Telegram Web Link
#የሚገርም እና የሚጠቅም ታሪክ!
ከ1068 አመት በፊት የተደረገ ቃለ ምልልስ

-በእርጋታ ያንብቡት የካሀዲዎችን መሀይምነት የአሊሞችን የእውቀት ምጥቀት ያስተውሉበታል!
_
💫💫አቡበክር አል—ባቂላኒ (ረሂመሁላሁ ተአላ) በዘመናቸው ታላቅ አሊም ነበሩ

- የኢራቁ (የሙስሊሙች) ንጉስ በ371ሂ ቂስጦንጦኒያ ወደተባለች የሮም ግዛት ከነሷራዎች (ክሪስቲያኖች) ጋር እንዲወያዩ መርጡ ልኳቸዋል።

- የሮሙ ንጉስ አቡበክር አል—ባቂላኒ መምጣታቸውን ሲሰማ አቡበክር ከበሩ እጥረት የተነሳ ልክ ሩኩእ እንደሚያደርግ ሰው ከንጉሱ እና ከአጃቢዎቹ ፊት እንዲያጎነብሱ (ወደንጉሱ የሚያስገባውን) በር እንዲያሳጥሩት አዘዘ!

🌙አቡበክርም (በሩ ዝቅ ተደርጎ ሲያዩት የታሰበውን ተንኮል) ተረዱ እና ፊታቸውን አዙረው ጎንበስ በማለት ወደኋላ እየተራመዱ ገቦ በማለት ፊት ለፊት ሳይሆን ጀርባቸውን ለንጉሱ ስጥተው ወደኋላ እየተራመዱ በሩን
አለፉት)

- የዝህኔ የሮሙ ንጉስ ነገሮችን ፈጥኖ የሚረዳ ሰው ፊት እንዳለ ተረዳ!

- አቡበክርም ገቡ ሰላም አሏቸው በኢስላማዊው ሰላምታ ግን አይደለም ያሏቸው። ምክኒያቱም ነብዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም የመፅሀፍ ሰዎችን በሰላምታ መጀመርን ከልክለዋል።

- ከዚያም አቡበክር ወደ ትልቁ መነኩሴ ዘወር በማለት "እንዴት ነዎት ሚስትና ልጆቾዎስ እንዴት ናቸው።" አሉት

- እሄን ሲሰማ የሮሙ ንጉስ ተቆጣ "የኛ መነኩሴዎች እንደማያገቡ እና ልጅም እደማይወልዱ አታውቅምን?"አላቸው

🌙አቡበክርም አሏሁ አክበር!!! "እናንተ መነኩሲያችሁን ከትዳር እና ልጅ ከመውለድ ታጠራላችሁ ከዚያም ጌታችሁን መርየምን አግብቶ ኢሳን ወለደ በማለት ትጠራጠራላችሁ?!" አሉት

- ከዚያም ንጉሱ "አዒሻ በሰራችው ስራ ምን ትላለህ?" አላቸው።

- አቡበክርም አዒሻ (በሙናፊቆችና ራፊዷዎች) በዝሙት ብትጠረጠር መርየምም (አይሁዶች በዝሙት) ጠርጥረዋታል።

- ሁለቶቹም ቢሆኑ ከዝሙት የፀዱ ናቸው።
ነገርግን አዒሻ አግብታለች አልወለደችም መርየም ደግሞ ያለ ባል ወልዳለች!

- ታዲያ ማንኛይቷ ነች ውድቅ ለሆነው ጥርጣሬ ተገቢቷ?

- እኔ ግን ሁለቱንም (ንፁሀን ናቸው ብየ እመሰክራለሁ)" አሉት

ንጉሱም በንዴት አበደ "ነብያችሁ ጦር ይሄድ ነበር?"

አቡበክር "አዎ"

ንጉሱ "ከጦር ፊት ተሰልፎ ከጠላት ጋር ይገዳደል ነበርን?"

አቡበክር "አዎ"

ንጉስ "ያሸንፍስ ነበር?"

አቡበክር "አዎ"

ንጉስ "ይሸነፍስ ነበር"

አቡበክር "አዎ"

ንጉሱ "ይገርማል ነብይ ይሸነፋልን?" በማለት ተደነቀ🤔

አቡበክር አል—ባቂላኒም
" #ጌታ #ይሰቀላልን??" በማለት አፉን አስያዙት🤫

*ያም (በጌታው) የካደው ሰው ዋለለ (መልስ አጣ)!!*🤷‍♂

 @yasin_nuru  @yasin_nuru
💐💐የኒካሕ መስፈርቶች /ሸርጦች/

1⃣. የተጋቢዎቹን ስም ለይቶ መግለፅ፡- ከአንድ በላይ ልጆች ባሉበት ሁኔታ “ልጄን አጋብቼሃለሁ” ወይም ለልጅህ አጋብቼያለሁ” ቢል በቂ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ስም ተጠቅሶ ለምሳሌ “ልጄን ፋጢማን ለዐብደላህ አጋብቼያለሁ” ሊል ነው፡፡

2⃣. የሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት፡- የግዴታ ጋብቻ ተቀባይነት የለውም፡፡
[ቡኻሪ፡ 5136፣ ሙስሊም፡ 1419]

3⃣. ለሴቷ ወልይ መኖር፡፡ ነብዩ ﷺ “ያለ ወልይ ኒካሕ የለም” ብለዋልና፡፡
[ሶሒሕ ኢብን ማጃህ፡ 1537]

4⃣ ኒካሑ ሲታሰር ሁለት ብቁ ምስክሮች መኖራቸው፡፡ [ሶሒሕ ኢብን ሒባን፡ 4075]

5⃣. ተጋቢዎቹን እንዳይጋቡ የሚከለክል ነገር (ቅርብ ዝምድና፣ አማችቻ፣ ጥቢ፣ የእምነት ልዩነት፣ …) አለመኖር፡፡

የኒካሕ ማእዘናት፡-

☞. ጋብቻን ከሚከለክሉ ነገሮች ነፃ የሆኑ ተጋቢዎች

☞. ከሴቷ ወልይ በኩል “አጋብቻለሁ” ወይም መሰል የይሁንታ ቃል

☞. የአግቢው ወይም ወኪሉ “ተቀብያለሁ” ወይም መሰል የመስማማት ቃል

(ከአልፊቅሁል ሙየስሰር ኪታብ የተወሰደ ገፅ፡404-406)

በወንድም ኢብኑ ሙነወር

@yasin_nuru @yasin_nuru
#አንድ #ሀብታም ሰው ዘመናዊ መኪናውን አቁሞ ለጉዳዩ ገባ ይላል ጉዳዩን ጨርሶ ወደመኪናው ሲመለስ የአንዱ ጎማው 4 ብሎኖች ተፈተው ተወስዶበት ያያል ይህኔ ይበሳጭ😡😡 እና አከባቢው ላይ ዞር ዞር ብሎ ብሎን ፈልጎ ያጣል::

ያኔ መኪናውን ተደግፎ በጭንቀት ቆዝሞ ሰለ አከባቢው ላይ ያለ አንድ "# አእምሮ ህመምተኛ" ነገሩን ተከታትሎ ኖራል ምን ሆነህ ነው ይለዋል ሰውየውም በንቀት አይን አየት እያደረገ

" የጎማዬ ብሎኖች ተፈተው ተወስዶብኝ ነው እንዳልገዛ አከባቢው ላይ የለም " ይለዋል በብስጭት ስሜት🥺

ይህኔ " #የአእምሮ ህመምተኛው ነው እንዴ ታዲያ ለምን ከ3 ጎማዎች #አንድ አንድ ብሎን ፈተህ አራተኛውን ጎማ አታስርም "አለው::

👍ሰውየውም በመገረም ሀሳቡ በጣም አስደሰተው አንዳለውም አደረገ።

ግን " #የአይምሮ ህመምተኛው " ዘዴውን ነገሮት ሊሄድ ሲል

ሰውየው " ቆይ አንተ "እብድ "አይደለህ እንዴ አንዴት ይህ ሀሳብ ሊመጣልህ ቸለ ይለዋል "

" #አእምሮ ህመምተኛው" ቀበል አድርጎ
"ታዲያ እኔ " እብድ ነኝ እንጂ ደደብ አይደለሁም" ብሎ ይመልስለታል ፡፡

☞ዝቅ በል ዝቅ ስትል ከፍ ትላለህ ተናነስ ራስህን አትቆልል

☞ሁሌም እኔ አዋቂነኝ አትበል፡፡

☞ሰውን በአለባበሱ አንገምት።,

Islam & science

@yasin_nuru @yasin_nuru
2025/07/06 12:22:46
Back to Top
HTML Embed Code: