Telegram Web Link
"...እግዚአብሔር እኮ ታላቅ ነው.." |ያሬድ ነጉ|

አዲስ አበባ መቻሬ ሜዳ ላይ March 6 /የካቲት 27/2013 ዓ.ም/ ትልቅ ኮንሰርት ተዘጋጆቶ አንድ ድምጻዊ ከጎረቤት አገር ይጠራል። ድምጻዊው በመድረክ ስሙ ዳይመንድ ፕላትኒየም ይባላል። ወጣት ዘፋኝ ሲሆን ከአፍሪካ ወጣት አርቲስቶች መካከል ተጠቃሽ ነው። ወደ ኢትዮጵያ በውድ ክፍያ ሲመጣ ኢትዮጵያ ከደረሰ እና ካረፈ በኋላ ያሬድ ነጉ ስለ ተባለው ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ማጣራት ነበር የቀድሞ ስራው ያደረገው።

በቅርቡ ያሉት ኢትዮጵያውያንም ያሬድ ነጉ ብዙ ተከታይ ካላቸው ወጣት ድምጻውያን መካከል አንዱ ሲሆን በመድረክ አያያዙም የተዋጣለት ጎበዝ ስለመሆኑ በመጠኑ ነገሩት። ዳይመንድ በውስጡ ፍርኃት አድሯል። በሄደባቸው አገሮች ሁሉ የመድረኩ የበላይ እሱ ነበር። እዚህ ግን ፈራ! ቢሆንም የቅርቡ ሰዎች አበረታቱት። ከመቻሬ ኮንሰርት ቀድሞ በአንድ ክለብ ላይ ለሰዓት ያህል እንዲዘፍን ተስማምቶ ስለነበር March 5 /የካቲት26/ ወደዛ ክለብ ሄዶ ከመቶ የማይበልጡ ሰዎች ባሳዩት ፍቅር በራስ መተማመኑን አሳድጎ በቀጣይ ቀን በጥሩ ዝግጅት ወደ መቻሬ ሜዳ መጣ! ዳይመንድ በውድ መኪናዎች እና በጋርድ ታጅቦ ወደ ስፍራ እንደሚመጣ የታወቀ ነው። አሁን በኢትዮጵያ ያሉ ዘፋኞች በዛ ልክ ክብር "ተሰጥቷቸው ይመጡ ይሆን..?" የሚለው ስጋት በውስጡ ያላደረ አልነበረም። ቢሆንም ግን ያሬድ ነጉ በዕለቱ አስደናቂ በሆነ አለባበስ እና ልዩ በሆነ ዝግጅት መድረኩን ተቆጣጠረው። ወደ ስፍራውም ሲመጣ ከዳይመንድ ፕላቲኒየም በሚስተካከል እጀባ እና ጥንቃቄ በተሞላበት መልኩ ነበር። ይኽ ደግሞ በእንግዶቹ ላይ የሚፈጥረው አዎንታዊ ተፅዕኖ አለው።

በአርቲስቶቻችን የኑሮ ደረጃ ለሚንቁን የጎረቤት አገር ዘፋኞች ያሬድ ነጉ በቂ ምላሽ ሰጥቶ ከስፍራው በጋርዶች ታጅቦ ተሰወረ። በዕለቱ በነበረው ትዕይንት በስፍራው የታደሙ አርቲስቶች እና የቅርብ ጓደኞች እንዲሁም የሙያ አጋሮቹ ሲያወሩ በያሬድ ነጉ የተሰማቸው ደስታ ልዩ እንደሆነ ነው ያስተዋልኩት። እኔም ነገርየው ስላስደሰተኝ ለያሬድ ስልክ ደውዬ ከወዳጅነት ሰላምታ በኋላ "ስለ ኮንሰርታችሁ እየተወራ ያለው ነገር በጣም ደስ የሚል ነው። በተለይ በአንተ ሁሉም ሰው በዕለቱ በነበረክ የመድረክ አያያዝ እና ወደ ዝግጅቱ ስፍራ ስለተጓዝክበት ፕሮቶኮል እያደነቀ በመደሰት ስላንተ እያወራ ነው እንኳን ደስ አለህ ወንድሜ አልኩት። ያሬድም "...ወንድሜ እግዚአብሔር እኮ ታላቅ ነው አለኝ!" ደስ የሚል ቃል! አዎ እግዚአብሔር ታላቅ ነው! ምክኒያቱም እግዚአብሔር ሲባርክ እና ሲፈቅድ ነው ሁሉም ነገር የሚሳካው። ይኽ ቃሉ ነው ብዕር አንስቼ ይኼን ጦማር እንድጦምር ያደረገኝ።

እንደምትመለከቱት ያሬድ ነጉ በቀድሞ የባህር ኃይላችን ልብስ ዘንጦ ወደ መድረክ ወቷል። በልብሱ የደረት ኪስ እና ኮፍያው ላይ የይሁድ አንበሳ አርማ፣ የጎን ኪሶች ላይ በአገር ቀለማችን የፍሪካን ካርታ በመኃሉ ደግሞ የአንበሳ ምስል አኑሮበት ነበር ለብሶ የወጣው። በተጨማሪም በዚህ የተከበረ አለባበሱ ላይ የተወደደች ባንዲራችንን ከፍፍፍ አድርጎ አውለብልቧል። ወጣት አርቲስቶች በዚህ ልክ ሲረቁ ማየት ኩራት ነው!

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
Channel photo updated
#አፋር💚💛
#ሲመሽ የተሰኘው የሶል አባ እና የጊል ሙዚቃ Sample ላይ እንዳለ ተሰርቆ ተለቆ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ሙሉ ሙዚቃውን አጠናቆ ወደናንተ ለማድረስ በቅቷል። ገብታችሁ እንድታዩለት እጋብዛለሁ!

https://youtu.be/nWSZyCpJu9w
እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓለ ትንሣዔ ወዕርገት በሰላም አደረሰን!!
መልካም በአል
የዓመት ሰዎች ይበለን፡፡ አሜን!
http://www.instagram.com/yarednegu
ውድ ኢትዮጵያውያን እና ኤርትራውያን ወዳጆቼ ሰሞኑን በድምጻዊት ሚለን ሀይሉ ዙሪያ ያጋራሁት መልዕክት በብዙዎች ዘንድ ግርታን ፈጥሯል::

እኔ እንደማንኛው ሰው የማከብራቸውን፣ ትልቅ ቦታ የምሰጣቸውን ሰዎች የምገልፅበት እና የማደንቅበት መንገድ አለኝ::

ለምን በዚህ መጠን አነጋጋሪ ሊሆን እንደቻለ አላውቅም ለማንኛውም ከዚህ ጋር በተያያዘ በወዝወዝ አዲስ ከኪንጎ ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል:: አመሰግናለሁ!

ያሬድ ነጉ
https://youtu.be/VgJf0QKNEeI
ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ...💚💛

የአፍሪካ ሙዚቃ በተለይም የምስራቅ አፍሪካ በይበልጥም የአገሬ ኢትዮጵያ ሙዚቃ 'ባህል ዘመናዊ' የሚል ምት ከተጀመረበት ወቅት አንስቶ ቁልቁል በአናቱ የተተከለ እስኪመስለኝ ድረስ በጣም ዘቅጦብኝ ነበር። እንዲሁም ወጣት ድምጻውያን ከምስራቅ አፍሪካ ሙዚቀኞች በጣም አንሰው በመታየታቸው ይቆጨኝም ነበር። ሁሌ ፉክክሩ ከኢትዮጵያ የሚሻገረው መቼ ነው እል ነበር። /ይኼ ወጣቶቹን ብቻ ይወክላል/

ያሬድ ነጉ ከትውልደ ታንዛኒያዊ አርቲስት ሐርመናይዝድ ጋ ሊሰራ መሆኑን ከሰማውበተ ዕለት ጀምሮ እውን የሚሆንበትን ቀን በጉጉት ስጠብቅ ነበር። ምክኒያቱም የምስራቅ አፍሪካ ሙዚቃ መርቀቅ የሚችለው በዚህ አይነት ጥምረት እንደሆነ ስለማምን ነው። ዛሬ ይኼንን በማየቴ እጅግ ደስተኛ ነኝ። አሁን ለወጣት ድምጻውያንም ሆነ ለኢትዮጵያ ሙዚቃ የተደማጭነት መጠን መስፋት የያሬድ ነጉ እና የሙያ አጋሮቹ ጥረት እንደ ትልቅ ስኬት የሚቆጠር ነው።

አገራችንን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ኮከብ አርቲስት የሆነው ይኽ ታንዛኒያዊ ወጣት አርቲስት በኢትዮጵያ የተመረተ የሙዚቃ ምት ስቦት ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ መስራት መቻሉ ለአገሬ የሙዚቃ ዘርፍ እድገትና ተደማጭነት ትልቅ የሚባል እድል የሚፈጥር አጋጣሚ ነው። ይኼንንም ማበረታታት እና ማድነቅ ከጥበብ አፍቃሪያን የሚጠበቅ ተግባር ነው።

Yared Negu & Harmonize

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
የእግር እሳት የተሰኘው የአርቲስት ያሬድ ነጉ አገራዊ የሙዚቃ ቪዲዮ ነገ ማታ ይለቀቃል
"ጊዜ እያስቆጠረ ታሪክ ሳይወሳ
ጀግና አይወለድም ጀግና እየተረሳ
የቆምንበት አፈር የያዝነው ባንዲራ
አለመደበትም ድል እንጂ መከራ
ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲሉ ሲሉ
ሞገስ ክብር አለው ቃሉ
አንድነቱ ነው ስንቄ ስንቄ
ነገን ለመሄድ 'ርቄ

https://youtu.be/VxtAy6-hSIc
"ጊዜ እያስቆጠረ ታሪክ ሳይወሳ
ጀግና አይወለድም ጀግና እየተረሳ
የቆምንበት አፈር የያዝነው ባንዲራ
አለመደበትም ድል እንጂ መከራ
ኢትዮጵያዊ ነኝ ሲሉ ሲሉ
ሞገስ ክብር አለው ቃሉ
አንድነቱ ነው ስንቄ ስንቄ
ነገን ለመሄድ 'ርቄ..."

እናመሰግናለን 300 ሺህ እይታዎች በአንድ ቀን ውስጥ!

https://youtu.be/VxtAy6-hSIc
2025/10/16 22:56:10
Back to Top
HTML Embed Code: