Telegram Web Link
💐💐የኒካሕ መስፈርቶች /ሸርጦች/

1⃣. የተጋቢዎቹን ስም ለይቶ መግለፅ፡- ከአንድ በላይ ልጆች ባሉበት ሁኔታ “ልጄን አጋብቼሃለሁ” ወይም ለልጅህ አጋብቼያለሁ” ቢል በቂ አይሆንም፡፡ ስለዚህ ስም ተጠቅሶ ለምሳሌ “ልጄን ፋጢማን ለዐብደላህ አጋብቼያለሁ” ሊል ነው፡፡

2⃣. የሁለቱ ተጋቢዎች ስምምነት፡- የግዴታ ጋብቻ ተቀባይነት የለውም፡፡
[ቡኻሪ፡ 5136፣ ሙስሊም፡ 1419]

3⃣. ለሴቷ ወልይ መኖር፡፡ ነብዩ ﷺ “ያለ ወልይ ኒካሕ የለም” ብለዋልና፡፡
[ሶሒሕ ኢብን ማጃህ፡ 1537]

4⃣ ኒካሑ ሲታሰር ሁለት ብቁ ምስክሮች መኖራቸው፡፡ [ሶሒሕ ኢብን ሒባን፡ 4075]

5⃣. ተጋቢዎቹን እንዳይጋቡ የሚከለክል ነገር (ቅርብ ዝምድና፣ አማችቻ፣ ጥቢ፣ የእምነት ልዩነት፣ …) አለመኖር፡፡

የኒካሕ ማእዘናት፡-

☞. ጋብቻን ከሚከለክሉ ነገሮች ነፃ የሆኑ ተጋቢዎች

☞. ከሴቷ ወልይ በኩል “አጋብቻለሁ” ወይም መሰል የይሁንታ ቃል

☞. የአግቢው ወይም ወኪሉ “ተቀብያለሁ” ወይም መሰል የመስማማት ቃል

(ከአልፊቅሁል ሙየስሰር ኪታብ የተወሰደ ገፅ፡404-406)

በወንድም ኢብኑ ሙነወር

@yasin_nuru @yasin_nuru
👍8260👌4😍4🥰3👏3❤‍🔥2
#አንድ #ሀብታም ሰው ዘመናዊ መኪናውን አቁሞ ለጉዳዩ ገባ ይላል ጉዳዩን ጨርሶ ወደመኪናው ሲመለስ የአንዱ ጎማው 4 ብሎኖች ተፈተው ተወስዶበት ያያል ይህኔ ይበሳጭ😡😡 እና አከባቢው ላይ ዞር ዞር ብሎ ብሎን ፈልጎ ያጣል::

ያኔ መኪናውን ተደግፎ በጭንቀት ቆዝሞ ሰለ አከባቢው ላይ ያለ አንድ "# አእምሮ ህመምተኛ" ነገሩን ተከታትሎ ኖራል ምን ሆነህ ነው ይለዋል ሰውየውም በንቀት አይን አየት እያደረገ

" የጎማዬ ብሎኖች ተፈተው ተወስዶብኝ ነው እንዳልገዛ አከባቢው ላይ የለም " ይለዋል በብስጭት ስሜት🥺

ይህኔ " #የአእምሮ ህመምተኛው ነው እንዴ ታዲያ ለምን ከ3 ጎማዎች #አንድ አንድ ብሎን ፈተህ አራተኛውን ጎማ አታስርም "አለው::

👍ሰውየውም በመገረም ሀሳቡ በጣም አስደሰተው አንዳለውም አደረገ።

ግን " #የአይምሮ ህመምተኛው " ዘዴውን ነገሮት ሊሄድ ሲል

ሰውየው " ቆይ አንተ "እብድ "አይደለህ እንዴ አንዴት ይህ ሀሳብ ሊመጣልህ ቸለ ይለዋል "

" #አእምሮ ህመምተኛው" ቀበል አድርጎ
"ታዲያ እኔ " እብድ ነኝ እንጂ ደደብ አይደለሁም" ብሎ ይመልስለታል ፡፡

☞ዝቅ በል ዝቅ ስትል ከፍ ትላለህ ተናነስ ራስህን አትቆልል

☞ሁሌም እኔ አዋቂነኝ አትበል፡፡

☞ሰውን በአለባበሱ አንገምት።,

Islam & science

@yasin_nuru @yasin_nuru
163👍58💯10👏7🥰6🤝2
Forwarded from Mᴜᴀᴢ
ታዳጊ ህፃን ማሂር ሸረፈዲን እናድነው !!!!!!!

በቡራዮ አካባቢ የሚገኘው የታላቁ የሙአዝ ኢብኑ ጀበል መስጂድ ኢማማችን ልጅ በትቦ መጥበብ፣ የልብ ክፍተት እና የሳንባ ችግር የተገኘበት ታዳጊ ሲሆን እንደ ኢማምነት ማሳካት ከባድ ነውና ለመላው መሀበረሰብ ልጄን በማዳን ሰበብ እንድትሆ በአላህ ስም እጠይቃለሁ


ለበለጠ
መረጃ ፦
0911335486/0913753913
CBE፦1000029286958

🛑ሁላችንም ሼር በማድረግ ማህሮን እንታደግ
#1ሼር ትልቅ የሆነ ዋጋ አላትና ሼር በማድረግ የኡስታዛችንን እናግዝ‼️
94💔58👍26😢3😁1
#አምስት #የቀዝቃዛ #ሻወር ታምራዊ ጥቅሞች

ግሪኮች በአንደኛው ክፍለ ዘመን ለህዝብ አገልግሎት የሚውል የሙቅ ሻወር አገልግሎትን ፈጠሩ ነገር ግን በሚገርም ሁኔታ አብዛኛዎቹ ግሪካዊያን ካለው የጤና ጥቅም አንፃር ቀዝቃዛ ሻወርን ነበር የመረጡት፡፡
⭐️ ታምራዊ ጥቅሞቹ እነሆ፦

1⃣ ከስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በኋላ

ቶሎ እንድናገግም ያረዳል!
አትሌቶች ከባድ ልምምድ ካደረጉ በኋላ የሚያጋትማቸውን ድካምና ህመም ለመቀነስ በበረዶ ውሃ ሻወር ይወስዳሉ/ይዘፈዘፋሉ እኛ ግን ያን ያህል እርቀት መጓዝ አይጠበቅብንም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ ጥቅም ለማግኝት ከልምምድ በኋላ ቀዝቃዛ ሻወር መውሰድ ተገቢ ነው፡፡

2⃣. ስብን (ፋት) ለማቅለጥ!

ሁለት የስብ አይነቶች በሰውነታችን ውስጥ ይገኛሉ ነጭ ስብ እና ቡናማ ስብ። ነጩን ስብ እንደ መጥፎ ሰው እንቁጠረው ቡናማውን ደግሞ እንደ ጥሩ ሰው፡፡
ነጩ ስብ ሁላችንም የምናውቀው የሰውነታችን ስብ ሲሆን ሁላችንም ለማጥፋት የምታገለው ነው፡፡ ሰውነታችን ከሚፈልገው በላይ የሆነ ከፍተኛ ካሎሪ በምንወስድበት ጊዜ በሃይል(Energy) መልክ እንዲጠፋ ማድረግ ይሳነናል/ ያቅተናል በሃይል/ጉልበት መልክ ካልተወገደ/ካልጠፋ ግን ይህ ነጭ ስብ በታችኛው ጀርባችን፣ አንገት፣ ከዳሌ ከፍ ብሎ ባለው የመካከለኛው ሰውነት ክፍል እና ከጉልበታችን ከፍ ብሎ ባለው የእግር ክፍል ላይ ይከማቻል፡፡

☞በከባድ ቅዝቃዜ ወቅት እነዚህ ቡናማ ስቦች ይነሳሱና ካሎሪን በማቅለጥ የሰውነታችን ሙቀት እንዲጨምር ያደርጋሉ ይህም የሰውነት ክብደትን በመቀነስ ይረጋናል፡፡

3⃣. #የደም #ዝውውርና #በሽታን የመከላከል አቅምን ይጨምራል!

ስብን ለመቀነስ ቀዝቃዛ ሻወር እንዴት እንደሚረዳን ከላይ ተመልክተናል ሰውነታችን ስብን ለማቃጠል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የበሽታ መከላከያ ስርዓታችንን ያነሳሳል
☞ይህም ቫይረስን የሚዋጉነጭ የደም ሴሎች እንዲመረቱ ያደርጋቸዋል የእነዚህ ሴሎች መመረት በህመም የመጠቃት እድላችን
እንዲቀንስ ያደርገዋል፡፡
☞ቀዝቃዛ ሻወር አጠቃላይ የደም ዝውውርን ይጨምራል ይህም የደም ቧንቧዎች እንዳይጠነክሩ እና የደም ግፊት ያስወግዳል፡፡

4⃣. #የሚስብ #ፀጉር እና ቆዳ እንዲኖረን ያደርጋል!

☞በሰውነታችን ላይ ያለውን ብጉር ለመቀነስ ቀዝቃዛ ሻወር ከፍተኛ ድርሻ አለው። ሙቅ ውሃ ቆዳን ያደርቃል ቀዝቃዛ ውሃ ኩቲክልና ቀዳዳዎችን በመዝጋት በቆሻሻ
ከመደፈን ይከላከላል፡፡
☞ቀዝቃዛ ውሃ የሚያንፀባርቅና በጣም የሚስብ ፀጉር እንዲኖረን ያደርጋል፡፡ ቀዝቃዛ ውሃ ኩቲክሎችን በመዝጋት ቆሻሻ በራስ ቅላችን ላይ እንዳይከማች ይረዳል፡፡

5⃣ #ደስተኛ እና #ፈጣን እንድንሆን ያደርጋል!

ጠዋት ከአልጋ ላይ ሲወርዱ ደብርዎትና ተጫጭኖዎት የሚይነሳ ማነው? ይህ ሁሉም ሰው የሚያጋጥመው ነገር ይመስለኛል ነገር ግን ጠዋት ወደ ስራ ከመሄድዎ በፊት ገና ከአልጋዎ እንደወረዱ ቀዝቃዛ ሻወር ይውሰዱ፡፡

☞ቀዘቃዛ ውሃ በሰውነትዎ ላይ በሚፈስበት ጊዜ ለቅዝቃዜው ምላሽ በጥልቀት ይተነፍሳሉ(ይህ
ሰውነትዎ ኦክስጂን አወሳሰዳችን በመጨመር ሰውነታችን ራሱን ለማሞቅ የሚያደርገው ሙከራ ነው፡፡

☞የልብ ምትዎ ይጨምራል የዚህ ውጤት ደም በተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን እንዲዳረስ በማድረግ ጉልበት እንዲኖረን ያደርጋል፡፡

💐መልካም ጤንነት!!

@yasin_nuru @yasin_nuru
👍4839👏3🤝2
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ካነበብኳቸው አስቂኝ ነገሮች ላካፍላችሁ ይሉናል  #ሸይኽ_ሱለይማን_አር-ሩሃይሊ🥰🥰

አንድ ባለ ፂም ወጣት ከልጁ ጋር ቁጭ ብሎ ሳለ ህፃን ልጁ ማልቀስ ጀመረ

ከህፃን ልጁ አባት ጎን ሌላ ፂም የሌለው ወጣት መጣ🙃

ምንም ፂም የሌለው ፂሙን የሚላጭ ነው🥺

ይህ ፂም የሌለው ወጣት ህፃኑን እንደያዘው ወዲያው ህፃኑ ለቅሶውን አቆመና ፀጥ አለ🥰

ይህ ፂሙን የሚላጨው ወጣት ፂም ላለው ለልጁ አባት እንዲህ አለው:-

እናንተ ፂማችሁን የምታሳድጉ ሰዎች ህፃናትን ራሱ ታስፈራላችሁ🤔 ይህ ህፃን እኮ እያለቀሰ ነበር አለው😂

ባለ ፂሙ ወጣትም እንዲህ አለው፦

እናቱ መስለኸው ነው ዝም ያለው
አለው🥺🥺

ፂማችንን እያሳደገን🥰🥰

@yasin_nuru @yasin_nuru
🥰96😁5035🤣23👍14👏4
ከቂያማ ምልክቶች መካከል የተወሰኑት የሚከተሉት ናቸዉ

1⃣ ዝሙት ይስፋፋል
2⃣ ወንዶች ሀር ይለብሳሉ
3⃣ ሙዚቃ እንደሚፈቀድ ይነገራል
4⃣ ሴቶች ዘፋኞች በአጫዋችነት ይያዛሉ
5⃣መጥፎ ቃላቶችንመለዋወጥ ይበዛል
6⃣ዝምድናን መቁረጥ ይበረክታል
7⃣ታማኝ ሰዉን እንደ ከዳተኛ መቁጠር እና መወንጀል
8⃣ ከዳተኛን ማገዝ እና ማቅረብ
9⃣ድንገተኛ ሞት መከሰት
🔟 መስጅድን እንደ መተላለፊያ መንገድ መጠቀም
1⃣1⃣ ጥሪያቸዉ ወይም ተልእኮአቸዉ ተመሳሳይ የሆነ ሁለት ቡድኖች ይፋ ጦር ይማዘዛሉ (የአልይ ና የሙአዉያዉያንን ዉጊያን ያመለክታሉ
1⃣2⃣ የዘመን መቀራረብ ወይም የጊዜ መፍጠን (በረካ ማጣት)
1⃣3⃣ ፈተናዎች ይደራርሳሉ ፣ተንኮል ይስፋፋል
1⃣4⃣ ኢልም ከህፃናት ይፈለጋል
1⃣5⃣ የመሬት መንቀጥቀጥ
1⃣6⃣ ሰዉነታቸዉን አግባብ ባለዉ ልብስ ያልሸፈኑ ሴቶች ይበዛሉ
1⃣7⃣ እዉቀት የሌላቸዉ ሰዎች ህዝባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ይወስናሉ
1⃣8⃣ሰላምታ በትዉዉቅ ላይ ብቻ ይመሰረታል
1⃣9⃣ ዉሸት መናገር ይስፋፋል::
2⃣0⃣ የንግድ ቤቶች ተቀራርበዉ ይገነባሉ።
2⃣1⃣ ለሰይጣን አገልግሎት የሚዉሉ ግመሎች ና ለሰይጣን አገልግሎት የሚዉሉ ቤቶች ይገነባሉ። ማለትም 1 አንድ ሰዉ ከሚጠቀምባቸዉ ዉጭ ያሉ ግመሎች በስድ ሲለቀቁ ሰይጣን ይጋልባቸዋል። 2 ከመኖሪያ ቤት ዉጭ ያሉ ትርፍ ቤቶች ለረጅም ጊዜ ሰዉ ሳይገባባቸዉ ከቆዩ የሰይጣን መኖሪያ ይሆናል።

2⃣2⃣ ሰዎች በመስጊድ ዉበት ይፎካከራሉ_በዉስጡ ይመፃደቃሉ።
2⃣3⃣ ሺበታቸዉን በጥቁር ቀለም የሚያጠቁሩ ሰዎች ይመጣሉ። እነዚህ ሰዎች የጀነትን ሽታ እንኳን አያገኙም።
2⃣4⃣ ሰዎች አላህን የመታዘዝ ባህሪያቸዉ ይመነምናል።ለአኼራ መስራትም ይቀንሳል።
2⃣5⃣ ስስት ይስፋፋል፣ሁሉም ሰዉ ግለኛ ይሆናል፣አዋቂ እዉቀቱን ለማካፈል ይሳሳል።
2⃣6⃣ ሰዎች አላማዉን በማያዉቁት ዉጊያ ዉስጥ ይሳተፋሉ (ይጋደላሉ።)"ነፍሴ በእጁ በሆነዉ ጌታ እምላለሁ በሰዎች ላይ ይህ ዘመን ይመጣል።ገዳይ በምን ምክንያት እንደገደለ አያዉቅም-ተገዳይ በምን ምክንያት እንደተገደለ አያዉቅም።
2⃣7⃣ የህዝብ ገንዘብ ያለ አግባብ ይመዘበራል።
2⃣8⃣ አማና (ታማኝነት) ይጎአደላል።
2⃣9⃣ ባል ሚስቱን እየታዘዘ እናቱን ይበድላል።
3⃣0⃣ በአባቶች ላይ እየተፌዘ (አባት ሳይከበር) ጎአደኛ ይከበራል።
3⃣1⃣ በመስጅድ ዉስጥ ጩሀት ይበራከታል።
3⃣2⃣ ተንኮሉ ተፈርቶ ሰዉ ይከበራል-ችሎታና ስነ-ምግር ግን የለዉም።
3⃣3⃣ ፖሊስ ይበዛል፤ይህም ማለት ወንጀል መበራከቱን ያመለክታል።
3⃣4⃣ አንድ ሰዉ በእዉቀቱ አናሳ ሆኖ እና በባህሪዉም ገና ያልተገራ ሆኖ ሳለ ድምፁ የሚያምር ሆኖ በመገኘቱ ብቻ ሶላት እንዲመራ (እንዲያሰግድ) ይደረጋል።
3⃣5⃣ ሚስት ባሏን በንግድ እና በስራ ላይ ትጋራለች።
3⃣6⃣ ብእር ይበራከታል፤ድርሰት እና ህትመት ይስፋፋል።
3⃣7⃣ ልጅ መመኪያ መሆኑ ቀርቶ መተከዣ እና መቆጫ ይሆናል።
3⃣8⃣ የዝናብ እጥረት ይስተዋላል።
3⃣9⃣ መኪና ይፈለሰፋል። "ከኡመቶቼ መካከል ወደመጨረሻዉ የሚመጡት 'ሱሩጅ ወይም (መኪና) ላይ ይሳፈራሉ። የመጎጎዣ አይነት ነዉ በመስጅድ በሮች ያቆሙታል (ይወርዳሉ) ሴቶቻቸዉ ግን የለባሽ እርቃን ናቸዉ።
4⃣0⃣ ፊትና በመብዛቱ ሳቢያ ሞትን መመኘት።
4⃣1⃣ ኢራቅ ማእቀብ ይጣልባታል-ምግብናእርዳታ ትከለከላለች።
4⃣2⃣ በመቀጠልም ሻም (ሶሪያ፣ሊባኖስ፣ዩርዳኖስ እና ፍልስጤም) ምግብና እርዳታ ይከለከላሉ ማእቀብ ይጣልባቸዋል።
4⃣3⃣ የነብዩ ሙሀመድ (ሶ.አ.ወ) ከዚህ አለም በሞት መለየት እንደ አንድ የቂያማ
ቀንመድረስ ምልክት ተወስዷል።
4⃣4⃣ በይተል መቅደስ (እየሩሳሌም) በሙስሊሞች ቁጥጥር ስር መግባት።
4⃣5⃣ በጅምላ ጨራሽ በሽታም ሆነ ጦርነት የሰዉ ህይወት መጥፋት።
4⃣6⃣ ሙስና፣ማጭበርበር እናየ ዋጋ ንረት እያየለ መምጣት።
4⃣7⃣ በአረቦችም ሆነ በሌሎች ወገኖች ቤት ዉስጥ ጣልቃ ገብነት እና ፊትና (መከራ) ይስተዋላል።
4⃣8⃣ በሙስሊሞች እና በሮማዉያን(አዉሮፓ እና አሜሪካ) የጋራ ስምምነት ይፈረማል።

አዉፍ ኢብን ማሊክ (ረ.አ) እንዳስተላለፉት የአላህ መልእክተኛ (ሶ.አ.ወ) እንዲህ ብለዋል፦ የቂያማ ቀን ከመድረሱ በፊት ስድስት ነገሮች ይከሰታሉ፥

1 የኔሞት።
2 ከዚያም በይተል መቅዲስ ይከፈታል።
3 ከዚያም ሁለት ሞት እዉን ይሆናል።
4 አንድ ሰዉ መቶ ዲናር ቢሰጠዉ እንኳን ምንም አይመስለዉም።
5 ከዚያ በሁላ ደግሞ ፊትና ይከሰታል።
6 ከዚያም በናንተና በነጮች መካከል ስምምነት ይኖራል። ይከዷችሁል ። 80 አላማ ይዘዉ ይመጣሉ እያንዳንዱ አላማ ደግሞ 12 ሺህ (ንኡስ አላማ) አለዉ።

#copied

@yasin_nuru @yasin_nuru
85😢53😭24💔8👌4😍2🔥1🥰1
#የዝንጅብል__ሻይ - 10 የጤና በረከቶች

📌 ከራስ ህመም/ማዞር/ ይገላግልዎታል፡፡

📌 በወር አበባ ጊዜ የሚከሰት ቁርጠትን ይቀንሳል፡፡

📌 የትልቅ አንጀት ካንሰርን ይከላከላል፡፡

📌 በመኪና ሲጓዙ ለሚያስመልሳቸው ሰዎች በጣም ጠቃሚ ነው።

📌 በስኳር በሽታ ምክንያት የሚመጣን የኩላሊት ህመም/ጉዳትን ይከላከላል፡፡

📌. በቃር ለሚሰቃዩ ፍቱን ነው፡፡

📌 ህመምና ኢንፍላሜሽን (የሰውነት መቆጣትን) እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

📌. ጠዋት ጠዋት ለሚከሰቱ ህመሞች ፍቱን ነው፡፡

📌. ለጉንፋን እና ፍሉ ህመሞች በጣም ጠቃሚ ነው፡፡

📌. የእንቁላል ከረጢት ካንሰርን ይከላከላል፡፡

⚂አሁኑኑ ለሚወዱት ሼር ያድርጉት፣ እርስዎም ይሞክሩት፡፡

ምንጭ ዶ/ር⇄ ኑርሁሴን አህመድ

@yasin_nuru @yasin_nuru
👍9655👏7🥰3
የጥሩ ሚስት መገለጫዎች

① የትም ብትሆን አላህን ትፈራለች፣ በሁሉም ነገር የነቢዩን ሱና ትከተላለች

②ባሏ ያዘዛትን በሙሉ -ከዲን ጋር የሚጋጭ እስካልሆነ ድረስ- ትታዘዛለች

③ከሷ ጥሩን ነገር እንጂ እንዳያይ፣ እንዳይሰማና እንዳያሸት ጥረት ታደርጋለች

④ቤትና ንብረቱን እንዲሁም ቤተ-ሰቦቹን ትጠብቃለች

⑤እሱ የማይፈልገውን ሰው አትጠጋም አታስጠጋምም

⑥ ባሏን ሳታሳውቅ ሱና ጾም አትጾምም
ከቤትም አትወጣም

⑦ የባሏንና የቤቷን ሚስጥር በሚገባ ትጠብቃለች

⑧ ባሏን በመልካም ነገር ላይ ታግዛለች ሲሰንፍ ታበረታታዋለች፣ ሲረሳ ታስታውሳለች

⑨ሐላል ከስብ እንዲከስብ ሐራምን እንዲርቅ ዘወትር ትገፋፋዋለች፣ለእሷና ለቤቱ ብሎ ዲኑ የማይፈቅደውን ስራ እንዳይሰራም ታሳስበዋለች

①∅ ደስታና ሃዘኑን ትጋራለች፥ እርሱ ሐሳብና ጭንቀት ውስጥ ሆኖም እሷ አትስቅም፣ እሱ ማረፍና መደሰት በሚፈልግበት ወቅት ላይም እሷ በተቃራኒው ተከፍታ አታስከፋውም

①①በሚያደርግላት ነገር በሙሉ ይብዛም ይነስ ታመሰግነዋለች

①② ቤቷን እያቀዘቀች የሰው ቤት አታሞቅም ቤቷንም እያፈረሰች የሰው ቤት አትገነባም!

①③ አላህ የሰጣትን ልጆች በኢስላም ስርዓት ቀርጻ ታሳድጋለች ትልቁ የእሷ ስራም ይህ እንደሆነ በማወቅ በስራዋ ትኮራለች! ልጅም ያጣች እንደሆነ ታግሳ ተስፋ ሳትቆርጥ ጌታዋን ትለምናለች።

"ሁላችንም አላህ ሳሊሖች ያድርገን"

@yasin_nuru @yasin_nuru
125👍26🥰16😭5😘3🔥1👏1💯1🤗1
°•የጁምዓ ቀን ሱናዎች•°

1 ገላን መታጠብ።

2. ሽቶን መቀባባት (ለወንድ) እና መዋብ።

3. ሲዋክን መጠቀም።

4. የክት ልብስ መልበስ።

5. በጊዜ መስጂድ መጓዝ።

6. በእግር እየተጓዙ ወደ መስጅድ መሄድ።

7. መስጂድ ከደረሱ በኋላ የሰዎችን ትከሻ በመረማመድ ሰዉን አለማስቸገር።

8. ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ተህየቱ መስጂድ መስገድ።

9. ኹጥባ ወደ የሚያደርገው ኢማም መዞርና እሱን እያዩ ኹጥባ ማድመጥ።

10. ኹጥባ በሚደረግበት ሰዓት ፀጥታን መላበስ።

11. ሰደቃን ማብዛት።

12. ከሀሙስ ዐስር  ጀምሮ እሰከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱ ከሕፍ መቅራት።

13. ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሰዓትን መጠባበቅ።

14. በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን በብዛት ማውረድ።
    
      ፏ ያለ ጁምዐ ይሁንላችሁ

@yasin_nuru @yasin_nuru
140👍39🥰11🤗5
ሸይኽ ረቢዕ ቢን ሃዲ አል-መድኸሊይ ወደ አኺራህ ሄደዋል። አላህ ይዘንላቸው። ለመላው ሙስሊምና ቤተሰቦቻቸው አላህ ሶብሩን ይስጥ።

ሸይኽ ታላቅ የጀርህና ተዕዲል ቀንዲል ነበሩ። አላህ ይማራቸው! ወንጀላቸውን ይማርላቸው፣ መልካም ሥራቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎ ይቀበላቸው።

@yasin_nuru
👍83😢3730😭17💔14😁2
አንድ ታሪክ

ሁለት ጓደኛሞች በጫካ ዉስጥ ሲጓዙ ድብ ያገኛሉ። አንደኛው በፍጥነት ዛፍ ላይ ለመውጣት ሲችል ሌላኛው ግን እንደዚያ ለማድረግ ባለመቻሉ መሬት ላይ የሞተ በመምሰል ይተኛል።

ድቡ ጆሮዉ ስር ያሸተዉና ትቶት ይሄዳል በዚህ ጊዜ ዛፍ ላይ የወጣው ሰው ወደመሬት ይወርድና <<ድቡ ምን አለህ?>> ብሎ ሲጠይቀው እሱም <<በአደጋ ጊዜ ትቶህ የሚሄድ ጓደኛ እንዳታምን ብሎ ነገረኝ!
>> ይለዋል።

🎖"በመከራ ጊዜም ቢሆን ታማኝ ጓደኛ በመሆን መልካም ስብእናችንን እንገንባ!"

☞አንድ ቀን ይመጣል አንተ ራስህ የለበስከውን ልብስ ሰዎች አገላብጠው የሚያወልቁልህ ቀን

☞የተከፈተ አፍ እና አይንህን ሰዎች የሚዘጉልህ ቀን

☞ተራምደህ ከሄድክበት ቦታ ሰዎች: ተሸክመው የሚያስወጡህ ቀን

☞ ቤተሰብሽን እንኳን ታፍሪ የነበርሽው በሰው እጅ ገላሽ የሚታጠብበት ቀን

☞ጌጣጌጥሽ ሁሉ ከላይሽ ላይ ወልቆ ሌላ ሰው የሚወርስበት ቀን

ይህ ቀን ሳይመጣ በፊት በመልካም ስራ ልይ እንትጋ

@yasin_nuru @yasin_nuru
👍8938👏5💯5🔥2
2025/07/12 16:56:01
Back to Top
HTML Embed Code: