Telegram Web Link
በበጀት ዓመቱ የተጠናቀቁ የፕሮጀክቶችን አስመልክቶ ፡-

(ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም)
የሕዝባችንን የማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን ከመመለስ አንጻር በመንግስትና በህብረተሰብ ተሣትፎ 15‚69ዐ ግንባታዎችን ማጠናቀቅ የተቻለ ሲሆን፤ ካቀድነው በላይ ማከናወን ተችሏል፡፡

205 በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰሩ የተለያዩ ኘሮጀክቶች

8,786 በበጎ ፈቃደኞችን በማስተባበር ለአቅመ ደካሞች የተገነቡ ቤቶች

5,176 በከተማ አስተዳደር የተገነቡ ቤቶች

1064 የመስሪያ ሼዶች

5,563 ሱቆች / ካዛንቺስ፣ ቦሌ፣ ላፍቶ፣ ልደታ፣ አራዳ እና አራት ኪሎ ሽሮሜዳ/ የተገነቡ

1,155 የህፃናት መጫወቻ ቦታዎች

122 የእስፖርት ማዘወተሪያ ሜዳዎች

245 የአረንጓዴ ልማት ስራ

153 የመኪና ፓርኪንጎችና ተርሚናሎች

ከዚህ ውስጥ 16 ቱ ሜጋ ኘሮጀክቶች ሲሆኑ ወደ 9ሺ ኘሮጀክቶች በህብረተሰብ ተሳትፎና በበጎ ፈቃድ አገልግሎት የተሰሩ ናቸው፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
13👎5
በበጀት ዓመቱ የኑሮ ውድነት ቅነሳን በተመለከተ፡-

(ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም)
በከተማዋ አምራቾች ምርታቸውን በቀጥታ በገበያ በማዕከላት እንዲያቀርቡ በተፈጠረው እደል 3.5 ሚሊዮን ኩንታል ምርት እንዲቀርብ ተደርጓል።

የቅዳሜና እሁድ የገበያ ቦታዎችን በማስፋት ከ193 ወደ 219 በማሳደግ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ እየቀረበ ይገኛል፡፡

በድጎማ ከሚቀርቡ ምርቶች የስኳር ምርት 305,295 ኩንታል፤ የምግብ ዘይት 4,382,179 ሊትር በትስስር ማሰራጨት ተችሏል።

በትራንስፖርት፣በጤና መድን፣ በዳቦ አቅርቦት፣ በምገባና በምርት አቅርቦት ከ14 ቢሊዬን ብር በላይ በመደጐም የነዋሪዎቻችን የኑሮ ጫናን የማቅለል ስራ ተሰርቷል፡፡

የዳቦ አቅርቦትን ለመጨመር በመንግስትና በግል ባለሀብቶች የጋራ ጥምረት በተሰራው ሥራ የሸገር ዳቦና ብረሃን ዳቦ ፋብሪካ ውደ ስራ በማስገባት፤በአጠቃላይ በ26 ዳቦ ፋብሪካዎች በሚሊዮኖች ዳቦ በማምረት የነዋሪውን ኑሮ ለመደገፍ ጥረት ተደርጓል።

በ26 የምገባ ማእከልላት በቀን አንድ ጊዜ ምግብ ማግኘት ችግር ላለባቸው 36ሺ ሰዎችን በምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
11👎5
በበጀት ዓመቱ አምራች ኢንዱስትሪውን በተመለከተ፡-

(ሀምሌ 4/2017 ዓ.ም)

የምርት ጥራት፣ ምርትና ምርታማነታቸውን ከማሳደግ አንፃር ለ566 አምራች ኢንዱስትሪዎች 4,235 ማሽነሪ መሳሪያ እና በብር ደግሞ 1,860,822,877 በማቅረብ ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡


መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
10👏6
2025/07/14 04:44:24
Back to Top
HTML Embed Code: