Telegram Web Link
የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት ከተለያዩ ተቋማት ጋር ትስስር ፈጥሮ በቅንጅት መስራቱ ውጤታማ እንዳደረገው በከንቲባ ጽህፈት ቤት የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ቢሮ ኃላፊው አቶ ሞላ ንጉስ አስታወቁ።

(ሰኔ 28/2017 ዓ.ም) ቢሮው የ2017 ዓ.ም የቅንጅታዊ አሰራር እና የመልካም አስተዳደር እቅድ አፈጻጸም እንዲሁም በ2018 ዓ.ም የዘርፉ እቅድ ዙሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ውይይት አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በከተማ አስተዳደሩ ከሚገኙ ተቋማት መካከል በየአመቱ ውጤታማ በመሆን በተደጋጋሚ ዕውቅና ከሚሰጣቸው ተቋማት መካከል ግንባር ቀደም መሆኑን በከንቲባ ጽህፈት ቤት የተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ክትትልና ድጋፍ ዘርፍ ቢሮ ኃላፊ አቶ ሞላ ንጉስ በመርሀግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ጠቁመው ቢሮው ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር ትስስር ፈጥሮ በቅንጅት መስራቱ ለተገኘው ውጤት ዋነኛ ምክንያት እንደመሆኑ ዘንድሮ የተገኙ ውጤቶችን በማስቀጠል እና ቀሪ ተግባራትን በመገምገም በ2018 ዓ.ም የተሻለ ስራ መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው በ2017 ዓ.ም የበጀት አመት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ከማሻሻል ጀምሮ አጠቃላይ የመማር ማስተማር ስራው ውጤታማ እንዲሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መሰራቱ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸው በቅንጅታዊ አሰራርም ሆነ በመልካም አስተዳደር ዘርፍ የተመዘገቡ ውጤታማ ስራዎችን በማስቀጠል በ2018
በ2018 ዓ.ም የተሻለ ስራ የሚሰራ መሆኑን በመጥቀስ ከቢሮው ጋር በትስስር እየሰሩ የሚገኙ ባለድርሻ አካላትም ለመማር ማ ስተማር ስራው ውጤታማነት የሚያበረክቱትን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አመላክተዋል።

ቢሮው በየወቅቱ በተፈራረመው የትስስር ሰነድ መሰረት ከተለያዩ ተቋማት ጋር በቅንጅት ያከናወናቸውን ተግባራት እየገመገመ የተሻለ ስራ ለሰሩ ተቋማት ዕውቅና በመስጠት ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪ እና የዘርፉ አስተባባሪ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ጠቁመው በ2017 ዓ.ም በተደረገ የቅንጅታዊ አሰራር ፍረጃ መሰረት ከቢሮው ጋር ትስስር ፈጥረው ወደተግባር የገቡ ተቋማት በሙሉ አፈጻጸማቸው በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ መረጋገጡን ገልጸዋል።

በመርሀ ግብሩ ከከንቲባ ጽህፈት ቤት እና ከፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የመጡ የድጋፍና ክትትል ባለሙያዎች ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ፣ የክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች እንዲሁም ከቢሮው ጋር የስምምነት ፊርማ ተፈራርመው በቅንጅት በመስራት ላይ ከሚገኙ ተቋማት የመጡ የስራ ኃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በመድረኩ በቀጣይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ ፊርማ ከመፈረሙ ባሻገር በ2017 ዓ.ም ከቢሮ ጋር በቅንጅት ሰርተው ውጤታማ ለሆኑ ተቋማት ዕውቅና ተሰቷል።

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
የረዳን ፈጣሪ ይመስገን !
እንኳን ደስ አላችሁ!


(ሰኔ 29/2017 ዓ.ም) ዛሬ በመዲናችን 31.5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያላቸዉ 13 የመንገድ ፕሮጀክቶችን እና 8 ድልድዮችን አጠቃላይ 21 ፕሮጄክቶችን መርቀን ለአገልግሎት ክፍት አድርገናል፡፡


ከተማችንን ለማዘመን ከኮሪደር ልማት ስራዎቻችን ባሻገር የመንገድ መሰረተ ልማት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ልዩ ትኩረት ሰጥተን እየሰራ እንገኛለን፡፡


ዛሬ የተመረቁት እነዚህ የመንገድ መሰረተ ልማቶች ፦

ከአጉስታ- ወይራ መጋጠሚያ፣ቱሉዲምቱ ኮንዶሚኒያም መቃረቢያ፣ ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ ዐደባባይ - በአቃቂ ድልድይ-ቱሉ ዲምቱ ዐደባባይ፣ ከቃሊቲ ቀለበት መንገድ አደባባይ ቡልቡላ-ቂሊንጦ 2ኛ ቀለበት መንገድ አደባባይ፣
የለቡ አደባባይ ማሻሻያ ፕሮጀክት፣ ከአፍሪካ ህንፃ- ጀሞ መስታዎት ፋብሪካ፣ ከቂርቆስ ማርገጃ - ቡልጋሪያ፣ ከቤላ -ፈረንሣይ ፓርክ - ፈረንሣይ አቦ ቤተክርስቲያን፣ ከናሰዉ ሪል ስቴት አርሴማ ቀለበት መንገድ እና ዮናስ ሆቴል ኬብሮን ፋርማሲ አስፋልት መንገዶች ናቸው፡፡


ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቧቿን ይባርክ
ከንቲባ አዳነች አቤቤ


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
2025/07/07 13:49:49
Back to Top
HTML Embed Code: