ከ90 ቀናት ስራዎች መካከል አንዱ የሆነው የከተማ ግብርናን ወደተሻለ ደረጃ ማሸጋገር የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሀ ግብር ተካሄደ ::
(ሰኔ 19/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የከተማ ግብርናን ወደተሻለ ደረጃ ለማሸጋገር የተዘጋጀ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በቦሌ ሕብረተሰብ ቅድመ አንደኛ ፣ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አካሂዷል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ ላይ ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት ንቅናቄው ከ90 ቀናት ስራዎች መካከል አንዱ አካል መሆኑን ጠቅሰው ትምህርት ቤቶች ለምግብ ግብዓትና ለውበት የሚሆኑ የከተማ ግብርና ሥራዎች ሲያከናውኑ መቆየታቸውን ጠቁመው በዛሬው በትምህርት ቤቶች የሚከናወኑ የከተማ ግብርና ሥራዎችን ወደላቀ ደረጃ ለማሻገር በምናደርገው ንቅናቄ ትምህርት ቤቶች ፣ ወረዳዎች ፣ ክፍለከተሞች ፣ የትምህርት ማህበረሰብና ባለድርሻ አካላትን ክፍት ቦታዎችን ለምግብ ግብዓትና የትምህርት ቤት ግቢን ሳቢና ማራኪ በሚያደርጉ አትክልቶች እንዲያስውቡ የበለጠ ዕድል ይፈጥራል ብለዋል ::

❤22👍1👏1
ዶክተር ዘላለም አያይዘውም በቦሌ ሕብረተሰብ ትምህርት ቤት በከተማ ግብርና ሥራ ሞዴል ሆኖ እየወጣ መሆኑን ተናግረው የትምህርት ቤቱ ሥራ ለሌሎች ልምድ የሚሆን እና በቀጣይም ስራችንን ወደላቀ ደረጃ በማሻገር ለመማር ማስተማር ሂደቱ ትልቅ አቅም የምንፈጥርበት ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል :: አክለውም ለንቅናቄ ስራው ልዩ ትኩረት በመስጠት በከተማ ግብርና ሥራ ተቀራራቢ አፈፃፀም ማስመዝገብ ከሁሉም የትምህርት ተቋማት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል ::
የቦሌ ክፍለ ከተማ ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ መስፍን ታደሰ በንቅናቄ መድረኩ ተገኝተው እንዳሉት የትምህርት ሴክተሩ የመማር ማስተማር ሥራ ይበልጥ በተግባር የተደገፈ እንዲሆን ለማድረግና የዋጋ ንረትን ለማረጋጋት ሰፊ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመው ስራው ቀጣይነት እንዲኖረው መልዕክት አስተላልፈዋል::
በተያያዘም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ቀደም ሲል የከተማ ግብርና ሥራዎች ላይ ባደረገው ምዘና የከተማ ግብርና ላይ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ 36 ትምህርት ቤቶች በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ግብርና ኮሚሽን የከተማ ግብርናውን የበለጠ ለማሳደግ የሚያስችሉ የዶሮ ኬጅ ድጋፍ እንዳደረገ የሚታወስ ሲሆን የግብርና ኮሚሽን ኮሚሽነር ባዩ ሽጉጤ በንቅናቄ መድረኩ ተገኝተው ለተሸላሚ ትምህርት ቤቶች የዶሮ ኬጅ ርክክብ አድርገዋል ::
በንቅናቄ መርሀ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላት የሁሉም ክፍለከተሞች ትምህርት ፅ/ቤት ኃላፊዎችና የትምህርት ቤት ዳይሬክተሮች እንዲሁም መምህራን ተሳታፊ ሆነዋል ::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

❤26👍3🥰1
ከከተማ አስተዳደሩ የተውጣጣ የሱፐርቪዥን ቡድን ቢሮው በበጀት አመቱ ያከናወናቸውን ተግባራት መሰረት ያደረገ ድጋፍና ክትትል አካሄደ።
(ሰኔ 19/2017 ዓ.ም) ድጋፍና ክትትሉ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ፣ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት እንዲሁም ከፓርቲ ጽህፈት ቤት በተውጣጡ የሱፐርቪዥን ቡድን አባላት የተካሄደ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በ2017 ዓ.ም መሪ እቅድን ጨምሮ በመልካም አስተዳደር፣ በአገልግሎት አሰጣጥና በቅንጅታዊ አሰራር እንዲሁም በፓርቲ ስራዎች የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዷል።
ቢሮው ከተለያዩ ተቋማት ጋር የፈጠረውን ቅንጅታዊ አሰራር አጠናክሮ መቀጠሉ በትምህርት ቤቶች ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስርአት በማስፈን የተማሪዎች ውጤትና ስነምግባር እንዲሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበረከቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀግብሩ በሰጡት ማብራሪያ ጠቁመው በቀጣይ በሱፐርቪዥን ቡድኑ የተሰጡ አስተያየቶችን መሰረት በማድረግ ውጤታማ ስራ የሚሰራ መሆኑን አመላክተዋል።
ከቢሮ ጀምሮ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በተሰሩ ስራዎች ውጤታማ ለመሆን መቻሉን ምክትል ቢሮ ኃላፊ እና የቢሮው የብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ አቶ ሳምሶን መለሰ ተቋሙ በፓርቲ ስራ ያከናወናቸውን ተግባራት ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል።

❤22👎1🥰1
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ ደረጃ የተሻለ ስራ በመስራት ውጤታማ መሆን ከቻሉ ተቋማት መካከል አንዱ እንደሆነ በተደጋጋሚ በሚደርግ ምዘና መረጋገጡን የሱፐር ቪዥን ቡድን አባላቱ ገልጸው በቀጣይ ቀሪ ተግባራትን መሰረት በማድረግ የትምህርት ልማት ስራውን ውጤታማ ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
የሱፐርቪዥን ቡድን አባላቱ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አቅርበው በቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ምላሽ ተሰቷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
የሱፐርቪዥን ቡድን አባላቱ በቀረቡ ሪፖርቶች ላይ የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎችን አቅርበው በቢሮ ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት ምላሽ ተሰቷል።
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
❤30
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የአስፈፃሚ አካላትን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃም ሪፖርት መገምገም ጀምሯል፡፡
(ሰኔ 19/2017 ዓ.ም) በመድረኩ የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን ካስተላለፉ በኋላ ይህ ግምገማ በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ላይ በተፈራረምነው የዋና ዋና ግቦች ዕቅድን መነሻ ያደረገ እንደሆነና ይህንንም መነሻ አድርጎ ቋሚ ኮሚቴው በየሩብ ዓመቱ እየገመገመ መምጣቱንና በዚህም የተሰሩ ስራዎች ምን ውጤት አስገኝተዋል የሚለውን አድምጦ በቀጣይ አጠቃላይ ሪፖርት እንደሚያቀርብ ክብርት አፈ ጉባኤ ገልፀዋል።
በዛሬው መድረክም የትምህርት ቢሮ ሪፓርት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ የቀረበ ሲሆን ማጠቃለያ ሪፖርቱን ምክር ቤቱ በማዳመጥ ገምግማል።

❤55🖕6😁2👍1