Telegram Web Link
በ25/75 ፕሮግራም የተደራጁ ቤት ፈላጊ መምህራንን ወደ ስራ ለማስገባት እንዲቻል የተቋቋመው የቴክኒክ ኮሚቴ እስካሁን ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

(ሰኔ 27/2017 ዓ.ም) በመርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላትን ጨምሮ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የስራ ኃላፊዎች ፣ የመሬት አስተዳደር ቢሮ እና የህብረት ስራ ኮሚሽን አመራሮች እንዲሁም የመምህራን ማህበር ተወካዮች ተሳታፊ ሆነዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የቴክኒክ ኮሚቴው የመምህራንን አቅም እና ወቅታዊ ዋጋን ታሳቢ በማድረግ ባቀረባቸው የዲዛይን አማራጮች ዙሪያ በማህበር ለተደራጁ መምህራን ግንዛቤ በመፍጠር በቀጣይ በፍጥነት ወደ ግንባታ እንዲገቡ በትኩረት መስራት እንደሚገባ ጠቁመው በመሬት ልማት አስትዳደር ቢሮ በኩል ለግንባታው የሚሆን ቦታ ዝግጁ የማድረግ እና ተያያዥ ጉዳዮችን መስራት የሚጠበቅ መሆኑን አመላክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ቅድስት ወልደጊዮርጊስ በበኩላችው የቴክኒክ ኮሚቴው ያቀረባቸው አማራጮች የመምህራኑን አቅም ታሳቢ ያደረጉ እና በፍጥነት ወደግንባታ የሚያስገቡ በመሆናቸው በፍጥነት ወደ ግንባታ በመግባት መምህራኑ የቤት ባለቤት እንዲሆኑ ተቋማቸው በትኩረት የሚሰራ መሆኑን አስገንዝበዋል።

ለግንባታ የተለዩ ቦታዎችን በፍጥነት ርክክብ በማድረግ በቀረቡት የዲዛይን አማራጮች መሰረት ወደ ግንባታ መግባት እንዲቻል የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተሰጣቸው ኃላፊነት መሰረት በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የቴክኒክ ኮሚቴው ባቀረበው ሪፖርት አስታውቋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
በትምህርት ሴክተሩ በርካታ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን በመስክ ምልከታ ማረጋገጡን ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን አስታወቀ።

(ሰኔ 27/2017 ዓ.ም) የሱፐርቪዥን ቡድን ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ባካሄደው የድጋፍና ክትትል ግብረ መልስ ዙሪያ የቢሮው ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተገኙበት ውይይት ተካሂዷል።

የሱፐርቪዥን ቡድኑ ከቢሮ ጀምሮ በተመረጡ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባካሄደው የመስክ ምልከታ በርካታ ውጤታማ ስራ በመሰራት ላይ እንደሚገኝ መረጋገጡን በግብረ መልሱ የተገለጸ ሲሆን በ2017 ዓ.ም የተማሪዎችን የሒሳብና እንግሊዘኛ ውጤት ለማሻሻል የተዘጋጀው ስትራቴጂ በተማሪ ውጤት ላይ መታየት መጀመሩ ፣ በትምህርት ተቋማት መካከል ተቀራራቢ አፈጻጸም እንዲኖር ተከታታይ የድጋፍና ክትትል ስራ መሰራቱ ፣ የትምህርት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በርካታ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸው ፣ የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን ውጤታማ ለማድረግ የ90 ቀን እቅድ ተዘጋጅቶ ወደ ተግባር መገባቱ ፣ የ2018 ዓ.ም እቅድ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መደረጉ ፣ ከቢሮ ጀምሮ በየደረጃው የተቀናጀ አመራር በመፍጠር የመማር ማስተማር ሂደቱ የሚደገፍበት ስርአት መፈጠሩ እንዲሁም የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ የተሰሩ ስራዎች ሴክተሩ ውጤታማ እንዲሆን ከተከናወኑ ተግባራት መካከል የሚጠቀሱ መሆናቸው ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ የሱፐርቪዥን ቡድኑ ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ በመውረድ የትምህርት ዘርፉን ለመደገፍ ላደረገው ድጋፍና ክትትል ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በሱፐር ቪዥን ቡድኑ የተሰጡ ግብረ መል ሶችን መሰረት በማድረግ የተሻለ ስራ እንደሚሰራ አስታውቀዋል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
2025/07/07 13:02:48
Back to Top
HTML Embed Code: