Telegram Web Link
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበይነ መረብ (online) የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ተጀመረ ።

(ሰኔ 23/2017 ዓ.ም) ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በ108 የማስፈተኛ ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፈተናው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቀደም ሲል ተማሪዎቹ የልምምድ ፈተና እንዲወስዱ መደረጉን እና በቂ ኦረንቴሽን መሰጠቱ እንዲሁም በየመፈተኛ ጣቢያው መሰረተ ልማቶቹን ዝግጁ የማድረግ ስራን ጨምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱ ይታወቃል።

በዛሬው የመጀመሪያ ዙር ፈተና ከ13ሺ በላይ ተማሪዎች በ108 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን በበይነ መረብ በመውሰድ ላይ የሚገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከኢፌድሪ ትምህርት ሚኒስቴር ዴታ ከወይዘሮ አየለች እሸቴ እና ከምክትል ቢሮ ኃላፊው አቶ ዲናኦል ጫላ ጋር በመሆን ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል አንዱ በሆነው አብረሆት ተገኝተው የፈተናውን አጀማመር በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በበይነ መረብ መሰጠቱ ተማሪዎቹ ፈተናውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲፈተኑ ከማስቻሉ ባሻገር ከኩረጃ ነጻ የሆነ የፈተና ስርአት እንዲሰፍን የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ጠቁመው ቢሮው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመሆን ፈተናው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ በርካታ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ መቆየቱን በመግለጽ ለተፈታኝ ተማሪዎች የመልካም ምኞት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ከ280 አስፈታኝ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ 51,259 የተፈጥሮ እና የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በአራት ዙር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንደሚወስዱ ቀደም ሲል መገለጹ ይታወቃል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
የሰኞ ማለዳ የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

(ሰኔ 23/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎችና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ ላይ አቶ ናትናዬል ገብረዋሃድ የቢሮ የምገባ ቡድን መሪ በስትራቴጂክ ማኔጅመት ላይ መሰረት ያደረገ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ የቀረበው ሰነድ ተጨባጭ እውቅትን የያዘ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበይነ መረብ (online) የሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና በመሰጠት ላይ ይገኛል ።

(ሰኔ 23/2017 ዓ.ም) ፈተናው በከተማ አስተዳደሩ በ108 የማስፈተኛ ጣቢያዎች ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ በመሰጠት ላይ የሚገኝ ሲሆን ፈተናው ስኬታማ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ቀደም ሲል ተማሪዎቹ የልምምድ ፈተና እንዲወስዱ መደረጉን እና በቂ ኦረንቴሽን መሰጠቱ እንዲሁም በየመፈተኛ ጣቢያው መሰረተ ልማቶቹን ዝግጁ የማድረግ ስራን ጨምሮ የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱ ይታወቃል።

በዛሬው የመጀመሪያ ዙር ፈተና ከ13ሺ በላይ ተማሪዎች በ108 የመፈተኛ ጣቢያዎች ፈተናውን በበይነ መረብ በመውሰድ ላይ የሚገኙ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ፣ ከቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ ከአቶ ዲናኦል ጫላና ከአቶ ሳምሶን መለሰ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተ/ፕሬዝዳንት ከሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) እና ከሌሎች አመራሮች ጋር በመሆን ፈተናው ከሚሰጥባቸው ጣቢያዎች መካከል በአድዋ ድል መታሰቢያ እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተገኝተው የፈተናውን አጀማመር በመመልከት ተማሪዎችን አበረታተዋል።


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
2025/07/07 16:39:12
Back to Top
HTML Embed Code: