Telegram Web Link
ብቸኛው ወደ ጀነት መግቢያ በር ተውሒድ ነው።

ሌሎች እንደ ሰላት፣ ጾምና ሰደቃ ወዘተ ያሉ ዒባዳዎች በሮች የሚገኙት ዋናውን የተውሒድ በር ካለፉ በኋላ ነው።

@yasin_nuru
#አምስቱ_የእስልምና_መሰረቶች

1.መመስከር :- ከአላህ ውጪ ሌላ አምላክ እንደሌለ እና ሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መልዕክተኛ አንደሆኑ መመስከር

2.አምስቱንም ወቅት ሰላት ጠብቆ መስገድ

3.ዘካን መስጠት

4.ረመዳንን መፆም

5.ሀጅን ማድረግ


#ስድስቱ_የኢማን_መስፈርቶች

1.በአላህ ማመን

2.በመላኢኮች ማመን

3.በመፅሀፎች(በኪታቦች) ማመን

4.በመልዕክተኞች ማመን

5.በመጨረሻው ቀን ማመን

6.በቀዳ እና በቀድር(ባለፈው ነገር እና በሚመጣው ነገር) ማመን

Luhena

@yasin_nuru @yasin_nuru
🏷️የመልካም ተርቢያ ጸር የሆኑ
             10 ነገሮች

♻️ማንኛውም ወላጅ ልጆቹን ትክክለኛ አስተዳደግ ማሳደግ የሚችለው የተሳሳቱ የተርቢያ መንገዶችን አውቆ ሲርቃቸው ነው።
በዋናነት ከሚጠቀሱ የመጥፎ ተርቢያ መገለጫዎች ውስጥ:-

1/ ከመምከርና ችግሮችን በውይይት ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ በሁሉም ነገር ላይ ደረቅ ትችትና ወቀሳን መጠቀም፣ወይም ማብዛት

2/ በንግግርም ይሁን በተግባር ልጆች ላይ መጠንከርና ሁሌም ጉልበት መጠቀምን ማስቀደም፣

3/የልጆችን ሚስጥር ወይም ደካማ ጎኖቻቸውን ለሌሎች በማሳወቅ እንዲሸማቀቁና እንዲያፍሩ ምክንያትመሆ፣

4/ ልጆች ላይ በማሾፍና በመሳለቅ ሞራላቸው እንዲነካ ማድረግ፣

5/ ተፈጥአዊ በሆኑና የግድ ባልሆኑ ነገሮች ላይም ጭምር ልጆች ወላጆቻቸውን እንዲመስሉና በሁሉም ነገር ልክ እንደነሱ ሆነው እንዲያድጉ መፈለግና ጫና ማድረግ፣

6/ልጆች እንዲያደርጉት ወይም እንዳያደርጉት የምንፈልገውን ነገር በሙሉ ከገንዘብ ወይም ከሆን ጥቅም ጋር ማያያዝ (ብር... እሰጥሃለሁ እንዲህ... አድርሃለሁ ወዘተ) ማለት፣

7/ለአካላዊም ይሁን መንፈሳዊ ጤንነታቸው በቂ ትኩረት አለመስጠት፣

8/ለልጆች በቂ ጊዜ በመስጠት እነሱን አለማጫወትና የሚገጥሟቸው ችግሮችን አድምጦ መፍትሄ አለማበጀት፣

9/ በልጆች ጉዳይ ፍትሃዊ አለመሆን፣ (ለአንዱ በጎ ሆኖ ለሌላው መጥፎ መሆን፣ ለአንዱ የሚፈልገውን እያደረጉ ሌላኛውን ችላ ማለት ወዘተ)፣

10/ ወላጆች ልጆቻቸው ስርዓት እንዲይዙና ጥሩ እንዲሆኑ እየመከሩ እራሳቸው ግን  ከመልካም ነገሮች የራቁና ከዛም አልፈው ልጆቻችው ፊትም መጥፎ ነገሮችን ማድረግ ወዘተ መስለ የመልካም ተርቢያ ጸር የሆኑ ነገሮችን  አውቀን መራቅ ካልቻልን በስተቀር ለልጆች ጥሩ ተርቢያ መመኘትና  አንዳንድ ነገሮችን ማድረጋችን ብቻ ጥሩ ልጆችን ለማፍራት በቂ አይሆንም።

@yasin_nuru @yasin_nuru
የነብዩ_ሙሐመድ_ﷺ_ሚስቶች_ስም

★زوجات الرسول ﷺ ﺇﻧّﻬﻦ ﺍﺛﻨﺘﺎ ﻋﺸﺮﺓ ﺯﻭﺟﺔً،
(١) ☜السيدة خديجة بنت خوليد
(٢)☜السيدة السودة بنت زمعة
(٣)☜السيدة عائشة بنت ابي بكر
(٤)☜السيدة حفصة بنت عمران
(٥)☜السيدة زينب بنت خزيمة
(٦)☜السيدة هند بنت أمية
(٧)☜السيدة زينب بنت جحش
(٨)☜السيدة جورية بنت الحارث
(٩)☜ السيدة ﻣﺎﺭﻳﺔ ﺍﻟﻘﺒﻄﻴﺔ  ﺑﻨﺖ ﺷﻤﻌﻮﻥ
(١٠)☜السيدة رملة بنت ابي سفيان
(١١)☜ السيدة صفية حيي بن اخطب
(١٢)☜السيدة ميمونة بنت الحارث

#የነብዩ_ሙሐመድ_ﷺ_ሚስቶች_12_ናቸው። እነሱም፦👇👇👇

①☞ ሰይደቲ #ኸዲጃ    ቢንቲ ኹይሊድ
②☞ ሰይደቲ #ሰውዳእ  ቢንቲ ዘመዐህ
③☞ ሰይደቲ #አዒሻ      ቢንቲ አቡበክር
④☞ ሰይደቲ #ሓፍሷ     ቢንቲ ዒምራን ልጅ
⑤☞ ሰይደቲ #ዘይነብ    ቢንቲ ኹዘይማህ
⑥☞ ሰይደቲ #ሂንድ       ቢንቲ  ኡመያህ
⑦☞ ሰይደቲ #ዘይነብ     ቢንቲ ጀሕሽ
⑧☞ ሰይደቲ #ጁወይሪያ ቢንቲ ሓሪስ
⑨☞ሰይደቲ #ማሪያ_አልቂብጢያ ቢንቲ ሸምዑን
10☞ ሰይደቲ #ረምላ       ቢንቲ አቡ ሱፍያን
11☞ ሰይደቲ #ሶፍያ       ቢንቲ ሓይይ
12☞ ሰይደቲ #መይሙና ቢንቲ ሓሪስ

@yasin_nuru @yasin_nuru
ቁርጥ እርሣቸዉን የምትመስል ቆንጆ ናት፣ ዉብ ዕድሜዋ ለጋብቻ ሲደርስ ብዙ ሰዎች ሊጠይቋት እርሣቸው ጋር መጡ፤ ብዙ የተከበሩና ትላልቅ ሰዎች …

አንዲት ዐሊን የምትወድ የአንሷር ሴት ዐሊ ዘንድ ሄዳ
“ፋጢማን ብዙ ሰው እንደጠየቃት ታውቃለህ ግን?” አለችው፡፡
“አዎን” አላት፡፡
“አንተሰ ለምን ሄደህ አትጠይቅም፤ ለምን ዳሩልኝ አትላቸዉም፣ ትወዳት የለ?” አለችው፡፡
አንገቱን አቀረቀረ
“ድሃ ነኝ ምን አለኝና? በምንድነው የማገባት?” አላት፣
“ዝምብለህ ሂድና ጠይቅ፤ መልካም ነገር ልትሰማ ትችላለህ አብሽር፡፡” ብላ አሳመነችው፡፡

ሄደ፡፡ ፈራቸው፤ እርሣቸው ፊት ተቀምጦ መናገር ከበደው፡፡ እናም ዝም አለ፡፡
“ምነው ዐሊ ምን ሆነህ ነው? ምንድነው ያመጣህ ጉዳይ?” አሉት፤ አከታትለው ጠየቁት፡፡
ዐሊ አሁንም ዝም አለ፡፡
“ምናልባት ፋጢማን እንድሰጥህ ለመጠየቅ መጥተህ እንዳይሆን፡፡” አሉት፡፡
አዎን በሚል ሀሳብ ራሱን ነቀነቀ፤
“ታዲያ ጥሎሽ ይኖርሃልን?” አሉት፡፡
“ምንም የለኝም” አላቸው፡፡
“የሆነ ጋሻ እንዳለህ አስታውሳለሁ፡፡” አሉት፡፡
“አዎን አለኝ፣ ግን እሱ ምን ያደርጋል፣ ምን ዋጋ ያወጣል?” አላቸው፡፡
“ይጠቅማል ሽጠዉና ...፡፡” አሉት፡፡

ቤት ገዙላቸው፤ ጋብቻው ተፈፀመ፡፡

ዐሊ እንዲህ ይላል 
'ከዚያ በኋላ ፋጢማን እጅግ ወደድኳት፡፡ አንድም ቀን በስሟ ጠርቻት አላውቅም፤ “ የአላህ መልዕክተኛ ልጅ ሆይ” ነበር የምላት፡፡
ልክ እሷን ሳይ ሀሳብና ጭንቀቴ ሁሉ ይወገዳል፣ ልቤ እረፍት ይሰማዋል፣ አንድም ቀን አስቆጥቻት አላውቅም፣ አንድም ቀን አላስለቀስኳትም፣ አንድም ቀን አስቆጥታኝ፣ አንድም ቀን አስቸግራኝ አታውቅም፡፡ በአላህ አምላለለሁ አንድም ቀን ጀርባዬን ሰጥታችት አላውቅም፤ ሁሌም እጆቿን እንደሳምኳት …   

ፋጢማ ከአባቷ ከአላህ መልዕክተኛ (ሶ.ዐ.ወ.) ህልፈት ከስድስት ወር በኋላ ተከተለቻቸው፡፡ በሞተችም ጊዜ ባለቤቷ ዐሊ አጠባት፣ ከፈናትም፣  ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብሎም
      
“ፋጢማዬ እኔ ዐሊ ነኝ፡፡” አላት፡፡  

@yasin_nuru @yasin_nuru
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
"ጁመዓ!
-----------------



በጁምዓ ክልክል የሆኑ ተግባራት።
,
ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ መናገር አይፈቀድም፡፡
,
   ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብለዋል፦
,
በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ የተናገረ መፅሐፍ እንደተሸከመ አህያ ነው››

      ,        አህመድ 1/23ዐ


   በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል፦
ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጓደኛህ ዝም በል ካልክ ከንቱ ንግግር ተናገርክ››

   ቡኻሪ 394  ሙስሊም 851
,
በተቀመጡ ሰዎች ትከሻ በኩል በመሸጋገር መተላለፍ፦
,
ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የሰዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ሲያልፍ ለተመለከቱት ሰው ‹‹ተቀመጥ ሰውን አስቸገርክ›› ብለውታል::
  ,
በዚህ ተግባር ሰውን ማስቸገርና ኹጥባን የሚያደምጥን ማዘናጋትም ይፈጠራል::
,
  ኢማሙ ግን የሠዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ካልሆነ ወደ ቦታው የሚደርስበት ሌላ አማራጭ ከሌለው ይህን ሊፈፅም ይችላል፡፡
,
ሁለት ሰዎችን በመለየት በመካከላቸው መቀመጥም አይፈቀድም፡፡
  ነብዩ (ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)
       እንዲህ ብለዋል ፦
,
የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ ከዚያ በኋላ በሰዎች መካከል ሳይለይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፀሙ ኃጢአቶች ይሰረዝለታል››

            ቡኻሪ 910

©«አል ኢኽላስ የሙስሊሞች ጀመዓ»\

@yasin_nuru @yasin_nuru
📨20 ወንድማዊ ምክር ለውዷ እህቴ

1,በተውሒድ ላይ አደራ! ሽርክን ራቂ!!

2,, ሁሌ ቤት ውስጥ መቀመጥ ምርጫሽ ይሁን።ወጣ ወጣ አትበይ!!

3,,ተቅዋን(አላህን መፍራት) የውስጥ መዋቢያሽ ካደረግሽ ሀያእን ደሞ ውጫዊ መዋቢያሽ አድርጊው!!

4,,ከ ወንዶች እና ከካፊር ሴቶች ጋ ያለሽ ግንኝነት በጣም አስፈላጊ ሆኖ እስካላገኘሽው ድረስ ራቂ!!

5,,ሒጃብሽ ሰፋ ያለና ረዘም ያለ ይሁን!!

6,,አካሄድሽ ረጋ ያለና አደብ የተላበሰ ይሁን!!

7,,በየቀኑ ብታጠፊ በየቀኑ ወደ አላህ ተመለሺ!!

8,,በአለባበስሽና በሥነ-ምግባርሽ ለሌሎች ሴቶችና ለሴት ልጆችሽ ምሳሌ ሁኚ!!

9,,ያልተፈቀደልሽን ባዕድ ወንድም ሆነ ሊያገባሽ የሚፈቀድለትን የቅርብ ዘመድ አትጨብጭ!!

10,,ከላይ አላህን ሳይታዘዙ፤ ዉስጤ ንፁህ ነው አላህን ፈራለሁ ማለት ቅጥፈት ነው!!

11,ከባዕድ ወንድ ጋር ስታወሪ መቅለስለስ፤ በሽታ ያለበትን በሽታውን መቀስቀስ ነውና አደብ ይኑርሽ በንግግርሽ…!!

12,መስመር እየሳቱ የሚመስሉ የስልክ ወሬዎችንና ቻቶችን ከወድሁ ቁረጪ!!

13,እየተኳኳሉና እየዘለሉ አላህን እና መልዕክተኛዉን እወዳለሁ ማለት ዉሸት ነውና…

14,ሒጃብና ኒቃብ እየለበሱ መጥፎ መሥራት የኢስላምን ንጽሕት የሙስሊምን ሥም ጭምር ማጠልሸት ነውና… በቻልሽው አቅም አደብ ይኑርሽ!!

15,በሐራም መንገድ ገንዘብም ሆነ ትዳር ባገኙት አትቅኚ ፈፃሜው አያምርም እና!!

16,- ፀጉርሽን አትጎዝጉዢ(ከፍ አድርገሽ አትሰሪው) አትቀጥይውም፣ሽቶም ሆነ ዶድራንት አትቀቢ!!

17,ስትስቂ በስሱ፤ ሰታወሪ ድምጽሽ ዝቅ ይበል!!

18,በሥራ ቦታ እና በት/ት ቤት  ከሰዎች ጋር ባለሽ ግንኙነት ቀይ መስመር ይኑርሽ!!

19,,ከ እህቶችሽ ጋር ተግባቢ እና ትህትና ያለሽ ሁኚ!!

20,,የሸሪዓ እውቀትን በመፈለግ ላይ አደራ እስካሁን ለጠቀስኩት ምክሮች መሰረቱ ነው እና!!

[▫️አቡ ሡፍያን]

@yasin_nuru @yasin_nuru
💫መልካም አባባሎች
📖 እኔ ዘንድ በጣም የተወደደው ሰው ደካማ ጎኖቼን የሚነግረኝ ሰው ነው።
🖊 ዑመር አልኸጧብ(ረ. አ)

📖የበጎ ነገርና አላህን በመፍራትም ተረዳዱ ግን በሀጢአትና ወሰንን በማለፍ አትረዳዱ።
🖊 (5:2) ሱረቱል ማኢዳ

📖 ሙስሊም ባሪያውን በመርዳት ላይ ነው። ባሪያው ወንድሙንና እህቱን እስካልተባበረ ድረስ ።
🖊 ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም

📖 ከሷሊህ ሰዎች ጋር ድንጋ መሸከም ከመጥፎ ሰዎች ጋር ከሚበሉት ምርጥ ምግብ ይጣፍጣል ።
🖊 ማሊክ ኢብኑ ዲናር

📖 ብዙ ጓደኛ አይቻለሁ ምላስን ከመጠበቅ የተሻለ ጓደኛ አላየሁም ። ብዙ ልብሶች አይቻለሁ አላህን ከመፍራት ያማረ ልብስ አላየሁም።

🖊 ኡመር አልኸጧብ(ረ. አ)

📖 ከመጥፎ ሰዎች ጋር ከመቀላቀል ለብቻ መሆን እረፍት ነው።
🖊 ኡመር አልኸጣብ(ረ. አ)

📖 ከስህተቶች ሁሉ ታላቁ ውሸት ነው። ምላሱ የሚዋሽ ሰው አይኑን ጆሮውን መላ አካሉን ያስዋሻል ።ያላየውን አየሁ ያልሰማውን ሰማሁ ይላል።
🖊 አብደላህ ኢብን መስኡድ (ረ .አ)

📖 አላህ የላይ ገፃችሁንና ገናዘባችሁን አይመለከትም ። ነገር ግን ቀልቦቻችሁንና ስራዎቻችሁን ይመለከታል።
🖊 ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ።

📖 አላህ ዘንድ የሚበላለጠው ስራ መብዛት ሳይሆን ቀልብ ውስጥ በተቀመጠው ነገር ነው።
🖊 ኢማሙ ኢብኑ ቀዩም

📖 በሚጠቅምህ ነገር ላይ ጉጉት ይኑርህ በአላህ ታገዝ ደካማና ስልቹ አትሁን አንድ ነገር ባጋጠመህ ጊዜ ይህን ነገር እንዲህ ባረገው ኖሮ አትበል።

ነገር ግን አላህ የወሰነውን ሆነ አላህ የፈለገውን ፈፀመ በል።እንዲህ ቢሆን ኖሮ የሚለውን ንግግር ለሰይጣን ስራ በር ይከፍታል።
🖊 ረሱል ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም።

📖 እኔኮ አንድን ሰው ማየት ያስጠላኛል በጣም ይከብደኛል ቢዚ ይሆናል የሆነበት ምክንያት ግን ለዲኑም ለዱንያውም በማይጠቅመው ነገር ምንም አላማ የለውም።

🖊 ኢማሙ ሻፊኢይ ናቸው ረሂመሁላህ።

🔗SHARE 🔗SHARE
╔════════════╗
JOIN: @yasin_nuru        
JOIN: @yasin_nuru            ╚════════════╝
🖌በሀገረ እንግሊዝ የምትኖር አንዲት ሚስኪን ትውልደ ሶማሊያዊት ሙስሊም ሴት እርዳታን ለማግኘት ወደ ሬዲዮ ጣቢያ ደወለች። አምላክ የለም በሚለው እምነቱ የሚታወቀው ሰው የስልኩን እጀታ አነሳና አዳመጣት።

📍ፋጡማ ቤቷ የሚላስ የሚቀመስ አለመኖሩን በመንገር ለችግሯ መፍትሄ እርዳታ ያደርግላት ዘንድ ተማፅና ቁጥሯን እና አድራሻዋን ሰጥታ ስልኩን ዘጋችው።

✒️ምግብና ሌሎች እርዳታዎች ተዘጋጅተው ወደ አድራሻዋ እንዲያደርስ ለግል ጸሃፊው መመሪያ ሰጠ። እንዲህም አለ፡- 

💠"የእርዳታውን ምንጭ ከጠየቀችሽ ከሸይጣን የተሰጣት ስጦታ መሆኑን ንገርያት" በማለት ሴትየዋ ላይ እየተሳለቀ አዘዛት።

ፀሐፊዋ የሚያስፈልጋትን ሁሉ ሸክፋ ወደ ሴትየዋ ቤት አቀናች።

❇️ምስኪኗ ሴት በደስታ እያነባች የተላከላትን ተቀብላ ወደ ውስጥ ለመግባት በመራመድ ላይ ሳለች ጸሃፊዋ
"የዚህን እርዳታ ምንጭ ማን እንደላከልሽ ማወቅ አትፈልጊምን?"  ስትል ጠየቀቻት።

🔰ይህች ማንበብና መጻፍ የማትችል ሙስሊሟ ፋጡማ የሰጠችው ምላሽ እምነት አልባውን ዶ/ር ቲሞሲ ቬንተርን አስተሳሰብ ቀይራ እስልምናን እንዲቀበል አደረገው ስሙንም ዐብዱልሀኪም ሙራድ ብሎ እንዲሰይም አስገደደው።
ምላሿ ይህ ነበር፡-

❤️ "ለማወቅ አልፈልግም ማንነቱም ግድ አይሰጠኝም። ጌታዬ አላህ አንድን ነገር ከፈለገ ሰይጣኖችም እንኳ ቢሆኑ ይታዘዙታልና"

#አላህ ሆይ" እምነታችንን አፅናልን!!

©️®ምንጭ"f.book.ድ/ገጽ

#ዘላለም_ኗሪ_አላህ_ነው

@yasin_nuru       @yasin_nuru
አስተውል!

~ ሰዎች ዘንድ ለመወደድ ስትለፋ ጌታህ ዘንድ እንዳትጠላ ተጠንቀቅ።

~ ለምትወዳቸው ሰወች ክብር ስታበዛ የጌታህን ክብር እንዳትነካ ተጠንቀቅ።

~ ሰወችን በመውደድ ብቻ ስትጠመድ የጌታህን ውዴታ እንዳትነፈግ ፍራ! ጥላቸው ማለት አይደለም ውዴታህ በልክ ይሁን!

~ እውነት ለመናገር ከሰወች ጥቅምን አትፈልግ! ሰወችን ለማስደሰት አትዋሽ! ለህሊናህ እረፍት አስበህ እውነተኛ ሁን!

~ የራስክን ደስታ ለማሞቅ ለሌሎች ሃዘን ሰበብ አትሁን! በሌሎች ደስታ ተደሰት! ከምቀኝነት እራቅ!

~ ለጥፋት መሆንን እንጂ መባልን አትፍራ! ሆኖ ለመገኘት እንጂ ለመባል አትድከም።

~ ፍርድ ለመስጠት ከመወሰንህ በፊት ዳኛ ለመሆን አቅሙ እንዳለክ እራስክን ጠይቅ።

~ ለመውቀስ ከመቸኮል ለማጣራት ሞክር ! መልስ ከመስጠትህ በፊት ጥያቄውን አስተንትን!

~ ማንነትህን ለማሳወቅ በአፍህ ከመናገር ይልቅ ስራበት! ተግባርህ ያስረዳ!

~ መልካም ለመሆን አትምረጥ። ለሁሉም መልካም ሁን አትጎዳበትም።

~ ክብርን ለማግኘት ክብር ከሌለው ተግባር ተቆጠብ!

~ ሀቅን እንጂ ሰወችን አትከተል።

~ መኖርህን ስታይ መሞትህንም አትርሳ! ኖረህም የሚጠቅምህን ስትሞትም የሚከተልህን ስራ!!

JOIN: @yasin_nuru 
JOIN: @yasin_nuru  
🔖የጁምዓ ሰላት ሸሪዓዊ ብይኑና ማስረጃዎቹ🔖

🌂የጁምዓ ሰላት በያንዳንዱ ሙስሊም በሆነ ወንድ ላይ ግዴታ ነው፡፡

አላህ እንዲህ ይላል፡-

‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡›› ጁምዓ 9

ነብዩም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

‹‹አቅመ አዳም በደረሰ በያንዳንዱ ሰው ጁምዓ ግዴታ (ዋጂብ) ነው››[ነሳኢይ 1371]

በሌላም ሐዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

‹‹ሠዎች ጁምዓን ከመተው የማይታቀቡ ከሆነ አላህ ልቦናቸውን ያሽግና ዝንጉዎች ይሆናሉ››[ሙስሊም 865]

ጁምዓ ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች

ጁምዓ በእያንዳንዱ ወንድ፣ ከባርነት ነፃ በሆነ፣ አቅመ አዳም በደረሰ፣ የአእምሮ ጤነኛ በሆነና ወደ ጁምዓ የመምጣት ችሎታ ባለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡፡ በአንፃሩ በባሪያ፣ ሴት ልጅ፣ ያልደረሰ ልጅ፣እብድ፣ህመምተኛና መንገደኛ ላይ ግዴታ አይደለም፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

‹‹ጁምዓን በህብረት መስገድ ከአራት ሰዎች በስተቀር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡- ባሪያ፣ ሴት ልጅ፣ ህፃንና ህመምተኛ››[አቡዳውድ 1ዐ54]

መንገደኛ የሆነ ሰው ላይ ጁምዓ ግዴታ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) ባደረጓቸው ጉዞዎች ላይ አንድም ቀን ጁምዓ አልሰገዱም:: ነብዩ (ﷺ) ባደረጉት የመሰናበቻ ሐጅ ላይ ጁምዓ ገጥሟቸው ነበር ነገር ግን የሰገዱት ዙህርና ዓስርን በማቆራኘት እንጂ ጁምዓን አልነበረም፡፡ ይሁንና አንድ መንገደኛ ሙስሊምች ጁምዓ የሚሰግዱበት ቦታ ላይ በአጋጣሚ ቢገኝ ከነሱ ጋር አብሮ ጀምዓ መስገድ አለበት፡፡ ባሪያ፣ ሴት፣ልጅ፣ህፃን፣ህመምተኛ ወይም መንገደኛ ጁምዓ ተገኝተው ከሰገዱ ዙህርን መስገድ አይጠበቅባቸውም::

የጁምዓ ወቅት🌤

የጁምዓ ሰላት ወቅት ልክ እንደ ዙህር ፀሀይ ወደ ምዕራብ ዘንበል ካለችበት ወቅት አንስቶ የአንድ ነገር ከፀሐይ የሚያገኘው ጥላ በቁመቱ ልክ እስከሚሆን ድረስ ነው፡፡ አነስ ኢንብ ማሊክ እንዳሉት

‹‹ነብዩ (ﷺ) ጁምዓ የሚሰግዱት ፀሐይ ዘንበል ስትል ነበር››[ቡኻሪ 9ዐ4]

በዚህ ወቅት ጁምዓ መስገድ የሰሃቦች የተለመደ ተግባር እንደነበርም ተዘግቧል፡፡ በዚህ መሰረት ወቅቱ ከማብቃቱ በፊት አንድ ረከዓ የመስገጃ ያህል ጊዜ ላይ የደረሰ  ጁምዓን ይሰግዳል፡፡ ወቅቱ ያለፈበት ከሆነ ግን መስገድ ያለበት ዙህርን ነው፡፡

📔የጁምዓ ኹጥባ📚

ኹጥባ ነብዩ (ﷺ) በሰገዷቸው ጁምዓዎች ሁሉ የፈፀሙትና ትተውት የማያውቁ በመሆኑን የጁምዓ መሰረት ነው፡፡ ስለዚህ ጁምዓ ያለ ኹጥባ መሰረተቢስ ነው:: በጁምዓ የሚደረጉት ኹጥባዎች ሁሉት ኹጥባዎች(ሁለት ኹጥባዎች የሚባሉት ኢማሙ አንደኛውን ኹጥባ ካደረገ በኋላ በመሃል ተቀምጦ ለሁለተኛ ጊዜ ቆሞ የሚያደርጋቸው ናቸው)ሲሆኑ መስፈርቱም ከሰላት አስቀድሞ ማድረግ ነው፡፡

🔖የኹጥባ ሱናዎች🔖

ለሙስሊሞች ዱንያዊና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች መስተካከልና ለመሪዎች ዱዓ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) የጁምዓ ዕለት ኹጥባ ሲያደርጉ በጣታቸው ወደ ላይ እየጠቆሙ ዱዓ ሲያደርጉ ሰዎችም አሚን ይሉ ነበር፡፡

ኹጥባና ሰላት በአንድ ሰው ቢፈፀሙ ይወደዳል፤ ኹጥባ አድራጊው በተቻለ አቅም ድምፁን ከፍ ቢያደርግ የተወደደ ነው፤ ኹጥባን ቆሞ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡

ጃቢር ኢብን ሰሙራ እንዳሉት

‹‹ነብዩ (ﷺ) ቆመው ኹጥባ ካደረጉ በኋላ በመሀል ተቀምጠው ከዚያ እንደገና ቆመው ያደርጉ ነበር››[ሙስሊም 862]

    ኹጥባን አጠር ማድረግና የሁለተኘውን ኹጥባ ከመጀመሪያው ይበልጥ አጠር ማድረግ፡፡ ዓማር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ

‹‹የአንድ ሰው ኹጥባ አጠር ማለቱና ሰላቱን ረዘም ማድረጉ የአዋቂነቱ ምልክት ነው፡፡ ሰላትን አስረዝሙ ኹጥባን አሳጥሩ››[ሙስሊም 869]

ኹጥባ አድራጊው ወደ ህዝቦች ዞር ብሎ ሠላምታን ማቅረብ፡- ጃቢር እንዳሉት

‹‹ ነብዩ (ﷺ) ሚንበር[የኹጥባው መድረክ (ምኹራብ)] ላይ ሲወጡ ሠላምታ ያቀርቡ ነበር”

 አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪያጠናቅቅ ሚንበር ላይ መቀመጥ  ኢብን ዑመር እንዳሉት ‹‹ነብዩ (ﷺ) በሚንበር ላይ ወጥተው አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪጨርስ ሚንበር ላይ ይቀመጡና ሲጨርስ ተነስተው ኹጥባ ያደርጉ ነበር››

🔊በጁምዓ ክልክል የሆኑ ተግባራት🔊

     ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ መናገር አይፈቀድም፡፡  ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ

‹‹በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ የተናገረ መፅሐፍ እንደተሸከመ አህያ ነው››[አህመድ 1/23ዐ]

በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል

‹‹ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጓደኛህ ዝም በል ካልክ ከንቱ ንግግር ተናገርኽ››

በተቀመጡ ሰዎች ትከሻ በኩል በመሸጋገር መተላለፍ :
 ነብዩ (ﷺ) የሰዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ሲያልፍ ለተመለከቱት ሰው ‹‹ተቀመጥ ሰውን አስቸገርክ›› ብለውታል:: በዚህ ተግባር ሰውን ማስቸገርና ኹጥባን የሚያደምጥን ማዘናጋትም ይፈጠራል:: ኢማሙ ግን የሠዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ካልሆነ ወደ ቦታው የሚደርስበት ሌላ አማራጭ ከሌለው ይህን ሊፈፅም ይችላል፡፡

ሁለት ሰዎችን በመለየት በመካከላቸው መቀመጥም አይፈቀድም፡፡ ነብዩ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል

የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ ከዚያ በኋላ በሰዎች መካከል ሳይለይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፀሙ ኃጢአቶች አላህ ይቅር ይለዋል።

[ቡኻሪ 91ዐ]

🔖ጁምዓ ላይ መድረስ የሚቻለው በምንድን ነው?

💡ከኢማሙ ጋር አንድ ረከዓ ከደረሰ ጁምዓን በማግኘቱ የቀረውን አንድ ረከዓ ይጠበቅበታል:: ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ከጁምዓ አንድ ረከዓን የደረሰ ሰላት ላይ ደርሷል›› ኢማሙ ላይ የደረሰው ግን ከአንድ ረከዓ ባነሰ ከሆነ መሙላት ያለበት ዙህር ሰላትን ነው፡፡

💡የጁምዓ ሱና ሰላት💡

ከጁምዓ በፊት የሚሰገድ መደበኛ ሱና የለም፡፡ ነገር ግን ወቅቱ ከመድረሱ በፊት መደበኛ ያልሆነ ሱና ቢሰግድ ምንም ችግር የለውም ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) በጥቅሉ ሱና መስገድን አበረታተዋል፡፡ ከጁምዓ በኋላ ግን መደበኛ የሆኑ ሁለት፣ አራት ረከዓ ወይም ስድስት ረከዓ ሱናዎችን እንደሁኔታው ሊሰገድ ይችላል፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ባስተላለፉት ሀዲስ

‹‹ነብዩ (ﷺ) ከጁምዓ በኋላ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር››[ቡኻሪ 937 ሙስሊም 882]

በሌላ ሀዲስ ደግሞ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል

‹‹ ከጁምዓ በኋላ አራት ረከዓ ሱናዎችን ስገዱ››[ሙስሊም 881]

ኢብን ዑመርም ከጁምዓ በኋላ ስድስት ረከዓዎችን ይሰግዱ እንደነበር ‹‹ነብዩ ይፈፅሙት ነበር››[አቡዳውድ 113ዐ]

እንዳሉ አቡዳውድ ዘግበዋል፡፡ በዚህ መሰረት ከጁምዓ በኋላ የሚሰገድ መደበኛ ሱና ከፍተኛው ስድስት አነስተኛው ሁለት መሆኑን እንረዳለን::

🔖የጁምዓ ሰላት አሰጋገድ🔖

🎯የጁምዓ ሰላት ድምፅ ከፍ በመደረግ የሚሰገዱ ሁለት ረከዓዎች እንደሆኑ በነብዩ (ﷺ) ተግባርና በዑለማዎች ስምምነት የተረጋገጠ ነው፡፡ በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል ጁምዓ በሁለተኛው ረከዓ ደግሞ ሱረቱል ሙናፊቁን[ሙስሊም 877] ወይም በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል አዕላ በሁለተኛው ሱረቱል ጋሺያ እንደሚነበብም ነብዩ (ﷺ) በተግባር አስተምረዋል፡፡[ሙስሊም 878]

@yasin_nuru @yasin_nuru
የሞቀ ውሃ ስንደፋ ቢስሚላህ እንበል?

#ሸይኽ ኢብን ባዝ ተጠየቁ ፡ ሙቅ ውሃን በምናፈስበት ጊዜ ቢስሚላህ እንላለን? ይህም ጂን ቦታው ላይ ይኖራል ብሎ በመፍራት ነው
መልስ፡
"አዎን! ቢስሚላህ ይበል ምን አልባት ቦታው ላይ ጂን ካለ እንዲነቃ ለማድረግ ነው" ከዛም ሽይኹ እንዲህ አሉ" በርግጥም በአንድ ወቅት አንድን ሰው ጂን ይዞት በሚቀራበት ቦታ ተገኝቼ ነበር
#ሩቃ የሚያደርገው ሰው በሰውየው ላይ ለተደበቀው ጂኒ
"ለምን ያዝከው "አለው
#ጂንውም "የሞቀ ውሃ በአንዱ ልጄ ላይ ደፋና ገደለው "አለ
#የሚቀራው ሰውዬ ደግሞ "እሱ ልጅህ በቦታው መኖሩን ስላላወቀ ነው" አለው
#ጂኒው ደግሞ "ለምን ቢስሚላህ አይልም ነበር እንዲያሳውቀው(እንዲያነቃው)"
#ሽይኽ ዘይድ አል መድኸሊ ረሂምሁሏህ እንዲህ አሉ ፡
"ለማንኛውም የሞቀ ውሃ በፍሳሽ ትቦዎችም ይሁን በመሬት ላይ አይደፋም ምክኒያቱም መሬት በነዋሪዎች የተሞላች ነች ምናልባትም በጂኖች አለም ወይም በትንንሽ ፍጡሮች ላይ ያርፋል በዚህም ለበቀል ይነሳሱና ይይዙታል።ስለዚህ አንድ ሰው የሞቀን ውሃ መድፋት ከፈለገ በቀዝቃዛ ውሃ ቅዝቃዜው የማያስቸግር እስኪሆን ያብርደው ከዛም ከፈለገ የፍሳሽ ትቦዎች ውስጥ ከፈለገ መሬት ላይ ያፍሠው" ንግግራቸው እዚህ ጋር አለቀ ረሂመሁሏህ.

#ጉዳዩ አደገኛ ነው ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ ለወንድሞቻችሁ ለእህቶቻችሁ ለእናቶቻችሁ አድርሱላቸው ስንትና ስንት እህቶች በዚህ ሰበብ ችግር ውስት ይገባሉ ፓስታ የቀቀሉበትን ውሃ አውጥተው በመድፋት !

Copied

@yasin_nuru @yasin_nuru

የቴሌግራም መክተባዎች

• የኢብኑ ተይሚያህ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/abntaymia3

• የኢብኑል ቀዪይም ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbibnalqaim

• የኢማም ኢብኑ ረጀብ ኪታቦች
www.tg-me.com/abnrajab2

• የኢማም ኢብኑ ከሢር ኪታቦች
www.tg-me.com/abnkthyr

• የኢማም ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ኪታቦች
http://www.tg-me.com/ktbMBinAbdulwahab

• የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ባዝ ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbEmambinbaz

• የሸይኽ ዐብዱላህ ብኑ ሑመይድ ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbAlulamapdf/47

• የሸይኽ ሙሐመድ አልአሚን አሺንቂጢ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbalshengiti

• የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አሰዕዲ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbbinsaadi

• የሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልባኒ ኪታቦች
www.tg-me.com/Aallbany/3328

• የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አል-ሙዐሊሚ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbalmalmai

• የሸይኽ ሐፊዝ ብኑ አሕመድ አልሐከሚ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/hafithalhakmiy

• የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሷሊሕ አልዑሠይሚን ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbmB_othaimen

• የሸይኽ ዐብዱላህ አልጂብሪን ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbbinJebreen

• የሸይኽ ዶር. ሷሊሕ አልፈውዛን ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbalfawzan

• የሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ ኪታቦች
http://www.tg-me.com/Ktbalabbaad

• የሸይኽ በክር አቡ ዘይድ ኪታቦች
www.tg-me.com/bkrabzd

• የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አልበራክ ኪታቦች
www.tg-me.com/mAlBraak/7592

• የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ አራጂሒ ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbAlRajhi

• የሸይኽ ዐብዱል ከሪም ኹዶይር ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbAlkhudheir

• የሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ አደም ኪታቦች
www.tg-me.com/Ktbaletiopi

• የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ ኪታቦች
www.tg-me.com/Salehshaikh/2052

• የሸይኽ ሷሊሕ አልዑሶይሚ ኪታቦች
www.tg-me.com/mnmhln

• የሸይኽ ሰዒድ አልቀሕጧኒ ኪታቦች
http://www.tg-me.com/Ktbbinwahaf

• የሸይኽ ዐብዱ ረዛቅ አልበድር ኪታቦች
www.tg-me.com/Ktbalbadr


@yasin_nuru @yasin_nuru
🔖ወርቃማ የዙል-ሒጃ 10 ቀናትና
መልካም ስራ ላይ መበርታት


بسم الله الرحمن الرحيم
فضل عشر ذي الحجة ووصايا لمن أدركها

ምስጋናና ውዳሴ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን ሰላትና ሰላም የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነቢዩ ሙሐመድ ላይ ይስፈን አላህ በእዝነቱ ለባሮቹ የተለያዩ ወደርሱ የሚያቃርቡ ልዩ የመልካም ስራ እድሎችን ፈጥሯል በዚህም ተፎካካሪዎች እንዲፎካከሩ፣ ተሽቀዳዳሚዎችም እንዲሽቀዳደሙ ገፋፍቷል የስው ልጅ ነፍስ ሁሌ አንድ አይነት ሁኔታ ላይ ስትሆን ትሰለቻለች አዲስ ነገር ስታገኝም ትነቃቃለች ይህንም ባህሪይ ሽሪዓችን ለነፍሲያ በሚገባ ጠብቆላታል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው የሚከተለውን ብለዋል

" ነፍስ፥ አንዳንዴ ለመልካም ስራ ትነቃቃለች አንዳንዴም ትሰለቻለች ንቃትና ከፍተኛ ፍላጎት ባላት ጊዜ ኸይርን ስራ በሚገባ አሰሯት በታከተችና በሰለቸች ጊዜ ግዴታ ለሆኑ ነገሮች እንጂ አትጫኗት" ብለዋል

🔹ይህ በጌታው በሚገባ የሚያምንና ስሜቱንም የማይከተልን ሰው ነፍስ ለማለት እንጂ በመሰረቱ ስሜቱን የሚከተልና የጌታውን ህግ የሚጥስን ሰው ነፍስ አይመለከትም!

🔸መንፈስን ለማደስና ነፍስንም መልካም ነገር ላይ ለማነቃቃት አላህ በየጊዜው በመጠነኛ ልፋትና ጥረት ከፍተኛ ምንዳ የሚያስገኙ እድሎችን አስገኝቷል ይህንንም እድል ፈጥነን እንድንጠቀም ትሩፋቱን ገልጿል

ከነዚህም እድሎች መካከል አንዱ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያ 10 ቀናቶች ናቸው ቡኻሪይና ሌሎችም ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል

[ما من أيام العمل الصالح فيها أحب إلى الله من هذه الأيام يعني أيام العشر .... الحديث]

"ከዙል ሒጃ 10 ቀናት የበለጠ መልካም ስራ ከመቼውም በላይ አሏህ ዘንድ ውድ የሚሆንበት ቀን የለም"

🔸እነሆ አዱኒያ አጭር ናት እድሜያችንም አጭር ነው ከአጭሯ ዱኒያ የቀረውም በጣም አጭር ከአጭሯ ዱኒያ የአንተ ድርሻ ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ነው ይህም እውነታ ቀደም ሲል በቁርኣን ተነግኖራል

[قُل متاعُ الحياةِ الدنيا قَليل والآخِرةُ خَيرٌ لِمَن اتَقى....] النساء 77

" ነቢዩ ሙሐመድ ሆይ ንገራቸው፥ የዱኒያ ህይወትና መጠቃቀሚያዋ አጭርና ጥቂት ነው የአኼራ ህይወትም (አሏህን ለሚፈሩ) ከዱኒያ የተሻለ ነው" "ሱረቱንኒሳእ 77"

አጭርና ጥቂት ከሆነችዋ የዱኒያ ህይወት የቀረው ጥቂቱ መሆኑንም ሲነግረንም አሏህ እንዲህ ብሏል

(اقتَرَبَت الساعةُ وانشَقَّ القَمَر)

" ቂያማ ተቃረበች ጨረቃም ለሁለት ተከፈለች “ ሱረቱልቀመር 1

(اقتَرَبَ للنَّاسِ حِسابُهم)

“ የሰው ልጆች መተሳሰቢያና መመርመሪያ ጊዜያቸው ተቃረበ እነሱ ግን ቸልታና መዘናጋት ላይ ናቸው
” ሱረቱል አንቢያ 1

▪️አጭሩ እድሜያችን መች እንደሚቋጭ አናውቅምና ሁሌም ራስን ለሞት ማዘጋጀት ብልህነት ነው
ለሞት መዘጋጃትም፥ መልካምን ስራ ተሽቀዳድሞ በመስራት ከወንጀል በመራቅ አኼራን በመናፈቅ ነው

▪️ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም የውርደትም ይሁን የስኬት ሰበቡ የጊዜ አጠቃቀም ነው፣በዱኒያም በአኼራ በማይጠቅም ነገር ጊዜና ገንዘባችንን የምናባክን ሰዎች:-

ቀጣይ ምርጥ 10 የዙልሒጃ ቀናትን በአግባቡና ወደ አላህ በሚያቃርብ ስራ ለማሳለፍ ከወዲሁ ነፍሲያችሁን አሸንፉ!
ሌት-ከቀን በኔት ጊዜ፣ ገንዘብና አይናችሁን የምታቃጥሉ፥ አሏህን ፍሩ እራሳችሁንም ፈትሹ ከማይጠቅም ወሬና ተግባርም ራቁ መለከል_መውት ከመምጣቱ በፊትም ከእንቅልፋችሁ ንቁ! የአኼራው ድልድይ/ ሲራጥ ላይ እንዳትወድቁ አላህ ከሚጠላው ስራ በሙሉ በመራቅ ቁርኣን ቅሩ ዘክሩ የኔትና የወሬን ፍቅር በአላህ ውዴታ ቀይሩ!

💥 ውድ የአሏህ ባሮች

አላህ ዘንድ ውድ የሆኑ 10 ቀናትን:-

▪️አምስት ወቅት ሰላቶችን በወቅታቸው፣ ከፊትና ከኋላ የሚሰገዱ ሱናችን ከመጠበቅ ጋር፣ ወንዶች በጀማዓ በመስገድ፣

▪️ቁርኣን በመቅራት፣ ዚክር፣ ዱዓ እንዲሁም ተክቢራ በማብዛት፣

▪️የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና የታመሙን በመጠየቅ፣

▪️ከዙልሂጃ 1 ጀምሮ እስከ 9ኛው ቀን በመጾምና የጾሙ ሰዎችንም በማስፈጠር ወዘተ አሏህ የሚወዳቸው መልካም ስራዎችን በመስራት እናሳልፋቸው

ከላይ እንደተጠቀሰው የሰው ልጅ እድሜ በጣም አጭር ነው አሏህ ኸይርን የሻለት ሰው ግን በአጭር ጊዜ ብዙ ቁም ነገር መስራት ይችላል::
በነዚህ ውድ ቀናት ለአኼራችን ስንቅ እንሸምት በጣም ድንቅና የተከበሩ ቀናት ናቸው አሏህ በተከበረው ቁርኣኑ በነዚህ ቀናት ምሏል አሏህ ትልቅ ነው በትልቅና ጠቃሚ ነገር እንጂ አይምልም! ነቢያችንም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ቀናት መልካም ስራ ላይ እንደንበረታ ገፋፍተውናል
እራሳቸውም ቀናቱን በመልካም ስራዎች ያሳልፏቸው እንደነበረ ተዘግቧል

እነሆ ኢማሙ አሕመድና ሌሎችም ዘግበውት አልባኒይ ሰሒህ ባሉት ሐዲስ የምእምናን እናት ሐፍሳ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብለዋል "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዓሹራ፣ የዙልሒጃ 10 ቀናትና በየወሩ 3ቀን መጾምን አይተውም ነበር" ብላለች

▪️እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ነጥብ ቢኖር እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ " ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዙልሒጃ10 ቀናትን ጾመው አያውቁም" ብላ የተናገረችበት አጋጣሚ አለ ይህ ማለት እሷ እስከ ምታውቀው ድረስ ለማለት ነው ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘጠኝ ሚስቶች ነበር ያሏቸው እሷ ቤት በሚያድሩበት እለት ጾመው አለማየቷን ነው የሚያሳየው እንጂ በጭራሽ አይጾሙም ነበረ ማለት አይደለም።ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር አመላክተው እራሳቸው ወደ ኋላ አይቀሩም!

ይህ በእንዲህ እንዳለ የኡሱል ትምህርት ዘርፍ ዑለሞች እንደጠቀሱት አንድን ጉዳይ በተመለከተ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አድርገዉታል ወይስ አላደረጉትም የሚል ውዝግብ ከተነሳ ማድረጋቸው የተጠቀሰው በትክክለኛ ሰነድ መሆኑ ከተረጋገጠ ቅድሚያ የሚሰጠውና ተቀባይነት የሚያገኘው እሱ ነው ምክንያቱም አላደረጉም ያለው አካል የማያውቀውን ነገር እርሱ በማወቁ ጉዳዩ ላይ ይበልጥ አዋቂው ቅድሚያ ይሰጠዋል:: በመሆኑም ከነቢዩ ባለቤቶች መሀል አንደኛዋ ጾመዋል ስትል ሌላኛዋ ደግሞ አልጾሙም ካለች ተቀባይነትና ቅድሚያ የሚያገኘው ጾመዋል ያለችዋ ሃሳብ ይሆናል ማለት ነው።
ሰሓቦችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም ፈለጋቸውን ይከተሉ የነበሩ ደጋግ ቀደምቶች ትልቁ ጭንቃቸውና የህይወት ዓላማቸው "ዒባዳ" ወይም መልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ነበር ለዚህም ነው ከነሱ መካከል አንዱ እንዲህ ያሉት

" በዱኒያ ጉዳይ አንድ ሰው ሊቀድምህ ቢፈልግ መንገዱን አስፋለት በአኼራ ጉዳይ ግን ማንም እንዳይቀድምህ! "
አሁን አሁን እየዘነጋን ኖሮ እንጂ አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል መክሮን ነበር

(سابقوا إلى مغفرة من ربكم وجنة)

" ተሽቀዳደሙ……..ወደ ጌታህቹ ምህረትና ወደ ጀነት" ሱረቱልሀዲድ 21 አላህ መልካሙን ሁሉ ካገራላቸው እርሱ ከሚጠላው ነገር በሙሉ ከጠበቃቸው ባሮቹ ያድርገን!

@yasin_nuru @yasin_nuru
የአስርቱ_የዙልሂጃ_ቀናት_ትሩፋቶች.pdf
333.4 KB
ነገ ረቡዕ ወይም ሐሙስ የሚጀምሩት አስሩ የዙልሂጃ ቀናት

ረሱል ﷺእንዲህ ብለዋል፦

ما مِن أيّامٍ العملُ الصّالحُ فيها أحبُّ إلى اللَّهِ من هذِهِ الأيّام يعني أيّامَ العشرِ، قالوا: يا رسولَ اللَّهِ، ولا الجِهادُ في سبيلِ اللَّهِ؟ قالَ: ولا الجِهادُ في سبيلِ اللَّهِ، إلّا رَجلٌ خرجَ بنفسِهِ ومالِهِ، فلم يرجِعْ من ذلِكَ بشيءٍ

“በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም። ‘በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?’ ተባሉ። እርሳቸውም ‘ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም’ አሉ።”

📚 ቡኻሪ 969
 
በዒባዳ ላይ እንጠናከር::

ለምታቁት ሰው ሼር አርጉት

@yasin_nuru              @yasin_nuru
2025/07/04 07:21:37
Back to Top
HTML Embed Code: