Telegram Web Link
⚠️🚫ለዘፈን_አፍቃሪያን_መገሠጫ_ትሆን_ዘንዳ_ይህችን_ታሪክ_አንብቧት 👇👇👇

*ልጁ በጣም ሙዚቃ ማዳመጥ ይወዳል። ጠዋት፣ ማታ፣ቀን፣ለሊት፣ሁልም ጆሮው ላይ ኤርፎን ሰክቶ፣ አላህ ለቁርአን፣እንዲሁም ለተግሰጽ የለገሰውን ጆሮ ለሃራም እናለማይወደው ድርጊት ይጠቀማል።

ታድያ ከዕለታት አንድ ቀን ት/ቱን ጨርሶ፣ ቤት ይገባል። ልቡ የሚገኘው ዛሬ ምን አይነት ዘፈን አውርጄ ላዳምጥ ነው ። ከዚያም ፍራሹ ላይ ጋደም ብሎ፣ ሞባይሉን ከፍቶ፣በማዳመጥ ላይ ሳለ የክፍሉ መብራት ድንገት በኃይል ድርግም ብሎ ይጠፋል ።

ደንግጦ የሞባይሉን ፍላሽ በማብራት፣ ኤርፎኑን ለመንቀል ቢሞክር እንቢ ይለዋል። ከጆሮው ውስጥ የተጣበቀው ኤርፎን፣አልነቀልም ብሎ ብዙ አታገለው። በመጨረሻም ስላልቻለ ለቤተሰቡ ተናገረ።

ቤተሰቡ ሙዚቃ በማዳመጡ ቢናደዱም፣አሁን ለችግሩ መፍትሔ እንፈልግ በማለት በፍጥነት ወደ አቅራቢያው ከአንገት በላይ እስፔሽላይስት ህክምና ወሰዱት።

ዶክቶሮች በድንጋጤ እንዲሁም በመገረም እንዲህ አይነት ሁኔታ አጋጥሟቸው እንደማያውቁና ከአቅም በላይ ስለሆነባቸው ወደ ሌላ የሕክምና ማዕከል ሪፈር ይጽፋለታል። ቤተሰብ በጣም ተጨንቋል።

ልጁ ምንም አያወራም፣ ዝምታን ተከናንቦ አይኑን ያቁለጨልጫል።በአብዋራ የተሞላ ፀጉሩን እያከከ በዙሪያው ያሉ ሰዎች የሚያወሩትን ለማዳመጥ ይሞክራል።

ነገር ግን ምንም ነገር አይሰማውም። ጆሮው ደን ቁሯል። አላህ የሰጠውን ጆሮ ቁርአንን ለማዳመጥ ሳይጠቀም ሙዚቃ አዳምጦበታል። በዚህም የፀፀተው ይመስላል።

ወደ ሌላ ሕክምና ማዕከል ተጉዘው ከከባድ የ 2፡00ሠዓት ቀዶ ጥገና ሕክምና በኃላ ኤርፎኑ ለብቻው መወገድ ስላልቻለ ሁለቱ ጆሮዎች፣ከቦታቸው ተነቅለው የማዳመጥ ፀጋን አሳጥቶት ከሕክምና ማዕከሉ ወደ ቤት ተመለሰ። ከዚያ በኃላም ጤና እያለው ያልቀራውን ቁርአን ለማንበብ ይታገላል። ሕይወቱንም በፀፀት እና በማልቀስ ለመግፋት ተገዷል።


ኢኽዋኒ ወ አኽዋቲ አላህ የሰጠንን ፀጋ እሱን ለማመስገን እንጂ፣እሱን ለማስቆጣት አንጠቀመው። ሙዚቃን ከመስማት ርቀው፣ ቁርአንን በማዳመጥ ከሚረኩት ያድርገን!!!
አላሁመ አሚን!

    በተቻለን አቅም ለሌሎች በማድረስ ከሀራም ነገራቶች እንዲርቁ  ሰበብ  እንሁናቸው ።

@yasin_nuru @yasin_nuru
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ዓረባዊያን ቢክዱም🥺🥺

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ከጽዮናውያን እና ከአሜሪካዊያን ጋር ቢተባበሩም🤷‍♂🤷‍♂

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
አብሽሪ ከአላህ ሰራዊት ጋር💪💪
ሆነን እንመጣልሻለን🔥🔥

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ከአይሁድም ነፃ ትወጪያለሽ🥺🥰

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
መስዋእት እንሆንልሻለን💪💪

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
ድንበሩም ይፈርሳል🦁🦁

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸
የዓለም ሙስሊሞችም አንድ ይሆናሉ 🤝🤝

🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸🇵🇸

@yasin_nuru    @yasin_nuru
📌 የዱዓችን ተቀባይነት ማጣት ምክንያቱ ምን ይሆን?

ﻣﺮ ﺇﺑﺮﺍﻫﻴﻢ ﺑﻦ ﺃﺩﻫﻢ ﺭﺣﻤﻪ ﺍللّٰه تعالى ﺑﺴﻮﻕ ﺍﻟﺒﺼﺮﺓ ؛ ﻓﺎﺟﺘﻤﻊ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺇﻟﻴﻪ، ﻭﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻳﺎ ﺃﺑﺎ ﺇﺳﺤﺎﻕ: ﻣﺎ ﻟﻨﺎ ﻧﺪﻋﻮﺍ ﻓﻼ ﻳُﺴﺘﺠﺎﺏ ﻟﻨﺎ؟

ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም (رحمه الله) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦ ያ አባ ኢስሃቅ ዱዓእ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ?

ﻗﺎﻝ: لإﻥ ﻗﻠﻮﺑﻜﻢ ﻣﺎﺗﺖ ﺑﻌﺸﺮﺓ ﺃﺷﻴﺎﺀ!.

እሳቸውም፦ ቀልባችሁ (ልባችሁ) በአስር ነገሮች ሞታለች አሏቸው።

ﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻭﻣﺎ ﻫﻲ؟ ﻗﺎﻝ:

እነሱም፦ ምን ምንድ ናቸው? ብለው ጠየቋቸው።
እሳቸውም፦

ﺃﻧﻜﻢ ﻋﺮﻓﺘﻢ ﺍللّٰه؛ ﻓﻠﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺣﻘّﻪ.
‏አንደኛ፡ አላህን አውቃቹት።ሐቁን አልተወጣችሁም።

‏ ‏ﺯﻋﻤﺘﻢ ﺃﻧﻜﻢ ﺗﺤﺒّﻮﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠّٰﻪ (ﷺ) ﺛﻢ ﺗﺮﻛﺘﻢ ﺳﻨّﺘﻪ.
‏ሁለተኛ፡ ነቢዩን (ﷺ) እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ፤  ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።

‏ ‏ﻗﺮﺃﺗﻢ ﺍﻟﻘﺮﺁﻥ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﺑﻪ.
‏ሶስተኛ፡ ቁርኣንን አነበባችሁት አልሰራችበትም።

‏ ‏ﺃﻛﻠﺘﻢ ﻧﻌﻤﺔ الله، ﻭﻟﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺷﻜﺮﻫﺎ.
‏አራተኛ፡ የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።

‏ ‏ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥّ ﺍﻟﺸﻴﻄﺎﻥ ﻋﺪﻭّﻛﻢ، ﻭﻭﺍﻓﻘﺘﻤﻮﻩ.
‏አምስተኛ፡ ሸይጣን ጠላታችነው ብላችሁ ከሱ ጋር ገጠማቹ።

‌‏ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﺠﻨّﺔ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﻟﻬﺎ.
‏ስድስተኛ፡ ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ የሚሆን ስራ አልሰራችሁም።

‏ ‏ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻨّﺎﺭ ﺣﻖ، ﻭﻟﻢ ﺗﻬﺮﺑﻮﺍ ﻣﻨﻬﺎ.
‏ሰባተኛ፡ የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።

‏ ‏ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻤﻮﺕ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﺴﺘﻌﺪّﻭﺍ ﻟﻪ.
‏ስምንተኛ፡ ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።

‏ ‏ﺍﻧﺘﺒﻬﺘﻢ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﻮﻡ، ﻭﺍﺷﺘﻐﻠﺘﻢ ﺑﻌﻴﻮﺏ ﺍﻟﻨﺎﺱ، ﻭﺗﺮﻛﺘﻢ ﻋﻴﻮﺑﻜﻢ.
‏ዘጠነኛ፡ ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፤ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።

‏ ‏ﺩﻓﻨﺘﻢ ﻣﻮﺗﺎﻛﻢ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﺘﺒﺮﻭﺍ ﺑﻬﻢ
‏አስር፡ ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።

📙 ጃሚዑል በያን ዓልዒልም ወፈድሊህ፡ 2/12

@yasin_nuru     @yasin_nuru
በዚህ መንግስት ብዙ ትልልቅ ነገሮች ተደርገውልናል እና ጥፋት ሲያጠፋ ዝም ማለት አይገባም።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ሰው ሸይኽ ዑሰይሚንን {ረሂመሁላህ} እንዲህ ሲል ጥያቄ አቀረበላቸው።

➻ሁለተኛ የምጨምራት ሴት ሀራም ላይ እንዳትወድቅ ስለፈራሁላት ላገባ ነው ምን ይመክሩኛል?

➻እሳቸውም ፦" ለሁለተኛዋ ለማግባት የመደብከውን ገንዘብ ትዳር ለሌለው ወንድምህ ስጠውና እሱ ያግባት:: የሁሉቱንም አጅር ታገኛለህ::" በማለት መለሱለት።
   
  አልፈታዋ 6/241
👍ለሌሎች ሼር ማድረጎን አይዘንጉ

@yasin_nuru    @yasin_nuru
  🚗መኪናና ሞባይል📲

💨ድሮ ሾፌሮች ሞባይሎቻቸውን በተደጋጋሚ መኪና ውስጥ እየረሱ ይወረዱ ነበር፣ አንዳንዴም አናግረውበት ታፋቸው ላይ ጣል እንዳደረጉት መጨረሻ ላይ መኪና አቁመው ሲወርዱ ታፋቸው ላይ የተረሳው ስልካቸው ቀድሟቸው መሬት በመድረስ ይሰባበር ወይም ይወላልቅ ነበር፣

👌ዛሬ ግን ከመሪው ይልቅ በእጃቸው ሞባይሎቻቸውን በመያዝ ለአደጋ ሰበብ የሚሆኑ በዝተዋል  በሞባይላቸው በመጠመድ ሞተር ሳያጠፉ ረስተው የሚወርዱም አይጠፉም

🔑ወንድሜ ሆይ ስማ፦ በዘመኑ ዓለም ላይ እየበዛ ከመጣው የትራፊክ አደጋ ዋና ዋና ምክንያቶች መሀል አንዱ ሞባይል ነው

አንድን ነፍስ  የራሱንም ቢሆን- ያለ አግባብ ያጠፋ ሰው ምድር ላይ ያሉ ሰዎችን በሙሉ ህይወት እንዳጠፋ ይቆጠራል አላህ ዘንድም ይጠየቃል

ህይወቶች እንዲጠፉ ሰበብ የሆነም ሰው ወንጀሉ ተመሳሳይ ነው::

@yasin_nuru @yasin_nuru
ትዳር ትልቅ ሀላፊነት መወጣትን ጥንቃቄን ብርታትን ብልሃተኝነትን የሚጠይቅ ትልቅ ተቋም ነው።

ለትዳር ለባል ዝቅ ማለት ውርደት አይደለም
ባለው የገቢ ምንጭ የሚያስፈልገውን
በመመዝገብ የሚቀድሙትንና ሊዘገዩ የሚችሉትን ለይቶ በማውጣት በሰላም መኖር ይቻላል።

ሚስት ሆይ ጓደኞችሽ የሚኖሩትን ኑሮ ሳይሆን
ቤትሽን ተመልከች ምን አልባት ጓደኞችሽ ብዙ
የሚያማምሩ ልብስና ጫማ ይኖራቸው ይሆናል።

ደስ ይላል ነገር ግን አንች እና ባለቤትሽ እጅ ኑሯችሁን የምትኖሩት ጓደኞችሽ አይደሉም ስለዚህ ባለሽ በሚያቀርብልሽ ነገር አመስግኝው።

ይሄንን በማረግሽ በቤትሽ ሰላም በረከት ይሞላል ባልም ውጭ የምታያቸውን ያማሩ ሴቶች ከሚስትህ ጋር አታወዳድር ዝቅ ያለችው ለአንተ ፍቅርና ለቤትህ ማማር ለጓዳችሁ መሙላት ነውና።

መፋቀር መከባበር መተሳሰብን አዳብሩ ባል ለሚስትህ ሰላም እና ደስታ አስብላት ሚስትም እንደዚያው ትዳር ማለት አንዱ አንዱን የሚደግፍበት ነውና በመተሳሰብ ኑሩ።

@yasin_nuru @yasin_nuru
ለጥንቃቄ

ከዚህ ቡሃላ በመዲናችን አዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ሲሸና የተገኘ ግለሰብ 2000 ብር እንደሚቀጣ ተገልጿል።

ዛሬ ሲሸኑ ከተያዙ 50 ግለሰቦች የኢትዮጵያ ደንብ ማስከበር ባለሰልጣን +100ሺ ብር ከቅጣት ማግኙትን ይፋ አድርጓል።

ሙስሊምን ይመለከተዋል እንዴ ይሄ ዜና ጀምዓው?😂😂

@yasin_nuru @yasin_nuru
ዚክርና  ጥቅሞቹ
🕯አላህን ማሥታወሥ ያለዉ ጥቅም እና ትሩፋት

🔸አላህን ማሥታወሥ ነፍሥያ እና ሸይጧን ላይ ድል የመቀዳጃ ትልቅ በር ነው

🔹 ወደ አላህ ሡብሀነ ወተዓላ መዳረሻ መንገድ ነው

🔸 አላህ ሡብሀነ ወተዓላ የዚክርን በር የከፈተለት ሰው የሁሉንም የኸይር በሮች አግኝቷል

  🔹የዚክር በር የተዘጋበት ሰው የኸይር በሮች ተዘግተውበታል

  🔸ዚክርን አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ያገራለት ሠው ዒባዳዎች ሁሉ ይገሩለታል 

   🔹ዚክር የከበደውና  ከዚክር የሠነፈ   ሰው ከዒባዳዎችም ይሠንፋል

🔸 ዚክር ማብዛት ሸይጧንን ከሰው ልጆች ያርቃል

🔹ዚክር አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ያሥደሥታል፣የአዱንያን ጭንቀት ያሥወግዳል

🔸በልብ ውሥጥ ደሥታን ይፈጥራል፣የደረቁ ቀልቦችን ያረጥባል

🔹ወንጀሎችን ያራግፋል የብቸኝነትን ስሜት ያሥወግዳል ከአላህ ሡብሀነሁ ወተዓላ ቅጣትም ይጠብቃል

🔸 ዚክር የሚያበዛ ሠው ከሙናፊቅነት ይድናል

🔹የቂያማ ቀን ከመፀፀት እና ከመቆጨትም  ያድናል

   🔸ጀነት ላይ የሰው ልጆች  አትክልት እና ፍራፍሬ የሚያገኙትም በአዱንያ በሚያደርጉት ዚክር ልክ ነው፡፡

   🔹የህሊናን እረፍት  ይሠጣል

🔸ዚክር የሚል ሰው ላይ የአላህ ራህመት ይወርድበታል፣ መላኢኮች ዙሪያውን ይከቡታል

🔹 በአዱኒያ ዚክር ለሚያበዛ ሰው አላህ ግንባሩ ላይ ኑርን ይሠጠዋል፣ ቀብር ውስጥም  አላህ ብርሃንን ይፈጥርለታል፡፡

🔸የቂያማ ቀንም በአዱኒያ ያደርገው የነበረው ዚክር ሲራጥን በሠላም እንዲሻገር ያደርገዋል፣ ፊቱም ያበራል፡፡ለዚህም ነው አላህ ሡብሀነሁ  ወተዓላ የሠው ልጆች ዚክርን እንዲያበዙ በተለያዩ የቁርኣን አያዎች (አንቀፆች) ያዘዛቸው፣ ረሡልም  ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም በብዙ ሀዲሶች ዚክርን ማብዛት እንዳለብን ገልፀዋል፣ ዚክር የሚያበዙ ሰዎች የሚያገኙትን ትሩፋትም ጠቅሠዋል፣
🚩አላህ ሡብሀነ ወተዓላ በቁርኣኑ
يَا أَيُّهَا الَّذَ آمَنُوا اذْكُرُوا اللَّهَ ذِكْرًا كَثِيرًا
وَسَبِّحُوهُ بُكْرَةً وَأَصِيلًا
(ሡረቱል አህዛብ፡41-42)

  [  "እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ :—አላህን ሡብሀነሁ ወተዓላ ብዙ ማሥታወሥን አሥታውሡት ጠዋትና ማታም አጥሩት"] ይላል

🚩በሌላውም የቁርአን አያ የሡን ትክክለኛ ባሮችን መገለጫ ሢገልፅ እነዚያ ያመኑ አላህን በማሥታወሣቸው ልባቸዉ ይረጋጋል የሠው ልጆች ሆይ አላህን በማሥታወሥ የልብ ሠላም እና እርጋታ ይገኛል፡፡ብሏል ፣

🚩በሌላኛው የቁርኣን አያም "አሥታውሡኝ አሥታውሣችኋለሁ "ብሏል፡፡

ሐጅ ሥርአት ላይ ዒባዳችሁን ሥትጨርሡ አላህ ሡብሀነ ወተአላን አሥታውሡ ቤተሠቦቻችሁን እና ዘመዶቻችሁን ከምታሥታውሡት የበለጠ ይላል "
"አላህን ሡብሀነ ወተዓላ በብዛት አሥታውሡት ፣እነሆ ይህን ያደረጋችሁ እንደሆነ ትድናላችሁ" ይላል

🔸በተለያዩ የቁርኣን አያዎች ላይ የዚክርን ጥቅሞች አላህ ገልጿል።

📎ዐብዱሏህ ኢብኑ ዐባስ ረዲየሏሁ ዐንሁ የሚከተለውን ብለዋል("አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ባሮቹ ላይ ማንኛውንም አይነት ዒባዳ አልደነገገም ዒባዳው በግልፅ በውል የሚታወቅ ገደብና መጠን ቢያደርግለት እንጂ!" )

ይህን ዒባዳ የታዘዙ እና የተደነገገላቸው ሰዎችን ኡዝር ባላቸው ሠአት ይህን ዒባዳ ቢተውት ምንም ችግር የለውም ብሎም ቢያሣውቅ እንጂ ፡፡ ዚክር ሢቀር 👌

📌ዚክርን በተመለከተ ይሄን ያህል ብቻ ዚክር አድርጉ ብሎ አላህ አልገደበውም ፣እንዲሁ ዚክርን መተውም አላህ ሡብሀነ ወተዓላ ለማንም አልፈቀደም ለመተዉም ኡዝር አልሰጠም። አእምሮውን የሣተ፣ ራሡን መቆጣጠር ያቃተው ሰው ካልሆነ በሥተቀር ዚክርን ለመተው አላህ ለማንም ኡዝር አልሠጠም፡፡

እንዲሁም  ዚክርንም በዚህ ሠአት በሉ ብሎ አላህ አልገደባቸውም፡፡በጊዜ የተገደቡ ዚክሮች ቢኖሩም በዛ ወቅት እነዚህ ዚክሮች መባል አለባቸው በዚህ ሠአት ቢባሉ ይመረጣል ፣በማለት ነብያችን ሠለላሁ አለይሂ ወሠለም የተናገሩት ካልሆነ በስተቀር! እንጂ ከዚህ ሠአት ውጭ አላህን ማሥታወሥ አይቻልም ማለት አይደለም፡፡

ቆማችሁም፣ተቀምጣችሁም ተኝታችሁም አላህን አሥታውሡ፡፡ቀንም ሌሊትም ባህርም ውስጥ የብሥም ላይ አላህን አሥታውሡ፣ ሀገርም ላይ ይሁን መንገድ ላይ ፣በድንጋጤና በሀዘንም ሆነ በደሥታ  ጊዜ በህመምም ሆነ በጤንነት ጊዜ አላህን አሥታውሡ! በገሀድም በሚሥጥርም በየትኛውም ሁኔታ ላይ ብትሆኑ አላህን አሥታውሡት!

ኡስታዝ አህመድ ኣደም
20/12/1437 ዓ.ሂ

@yasin_nuru @yasin_nuru
1⃣ ሱብሂ፥ ፈርዱ 2 "ረካ" ነው
ሱናው ከፊት 2 "ረካ" ይሰገዳል
🔸ከኋላ የለውም አይሰገደም

2⃣ ዝሁር ፈርዱ 4 "ረካ" ነው
ሱና ከፊት 4 ከኋላ 4 መስገድ ይቻላል

3⃣ አስር ፈርዱ 4 "ረካ" ነው
ሱና ከፊት አራት "ረካ" መስገድ ይቻላል
🔸ከኋላ የለውም አይሰገድም

4⃣ መጝሪብ ፈርዱ 3 "ረካ" ነው
ሱና ከፊት ከፈለጉ- 2 "ረካ" መስገድ ይቻላል
ከኋላ 2 "ረካ" ይሰገዳል

5⃣ ዒሻ ፈርዱ 4 "ረካ" ነው
ሱና ከፊት ከፈለጉ- 2 "ረካ" መስገድ ይቻላል ከኋላ 2 ረካ ይሰገዳል

☞ ጥብቅ ማሳሰቢያ ከአስርና ከሱብሂ ፈርድ ሰላት በኋላ ሱና ሰላት አይሰገድም!

@yasin_nuru @yasin_nuru
《8ቱ ሰላትን የሚያበላሹ ነገሮች》

🔸1/ ሆን ብሎ ከሰላት ጋር ግንኙነት የሌለውን ንግግር መናገር ሁለት ፊደል እንኳ ቢሆን

🔹2/ጠሃራና ውዱዕን የሚያፈርስ ነገር መከሰት

🔸3/መሳቅ

🔹4/ሰላት ሲሰገድ መሸፈን ያለበት የሰውነት አካል መገለጥ
📌(እዚህ ጋር ☞ልብ መባል ያለበት ነገር  ብዙ ሱሪና ሸሚዝ ወዘተ መሰል ነገሮችን ለብሰው የሚሰግዱ ሰዎች ጥንቃቄ ካላደረጉና ቲሸርት (ሸሚዛቸውን) ከሱሪያቸው  ወይም ከሽርጣቸው ስር በደንብ አስገብተው ቀበቷቸውን አጥብቀው ካላሰሩ ሱጁድና ሩኩዕ ሲያደርጉ ወገባቸው ከታች ይገለጣል በዚህም ሰላታቸው ይበላሻል!)

🔹5/ቂብላን ለቆ ሙሉ በሙሉ ወደ ኋላ መዞር እንዲሁም ወደ ቀኝና ግራ አብዛኛውን የሰውነት አካል በጣም ማዞር

🔸6/ መብላት

🔹7/ መጠጣት

🔸8/ሰላት ውስጥ ሆኖ ሰላት ከሚሰግድ ሰው የማይጠበቅን ነገር በተከታታይ እየፈጸሙ መጫወት፡፡

🔘ማሳሰቢያ፦
1/ እነዚህን ነገሮች ረስቶ ወይም ባለማወቅ ወይም ሌላ ሰው በቁም ነገር አስፈራርቶና  አስገድዶት ከሆነ ያደረገው ሰላቱ አይበላሽም!

2/ ሴት ልጅ እየሰገደች:ـክንዷ ወይም እግሯ ወይም አንገቷና ትንሸም ቢሆን ፀጉሯ የታየና የተገለጠ እንደሆነ ሰላቷ ይበላሻል

🔸የምትሰግደው አጅነቢይ ያለበት ቦታ ላይ ከሆነም ፊቷንም ሙሉ መሸፈን ይጠበቅባታል።

ወላሁ አዕለም

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

 @yasin_nuru @yasin_nuru
የታመመ ባሏን በጀርባዋ የተሸከመችው ድንቅ ሴት...የ32 አመቷ ሂባ የ3 ልጆች እናት ናት ከ6 አመታት በፊት ቧሏ በተደራረበበት በሽታ እግሮቹ መንቃሳቀስ ይሳናቸዋል በየቀኑ ሆስፒታል መሄድና ህክምናውን መከታተል ነበረበት።

ታዲያ ይህች ድንቅ ሴት ፍታኝ አላለችም ወይም ጥላው አልሄደችም አብሽር እኔ አለውልህ ብላ በሴት አቅሟ ባሏን ጀርባዋ ላይ አዝላ በየቀኑ ወደ ሆስፒታል ታመላልሳለች።

በኔ እንዳታፍር ልፍታሽ ብያት ነበር እሷ ግን አልተቀበለችኝም። ሚስቴ ለኔ ልዩ ሴት ናት እናቴ በሆዷ 9 ወር ሚስቴ ደሞ ለ6 አመት በጀርባዋ ተሽክማኛለች ይላል። እሷም በበኩሏ እስክሞት ድረስ እሸከመዋለሁ ትላለች ።

ምን አይነት ድንቅ ፍቅር ነው

(MP Ethiopia)

@yasin_nuru @yasin_nuru
#ጀናባን_የሚመለከቱ_ህግና_ደንቦች

#አንብባችሁ_ለወንድሞቻችሁና_እህቶቻችሁ_አስተላልፉ_በጣም_ጠቃሚ_እና_አስፈላጊ_እውቀት_ያስጨብጣል።


የቃላት መፍቻ፡-

#1.መኒይ (የዘር ፈሳሽ)፡-
- በስሜት ተስፈንጥሮ ከእርካታ ጋር የሚወጣ ፈሳሽ ነው፡፡
- ለወንድ ወፍራምና (ወደ ቢጫነት የሚያደላ) ነጭ ፈሳሽ ሲሆን ለሴት ደግሞ ቀጭንና ቢጫ ነው፡፡ [ሙስሊም፡ 311]
ሽታው ወደሊጥ ሽታ የቀረበ ነው፡፡ በሆነ ምክንያት እነዚህ መታወቂያዎች ሊቀየሩ ይችላሉ፡፡
- ከወጣ በኋላ የሰውነት መቀዝቀዝ ዘና ማለት (ፉቱር) ይከተላል፡፡
- ፈሳሹ ሚዛን በሚደፋው የዑለማእ እይታ ጦሀራ እንጂ ነጃሳ አይደለም፡፡ ይህን የሚደግፉ ሶሒሕ ማስረጃዎች መጥተዋል፡፡
[ሙስሊም፡ 694] [አልኢርዋእ፡ 1/197]
- በውንም ይሁን በህልም ከወጣ ገላን መታጠብ ግዴታ ነው፡፡


#2.መዚይ፡-
- ግንኙነትን ሲታሰብ ወይም ሲፈለግ የሚወጣ ያዝ የሚያደርግ (የሚያጣብቅ)፣ ቀለም አልባ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡
- አወጣጡ ከእርካታ ጋር አይደለም፡፡ ተስፈንጥሮ ስለማይወጣ
መውጣቱ ላይስተዋል ይችላል፡፡
- ነጃሳ ስለሆነ የነካውን አካል ማጠብ ይገባል፡፡ ልብስን ግን የነካው ቦታ ላይ ውሃ በመርጨት ማፅዳት በቂ ነው፡፡
- የነካውን ቦታ እንጂ ገላን መታጠብ ግን ግዴታ አይደለም፡፡ ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡



#3.ወዲይ፡-
- ከሽንት በኋላ የሚወጣ ነጭ ሽታ አልባ ፈሳሽ ነው፡፡
- የሚያጣብቅ አይደለም፡፡
- ብይኑ ከሽንት ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡


#4.ከሴቶች ብልት የሚወጣ ፈሳሽ፡-
- ከማህፀን የሚወጣ ቀጭን ፈሳሽ ነው፡፡ መጠኑ ከሴት ሴት ይለያያል፡፡
- ሴቷ መውጣቱንም ላታስተውለው ትችላለች፡፡
- አካልንም ልብስንም ቢነካ አይነጅስም፣ ጦሃራ ነው፡፡
- ውዱእን ግን ያፈርሳል፡፡ ከሁለቱም መፀዳጃዎች በኩል የሚወጣ ነገር ውዱእ ያፈርሳልና፡፡ አወጣጡ ቋሚ ከሆነ ግን ለያንዳንዱ ሶላት ወቅቱ ከገባ በኋላ ውዱእ እያደረገች መስገድ ይገባል፡፡ ውዱእ ካደረገች በኋላ ቢወጣ ቦታም አይሰጠውም፡፡


#ገላን_መታጠብ_ግዴታ_የሚሆነው_መቼ_ነው?

#1.በውኑ ግንኙነት ከተፈፀመ የዘር ፈሳሽ (መኒይ)
#ቢፈስም_ባይፈስም ትጥበት ግዴታ ነው፡፡

#2. ግንኙነት #ባይፈፀምም የዘር ፈሳሽ (መኒይ)
#ከእርካታ ጋር ከወጣ ትጥበት ግዴታ ነው፡፡

#3. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ የዘር ፈሳሽ (መኒይ)ካገኘ በማያሻማ መልኩ መታጠብ ግዴታ ነው፡፡

#4. በህልሙ ግንኙነት እንደፈፀመ አይቶ ነገር ግን ሲነቃ ምንም አይነት የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካላገኘ በማያሻማ መልኩ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ኡሙ ሱለይም የተባለችዋ ሶሐቢያህ ረዲየላሁ ዐንሃ “የአላህ መልእክተኛ ሆይ! አንዲት ሴት ኢሕቲላም ከሆነች (በህልሟ ግንኙነት ስትፈፅም ካየች) የመታጠብ ግዴታ አለባትን?” ብላ ስትጠይቅ “ፈሳሽ ካየች አዎ”ሲሉ መልሰውላታል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

#5. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ካገኘ በማያሻማ መልኩ
የመታጠብ ግዴታ አለበት፡፡


#6. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ነገር ግን ሲነቃ ፈሳሽ አገኘ፡፡ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) እንዳልሆነ እርግጠኛ ከሆነ የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ የነካውን ግንሊያጥብ ይገባል፡፡ ብይኑ የሽንት ብይን ነውና፡፡

#7. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን #መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘ በ ሽታ ወይም በቻለው መንገድ ለመለየት ይሞክርና ጥርጣሬው መኒይ ወደመሆኑ ካደላ ይታጠብ፡፡ ጥርጣሬው መዚይ ወደመሆኑ ካደላ ግን በተለይም ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት አስቦ ከነበር እንደ መዚይ ይቁጠረውና የነካውን ቦታ ብቻ ይጠብ፡፡ ገላውን የመታጠብ ግዴታ የለበትም፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡

#8. በህልሙ ግንኙነት ሲፈፅም አላየም ወይም አያስታውስም፡፡ ነገር ግን ሲነቃ የዘር ፈሳሽ (መኒይ) ይሁን አይሁን #መለየት_ያልቻለው ፈሳሽ ካገኘና ግምቱ ወደየትኛውም ካላደላ፣ ከመተኛቱ በፊት ስለ ግንኙነት #ያላሰበ ከሆነ ጉዳዩ አወዛጋቢ ቢሆንም ትክክለኛው ትጥበት የለበትም የሚል ነው፡፡ ቢታጠብ ከጥንቃቄ አንፃር የተሻለ ነው፡፡ [ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን፡ 11/161]


#የጀናባ_አስተጣጠብ_ሁለት_አይነት_ነው፡፡


#1. የሚያብቃቃ ማለትም ግዴታውን ለማውረድ የሚጠበቅ ሲሆን እሱም ሙሉ አካልን በውሃ ማዳረስ ነው፡፡ ባይሆን መጉመጥመጥና በአፍንጫ ውሃ መሳብ (ኢስቲንሻቅ) እንዳይረሳ፡፡ ለትጥበት ኒያ ሊዘነጋ አይገባም፡፡ አንድ ሰው ጀናባ ማውረድን ሳያስብ እንዲሁ ውሃ ውስጥ ዋኝቶ ቢወጣ መላ አካላቱ ውሃ መንካቱ ብቻ ጀናባው ለመውረዱ በቂ አይሆንም፡፡ ይስተዋል! ይህን ትጥበት ካደረጉ በኋላ ውዱእም ባያደርጉ መስገድ ይቻላል፡፡ ባይሆን ከትጥበቱ መሀል ውዱእ የሚያፈርስ ነገር መፈፀም የለበትም፡፡

#2. ሌላኛውና በላጩ ግን በቅድሚያ ሁለት እጆችን መታጠብ፡፡ ከዚያም ኢስቲንጃእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ውዱእ ማድረግ፡፡ ከዚያም ከእራስ ጀምሮ ቀሪ አካላትን ውሃ ማዳረስ፡፡ እግርን ከውዱእ ጋር ማጠብም ይቻላል፤ መጨረሻ ላይ ማጠብም ይቻላል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

ማሳሰቢያ፡-

ሴቷ ለትጥበት ስትል የፀጉር ጉንጉኗን የመፍታት ግዴታ የለባትም፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም: ኡሙ ሰለማህ ለጀናባህ ወይም ለሐይድ ትጥበት ፀጉሯን “ልፍታው ወይ?” ብላ ስትጠይቃቸው “አይ! የሚበቃሽ ከእራስሽ ላይ ሶስት ጊዜ ውሃ ማፍሰስ ብቻ ነው” ብለዋታል፡፡ [ሙስሊም]
ስለዚህ ፀጉር ሳይፈታ ውሃ መድረስ ከቻለ መፍታት አይጠበቅም፡፡

#ለማጣቀሻነት_የተጠቀምኩት
#1. ፈታዋ ኢብኑልዑሠይሚን
#2. ፈትሑልዐላም ፊ ዲራሰቲ አሓዲሢ ቡሉጊልመራም እና ሌሎችም

ሼር ማድረግ እንዳይረሱ

@yasin_nuru       @yasin_nuru
💥1•
” የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ኣምላክና ኣባት ይባረክ”( 2ኛ ቆሮንጦስ 1:3)

“የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ኣምላክና ኣባት ይባረክ”(ኤፌሶን 1:3)

“የጌታችን የእየሱስ ክርስቶስ ኣምላክና ኣባት ይባረክ”(1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 1:3)

የኛ ጥያቄ:

1• ማነው የእየሱስ ክርስቶስ ኣምላክ?

2• እየሱስ ክርስቶስ ኣምላክ ከሆነ, ለኣምላክ ሌላ ኣምላክ ኣለው ወይ? ኣምላክ ስንት ነው?

💥 2•
“እውነተኛ ኣምላክ ብቻ የሆንህ ኣንተን የላክኸውንም እየሱስ ክርስቶስ ያውቁ ዘንድ ይህች የዘላለም ሂወት ናት”( የዬሐንስ ወንጌል 17:3)

የኛ ጥያቄ:

እየሱስ ክርስቶስን የላከ እውነተኛውና ብቸኛው ኣምላክ ማነው?

💥 3•

” ሁሉ ከተገዛለት በኃላ ግን እግዚኣብሄር ሁሉ በሁሉ ይሆን ዘንድ በዚያን ጊዜ ልጁ ራሱ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል”(1ኛ ቆሮንጦስ 15:28)

የኛ ጥያቄ:

1•ለእየሱስ ክርስቶስ ሁሉን ያስገዛለት ማነው?

2• እየሱስ ክርስቶስ ኣምላክ ከሆነ ኣምላክ ገዢ ነው ወይስ ተገዢ? ለማን ነው የሚገዛው?

💥 4•
“ኢየሱስም ገና ወደኣባቴ ኣረግሁምና ኣትንኪኝ, ነገር ግን ወደ ወንድሞቼ ሄደሽ,እኔ ወደ ኣባቴና ወደ ኣባታችሀ ወደ ኣምላኬና ወደ ኣምላካችሁ ኣርጋለሁ ብለሽ ንገሪያቸው ኣላት”( የዬሐንስ ወንጌል 20:17)

የኛ ጥያቄ:

1• ወደ ኣምላኬና ወደ ኣምላካችሁ ሲል ኣምላኩ ማነው?

2• እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ወደ ወንድሞቼ ሲል, ኣምላክ ወንድሞች ኣሉት ወይ?

💥 5•
” በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ,ኢሎሄ ኢሌሄ ላማሰበቅታኒ? ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ ትርጓሜውም ”

ኣምላኬ ኣምላኬ ለምን ተዉከኝ? ማለት ነው”( ማርቆስ ወንጌል 15:34)

የኛ ጥያቄ:

እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ማንን ነው ኣምላኬ ኣምላኬ እያለ የሚጠራው?

💥 6•
” እየሱስም መልሶ እንዲህ ኣለው,ከትእዛዛቱ ሁሉ ፊተኛይቱ,እስራኤል ሆይ ስማ ጌታ ኣምላካችን 1 ጌታ ነው”( ማርቆስ 12:29)

እዚህ ላይ እየሱስ ጌታ ኣምላካችሁ ሳይሆን ጌታ ኣምላካችን ነው ያለው።

የኛ ጥያቄ:

እየሱስ ኣምላክ ከሆነ ” እኔ ነኝ ኣምላካችሁ” ለምን ኣላለም?

💥 7•
“ኢየሱስም ስለምን ቸር ትለኛለህ? ከኣንዱ ከእግዚኣብሄር በቀር ቸር ማንም የለም”( ማርቆስ 10:17)

የኛ ጥያቄ:

እየሱስ ኣምላክ ከሆነ, ቸር መምህር ሆይ ተብሎ ሲጠራ ለምን ተቃወመ?

@yasin_nuru @yasin_nuru
~ አዲስ ቤት ገዛህ? ዝም በል አታውራ! አዲስ መኪና ገዛህ? አትናገር ! ትዳር መሰረትክ? ብዙ አታውራለት! ለመዝናናት ከከተማ/ሀገር ወጣ ብለህ ነበር? ዝም በል!

ንግድ ልትጀምር ነው? ድምፅህን አጥፋ! ኑሮ እየሰመረልህ ነው? ብዙ አታውራ!

አብዛኛውን ጊዜ ያሰብናቸው ህልሞች እና የወጠንናቸው ራእዮች የማይሳኩበት ዋነኛው ምክንያት ከመከናወናቸው በፊት ብዙ ስለምናወራ ነው -ገና እንቁላሉን ስንታቀፍ ማውራት እንጀምርና ብዙ ሸለምጥማጦችን እንጠራለን።

ወዳጅ እና የቅርብ ሰዎች የምንላቸው ሰዎች «ሰዋዊ ቅናት» እና «የጥሎ ማለፍ ውስጣዊ ትንቅንቅ» በጣም የሚጠበቅ ተፈጥሯዊ ሁነት ነው። ስለዚህ ህልሞችህ መስመር ይዘው ፍሬ እስኪያፈራ ድረስ ዝም ብለህ መስራትን ምረጥ።

አብዛኛው ሰው ቢያልፍልህ እና ህልምህ ቢሰምርልህ ደስ ይለዋል ሆኖም ግን ጥለኸው እንድትሄድ እና አንጋጦ ሊያይህ ይተናነቀዋል።

Abusufyan

@yasin_nuru         @yasin_nuru
🔮የቁጣ መድሐኒት💊

በመሰረቱ ቁጣ የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባህሪይ ሲሆን ሲበዛና ያለበቂ ምክንያት በተደጋጋሚ የሚፈጠር  ከሆነ ግን እጅጉኑ ይወገዛል

በቦታውና በመጠኑ ሲሆን ደግሞይመሰገናል አርኣያችንና ውዱ ነቢያችንም 
صلى الله عليه وسلم
ይቆጡ እንደነበረ ታሪካቸው ላይ ተዘግቧል። ነገር ግን ቁጣቸው የአላህ ድንበር ሲጣስና ዲኑ ሲነካ ብቻ ነበር ለስብእናቸው ( ለነፍሳቸው ) ብለው አንድም ቀን ተቆጥተው አያውቁም

💦በሁሉም ነገር ☞እርሳቸውን የተከተለ ምንኛ የታደለ ሰው ነው?!

📌የቁጠኝነትን ባህሪይ ለመከላከልና በሆነ ባልሆነው የመቆጣትን ችግር ለመቅረፍ የሚከተሉትን ምክሮች ይተግብሩ፦

1/ ቁጣቸውን ዋጥ ለሚያደርጉና ይቅር ለሚሉ ሰዎች አላህ አኼራ ላይ ያዘጋጀውን ከፍተኛ ምንዳና ደረጃ ማስታወስ

2/ አዑዙ ቢላህ ሚነሽሸይጧኒር`ረጂም ማለትና ዚክር ማለት

3/ ከንግግርና መልስ ከመስጠት መታቀብ (ዝም ማለት)

4/ ቁጣው የተፈጠረው ቆመው ከሆነ መቀመጥ፣ ቁጭ ብለው ከሆነም ጋደም ማለትና ሁኔታን መቀየር፣

5/ ውዱእ ማድረግና ከተቻለም ሁለት ረካኣ ሰላት መስገድ ሙሉ ውዱእ ማድረግ እንኳ ባይቻል የተወሰነ ሰውነት ላይ ውኃ በማፍሰስ ሰውነትን ማቀዝቀዝ፣

6/ ቁጣና ንዴት የሚያስከትለውን የጤና ችግር  እንዲሁም በቁጣ ጊዜ እራሳችን ላይ የሚታየውን መጥፎና አሳፋሪ የፊት ገፅታ እና የማይገቡ እንቅስቃሴዎችን ልብ ማለትና ይህን ከሰዎች እንደምንጠላው ሁሉ ለራሳችንም መጥላት፣

7/ ቁጣን መተው ነቢዩን صلى الله عليه وسلم መታዘዝ እንደሆነ ማወቅ፥ ምክንያቱም ነቢዩ ("አትቆጣ!") ብለዋልና
ይህም ሊሳካ የሚችለው ለቁጣ የሚዳርጉ ነገሮችን በመራቅና የተቆጡም እንደሆነ ራስን በመቆጣጠር  ብቻ ነው

8/ በሆነ ባልሆነው የሚቆጣ ሰው ቤተ-ሰቦቹንና በተለያዩ ምክንያቶች የሚገናኙትን ሰዎች አዛ ስለሚያደርጋቸው እንደሚጠሉት ማወቅና ከቁጣ በሽታ እንዲገላግለን አላህን ዘወትር መለመን
አበቃ!

🕯አላህ መልካም ባህሪያትን በሙሉ ያግራልን! እርሱ ከሚጠላቸው ባህሪያትና ድርጊቶችም ይጠብቀን

ኡስታዝ አሕመድ ኣደም

@yasin_nuru @yasin_nuru
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በአንቺ ፎቶ የተነሳ በአንቺ ምስል የተነሳ እንቅልፍ የሚያጣ ወንድ ይኖራል መቆጣጠር አትችይም።

ፕሮፋይልሽ ላይ የለጠፍሽውን ያንቺን ምስል ሴቭ አድርጎ ሲተኛ ያንቺን ፎቶ እያዬ እንቅልፍ ሊያጣ ይችላል🥺🥺

ለምን ባንቺ የተነሳ ወንድምሽን  አደጋ ውስጥ ትጥይዋለሽ።

አላህን ልትፈሪ ይገባል

ለተቃራኒ ፆታ ፈተና መሆን ያስጠይቃል!

@yasin_nuru @yasin_nuru
2025/07/04 23:53:33
Back to Top
HTML Embed Code: