Telegram Web Link
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ስልጠናው በተግባር ተደግፎ በዘርፉ መጽሐፍ እስከማዘጋጀት የደረ ሰ ልምድ ባላቸው ባለሙያ እንደመሰጠቱ የክህሎት ማሳደጊያ ስልጠናውን የወሰዱ አካላት  በየትምህርት ቤቱ ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ ግንዛቤ በመፍጠር የአካቶ ትምህርት ስርአቱ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።



የቢሮው የልዩ ፍላጎት ትምህርት ባለሙያው አቶ ፀጋዬ ሁንዴ በበኩላቸው ስልጠናው የመምህራንን እና ርዕሳነ መምህራንን የምልክት ቋንቋ ክህሎት በማሻሻል መስማት የተሳናቸው ተማሪዎችን በአግባቡ በመደገፍ  በከተማ አስተዳደሩ ተግባራዊ የተደረገው የአካቶ ትምህርት በሚጠበቀው ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸው ቢሮው በቀጣይ ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ተመሳሳይ ስልጠና መስጠቱን አጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል።




መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
16👍4🥰1
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከናወነ ባለው የ2017 የአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ በይፋ ተጀምሯል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብር የከተማዋን ገፅታ ውብና ማራኪ ለኑሮ ምቹ ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡



የዘንድሮ ችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር የሚከናወነው በሸገር ወንዝ ከእንጦጦ ተራራ ጫፍ በመነሳት እስከ ፒኮክ በሚደርስ 21 ኪሎ ሜትር በሚሸፍን 860 ሄክታር መሬት ላይ መሆኑን ያነሱት ከንቲባዋ፣ በዚህ መርሐ-ግብር የተሳፉ አሻራቸውን በእነዚህ አካባቢዎች ማስቀመጣቸው ትልቅ ዕድል መሆኑን ተናግረዋል፡፡


በዛሬው የችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ-ግብር ላይ ተማሪዎች መምህራንና የትምህርት አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።



መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
19🤮6👍4👎2
ለ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ገለጻ/Orientation/ ተሰጠ፡፡

(ሰኔ 22/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት በቂ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት በመከናወን ላይ የሚገኙ ሲሆን ዛሬ በነገው እለት ለፈተና ለሚቀመጡ ለተፈጥሮ ሳይንስ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች የፈተና ገለጻ/Orientation/ ተሰጥቷል፡፡

ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣባያዎች መካከል ከሆኑት መካከል በአብሮህት ቤተ መፃህፍትና በአድዋ ሙዚየም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ እና ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ዲናኦል ጫላ ተገኝተው ተማሪዎችን አበረታተዋል።
20👎10😁2🖕1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተናን በኦላይን ለመስጠት ዝግጅቶች መጠናቀቃቸዉን እንዲሁም ፈተናው ከሰኞ ጀምሮ እንደሚሰጥ የገለጹ ሲሆን ዛሬ ለመጀመሪያ ዙር ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች በሁሉም የፈተና መስጫ ጣቢያዎች ላይ ሰለ ፈተናው ገለፃ መሰጠቱን የተናገሩ ሲሆን ፈተናው በሚሰጥበት ወቅት ጠንካራ የፍተሻ ስርዓት ሰለሚኖር ተፈታኝ ተማሪዎች በጠዋቱ በመገኘት በሂደቱ ውስጥ ማለፍ እንዳለባቸው ፤ በፈተና አሰጣጡ ላይ የተከለከሉና የተፈቀዱ ነገሮችን በደንብ በመገንዘብ ፈተናው ውጤታማ እንዲሆን የሚናቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ለሁለተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ ከቀኑ 7፡30 ፤ ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ጠዋት 2፡30 ፤ ለሁለተኛ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች እሁድ በ29/10/2017 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ በኦላይን ፈተና መስጫ ጣቢያዎች ላይ ገለጻ/Orientation/ በቀጣይ የሚሰጥ መሆኑ ቀደም ሲል መገለጽ ይታወሳል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
26👎7👍3🖕1
ዛሬ ከሁሉም የከተማችን የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተክለናል!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን አና ህዝቦቿን ይባርክ

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

(ሰኔ 22/2017 ዓ.ም)

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
39👎20👍11🤮8🖕6😁4💩2
2025/07/12 15:42:27
Back to Top
HTML Embed Code: