Telegram Web Link
#ልጅ #አገረድ #አገባ #ግን (ቢክራ) ድንግል አላገኘባትም ??
ሸይኽ ኢብኑ ባዝ (ረሂመሁላህ) ተጠየቁ :-

▶️ #ጥያቄ:- ሰውየው ልጅ አገረድ አግብቶ ድንግል ሁና ካላገኛት ምን ማድረግ ነው ያለበት ?

✔️ #መልስ:- ይሄ ብዙ ምክኒያቶች ይኖሩታል : ድንግሏ ምናልባት ያለ ዝሙት ሊፈርስ ይችላል። የልጂቱ ውጫዊ ስብዕናዋ መልካም ከሆነ እናም በዲኗ የተስተካከለች ከሆነች በሷ ላይ ጥሩ ግምትና መልካም ጥርጣሬን ማሳደር የግድ ነው። በዚያ ላይ ጥሩ ጥርጣሬን ማሳደር ግድ ይላል።

☞ ወይንም አፀያፊውን ዝሙት ሰርታ ከዚያ አላህ መርቷት ከሰራችሁ መጥፎ ተግባር ተፀፅታና ቶብታም ሊሆን ይችላል። ከዚያም ወደ ጥሩነትና መልካምነት ከተቀየረች (ቢክራ) ድንግል አለመኖሯ እሱን አይጐዳውም።

✔️ ምናልባትም ድንግሏ በወር አበባ ብርታት ምከንያት ፈርሶ ሊሆን ይችላል።
☞ጠንካራ (ሃይድ) የወር አበባ (ቢክራን)ድንግልን ያፈርሳል። ይሄህ ኡለሞች አውስተውታል።

✔️ ልክ እንደዚሁም በአንዳንድ ዝላዮች ድንግል ሊፈርስ ይችላል። ከሆነ ቦታ ወደሆነ ቦታ ስትዘል። ወይንም ከከፍተኛ ቦታ ወደ ዝቅተኛ ቦታ በምትወርድ ጊዜ በዚህ አጋጣሚ ድንግል ሊፈርስ ይችላል።

🌿 #ስለዚህ የድንግል መፍረስ የግድ በአፀያፊው ዝሙት ብቻ ሊሆን አይችልም። በጭራሽ። ከዝሙት ውጭ በሆነ ክስተት ነው ድንግል የፈረሰው ካለች ወይንም በዝሙት ነው ድንግሌ የፈረሰው ግን ተገድጄ እና ተደፍሬ ነው ካለች ይሄ እሱን አይጎዳውም።
-
✔️ #ወይንም በፍላጎቷ ዝሙት ሰርታ ከሆነ ድንግሏ የፈረሰው ግን ያንን ያደረገችው በማታውቅበትና በመሃይምነቷ ጊዜ እንደሆነም እናም አሁን ከዚያ ቶብታና ተፀፅታ ከሆነ ይሄም እሱን አይጎዳውም።

🍂 #ይሄን #የሷን ሚስጥር ሊበትንባት እና ሊያሰራጭባት አይገባም ይልቁንስ ሊደብቅላት ይገባል። በእርሱ ግምት እውነተኛነቷንና ቅንነቷን እናም መስተካከሏን ካመነበት ከእርሱ ጋር ያስቀራታል። ካሎነ ግን በሷ ላይ ያደረበት ግምት ጥሩ ካልሆነ ይፈታታል የሷን ሚስጥር ከመደበቅና ከመጠበቅ ጋር በጭራሽ ሚስጥሯን ባደባባይ መግለፅ አይገባውም።

ምንጭ፡- መጅሙዕ አል-ፈታዋ (287/286-30)

@yasin_nuru           @yasin_nuru
"ሒጃብ ካላወለቃችሁ ነገ ጠዋት መሰጠት የሚጀምረውን የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መፈተን አትችሉም"

ሒጃብ ካላወለቁ በነገው እለት የሚሰጠውን የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና መፈተን እንደማይችሉ በሀድያ ዞን ሆሳዕና ከተማ የሚገኘው የዋቻሞ ዩንቨርሲቲ መግለጹን ተማሪዎች ለሀሩን ሚዲያ ተናግረዋል።

በዚህም ምክንያት 12 አመት የደከሙበት ትምህርት በመጨረሻ ቀን ሊያሰናክሉባቸው መሆኑንና የሚመለከተው አካል አፋጣኝ መፍትሄ እንዲሰጣቸው ተማጽነዋል።

@yasin_nuru @yasin_nuru
የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለምትወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መልካም ዕድል እንመኛለን ❤️

አላህ ጥሩ ውጤት የምታመጡ ያድርጋችሁ🥰


@yasin_nuru @yasin_nuru
🎖🎖=========== #ሃያእ========🎖🎖
                   አሚር ሰይድ

    ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል- 'ሃያእና ኢማን አንዱ ከሌላዉ ጋር የተጠላለፉ ናቸው። እንድ ሰው እንዱን ካጣ ሌላውንም ማጣቱ አይቀርም፡፡*

☞ ኢምራን ኢብን ሁሴን (ረ.ዐ) ባወሩት ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ኢስላማዊ ሃፍረት (ሃያእ) የሚያመጣው ነገር ሌላ ሳይሆን ጥሩነትን ነው፡፡''

☞እንደገናም በሌላ ሐዲስ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ሃያእ የሚመጣው ከኢማን (እምነት) ነው፡፡ እምነት ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስድነት (ባለጌነት) ከክህደት የሚመነጭ ሲሆን ክህደት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል፡፡

#የኢማም_ማሊክ መወጠእ ኪታብ ላይ የተጠቀሰ
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “እያንዳንዱ ሃይማኖት የየራሱ የሆነ ተፈጥሮኣዊ ባህሪያት አሉት፡፡ የኢስላም ተፈጥሮአዊ ባህሪ ሃያእ ነው፡፡"


⚡️⚡️⚡️ አዒሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ብላለች
"የአላህ መልዕክተኛ ﷺእንዲሁም አባቴ አቡበክር (ረ.ዐ) በቤቴ አንድ ጥግ ላይ ተቀብረው እያሉ በቤት ውስጥ እንደልቤ ተገላልጬ እቀመጥ ነበር። ሆኖም ግን ከጊዜ በኋላ ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) ሞተው ከእነርሱ ጐን ሲቀበሩ ለእርሳቸው ከነበረኝ ሃያእ የተነሳ በቤቴ ውስጥ እያለሁም እሸፋፈን ነበር፡፡ የምሸፋፈነዉ  ኡመር (ረ.ዐ) ሙት መሆናቸውን እያወቅኩ ነው... ግን እሷቸዉ ቢሞቱትም ቀብራቸዉ ከነብዩ ﷺ ቅርብ ስለሆነ ነዉ ብላለች
፡፡

⚠️ግን እኛስ የሀያእ መጠናችን ምን ያህል ይሆን???

@yasin_nuru @yasin_nuru
2025/07/01 08:17:41
Back to Top
HTML Embed Code: