አስተውል!
~ ሰዎች ዘንድ ለመወደድ ስትለፋ ጌታህ ዘንድ እንዳትጠላ ተጠንቀቅ።
~ ለምትወዳቸው ሰወች ክብር ስታበዛ የጌታህን ክብር እንዳትነካ ተጠንቀቅ።
~ ሰወችን በመውደድ ብቻ ስትጠመድ የጌታህን ውዴታ እንዳትነፈግ ፍራ! ጥላቸው ማለት አይደለም ውዴታህ በልክ ይሁን!
~ እውነት ለመናገር ከሰወች ጥቅምን አትፈልግ! ሰወችን ለማስደሰት አትዋሽ! ለህሊናህ እረፍት አስበህ እውነተኛ ሁን!
~ የራስክን ደስታ ለማሞቅ ለሌሎች ሃዘን ሰበብ አትሁን! በሌሎች ደስታ ተደሰት! ከምቀኝነት እራቅ!
~ ለጥፋት መሆንን እንጂ መባልን አትፍራ! ሆኖ ለመገኘት እንጂ ለመባል አትድከም።
~ ፍርድ ለመስጠት ከመወሰንህ በፊት ዳኛ ለመሆን አቅሙ እንዳለክ እራስክን ጠይቅ።
~ ለመውቀስ ከመቸኮል ለማጣራት ሞክር ! መልስ ከመስጠትህ በፊት ጥያቄውን አስተንትን!
~ ማንነትህን ለማሳወቅ በአፍህ ከመናገር ይልቅ ስራበት! ተግባርህ ያስረዳ!
~ መልካም ለመሆን አትምረጥ። ለሁሉም መልካም ሁን አትጎዳበትም።
~ ክብርን ለማግኘት ክብር ከሌለው ተግባር ተቆጠብ!
~ ሀቅን እንጂ ሰወችን አትከተል።
~ መኖርህን ስታይ መሞትህንም አትርሳ! ኖረህም የሚጠቅምህን ስትሞትም የሚከተልህን ስራ!!
JOIN: @yasin_nuru

🔖የጁምዓ ሰላት ሸሪዓዊ ብይኑና ማስረጃዎቹ🔖
🌂የጁምዓ ሰላት በያንዳንዱ ሙስሊም በሆነ ወንድ ላይ ግዴታ ነው፡፡
አላህ እንዲህ ይላል፡-
‹‹እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በዐርብ ቀን ለስግደት ጥሪ በተደረገ ጊዜ ወደ አላህ ማውሳት ኺዱ፡፡ መሸጥንም ተዉ፡፡›› ጁምዓ 9
ነብዩም (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹አቅመ አዳም በደረሰ በያንዳንዱ ሰው ጁምዓ ግዴታ (ዋጂብ) ነው››[ነሳኢይ 1371]
በሌላም ሐዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹ሠዎች ጁምዓን ከመተው የማይታቀቡ ከሆነ አላህ ልቦናቸውን ያሽግና ዝንጉዎች ይሆናሉ››[ሙስሊም 865]
☄ጁምዓ ግዴታ የሚሆንባቸው ሰዎች☄
ጁምዓ በእያንዳንዱ ወንድ፣ ከባርነት ነፃ በሆነ፣ አቅመ አዳም በደረሰ፣ የአእምሮ ጤነኛ በሆነና ወደ ጁምዓ የመምጣት ችሎታ ባለው ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡፡ በአንፃሩ በባሪያ፣ ሴት ልጅ፣ ያልደረሰ ልጅ፣እብድ፣ህመምተኛና መንገደኛ ላይ ግዴታ አይደለም፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹ጁምዓን በህብረት መስገድ ከአራት ሰዎች በስተቀር በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው፡- ባሪያ፣ ሴት ልጅ፣ ህፃንና ህመምተኛ››[አቡዳውድ 1ዐ54]
መንገደኛ የሆነ ሰው ላይ ጁምዓ ግዴታ አይደለም፡፡ ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) ባደረጓቸው ጉዞዎች ላይ አንድም ቀን ጁምዓ አልሰገዱም:: ነብዩ (ﷺ) ባደረጉት የመሰናበቻ ሐጅ ላይ ጁምዓ ገጥሟቸው ነበር ነገር ግን የሰገዱት ዙህርና ዓስርን በማቆራኘት እንጂ ጁምዓን አልነበረም፡፡ ይሁንና አንድ መንገደኛ ሙስሊምች ጁምዓ የሚሰግዱበት ቦታ ላይ በአጋጣሚ ቢገኝ ከነሱ ጋር አብሮ ጀምዓ መስገድ አለበት፡፡ ባሪያ፣ ሴት፣ልጅ፣ህፃን፣ህመምተኛ ወይም መንገደኛ ጁምዓ ተገኝተው ከሰገዱ ዙህርን መስገድ አይጠበቅባቸውም::
የጁምዓ ወቅት🌤
የጁምዓ ሰላት ወቅት ልክ እንደ ዙህር ፀሀይ ወደ ምዕራብ ዘንበል ካለችበት ወቅት አንስቶ የአንድ ነገር ከፀሐይ የሚያገኘው ጥላ በቁመቱ ልክ እስከሚሆን ድረስ ነው፡፡ አነስ ኢንብ ማሊክ እንዳሉት
‹‹ነብዩ (ﷺ) ጁምዓ የሚሰግዱት ፀሐይ ዘንበል ስትል ነበር››[ቡኻሪ 9ዐ4]
✔በዚህ ወቅት ጁምዓ መስገድ የሰሃቦች የተለመደ ተግባር እንደነበርም ተዘግቧል፡፡ በዚህ መሰረት ወቅቱ ከማብቃቱ በፊት አንድ ረከዓ የመስገጃ ያህል ጊዜ ላይ የደረሰ ጁምዓን ይሰግዳል፡፡ ወቅቱ ያለፈበት ከሆነ ግን መስገድ ያለበት ዙህርን ነው፡፡
📔የጁምዓ ኹጥባ📚
ኹጥባ ነብዩ (ﷺ) በሰገዷቸው ጁምዓዎች ሁሉ የፈፀሙትና ትተውት የማያውቁ በመሆኑን የጁምዓ መሰረት ነው፡፡ ስለዚህ ጁምዓ ያለ ኹጥባ መሰረተቢስ ነው:: በጁምዓ የሚደረጉት ኹጥባዎች ሁሉት ኹጥባዎች(ሁለት ኹጥባዎች የሚባሉት ኢማሙ አንደኛውን ኹጥባ ካደረገ በኋላ በመሃል ተቀምጦ ለሁለተኛ ጊዜ ቆሞ የሚያደርጋቸው ናቸው)ሲሆኑ መስፈርቱም ከሰላት አስቀድሞ ማድረግ ነው፡፡
🔖የኹጥባ ሱናዎች🔖
ለሙስሊሞች ዱንያዊና ሀይማኖታዊ ጉዳዮች መስተካከልና ለመሪዎች ዱዓ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡ ነብዩ (ﷺ) የጁምዓ ዕለት ኹጥባ ሲያደርጉ በጣታቸው ወደ ላይ እየጠቆሙ ዱዓ ሲያደርጉ ሰዎችም አሚን ይሉ ነበር፡፡
ኹጥባና ሰላት በአንድ ሰው ቢፈፀሙ ይወደዳል፤ ኹጥባ አድራጊው በተቻለ አቅም ድምፁን ከፍ ቢያደርግ የተወደደ ነው፤ ኹጥባን ቆሞ ማድረግ የተወደደ ነው፡፡
ጃቢር ኢብን ሰሙራ እንዳሉት
‹‹ነብዩ (ﷺ) ቆመው ኹጥባ ካደረጉ በኋላ በመሀል ተቀምጠው ከዚያ እንደገና ቆመው ያደርጉ ነበር››[ሙስሊም 862]
ኹጥባን አጠር ማድረግና የሁለተኘውን ኹጥባ ከመጀመሪያው ይበልጥ አጠር ማድረግ፡፡ ዓማር ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ
‹‹የአንድ ሰው ኹጥባ አጠር ማለቱና ሰላቱን ረዘም ማድረጉ የአዋቂነቱ ምልክት ነው፡፡ ሰላትን አስረዝሙ ኹጥባን አሳጥሩ››[ሙስሊም 869]
ኹጥባ አድራጊው ወደ ህዝቦች ዞር ብሎ ሠላምታን ማቅረብ፡- ጃቢር እንዳሉት
‹‹ ነብዩ (ﷺ) ሚንበር[የኹጥባው መድረክ (ምኹራብ)] ላይ ሲወጡ ሠላምታ ያቀርቡ ነበር”
አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪያጠናቅቅ ሚንበር ላይ መቀመጥ ኢብን ዑመር እንዳሉት ‹‹ነብዩ (ﷺ) በሚንበር ላይ ወጥተው አዛን አድራጊው አዛኑን እስኪጨርስ ሚንበር ላይ ይቀመጡና ሲጨርስ ተነስተው ኹጥባ ያደርጉ ነበር››
🔊በጁምዓ ክልክል የሆኑ ተግባራት🔊
✔ ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ መናገር አይፈቀድም፡፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ
‹‹በጁምዓ ቀን ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ የተናገረ መፅሐፍ እንደተሸከመ አህያ ነው››[አህመድ 1/23ዐ]
በሌላም ሀዲስ እንዲህ ብለዋል
‹‹ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ለጓደኛህ ዝም በል ካልክ ከንቱ ንግግር ተናገርኽ››
በተቀመጡ ሰዎች ትከሻ በኩል በመሸጋገር መተላለፍ :
✔ ነብዩ (ﷺ) የሰዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ሲያልፍ ለተመለከቱት ሰው ‹‹ተቀመጥ ሰውን አስቸገርክ›› ብለውታል:: በዚህ ተግባር ሰውን ማስቸገርና ኹጥባን የሚያደምጥን ማዘናጋትም ይፈጠራል:: ኢማሙ ግን የሠዎችን ትከሻ እየተሸጋገረ ካልሆነ ወደ ቦታው የሚደርስበት ሌላ አማራጭ ከሌለው ይህን ሊፈፅም ይችላል፡፡
ሁለት ሰዎችን በመለየት በመካከላቸው መቀመጥም አይፈቀድም፡፡ ነብዩ(ﷺ) እንዲህ ብለዋል
✔የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በጊዜ ወደ ጁምዓ የሄደ ከዚያ በኋላ በሰዎች መካከል ሳይለይ አላህ የወሰነለትን የሰገደ በዕለቱና በሚቀጥለው ጁምዓ መካከል የሚፈፀሙ ኃጢአቶች አላህ ይቅር ይለዋል።
[ቡኻሪ 91ዐ]
🔖ጁምዓ ላይ መድረስ የሚቻለው በምንድን ነው?
💡ከኢማሙ ጋር አንድ ረከዓ ከደረሰ ጁምዓን በማግኘቱ የቀረውን አንድ ረከዓ ይጠበቅበታል:: ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ከጁምዓ አንድ ረከዓን የደረሰ ሰላት ላይ ደርሷል›› ኢማሙ ላይ የደረሰው ግን ከአንድ ረከዓ ባነሰ ከሆነ መሙላት ያለበት ዙህር ሰላትን ነው፡፡
💡የጁምዓ ሱና ሰላት💡
✔ከጁምዓ በፊት የሚሰገድ መደበኛ ሱና የለም፡፡ ነገር ግን ወቅቱ ከመድረሱ በፊት መደበኛ ያልሆነ ሱና ቢሰግድ ምንም ችግር የለውም ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) በጥቅሉ ሱና መስገድን አበረታተዋል፡፡ ከጁምዓ በኋላ ግን መደበኛ የሆኑ ሁለት፣ አራት ረከዓ ወይም ስድስት ረከዓ ሱናዎችን እንደሁኔታው ሊሰገድ ይችላል፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ባስተላለፉት ሀዲስ
‹‹ነብዩ (ﷺ) ከጁምዓ በኋላ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር››[ቡኻሪ 937 ሙስሊም 882]
በሌላ ሀዲስ ደግሞ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል
‹‹ ከጁምዓ በኋላ አራት ረከዓ ሱናዎችን ስገዱ››[ሙስሊም 881]
ኢብን ዑመርም ከጁምዓ በኋላ ስድስት ረከዓዎችን ይሰግዱ እንደነበር ‹‹ነብዩ ይፈፅሙት ነበር››[አቡዳውድ 113ዐ]
✔እንዳሉ አቡዳውድ ዘግበዋል፡፡ በዚህ መሰረት ከጁምዓ በኋላ የሚሰገድ መደበኛ ሱና ከፍተኛው ስድስት አነስተኛው ሁለት መሆኑን እንረዳለን::
🔖የጁምዓ ሰላት አሰጋገድ🔖
🎯የጁምዓ ሰላት ድምፅ ከፍ በመደረግ የሚሰገዱ ሁለት ረከዓዎች እንደሆኑ በነብዩ (ﷺ) ተግባርና በዑለማዎች ስምምነት የተረጋገጠ ነው፡፡ በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል ጁምዓ በሁለተኛው ረከዓ ደግሞ ሱረቱል ሙናፊቁን[ሙስሊም 877] ወይም በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል አዕላ በሁለተኛው ሱረቱል ጋሺያ እንደሚነበብም ነብዩ (ﷺ) በተግባር አስተምረዋል፡፡[ሙስሊም 878]
@yasin_nuru @yasin_nuru

የሞቀ ውሃ ስንደፋ ቢስሚላህ እንበል?
#ሸይኽ ኢብን ባዝ ተጠየቁ ፡ ሙቅ ውሃን በምናፈስበት ጊዜ ቢስሚላህ እንላለን? ይህም ጂን ቦታው ላይ ይኖራል ብሎ በመፍራት ነው
መልስ፡
"አዎን! ቢስሚላህ ይበል ምን አልባት ቦታው ላይ ጂን ካለ እንዲነቃ ለማድረግ ነው" ከዛም ሽይኹ እንዲህ አሉ" በርግጥም በአንድ ወቅት አንድን ሰው ጂን ይዞት በሚቀራበት ቦታ ተገኝቼ ነበር
#ሩቃ የሚያደርገው ሰው በሰውየው ላይ ለተደበቀው ጂኒ
"ለምን ያዝከው "አለው
#ጂንውም "የሞቀ ውሃ በአንዱ ልጄ ላይ ደፋና ገደለው "አለ
#የሚቀራው ሰውዬ ደግሞ "እሱ ልጅህ በቦታው መኖሩን ስላላወቀ ነው" አለው
#ጂኒው ደግሞ "ለምን ቢስሚላህ አይልም ነበር እንዲያሳውቀው(እንዲያነቃው)"
#ሽይኽ ዘይድ አል መድኸሊ ረሂምሁሏህ እንዲህ አሉ ፡
"ለማንኛውም የሞቀ ውሃ በፍሳሽ ትቦዎችም ይሁን በመሬት ላይ አይደፋም ምክኒያቱም መሬት በነዋሪዎች የተሞላች ነች ምናልባትም በጂኖች አለም ወይም በትንንሽ ፍጡሮች ላይ ያርፋል በዚህም ለበቀል ይነሳሱና ይይዙታል።ስለዚህ አንድ ሰው የሞቀን ውሃ መድፋት ከፈለገ በቀዝቃዛ ውሃ ቅዝቃዜው የማያስቸግር እስኪሆን ያብርደው ከዛም ከፈለገ የፍሳሽ ትቦዎች ውስጥ ከፈለገ መሬት ላይ ያፍሠው" ንግግራቸው እዚህ ጋር አለቀ ረሂመሁሏህ.
#ጉዳዩ አደገኛ ነው ሙስሊሞች ሆይ ነቃ በሉ ለወንድሞቻችሁ ለእህቶቻችሁ ለእናቶቻችሁ አድርሱላቸው ስንትና ስንት እህቶች በዚህ ሰበብ ችግር ውስት ይገባሉ ፓስታ የቀቀሉበትን ውሃ አውጥተው በመድፋት !
Copied

•
የቴሌግራም መክተባዎች
• የኢብኑ ተይሚያህ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/abntaymia3
• የኢብኑል ቀዪይም ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbibnalqaim
• የኢማም ኢብኑ ረጀብ ኪታቦች
www.tg-me.com/abnrajab2
• የኢማም ኢብኑ ከሢር ኪታቦች
www.tg-me.com/abnkthyr
• የኢማም ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ኪታቦች
http://www.tg-me.com/ktbMBinAbdulwahab
• የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ባዝ ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbEmambinbaz
• የሸይኽ ዐብዱላህ ብኑ ሑመይድ ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbAlulamapdf/47
• የሸይኽ ሙሐመድ አልአሚን አሺንቂጢ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbalshengiti
• የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አሰዕዲ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbbinsaadi
• የሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልባኒ ኪታቦች
www.tg-me.com/Aallbany/3328
• የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አል-ሙዐሊሚ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbalmalmai
• የሸይኽ ሐፊዝ ብኑ አሕመድ አልሐከሚ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/hafithalhakmiy
• የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሷሊሕ አልዑሠይሚን ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbmB_othaimen
• የሸይኽ ዐብዱላህ አልጂብሪን ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbbinJebreen
• የሸይኽ ዶር. ሷሊሕ አልፈውዛን ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbalfawzan
• የሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ ኪታቦች
http://www.tg-me.com/Ktbalabbaad
• የሸይኽ በክር አቡ ዘይድ ኪታቦች
www.tg-me.com/bkrabzd
• የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አልበራክ ኪታቦች
www.tg-me.com/mAlBraak/7592
• የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ አራጂሒ ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbAlRajhi
• የሸይኽ ዐብዱል ከሪም ኹዶይር ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbAlkhudheir
• የሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ አደም ኪታቦች
www.tg-me.com/Ktbaletiopi
• የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ ኪታቦች
www.tg-me.com/Salehshaikh/2052
• የሸይኽ ሷሊሕ አልዑሶይሚ ኪታቦች
www.tg-me.com/mnmhln
• የሸይኽ ሰዒድ አልቀሕጧኒ ኪታቦች
http://www.tg-me.com/Ktbbinwahaf
• የሸይኽ ዐብዱ ረዛቅ አልበድር ኪታቦች
www.tg-me.com/Ktbalbadr
@yasin_nuru @yasin_nuru
የቴሌግራም መክተባዎች
• የኢብኑ ተይሚያህ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/abntaymia3
• የኢብኑል ቀዪይም ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbibnalqaim
• የኢማም ኢብኑ ረጀብ ኪታቦች
www.tg-me.com/abnrajab2
• የኢማም ኢብኑ ከሢር ኪታቦች
www.tg-me.com/abnkthyr
• የኢማም ሙሐመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ ኪታቦች
http://www.tg-me.com/ktbMBinAbdulwahab
• የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ ብኑ ባዝ ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbEmambinbaz
• የሸይኽ ዐብዱላህ ብኑ ሑመይድ ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbAlulamapdf/47
• የሸይኽ ሙሐመድ አልአሚን አሺንቂጢ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbalshengiti
• የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አሰዕዲ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbbinsaadi
• የሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልባኒ ኪታቦች
www.tg-me.com/Aallbany/3328
• የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አል-ሙዐሊሚ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/ktbalmalmai
• የሸይኽ ሐፊዝ ብኑ አሕመድ አልሐከሚ ኪታቦች
https://www.tg-me.com/hafithalhakmiy
• የሸይኽ ሙሐመድ ብኑ ሷሊሕ አልዑሠይሚን ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbmB_othaimen
• የሸይኽ ዐብዱላህ አልጂብሪን ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbbinJebreen
• የሸይኽ ዶር. ሷሊሕ አልፈውዛን ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbalfawzan
• የሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድ ኪታቦች
http://www.tg-me.com/Ktbalabbaad
• የሸይኽ በክር አቡ ዘይድ ኪታቦች
www.tg-me.com/bkrabzd
• የሸይኽ ዐብዱ ረሕማን አልበራክ ኪታቦች
www.tg-me.com/mAlBraak/7592
• የሸይኽ ዐብዱል ዐዚዝ አራጂሒ ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbAlRajhi
• የሸይኽ ዐብዱል ከሪም ኹዶይር ኪታቦች
www.tg-me.com/ktbAlkhudheir
• የሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ አደም ኪታቦች
www.tg-me.com/Ktbaletiopi
• የሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ ኪታቦች
www.tg-me.com/Salehshaikh/2052
• የሸይኽ ሷሊሕ አልዑሶይሚ ኪታቦች
www.tg-me.com/mnmhln
• የሸይኽ ሰዒድ አልቀሕጧኒ ኪታቦች
http://www.tg-me.com/Ktbbinwahaf
• የሸይኽ ዐብዱ ረዛቅ አልበድር ኪታቦች
www.tg-me.com/Ktbalbadr
@yasin_nuru @yasin_nuru
🔖ወርቃማ የዙል-ሒጃ 10 ቀናትና
መልካም ስራ ላይ መበርታት
بسم الله الرحمن الرحيم
فضل عشر ذي الحجة ووصايا لمن أدركها
ምስጋናና ውዳሴ ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ይሁን ሰላትና ሰላም የሰው ልጆች ሁሉ ምርጥ በሆኑት በነቢዩ ሙሐመድ ላይ ይስፈን አላህ በእዝነቱ ለባሮቹ የተለያዩ ወደርሱ የሚያቃርቡ ልዩ የመልካም ስራ እድሎችን ፈጥሯል በዚህም ተፎካካሪዎች እንዲፎካከሩ፣ ተሽቀዳዳሚዎችም እንዲሽቀዳደሙ ገፋፍቷል የስው ልጅ ነፍስ ሁሌ አንድ አይነት ሁኔታ ላይ ስትሆን ትሰለቻለች አዲስ ነገር ስታገኝም ትነቃቃለች ይህንም ባህሪይ ሽሪዓችን ለነፍሲያ በሚገባ ጠብቆላታል ነቢያችን ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በሐዲሳቸው የሚከተለውን ብለዋል
" ነፍስ፥ አንዳንዴ ለመልካም ስራ ትነቃቃለች አንዳንዴም ትሰለቻለች ንቃትና ከፍተኛ ፍላጎት ባላት ጊዜ ኸይርን ስራ በሚገባ አሰሯት በታከተችና በሰለቸች ጊዜ ግዴታ ለሆኑ ነገሮች እንጂ አትጫኗት" ብለዋል
🔹ይህ በጌታው በሚገባ የሚያምንና ስሜቱንም የማይከተልን ሰው ነፍስ ለማለት እንጂ በመሰረቱ ስሜቱን የሚከተልና የጌታውን ህግ የሚጥስን ሰው ነፍስ አይመለከትም!
🔸መንፈስን ለማደስና ነፍስንም መልካም ነገር ላይ ለማነቃቃት አላህ በየጊዜው በመጠነኛ ልፋትና ጥረት ከፍተኛ ምንዳ የሚያስገኙ እድሎችን አስገኝቷል ይህንንም እድል ፈጥነን እንድንጠቀም ትሩፋቱን ገልጿል
☄ከነዚህም እድሎች መካከል አንዱ የዙል-ሒጃ የመጀመሪያ 10 ቀናቶች ናቸው ቡኻሪይና ሌሎችም ባስተላለፉት ሐዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል
[ما من أيام العمل الصالح فيها أحب إلى الله من هذه الأيام يعني أيام العشر .... الحديث]
"ከዙል ሒጃ 10 ቀናት የበለጠ መልካም ስራ ከመቼውም በላይ አሏህ ዘንድ ውድ የሚሆንበት ቀን የለም"
🔸እነሆ አዱኒያ አጭር ናት እድሜያችንም አጭር ነው ከአጭሯ ዱኒያ የቀረውም በጣም አጭር ከአጭሯ ዱኒያ የአንተ ድርሻ ደግሞ እጅግ በጣም አጭር ነው ይህም እውነታ ቀደም ሲል በቁርኣን ተነግኖራል
[قُل متاعُ الحياةِ الدنيا قَليل والآخِرةُ خَيرٌ لِمَن اتَقى....] النساء 77
" ነቢዩ ሙሐመድ ሆይ ንገራቸው፥ የዱኒያ ህይወትና መጠቃቀሚያዋ አጭርና ጥቂት ነው የአኼራ ህይወትም (አሏህን ለሚፈሩ) ከዱኒያ የተሻለ ነው" "ሱረቱንኒሳእ 77"
አጭርና ጥቂት ከሆነችዋ የዱኒያ ህይወት የቀረው ጥቂቱ መሆኑንም ሲነግረንም አሏህ እንዲህ ብሏል
(اقتَرَبَت الساعةُ وانشَقَّ القَمَر)
" ቂያማ ተቃረበች ጨረቃም ለሁለት ተከፈለች “ ሱረቱልቀመር 1
(اقتَرَبَ للنَّاسِ حِسابُهم)
“ የሰው ልጆች መተሳሰቢያና መመርመሪያ ጊዜያቸው ተቃረበ እነሱ ግን ቸልታና መዘናጋት ላይ ናቸው
” ሱረቱል አንቢያ 1
▪️አጭሩ እድሜያችን መች እንደሚቋጭ አናውቅምና ሁሌም ራስን ለሞት ማዘጋጀት ብልህነት ነው
ለሞት መዘጋጃትም፥ መልካምን ስራ ተሽቀዳድሞ በመስራት ከወንጀል በመራቅ አኼራን በመናፈቅ ነው
▪️ጊዜያችንን በአግባቡ እንጠቀም የውርደትም ይሁን የስኬት ሰበቡ የጊዜ አጠቃቀም ነው፣በዱኒያም በአኼራ በማይጠቅም ነገር ጊዜና ገንዘባችንን የምናባክን ሰዎች:-
☄ቀጣይ ምርጥ 10 የዙልሒጃ ቀናትን በአግባቡና ወደ አላህ በሚያቃርብ ስራ ለማሳለፍ ከወዲሁ ነፍሲያችሁን አሸንፉ!
ሌት-ከቀን በኔት ጊዜ፣ ገንዘብና አይናችሁን የምታቃጥሉ፥ አሏህን ፍሩ እራሳችሁንም ፈትሹ ከማይጠቅም ወሬና ተግባርም ራቁ መለከል_መውት ከመምጣቱ በፊትም ከእንቅልፋችሁ ንቁ! የአኼራው ድልድይ/ ሲራጥ ላይ እንዳትወድቁ አላህ ከሚጠላው ስራ በሙሉ በመራቅ ቁርኣን ቅሩ ዘክሩ የኔትና የወሬን ፍቅር በአላህ ውዴታ ቀይሩ!
💥 ውድ የአሏህ ባሮች
አላህ ዘንድ ውድ የሆኑ 10 ቀናትን:-
▪️አምስት ወቅት ሰላቶችን በወቅታቸው፣ ከፊትና ከኋላ የሚሰገዱ ሱናችን ከመጠበቅ ጋር፣ ወንዶች በጀማዓ በመስገድ፣
▪️ቁርኣን በመቅራት፣ ዚክር፣ ዱዓ እንዲሁም ተክቢራ በማብዛት፣
▪️የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና የታመሙን በመጠየቅ፣
▪️ከዙልሂጃ 1 ጀምሮ እስከ 9ኛው ቀን በመጾምና የጾሙ ሰዎችንም በማስፈጠር ወዘተ አሏህ የሚወዳቸው መልካም ስራዎችን በመስራት እናሳልፋቸው
☄ከላይ እንደተጠቀሰው የሰው ልጅ እድሜ በጣም አጭር ነው አሏህ ኸይርን የሻለት ሰው ግን በአጭር ጊዜ ብዙ ቁም ነገር መስራት ይችላል::
በነዚህ ውድ ቀናት ለአኼራችን ስንቅ እንሸምት በጣም ድንቅና የተከበሩ ቀናት ናቸው አሏህ በተከበረው ቁርኣኑ በነዚህ ቀናት ምሏል አሏህ ትልቅ ነው በትልቅና ጠቃሚ ነገር እንጂ አይምልም! ነቢያችንም ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም በነዚህ ቀናት መልካም ስራ ላይ እንደንበረታ ገፋፍተውናል
እራሳቸውም ቀናቱን በመልካም ስራዎች ያሳልፏቸው እንደነበረ ተዘግቧል
☄እነሆ ኢማሙ አሕመድና ሌሎችም ዘግበውት አልባኒይ ሰሒህ ባሉት ሐዲስ የምእምናን እናት ሐፍሳ ረዲየላሁ ዐንሃ እንዲህ ብለዋል "ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዓሹራ፣ የዙልሒጃ 10 ቀናትና በየወሩ 3ቀን መጾምን አይተውም ነበር" ብላለች
▪️እዚህ ላይ ልብ መባል ያለበት ነጥብ ቢኖር እናታችን ዓኢሻ ረዲየላሁ ዐንሃ " ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የዙልሒጃ10 ቀናትን ጾመው አያውቁም" ብላ የተናገረችበት አጋጣሚ አለ ይህ ማለት እሷ እስከ ምታውቀው ድረስ ለማለት ነው ምክንያቱም ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ዘጠኝ ሚስቶች ነበር ያሏቸው እሷ ቤት በሚያድሩበት እለት ጾመው አለማየቷን ነው የሚያሳየው እንጂ በጭራሽ አይጾሙም ነበረ ማለት አይደለም።ኡመታቸውን ወደ መልካም ነገር አመላክተው እራሳቸው ወደ ኋላ አይቀሩም!
ይህ በእንዲህ እንዳለ የኡሱል ትምህርት ዘርፍ ዑለሞች እንደጠቀሱት አንድን ጉዳይ በተመለከተ ነቢዩ ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም አድርገዉታል ወይስ አላደረጉትም የሚል ውዝግብ ከተነሳ ማድረጋቸው የተጠቀሰው በትክክለኛ ሰነድ መሆኑ ከተረጋገጠ ቅድሚያ የሚሰጠውና ተቀባይነት የሚያገኘው እሱ ነው ምክንያቱም አላደረጉም ያለው አካል የማያውቀውን ነገር እርሱ በማወቁ ጉዳዩ ላይ ይበልጥ አዋቂው ቅድሚያ ይሰጠዋል:: በመሆኑም ከነቢዩ ባለቤቶች መሀል አንደኛዋ ጾመዋል ስትል ሌላኛዋ ደግሞ አልጾሙም ካለች ተቀባይነትና ቅድሚያ የሚያገኘው ጾመዋል ያለችዋ ሃሳብ ይሆናል ማለት ነው።
ሰሓቦችና ተከታዮቻቸው እንዲሁም ፈለጋቸውን ይከተሉ የነበሩ ደጋግ ቀደምቶች ትልቁ ጭንቃቸውና የህይወት ዓላማቸው "ዒባዳ" ወይም መልካም ስራ ላይ መሽቀዳደም ነበር ለዚህም ነው ከነሱ መካከል አንዱ እንዲህ ያሉት
☄" በዱኒያ ጉዳይ አንድ ሰው ሊቀድምህ ቢፈልግ መንገዱን አስፋለት በአኼራ ጉዳይ ግን ማንም እንዳይቀድምህ! "
አሁን አሁን እየዘነጋን ኖሮ እንጂ አላህም በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል መክሮን ነበር
(سابقوا إلى مغفرة من ربكم وجنة)
" ተሽቀዳደሙ……..ወደ ጌታህቹ ምህረትና ወደ ጀነት" ሱረቱልሀዲድ 21 አላህ መልካሙን ሁሉ ካገራላቸው እርሱ ከሚጠላው ነገር በሙሉ ከጠበቃቸው ባሮቹ ያድርገን!

የአስርቱ_የዙልሂጃ_ቀናት_ትሩፋቶች.pdf
333.4 KB
ነገ ረቡዕ ወይም ሐሙስ የሚጀምሩት አስሩ የዙልሂጃ ቀናት❕
ረሱል ﷺእንዲህ ብለዋል፦
ما مِن أيّامٍ العملُ الصّالحُ فيها أحبُّ إلى اللَّهِ من هذِهِ الأيّام يعني أيّامَ العشرِ، قالوا: يا رسولَ اللَّهِ، ولا الجِهادُ في سبيلِ اللَّهِ؟ قالَ: ولا الجِهادُ في سبيلِ اللَّهِ، إلّا رَجلٌ خرجَ بنفسِهِ ومالِهِ، فلم يرجِعْ من ذلِكَ بشيءٍ
“በነዚህ አስር ቀናቶች ውስጥ ከሚፈጸም መልካም ስራዎች በበለጠ መልካም ስራዎች አላህ ዘንድ የተወደዱ የሚሆኑባቸው ቀናት የሉም። ‘በአላህ መንገድ ላይ የሚደረግ ጂሀድም ጭምር?’ ተባሉ። እርሳቸውም ‘ራሱንና ንብረቱን ይዞ ወጥቶ ምንም ያልተመለሰለት ሰው ሲቀር ጂሀድም ከዚህ አይበልጥም’ አሉ።”
📚 ቡኻሪ 969
በዒባዳ ላይ እንጠናከር::
ለምታቁት ሰው ሼር አርጉት

1446ኛው የኢደል አድሀ አረፋ በዓል ግንቦት 29/2017 ዕለተ ጁምአ እንደሚከበር ታወቀ።
የሳኡዲ አረቢያ የስነፈለክ ባለሙያዎች ዛሬ አመሻሽ የዙልሂጃህ ወር አዲስ ጨረቃ ማየታቸውን ተከትሎ በ የኢደል-አድሀ (አረፋ) በዓል ግንቦት 29/2017 በዕለተ ጁምአ ተከብሮ ይውላል።
በዚህም ወርቃማዎቹ 10 ቀናቶች ከነገ ረቡዕ ጀምሮ በመላው ዓለም በሚገኙ ሙስሊሞች በጾም፣በኢባዳና በቅዱሱ የመስጂደል ሀረም በመሰባሰብ የሀጅ ስነስርዓት ያከናውናሉ።

ተመልከት የእስልምናን ውበት‼️
==================
ሱብሐነል'ሏህ‼️
~~
መልዕክተ-ዙል ሒጃ‼️
ክፍል፡ [3]፦ «የአስተራረድ ስነ-ስርአት‼️»
ለእንስሳት ይህን ያክል አዛኝ የሆነ እምነት፤
ለሰው ልጅ ምን ሊያክል ነው⁉️
*****
አንድ ሰው እርድ ሊያርድ ከፈለገ፤
ከአስተራረድ ስነ-ስርአቶች ውስጥ የሚከተሉት ይገኙበታል።
||
"ማረድን ከፈለገ (የሚከተሉት) ነገሮች ይጠበቁበታል፦
① በተሳለ (ስለት ባለው) ቢላዋ (ካራ) ሊያርድ ይገባል።
ምክንያቱም ነብዩ ሶለልላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«ባረዳችሁ ጊዜ እርድን አሳምሩ፤ ከእናንተ አንዳችሁ (የቢላዋውን) ጫፍ ይሳል፤ እርዱን ያሳርፍ።» [ሙስሊም ዘግበውታል]
② እርሷ (የምትታረደዋ እንስሳ)እየተመለከተችው (ቢላዋውን) ላይስል ነው።
(ቢላዋውን) ሊስላት ወይም ሊያሾላት በፈለገ ጊዜ፤
ይህን (መሳሉን ማሾሉን) እንስሳዋ እየተመለከተችው እንዳያደርግ።
ለምን፥ ምክንያቱም እርሷ ስለምትንቀጠቀጥ (ስለምትጨነቅ)።
እርሱ ፊት ለፊቷ (ቢላዋውን) በሳለ ጊዜ፤
በርግጥ ያጨናንቃታል፣ ሊያርዳት እንደሚፈልግ ታውቃለች፤ (በዚህም የተነሳ) ትንቀጠቀጣለች።
ከኢብኑ ዐባስ በተገኘ (ሐዲሥ) ላይ፤
አንድ ግለሰብ (የቢላዋውን) ጫፍ እየሳለ (የሚያርዳትን) ፍየል አጨናነቃት።
ነብዩ ሶለልሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ አሉ፦
«ሁለት ሞቶችን ልትገድላት ትፈልጋለህን
ከምታጨናንቃት በፊት (የቢላዋህን) ጫፍ አስት ስልም ነበርን አሉት።»
[ሶሒሑ ተርጚብ ወትተርሂብ፡ 2265]
እንዲሁም፥ ሌላዋ እየተመለከተች ሊያርዳት አይገባም። ምክንያቱም እርሷ ትንቀጠቀጣለች (በፍርሃት)።
እንዲሁም፥ እህቷ ካየች ትጨነቃለች፣ እየተንቀጠቀጠች ሳለ ትታረዳለች።"
[ሊቃኡ ሸህሪ፡ ኢብኑ ዑሠይሚን፥ ካሴት ቁጥር 44 ]
||
አስባችሁታል ተመልከት የእስልምናን ውበት⁉️
ባልተሳለ ቢላዋ እንዳታርዳት፣ ቶሎ ሩሗ ስለማይወጣ ብዙ ትታገላለች።
ሊያርደኝ ነው ብላ እንዳትጨነቅ፤ ፊት ለፊቷ ቢላዋህን አትሳል።
አንዷ ስትታረድ ሌላኛዋ እንዳትጨነቅ አትመልከት።
ተመልከቱ‼️
እንኳን ለሰብአዊ ፍጡር ለእንስሳ እንኳ ይህንና መሰል ሰናይ ስርአቶችን ያዘለን እምነት ነው ሽብርተኛ የሚሉት‼️
||
ለማጠናከሪያ ያክል፤
"أن لا تذبح بهيمة أمام أختها"
የፊቂህ ምሁራን አንድት እንስሳ እህቷ ፊት ለፊት እንደማትታረድ ተስማምተዋል።
[መውሲዓቱ ፊቂህይያህ፡ 10/221]
*
ኢማም ኢብኑ ቁዳማህ እንዲህ ይላል፦
" وَيُكْرَهُ أَنْ يَذْبَحَ شَاةً وَالْأُخْرَى تَنْظُرُ إلَيْهِ "
«ሌላኛዋ ወደርሷ እየተመለከተች ፍየልን ማረድ ይጠላል።»
[አል-ሙጝኒ፡ 9/317]
*
ኢማም ኢብኑ ባዝም እንዲህ ይላሉ፦
"ويكره أن تذبح وأخرى تنظر "
«ሌላኛዋ እየተመለከተች ማረድ ይጠላል።»
[መጅሙዑል ፈታዋ፡ 23/73-74]
*
ሸይኽ ዐብዱል ሙሕሲን አልዐባድም እንዲህ ይላሉ፦
" ولا يذبحها بآلة كالة ثم يعذبها وهو يذبحها . وأيضاً لا يذبحها أمام أختها ؛ لأن هذا تعذيب "
«በዶሎዶመ መሳሪያ ሊያርዳት አይገባም፤ ከዚያም እያረዳት ሊቀጣት (አይገባም)። እንዲሁም እህቷ ፊት ሊያርዳት አይገባም። ምክንያቱም ይህ ቅጣት ነው።»
[ሸርሕ ሱነን አቢ ዳውድ፡ 15/212]
||
በነገራችሁ ላይ ከዚህ ጋር ተያያዥ ነጥብ፤
ብዙ እንስሳትን በአንድ ላይ በዘመናዊው ማሽን ማረድ ይቻላል።
አንድ ጊዜ ማሽኑን ሲያሳርፉ ብቻ ቢስሚልላሂ ማለትም ያብቃቃል።
የ"ለጂነቲ ዳኢማህ ፈታዋ፡ 22/463" ላይ ተመልከቱ።
||
አላሁ ተዓላ አዕለም።
Murad
@yasin_nuru @yasin_nuru
==================
ሱብሐነል'ሏህ‼️
መልዕክተ-ዙል ሒጃ‼️
ክፍል፡ [3]፦ «የአስተራረድ ስነ-ስርአት‼️»
`
```````````````````````````````````ለእንስሳት ይህን ያክል አዛኝ የሆነ እምነት፤

➥ የዐረፋን ቀን መፆም ያለው ቱሩፋት
ከአቡ ቀታዳ አል አንሷሪይ(ረዲዬሏሁ ዐንሁ) የሚከተለው ሐዲሥ ተላልፏል ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ «ያለፈውን አመት ወንጀል እና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል» አሉ [ሙስሊም (ቁ 1162)]
➼ ይህ ሐዲሥ የዐረፋን ቀን በፆም ማሳለፍ ትልቅ ምንዳ እንዳለው ማስረጃ ነው።
✔️ማሳሰቢይ:- የዐረፋ ቀን የሚባለው ከዙልሂጃ የዘጠነኛው ቀን ነው እንጅ እኛ በተለምዱ የዒዱን ለት ዐረፋ ብለን የምን ጠረው አይደለም። እኛ ዐረፋ ብለን የምንጠራው የዒድ ለት ከዙልሂጃ አስረኛው ቀን ሲሆን የውመነሕር በመባል ይታወቃል። እሄንቀን መፆም ሐራም ነው።
➼ የዐረፋን ቀን መፆም የሚወደደው ሐጅ ላይ ካለ ሰው ውጭ ላለ ነው።
➼ ከሐጅኛ ውጭ ያለ ሙስሊም እሄን ቀን በፆም ማሳለፍ ሱና ነው። እንድሁም የሁለት አመት ሀጢአት ያስምራል። ያለፈውን የአንድ አመት ሐጢአትና የሚመጣውን የአንድ አመት ሐጢአት ያስምራል።
➼ የጁሙዓ ቀን እና ዐረፋ ከተገናኘ የጁሙዐ ቀን ቢሆንም መፆም አይጠላም። የጁሙዐን ቀን ብቻውን መፆም የተከለከለው ያለምክኒያት ለይቶ መፆም ነው እንጅ በምክኒያት ከሆነ አይጠላም። በዚህም መሰረት የዚህ አመት ዓረፋ ቀን ከጁሙዓ ጋር የገጠመ ነው። በመሆኑም እርሱን መፆም የተጠላ አይደለም
➼ በዓረፋ ፆም ምክኒያት የሚማረው ወንጀል ትንንሽ ወንጀል ነው እንጅ ትልልቅ ወንጀል አይደለም ። ትልልቅ ወንጀል ማሻርክ፣ዝሙት፣ማማት፣ነገር ማዋሰክ፣የወላጅ ሐቅ እና መሰል ትልልቅ ወንጀሎች በመልካም ስራ ምክኒያት አይማሩም የግድ ሸርጡን ያሟላ ትክክለኛ ተውበት ያስፈልጋቸውል። በመልካም ስራ አማካኝነት የሚማረው ትንንሽ ወንጀል ነው።
➼ ማሳሰቢያ:- ዑለሞች የዓረፋን ቀን ፆም ስለፆመ ከትንንሽ ወንጀል ሊዘናጋ አይገባውም አቅሙ እስከፈቀደ ድረስ ሊጠነቀቅና ከወንጀል ሊርቅ ይገባዋል አንዳንዶች የዐረፋን ፆም ሲፆሙ በውስጣቸው መጥፎ ኒያን ይቋጥራሉ እርሱም እኔ እሄን ፆም ከፆምኩ የአመት ወንጀሌ ስለሚማር ከወንጀል አልጠነቀቅም የፈለግኩትን እሰራለሁ ይላሉ። የዚህ አይነት መጥፎ ኒያ በውስጡ የቋጠረ ሰው ፆሙም ተቀባይነት አይኖረውም ወንጀሉም አይማርም ይላሉ። ስለዚህ ውስጣችንን ከንድህ አይነት ርካሽና መጥፎ ኒያ ልናጠራ ይገባናል።
በውስጣችን ከወንጀል ለመራቅ ልንወስን ይገባል።
➼ በዚህ እለት ዱዓና መልካም ስራ በማብዛት ልንበረታ ይገባናል
✔️ የዘንድሮው የዐረፋ ቀን ፆም ነገ ጁሙ ስለሆነ እሄን ቀን በፆም እናሳልፍ ሌሎችንም እንዲፆሙት እናስታውሳቸው።
✔️ማሳሰቢያ:- ፆማችን ተቀባይነት ሊኖረው ዘንድ ከዚህ በስተፊት ስለፆም ሲነገሩን ከነበሩ አፍራሽና የሚጠሉ ነገሮች ልንርቅ ይገባናል።
አሏህ ለመልካሙ ነገር ይወፍቀን ፆማችንን ተቀብሎ ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ባሮቹ ያድርገን
✍ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሐመድዘይን

#የሸይኽ ፈውዛን ሃፊዘሁላህ ምክር!
~\\~~ ~ ~ ~ ~ ~
·
#ሃውድን መጠጣት ከፈለግክ በመንሃጅ ላይ ቀጥ በል!
·
#ሸይኽ ፈውዛን፡ ከነብዩ (ﷺ)ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሀውድ መጠጣት ከፈለግክ አላህ እና መልክተኛውን ታዘዝ፡፡
·
#የሙሀመድ ኡመት ነኝ ብሎ ነገር ግን የመልክተኛውን (ﷺ)ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መንሀጅ የማይታዘዝ፤ የማይተገብር እና የማይከተል ይህ ሰው ኢስላም ከሚለው ስም አይጠቀመም፡፡
·
#ይልቁንስ ሰዎች በተጠሙበት ሰዓት ሃውድን አይጠጣም አላህ ይጠብቀን እና፡፡
·
#እናም ከዚህ ሀውድ መጠጣት የፈለገ ሱናን አጥብቆ ይያዝ (ይተግብር)፤ ሱናን አጥብቆ መያዝ ደግሞ ቀላል ነገር አይደለም፤ ፈተና እና መከራ አለው፡፡ #የሚያነውሩህ፤ የሚያስቸግሩህ፤ ክብርህን የሚያጎድፉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡
·
#ይሄ ሰው ፅንፈኛ፤ ጠርዘኛ፤ እናም ሌላም›› ይሉሃል፤ ወይንም በንግግር ብቻ ላያበቁ ይችላሉ ይገሉሃል፤ ወይንም ያስሩሃል፡፡
·
#ነገር ግን ታገስ ደህንነትን እና ከሃውድ መጠጣትን ከፈለግክ፡፡ #የአላህ መልክተኛን (ﷺ) አለይሂ ወሰለም) ሀውድ ላይ እስክታገኝ ድረስ #ሱናን በመያዝ ላይ ታገስ (ፅና)፡፡
#ምንጭ ☞
شرح الدّرة المضيّة في عقد أهل الفرقة المرضية

#አጂብ_ቂሷ ▼
አሞራው በሰማይ ላይ 🦅
ነቢዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት
«ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ?» የሚል ድንገተኛ ጥያቄን ሰነዘረች ለምን እንደዚህ እንዳለች ምክንያቷን ታብራራ ዘንድ ጠየቋት
«አባታቸው የሞተባቸውን ሶስት የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ ጉሮሯቸውን የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው። ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ውስጥ አድርጌ ልሸጥ ወደ ሱቅ አመራሁ።
በመንገዴ ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ከረጢቴን ይዞብኝ በረረ ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ በረሀብ እየተንገላቱ ነው ···· » ንግግሯን ሳትጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፈቃድ ተሰጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ። አስር ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው 1000 ዲናር ይዘዋል ከመሐላቸው አንዱ መናገር ጀመረ
«አንቱ የአላህ ነብይ ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን ተቀደደና መስመጥ ጀመረ። ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ የተፈተለ ጥጥን የያዘ ቀይ የጨርቅ ከረጢት ከላይ ጣለልን። ቀዳዳውን በጨርቁ ደፈንን መርከባችንም ወደ ላይ ተንሳፈፈ። ከሞት ዳንን።
አላህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን መቶ መቶ ዲናር ለመስጠት ቃል ገባን። ይሄው ገንዘባችን እርስዎ ዘንድ ላሉ ሚስኪኖች ሰደቃ ይስጡት » በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ።
ነቢዩላህ ዳውድም ወደ ሴትዬዋ በመዞር
《ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ 》በማለት አዘዟት
ابشر يا اخي البطل والله واسع كريم والله غني الحمد فيبشرك بالخيرات كما تريد يا اخي.

ባሌ ናፈቀኝ። 😞
Inbox ጉርሻዬ የቀድሞ ትዳሬን ሳስብ፣ እንዴት በክብርና በፍቅር እንደተጋባን አስታውሳለሁ። አሁን ግን ያ ሁሉ አፈር ሆኗል::
እኔና ባለቤቴ ከተፋታን 3 ዓመት ሆኖናል። በፍቅር 2 ዓመት፣ በትዳር ደግሞ 3 ዓመት — በድምሩ 5 ዓመታት አብረን ኖረናል።
ነገር ግን ብዙ ጊዜዬን ከጓደኞቼ ጋር ነበር የማሳልፈው። 'ተይ ተይ' ስባል እንኳን እልህ ይዞኝ አንዳንዴም እነሱ ጋር አድሬ እመጣ ነበር።
'ፍቺው ለወንድ ደሞ!' ይሉኝ ነበር። እኔም በቃ ንቀቴ በጣም በርትቶ ሲናገርኝ 'ፍታኝ' እያልኩት እመልስለት ነበር።
በጣም ጥሩ፣ መሬት የወረደ እና ጥሩ ስነምግባር ያለው ባል ነበር። ልጅ እንውለድ ሲለኝ ደግሞ 'ቅርጼ ይበላሻል' እያልኩ 'ቆይ' እለው ነበር።
ይሄ የምነግርህ ለብዘ ዓመታት የማደርገውን ነው::
ነገር ግን አንድ ቀን እንደተለመደው አምሽቼ ስመጣ ስናገረው እንደድሮ ዝም ይለኛል ብዬ 'ባክህ ፍታኝ ከፈለክ' ስለው…
በሁለተኛው ቀን ሄዶ የፍቺ ክስ አስገባ።
ማመን አቃተኝ!
ጓደኞቼም 'ፍቺው ደግሞ ለወንድ' እያሉ ያሟሙቁኝ ጀመር። እኔም በሰው ሆሆይታ ፈታሁት።
ይህውልህ ጉርሻዬ፣ እሱን ከፈታሁኝ በኋላ የቀረብኳቸው ወንዶች ሁሉ እንኳን እንደሱ ሊሆኑ፣
እሩቡን እንኳን አይሆኑም።
በዚህ ላይ ሌላ ትዳር ይዞ በቅርቡም ደሞ
ወንድ ልጅ እንደወለደ ሰማሁ።
እኔም ከእነዛ ጓደኞች ጋር ተለያይተን፣ እነሱ በፊናቸው እኔም ብቸኝነቴ በርትቶብኝ ቀረሁ።
አሁን አሁን ዝም ብዬ ሳስበው 'ምን ሆኜ ነበር ግን ?'
ብዬ አስባለሁ።
ብዙ ቦታ ሄጃለሁ፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግን አላውቅም።
ስሞኑን ደግሞ እየናፈቀኝ ነው።
ምን ትመክሩኛላችሁ?
ምንድን ነው መፍትሔው?"
እህታችሁ ነኝ::
እኛ ሙስሊሞች ደሞ ምን ብለን እንምከራት?

በአሁን ሰዐት ሂጃብን አሟልቶ እንደመልበስ ሴትን ልጅ የሚፈትን ነገር አለ ብዬ አላስብም፤ በየድግሱ እና በየeventኡ ስንታደም ሂጃቡን አሟልቶ የለበሰውን ብንቆጥር ከጣት ብዛት አይዘልም፣ ዘመናዊነት እና fashionን ተከትሎ የመጣ የመራቆት trend ሳናስበው አዕምሮአችንን dominate እያደረገው ይመስለኛል
ከስር በምስሉ ላይ የምትመለከቷት የዝነኛው እግር ኳስ ተጫዋች ኡስማን ዴምቤሌ ባለቤት፣ ባለቤቷ የUEFA ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያሸነፈበት ትልቅ ድል ላይ modest የሆነ አለባበስ ለብሳ ሀይማኖቷን እና ባህሏን አክብራ የአለም ህዝብ ፊት በኩራት ወጥታለች
ውበቷ አይደለም ተገልጦ እንዲሁ ተሸፍናም እንኳን ምን ያህል strike እንደሚያደርግ ግልፅ ነው ሆኖም ግን ፊቷን ለማሳየት ፈቃደኛ አልሆነችም ሙሉ ፊቷን በጭራሽ ገልጣ አታውቅም ዝነኝነት እና ሀብት ሊቀይረው ያልቻለውን ውብ ስብዕናዋን በተለያዩ አጋጣሚዎች አስመስክራለች።
ወደኛ ስመለስ፥ እንደ ትውልድ የከሸፍንበት ጉዳይ ቢኖር ሂጃብ ነው አንድም ቀን ፀጉሯን ገልጣም ሆን ሂጃቧን አላልታ የማታውቅ ሴት የምርቃቷ ቀን፣ የጓደኛዋ ሰርግ ቀን፣ የሆነኛው ሀገራዊ event ላይ የዒድ ቀን፣ ዋናው ደግሞ የሰርጓ ቀን ላይ አይሆኑ መገላለጥን ስትገላለጥ ትታያለች። ሁሌም አላህን አጥብቄ የምለምነው ነገር ቢኖር “ሰው ላይ አይቼ ቀልቤ በጠላው ነገር አትፈትነኝ” እያልኩ ነው። ነገር ግን ነገ መውደቂያዬ አይታወቅም በሚል ፍርሀትና judgement ውስጥ እንዳልገባ በሚል ጥንቃቄ በጥሩ ከማዘዝ እና ከመጥፎ መከልከልን እየተውን እንዳንመጣ እፈራለሁ።
moon kemal

ከትዳር ሱናዎች መሀከል፦
1. በእድሜ የገፋች ሴትን ማግባት ሱና ነው።
2. የተፈታች ሴትን ማግባት ሱና ነው።
3. ባሏ የሞተባት ሴትን ማግባት ሱና ነው።
4. ሴቶችን በቤት ውስጥ በሚሰሩ ስራዎች ማለትም ምግብ በማብሰል፣ በማፅዳት፣ በማጠብ ፣ወዘተ ማገዝ ሱና ነው።
5. በገበታ ወቅት ሚስትህን ማጉረስ ሱና ነው።
6. ለሚስትህ ፍቅርን፣ አድናቆትንና ክብርን በቃላት መግለጽ ሱና ነው።
7. ስህተቷን ይቅር ማለት ሱና ነው።
8. ለሚስትህ ተውቦ መቅረብ ሱና ነው።
9. የሚስትህን ስሜት ለማወቅ መሞከር ሱና ነው።
10. ከሚስትህ ጋር ተጫዋች መሆን እና ጥሩ ጊዜን በጋራ በመዝናናት ማሳለፍ ሱና ነው። (እሽቅድምድም፣ ተረት መተረክ፣ አስደሳች አጋጣሚን ከእሷ ጋር ማውጋት) ሱና ነው።
11. በሚስትህ ታፋ ላይ መተኛት እና ዘና ማለት ሱና ነው።
12. ሚስትህን በመልካም ስሞች መጥራት ሱና ነው።
13. የግል ጉዳዮቿን ለሌሎች ከሌሎች መደበቅ ሱና ነው።
14. ወላጆቿን መውደድና ማክበር ሱና ነው።
15. በከፋት ጊዜ ማፅናናት ሱና ነው።
የብዙዎች አርአያ የሆኑት ረሱል (ሰ•ዐ•ወ) ከሚስቶቻቸው ጋር ተጫዋች የነበሩ፣ ጥሩ ጊዜዎችን በጋራ በመዝናናት የሚያሳልፉ፣ አንዳንድ ጊዜዎችንም በሩጫ የሚሽቀዳደሙ፣ ተረት የሚተርኩ፣ አስደሳች አጋጣሚዎችን ከሚስቶቻቸው ጋር በማውጋት የሚያሳልፉ ድንቅ ሰው ነበሩ።
አሏህ (ሱ•ወ) እኒህን ሱንናዎች የምንከተል ያድርገን ላላገባነውም ሳሊህ የትዳር አጋር ይስጠን።
ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።

ኢድን በምን ለማሳለፍ አሰባችሁ?
የኛ ሙዚቃ ሃላል ነው ብላችሁ እየሰማችሁ
ወደ ሃገር ቤት የምትሄዱ ሰዎች ደሞ አላህን እንፍራ።
የኛ ሙዚቃ ሃላል ነው ብላችሁ እየሰማችሁ
ወደ ሃገር ቤት የምትሄዱ ሰዎች ደሞ አላህን እንፍራ።
#ነገ_ሐሙስ_ሊያልፎት_የማይገባ_ቀን
🤲 የአረፋ ቀን! 🤲
ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦
﴿لا إلَهَ إلّا اللهُ وحدَهُ لا شريكَ لَهُ، لَهُ الملكُ ولَهُ الحمدُ وهوَ على كلِّ شَيءٍ قديرٌ.﴾
“ምርጡ #ዱዓ የዓረፋ ቀን የሚደረገው ዱዓ ነው። እኔም ሆንኩ ከኔ በስተፊት የነበሩት ነቢያት ከተናገሩት ቃል መካከል በላጩም፦ ‘ከአላህ #በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው #አምላክ የለም። እሱ #ብቸኛ ነው። #አጋር የለውም። ንግስናም ለሱ ነው። #ምስጋናም_የሚገባው_ለሱ_ነው። እሱ በሁሉም ነገር ላይ #ቻይ ነውና።’ የሚለው ቃል ነው።”
እንዳያመልጠን‼️
➥የነገው #ሀሙስ #የዐረፋን 9ንኛ ቀን በመፆም ያለው ቱሩፋት
🥰ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ «ያለፈውን አመት ወንጀል እና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል» አሉ [ሙስሊም (ቁ 1162)]
#ለጓደኞቻችሁ_ሼር_አርጉላቸው

ነገ ለመፆም ዝግጁ ናችሁ አይደል?
ያለፈውን እና የሚመጣውን አመት ወንጀል የሚያስምራላችሁን አንድ ቀን አንድ ቀን አለመፆም የማይታሰብ ነው።
#እንዳያመልጣችሁ! #በፍፁም!