Telegram Web Link
የዐረፋን ቀን መፆም ያለው ቱሩፋት

ከአቡ ቀታዳ አል አንሷሪይ(ረዲዬሏሁ ዐንሁ) የሚከተለው ሐዲሥ ተላልፏል ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ «ያለፈውን አመት ወንጀል እና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል» አሉ [ሙስሊም (ቁ 1162)]

➼ ይህ ሐዲሥ የዐረፋን ቀን በፆም ማሳለፍ ትልቅ ምንዳ እንዳለው ማስረጃ ነው።

✔️ማሳሰቢይ:- የዐረፋ ቀን የሚባለው ከዙልሂጃ የዘጠነኛው ቀን ነው እንጅ እኛ በተለምዱ የዒዱን ለት ዐረፋ ብለን የምን ጠረው አይደለም። እኛ ዐረፋ ብለን የምንጠራው የዒድ ለት ከዙልሂጃ አስረኛው ቀን ሲሆን የውመነሕር በመባል ይታወቃል። እሄንቀን መፆም ሐራም ነው።

➼ የዐረፋን ቀን መፆም የሚወደደው ሐጅ ላይ ካለ ሰው ውጭ ላለ ነው።

➼ ከሐጅኛ ውጭ ያለ ሙስሊም እሄን ቀን በፆም ማሳለፍ ሱና ነው። እንድሁም የሁለት አመት ሀጢአት ያስምራል። ያለፈውን የአንድ አመት ሐጢአትና የሚመጣውን የአንድ አመት ሐጢአት ያስምራል።

➼ የጁሙዓ ቀን እና ዐረፋ ከተገናኘ የጁሙዐ ቀን ቢሆንም መፆም አይጠላም። የጁሙዐን ቀን ብቻውን መፆም የተከለከለው ያለምክኒያት ለይቶ መፆም ነው እንጅ በምክኒያት ከሆነ አይጠላም። በዚህም መሰረት የዚህ አመት ዓረፋ ቀን ከጁሙዓ ጋር የገጠመ ነው። በመሆኑም እርሱን መፆም የተጠላ አይደለም

➼ በዓረፋ ፆም ምክኒያት የሚማረው ወንጀል ትንንሽ ወንጀል ነው እንጅ ትልልቅ ወንጀል አይደለም ። ትልልቅ ወንጀል ማሻርክ፣ዝሙት፣ማማት፣ነገር ማዋሰክ፣የወላጅ ሐቅ እና መሰል ትልልቅ ወንጀሎች በመልካም ስራ ምክኒያት አይማሩም የግድ ሸርጡን ያሟላ ትክክለኛ ተውበት ያስፈልጋቸውል። በመልካም ስራ አማካኝነት የሚማረው ትንንሽ ወንጀል ነው።

ማሳሰቢያ:- ዑለሞች የዓረፋን ቀን ፆም ስለፆመ ከትንንሽ ወንጀል ሊዘናጋ አይገባውም አቅሙ እስከፈቀደ ድረስ ሊጠነቀቅና ከወንጀል ሊርቅ ይገባዋል አንዳንዶች የዐረፋን ፆም ሲፆሙ በውስጣቸው መጥፎ ኒያን ይቋጥራሉ እርሱም እኔ እሄን ፆም ከፆምኩ የአመት ወንጀሌ ስለሚማር ከወንጀል አልጠነቀቅም የፈለግኩትን እሰራለሁ ይላሉ። የዚህ አይነት መጥፎ ኒያ በውስጡ የቋጠረ ሰው ፆሙም ተቀባይነት አይኖረውም ወንጀሉም አይማርም ይላሉ። ስለዚህ ውስጣችንን ከንድህ አይነት ርካሽና መጥፎ ኒያ ልናጠራ ይገባናል።
በውስጣችን ከወንጀል ለመራቅ ልንወስን ይገባል።

➼ በዚህ እለት ዱዓና መልካም ስራ በማብዛት ልንበረታ ይገባናል

✔️ የዘንድሮው የዐረፋ ቀን ፆም ነገ ጁሙ ስለሆነ እሄን ቀን በፆም እናሳልፍ ሌሎችንም እንዲፆሙት እናስታውሳቸው።

✔️ማሳሰቢያ:-  ፆማችን ተቀባይነት ሊኖረው ዘንድ ከዚህ በስተፊት ስለፆም ሲነገሩን ከነበሩ አፍራሽና የሚጠሉ ነገሮች ልንርቅ ይገባናል።

አሏህ ለመልካሙ ነገር ይወፍቀን ፆማችንን ተቀብሎ ወንጀላቸው ከሚማርላቸው ባሮቹ ያድርገን

ወንድማችሁ ኢብኑ ሙሐመድዘይን

@yasin_nuru @yasin_nuru
#የሸይኽ ፈውዛን ሃፊዘሁላህ ምክር!

~\\~~ ~ ~ ~ ~ ~
·
#ሃውድን መጠጣት ከፈለግክ በመንሃጅ ላይ ቀጥ በል!
·
#ሸይኽ ፈውዛን፡ ከነብዩ (ﷺ)ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ሀውድ መጠጣት ከፈለግክ አላህ እና መልክተኛውን ታዘዝ፡፡
·
#የሙሀመድ ኡመት ነኝ ብሎ ነገር ግን የመልክተኛውን (ﷺ)ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም መንሀጅ የማይታዘዝ፤ የማይተገብር እና የማይከተል ይህ ሰው ኢስላም ከሚለው ስም አይጠቀመም፡፡
·
#ይልቁንስ ሰዎች በተጠሙበት ሰዓት ሃውድን አይጠጣም አላህ ይጠብቀን እና፡፡
·
#እናም ከዚህ ሀውድ መጠጣት የፈለገ ሱናን አጥብቆ ይያዝ (ይተግብር)፤ ሱናን አጥብቆ መያዝ ደግሞ ቀላል ነገር አይደለም፤ ፈተና እና መከራ አለው፡፡ #የሚያነውሩህ፤ የሚያስቸግሩህ፤ ክብርህን የሚያጎድፉ ሰዎች ይኖራሉ፡፡
·
#ይሄ ሰው ፅንፈኛ፤ ጠርዘኛ፤ እናም ሌላም›› ይሉሃል፤ ወይንም በንግግር ብቻ ላያበቁ ይችላሉ ይገሉሃል፤ ወይንም ያስሩሃል፡፡
·
#ነገር ግን ታገስ ደህንነትን እና ከሃውድ መጠጣትን ከፈለግክ፡፡ #የአላህ መልክተኛን  (ﷺ) አለይሂ ወሰለም) ሀውድ ላይ እስክታገኝ ድረስ  #ሱናን በመያዝ ላይ ታገስ (ፅና)፡፡


#ምንጭ
شرح الدّرة المضيّة في عقد أهل الفرقة المرضية
  
@yasin_nuru @yasin_nuru
#አጂብ_ቂሷ
            አሞራው በሰማይ ላይ 🦅

ነቢዩላህ ዳውድ በዙፋናቸው ላይ ተቀምጠው ሳለ አንዲት ሴት

  «ጌታህ ፍትሀዊ ነው ወይስ በዳይ?» የሚል ድንገተኛ ጥያቄን ሰነዘረች ለምን እንደዚህ እንዳለች ምክንያቷን ታብራራ ዘንድ ጠየቋት
«አባታቸው የሞተባቸውን ሶስት የቲም ልጆችን አሳድጋለሁ ጉሮሯቸውን የምደፍነውም ጥጥ በመፍተልና በመሸጥ ከማገኘው ገንዘብ ነው።  ዛሬ ግን ጥጤን ፈትዬ በጨርቅ ከረጢት ውስጥ አድርጌ ልሸጥ ወደ ሱቅ አመራሁ።

በመንገዴ ላይ ሳለሁ አንድ አሞራ ከረጢቴን ይዞብኝ በረረ ለልጆቼ ዳቦ መግዣ አጣሁ በረሀብ እየተንገላቱ ነው ···· » ንግግሯን  ሳትጨርስ በሩ ተንኳኳ። ፈቃድ ተሰጣቸውና ወደ ውስጥ ገቡ። አስር ነጋዴዎች ነበሩ። በእጃቸው 1000 ዲናር ይዘዋል ከመሐላቸው አንዱ መናገር ጀመረ

  «አንቱ የአላህ ነብይ ባህር ላይ እየተጓዝን ሳለ መርከባችን ተቀደደና መስመጥ ጀመረ። ሞታችንን በመጠባበቅ ላይ ሳለን አንድ አሞራ የተፈተለ ጥጥን የያዘ ቀይ የጨርቅ ከረጢት ከላይ ጣለልን። ቀዳዳውን በጨርቁ ደፈንን መርከባችንም ወደ ላይ ተንሳፈፈ። ከሞት ዳንን።

አላህ ለዋለልን ውለታ ምስጋና ይሆን ዘንድ እያንዳንዳችን መቶ መቶ ዲናር ለመስጠት ቃል ገባን። ይሄው ገንዘባችን እርስዎ ዘንድ ላሉ ሚስኪኖች ሰደቃ ይስጡት » በማለት ብሩን እንዲቀበሏቸው እጃቸውን ዘረጉ።

ነቢዩላህ ዳውድም ወደ ሴትዬዋ በመዞር
《ጌታሽ አንቺን ከድካም አሳርፎ በየብስና በባህር ይነግድልሻል አንቺ ግን በዳይ ትይዋለሽ በይ ገንዘቡን ተቀብለሽ ይዘሽ ሂጂ 》በማለት አዘዟት
ابشر يا اخي البطل والله واسع كريم والله غني الحمد فيبشرك بالخيرات كما تريد يا اخي.

@yasin_nuru @yasin_nuru
ባሌ ናፈቀኝ። 😞

Inbox ጉርሻዬ የቀድሞ ትዳሬን ሳስብ፣ እንዴት በክብርና በፍቅር እንደተጋባን አስታውሳለሁ። አሁን ግን ያ ሁሉ አፈር ሆኗል::

እኔና ባለቤቴ ከተፋታን 3 ዓመት ሆኖናል። በፍቅር 2 ዓመት፣ በትዳር ደግሞ 3 ዓመት — በድምሩ 5 ዓመታት አብረን ኖረናል።

ነገር ግን ብዙ ጊዜዬን ከጓደኞቼ ጋር ነበር የማሳልፈው። 'ተይ ተይ' ስባል እንኳን እልህ ይዞኝ አንዳንዴም እነሱ ጋር አድሬ እመጣ ነበር።

'ፍቺው ለወንድ ደሞ!' ይሉኝ ነበር። እኔም በቃ ንቀቴ በጣም በርትቶ ሲናገርኝ 'ፍታኝ' እያልኩት እመልስለት ነበር።

በጣም ጥሩ፣ መሬት የወረደ እና ጥሩ ስነምግባር ያለው ባል ነበር። ልጅ እንውለድ ሲለኝ ደግሞ 'ቅርጼ ይበላሻል' እያልኩ 'ቆይ' እለው ነበር።

ይሄ የምነግርህ ለብዘ ዓመታት የማደርገውን ነው::

ነገር ግን አንድ ቀን እንደተለመደው አምሽቼ ስመጣ ስናገረው እንደድሮ ዝም ይለኛል ብዬ 'ባክህ ፍታኝ ከፈለክ' ስለው…

በሁለተኛው ቀን ሄዶ የፍቺ ክስ አስገባ።

ማመን አቃተኝ!

ጓደኞቼም 'ፍቺው ደግሞ ለወንድ' እያሉ ያሟሙቁኝ ጀመር። እኔም በሰው ሆሆይታ ፈታሁት።

ይህውልህ ጉርሻዬ፣ እሱን ከፈታሁኝ በኋላ የቀረብኳቸው ወንዶች ሁሉ እንኳን እንደሱ ሊሆኑ፣
እሩቡን እንኳን አይሆኑም።

በዚህ ላይ ሌላ ትዳር ይዞ በቅርቡም ደሞ
ወንድ ልጅ እንደወለደ ሰማሁ።

እኔም ከእነዛ ጓደኞች ጋር ተለያይተን፣ እነሱ በፊናቸው እኔም ብቸኝነቴ በርትቶብኝ ቀረሁ።

አሁን አሁን ዝም ብዬ ሳስበው 'ምን ሆኜ ነበር ግን ?'
ብዬ አስባለሁ።

ብዙ ቦታ ሄጃለሁ፣ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ግን አላውቅም።

ስሞኑን ደግሞ እየናፈቀኝ ነው።

ምን ትመክሩኛላችሁ?
ምንድን ነው መፍትሔው?"

እህታችሁ ነኝ::

እኛ ሙስሊሞች ደሞ ምን ብለን እንምከራት?

@yasin_nuru @yasin_nuru
በአሁን ሰዐት ሂጃብን አሟልቶ እንደመልበስ ሴትን ልጅ የሚፈትን ነገር አለ ብዬ አላስብም፤ በየድግሱ እና በየeventኡ ስንታደም ሂጃቡን አሟልቶ የለበሰውን ብንቆጥር ከጣት ብዛት አይዘልም፣ ዘመናዊነት እና fashionን ተከትሎ የመጣ የመራቆት trend ሳናስበው አዕምሮአችንን dominate እያደረገው ይመስለኛል

ከስር በምስሉ ላይ የምትመለከቷት የዝነኛው እግር ኳስ ተጫዋች ኡስማን ዴምቤሌ ባለቤት፣ ባለቤቷ የUEFA ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫን ያሸነፈበት ትልቅ ድል ላይ modest የሆነ አለባበስ ለብሳ ሀይማኖቷን እና ባህሏን አክብራ የአለም ህዝብ ፊት በኩራት ወጥታለች

ውበቷ አይደለም ተገልጦ እንዲሁ ተሸፍናም እንኳን ምን ያህል strike እንደሚያደርግ ግልፅ ነው ሆኖም ግን ፊቷን ለማሳየት ፈቃደኛ አልሆነችም ሙሉ ፊቷን በጭራሽ ገልጣ አታውቅም ዝነኝነት እና ሀብት ሊቀይረው ያልቻለውን ውብ ስብዕናዋን በተለያዩ አጋጣሚዎች አስመስክራለች።

ወደኛ ስመለስ፥ እንደ ትውልድ የከሸፍንበት ጉዳይ ቢኖር ሂጃብ ነው አንድም ቀን ፀጉሯን ገልጣም ሆን ሂጃቧን አላልታ የማታውቅ ሴት የምርቃቷ ቀን፣ የጓደኛዋ ሰርግ ቀን፣ የሆነኛው ሀገራዊ event ላይ የዒድ ቀን፣ ዋናው ደግሞ የሰርጓ ቀን ላይ አይሆኑ መገላለጥን ስትገላለጥ ትታያለች። ሁሌም አላህን አጥብቄ የምለምነው ነገር ቢኖር “ሰው ላይ አይቼ ቀልቤ በጠላው ነገር አትፈትነኝ” እያልኩ ነው። ነገር ግን ነገ መውደቂያዬ አይታወቅም በሚል ፍርሀትና judgement ውስጥ እንዳልገባ በሚል ጥንቃቄ በጥሩ ከማዘዝ እና ከመጥፎ መከልከልን እየተውን እንዳንመጣ እፈራለሁ። 

moon kemal

@yasin_nuru @yasin_nuru
ከትዳር ሱናዎች መሀከል፦

1. በእድሜ የገፋች ሴትን ማግባት ሱና ነው።

2. የተፈታች ሴትን ማግባት ሱና ነው።

3. ባሏ የሞተባት ሴትን ማግባት ሱና ነው።

4. ሴቶችን በቤት ውስጥ በሚሰሩ ስራዎች ማለትም ምግብ በማብሰል፣ በማፅዳት፣ በማጠብ ፣ወዘተ ማገዝ ሱና ነው።

5. በገበታ ወቅት ሚስትህን ማጉረስ ሱና ነው።

6. ለሚስትህ ፍቅርን፣ አድናቆትንና ክብርን በቃላት መግለጽ ሱና ነው።

7. ስህተቷን ይቅር ማለት ሱና ነው።

8. ለሚስትህ ተውቦ መቅረብ ሱና ነው።

9. የሚስትህን ስሜት ለማወቅ መሞከር ሱና ነው።

10. ከሚስትህ ጋር ተጫዋች መሆን እና ጥሩ ጊዜን በጋራ በመዝናናት ማሳለፍ ሱና ነው። (እሽቅድምድም፣ ተረት መተረክ፣ አስደሳች አጋጣሚን ከእሷ ጋር ማውጋት) ሱና ነው።

11. በሚስትህ ታፋ ላይ መተኛት እና ዘና ማለት ሱና ነው።

12. ሚስትህን በመልካም ስሞች መጥራት ሱና ነው።

13. የግል ጉዳዮቿን ለሌሎች ከሌሎች መደበቅ ሱና ነው።

14. ወላጆቿን መውደድና ማክበር ሱና ነው።

15. በከፋት ጊዜ ማፅናናት ሱና ነው።

የብዙዎች አርአያ የሆኑት ረሱል (ሰ•ዐ•ወ) ከሚስቶቻቸው ጋር ተጫዋች የነበሩ፣ ጥሩ ጊዜዎችን በጋራ በመዝናናት የሚያሳልፉ፣ አንዳንድ ጊዜዎችንም በሩጫ የሚሽቀዳደሙ፣ ተረት የሚተርኩ፣ አስደሳች አጋጣሚዎችን ከሚስቶቻቸው ጋር በማውጋት የሚያሳልፉ ድንቅ ሰው ነበሩ።

አሏህ (ሱ•ወ) እኒህን ሱንናዎች የምንከተል ያድርገን ላላገባነውም ሳሊህ የትዳር አጋር ይስጠን።

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።

@yasin_nuru @yasin_nuru
ኢድን በምን ለማሳለፍ አሰባችሁ?

የኛ ሙዚቃ ሃላል ነው ብላችሁ እየሰማችሁ
ወደ ሃገር ቤት የምትሄዱ ሰዎች ደሞ አላህን እንፍራ።
#ነገ_ሐሙስ_ሊያልፎት_የማይገባ_ቀን

🤲 የአረፋ ቀን! 🤲

ረሱል (🤍) እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا إلَهَ إلّا اللهُ وحدَهُ لا شريكَ لَهُ، لَهُ الملكُ ولَهُ الحمدُ وهوَ على كلِّ شَيءٍ قديرٌ.﴾

“ምርጡ #ዱዓ የዓረፋ ቀን የሚደረገው ዱዓ ነው። እኔም ሆንኩ ከኔ በስተፊት የነበሩት ነቢያት ከተናገሩት ቃል መካከል በላጩም፦ ‘ከአላህ #በስተቀር በሀቅ ሊመለክ የሚገባው #አምላክ የለም። እሱ #ብቸኛ ነው። #አጋር የለውም። ንግስናም ለሱ ነው። #ምስጋናም_የሚገባው_ለሱ_ነው። እሱ በሁሉም ነገር ላይ #ቻይ ነውና።’ የሚለው ቃል ነው።”

እንዳያመልጠን‼️

➥የነገው #ሀሙስ #የዐረፋን 9ንኛ ቀን በመፆም ያለው ቱሩፋት               

🥰ረሱል (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ስለ ዐረፋ ቀን ፆም ተጠየቁ «ያለፈውን አመት ወንጀል እና የሚመጣውን አመት ወንጀል ያስምራል» አሉ [ሙስሊም (ቁ 1162)]

#ለጓደኞቻችሁ_ሼር_አርጉላቸው

@yasin_nuru @yasin_nuru
ነገ ለመፆም ዝግጁ ናችሁ አይደል?

ያለፈውን እና የሚመጣውን አመት ወንጀል የሚያስምራላችሁን አንድ ቀን አንድ ቀን አለመፆም የማይታሰብ ነው።

#እንዳያመልጣችሁ! #በፍፁም!

@yasin_nuru @yasin_nuru
አላህ ፍልስጤሞችን ከወራሪዋ ነፃ ያድርጋቸው። ልፍስፍሱንም ኡማ ጥንካሬ ይስጠው። በዱዓችሁ አትርሷቸው🥺🥺

@yasin_nuru @yasin_nuru
اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ كَبِيْرًا، وَالْحَمْدُ لِلَّهِ كَثِيْرًا، وَسُبْحَانَ اللَّهِ بُكْرَةً وَأَصِيلاً
لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَحْدَهُ، صَدَقَ وَعْدَهُ، وَنَصَرَ عَبْدَهُ، وَأَعَزَّ جُنْدَهُ، وَهَزَمَ الأَحْزَابَ وَحْدَهُ
لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ، وَلاَ نَعْبُدُ إِلاَّ إِيَّاهُ، مُخْلِصِيْنَ لَهُ الدِّيْنَ، وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُوْنَ
اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ وَلِلَّهِ الْحَمْدُ
اللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ، لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ وَاللَّهُ أَكْبَرُ، اللَّهُ أَكْبَرُ وَلِلَّهِ الْحَمْدُ

@yasin_nuru @yasin_nuru
🌻 ዒድ ሙባረክ

💐 እንኳን ለ1446ኛው ዒድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሠላም አደረሰን።

🌸 تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال

人  ★* 。 • ˚* ˚ 🌙
.  (_ _) * ዒድ * ★
. ┃口┃ *     mubark     *
. ┃口┃★ *   ***.    .  *˛•
. ┃口┃★   * •★ 。•˛˚˛*
. ┃口┃ •˛˚˛*   人  •˛˚  *       
. ┃口┃     .-:'''"''''"''.-.     
. ┃口┃  (_(_(_()_)_)_)         
  ┃口┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
. ┃.   ┃_┃∩∩∩∩∩∩┃
_三三三三三
🌷አላህ መልካም ሥራችንን ሁሉ ይቀበለን!  ጥፋታችንንም ይቅር ይበለን። የደስታ የሰላም እና የተባረከ ዒድ ይሁንልን!!

🌼 ዒድኩም ሙባረክ እንኳን አደረሳቹ🥰

@yasin_nuru @yasin_nuru
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🛑 የኢድ ሰላት አሰጋገድ በቤት ውስጥ || አብሶ ለመዳም ቅመሞች

san tube

@yasin_nuru @yasin_nuru
ኢዱ እንዴት እያለፈ ነው?

እስኪ የማትረሱት የኢድ ገጠመኝ ካለ አካፍሉን
🐑 አያመ ተሽሪቅ! 1⃣1⃣🔣1⃣2⃣🔣1⃣3⃣

ከበሺር ቢን ሰሂም ተይዞ ነቢዩ (🤍) ስለ አያመ ተሽሪቅ ሲናገሩ እንዲህ ብለዋል፦

﴿لا يدخلُ الجنَّةَ إلاَّ نفسٌ مسلمةٌ، وإنّ هذِهِ الأيّامَ أيّامُ أكلٍ وشربٍ..﴾

“ነፍሱ ሙስሊም የሆነች ቢሆን እንጂ ጀነትን አይገባም። እነዚህ ቀናቶች ደግሞ የመብያና የመጠጫ ቀናቶች ናቸው።”

📚 ኢብኑ ማጃህ ሶሂህ ብለውታል: 1407


@yasin_nuru
#ጣፋጭ #ሀዲስ

አንብበው ለሌሎችም ማካፈል አይዘንጉ!!

ረሱል ሰ.ዐ.ወ ከሶሃቦቻቸው ጋር ቁጭ ብለው በዱኒያ ላይ በጣም  ስለሚዎዷቸው ነገሮች
አየተጨዋወቱ እያሉ ነብዩ አቡበክርን "ያ አባ በከር አንተ በዱኒያ ላይ በጣም የምትወደው
ነገር ምንድነው?" ብለው ጠየቁት።

አቡበክርም "3 ነገሮችን እወዳለሁ:-

1.ከአንተ ጋር መቀመጥ፣
2.አንተን ማየት፣
3.አንተ ባዘዝካቸው ነገሮች ላይ በሙሉ ገንዘቤን መለገስ" ብሎ መለሰ።
°
ዑመርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያዑመር ?"

"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ
1.በድብቅ እንኳን ቢሆን በመልካም ነገር ማዘዝ፣
2.በግልጽ እንኳን ቢሆን ከመጥፎ ነገር መከልከል፣
3 መራራ እንኳን ቢሆን እውነትን መናገር።" ብሎ መለሰ።
°
ዑስማንን ጠየቁት "አንተስ ያዑስማን?

በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሰዎችን ማብላት፣
2.ሰላምታን ማብዛት፣
3.ሰዎች በተኙ ጊዜ ሶላትን ማብዛት፣
°
አልይን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአልይ ?"
"በዱኒያ ላይ 3ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.እንግዳን ማክበር፣
2.በሙቀት ወቅት ፆምን መፆም፣
3.ጠላቴን በሰይፍ መቅላት፣
°
አባ ዘርን በተራው ጠየቁት "አንተስ ያአባ ዘር?"

"በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ :-
1.እርሃብን እወዳለሁ፣
2.በሽታን እወዳለሁ፣
3.ሞትን እወዳለሁ፣

ነብዩም "ያ አባ ዘር ለምን እነዚህን ወደድክ?"

አቡዘር መለሰ "ረሃብን ወደድኩት ቀልቤን ፈሪ ሊያደርግልኝ ዘንድ፣ በሽታን ወደድኩት ወንጀሌን ሊያቀልልኝ ዘንድ፣ ሞትን ወደድኩት ከጌታየ ጋር ሊያገናኜኝ ዘንድ።" ብሎ መለሰ።
°
ነብዩ ሰለላሁ አለየሂ ወሰለም🥰
" እኔም በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.ሽቶን እወዳለሁ፣
2.ሚስቶቼን እወዳለሁ፣
3.የአይኔ ማረፊያ ሶላቴን እወዳለሁ፣

በዚህ መካከል ድንገት ጅብሪል ዱብ አለ ሰላምታ ካወረደ በኋላ እንዲህ አለ

"አንቱ የአላህ መልዕክተኛ በዱኒያ ላይ እኔም 3 ነገሮችን እወዳለሁ ነብዩም ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም

"ምንድናቸው ያ ጀብሪል?" ብለው ጠየቁት።
1.መልዕክትን ማድረስ፣
2. አማናን አደራን መጠበቅ፣
3.ሚስኪኖችን መውደድ፣

ጅብሪል ተመልሶ ወደ ሰማይ ከወጣ በኋላ ረሱልና ሱሃቦቻቸው ከመቀመጫቸው ሳይነሱ
ተመልሶ ወደ መሬት ዱብ አለ

አሁንም ሰላምታውን አቅርቦ:-

"አላህም ሰላም ብሏችኋል ካለ በኋላ አላህም እንዲህ ብሏል:-
በዱኒያ ላይ 3 ነገሮችን እወዳለሁ:-
1.አላህን አውሺ የሆነችን ምላስ፣
2.አላህን ፈሪ የሆነችን ቀልብ፣
3.መከራ የበዛበት ታጋሽ የሆነችን ጀሰድ።

አላህ ታጋሾች አድርጎ ነብዩና ሱሃቦች የወደዱትን ያስወድደን!
°
ይህን ጣፋጭ ሐዲስ በማንበባችሁ ከፍ ያለ አጅር ታገኛላችሁ -ኢንሻ አሏህ።

ሼር በማድረግ ለሌሎች ብታካፍሉ ግን እነሱ ባነበቡት ልክ ለናንተም ሀሰናት ይፃፍላችኋል!
ኢንሻ አሏህ!!

አላህ አንብበው ከመጠቀሙት ያድርገን!!

@yasin_nuru @yasin_nuru
❥:::::::: ጠቃሚ ምክሮች::::::::❥

☞ በእጅህ የያዝከውን አትልቀቅ ካጣኸው በኃላ ይቆጭሀል እና

☞ ባጣኸው ነገር አትበሳጭ የተሻለውን አላህ ይሰጥሀል እና

☞ የበደለህን ይቅር በል አላህ ይቅር ባዮችን ይወዳል እና

☞ ስትደሰት ብቻ ሳይሆን ስትከፋም አልሀምዱሊላህ በል አላህ አመስጋኞችን ይወዳል እና

☞ ባለህ ነገር አመስግን አላህ ይጨምርልሀል እና

☞ በወንድምህ ውድቀት አትደሰት ነገ ሌላ ቀን ነው ባንተ ይደርሳል እና

☞ የትም ብትሆን አላህን ፍራ አላህ ካንተ ጋር ነው እና

☞ድሆችን እርዳ ሰደቃ ወንጀልን ታብሳለች እና

☞ ሰወችን አትመቀኝ ምቀኝነት መልካም ስራን ትበላለች እና

☞ወደ አላህ ተጠጋ እሱ ለባሪያው ቅርብ ነው እና

☞ አላህን አፍቅረው እሱ የእውነተኛ ፍቅር ባለቤት ነው እና

☞ አላህን ፍራው ወደርሱ ትቀርባለህ እና

☞ ተስፋህ ባአላህ ይሁን ሁሉን ማድረግ የሚችል ጌታ ነው እና

☞ ያንተ ያልሆነን ነገር ያንተ ለማድረግ ብዙ አትድከም ውሳኔው የአላህ ነው እና

☞ በሁሉም ነገር ላይ ታገስ አላህ ከታጋሾች ጋር ነው እና

☞ ለሁሉም ነገር አትቸኩል ችኮላ የሸይጧን ነው እና

☞ አትበሳጭ ብስጭት የሸይጧንን በር ትከፍታለች እና

☞ የትም ብትሆን አላህን አስታውስ ያስታውስሀል እና።

#ሼር  መድረጉን አይርሱ📌

@yasin_nuru @yasin_nuru
2025/07/05 05:04:16
Back to Top
HTML Embed Code: