••●🍃እበጂልኝ••●🍃

ፍቅርሽ ክፉኛ ቢቀጣኝ
አንደበቴ ታስሮ
መናገር ቢያቅተኝ
መፍትሔ ፈልጌ
ደፍሬሽ መጣሁኝ።

ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ
አፌ ኩልትፍ ኩልትፍ
ላብድ ነዉ በፍቅርሽ
ብዬ ብጠይቅሽ
እስቲ አብደህ አሳየኝ
ነበረ ምላሽሽ

ፍቅርሽ አጃጅሎኝ
እብደትን ሞከርኩት
ፀጉሬን አሳድጌ
ልብሴን ቀዳደድኩት
ወጣሁኝ ጎዳና
ብርዱን ተላመድኩት

ለካስ እብደት ውስጥ
ጥልቅ የሆነ ሚስጥር
የራስ ነፃ ዓለም
ጭንቀት የሌለበት
ፍቅርሽን ረስቼ
እብደት ተመችቶኝ
በዛው ቀጠልኩበት

ምን ይሆን ምላሽሽ
እንዲ ስሆን አይተሽ
መሥዋት መሆኔን
እንደፍላጐትሽ

ፀፀቱን ካልቻልሽው
እየነሳሽ ጤና
አንድ ላይ እንሁን
አንቺም እበጂና።

ቻፒ

@wisdomic #Share
❥❥________⚘_______❥❥
🌹🌿🌙✿...

አንድ ቀን የሱፊው ደቀመዝሙር ወደ ሩሚ ዘንድ በመምጣት ❝መምህር ወይ ! ፍቅርን ፈልጎ ለማግኘት መንገዱን ይምሩኝ❞ ይለዋል..

ሩሚም……❝የአንተ ድርሻ ፍቅርን መፈለግ አይደለም ፣ ነገር ግን ከእሱ ጋር እንዳትገናኝ ያገደህንና በልብህ የገነባኸውን የጥላቻ ቅጥር ማፍረስ ነው።❞ በማለት አሰናበተው።

ለልቤ ሰው ሩሚ ❝ፍቅር ከፈጣሪ የተሰጠ ስጦታ ነው..ለዚህም ደሞ ቀላሉ መንገድ ሰጭውን አጥብቆ መፈለግ ነው❞ ይላል።...


@wisdomic #Share
❥❥________⚘_______❥❥
​​😘ጭንብል😘

🔥ክፍል 46

ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
" የምወድሽ እህቴ እንኳን ለዝህች ቀን አደረሰሽ " አለቾ ኤፍራታ
ከልብ የመነጨ ፈገግታ እየለገሰቻት
" እንኳን ደህና ቆየሺኝ የምወድሽ ቀጫጫዋ እህቴ " አለች መና
በጉጉት በስስት እያየቻት ከዛም በፍቅር በደስታ ለደቂቃ ተቃቅፈው
ተሳሳሙ ከልኡል ጋርም ሰላም ተባባሉ ።
እቤት ደርሰው በደስታ ሲሳሳቁ ሲጨዋወቱ አመሹና ከኤፍራታ
ቀጮ ናፍቆታቸውን ለመወጣት በአንድ አልጋ ላይ ተቃቅፈው
ለመተኛት ወደ መኝታ ክፍላቸው ሄዱ ገቡ በሩን ዘግተው የለሊት
ልብስ መቀየር ጀመሩ ድንገት ኤፍራታ ወደ መና ስትዞር ሰውነቷን
አየቺውና በድንጋጤ ደጋግማ ስትጮህ መና ደንግጣ እሮጣ አፏን
አፈነቻት እና ምን እንደሆነች ጠየቀቻት ። አፏን ስላፈነቻት እንዴት
ብላ ታውራ በዚህ ወቅት ልኡል ሽጉጡን ደግኖ በሩን ከፍቶ ገባና።
" ምን ሆናቹሁ ነው ....." አላቸው የመናን ሰውነት አላየም ነበር።
መና ዝም ብላ መልስ ሳትሰጠው አየቺው በዚህ ወቅት ነበር
ኤፍራታ አፏ መያዟን ያየው ።" .... ምን ሆነሽ ነው አፏን ልቀቂያት
እንጂ " ሲላት ደንግጣ ለቀቃች ።
" ልኡሌ የመናን ሰውነት አይተሀው ነው ዝም ያልከው ነው
አላየሀውም እ... ልኡሌ " አለች ኤፍራታ ልኡል ወዲያው
ሰውነቷን አያትና።
" መና ምን ሆነሽ ነው እ.... ንገሪኝ ምንድን ነው የሆንሺው ያ
አረመኔ ሰውዬ ነው እንዲህ ያረገሽ ?" አላት በጣም በንዴትና
በብስጭት ሆኖ ጠየቃት። መናም በዝምታ ልብሷን መልሳ
ለበሰችና ወደ ሳሎን ይዛቸው ሄዳ ሁሉንም ነገር ነገረቻቸው።
" በጣም እርግጠኛ ነኝ ያ እርኩስ ነው ይሄን ያደረገው " አለ
ልኡል መና በደረሰባት ስቃይ እያዘነ።
" እርግጠኛ አይደለሁም ግን ማንም ይሁን ማንም ለዚህ ጥፋቱ
ዋጋውን እንዲከፍል አረገዋለው " አለች መና ኤፍራታ እያየቻት
የዝምታ እንባ በጉንጯ ላይ ይፈሳል።
" ልክ ነሽ በቅጣቱ ያደረገው ነገር እንዲፀፅተው እናረገዋለን ...
አንቺ ግን ሰውነትሽ እንዲህ ሆኖ አይቀጥልም ወደ ውጭ ሄደን እኔ
አስተካክለዋለው " አላት።
" አይ አልፈልግም እሱ በሰውነቴ መኖሩ ደፋርና ጀግና ያረገኛል
እሱ ከሌለ ሁሉን ነገር እረስቼው እተዋለው ይህ ደግሞ እንዲሆን
አልፈልግም " አለችው ። የተናገረችው እውነት ለመሆኑ
ጭንቅላቱን አወዛወዘላት።
" የእኔ እህት ይህ ሁሉ ስቃይ ለእኔ ለእህትሽ ስትይ ነው
አይደል ?" አለቻትና እያለቀሰች ወደ መኝታ ክፍሏ ሮጠች።
አሁን ወደ አለው ታሪክ ተመለስን ።
" እስር ቤት እንድቃጠል ያረከኝ አንተ አይደል ?" አለችው ንጉሴ
የተጠበሰው ብልቱ እየለበለበው በመጋዝ እግሩ ተቆርጦ የኋላው
ትንሽዬ ስጋ ተጠልጥላ ህመምና ስቃዩ በዝቶበት ከአቅሙ በላይ
ሆኖበት ስለነበር በእንዲህ ሁኔታ ከመኖር አለመኖርን መርጦ
እንድትገለውም ፈልጎ ሁሉንም ነገራት ።
ከደፈሯት ሶስት ሰዎች ሁለቱ ልጆቹ እንደሆኑ መሀል የእጁ መዳፍ
ላይ የወጋችው የኔነህ እንደሆነ ትንሹንም ልጁን ያው
እንደገደለቺው ከየኔነህ ጋር እንደተጣሉና የት እንዳለ እንደማያውቅ
ነግሮት ሶስተኛው ከበደ እንደሆነ ነገረችው ከበደም ታሞ እንደሞተ
አንድ ወንድ ልጅ ሰካራም የሆነ እንዳለው ሚስቱም አሁንም
በድህነት ማቅ ውስጥ እንዳሉ ነገራት ገድልሻል የተባለችው
ልጆችም እሱ የገደላቸው ሰዎች እንደሆኑ ይህን ሁሉ ያረገው በቃ
ሀብታም ለመሆን ፈልጎ እንደሆነ ከእስርም ስትፈታ ማንም
የማይመጣላት መስሎት ሊያስገድላት አስቦ እንደነበር አስረዳት
ተስፋ በመቁረጥ ።
መና በዝምታ ስትሰማው ቆይታ ምን ብታረገው አንጀቷ አንደሚረካ
እያሰበች ሳለ ከኋላዋ.....
" አንድ የደበቀሽ ሚስጥር አለ የከበደ ልጅ ማለት አሁን የኤፍራታ
አፍቃሪ አሁን ሆ/ል ያለው ሙሉነህ ነው " አላት ባለ ጭንብሉ
ከኋላዋ በመምጣት ። ጭንብሉን አወለቀ ልኡል ነበር መና
ንጉሴን ስታየው እሱም አለማወቁን ሲነግራት ወደ ልኡል ዘወር
ብላ በንዴት አየቸውና አፍጥጣበት ።
" እንዴት እስከ አሁን አልነገርከኝም " አለችው
" አትጨናነቂ አሁን እኮ እዛው ሆ/ል ነበርኩ እሱ ምንም አያረግም
ምንም አያወቅም " አላት ተረጋግቶ
" ምንም እንዳማያመጣ እንዴት አወክ እህትህ ስላልሆነች ነው
ለማንኛውም አሁን ሆስፒታል ሄጄ እሱን ገድዬ እህቴን ላድናት
ይገባል አንተ የፍቃዱን እናትና ልጅ የት እንዳሉ ጠይቀውና
ይዘህለት ና " አለችና መና እሮጣ ልትወጣ ንጉሴ ጠራትና
ያሉበትን ነገራትና ሆስፒታል እንድትወስደው ለመናት እሷም ፈገግ
ብላ አይታው።
" አንተ እኔንም ቤተሰቤንም ካደረስክብን መከራና ስቃይ እኔ ምንም
አላደረኩሁም እንደዚሁ ጥዬህ እሄዳለው ከተረፍክ ተረፍክ
ከሞትክም ተገላገልክ መትረፍህን ባትወደው ይሻላል" ብላ
እየሮጠች ወጣች።
ፍቃዱ በጠቋሚ ጣቱ በምርመራ ቢሮ ውስጥ ተቀምጦ ከፊቱ
ያለውን ጠረጴዛ እየቆረቆረ በር በሩን ያያል ከትንሽ ቆይታ በኋላ
በሩ ተከፍቶ ሌላው ባለጭንብሉ ፊቱን እንደሸፈነ እጁ በካቴና
ታስሮ ገባ ወንበር ላይ ተቀመጠ ለትንሽ ደቂቃ ፍቃዱ ብቻ
ሲጠይቀው መልስ አልመልስም ብሎ ዝም ካለው በኋላ
በመጨረሻ እስኪቢርቶ እና ወረቀት እንዲሰጠው ጠየቀው
ፍቃዱም ሰጠው የሆነ ነገር ፅፎ ሰጠው ፍቃዱ አንብቦት ቀና ብሎ
አየው።.......

ይቀጥላል...

@wisdomic #Share
❥❥ ⚘ ❥❥
​​😘ጭንብል😘

🔥ክፍል 47

ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
.
" ቂቂቂቂ አንገቴን ትቆርጠዋለህ እንጂ ጭንብሉን አላወልቅም
..... ኪኪኪኪ ስላላወከው ህግ በቃ ወደ ቤት ሂድ የሚልህ
ይመስልሀል ? ለሰራሀቸው ወንጀል ሁሉ ትንከናነባታለህ እሺ
ቀልድ የለም ከምንም አታመልጥም " አለው ፍቃዱን ቃላቶቶቹን
በሳቅ እያዋዛ ።
" እረ እኔ ብዙ ሰው አልገደልኩም የሆቴሏን ሰራተኛ እሱም መና
አዛኝ ሌላውን እንዳለ መና ነች የሰራችው " አለ ባለ ጭንብሉ
ፍቃዱን እያየው ።
" ለካ መናገርም ትችላለህ ...... ጥሩ መና ነች ያዘዘችሀ እራሷን
ቤተሰቧን ግደል ብላ " አለ በፈገግታ
" እንደዛ ብላ አላዘዘቺኝም በአንተ ቀንታ የሆቴሉን ሰራተኛ እንጂ "
አለ። በዚህ ወቅት በሩ ተንኳኩቶ አንድ ተራ ወታደር መጥቶ
ፍቃዱን በር ላይ ሰው እየፈለገው እንደሆነ ነገረው ወዲያው
ተነስቶ ከምርመራ ቢሮ ወጣ።
በፖሊስ ጣቢያው ኮሪደር ላይ በመሄድ ሌላ ቢሮ ሲገባ እናቱንና
ልጁኝ አገኛቸው በድንጋጤ ካያቸው በኋላ ሁለቱን አቅፎ ሳማቸው
ልኡል መኖሩን ያስተዋለው እነሱን ሰላም ካለ በኋላ ነበር ።
" አንተን ማን ልበል " አለው በተረጋጋ ስሜት
" ልኡል እባላለው ሰላም ነው " ከተቀመጠበት በመነሳት
በአክብሮት እጁን ለመጨበጥ እየተነሳ አልጨበጠውም ፍቃዱ
የተዘረጋውን እጁን ተመልክቶ ተመልሶ ፊቱን ተመለከተው እና ።
" አሀ አንተ ነበርክ ማለት ነው ያገትካቸው " አለው በቁጣ
" እኔን መና ነች የላከችኝ ሌላ ምን የማውቀው ጉዳይ የለኝም
" አባ መናም አድናን ነው እነሱ እኮ አይደሉም ያፈኑን የሆነ
ሽማግሌ ሰውዬ ነው አንተ የሆነ ሰውዬ ይዘህበታል እሱን
ካልፈተሀለት እንደሚገለን ነግሮን ነበር የሰውዬው ስም ማን ነበር
እንኳ......."አለችና የፍቃዱ ልጅ ትንሽ አሰብ አድርጋ እናቷንና
ልኡልን ተመለከተች አግዙኝ እንጂ የሚል በሚመስል ሁኔታ
እናትየው ዝም ሲሉ ልኡል ግን አገዛት።
" ንጉሴ የተባለው ሰውዬ ነው ያሰርከው ሰው ጭንብል አድርጓል
መሰለኝ አይደል እናም ጭንብሉን አወለቀልህ ? " አለው ልኡል
ፍቃዱ እንዳላወለቀ ጭንቅላቱን በመወዝወዝ ሲነግረው ።"......
ፍቃደኛ ከሆንክ እኔ ላግዝህ እችላለው ጭንብሉን ለማውለቅ ..."
አለው
" እረ ........እውነትህን ........ ና እርዳኝ እኔ እኮ ጭንቃሉቱን
በትኜው ላወልቀው ነበር በል ና እንሂድ " አለውና ይዞት ወደ
ምርመራ ቢሮ በኮሪደሩ ላይ እየሄደ ሳለ ፍቃዱ የልኡልን እጅ ይዞት
ቆመና ፊት ለፊት እየተያዩ።
" ልኡል...... ልኡል ማለት የአቶ ጥላሁን የመጀመሪያ ልጅ እናቱን
በአሳዛኝ ሁኔታ በቃጠሎ ያጣ ኑሮው ከኢትዮጵያ ውጪ የቀዶ
ህክምና ከፍተኛ ተመራቂ ዶክተርና እና በኮፒተር ሳይስም በከፍተኛ
ውጤት ተመራቂ ለእናትና ለአባቱ ከእህቶቹ ጋር በመሆን ሊበቀል
መጣ ዋናው ባለ ጭንብሉ አንተ ነህ ስለዚህ አንተም የልጁን
ጭንብል ካወለክልኝ በኋላ ከዚህ አትወጣም ከዛ እህቶች ደግሞ
ይመጣሉ ማለት ነው " አለው ፍቃዱ የልኡል ፊት ወዲያው
ተለዋወጠ ።
" ትሰማለህ እኔን እንደፈለክ ልታደርገኝ ትችላለህ እህቶቼ ጋ ግን
እንዳትደርስባቸው ታውቃለህ እስከ ዛሬ ወንድማቸው እንደሆንኩኝ
አያውቁም ለምን የሚል ጥያቄ ይኖረሀል አይደል እነሱን
ለመጠበቅ እኔ ኑሮዬን ኖሬያለው እነሱ ግን እስከ አሁን አልኖሩም
ወድማቸው መሆኔን ከታወቀ ሊታሰሩ አሊያም አደጋ ሊደርስባቸው
ይችላል ብዬ ስለዚህ አትነካቸውም ለነገሩ እኔ ሁሉንም አምናለው
በእነሱ ላይ ምን መረጃ አይኖርህም እሺ "አለ ልኡል
" ይህንን ሁሉ ስለ አንተ መረጃ ካገኘው እንዴት ስለ እነሱ መረጃ
አጣለው ብለህ ነው ለእሱ አታስብ እሺ ታየዋለህ ና አሁን እንሂድ
አፍጥነው "ብሎት ይዞት ወደ ምርመራ ቢሮ ገቡ
ሊሾ የሆነው የቤቱ የቤቱ ወለል በደም ተጨማልቋል የንጉሴ
እግር በጨርቅ ታስሮ ደሙ እየተጠባጠበ መሬቱን አጨቅይቶታል
ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ ይላል አይኑ ደሙ ከማለቁ የተነሳ ነጭ ሆኗል
ከኪሱ እንደምንም ብሎ ስልክ በማውጣት ደውሎ ወደ ጆሮው
ወሰደው ።
" ልጄ ....... ልጄ ምንም ይሁን ለፍቼ አሳድጌሀለው እባክህ አሁን
ልሞት ነው እርዳታህን እፈልጋለው እባክህ እባክህ ድረስልኝ
ሁሉም ነገር እየፀፀተኝ ነው ልጄ ድረስልኝ " አለና ስልኩን ሳይዘጋ
አቅም አንሶት ጣለው።
መና ወደ ሆ/ል በፍጥነት በመግባት ወደ ኤፍራታ የተኛችበት
ክፍል በመሄድ ኮሪደሩ ላይ ስትደርስ ሙሉነህ ጠረጴዛ ላይ ተኝቶ
አገኘቺው በፍጥነት ቀሰቀሰችውና ወደ አንድ ጥግ ይዛው በመሄድ
ሽጉጥ አውጥታ እንዳይታይ አድርጋ አፈሙዙን ሆዱ ላይ
ደቀነችበትና ግድግዳ ላይ በጀርባው ለጥፋው እሷም ተለጥፋበት

" አላማህ ምንድን ነው ምን ልትሰራ ነው እህቴን የቀረብካት"
አለቺው የእጇን ክንድ አንገቱ ላይ ተጭና እንደማነቅ አድራጋው
እሱ በድንጋጤ ፈጦ ያያታል ።" ተናገር" አለችው
" ምንም እህትሽን ስላፈቀርኳት " አለ እየፈራ
"አትቀልድ ሳልደፋህ እዚሁ ...... " ስትል ከኋላዋ ዶከተር መጥቶ
ሲጠራት ደንግጣ ሙሉነህን ለቃ ሽጉጧን ወደ ኆላ አድርጋ የግድ
ፈገግ አለች ።
" እንኳን ደስ አለሽ እህትሽ ተሽሏታል ነቅታለች ሄደሽ ልታያት
ትችያለሽ " አሉና ዶከተር ዘወር ሲል መና ዘወር ብላ
" ከዚህ በኋላ እህቴ አጠገብእንዳትደርስ አለበለዚያ ምንም
ሳላገራግር ጭንቅላትህን በጥይት እበትነዋለው " ብላ ወደ እህቷ
መኝታ ክፍል ስትሄድ አበር ላይ ደግሞ ፍቃዱ የፖሊስ ሰራዊት ይዞ
እየገባ ነበር።
ንጉሴ አንድ ያረጀ እና የዛገ ብርት ላይ በጀርባው አስተኝቶት እግሩ
እና እጆቹ በገመድ ታስረዋል የተለያየዩ ስለታም የሆኑ መሳሪያዎች
በሌላ ቦታ ላይ ይታያሉ ። ቢላውንና መቀሱን ልጁ የኔነህ አንስቶ።
" አባቴ ለእውነቱ ቆመህ እንኮን አልጠከምከኝም እስቲ ሞተህ
እንድትጠቅመኝ ብዬ የሰውነት አካልህን አውጥቼ ልሸጠው ነው
አመሰግናለው ለዚህ ትብብርህ " አለውና ሸሚዙን በመቅደድ
ቢላውን አንስቶ ሆዱን ይቀደው ጀመር ንጉሴ እያለቀሰ ይጮህ
ጀመር።........

ይቀጥላል...

@wisdomic #Share
❥❥ ⚘ ❥❥
ስመ ጥሩ የፋርስ ባለቅኔ ሩሚ እንዲህ ይላል
❝ንግግር ከማድረግህ በፊት ንግግርህን በነዚህ ሶስት በሮች ፈትሸህ አሳልፈው...

ትክክል ነው ወይ...?
አስፈላጊ ነው ወይ...?
በጎ ነገር ነው ወይ...?❞

ጉተማ ቡድሃ ደግሞ የሩሚን ንግግር ግልፅ ሲያደርገው :- ❝ቃላቶችህ ከዝምታ የተሻሉ ሲሆኑ ብቻ ተናገር❞ ይለናል...

...እወደድ ብሎ ሀሰትን መናገር
አድርባይነት ነው... እጠላ ይሆን ብሎ እውነትን መሸሸግም አግባብ አይደለም።...በአስፈላጊው ጊዜ እና ቦታ እውነቱን መናገር ቢከብድም እንኳን አስፈላጊ ነው ።

@wisdomic #Share
❥❥________⚘_______❥❥
​​​​😘ጭንብል😘

🔥ክፍል 48

ደራሲ ዳኒ የወሰን ልጅ
.
#ሊጠናቀቅ ሁለት ክፍል ብቻ ይቀረዋል!!
.
.
notice: ክረምት እንደመሆኑ መብራት በየጊዜዉ ይጠፋል...ቻርጅ አይኖረንም ማለት በተቻለ አቅም ፕሮግራሞችን ለማቅረብ እየሞከርኩ ነዉ ግን በቂ እንዳልሆነ ይሰማኛል..እንደበፊቱ የተለያዩ አስተማሪ ነገሮችን እያቀረብኩ አይደለም ስለዚህ ችግሩን ተረድታችሁ ታገሱን...ቻሉን።።
.
.
ጩሀት በበረከት ቤት ሳቅ ተደግሷል የአንዱ ህመም የሌላው
የደስታ ምንጭ ሆኗል ገንዘብ ፍቅርን ብቻ ሳይሆን ህይወትን
የሚገዛ የሚመስላቸው ሞልተዋል ገንዘቡን ከስክሰው የፈለጉትን
ሲያጡ ምን ሊሉ እንደሚችሉ ማሰብ ብቻ በቂ ነው ምን
እንደሚናገሩ ጭምር።
" እኔ ለአንተ ህይወት ካንተ ፍቅር ለማግኘት ስንት ብሬን ከሰከሰኩ
አንተ የእኔን የሰውነት አካሌን አውጥተህ ልትሸጥ ነው የኔ ልጅ
.... እባክህ ተው " አለ ንጉሴ እየጮሀ እያለቀሰ።
" የኔ አባት ታስቀኛለህ እኮ ፍቅርን እንዴት በገንዘብ ልትገዛ
ትፈልጋለህ ለእውነቱ ገንዘቡን እኔ ሳልፈልግ አንተ ነህ የሰጠሀኝ
ገንዘቡ ቀርቶብኝ ፍቅርህን ብትሰጠኝ በእኔ ላይ እምንት ቢኖርህ
የእኔን ሁሉንም ፍቅሬን ታገኝ ነበር ፍቅር በፍቅረ እንጂ በገንዘብ
አይገዛም ይሄንን ያሰበ ሁሉ ስህተት እንደሆነ ማወቅ አለባቹሁ "
አለና በዛገ ቢላዋ ሆዱን ከደረቱ አጥንት ስር ይቀደው ጀመር።
" እሺ አሟሟቴን አሳምርልኝ ተው በዛገ ቢላዋ አትቅደደኝ " አለ
ንጉሴ በልመና እና በሚያሳዝን ቃል እያለቀሰ።
" ባክህ ዝም በለኝ ይሄም ሲበዛብህ ነው " አለውና አፍን በጨረቅ
ጠቅጥቆ ሆዱን ይቀደው ጀመር ከግራና ከቀኝ ንጉሴ የተኛበት
ብረት ደሙ ይፈስ ጀመር ድምፅ ማውጣት አልቻለም እንባዎቹ
ከግራ እና ከቀኝ በጆሮ ግንዱ ላይ ይፈሱ ጀመር ነፍሱ ከአካሉ
እየተለየች እንደሆነ ንጉሴ ገብቶታል ይሄ በቁሙ ስቃዩን አይቶ
መሞቱ ፈጣሪ ለሰራው ሀጢያት ሁሉ የከፈለው ክፍያ መሆኑ
ለመጀመሪያ ጊዜ ገባው ይሄ የስቃዩ መጀመሪያ እንጂ መጨረሻው
እንዳልሆነ ተረድቷል ከሞተ በኋላም የባሰ የስቃይ አለም ውስጥ
ይገባል ምን ያርግ በዚህ ሰአት ምንም ማድረግ አይችልም ስለ
ሀጢያቱም ይቅርታ አይጠይቅም አብቅቷላ አበቃ የንጉሴ ህይወት
በጣር ዜማ እና በእንባ እቺን አለም ተሰናበተ። የሰውነት አካሉን
ልጁ የኔነህ እያወጣው በአነስተኛ ፍሪጅ ውስጥ ያስቀምጠው
ጀመር ።
መና የኤፍራታ አይን እንደገና እንደ ንጋት ፀሀይ በርቶ ስታይ
ልትጨፍር አስባ ነበር ግን ሆ/ል ውስጥ መሆኑን አየችና ተወችው
ተቃቅፈው ተለቃቀሱ ተሳሳሙ እንደ መና ደስተኛ ሰው የለም ነበር
። በዚህ ሰአት ነበር ኤፍራታ ቀና ብላ ከመና እኋላ ያለውን ሰው
ተመለከተች ፈገግ ስትል መና እሷን አይታ ዘወር ስትል ሙሉነህ
ነው ኮስትር ብላ አየቺው።
" ሙሌ እስከዛሬ እዚሁ እኔን እየጠበከኝ ነበር።" አለችው በፍቅር
ስሜት እያየቺው።
" አንቺን እዚህ ጥዬሽ ብሄድ በሰላም እንቅልፍ ይወስደኛል
አዚህም ሆኜ እኮ አልቻልኩም ይገባኛል ለአንቺ ውበት ምላሽ
የሚሆን በቂ ውበት የለኝም የአንቺን ፍቅር የሚገዛ ገንዘብ የለኝም
ሁሉንም የሚያሸንፍ ነገር እዚህ ውስጥ አለ......... ፍቅር በእኔ
አቅም ልሸከመው የማልችል ፍቅር... "አላት ልቡን በእጁ
እየጠቆመ በዝምታ ውስጥ የሚወርድ እንባ በእሱም በኤፍራታም
ወስጥ እየዘነበ። መና ግን በንዴት ከተቀመጠችበት ተነስታ
እያፈጠጠችበት።
" ስማ ከየትኛው መፅሀፍ ላይ ነው ማንበብ የቻልከው እንዲህ
መሳጭ የሆነ የልብ ወለድ ንግግር ከበአሉ ግርማ ወይስ ከአዲስ
አለማየው ወይስ ዳንኤላ ስቲል...እ ከማን ነው ...... ስማ
አጠገቧ እንዳትደርስ አላልኩሁም " ብላ ጎትታው ይዛው ስትወጣ
ኤፍራታ እንድትተው ብትነግራትም መና ዝም ብላ ይዛው ወጥታ
ኮሪደር ላይ አቁማው ልታናግር ስትል ድምፅ ሰማች ዘወር ስትል
ፍቃዱ ከፖሊሶች ጋር ቆሞ እሱ ስልክ ሲያናግር አየቺው እና
ደነገጠች።
" አሁን ምን ይሻልሀል ባለ ጭንብሉ ቢላዴን ልበልህ ወይስ
በዋናው ስምህ ኢሳያስ ልጥራህ " አለው ፍቃዱን ቢላዴንን
እያየው በምርመራ ቢሮ ውስጥ ቢላዴንም አንገቱን ደፍቶ ቆየና ቀና
ብሎ እያየው ተስፋ በቆረጠ ስሜት ።
" የፈለከው አድርገኝ አሁን ምርጫ የለኝም " አለው
" እሺ ንገረኝ ጭንብል አርገህ ወንጀል ለምን ሰራህ "
" የእኔ ፍላጎት ሳይሆን የንጉሴ ፍላጎት ባለ ጭንብሏ መና ስለሆነች
የእሷን ወንጀል ለማብዛትና የሞት ፍርድ እንዲፈረድባት ፈልጎ
አዘዘኝ የመጀመሪያ የገደልኳት ልጅ የቡና ቤቷን ነው ሁለተኛዋን
ልገላት ስል አንተ ደረስክብኝ በቃ ያዝከኝ መናን ጎድቻለው ከሁለቱ
ውጪ ምንም ወንጀል አልሰራሁም " አለ ቢላዴን ኮስተር ብሎ።
" እእእ አትሳሳት በሁለቱ ወንጀል ብቻ ሳይሆን በሁሉም ወንጀል
የባለ ጭንብሉ ወንጀል ነው የምትጠየቀው ለሰው የደገሱት
ለእራስ ይደርሳል በል ተዘጋጅ ነገ ፍ/ቤት ትቀርባለህ እሺ " ብሎት
ፍቃዱ ሲወጣ ቢላዴን ደንግጦ ባልሰራው ወንጀል መጠየቅ
እንደማገባ እየጮሀ ሲናገር ፍቃዱ እየሳቀ ወጣ።
ጊዜያቶች በነዋል ኤፍራታም ሙሉ ለሙሉ ድና ከሆ/ል ወጥታለች
ሙሉነህን ግን እርቀዋለች ። ምሽት ላይ ሙሉነህ መናን ከኋላ
ከኋላ እየተከተላት ለኤፍራታ ስልክ ደውሎ እንደሚያፈቅራትና
አብራው እንድትሆን ለመናት እሷ ግን የጠላታችን ልጅ ነህ
አላማህን አላውቅም ብላ እንዲተዋት ተናግራ ስልኩን ዘጋችው።
መና ወደ ቤቷ የሚሄደውን መንገድ ይዛ እየሄደች ሳለ ከኋላዋ
አንድ ሰው መጥቶ አንገቷን በመርፌ ወጋት እራሷን ሳተች። ከደቂቃ
በኋላ መና አይኗን ስትገልጥ ንጉሴ ተኝቶበት በነበረው ብረት ላይ
በሰንሰለት እጅ እና እግሯ ታስሮ በጀርባዋ ተኝታለች ደንግጣ
አንገቷን በግድ አዙራ ስትመለከት የኔነህ ሁለት ቢላዋ እየሳለ ወደ
እሷ ፈገግ ብሎ መጣና አጠገቧ ቆሞ።
" ነቃሽ የኔ ፍቅር እንኳን ደህና መጣሽ የቄራን እርድ ላስተምርሽ
አስቤ ነው የመጣሁት " አለና ቲሸርቷን ወደ ላይ ሳበና ሆዷን
በግርምት አየው ስለቱንም ወደ ሆዷ ሰደደው።..

ይቀጥላል....

@wisdomic #Share
❥❥ ⚘ ❥❥
​​😘ጭንብል😘

🔥ክፍል 49

ዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
#ሊጠናቀቅ 1 ክፍል ብቻ ይቀረዋል...
.
.
" ምን ልታደርግ ነው " ነው አለችው መና የኔነህ ቢላዋን ስሎ
ወደ ሆዳ ሲሰደው እየተመለከተች።
" መንዬ እስከ ዛሬ የተሸወድኩትን ሞኝ የሆንኩበትን ምክንያት
ልንገርሽ ? " አላት ወደ ሆዳ የሰደደውን ስላታም እና የዛገውን
ቢላዋ እየመለሰው ሊያናግራት ብሎ።
" እስቲ ንገረኝ መቼም ዲያቢሎስ ደህና ነገር አያስብም ደህና
ነገርም ቢሆንም ልስማህ " አለችው በሰንሰለት የታሰረውን
እጇንም እግሯንም ለመፍታት እየሞከረች። የኔነህ ከት ብሎ
እየሳቀ እያያት።
" በሳቅ........ እረ በሳቅ ዲያቢሎስ ነህ እያልሺኝ ነው በይኝ ስራ
ፈጣሪ ሰው ዲያቢሎስ ከተባለ...." ሲላት መና በተራዋ ከት ብላ
ሳቀችበት እና ......
" ይሄ ስራ ፈጠራ ነው ማለት ነው ነገሩ ልክ ነህ ለአንተ....."
" ከዚህ በላይ ምርጥ ስራ አለ የሰውነት አካል ልብ፣ኩላሊት፣
ጉበት ሁላ ይሸጣል ልድመት ተፈልጎ አይደለም የሚገርምሽ
የአባቴን በቀደም ነው አውጥቼ የሸጥኩለት ቆሞ ያረዳኝ ከሞተ
በኋላ በሀይለኛው ገቢ ያስገባልኝ አይገርምም " ሲላት መና በጣም
ደነገጠች ግራ ገባት የሰው ልጅ ምንም አረመኔ ቢሆን እንዴት
በአባቱ ላይ እንዲህ እርኩስ ነገር ያረጋል ብላ ደነገጠች ተፈናጥሮ
ተራርቆ እጅና እግሯ መታሰሩን አረስታው ከተኛችበት ልትነሳ አስባ
ብድግ ለማለት ስትሞክር ያዛት።
"አንተ እንደው ምን አይነት ደምና ዘር ነው ያላቹሁ ግን እንዴት
በአባትህ ላይ ይሄን ያህል ጭካኔ በጣም ይገርማል"
" ለማንኛውም የአንቺን ደግሞ አሁን ልጀምር " ብሎ ቢላውን ወደ
ሆዳ ሲሰድ ያለበትን ክፍል በር ተንኳኳ የኔነህ ተናደደ ዘወር ብሎ
ወደ በሩ ሲመለከት ደጋግሞ ተንኳኳ ስለቱን እንደያዘ በሩን
ለመክፈት ሊሄድ ሲል መና ጠራችውና ።
" ዲያቢሎስ የሀገሬ ሰው ሲተርት ምን እንዳለ ታውቃለህ
ማምሻም እድሜ ነው..ሂድ ክፈት ጓደኛህን ተቀበል " አለችው
የኔነህ በፈገግታ አያትና ለመክፈት ሄደ።
በሩን እንደ ከፈተ የተቀበለው ጓደኛው ሳይሆን ጥሩ ቡጢ (ቦክስ)
ከፊቱ ላይ አረፈበት ደንግጦ ሲያይ ሁለተኛው ቦክስ አረፈበት ያለ
ጥርጥር ማንነቱን ከማወቅ የመጣበትን ጥቃት መከላከል
ነበረበትና ከሰውዬው ጋር ተያያዘ መደባደብ ጀመሩ አንዴ አንዱ
ሲመታው ሌላጊዜ ሌላኛው እቃ ይሰባበሩ ጀመር መና እንደምንም
ብላ ማንነቱን ስታይ ሙሉነህ ነበር በመጨረሻ ግን የኔነህ
ሙሉነህን ገልብጦት መሬት ላይ አስተኝቶት እላዩ ላይ
ተቀመጠበትና በቦክስ የየኔነህን ፊት አጣደፈውና በመጨረሻ
በያዘው ሴኒጢ ሁለት ጊዜ የእጁ መገጣጠሚያ ላይ ወጋው ።
ከትንሽ ቆይታ በኋላ መሬት ላይ ሙሉነህም መሬት ላይ እጅና
እግሩ ታስሯል ከትከሻውና ከአፍ ደም ይፈሳል የኔነህ ከንፈሩና
አይኑ አብጦ ቢላውን እየሳለ መናን እያያት።
" ሊያድንሽ መስሎሽ ነበር አይደል ..ሳታስቢው እኔን እረዳሺኝ
አመሰግናለው በይ እንጀምር ...... " ብሎ ቢላዋን ሲሰድ እረስቶት
እና በተከፈተው በር ፍቃዱ ተንደርድሮ በመግባት ሽጉጡን ደግኖ
ሁለቴ ተኮሰው የየኔነህን ሆድ እና ደረቱ አካባቢ መታውና ወደቀ።
ከቆይታ በኋላ መና ለኤፍራታ ደውላ እንድትመጣና ሙሉነህን ይዛ
ሀኪም ቤት እንድትወስደው ነግራት ይዛው ሄዳለች ፍቃዱን ደግሞ
የኔነህን ከማሰሩ በፊት ስቃይን ትንሽ ጊዜ ላሳየው ብላ
አስፈቀደቺው እሱም ተቀበላት የኔነህ እራሱን ስቶ የተመታበት በታ
ደሙ እንዳይፈስ ታስሮለት በአንድ ስስ ብረት በጀርባው አስተኝተው
እጅና እግሩን አስረውታል በሌላ ቦታ እሳት አያይዘው እሷ
የተሰረችበትን ብረት ጥዳው እስከሚግል ጠበቁት በመጨረሻ
ውሀ አርገው እንዲነቃ ካደረጉ በኋላ እሱ የተኛበትን ብረት እስከ
እነሱ አንስተው የጋለው ብረት ላይ አደረጉት የኔነህ አበደ
እንዲተውት ለመናቸው እንደውም ዘይት አርገው እንዳይሞት
አድርገው አገላብጠው ጠበሱት።
የኔነህ ሰውነቱ እንደ መና ተጠብሶ ቆዳው ተሸብሽቦ በህክምና
ሲረዳ ከቆየ በኋላ ታክሞ እንደ ጨረሰ ወደ እስር ቤት ገብቷል
።ከዚህ ጊዜ በኋላ ለመና አዲስ ህይወት አዲስ ብርሀን ፈንጥቋል
አብቅቷል የስቃይ ህይወቷ ምክንያት የነበሩትም ዛሬ ወደ
ሚገባቸው ሄደዋል ልኡልም ከእስር ቤት ተፈቶ መናን በቆዳዋ ላይ
ያለውን ችግር የስቃያ ማስታወሻ ሊያጠፋላት ተነጋግረው
ጨርሰዋል።
አሁን ደስ የሚል ምሽት ከፍቃዱ ጋር በአንድ መጠጥ ቤት
እየጠጡ እየተዝናኑ እየተደሰቱ እየደነሱም በጣም ደስተኛ ሆነዋል
ሞቅታ ከዛ ስካር ቀጥሎም በፍቅር አለም ተዘፍቀው እየደነሱ ሳለ
የፍቅር ስሜታቸው ደውሉን አሰማ በምን ፍጥነት የሆቴሉ መኝታ
ክፍል እንደገቡ ልብሳቸውን አወላልቀው ባዶአቸውን እራቁታቸውን
አልጋ ላይ እንደተገኙ አላወቁትም ግን እውነት ነው ናቸው። አካል
ለአካል ሊተሳሰሩ ሲሉ አስቆመችው ያለ3 የደፈሯት ትዝ አላት
ፍቃዱም አኮረፈና ጀርባውን ሲሰጣት እንዳኮረፈ ገባትና ዘላ
ወጣችበትና በፍቅር አለም በስሜት በሀር አብረው አንድ ላይ
ቀዘፍ። ንጋት ፍቃዱ አይን አይኗን እያያት ቆየ ከንፈር ለከንፈር
ተሳሳሙና የሆነ ነገር ሲነግራት በድንጋጤ አየችውና ከተኛችበት
ተነሳች።...........

ይቀጥላል...

@wisdomic #Share
❥❥ ⚘ ❥❥
​​​​​​😘ጭንብል😘

🔥ክፍል 50

ዳኒ የወሰን ልጅ
.
.
#የመጨረሻ ክፍል
.
.
መና የሰማችው ነገር የራስ ቅሏን ያናጋው መሰላት በጣም
ደነገጠች በአንሶላው ጡቶቿን ሸፍና አንዴ በፀጉር የተሞላውን
የፍቃዱን ደረት ከጠለች እንደ ፍም ቀልቶ በፀጉር መከበቡ በጫካ
ውስጥ የበቀለ ፖም የሚመስለውን የፍቃዱን ከንፈር አየችውና
ቀጥሎም ጥርት ነጭ ሆኖ የየሚታየውን አይኖቹን አየቺው እሱም
ፈገግ አርጎ አያት።
" እውነትህን ነው ፍቄ " አለችው መና ባለማመን
" ቆይ እሱን ከመናገሬ በፊት ነይ እስቲ እቀፊኝና ሳሚኝ " አላት እና
ጎትቶ ወደ እቅፍ አስገባትና እንደገና የለሊቱን ደስታ ዳግም
ሊደግመው ሊቋደሰው ሊጣጣመው ሊዋሀደው ፈለገ ከንፈሩን
ከከንፈሯ ጣዝማው ማር እንደገና ሊልሰው ተመኘ የተመኘውን
ፈፀመው መና ግን እንዳይልስ ከለከለቺው።
" ውይ አንተ ደግሞ እስቲ አትጨማለቅ ልኡል እውነት
ወንድማችን ነው ንገረኝ ከዛ ወደ ጀመርነው እንሄዳለን" አለች
ፈገግ ብላ እየተመለከተቺው ።
" እውነቴን ነው የኔ ቆንጆ ወንድማቹሁ ነው የመጀመሪያው
የአባትሽ የመጀመሪያ ልጅ ያልነገረሽ እናንተን አደጋ ላይ ላለመጣል
ነው እሺ " አላት በዚህ ወቀት በድንጋጤ ይሁን በደስታ ተነስታ
ልትሄድ ስትል " .... እረ ባክሽ ማንን ወስውሶ ዝም ብሎ ይኬዳል
አለቅሽም ...... " አላትና መልሶ አስተኛት እሷን ከስር እሱን ከላይ
ልብስ ማውለቅ የለም የተዘጋጀና የቀረበ የፍቅር ምግብ ነበር
ዝም ብሎ መቋደስ ሆነ ዳግም በበሀሩ መቅዘፍ በስሜቱ
መንሰፍሰፍ ህፃን ልጅ በጣም ፈልጎት እንደገኘ የሆነ ምግብ
ወይም መጠጥ እነሱም ይህ ጊዜ ይህ የስሜት ውህድ ጥፍጥና
ሳያልቅ እንዲህ በሆነ ሁኔታ እንዲቆይ እየተመኙ እየተቀያየሩ
መገላለብ ጀመሩ።
የዕነ መና ህይወት እንዲህ ሲቀጥል የዕነ ኤፍራታ እና ሙሉነህ
ደግሞ ገና ገና አልተኮተኮተም ግን ተተክሏል ልብ የፍቅር
መቀመጫ ነው እንጂ ፍቅር በልብ ውስጥ መናገሩን አይናገርም
አፍማ ለሌላ ነገር ይበርታ እንጂ ምን ወቶት ማፍቅርን ይናገራል
እሱ ( አፍን ማለቴ ነው ) የሚበረታው ሰውን ለማጣላት አንደኛ
ነው ሀሜትን ደግሞ አውራ በሉት ማን ይወዳደረዋል እና ምግብ
አላምጥ በሉት ወሬም አብሮ ስለሚያላምጥ በጣም ነው
የሚወደው እንደውም ይግረማቹሁ እንደ አፍ ፍቅርን የሚያራርቅ
አለ እንዴ? ልብ አካል በፍቅር ሲሰቃዩ ሲቃጠሉ እኔማ ምን
በወጣኝ አንተን (አንቺን) የምጠላህ ብሎ ሊያራርቅ ይሞክር የለ ።
የፍቅር ዋናው አቃጣሪ አይን ነው ልብ ውስጥ ያለን ፍቅር ሲያይ
መደበቅ በሚስጥር መያዝ አይችልም ስልምልም፣ ፍጥጥ ብሎ
ማየት፣ላለማየት ብንሞክር አትፍራ ( አትፍሪ) እየሄደ ያሳብቃል ።
ሙሉነህም ተሽሎት እቤቱ እናቱና ኤፍርታ እያስታመሙት
በነበረበት ወቀት እሷ ስትመጣ ቀጥታ አይኗን ያየዋል ስልምልም
፣ ድክምክም ፣ እርግብግብ ፣ ፍርትርት ፣ ሲል ሁሌም ያየዋል
ያቺን የመሰለች ጀግና ፍርሀት በልቧ ያልነገሰ እንደ ሰውነቷ
የቀጨጨች ሳትሆን ወኔዋ ጠብደል ዱርዬ የሚመስል ልጅ ዛሬ
ብርክ ይዟት መታጣጠፊያዎቿ አቅም ሲያሳየው መራመድ
ሲያቅታት ፍርሀት በደም ስሯ ተዋህዶ ልቧ መምታት ሲያቆም ሁሉ
አይኗ ሲያሳብቅ ያይ ነበር ብዙ ጊዜ በአንደበቷ እንድትነግረው
ጠይቋት ነበር አፍ ሰው ሲፋቀር አይወድም አይደል ሽምጥጥ
አድርጎ ዋሸ ። በቃ ሙሉነህ ተናደደ አፍ እያለ ሰው መፋቀር
ስለማይችል እናቱን እንደማይመጣ እና እዛው እንደሚያድር
ተናግሮ ከኤፍራታ ጋር ወጣ ። የግድ ነው በአፏ ስለማትናገር
መድፈር አለበት አለበለዚያ ለመና ህክምና ወንድማቸው ልኡል
ወደ ውጭ ሁለቱንም ይዟቸው ሊሄድ ሁሉም ነገር አልቆ ቢበዛ ከ3
እስከ 5 ቀን ነው ያላቸው በቃ ምሽቱን በደስታ በፍቅር ሲዝናኑ ቆዩ
ለሊቱ ሲገባደድ ወደ መኝታ ክፍሏ ይዟት ከገባ በኋላ" አላድርም
እቤቴ ውሰደኝ " ብላ ጠብ ገጠም ክርክር ነበር ያደረጉት " ይሄ
የፍቅር አላስ የሆነው የአፍ ስራ ነው" ብሎ ከጠብ ቀረሹ ክርክር
በኋላ አብረው አደሩ።
ለሊቱ በአፍ ተሸናፊነት በፍቅር አሸናፊነት ተጠናቆ ወገግ ያለች
ብርሀን ፀሀይ በወጣችበት ወቅት ሙሉነህ ተነስቶ ልብስ
ሲለባብስ ከለሊቱ አድካሚ የፍቅር ጨዋታ በኋላ አይኗን ገልፃ
አየቺው ለመሄድ እየተዘጋጀ ነው።
" መቼ ጨረስን ጀመርን እኮ ገና"አለችና ከተኛችበት እራቁቷን
ተነሳችና ይዛው መልሳ አሰተኛችውና የለበሰውን አወላለቀች እና
እላዩ ላይ........... እኔ በቃ አልናገርም ለሁለተኛ ጊዜ ምን
እንዳደረጉ።
ከ3 ቀን በኋላ መናም ኤፍራታም ልኡል ከሀገር ለመወጣት በቦሌ
በር ላይ አሳዳጊያቸው እማማ የፍቃዱ እናትና ልጅ እንዲሁም
ሙሉነህ እስከ እናቱ ነበር ተገኝተው ሽኝት ያደረጉት እንባ እንደ
ጎርፍ እየፈሰሰ ለፍቃዱም እማማን በአደራ ሰጠታው ወደ ወስጥ
ገቡ ። አውሮፕላኑ ተነስቶ ገና እንጭጭ የሆነውን ፍቅራቸውን
ይዞባቸው ሲበር በእንባ ተከተሉት።
ከረጅም ጊዜ በኋላ በየኔነህ እና ቢላዴን ( ኢሳያስ) ላይ
የተመሰረተባቸው ክስ ባለ ጭንብሉ ሰውን እያሳደደ የሚገለው
ቢላዴን እንደነበረ አዛዡም የኔነህ ሲሆን የዬኔነህ ሁለተኛ ክስ
የሰውን የሰውነት አካል አውጥቶ በመሸጥ ሁለቱም የእድሜ ልክ
እስር ተፈርዶባቸው ይህ የተወሰነው በሀገራችን የሞት ፍርድ ስለ
ቀረ እንደሆነ ተነግሯቸዋል።
ከውሳኔው በኋላ ፍቃዱ ኮማደሩ ጠርተውት ላደረገው ምርመራና
ውጤቱ ምስጋና ሰጥተውት በሚቀጥለው ሳምንትም እንደሚሸለም
ነግረውት በሁለቱ ብቻ ይቅር እንጂ ባለ ጭንብሎቹ ዋናዎቹ እነሱ
እንዳልሆኑና ያኔ ክብሩን አሳጥተውት ከስራ መባረሩ ዋናዋን
ወንጀለኛ መናን በፍቅር ስጦታ እንዳበረከቱለት ነገሩት ከዛ
እየተያዩ ተሳስቀው ተቃቀፍ።
ከሶስት ( 3 ) ዓመት በኋላ
ፍቃዱ ከእናትና ከልጁ ጋር ሙሉነህም ከእናቱ ጋር አበባ ይዘው
የዕነ መናን መምጣት በጉጉት ይጠብቃሉ።
ከጥቂት ቆይታ በኋላ መናም ሆነች ኤፍራታ እጅግ ተውበው
አምሮባቸው መናማ ፍፁም ተለይታለች ያ የተለጣጠፈ ቆዳዋ
ተወግዶላታል ፍፁም ውብና ማራኪ ሆናለች እነ ፍቃዱ ብቅ ሲሉ
አያቸው ወዲያው በድንጋጤ አይናቸው ፈጠጠ መናም ኤፍራታም
በግምት የሁለት የሁለት አመት ህፃን ሴት እና ወንድ ይዘዋል
ከእነሱ ኋላ ሁለት ወንዶች እየተሳሳቁ ይመጣሉ በእጆቻቸው
የያዙትን አበባ ጨመቁት ልባቸው ተሰበረ ሙሉነህ ወደ ፍቃዱ
ዘወር ብሎ።
" እኔ የምልህ ፍቄ የመርሳት በሽታ ካልያዘኝ ወደ ውጭ የሄዱት
ትዳር ይዘው ልጅ ለመውለድ አይደለም አይደል" አለው
" እኔንጃ እኔም እረሳሁት " አለ ፍቃዱ አበባውን ጨምድደው
እየያዙት ።....ወሬያቸዉን ሳይጨርሱ መና እና ቀጮ ሩጠው መጥተው ተጠመጠሙባቸዉ በስስት አቀፏቸዉ...ፍቃዱ ግራ ተጋብቶ ደንዝዟል መና ስታቅፈው መልሶ አላቀፋትም...ቀዝቅዟል..
"ምን ሆንክ ዉዴ በመምጣቴ ደስ አላለህም ወይስ አላወቅከኝም? አለችዉ መና ከእቅፉ እየወጣች ...
"እንደሱ አይደለም መና አንቺን ለማየት አለምን አጠፋለሁ ግን ልጁ" አላት በእጁ እየጠቆመ..
መና ጣቷን ፍቃዱ ከንፈር ላይ አደረገችዉና ፈገግ ብላ ይሄማ ከመሄዴ በፊት ሁለታችን የሰራነዉ ልጃችን ኪሩቤል ነዉ አለችዉ...
ፍቃዱ ባለማመን "ምን...? አላት የደስታ ሲቃ እያነቀዉ...
"ልጃችን" ስትለዉ ከስር ስቅስቅ አርጎ አንስቷት አብረዉ ለሰከንዶች ተሽከረከሩ...
.
.
🔥ተፈፀመ🔥

ጭንብል እንዴት ነበር እስኪ ያላችሁን ሀሳብ አስተያየት
@nahoom_g ላይ ያድርሱን !!

እስካሁን በጥሞና ስለተከታተላችሁን እናመሰግናለን🙏
ሀበሻ ጣፍጭ 😍
ከአማርኛ ወደ እንግሊዘኛ የሰዎች መዝገብ ቃላት.......
.
አቶ ደም መላሽ..........mr. blood return
ወ/ሮ አልጋነሽ.......... mrs you are a bed
ልጅ ሺመልስ........... son return a thousend
ዱባለ............. drop he said
አልጋ ወራሽ............ bad take over
ዘራብዛ......... increase race
አለማየሁ............ i saw world
አይናለም................ eye world
ግራዝማች ሺበሺ.......... left leader thousend by
thousand
አቶ ማስረሻ...........mr you make me forget
ሙሉ ነህ........... you are full
መንግስቱ................ the goverment
በልሁ............. by this stubborness
ማን ያዘዋል.......... who order him
አለምጸሀይ.............. world sun
ሁላገርሽ...............everything your country
👉@wisdomic
#ሀበሻ ምርጥ ግጥም
---------- የገበሬው ምርቃት --------
🗣
ከልጅ አመዳም
ከጥጃ ቀንዳም
ከሀምሌ በረዶ
ከዘመድ መርዶ
ከዘመድ ምቀኛ
ከአህያ ቀበኛ
ይጠብቃችሁ አሜን።
🗣
ከደጋ ብቅሉን
ከቆላ ጌሾውን
ይስጥልኝ !
🗣
ከጓሮ ማረስን
በቁና ማፈስን
ይስጥልን !
🗣
ከሴት ጨቅጫቃ
ከወንድ ጫንቃ
ይለያችሁ
አሜን !
ዕልልልልልልልልልልል.....😄😄😄
👉 @wisdomic
ለራስ የሚነገር መልዕክት ___
መልዕክት 1⃣
እራስክን ከማንማ ጋር አታወዳድር፡፡ ይህን ባደረክ ጊዜ
እራስክን በራስህ እንደሰደብክ ቁጠረው፡፡
መልዕክት 2⃣
ቁልፍን ያለመክፈቻ ማንም እንደማይሰራ ሁሉ ፈጣሪም
መፍትሄ የሌለው ችግር እንዲገጥምን አይፈቅድም፡፡
መልዕክት 3⃣
ደስታህን ከራስህ ባራቅህ ጊዜ ሕይዎት በአንተ ላይ
ትስቃለች፡፡ ደስተኛ በሆንክ ጊዜ ሕይዎት ፈገግታዋን
ትለግስሃለች፡፡ ሌሎች እንዲደሰቱ ምክንያት በሆንክ ጊዜ ግን
ሕይዎት የከበረ ሠላምታዋን ታቀርብልሃለች፡፡
መልዕክት 4⃣
ማንኛውም ስኬታማ ሰው ከበስተጀርባው አስቸጋሪ ታሪኮች
እንዳሉት ሁሉ ማንኛውም የችግር(አስቸጋሪ) ታሪክ
መጠናቀቂያው ስኬት ይሆናል፡፡ ስለሆነም ችግሩን ተቀበልና
ለስኬት ተዘጋጅ፡፡
መልዕክት 5⃣
የሌሎችን ስህተት ለመተቸት በጣም ቀላል ነው፡፡ ከባዱ ነገር
የእራስን ስህተት መረዳቱ ላይ ነው፡፡
መልዕክት 6⃣
የተፈጠረልህ መልካም አጋጣሚ ባመለጠህ ጊዜ እዛው
ባለህበት ቁመህ አይንህን በእንባ አትሙላ፡፡ ቀጣዩንና
የተሻለውን መልካም አጋጣሚ እንዳታይ ይከልልሃልና፡፡
መልዕክት 7⃣
ለችግር ፊትን ማዞር ችግሩን አይቀይረውም ችግሩን መጋፈጥ
እንጅ፡፡ በሌሎች ቅሬታን ከማሰማት እራስን ለውጦ ሠላምን
መግዛት፡፡
መልዕክት 8⃣
ስህተት ስህተቱ በተፈጠረበት ወቅት ስሜትን ይጎዳል፡፡
ከዓመታት በኋላ የስህተቶች ድምር የሚፈጥረውና ወደ ስኬት
የሚያመራው ከስህተት መማር ተሞክሮ(ልምድ) እንለዋለን፡፡
መልዕክት 9⃣
የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚሆነው፣
የተጠረበ ድንጋይ ሀውልት እንደሚሆነው ሁሉ፣
አንተም በብዙ ችግር ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን
አትርሳ፡፡ በመሆኑም ስትሸነፍ ጠንካራ ስታሸንፍ የተረጋጋ ሁን፡፡

@wisdomic
#ተፈፀመ

ነብሴን ጨፈለ‘ኳት ~ ስጋዬ #ተፈፀመኝ
ለኔ ብሎ ሲሞት ~ ለእርሱ መኖር ከብዶኝ
===||===
©ሙሉቀን ሰ.
@wisdomic
ድሎት እየዘሩ

ይቅርብኝ ፍሪዳው፥
አልጠግብ- ባይ ይብላው
ወይኑም በፅዋ ላይ ፤ እንደ እንኮይ የቀላው
ግዴለም ይለፈኝ !

ጊዜ ምቾት ነስቶ
ምንጣፉን አንስቶ ፤
ፅናቱን ያውሰኝ
በመጋዝ ጠርዝ ላይ፤
መራመድ ከተማርኩ፤ ማንም አይመልሰኝ::

አውቃለሁ

አሳር አሻራውን፣ ግንባር ላይ ሳያትም
ድሎት እየዘሩ ፥ ድል አይመረትም ::

©በእውቀቱ ስዩም
@wisdomic
እጠብቃታለው

አይን የማያየውን ሀሳብ ያያል ሄዶ
እጅ የማይነካውን ልብ ያንቃል አሳዶ
ተመለሽ አልልም ሞት ለያይቶን እንደው
ያባት ያያት እርስት
የመጨረሻው ቤት
ለፀጥታው አለም
እንግዳ አይደለንም
መለየት እንደሆን
ለይቶ ያስቀረን
ሃሳብ ይላላካል
ሃሳብ ይገናኛል
አይን የማያየውን ሀሳብ ያያል ሄዶ
ጆሮ የማይሰማውን
በፀጥታው ቦታ ልብ ያንቃል አሳዶ
ማን ያውቃል ለሞትም
ይኖራል መቃብር
ጉዞ አይቋረጥም
አለም እያረጀ አለም ይፈጠራል
አበባ በፍሬው ህይወትን ያድሳል
የፅጌረዳ እሾህ ያበባው ጠባቂ
ሳቂ የለም ሳቂ
እሾህ እሆናለው
የምወዳትን ልጅ እጠብቃታለው
በቁም ያሰረኝን የሃሳብ ሰንሰለት
ሰብሬ በጥሼ እኮበልላለሁ፡፡
እስከ ዓለም ዳርቻ እከተላታለሁ
ሳላያት አልቀርም አለ ስጦታዋ
አለ ትዝታዋ እሷን የሚያስታውስ
ስበላ ስጠጣ
ስተኛ ስነቃ ሳስብ ስተነፍስ
እሷን መርሳት አልችል
ፍቅር እምነት ህይወት
አብረን ተደስተን አብረን ተቸግረን
አበባ ለቅመናል ከወንዝ ዳር ሄደን
እሸት ፈልፍለናል መስክ ላይ በልተናል
ልብሳችን በስብሶ በዝናብ ሄደናል
እሳት አንድደናል
ፍሙን ተርኩሰናል
በርዷት ተኮራምታ ህፃኗ ጨረቃ
ፊቷ ደም ሲመስል ፀሀይ ተዘቅዝቃ
ሁሉንም አይተናል
በሁሉም ስቀናል
ህይወት እንደዚህ ነው
ዓለም ነው ብለናል
እርሷን መርሳት አልችል
እፈልጋታለው
እከተላታለው
እጠብቃታለው፡፡


©✍️ገብረክርስቶስ ጸስታ
@wisdomic
​​ሚስቶች ተሰበሰቡና እግዜርን ሊያናግሩ ሄዱ አሉ....
(በአሌክስ አብርሃም)
On @Winaedit2

እግዜር - ምን ሆናችሁ ልጆቸ
ሚስቶች -መረረን !
እግዜር - ምነው ምን የሚያማርርነገር ተፈጠረ
ሚስቶች - እኛ ሴቶች ጫናው በዛብን አንገፈገፈን እኛ አርግዘን፣ እኛ አምጠን ፣እኛው አጥብተን... አልቻልንም ! ይሄ ጉዳይ ስራ እንዳንሰራ ሆነ ተብሎ ወንዶችን ለመተባበር የተደረገ ሴራ ነው ይስተካከልልን አሉ እያለቀሱ፡፡
እግዜር -ጥሩ! ምን እንዲደረግላችሁ ትወዳላችሁ ታደያ
ሚስቶች -ቢያንስ ከማርገዝ ፣ከማማጥ ወይም ከማጥባት ወንዶች አንዱን የተፈጥሮ ግዴታ ያግዙን
(እግዜር ቅዱስ ገብኤልን ጠራና‹‹ እስቲ ወንዶችን ጥራልኝ ››አለው ወንዶች ገቡ)
እግዜር - ሴቶቻችሁ ተማረዋል ተመካከሩና ከማርገዝ ፣ከማማጥ ወይም ከማጥባት አንዱን አግዟቸው
ወንዶች ተመካከሩ 9 ወር መሸከም ይደብራል ....ማጥባትማ የባሰ ነው ....ያው ቢያምም ምጥ ይሻለናል አጠር ያለ ሰአት አምጠን ወደድራፍት ቤት በቃ!! ወሰኑ!
እግዜር- ‹‹እንግዲህ ይህ ውሳኔ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ሴቶች ያረግዛሉ ልክ ምጥ ሲጀምር ያስረገዘው ወንድ ያምጣል !በሰላም ሂዱ›› ብሎ ሸኛቸው !!
ከውሳኔው በኋላ የመጀመሪያዋ እርጉዝ በመንደሩ ስሟ የተጠራ ቆንጆ እና ሃብታም ወ/ሮ ሄለን ነበረች ባለቤቷ አቶ ዘሩ ጋር ያላቸው ፍቅር ሁሉን የሚያስቀና እግዜር ሁሉን ያሟላላቸው የተራበ የሚያበሉ የታረዘ የሚያለብሱ ወዘተ ነበሩ .....ይህን ደግነታቸውና ፍቅራቸው ነው የአዲሱ ህግ አስጀማሪ ያደረጋቸው ተብሎ በመንደሩ ተወራ...6..7..8...9 ወር ሞላት ወ/ሮ ሄለን ! ባለቤቷ አቶ ዘሩ ተዘጋጀ የህዝብ ጆሮ አይን አቶ ዘሩ ላይ ሆነ ወንድ ሲያምጥ ለማየት .....ቀኑ ገፋ ምጥ የለም !ልክ 9 ወር ከ9 ቀን ሆነ ምንም የለም! ....በቀጣዩ ቀን ማታ ይህን ተአምር ሊያይ ግቢውን የሞላው ሰው ሁሉ ግቢው በር ላይ ተንጫጫ... ምንድነው ብለው ቤት ውስጥ ያሉት ሲወጡ የነወይዘሮ ሄለንን ‹‹ ዘበኛ ምጥ እያጣደፈው ነበር !›› ያስረገዘው ወንድ ያምጥ አልነበር ውሳኔው ! አቶ ዘሩ ማሪያም ማሪያም በሚለው ህዝብ መሃል ‹‹ በማሪያም ውርደት›› ብለው እራሳቸውን ሳቱ!!
ሴቶችም ያኔውኑ ማታ ይሄ ውሳኔ ይነሳልን ሲሉ ወደግዜር ቀርበው ጮሁ የሚበዙት ቀናቸው የደረሰ ነፍሰ ጡር ሴቶች ነበሩ!

join & share
@wisdomic
በ1985 አንድ የኮካኮላ ሰራተኛ የፔፕሲ ሰራተኛን ሊያገባ መሆኑ ተደርሶበት ከስራ ተባሯል

#SHARE_ያድርጉ

ቻናላችንን ለወዳጆ ያጋሩ
Join and share

📢 @wisdomic
Amazon ባለቤት ስራውን ቢያቆምና በየቀኑ 1000000ዶላር ቢያወጣ ገንዘቡን ለመጨረስ466አመት ይፈጅበታል 😳😳

#SHARE_ያድርጉ

ቻናላችንን ለወዳጆ ያጋሩ
Join and share
📢
@wisdomic
የልብ ቅርፅ
.
.
ፍቅርን ያህል ነገር...
ተሸክሜ ስኖር ፣ በልቤ ትከሻ
"ቃል አጠስኖር የሚል....
ቃል ካ'ፌ አይወጣም ፣ ላወድስሽ ስሻ።
........................................................
እንደውም ሳፈቅርሽ ፣ ቃል ነው የተረፈኝ
ሁሉ ያጥርብኛል.....
በልብሽ ቅርፅ ውስጥ ፣ መውደድሽ ሲያገዝፈኝ።
...............................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ሰፊ ያልሁት አለም ፣ ባንድ እርምጃ አለቀ
ሳልሄደው ሚደክመኝ...
ተራራና ጋራው ፣ ከግሬ ስር ጠለቀ።
"ሩቅ" ያልሁት ሰማይ..
ሩቅ የሚመስለኝ ፣ ነካሁት በስንዝር
ጨረቃና ፀሀይ....
ከኮከብ ያንሳሉ ፣ ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር።
.......................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
ንጉስን ከዙፋን ፣ ማርከው የሚያወርዱ
የሀያላንን አቅም ፣ በጥቅሻ ሚያርዱ
ቆነጃጅት ሴቶች ...
"ቃል አጠረኝ" በሚል ቃላት የተሞሉ
ከፍቅርሽ ግዝፈት ስር..
ቃል ተገኝቶላቸው ፣ "ፋንጋዎች" ተባሉ።
.........................................
ሳፈቅርሽ ይህ ሆነ...
"ቃል አጠረኝ "በሚል...
ባፍቃሪ አንደበት ፣ ቃል ተትረፈረፈ
ሁሉን አሳንሶ...
በልቡ ቅርፅ ውስጥ ፣ ፍቅሩን አገዘፈ
አለሙን ሰርዞ ፣ ፍቅሩን ብቻ ፃፈ!!!
..........................................
ሳፈቅርሽ ይህን አልሁ...
ፍቅርን ተሸክሞ ፣ የሚኖር ልቦና
ሁሉም ከፍቅርሽ ስር ፣ መሆኑን አውቅና
አንቺን ለማወደስ .፣..እኔም ቃል ያጥረኛል
"ቃል አጠረኝ "ማለት...
ቃል እንደሆነ ግን ፣
ፍቅርሽ ይነግረኛል!!!

©በላይ በቀለ ወያ

@wisdomic
ለግዜር የተፃፈ ደብዳቤ

እንደምነህ እግዜር
ሰማይ ቤት እንዴት ነው
እመጣለሁ ብለህ ቆየህሳ ምነው?
እኛማ.....
ለእልፍ አእላፍ አለቃ… ማመልከቻ ፅፈን
ለወፈ ሰማይ ህዝብ …መድረክ ላይ ለፍፈን
ፆለት ቤታችንን ….እኛው ላይ ቆልፈን
የምድር አተካራ …..ህግጋቱን አልፈን
ደብዳቤ ላክንልህ፤
አይንህን ካየነው ሁለት ሽ ዘመን እንደቀልድ አለፈ
የመምጣትህ ተስፋ እየኮሰመነ መቅረትህ ገዘፈ
እንደውም እንደውም...
‹‹በመጣለሁ ተስፋ ሁለት ሽ ዘመን ቀጥሮን ከጠፋ
በቀጠሮው ሰአት መምጣት ከተሳነው
‹‹እግዜር አበሻ ነው›› እያሉ ያሙሃል!!
እኔ ምን አውቃለሁ...
አመስግነው ሲሉ እልልታ የማቀልጥ
ቃሉን ስማ ሲሉኝ ...ሰባኪው እግር ስር በደስታ እምቀመጥ
እግዚኦ በሉ ሲባል ...እንባየን የማፈስ
ሃሌ ሉያ ሲሉኝ ...በሳቅ ልቤ እሚፈርስ
ምናምኒት እውቀት ውስጤ ያልፀደቀ
እንበረከክበት ጉልበቴ ያለቀ
እኔ ምን አውቃለሁ...
ግን አንተ ደህና ነህ?
ከምር እንደሚያሙት ምፅአት ቀረ እንዴ ?
የሰናፍጭ ቅንጣት ታክል ጥርጣሬ አትከፋም አንዳንዴ!
ከሆነስ ሆነና ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
አብረሃም ሰላም ነው...
እዛስ ቤት ገነባ ዛሬም በድንኳን ነው ?
እኛማ ይሄውልህ...
በቤት ኪራይ ችንካር እየተሰቀልን
‹‹ኤሎሄ›› እንላለን ጎጆ እንድጥልልን....
ወደላይ ገነባን ወደጎን አሰፋን
ወደላይም ከላይ ወደጎንም ከጎን እ ን ደ ጉ ድ ተገፋን
ቤት ለእንግዳ ማለት ጭራሹኑ ጠፋን !!
አባታችን ሙሴ እነዴት ነው ለክብሩ
ውቂያኖስ መክፈያው ደህናናት ብትሩ?
እኛማ ይሄውልህ....
እንጀራ ፍለጋ ባህር ስናቋርጥ
የተስፋዋን ምድር አሸዋ ሳንረግጥ
የትም ውሃ በላን የትም አሳ ላሰን
ን ገ ር ል ን ና ብትሩን ያውሰን ?!
እናልህ እግዜር ሆይ....
ከተስፋዋ ምድር ወደሌላ ተስፋ አለን እየኳተን
መሄጃው ሲገርመን መመለሻ መንገድ መቆሚያ ቦታ አጥተን...!
ላባታችን ሙሴ እንደምትልልን...
‹‹የመሄድ ዘመን ነው ባህር የመሻገር
‹‹ዱላህን ላክልን›› ብሎሃል በልልኝ!!
ሰማይ ቤት እንዴት ነው? ....ዳዊትስ ደህና ነው?
ዛሬም ይዘምራል ...ዛሬም ይፎክራል ?
ሰላም ነው ጠጠሩ .... ሰላም ናት ወንጭፉ?
እዛስ አቅል ገዛ ጎሊያድ ተራራው ጎሊያድ ግዙፉ?
እልፍ አላፍ ጎሊያድ ከቦን ሲደነፋ
ወንጭፉን ጠቅልሎ ምነው ዳዊት ጠፋ ?
ብሎሃል በልልኝ!!
ለረከሰ ጠጠር ለሞላ ወርዋሪ
‹‹ወንጭፍህን ስጠው ለዚህ ታሪክ አውሪ››
ብለህ እዘዝልን!!
እንዴት ነህ ጌታ ሆይ... ሰማይ ቤት እንዴት ነው?
የሙሴ አልጋ ወራሽ እያሱ ሰላም ነው....?
ያቆማትን ፀሃይ ግቢ ቢላት ምነው?!
ያው እንደምታውቀው
አስራ ሶስት ወራት ነው ፀሃይ የምንሞቀው...
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
ኧረ ፀሃይ በዛ
የመጣው ወር ሀሉ ፀሃይ እያዘለ
የተሸመው ሁሉ ‹ፀሃይ ነኝ› እያለ
ያስራ ሶስት ወር የግዜር ፀሃይ
ያስራ ሶስት ወር የሰው ጀምበር
ባቃጠላት ምድጃ አገር
ምን ታምር ሊኖር ይችላል ፀሃይ ሁኖ እንደመፈጠር!!
ኧረ እግዜር በናትህ....
ኧረ እግዜር በናትህ...በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና!!
እናልህ እግዜር ሆይ ማጣፊያው አጥሮናል
ስም ያለው ሞኝ ነው ሁሉም ይጠራናል...
ጳውሎስ ሲሉን ...አቤት
ጴጥሮስ ሲሉን ...ወይየ
ይሁዳ ሲሉንም አቤት እንላለን
ስማችንን ሸጠን ...ሰላሳ ጭብጨባ እንቀበላለን!
ስንቱ ባለካባ ክብርህ የተሰጠው
ለሰላሳ ፍራንክ ለተራ ጭብጨባ አደራህን ሸጠው !
ተወው የኛን ነገር ...ሰማይ ቤት እንዴት ነው ....
ሂዋንስ ደህና ናት?
ያው የልጅ ልጆቿ በግሯ ተተክተው
የፍሬው ሲገርምህ ግንዱንም አንክተው
ለፍጥረተ አዳም ባይኑ ያገምጡታል
ሰይጣንም ደህና ነውኑሮ ተስማምቶታል....
ሰውን ለማሳሳት ላይ ታች ማለት ትቷል
ሳይጠራው የሚጎርፍ ህዝብ በዝቶለታል...!
ኧረ እግዜር በናትህ በጭንቅ አማላጇ
ባዘለህ ጀርባዋ ባቀፉህ እጆቿ
ወይ ዝናብ ላክልን ወይ ዝናብ ሁነህ ና
ሙቀት ገደለና!!

©አሌክስ አብርሃም
@wisdomic
Messages in this channel will be automatically deleted after 1 day
2024/05/04 19:16:15
Back to Top
HTML Embed Code: