Telegram Web Link
የ12ተኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለምትወስዱ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች መልካም ዕድል እንመኛለን ❤️

አላህ ጥሩ ውጤት የምታመጡ ያድርጋችሁ🥰


@yasin_nuru @yasin_nuru
🎖🎖=========== #ሃያእ========🎖🎖
                   አሚር ሰይድ

    ሀቢቡና ሙሀመድ ﷺ እንዲህ ብለዋል- 'ሃያእና ኢማን አንዱ ከሌላዉ ጋር የተጠላለፉ ናቸው። እንድ ሰው እንዱን ካጣ ሌላውንም ማጣቱ አይቀርም፡፡*

☞ ኢምራን ኢብን ሁሴን (ረ.ዐ) ባወሩት ሐዲስ የአላህ መልዕክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “ኢስላማዊ ሃፍረት (ሃያእ) የሚያመጣው ነገር ሌላ ሳይሆን ጥሩነትን ነው፡፡''

☞እንደገናም በሌላ ሐዲስ ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- ሃያእ የሚመጣው ከኢማን (እምነት) ነው፡፡ እምነት ደግሞ ወደ ጀነት ይመራል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ስድነት (ባለጌነት) ከክህደት የሚመነጭ ሲሆን ክህደት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል፡፡

#የኢማም_ማሊክ መወጠእ ኪታብ ላይ የተጠቀሰ
ነቢዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፡- “እያንዳንዱ ሃይማኖት የየራሱ የሆነ ተፈጥሮኣዊ ባህሪያት አሉት፡፡ የኢስላም ተፈጥሮአዊ ባህሪ ሃያእ ነው፡፡"


⚡️⚡️⚡️ አዒሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ብላለች
"የአላህ መልዕክተኛ ﷺእንዲሁም አባቴ አቡበክር (ረ.ዐ) በቤቴ አንድ ጥግ ላይ ተቀብረው እያሉ በቤት ውስጥ እንደልቤ ተገላልጬ እቀመጥ ነበር። ሆኖም ግን ከጊዜ በኋላ ኡመር ኢብን አል-ኸጧብ (ረ.ዐ) ሞተው ከእነርሱ ጐን ሲቀበሩ ለእርሳቸው ከነበረኝ ሃያእ የተነሳ በቤቴ ውስጥ እያለሁም እሸፋፈን ነበር፡፡ የምሸፋፈነዉ  ኡመር (ረ.ዐ) ሙት መሆናቸውን እያወቅኩ ነው... ግን እሷቸዉ ቢሞቱትም ቀብራቸዉ ከነብዩ ﷺ ቅርብ ስለሆነ ነዉ ብላለች
፡፡

⚠️ግን እኛስ የሀያእ መጠናችን ምን ያህል ይሆን???

@yasin_nuru @yasin_nuru
የመስጂድ ስርዕቶች

❶ መስጂድ ከመምጣት በፊት ነጭ ሽንኩርት ከመመገብ መቆጠብ

❷ ሴት ልጅ ሽቶ ከመቀባት መቆጠብ

❸ ወደ መስጂድ ሲኬድ በእርጋታ መራመድ

❹ ወደ መስጂድ ሲኬድ ይህን ዚክር(“አላሁመጅዕል ፊቀልቢ ኑራ ወፊ ሊሳኒ ኑራ ወፊ ሰምዒ ኑራ ወፊ በሰሪ ኑራ ወሚን ፈውቂ ኑራ ወሚን ታህቲ ኑራ ወአን የሚኒ ኑራ ወአን ሺማሊ ኑራ ወሚን አማሚ ኑራ ወሚን ኸልፊ ኑራ ወአእዚምሊ ኑራ ”)ማለት

❺ መስጂድ ሲገባ ቀኝ እግርን ማስቀደም

❻ መስጂድ ሲኬድ ይህን ዚክር(“አላሁመ ሰሊ ወሰሊም አላ ሙሀመድ ወአላ አሊ ሙሀመድ አላሁመፍታህሊ አብዋበ ራህመቲክ ”)ማለት

❼ ሁለት ረከዕ (ተህየተል መስጂድ) መስገድ

❽ መስጂድ ውስጥ ከመትፋት መጠንቀቅ

❾ መስጂድ ውስጥ ድምፅን ዝቅ ማድረግ

❿ መስጂድ ውስጥ ከመሸጥና ከመግዛት መቆጠብ

❶❶ መስጂድ ውስጥ የጠፋን ነገር አፋልጉኝ ከማለት መጠንቀቅ

❶❷ አዛን ከተደረገ በሆላ ከመስጂድ አለመውጣት

❶❸ ከመስጂድ ሲወጣ ግራ እግርን ማስቀደም

❶❹ ከመስጂድ ሲወጣ ይህን ዚክር (“አላሁመ ዒኒ አስአሉከ ሚን ፈድሊክ”)ማለት

@yasin_nuru @yasin_nuru
የዓሹራ ፆም መቼ ነው?
ዓሹራእ መቼ ነው?

የሙሀረም ወር አስረኛው ቀን ላይ ነው። የፊታችን ቅዳሜ ማለት ነው።

    እንዴት ነው የሚፆመው?

የሚፆመው 10ኛው ቀን ሲሆን ነገር ግን አህለል ኪታቦችን ለመኻለፍ 9ኛውን ጭምር መፆም በላጭ ነው።

9ኛውን ቀን መጨመር ያልቻለ ደግሞ 10ኛውን(ቅዳሜ) እና 11ኛውን(እሁድ) መፆም ይችላል። ከፊትም ሆነ ከኋላ ማስከተል ያልቻለ አስረኛውን ቀን ብቻውን መፆም ይችላል።

የ1447 ዓ.ሂ ዓሹራ ጾም

🔅ቀኑን መፆሙ የ አንድ ዓመት ያለፈ ወንጀልን ያስምራል።

ኡስታዝ አሕመድ ሸይኽ ኣደም

አሏህ በሰላም ደርሰው ከሚፆሙት ያድርገን🤲

@yasin_nuru @yasin_nuru
#ዱንያ_እንዲ_ናት

#ዲያጎ_ጆታ ፖርቹጋላዊ እግር ኳስ ተጫዋች
ባለፈው ሳምንት ለሠርጉ ስፔን ነበር ።ዛሬ ማለዳ በደረሰበት አሰቃቂ አደጋ ከዚህ አለም በሞት ተለይቷል።

ብዙ ህልሞች እቅዶች የነበሩት ገና የ29 አመት ወጣት ።
ሞት ዕድሜ አያውቅም። ገና ወጣት ስለሆንክ ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት ለመለወጥ እና ለማስተካከል በቂ ጊዜ እንዳለህ በማሰብ ዱንያ ላይ ባለህ ጊዜህ አትታለል ነገህ ዋስትና የለውም

#ሳይረፍድ_ቶሎ_ወደ_አላህ_እንመለስ

وَلِكُلِّ أُمَّةٍ أَجَلٌ ۖ فَإِذَا جَاءَ أَجَلُهُمْ لَا يَسْتَأْخِرُونَ سَاعَةً ۖ وَلَا يَسْتَقْدِمُونَ

ለሕዝብም ሁሉ የተወሰነ ጊዜ አላቸው፡፡ ጊዜያቸውም በመጣ ወቅት አንዲትን ሰዓት አይቆዩም፡፡ (ከጊዜያቱ) አይቀደሙምም፡፡

@yasin_nuru @yasin_nuru
#የሚገርም እና የሚጠቅም ታሪክ!
ከ1068 አመት በፊት የተደረገ ቃለ ምልልስ

-በእርጋታ ያንብቡት የካሀዲዎችን መሀይምነት የአሊሞችን የእውቀት ምጥቀት ያስተውሉበታል!
_
💫💫አቡበክር አል—ባቂላኒ (ረሂመሁላሁ ተአላ) በዘመናቸው ታላቅ አሊም ነበሩ

- የኢራቁ (የሙስሊሙች) ንጉስ በ371ሂ ቂስጦንጦኒያ ወደተባለች የሮም ግዛት ከነሷራዎች (ክሪስቲያኖች) ጋር እንዲወያዩ መርጡ ልኳቸዋል።

- የሮሙ ንጉስ አቡበክር አል—ባቂላኒ መምጣታቸውን ሲሰማ አቡበክር ከበሩ እጥረት የተነሳ ልክ ሩኩእ እንደሚያደርግ ሰው ከንጉሱ እና ከአጃቢዎቹ ፊት እንዲያጎነብሱ (ወደንጉሱ የሚያስገባውን) በር እንዲያሳጥሩት አዘዘ!

🌙አቡበክርም (በሩ ዝቅ ተደርጎ ሲያዩት የታሰበውን ተንኮል) ተረዱ እና ፊታቸውን አዙረው ጎንበስ በማለት ወደኋላ እየተራመዱ ገቦ በማለት ፊት ለፊት ሳይሆን ጀርባቸውን ለንጉሱ ስጥተው ወደኋላ እየተራመዱ በሩን
አለፉት)

- የዝህኔ የሮሙ ንጉስ ነገሮችን ፈጥኖ የሚረዳ ሰው ፊት እንዳለ ተረዳ!

- አቡበክርም ገቡ ሰላም አሏቸው በኢስላማዊው ሰላምታ ግን አይደለም ያሏቸው። ምክኒያቱም ነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም የመፅሀፍ ሰዎችን በሰላምታ መጀመርን ከልክለዋል።

- ከዚያም አቡበክር ወደ ትልቁ መነኩሴ ዘወር በማለት "እንዴት ነዎት ሚስትና ልጆቾዎስ እንዴት ናቸው።" አሉት

- እሄን ሲሰማ የሮሙ ንጉስ ተቆጣ "የኛ መነኩሴዎች እንደማያገቡ እና ልጅም እደማይወልዱ አታውቅምን?"አላቸው

🌙አቡበክርም አሏሁ አክበር!!! "እናንተ መነኩሲያችሁን ከትዳር እና ልጅ ከመውለድ ታጠራላችሁ ከዚያም ጌታችሁን መርየምን አግብቶ ኢሳን ወለደ በማለት ትጠራጠራላችሁ?!" አሉት

- ከዚያም ንጉሱ "አዒሻ በሰራችው ስራ ምን ትላለህ?" አላቸው።

- አቡበክርም አዒሻ (በሙናፊቆችና ራፊዷዎች) በዝሙት ብትጠረጠር መርየምም (አይሁዶች በዝሙት) ጠርጥረዋታል።

- ሁለቶቹም ቢሆኑ ከዝሙት የፀዱ ናቸው።
ነገርግን አዒሻ አግብታለች አልወለደችም መርየም ደግሞ ያለ ባል ወልዳለች!

- ታዲያ ማንኛይቷ ነች ውድቅ ለሆነው ጥርጣሬ ተገቢቷ?

- እኔ ግን ሁለቱንም (ንፁሀን ናቸው ብየ እመሰክራለሁ)" አሉት

ንጉሱም በንዴት አበደ "ነብያችሁ ጦር ይሄድ ነበር?"

አቡበክር "አዎ"

ንጉሱ "ከጦር ፊት ተሰልፎ ከጠላት ጋር ይገዳደል ነበርን?"

አቡበክር "አዎ"

ንጉስ "ያሸንፍስ ነበር?"

አቡበክር "አዎ"

ንጉስ "ይሸነፍስ ነበር"

አቡበክር "አዎ"

ንጉሱ "ይገርማል ነብይ ይሸነፋልን?" በማለት ተደነቀ🤔

አቡበክር አል—ባቂላኒም
" #ጌታ #ይሰቀላልን??" በማለት አፉን አስያዙት🤫

*ያም (በጌታው) የካደው ሰው ዋለለ (መልስ አጣ)!!*🤷‍♂

 @yasin_nuru  @yasin_nuru
2025/07/04 12:41:12
Back to Top
HTML Embed Code: