Telegram Web Link
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር 5ኛ ዙር የትምህርት ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ አካሄደ፡፡

(ሰኔ 14/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር 5ኛ ዙር የትምህርት ጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር በየደረጃዉ የሚገኙ አባላትና መምህራን በተገኙበት አካሂዳል፡፡

በመድረኩ የተገኙት የአዲሰ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ማህበሩ የትምህርት ጥራት እንዲጠበቅ የራሱን ሚና እየተወጣ መሆኑን መድረኩ ያሳያል ያሉ ሲሆን ማህበሩ የመምህራንን ጥቅማ ጥቅም ከማስጠበቅ በተጨማሪ በዚህ አይነት ስራ ላይ መሳተፍ ተጠናክሮ መቀጠል ይጠበቅበታል እንዲሁም በቀጣይ የቀረቡ ጥናቶች ታትመው ለትምህርት ልማት ስራው ግብዓት እንዲሆኑ ተደራሽ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ ሰላም ለትምህርት ትምህርት ለሰላም ፣ በተማሪዎች ስነ ምግባር ላይ እና ተከታተይ ምዘና ላይ ያጠነጠኑ 3 ጥናታዊ ጽሁፎች መቅረባቸው ገልጸው ጥናቶቹ ችግር ፈቺና ለቀጣይ ስራ አቅም የሚፈጥሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
55👍7
ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 989 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው።


(ሰኔ 15/2017 ዓ.ም) ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 1 ሺህ 989 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት እያስመረቀ ይገኛል፡፡


የኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርስቲ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ ዲግሪ እና በፒ.ኤች.ዲ ያስተማራቸውን ተማሪዎች በአድዋ ድል መታሰቢያ አዳራሽ እያስመረቀ ነው፡፡


በምረቃ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዘላለም ሙላቱ (ዶ/ር)፣ የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባላት፣ የየኮሌጁ ዲኖችና የሥራ ኃላፊዎች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች ታድመዋል፡፡




የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮችን ለማግኘት

https://linktr.ee/aacaebc
29👍9👏3👎1
እንኳን ደስ አላችሁ!


ከአንጋፋው ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ ዛሬ የተመረቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ።


ውድ ተመራቂዎች፤ የትምህርት ዘርፍ ተመራቂ እንደመሆናችሁ መጠን ትምህርት ትውልድን የሚቀርጽና የሚያንጽ መሳሪያ መሆኑን፣ መማር ደግሞ የአስተሳሰብ እና የአሰራር ለውጥ ማምጣት የሚስችል እንዲሁም የትምህርት ባለሞያነት ትውልድን በማነጽ ሃገርን የመገንባት የማይተካ ታላቅ ሃላፊነት ስለሆነ ስራ ላይ ስትሰማሩ ለአፍታም ሳትዘነጉ ለዉጤታማነቱ ልትተጉ ይገባል።



ተመራቂ ተማሪዎቻችን ወጣቶች ናቸሁ፤ መጪው ጊዜ ደግሞ የወጣቶች ነው። ከዛሬው የተሻለ ብሩህ ተስፋ ይጠብቃችኋል። ለሚጠብቃችሁ ብሩህ ዘመን የተማራችሁትን ወደተግባር መለወጥ ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ተማሩ፤ እየተለወጠ ላለዉ ነገ ራሳችሁን ይበልጥ አዘጋጁ።



የስራ ዘመናችሁ ስኬታማ እንዲሆን ከልቤ እመኛለሁ !


በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!


ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦችዋን ይባርክ

ክብርት ከንቲባ Adanech Abiebie- አዳነች አቤቤ
65👏9👍5🥰4😁3🔥1
2025/07/12 05:05:09
Back to Top
HTML Embed Code: