Telegram Web Link
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበይነ መረብ (online) የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ የ2ኛ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች ፈተናቸዉን በመውሰድ ላይ ይገኛሉ፡፡

(ሰኔ 30/2017 ዓ.ም) ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በ108 የማስፈተኛ ጣቢያዎች ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን በ2ኛ ዙር ፈተና ከ13ሺ በላይ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ መረብ በመውሰድ ላይ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከምክትል ቢሮ ኃላፊዎች ከአቶ ዲናኦል ጫላ እና ከአቶ ሳምሶን መለሰ እንዲሁም ከአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ትምህርት ቤት ኃላፊ ከአቶ ከበደ ድሪባ ጋር በመሆን 2ኛው ዙር ፈተና ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል አንድ በሆነው በአስቱ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የፈተናውን ሂደት በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
17🖕1
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የክረምት የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት የንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር አካሄደ።

(ሰኔ 30/2017 ዓ.ም) የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ2017 ዓ.ም የክረምት የተማሪዎችና የመምህራን ስፖርት ንቅናቄ ማስጀመርያ መርሃ ግብር በቀን 30/2017 ዓ.ም በዳግማዊ ሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ በክፍለ ከተማው ስር የሚገኙ ከሁሉም ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ መምህራን፣ የትምህርት ቤት አመራሮች፣ ተማሪዎች እና የትምህርት ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን በዕለቱም ሁሉም አካላትን ባሳተፈ መልኩ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተደርጓል።

በንቅናቄ መክፈቻ ስነስርዓቱ ላይ የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ሰማኝ አስታጥቄ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በመልዕክታቸውም ትውልድን በአካል ብቃት እና በስነልቦና ማብቃት አንዱ የትምህርት ተግባር እንደሆነና በHንድሮም አመት የክረምት ወቅት በሁሉም ትምህርት ቤቶች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ያለማቋረጥ መካሄድ ስላለበት ከዛሬ ጀምሮ ባሉት ቀናት ተማሪዎች እና መምህራን እንዲሁም የትምህርት ማህበረሰብ የሚሣተፋበት የስፖርት እንቅስቃሴ በሁሉም የትምህርት ተቋማት እንደ አንድ ተግባር በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ ማሳወቃቸዉን የክፍለ ከተማው ኮሙኒኬሽን ዘግባል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
14
በልደታ ክ/ከተማ የበጋ መዝጊያ እና የክረምት ማስጀመሪያ የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ተካሄደ።

(ሰኔ 30/2017 ዓ.ም) በልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት እና ወጣቶችና ስፖርት ጽ/ቤት አስተባባሪነት የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ላይ ትምህርት ቤቶች ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በማስ እስፖርቱ ላይ ተገኝተው እንደገለፁት ፥ስፖርት እንቅስቃሴ ለጤናችን አይነተኛ ፋይዳ አለው ብለው ከክረምት የማጠናከሪያ ትምህርት በተጨማሪ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ተማሪዎች ጤናማ እና ደስተኛ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

አቶ ጥላሁን አክለውም ፦ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ የተማሪዎች ፍቅርን ለማጠናከር የጎላ ፋይዳ እንዳላው በመጥቀስ የስፖርታዊ እንቅስቃሴ ባህላችን ልናዳብር ይገባል ብለዋል።

የልደታ ክ/ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አሰፋ ግርማ በበኩላቸው በክረምት በትምህርት ቤቶች ላይ የተማሪዎች የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንደሚደረግ ገልፀው ለተሳታፊ ትምህርት ቤቶች የምስጋና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
6
2025/07/08 20:11:02
Back to Top
HTML Embed Code: