♻"ማነው ያለው?! "♻
🔊ባልና ሚስት በተለያዩ ምክኒያቶች ለተወሰነም ይሁን ላልተወሰነ ጊዜ ተራርቀው ቢኖሩ በዚህ ብቻ ጋብቻቸው አይፈርስም (ኒካሑ አይወርድም)✔✔
✍ሐቁ ይህ ሆኖ ሳለ ግን ብዙ ሰዎች፦"ባልና ሚስት ከ6 ወይም ከ 4 ወር በላይ ተለያይተው ከቆዩ ኒካሑ ይወርዳል" ሲሉ ይሰማል
👉 ይህ አባባል ከቁርኣንም ይሁን ከሐዲሥ እንዲሁም ከዑለማዎች ንግግር -👌ምንም ዓይነት መሰረትና ማስረጃ የሌለው
ተራ ወሬ ነው❗
📌ባል በአንደበቱ ወይም 📝በፊርማው በተደገፈ ፅሁፉ ኒካሕ አውርጃለሁ እስካላለ ድረስ ወይም ሚስት ባሌ ለረጅም ጊዜ ከኔ በመራቁ ምክኒያት ሐቄን አልጠበቀም :- በማለት ሸሪዓ ፍርድ ቤት ቃዲ ጋር ሔዳ አመልክታ ሁኔታውን አጣርቶ ኒካሑን ቃዲ እስካላወረደው ድረስ ለ60 እና ለ70 ዓመታትም ኧረ እስከ ህይዎታቸው ፍፃሜም ድረስ ተራርቀው ቢኖሩ በመራራቃቸው ብቻ
ኒካሑ አይወርድም❗
✍ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ ባል ሚስቱን ቢበዛ ከ6 ወራት በላይ ያለ ፈቃዷ ተለይቷት
ርቋት ሊኖር አይገባም📍
ይህንንም ማድረጉ ከሚስት ሐቆች መሐል አንዱ ሊባል የሚችልን ነገር ትቷል ቢባል እንጂ በዚህ ብቻ ኒካሑ አይወርድም❗
✆✈ ችግርና የተለያዩ ምክኒያቶች ያለያያቸው ባልና ሚስቶችን አላህ በሰላምና በፍቅር ያገናኛቸው🍃
🚫ያለ እውቀት ለሚናገሩም አደብ ይስጣቸው✂
✉አሕመድ ኣደም አሽሸራሪይ✉
@yasin_nuru @yasin_nuru

አንዲት ሴት አስገራሚ ገጠመኟን እንዲህ በማለት ታወጋናለች፡-
"ከጓደኛዬ ጋር ተቀምጠን እያወራን ሳለ ሶስት ዓመት በቅጡ ያልሞላት ልጇ መጥታ ከእናቷ ኋላ ቆመች ቀሚሷን እየጎተተች በተብታባ አንደበቷ "እናቴ ሆይ ዛሬኮ የጀነት ህንፃችንን አልገነባንም" አለቻት። በስህተት የሰማሁት ቃል መሰለኝ። ግና ወንድሞቿም ተሰብስበው ታናሽ እህታቸው የተናገረችውን ቃል ተጠቅመው እናታቸውን ጠየቁ። "ማማ ዛሬኮ የጀነት ህንፃችንን አልገነባንም"
ጌታዬ ሆይ!
ብዕሬን እንደ ኻሊድ ኢብኑልወሊድ ሠይፍ የሰላ አድርግልኝ
Mahi Mahisho
እናት ግራ የመጋባት ስሜቴን በአይኖቼ ውስጥ አንብባ ፈገግ አለችና "እኔና ልጆቼ በጀነት ውስጥ ቤተ መንግስት እንዴት እንደምንገነባ ማየት ትፈልጊያለሽን?!" አለችኝና ተከታትለን ወደ ክፍላቸው ገባን።
ምን እንደሚያደርጉ ለማየት ጥጌን ያዝኩ። ልጆቹ በእናታቸው ዙሪያ ክብ ሰርተው ተቀመጡ። ዕድሜያቸው ከሶስት እስከ አስር ይደርሳል። ከሁሉም ፊት ላይ የደስታ ስሜት ይነበባል።
ሱረቱል-ኢኽላስን ከእናታቸው ጋር አብረዋት ማንበብ ጀመሩ
قل هو الله أحد ….
"በላቸው፡- እርሱ አላህ አንድ ነው ...."
አሥር ጊዜ ደጋግመው ቀሩ። ሲጨርሱ ደስ በሚል የተዘበራረቀ ቃል "ለጌታችን አላህ ምስጋና ይድረሰው በጀነት ውስጥ ቤት ገነባን" አሉ።
እናት "በጀነቱ ቤታችሁ ዙሪያ ስንት የዘንባባ ዛፍ መትከል ትፈልጋላችሁ?" ዓይን ዓይናቸውን እያየች። አላህን ማመስገን ጀመሩ። አልሐምዱሊላህ እያሉ ደጋገሙ።
"የአትክልት ሥፍራው ይበልጥ ቆንጆ እንዲሆን ምን ያህል ተክሎችን መትከል ትፈልጋላችሁ?" አለቻቸው ሱብሐነላህ፣ አልሐምዱሊላህ፣ አላሁ አክበር እያሉ ዚክር ላይ ተጠመዱ።
እንደጨረሱ "በጀነቱ ቤታችን ውስጥ ምን ማስቀመጥ ትፈልጋላችሁ?" አለቻቸው።
ልጆቹም "ጌጣጌጥና ውድ ሐብትን መሰብሰብ እንፈልጋለን" አሉና ላሐውለ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላህ ... የሚለውን ቃል መደጋገም ጀመሩ። እርሷ በረሱል አንደበት የጀነት ከንዝ ናት የተባለላት ዚክር አይደለችምን?!
መልሳ ጠየቃቸው፡-
"ከእናንተ ውስጥ የአላህ መልዕክተኛ ሰላምታውን እንዲመልሱለትና ከሐውዳቸው እንዲያጠጡት የሚፈልግ ማነው?" አለቻቸው
ሰለዋት ማድረግ ጀመሩ "አላሁመሰሊ አላ ሰዪዲና ሙሐመድ ወአላ አሊ ሰዪዲና ሙሐመድ...." ሰለዋታቸውን እንደጨረሱ ሁሉም ወደየስራቸው አቀኑ። አንዳንዶቹ ትምህርታቸውን ማጥናት ጀመሩ.. ሌሎቹ ደግሞ ያቋረጡትን ጨዋታ ቀጠሉ።
ሁኔታውን በተመስጦ ተውጬ ስከታተል የነበርኩት እኔ ይሄን ማድረግ እንዴት ቻልሽ? በማለት ጠየቅኳት ተገርሜ።
እሷም "ሰብስቤያቸው በመካከላቸው ስቀመጥ ደስ ስለሚላቸው አጋጣሚውን ተጠቅሜ እነሱን በማስተማር ላይ ራሴን እጠመዳለሁ። አላህን ማውሳት ማለማመድ እጀምራለሁ። ካርቶን ፊልሞች ላይ ቤት መገንባትና በጀግና አክተሮች ሲማረኩ አያለሁና የረሱልን ሐዲሶች ላስተገብራቸው እነሱን በሚስብ መልኩ ትንሽዬው አእምሯቸው በሚረዳው መንገድ ማስተማርን ወደድኩ" አለችኝ።
የሙስሊሙን ከፍታ ከፈለጋችሁ ዱንያዊም ሆነ አኺራዊ ደስታን ከከጀላችሁ ይህን መሰል ነገር በየምሽቱ እንዲተገብሩ አድርጋችሁ በተርቢያ ልጆቻችሁን አሳድጉ
✨SHARE ✨ SHARE✨
╔════════════╗
🌟JOIN: @yasin_nuru🌟
🌟JOIN: @yasin_nuru🌟 ☪ ╚════════════╝

#ባለ_ትዳሮች ማድረግ የሌለባቸው ነገሮች፦
1ኛ.ዉጪ ማምሸት በተለይ(ወንድ) በጊዜ ወደ ሚስቱ መሄድ አለበት። ሚስት ብቸኝነት ላፍታም ሊሰማት አይገባም!
2ኛ.በጊዜ ገብተዉ ቲቪ፣ስልክ ማብዛት አያስፈልግም! ወንዱ ለሴቷ ፤ ሴቷ ለወንዱ ጊዜ ሊሰጣጡ ያስፈልጋል!
3ኛ.የቢሮ ስራን ከተቻለ ቢሮ ጨርሶ መምጣት!
4ኛ.ሴቶች ቂቤ ተቀብታችሁ በፍጹም ባሎችን አትቀበሉ በጊዜ ታጥባችሁ ፏ ብላችሁ ተቀበሏቸዉ!
5ኛ.ሚስቶች ቤት ስትሆኑ የምትለብሱት ለባላችሁ ብቻ የተገባ ልብስ ይኑራችሁ! የሚደብር አለባበስ ቤት ዉስጥ አትጠቀሙ።
6ኛ.እልህን አትለማመዱት!
7ኛ.ቤተሰብን በትዳር ዉስጥ አለማስገባት!
8ኛ.ገንዘብ በአግባቡ መጠቀም አለማባከን!
#copied
#ቂቤው_ላይ_ይሰመርበታ_ወንዶች?😂

ኢንና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን!
ወጣቱ ሙነሽድ ሙሐመድ ሰዒድ በገጠመው ድንገተኛ ህመም ወደ አሄራ መሻገሩ ተሰማ!
በበርካታ የኅብረትና የግል ነሺዳዎቹ የሚታወቀው ወጣቱ ሙንሺድ ሙሐመድ ሰዒድ በገጠመው ድንገተኛ ህመም በህክምና ሲረዳ ቆይቶ ዛሬ አመሻሹን ወደ አኼራ መሻገሩ ተሰምቷል።
በደቡ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ተወልዶ ያደገው ሙሐመድ ሰዒድ በገጠመው ድንገተኛ ህመም ማለፉ ነው የተነገረው።
አላህ ለሙንሺድ ሙሐመድ ሰዒድ ማረፊያውን ጀነት ያድርግለት

⚠️🚫ለዘፈን_አፍቃሪያን_መገሠጫ_ትሆን_ዘንዳ_ይህችን_ታሪክ_አንብቧት 👇👇👇
*ልጁ በጣም ሙዚቃ ማዳመጥ ይወዳል። ጠዋት፣ ማታ፣ቀን፣ለሊት፣ሁልም ጆሮው ላይ ኤርፎን ሰክቶ፣ አላህ ለቁርአን፣እንዲሁም ለተግሰጽ የለገሰውን ጆሮ ለሃራም እናለማይወደው ድርጊት ይጠቀማል።
ታድያ ከዕለታት አንድ ቀን ት/ቱን ጨርሶ፣ ቤት ይገባል። ልቡ የሚገኘው ዛሬ ምን አይነት ዘፈን አውርጄ ላዳምጥ ነው ። ከዚያም ፍራሹ ላይ ጋደም ብሎ፣ ሞባይሉን ከፍቶ፣በማዳመጥ ላይ ሳለ የክፍሉ መብራት ድንገት በኃይል ድርግም ብሎ ይጠፋል ።
ደንግጦ የሞባይሉን ፍላሽ በማብራት፣ ኤርፎኑን ለመንቀል ቢሞክር እንቢ ይለዋል። ከጆሮው ውስጥ የተጣበቀው ኤርፎን፣አልነቀልም ብሎ ብዙ አታገለው። በመጨረሻም ስላልቻለ ለቤተሰቡ ተናገረ።
ቤተሰቡ ሙዚቃ በማዳመጡ ቢናደዱም፣አሁን ለችግሩ መፍትሔ እንፈልግ በማለት በፍጥነት ወደ አቅራቢያው ከአንገት በላይ እስፔሽላይስት ህክምና ወሰዱት።
ዶክቶሮች በድንጋጤ እንዲሁም በመገረም እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሟቸው እንደማያውቁና ከአቅም በላይ ስለሆነባቸው ወደ ሌላ የሕክምና ማዕከል ሪፈር ይጽፋለታል። ቤተሰብ በጣም ተጨንቋል።
ልጁ ምንም አያወራም፣ ዝምታን ተከናንቦ አይኑን ያቁለጨልጫል።በአብዋራ የተሞላ ፀጉሩን እያከከ በዙሪያው ያሉ ሰዎች የሚያወሩትን ለማዳመጥ ይሞክራል።
ነገር ግን ምንም ነገር አይሰማውም። ጆሮው ደን ቁሯል። አላህ የሰጠውን ጆሮ ቁርአንን ለማዳመጥ ሳይጠቀም ሙዚቃ አዳምጦበታል። በዚህም የፀፀተው ይመስላል።
ወደ ሌላ ሕክምና ማዕከል ተጉዘው ከከባድ የ 2፡00ሠዓት ቀዶ ጥገና ሕክምና በኃላ ኤርፎኑ ለብቻው መወገድ ስላልቻለ ሁለቱ ጆሮዎች፣ከቦታቸው ተነቅለው የማዳመጥ ፀጋን አሳጥቶት ከሕክምና ማዕከሉ ወደ ቤት ተመለሰ። ከዚያ በኃላም ጤና እያለው ያልቀራውን ቁርአን ለማንበብ ይታገላል። ሕይወቱንም በፀፀት እና በማልቀስ ለመግፋት ተገዷል።
ኢኽዋኒ ወ አኽዋቲ አላህ የሰጠንን ፀጋ እሱን ለማመስገን እንጂ፣እሱን ለማስቆጣት አንጠቀመው። ሙዚቃን ከመስማት ርቀው፣ ቁርአንን በማዳመጥ ከሚረኩት ያድርገን!!!
አላሁመ አሚን!
በተቻለን አቅም ለሌሎች በማድረስ ከሀራም ነገራቶች እንዲርቁ ሰበብ እንሁናቸው ።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ዓረባዊያን ቢክዱም🥺🥺
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ከጽዮናውያን እና ከአሜሪካዊያን ጋር ቢተባበሩም🤷♂🤷♂
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
አብሽሪ ከአላህ ሰራዊት ጋር💪💪
ሆነን እንመጣልሻለን🔥🔥
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ከአይሁድም ነፃ ትወጪያለሽ🥺🥰
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
መስዋእት እንሆንልሻለን💪💪
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ድንበሩም ይፈርሳል🦁🦁
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
የዓለም ሙስሊሞችም አንድ ይሆናሉ 🤝🤝
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
@yasin_nuru @yasin_nuru
ዓረባዊያን ቢክዱም🥺🥺
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ከጽዮናውያን እና ከአሜሪካዊያን ጋር ቢተባበሩም🤷♂🤷♂
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
አብሽሪ ከአላህ ሰራዊት ጋር💪💪
ሆነን እንመጣልሻለን🔥🔥
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ከአይሁድም ነፃ ትወጪያለሽ🥺🥰
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
መስዋእት እንሆንልሻለን💪💪
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ድንበሩም ይፈርሳል🦁🦁
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
የዓለም ሙስሊሞችም አንድ ይሆናሉ 🤝🤝
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
@yasin_nuru @yasin_nuru
📌 የዱዓችን ተቀባይነት ማጣት ምክንያቱ ምን ይሆን?
ﻣﺮ ﺇﺑﺮﺍﻫﻴﻢ ﺑﻦ ﺃﺩﻫﻢ ﺭﺣﻤﻪ ﺍللّٰه تعالى ﺑﺴﻮﻕ ﺍﻟﺒﺼﺮﺓ ؛ ﻓﺎﺟﺘﻤﻊ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺇﻟﻴﻪ، ﻭﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻳﺎ ﺃﺑﺎ ﺇﺳﺤﺎﻕ: ﻣﺎ ﻟﻨﺎ ﻧﺪﻋﻮﺍ ﻓﻼ ﻳُﺴﺘﺠﺎﺏ ﻟﻨﺎ؟
ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም (رحمه الله) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦ ያ አባ ኢስሃቅ ዱዓእ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ?
ﻗﺎﻝ: لإﻥ ﻗﻠﻮﺑﻜﻢ ﻣﺎﺗﺖ ﺑﻌﺸﺮﺓ ﺃﺷﻴﺎﺀ!.
እሳቸውም፦ ቀልባችሁ (ልባችሁ) በአስር ነገሮች ሞታለች አሏቸው።
ﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻭﻣﺎ ﻫﻲ؟ ﻗﺎﻝ:
እነሱም፦ ምን ምንድ ናቸው? ብለው ጠየቋቸው።
እሳቸውም፦
✅ﺃﻧﻜﻢ ﻋﺮﻓﺘﻢ ﺍللّٰه؛ ﻓﻠﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺣﻘّﻪ.
አንደኛ፡ አላህን አውቃቹት።ሐቁን አልተወጣችሁም።
✅ﺯﻋﻤﺘﻢ ﺃﻧﻜﻢ ﺗﺤﺒّﻮﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠّٰﻪ (ﷺ) ﺛﻢ ﺗﺮﻛﺘﻢ ﺳﻨّﺘﻪ.
ሁለተኛ፡ ነቢዩን (ﷺ) እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ፤ ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።
✅ﻗﺮﺃﺗﻢ ﺍﻟﻘﺮﺁﻥ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﺑﻪ.
ሶስተኛ፡ ቁርኣንን አነበባችሁት አልሰራችበትም።
✅ﺃﻛﻠﺘﻢ ﻧﻌﻤﺔ الله، ﻭﻟﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺷﻜﺮﻫﺎ.
አራተኛ፡ የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።
✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥّ ﺍﻟﺸﻴﻄﺎﻥ ﻋﺪﻭّﻛﻢ، ﻭﻭﺍﻓﻘﺘﻤﻮﻩ.
አምስተኛ፡ ሸይጣን ጠላታችነው ብላችሁ ከሱ ጋር ገጠማቹ።
✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﺠﻨّﺔ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﻟﻬﺎ.
ስድስተኛ፡ ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ የሚሆን ስራ አልሰራችሁም።
✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻨّﺎﺭ ﺣﻖ، ﻭﻟﻢ ﺗﻬﺮﺑﻮﺍ ﻣﻨﻬﺎ.
ሰባተኛ፡ የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።
✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻤﻮﺕ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﺴﺘﻌﺪّﻭﺍ ﻟﻪ.
ስምንተኛ፡ ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።
✅ﺍﻧﺘﺒﻬﺘﻢ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﻮﻡ، ﻭﺍﺷﺘﻐﻠﺘﻢ ﺑﻌﻴﻮﺏ ﺍﻟﻨﺎﺱ، ﻭﺗﺮﻛﺘﻢ ﻋﻴﻮﺑﻜﻢ.
ዘጠነኛ፡ ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፤ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።
✅ﺩﻓﻨﺘﻢ ﻣﻮﺗﺎﻛﻢ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﺘﺒﺮﻭﺍ ﺑﻬﻢ
አስር፡ ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።
📙 ጃሚዑል በያን ዓልዒልም ወፈድሊህ፡ 2/12

አንድ ሰው ሸይኽ ዑሰይሚንን {ረሂመሁላህ} እንዲህ ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው።
➻ሁለተኛ የምጨምራት ሴት ሀራም ላይ እንዳትወድቅ ስለፈራሁላት ላገባ ነው ምን ይመክሩኛል?
➻እሳቸውም ፦" ለሁለተኛዋ ለማግባት የመደብከውን ገንዘብ ትዳር ለሌለው ወንድምህ ስጠውና እሱ ያግባት:: የሁሉቱንም አጅር ታገኛለህ::" በማለት መለሱለት።
አልፈታዋ 6/241
👍ለሌሎች ሼር ማድረጎን አይዘንጉ

🚗መኪናና ሞባይል📲
💨ድሮ ሾፌሮች ሞባይሎቻቸውን በተደጋጋሚ መኪና ውስጥ እየረሱ ይወረዱ ነበር፣ አንዳንዴም አናግረውበት ታፋቸው ላይ ጣል እንዳደረጉት መጨረሻ ላይ መኪና አቁመው ሲወርዱ ታፋቸው ላይ የተረሳው ስልካቸው ቀድሟቸው መሬት በመድረስ ይሰባበር ወይም ይወላልቅ ነበር፣
👌ዛሬ ግን ከመሪው ይልቅ በእጃቸው ሞባይሎቻቸውን በመያዝ ለአደጋ ሰበብ የሚሆኑ በዝተዋል በሞባይላቸው በመጠመድ ሞተር ሳያጠፉ ረስተው የሚወርዱም አይጠፉም
🔑ወንድሜ ሆይ ስማ፦ በዘመኑ ዓለም ላይ እየበዛ ከመጣው የትራፊክ አደጋ ዋና ዋና ምክንያቶች መሀል አንዱ ሞባይል ነው❗
አንድን ነፍስ የራሱንም ቢሆን- ያለ አግባብ ያጠፋ ሰው ምድር ላይ ያሉ ሰዎችን በሙሉ ህይወት እንዳጠፋ ይቆጠራል አላህ ዘንድም ይጠየቃል❗
ህይወቶች እንዲጠፉ ሰበብ የሆነም ሰው ወንጀሉ ተመሳሳይ ነው::

ትዳር ትልቅ ሀላፊነት መወጣትን ጥንቃቄን ብርታትን ብልሃተኝነትን የሚጠይቅ ትልቅ ተቋም ነው።
ለትዳር ለባል ዝቅ ማለት ውርደት አይደለም
ባለው የገቢ ምንጭ የሚያስፈልገውን
በመመዝገብ የሚቀድሙትንና ሊዘገዩ የሚችሉትን ለይቶ በማውጣት በሰላም መኖር ይቻላል።
ሚስት ሆይ ጓደኞችሽ የሚኖሩትን ኑሮ ሳይሆን
ቤትሽን ተመልከች ምን አልባት ጓደኞችሽ ብዙ
የሚያማምሩ ልብስና ጫማ ይኖራቸው ይሆናል።
ደስ ይላል ነገር ግን አንች እና ባለቤትሽ እጅ ኑሯችሁን የምትኖሩት ጓደኞችሽ አይደሉም ስለዚህ ባለሽ በሚያቀርብልሽ ነገር አመስግኝው።
ይሄንን በማረግሽ በቤትሽ ሰላም በረከት ይሞላል ባልም ውጭ የምታያቸውን ያማሩ ሴቶች ከሚስትህ ጋር አታወዳድር ዝቅ ያለችው ለአንተ ፍቅርና ለቤትህ ማማር ለጓዳችሁ መሙላት ነውና።
መፋቀር መከባበር መተሳሰብን አዳብሩ ባል ለሚስትህ ሰላም እና ደስታ አስብላት ሚስትም እንደዚያው ትዳር ማለት አንዱ አንዱን የሚደግፍበት ነውና በመተሳሰብ ኑሩ።

ለጥንቃቄ
ከዚህ ቡሃላ በመዲናችን አዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሲሸና የተገኘ ግለሰብ 2000 ብር እንደሚቀጣ ተገልጿል።
ዛሬ ሲሸኑ ከተያዙ 50 ግለሰቦች የኢትዮጵያ ደንብ ማስከበር ባለሰልጣን +100ሺ ብር ከቅጣት ማግኙትን ይፋ አድርጓል።
ሙስሊምን ይመለከተዋል እንዴ ይሄ ዜና ጀምዓው?😂😂

ዚክርና ጥቅሞቹ
🕯አላህን ማሥታወሥ ያለዉ ጥቅም እና ትሩፋት
🔸አላህን ማሥታወሥ ነፍሥያ እና ሸይጧን ላይ ድል የመቀዳጃ ትልቅ በር ነው
🔹 ወደ አላህ ሡብሀነ ወተዓላ መዳረሻ መንገድ ነው
🔸 አላህ ሡብሀነ ወተዓላ የዚክርን በር የከፈተለት ሰው የሁሉንም የኸይር በሮች አግኝቷል
🔹የዚክር በር የተዘጋበት ሰው የኸይር በሮች ተዘግተውበታል
🔸ዚክርን አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ያገራለት ሠው ዒባዳዎች ሁሉ ይገሩለታል
🔹ዚክር የከበደውና ከዚክር የሠነፈ ሰው ከዒባዳዎችም ይሠንፋል
🔸 ዚክር ማብዛት ሸይጧንን ከሰው ልጆች ያርቃል
🔹ዚክር አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ያሥደሥታል፣የአዱንያን ጭንቀት ያሥወግዳል
🔸በልብ ውሥጥ ደሥታን ይፈጥራል፣የደረቁ ቀልቦችን ያረጥባል
🔹ወንጀሎችን ያራግፋል የብቸኝነትን ስሜት ያሥወግዳል ከአላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ ቅጣትም ይጠብቃል
🔸 ዚክር የሚያበዛ ሠው ከሙናፊቅነት ይድናል
🔹የቂያማ ቀን ከመፀፀት እና ከመቆጨትም ያድናል
🔸ጀነት ላይ የሰው ልጆች አትክልት እና ፍራፍሬ የሚያገኙትም በአዱንያ በሚያደርጉት ዚክር ልክ ነው፡፡
🔹የህሊናን እረፍት ይሠጣል
🔸ዚክር የሚል ሰው ላይ የአላህ ራህመት ይወርድበታል፣ መላኢኮች ዙሪያውን ይከቡታል
🔹 በአዱኒያ ዚክር ለሚያበዛ ሰው አላህ ግንባሩ ላይ ኑርን ይሠጠዋል፣ ቀብር ውስጥም አላህ ብርሃንን ይፈጥርለታል፡፡
🔸የቂያማ ቀንም በአዱኒያ ያደርገው የነበረው ዚክር ሲራጥን በሠላም እንዲሻገር ያደርገዋል፣ ፊቱም ያበራል፡፡✨ለዚህም ነው አላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ የሠው ልጆች ዚክርን እንዲያበዙ በተለያዩ የቁርኣን አያዎች (አንቀፆች) ያዘዛቸው፣ ረሡልም ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም በብዙ ሀዲሶች ዚክርን ማብዛት እንዳለብን ገልፀዋል፣ ዚክር የሚያበዙ ሰዎች የሚያገኙትን ትሩፋትም ጠቅሠዋል፣
🚩አላህ ሡብሀነ ወተዓላ በቁርኣኑ
يَا أَيُّهَا الَّذَ آمَنُوا اذْكُرُوا اللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا
وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
(ሡረቱል አህዛብ፡41-42)
[ "እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ :—አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ብዙ ማሥታወሥን አሥታውሡት ጠዋትና ማታም አጥሩት"] ይላል
🚩በሌላውም የቁርአን አያ የሡን ትክክለኛ ባሮችን መገለጫ ሢገልፅ እነዚያ ያመኑ አላህን በማሥታወሣቸው ልባቸዉ ይረጋጋል የሠው ልጆች ሆይ አላህን በማሥታወሥ የልብ ሠላም እና እርጋታ ይገኛል፡፡ብሏል ፣
🚩በሌላኛው የቁርኣን አያም "አሥታውሡኝ አሥታውሣችኋለሁ "ብሏል፡፡
ሐጅ ሥርአት ላይ ዒባዳችሁን ሥትጨርሡ አላህ ሡብሀነ ወተአላን አሥታውሡ ቤተሠቦቻችሁን እና ዘመዶቻችሁን ከምታሥታውሡት የበለጠ ይላል "
"አላህን ሡብሀነ ወተዓላ በብዛት አሥታውሡት ፣እነሆ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ትድናላችሁ" ይላል
🔸በተለያዩ የቁርኣን አያዎች ላይ የዚክርን ጥቅሞች አላህ ገልጿል።
📎ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሚከተለውን ብለዋል("አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ባሮቹ ላይ ማንኛውንም አይነት ዒባዳ አልደነገገም ዒባዳው በግልፅ በውል የሚታወቅ ገደብና መጠን ቢያደርግለት እንጂ!" )
▶ይህን ዒባዳ የታዘዙ እና የተደነገገላቸው ሰዎችን ኡዝር ባላቸው ሠአት ይህን ዒባዳ ቢተውት ምንም ችግር የለውም ብሎም ቢያሣውቅ እንጂ ፡፡ ዚክር ሢቀር 👌
📌ዚክርን በተመለከተ ይሄን ያህል ብቻ ዚክር አድርጉ ብሎ አላህ አልገደበውም ፣እንዲሁ ዚክርን መተውም አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ለማንም አልፈቀደም ለመተዉም ኡዝር አልሰጠም። አእምሮውን የሣተ፣ ራሡን መቆጣጠር ያቃተው ሰው ካልሆነ በሥተቀር ዚክርን ለመተው አላህ ለማንም ኡዝር አልሠጠም፡፡
እንዲሁም ዚክርንም በዚህ ሠአት በሉ ብሎ አላህ አልገደባቸውም፡፡በጊዜ የተገደቡ ዚክሮች ቢኖሩም በዛ ወቅት እነዚህ ዚክሮች መባል አለባቸው በዚህ ሠአት ቢባሉ ይመረጣል ፣በማለት ነብያችን ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም የተናገሩት ካልሆነ በስተቀር! እንጂ ከዚህ ሠአት ውጭ አላህን ማሥታወሥ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡
ቆማችሁም፣ተቀምጣችሁም ተኝታችሁም አላህን አሥታውሡ፡፡ቀንም ሌሊትም ባህርም ውስጥ የብሥም ላይ አላህን አሥታውሡ፣ ሀገርም ላይ ይሁን መንገድ ላይ ፣በድንጋጤና በሀዘንም ሆነ በደሥታ ጊዜ በህመምም ሆነ በጤንነት ጊዜ አላህን አሥታውሡ! በገሀድም በሚሥጥርም በየትኛውም ሁኔታ ላይ ብትሆኑ አላህን አሥታውሡት!
✍ ኡስታዝ አህመድ ኣደም
20/12/1437 ዓ.ሂ

1⃣ ሱብሂ፥ ፈርዱ 2 "ረካ" ነው
ሱናው ከፊት 2 "ረካ" ይሰገዳል
🔸ከኋላ የለውም አይሰገደም
2⃣ ዝሁር ፈርዱ 4 "ረካ" ነው
ሱና ከፊት 4 ከኋላ 4 መስገድ ይቻላል
3⃣ አስር ፈርዱ 4 "ረካ" ነው
ሱና ከፊት አራት "ረካ" መስገድ ይቻላል
🔸ከኋላ የለውም አይሰገድም
4⃣ መጝሪብ ፈርዱ 3 "ረካ" ነው
ሱና ከፊት ከፈለጉ- 2 "ረካ" መስገድ ይቻላል
ከኋላ 2 "ረካ" ይሰገዳል
5⃣ ዒሻ ፈርዱ 4 "ረካ" ነው
ሱና ከፊት ከፈለጉ- 2 "ረካ" መስገድ ይቻላል ከኋላ 2 ረካ ይሰገዳል
☞ ጥብቅ ማሳሰቢያ ከአስርና ከሱብሂ ፈርድ ሰላት በኋላ ሱና ሰላት አይሰገድም!

《8ቱ ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮች》
🔸1/ ሆን ብሎ ከሰላት ጋር ግንኙነት የሌለውን ንግግር መናገር ሁለት ፊደል እንኳ ቢሆን
🔹2/ጠሃራና ውዱዕን የሚያፈርስ ነገር መከሰት
🔸3/መሳቅ
🔹4/ሰላት ሲሰገድ መሸፈን ያለበት የሰውነት አካል መገለጥ
📌(እዚህ ጋር ☞ልብ መባል ያለበት ነገር ብዙ ሱሪና ሸሚዝ ወዘተ መሰል ነገሮችን ለብሰው የሚሰግዱ ሰዎች ጥንቃቄ ካላደረጉና ቲሸርት (ሸሚዛቸውን) ከሱሪያቸው ወይም ከሽርጣቸው ስር በደንብ አስገብተው ቀበቷቸውን አጥብቀው ካላሰሩ ሱጁድና ሩኩዕ ሲያደርጉ ወገባቸው ከታች ይገለጣል በዚህም ሰላታቸው ይበላሻል!)
🔹5/ቂብላን ለቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ኋላ መዞር እንዲሁም ወደ ቀኝና ግራ አብዛኛውን የሰውነት አካል በጣም ማዞር
🔸6/ መብላት
🔹7/ መጠጣት
🔸8/ሰላት ውስጥ ሆኖ ሰላት ከሚሰግድ ሰው የማይጠበቅን ነገር በተከታታይ እየፈጸሙ መጫወት፡፡
🔘ማሳሰቢያ፦
1/ እነዚህን ነገሮች ረስቶ ወይም ባለማወቅ ወይም ሌላ ሰው በቁም ነገር አስፈራርቶና አስገድዶት ከሆነ ያደረገው ሰላቱ አይበላሽም!
2/ ሴት ልጅ እየሰገደች:ـክንዷ ወይም እግሯ ወይም አንገቷና ትንሸም ቢሆን ፀጉሯ የታየና የተገለጠ እንደሆነ ሰላቷ ይበላሻል
🔸የምትሰግደው አጅነቢይ ያለበት ቦታ ላይ ከሆነም ፊቷንም ሙሉ መሸፈን ይጠበቅባታል።
ወላሁ አዕለም
✍ ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

የታመመ ባሏን በጀርባዋ የተሸከመችው ድንቅ ሴት...የ32 አመቷ ሂባ የ3 ልጆች እናት ናት ከ6 አመታት በፊት ቧሏ በተደራረበበት በሽታ እግሮቹ መንቃሳቀስ ይሳናቸዋል በየቀኑ ሆስፒታል መሄድና ህክምናውን መከታተል ነበረበት።
ታዲያ ይህች ድንቅ ሴት ፍታኝ አላለችም ወይም ጥላው አልሄደችም አብሽር እኔ አለውልህ ብላ በሴት አቅሟ ባሏን ጀርባዋ ላይ አዝላ በየቀኑ ወደ ሆስፒታል ታመላልሳለች።
በኔ እንዳታፍር ልፍታሽ ብያት ነበር እሷ ግን አልተቀበለችኝም። ሚስቴ ለኔ ልዩ ሴት ናት እናቴ በሆዷ 9 ወር ሚስቴ ደሞ ለ6 አመት በጀርባዋ ተሽክማኛለች ይላል። እሷም በበኩሏ እስክሞት ድረስ እሸከመዋለሁ ትላለች ።
ምን አይነት ድንቅ ፍቅር ነው ❤
(MP Ethiopia)

#ጀናባን_የሚመለከቱ_ህግና_ደንቦች
#አንብባችሁ_ለወንድሞቻችሁና_እህቶቻችሁ_አስተላልፉ_በጣም_ጠቃሚ_እና_አስፈላጊ_እውቀት_ያስጨብጣል።
የቃላት መፍቻ፡-
#1.መኒይ (የዘር ፈሳሽ)፡-
- በስሜት ተስፈንጥሮ ከእርካታ ጋር የሚወጣ ፈሳሽ ነው፡፡
- ለወንድ ወፍራምና (ወደ ቢጫነት የሚያደላ) ነጭ ፈሳሽ ሲሆን ለሴት ደግሞ ቀጭንና ቢጫ ነው፡፡ [ሙስሊም፡ 311]
ሽታው ወደሊጥ ሽታ የቀረበ ነው፡፡ በሆነ ምክንያት እነዚህ መታወቂያዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡
- ከወጣ በኋላ የሰውነት መቀዝቀዝ ዘና ማለት (ፉቱር) ይከተላል፡፡
- ፈሳሹ ሚዛን በሚደፋው የዑለማእ እይታ ጦሀራ እንጂ ነጃሳ አይደለም፡፡ ይህን የሚደግፉ ሶሒሕ ማስረጃዎች መጥተዋል፡፡
[ሙስሊም፡ 694] [አልኢርዋእ፡ 1/197]
- በውንም ይሁን በህልም ከወጣ ገላን መታጠብ ግዴታ ነው፡፡
#2.መዚይ፡-
- ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግ (የሚያጣብቅ)፣ ቀለም አልባ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡
- አወጣጡ ከእርካታ ጋር አይደለም፡፡ ተስፈንጥሮ ስለማይወጣ
መውጣቱ ላይስተዋል ይችላል፡፡
- ነጃሳ ስለሆነ የነካውን አካል ማጠብ ይገባል፡፡ ልብስን ግን የነካው ቦታ ላይ ውሃ በመርጨት ማፅዳት በቂ ነው፡፡
- የነካውን ቦታ እንጂ ገላን መታጠብ ግን ግዴታ አይደለም፡፡ ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡
#3.ወዲይ፡-
- ከሽንት በኋላ የሚወጣ ነጭ ሽታ አልባ ፈሳሽ ነው፡፡
- የሚያጣብቅ አይደለም፡፡
- ብይኑ ከሽንት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡
#4.ከሴቶች ብልት የሚወጣ ፈሳሽ፡-
- ከማህፀን የሚወጣ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡ መጠኑ ከሴት ሴት ይለያያል፡፡
- ሴቷ መውጣቱንም ላታስተውለው ትችላለች፡፡
- አካልንም ልብስንም ቢነካ አይነጅስም፣ ጦሃራ ነው፡፡
- ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡ ከሁለቱም መፀዳጃዎች በኩል የሚወጣ ነገር ውዱእ ያፈርሳልና፡፡ አወጣጡ ቋሚ ከሆነ ግን ለያንዳንዱ ሶላት ወቅቱ ከገባ በኋላ ውዱእ እያደረገች መስገድ ይገባል፡፡ ውዱእ ካደረገች በኋላ ቢወጣ ቦታም አይሰጠውም፡፡
#ገላን_መታጠብ_ግዴታ_የሚሆነው_መቼ_ነው?
#1.በውኑ ግንኙነት ከተፈፀመ የዘር ፈሳሽ (መኒይ)
#ቢፈስም_ባይፈስም ትጥበት ግዴታ ነው፡፡
#2. ግንኙነት #ባይፈፀምም የዘር ፈሳሽ (መኒይ)
#ከእርካታ ጋር ከወጣ ትጥበት ግዴታ ነው፡፡
#3. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ የዘር ፈሳሽ (መኒይ)ካገኘ በማያሻማ መልኩ መታጠብ ግዴታ ነው፡፡
#4. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ ነገር ግን ሲነቃ ምንም አይነት የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካላገኘ በማያሻማ መልኩ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ኡሙ ሱለይም የተባለችዋ ሶሐቢያህ ረዲየላሁ ዐንሃ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዲት ሴት ኢሕቲላም ከሆነች (በህልሟ ግንኙነት ስትፈፅም ካየች) የመታጠብ ግዴታ አለባትን?” ብላ ስትጠይቅ “ፈሳሽ ካየች አዎ”ሲሉ መልሰውላታል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
#5. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ በማያሻማ መልኩ
የመታጠብ ግዴታ አለበት፡፡
#6. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ነገር ግን ሲነቃ ፈሳሽ አገኘ፡፡ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) እንዳልሆነ እርግጠኛ ከሆነ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ የነካውን ግንሊያጥብ ይገባል፡፡ ብይኑ የሽንት ብይን ነውና፡፡
#7. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን #መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘ በ ሽታ ወይም በቻለው መንገድ ለመለየት ይሞክርና ጥርጣሬው መኒይ ወደመሆኑ ካደላ ይታጠብ፡፡ ጥርጣሬው መዚይ ወደመሆኑ ካደላ ግን በተለይም ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት አስቦ ከነበር እንደ መዚይ ይቁጠረውና የነካውን ቦታ ብቻ ይጠብ፡፡ ገላውን የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡
#8. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን #መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘና ግምቱ ወደየትኛውም ካላደላ፣ ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት #ያላሰበ ከሆነ ጉዳዩ አወዛጋቢ ቢሆንም ትክክለኛው ትጥበት የለበትም የሚል ነው፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡ [ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን፡ 11/161]
#የጀናባ_አስተጣጠብ_ሁለት_አይነት_ነው፡፡
#1. የሚያብቃቃ ማለትም ግዴታውን ለማውረድ የሚጠበቅ ሲሆን እሱም ሙሉ አካልን በውሃ ማዳረስ ነው፡፡ ባይሆን መጉመጥመጥና በአፍንጫ ውሃ መሳብ (ኢስቲንሻቅ) እንዳይረሳ፡፡ ለትጥበት ኒያ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ አንድ ሰው ጀናባ ማውረድን ሳያስብ እንዲሁ ውሃ ውስጥ ዋኝቶ ቢወጣ መላ አካላቱ ውሃ መንካቱ ብቻ ጀናባው ለመውረዱ በቂ አይሆንም፡፡ ይስተዋል! ይህን ትጥበት ካደረጉ በኋላ ውዱእም ባያደርጉ መስገድ ይቻላል፡፡ ባይሆን ከትጥበቱ መሀል ውዱእ የሚያፈርስ ነገር መፈፀም የለበትም፡፡
#2. ሌላኛውና በላጩ ግን በቅድሚያ ሁለት እጆችን መታጠብ፡፡ ከዚያም ኢስቲንጃእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ውዱእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ከእራስ ጀምሮ ቀሪ አካላትን ውሃ ማዳረስ፡፡ እግርን ከውዱእ ጋር ማጠብም ይቻላል፤ መጨረሻ ላይ ማጠብም ይቻላል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
ማሳሰቢያ፡-
ሴቷ ለትጥበት ስትል የፀጉር ጉንጉኗን የመፍታት ግዴታ የለባትም፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም: ኡሙ ሰለማህ ለጀናባህ ወይም ለሐይድ ትጥበት ፀጉሯን “ልፍታው ወይ?” ብላ ስትጠይቃቸው “አይ! የሚበቃሽ ከእራስሽ ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ማፍሰስ ብቻ ነው” ብለዋታል፡፡ [ሙስሊም]
ስለዚህ ፀጉር ሳይፈታ ውሃ መድረስ ከቻለ መፍታት አይጠበቅም፡፡
#ለማጣቀሻነት_የተጠቀምኩት
#1. ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን
#2. ፈትሑልዐላም ፊ ዲራሰቲ አሓዲሢ ቡሉጊልመራም እና ሌሎችም
ሼር ማድረግ እንዳይረሱ፡