንጨት አጣፈጠው። .... ሙሴ እጁን በመዘርጋት አማሌቃውያንን ረታ፤ [የእኛ ጌታ]ኢየሱስ በመስቀሉ ምልክት አጋንንትን ድል ነሳ"
[አፍራት: Of Persecution, 10]
✝️ "ልጄ ሆይ የምትሰራቸውን ሥራዎች ሁሉ #በህያው_መስቀል_ምልክት አትማቸው(አማትበህ ጀምር)፤ በመስቀል ምልክትም ሳታማትብ በፊት የቤትህን በር አልፈህ አትልውጣ፤ ስትበላም ይሁን ስትጠጣ፣ ስትተኛም ይሁን ስትራመድ፣ በቤትህ ውስጥም ሆነህ ይሁን ወይም በመንገድ ላይ፣ ወይም ሥራ በመፍታትም ጊዜ ቢሆን ይህንን ምልክት(የመስቀል) አትተው። እንደ እርሱ ያለ ጠባቂ የለም። በሥራዎችህ ሁሉ ፊት እንደ ግድግዳ ከለላ ይሆንሃል። አጥብቀውም ይይዙት ዘንድ #ይህንን_ለልጆችህም_አስተምር።"
[ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ፡ three homilies: on Admonition and Repentance, 17]
✝️ "#የመስቀልምልክት ባለበት.. አስማት ደካማ ነው ጥንቁልናም ብርታት የለውም"................. "ወደ እንጦንስም አንድ እጅጉን በአጋንንት የታሰረ ሰውን አመጡ እርሱም የክርስቶስን ስም ጠርቶ ሁለት ወይም ሦስት ጊዜ #በመስቀል ምልክት ሲያማትብበት ሰውዬው በዛው ሰዓት ድኖ ተነሳ"
[ቅዱስ አትናቴዎስ፡ Life of Anthony, 78 & 80]
✝️ "በዓለም ውስጥ ብዙዎች ተሰቅለው አልፈዋል ሰይጣን ግን በአንዳቸውም የደነገጠ አይደለም። ታድያ ግን ስለ እኛ የተሰቀለውን የክርስቶስን #የመስቀሉን_ምልክት እንኳ ገና ሲያይ ይንቀጠቀጣል።"
[ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፡ Catechetical Lecture 13፡ 3]
✝️ "በእጣቶቻችንም በግልጥ በማማተብ መስቀል ምልክታችን ይሁን። በማናቸውም ነገሮቻችን ላይ፤ በምንበላይ እንጀራም ላይ ይሁን በምንጠጣው ላይ፤ በምግባትና በመውጣታችን ቢሆን እንዲሁም ከመተኛታችንም በፊት፤ ስንቀመጥና ስንነሳ በመንገድም ሳለን ባለንበት ቦታ ሁሉ። ጠብቆቱ ሃያል ነው.. ለድሆች ያለ ዋጋ ለተማሙትም ያለ ፍጋት ነው። ጸጋው ከእግዚአብሔር ነው። መስቀል ለአማኞች ምልክት ለሰይጣን አሸባሪ ነው።"

✝️ "(ቅድስት ጳውላ ከዚህ አለም ልትለይና ወደላይኛው ቤት ለመሄድ በተቃረበችበት ደቂቃዎች "አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።" እያለች የዳዊትን መዝሙር ከዘመረች በኋላ ዝም አለች) እጇንም ወደ አፏ አንስታ በከንፈሯ ላይ በመስቀል ምልክት አማተበች"
[ቅዱስ ጄሮም፡ letter(to Eustochium) 108:29]
✝️ በየትኛውም እንቅስቃሴያችን፣ በመግባትና በመውጣታችን፣ ጫማና ልብሳችንን ስናደርግ፣ ስንታጠብ፣ ስንቀመጥ፣ መብራት እንኳን ስናበራ በማንኛውም ሁኔታ ሁሉ #በመስቀል ምልክት እናማትባለን።
[ጠርጡለስ፡ Apologetic, De Corona(the chaplets) 3]
✝️ ንጉስ ቁስጥንጥኖስ ለጦርነት ሲወጣ በሰማይ ላይ የመስቀል ምልክት ሲያንጸባርቅ አይቶ ነበር.. ታድያ መላእክትም መጥተው "በዚህ ምልክት ድል ንሳ" እንዳሉትና ድልም እንደነሳ ከዛም ይህንን ከእግዚአብሔር የተቀበለውን ምልክት ይዞ ወደ ክርስትና መጥቷል
[Sozomen፡ Ecclesial History Book 2: 3]
🔥ከላይ እንደተናገርነው በክርስትና ስም ራሳቸውን ከደበቁት ውስጥ እንዲሁ ባለማወቅ ከጌታ መስቀል የራቁት ፕሮቴስታንቶች ብቻ ናቸው። ይህ ማለት ወደ 1.5 ቢሊዮን የሚሆኑት ካቶሊካውያንም ሆኑ የትኞቹም ኦርቶዶክሶች ስለ መስቀል ያላቸው መረዳት ተመሳሳይ ነው።

እኔ እንደ ብዙ ክርስቲያን ቤተሰቦቼ የጥንታውያን አብያተ ክርስቲያናትን አንድነትን የምናፍቅ አይነት ሰው ነኝ(ኦሬንታል ኦርቶዶክስ፣ ምስራቃውያን ኦርቶዶክስ እና ካቶሊክ)። በዚህም ምክኒያት በእነዚህ መካከል ያለውንም ሕብረት በጣም ሃሪፍ እንደሆነ የማምን ነኝ
ታድያ ግን ወደ ፕሮቴስታንቱ ስመለከት በጣም ከመራቃቸው የተነሳ እንኳን ከእኛ ጋር እርስ በእርስም ተስማምተው አንድ መሆን የሚችሉ አይመስሉም። ሌላው ደግሞ በጌታ ሥጋና ደም ላይ ያ ሥጋና ደም ሕይወትን የሚሰጥ የክርስቶስ ሥጋና ደም አይደለም በማለት ስድብን መናገራቸው ቀጥታ አጋንንታዊ እንደሆነ ስለምንረዳው በምንም ጉዳይ ላይ ከእነርሱ ጋር ሕብረት ማድረግ በራሱ ስህተት እንደሆነ ይሰማኛል። መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቅዱስ ቁርባን በግልጽ ያስተማረ ቢሆንም እስቲ ከሐዋርያት በኋላ ከተነሱ አባቶች ውስጥ ስለ ቅዱስ ቁርባን የአግናጢዮስን ምስክርነት እንስማ። እንደምናውቀው አግናጢዮስ ማለት ቀጥታ ከራሳቸው ከሐዋርያት የተማረ ቅዱስ አባት ነው። እናም ይህ አባት ስለ ቁርባንና በቁርባን ላይ ያልተገባ ነገርን ስለሚናገሩ መናፍቃን እንዲህ አለ፡
"[መናፍቃን] ከቅዱስ ቁርባንና ከጸሎት(προσφοράς as quoted by Theodoret, መስዋዕት) ይርቃሉ፤ ይህን የሚያደርጉበት ምክኒያትም በምሥጢረ ቁርባን የሚቀርበው ኅብስት ስለ እኛ ኃጢዓት መከራ የተቀበለውና አባቱም ከሞት ያስነሳው የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋ መሆኑን ስለማያምኑ ነው። ስለዚህ በዚህ የእግዚአብሔር ሥጦታ ላይ[በቅዱስ ቁርባን ላይ] የማይገባ ነገር የሚናገሩ ሰዎች እነርሱ በክርክራቸው መካከል ሞትን በራሳቸው ላይ ያመጣሉ። ነገር ግን በአክብሮት ቢመለከቱትና ቢያምኑበት ይሻላቸው ነበር። ስለዚህ እንደዚህ ካሉት ሰዎች ትርቁ ዘንድ የተገባ ነው። ከእነርሱ ጋርም በግልም ሆነ በማሕበር ግንኙነት አይኑራችሁ።"
[ቅዱስ አግናጥዮስ ምጥው ለአንበሳ፡ to smyrna, chap 7]
በጣም የሚያስገርመን ስለ ቅዱስ ቁርባን የቤተ ክርስቲያን አባቶች ብቻ ሳይሆኑ የፕሮቴስታንት አባት የሆነው ማርቲን ሉተር እንኳን ይህ ቁርባን አማናዊ የጌታ ሥጋ እና ደም እንደሆነ ከተናገረ በኋላ እንዲህ ነበር ያለው፡
"መቶ ሺዎች አጋንንት ከእነ ጭፍሮቻቸው 'ሕብስቱና ወይኑ እንዴት የክርስቶስ ሥጋና ደም ይሆናል' በማለት እየጮሁ ወደፊት ቢገሰግሱ እኔስ ይህንን አውቃለሁ መናፍስት ሁሉና ጠቢባንም በአንድነት ተባብረው ቢመጡ በሃያሉ አምላክ ዘንድ የትንሿን ጣቱንም ያህል ጠቢባን ሊሆኑ አይችሉም(ስለዚህም እግዚአብሔር በጥበቡ ይህንን ያደርጋል ነው)"
Martin Luther: The Large Catechism, part 5 OF THE SACRAMENT OF THE ALTAR
ስለዛ በፕሮቴስታንት አባት ማርቲን ሉተር እይታ በቅዱስ ቁርባን ላይ ስድብን የሚናገሩ ሰዎች ምድባቸው ከአጋንንት ነው ማለት ነው።
ፕሮቴስታንቶች እንዴት ክርስቲያኖች ይባላሉ..?? እነርሱ የክርስቶስ ሳይሆኑ የስህተት ትምህርታቸውን የሰጣቸው አካል የእርሱ ናቸው።
2ቆሮ 11
13 እንደ እነዚህ ያሉ ሰዎች የክርስቶስን ሐዋርያት እንዲመስሉ ራሳቸውን እየለወጡ፥ ውሸተኞች ሐዋርያትና ተንኮለኞች ሠራተኞች ናቸውና።
14 ይህም ድንቅ አይደለም፤ ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ እንዲመስል ራሱን ይለውጣልና።
15 እንግዲህ አገልጋዮቹ(የሰይጣን) ደግሞ የጽድቅን አገልጋዮች እንዲመስሉ ራሳቸውን ቢለውጡ ታላቅ ነገር አይደለም፤ ፍጻሜአቸውም እንደ ሥራቸው ይሆናል።
አሁን ላይ ያለው ፕሮቴስታንት ባለማወቅ እንደዚህ ባሉ ሰዎች የተጀመረ ትምህርት ውስጥ ነው የተቀመጡት። ታድያ የመስራቾቹ እጣ ፈንታ እንደ ሥራቸው ከሆነ ተከታዮቻቸውስ ይቀርላቸዋል..??
ከእነ ቅዱስ አግናጥዮስ በኋላ የተነሳውም አባት ቅዱስ ሄራንዮስ እንዲህ አለ(ዲን ያረጋል በመድሎተ ጽድቅ ቅጽ 1 መጽሐፉ ላይ እንዳስቀመጠው)፡
"መናፍቃን 'የጌታችንን የከበረ ሥጋውንና ደሙን የበላውና የጠጣው የእኛ ሰውነት ወደመፍረስና መበስበስ ይሄዳል ሕይወትንም ገንዘብ አያደርግም' ለማለት እንዴት ይችላሉ? ስለዚህ ወይ አስተምህሮዋቸውን ያስተካክሉ(ይለውጡ)፤ አለዚያ ደግሞ ላያምኑበት ይህን ምሥጢር(ምሥጢረ ቁርባን) እንፈጽማለን እያሉ ከማስመሰል ያቁሙ"
[ቅዱስ ሄራንዮስ፡ በእንተ መናፍቃን 4፡18፡5]

ስለ ድንግል ማርያም ንጽሕና ቅዱስ አትናቴዎስ እንዲህ አለ፡
"ሞትን ረግጦ ሕይወትን ይመልስ ዘንድ 'ቃል' የባህሪያችንን ሥጋ ነሳ.. ከእንከን ሁሉ በጠራችው(spotless, immaculate) ድንግል በእርሷ ማሕጸን ውስጥ የራሱ አደረገው።
[በእንተ ተሰግዎተ ቃል(on the incarnation of the word): par. 8]
ቅዱስ ኤፍሬም ደግሞ እንዲህ አለ፡
"አንተ[ጌታ] ብቻ እና እናትህ ከሌሎች ሁሉ ይልቅ ውቦች ናችሁ። በአንተ ምንም እንከን በእናትህም ምንም እድፈት የለምና"
[Nisibene hymns 27:8 as cited in The Faith of the Early Fathers, vol. 2 by William Jurgens]
ቅዱስ ኤፍሬም በሚያስገርም ሁኔት ቅድስት ድንግልን ከሌላው ሁሉ ለይቶ ከጌታ ኢየሱስ ጋር አብሮ ንጽሕናዋን ይገልጻል ምክኒያቱም ከኃጢዓት ሁሉ የጠሩት እናትና ልጁ ብቻ ናቸውና ነው። በነገራችን ላይ ይህንን ሲናገር እንዲሁ ከሥጋና ደም ተገልጦለት ሳይሆን በቅድስት ኤልሳቤጥ ላይ የሞላው መንፈስ ቅዱስ በእርሱም ሞልቶ ነው። ቅድስት ኤልሳቤጥ በሉቃስ ወንጌል ላይ ምን እንዳለች እናስታውሳቹ(ያው ባትረሱትም)
"አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ፥ የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው።"(ሉቃ 1፡42)
የማሕጸኗ ፍሬ ጌታ ኢየሱስ የተባረከ ነው.. ቅድስት ድንግል ደግሞ ከሌሎች ተለይታ የተባረከች ናት። ጸጋ የሞላባት ናትና አብራ ከጌታ ጋር "የተባረክሽ" ተብላ ትጠራለች። ኃጢዓተኛ ከጌታ ጋር በሕብረት የተባረከ ተብሎ እንዴት ሊጠራ ይችላል። የሚያስገርመን ግን የቅድስት ድንግልን ታላቅነት በሞላባት መንፈስ ቅዱስ የተረዳችው ኤልሳቤጥ ድንግል ማርያምን ከጌታ ጋር አብራ "የተባረክሽ" ብቻ ብላ ጠርታ ያበቃች ሳይሆን እዛው ጋር ቀጠል አድርጋ እንዲህ አለች፡
"የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል"
ብራዘር ራስህን መርምር አንተ የሞላብህ መንፈስ ቅዱስ ይሁን እርኩስ መንፈስ ከኤልሳቤጥ ተማር። መንፈስ ቅዱስ ሲሞላብህ መንፈስ ቅዱስ እንደሞላባት ኤልሳቤጥ ትሆናለህ። እርኩስ መንፈስ ሲሞላብህ "የሴቲቱ ጠላት" ሥራ አስፈጻሚ ሆነህ ትቀመጣለህ። እኔ የሚበጀኝን መርጫለሁ አንተም የሚበጅህን ምረጥ። ነገረ ማርያም በነገረ ክርስቶስ የታቀፈ ነው።
በነገራችን ላይ ስለ ቅድስት ድንግል ንጽሕና ለመረዳት እርሷን እንደ አዲሲቷ ሔዋን መመልከት ነው። ብዙ አባቶች እጅግ ጥንታዊ የሚባሉት ሳቀሩ ድንግል ማርያምን አዲሲቷ ሔዋን ይሏታል። ከዚህ ጋር ተያይዞ በቅርቡ የአባቶችን ትምህርት እናቀብላችኋለን እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ።