Telegram Web Link
አለም ከገደል ማሚቶ የተሻለ አይደለም!!

ፍቅር በራችሁን አንኳኩቶ ያውቃል? በጭራሽ! ምክንያቱም ገና ፍቅር መስጠት አልቻላችሁም። ማስታወስ ያለባችሁ የሰጠነው ሁሉ ወደ እኛው ተመልሶ እንደሚመጣ ነው። ይህም ከህይወት ህጎች አንዱ ነው።

መላው ዓለም ከገደል ማሚቶ የተሻለ አይደለም። ጥላቻ እንሰጣለን፣ ጥላቻም ወደኛው ተመልሶ ይመጣል። ሌሎችን እንሳደባለን ከዛም ስድብ ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። እሾህ ስንሰጥ እሾህ ወደኛው ተመልሶ ይመጣል፡፡ የምንሰጠው ሁሉ በተለያዩ መንገዶች ወደኛ ተመልሶ ይመጣል። ፍቅርን ካካፈልንም እንደዚሁ በተለያዪ መንገዶች ተመልሶ ወደኛው ይመጣል። ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች ፍቅር ወደ እኛ ተመልሶ ካልመጣ ፍቅር እንዳልሰጠን ማወቅ አለብን፡፡

ፍቅር እምትሰጠው እንጂ እምትቀበለው አይደለም።

ኦሾ/osho
@yebezdebdabewoch
የሰው ልጅን በኦሾ እይታ
ስለ ሰው ልጅ ብዙ ብዙ
ያለው ኦሾ በዚች ምድር አምሳያውን የሚገድል ፍጡር ቢኖር
የሰው ልጅ ብቻ ነው በማለት ያስቀምጥና የትኛውም እንሰሳ
መርዝ አወጋጅቶ ስለት ስሎ ሰዋራ ቦታ ጠብቆ ወይ በገመድ
አንቆ አልያም ጥይት ተኩሶ አምሳያውን የገደለበት አጋጣሚ
በአለም አልታየም ይለናል
ሌላው በትምህርታዊ ነገር ስለ ሰው ልጅ የገለፀልን ነገር
እንዲህ ይላል በአንድ ሆስፒታል ውስጥ የመጀመሪያው ታማሚ
ክፍል የተዘጋ በር ላይ ' በእባብ የተነደፈ ሰው በህክምና ላይ
የሚገኝ ሲሆን ከ30 ደቂቃ ቦኃላ ድኖ ይወጣል ' ይላል
ሁለተኛው በር ላይ " በአንበሳ የተነከሰ ሰው በህክምና ላይ
ይገኛል ከአንድ ሰአት ቦኃላ ድኖ ይወጣል " ይላል ሶስተኛው በር
ላይ ደግሞ በሰው የተነከሰ ሰው በህክምና ላይ ይገኛል ህይወቱ
ስለ መትረፉ እንኳን እርግጠኞች አይደለንም " በማለት የሰው
ልጅን እርኩሳዊ ባህሪ ሊያስረዳን ሞክሯል ቅዱስ ሆናችሁ
ተወልዳችሁ ሰይጣን ሆናችሁ ትሞታላችሁ የሚለን እሾ
እርኩስም ቅዱስም የመሆን ምርጫው እኛው ጋር እንዳለ
አስረግጦ ያሳስበናል
የትኛውም እንሰሳ የተራክቦ ስሜቱን የሚወጣው የሴቷን ሽንት
አሽትቶና እርጉዝ አለመሆኗን አረጋግጦ ሲሆን ይህንንም
ለማድረግ ወቅትና የሴቷን ፈቃደኝነት ተከትሎ ነው የሰው ልጅ
ግን ስግብግብ በመሆኑ ያለ ሴቷ ፍቃድና አስገድዶ ደፋሪ ሆኖ
ከእንሰሳ በታች የዘቀጠ የስብዕና ኖሮት አለማፈሩ አስገራሚ
ፍጡር ያደርገዋል ።
ኦሾ/Osho.
@yebezdebdabewoch
የስሜት ጭቆና ምንድ ነው ?
🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡
"የስሜት ጭቆና መኖር የሌለባችሁን ህይወት መኖር ማለት ነው። የስሜት ጭቆና ማለት ፈጸሞ የማትፈልጓቸውን ነገሮች ማድረግ ማለት ነው። የስሜት ጭቆና ራስን የማወደሚያ መንገድ ነው። የስሜት ጭቆና ራስን ማጥፋት ነው። በርግጥ ራስ መሠጥፉቱ በጣም የዘገየ ነው። ግንበጣም እርግጠኛ የሆነ ምረዛ ነው።
....ስሜትን መግለጽ ህይወት ሲሆን ስሜትን መጨቆን ደግሞ ራስን የማጥፋ!ት ያህል ነው።"
🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡🎡

#ኦሾ/Osho
@yebezdebdabewoch
ያለ ቅድመ ሁኔታ የሚያፈቅሩ አፍቃሪ ይሁኑ ፍቅር ወሰን ወደሌለው መጨረሻ ወደሌለው ዓለም የሚያስገባ በር ነው ።
ፍቅር መጀመሪያ እንጂ መጨረሻ የለውም ይጀምራል እንጂ አያበቃም ።
ኦሾ/osho
@yebezdebdabewoch
"ሰዎች እየደጋገሙ የትም እንደማትደርስ የሚነግሩህ ከሆነ፤ ድምፃቸውን እስከማይሰማበት ርቀት ድረስ በስኬትህ ጥለሀቸው መሄድ አለብህ!" ይለናል ሚሸል ሩዝ።

አየህ ማን እንደሆንክ ስለማይረዱ አሁን ይንቁሀል፤ ደስ የሚለው ፈጣሪህ የናቁህን አንገት የሚያስደፋ አቅም ውስጥህ አስቀምጧል! ጠንከረህ ብዙ ርቀት ለመጓዝ መነሳት ያለብህ አሁን ነው! ጊዜ የለም ወዳጄ ፍጠን!

@yebezdebdabewoch
#የትኛውም እንሰሳ የተራክቦ ስሜቱን የሚወጣው የሴቷን ሽንት አሽትቶና እርጉዝ አለመሆኗን አረጋግጦ ሲሆን ይህንንም ለማድረግ ወቅትና የሴቷን ፈቃደኝነት ተከትሎ ነው።
#የሰው ልጅ ግን ስግብግብ በመሆኑ ያለ ሴቷ ፍቃድና አስገድዶ ደፋሪ ሆኖ ከእንሰሳ በታች የዘቀጠ የስብዕና ኖሮት አለማፈሩ አስገራሚ ፍጡር ያደርገዋል ።
ኦሾ/Osho
ሞት ለህይወት እንዲህ ሲል ይጠይቀዋል.... "ለምንድን ነዉ ግን ሁሉም አንተን የሚወድህ?።"

ህይወትም እንዲህ ስትል መለሰች "ሁሉም የሚወደኝ እኔ ቆንጆ ውሸት ስለሆንኩ ነዉ፤ አንተን የሚጠሉህ ደግሞ መራራ እዉነት ስለሆንክ ነዉ።"
#ሰው ላይ መፍረድ የዝቅተኛ ሰው መለያ ነው!
💥
ሰው ላይ እንድትፈርድ የሚያስቸኩልህ ባህሪ የሚያሳየው ሁሉንም ሰው ከአንተ በታች ለማድረግ የምታደርገውን ጥረት ነው።

አንድ ሰው ልእለ ሰብነት (ታላቅነት) ላይ ለመድረስ ታላቅ ንቃት ይጠይቃል። ከውስጣችሁ ካለው ተራራ ጫፍ ላይ መውጣትይጠበቅ ባችኋል። ይህ ደግሞ አስቸጋሪ ይመስላል።
💥
ስለዚህ ቀላሉና ርካሹ መንገዱ ራሳችሁን የበላይ ለማድረግ ከመጣር ይልቅ ....ምንም ድካም እማያስፈልገው ሌሎችን የበታች አርጎ መቁጠር ነው።
💥
ለዛ ነው ሰው ላይ ለመፍረድ የምትቸኩለው። ሌላው ላይ ለመፍረድ የምታደርገው ጥረት አንተ የተሻልክ እንደሆንክ ለማሳየት ያለህን ፍላጎት ያረጋግጣል። "ይህ ሰውየ እኮ ሌባ ነው፤ ይህ ሰውየ እኮ ሴት ተደፍሯል፤ ይህኮ የለየለት እብድ ነው።"
💥
ለሁሉም ሰው ልክ ታወጣና መጨረሻ አንተ ብቻ ንፁህ ሆነህ ትቀራለህ። ግን ሰው ላይ መፍረድ የዝቅተኛ ሰው መለያ ነው።"
💥
ኦሾ/Osho
@yebezdebdabewoch
ፍቅርን ማያዉቁ ሰዎች ፍቅር እዉር ነዉ ይላሉ፤
እኔ እላለሁ አይን ያለዉ ብቸኛ ነገር ፍቅር ብቻ ነዉ፤
ከፍቅር ዉጭ ሁሉንም ነገር እዉር ነዉ።
osho
@yebezdebdabewoch
☞ከህይወትህ ውስጥ የወደቀብህን ሁሉ ለማንሳት
አታጎንብስ። አንዳንዴ ለወደቀብህ ነገር ስታጎነብስ በብዛት
ይወድቅብሃል። ስለወደቁት ነገሮች ዘላቂ መፍትሄ አስብ።
ጉዞህንም በጥንቃቄ ቀጥል።
:¨·.·¨: ❀
`·.
@yebezdebdabewoch
እንቀሽማለን
ስላንተ ሳታውቅ ስለኔ አውቃለሁ፣ እራስህን ሳታከብር አከብርሻለሁ ካልከኝ እራስህን ሳትወድ ስለ መውደድ ልታብራራርኝ ሲያሻህ ፣ ለልጅ የምይጥም ተረት ልተርትርኝ ስትሞክር ድንቁርናህን ባደባባይ ገበናህን በገሀድ ትገልበዋለህ። ላንት እውነት ያልሆነ እውነትህን ፣ምንም ያህል ብታላምጠው አልዋጥ ያለ ማንነትህን ልታስረዳኝ ስትፍጨረጨር ፣ ያልሆንከውን ከሆንከው ፣ ያልኖርከውን ከኖርከው ፣ እውቀትህ ከድንቁርናህ ፣ ፅድቅህን ከኩነኔህ መለየት ተስኖህ ያልተረዳከውን ያንተ ያልሆነውን ስብዕና ልታስረዳኝ ስትጀምር እንደተረዳሁህ እንድታስብ ላንተ የተምታታብህን እውነት ለእኔ እንደተገለፀልኝ ከነገርኩህ ካንተ ይልቅ እኔ እቀሽማለሁ።
ካለመኖር ያለየከው መኖርህን ፣ ከሞት ያልተሻለ ህይወትህን ፣ ከጨለማ ያልገዘፈ ብርሀንህን በወረደው የማንነትህ ፀዳል አደብዝዘህ ብርሀን እንደሆንክ ስደሰኩርልኝ እህ ብዬ ላዳምጥህ የጀመርኩ እለት የመዝቀጥን አቦጊዳ መቁጠር እጀምራለሁ።
ላንተ ያልተዋጠልህን ጀብዱ ልተርክልኝ ሲዳዳህ ፣ ሳትወድ የተጫነብህ አስተሳሰብህን ሳልወድ ልትጭንብኝ ስትሞክር ፣ ባልዋልክበት ጦር ሜዳ ጀግና ሆኖ ሲወደሱ ማምሸት ሲያምርክ ልክ እንዳልሆንክ ልነግርህ ካልሞከርኩ ካንተ ይልቅ እኔ መዝቀጥ እጀምራለሁ።
ብቻ ምን አለፋህ ያልኖርነውን ለመኖር ፣ ያልተቀበልነውን እውነት ለማራመድ ፣ የኛ ያልሆነ እኛነትን የኛ ለማድረግ ስይፍጨረጨር ፣ ሰፍቶ አልሆን ያለንን ማንነት በኛ እና በኛ ልክ ብቻ ልናሰፋው ሲገባን ቀጣዩ ትውልድ በማይሆነው እሱነቱ ሲናኝ እና ሲባዝን እንዲኖር ስንፈቅድ ፣ ያንተን ልክ ባንተነትህ ሚዛን ሳይሆን በኔነቴ መስፈርት ልለካው ከቃጣኝ ፣ ስሳሳት ልታርመኝ ስትችል ሳይገባህ ይበል ባይ ፈገግታን ልትቸረኝ ስታትር ያኔ አዎ ያኔ እንተ ሳትሆን እኛ ሆነን ወደ ቅሽምና ገደል ቁልቁል እንምዘገዘጋለን።
@yebezdebdabewoch
የሕይወት ስንቅ ይሆናሉ ያልነውን ተቀበሉን፣*****

."በፍላጎትህና በምትችለው መካከል
ያለውን ልዩነት ለማጣጣም የሚችል ሰብእና ይኑርህ!"
:
√የምትፈልገውን ሁሉ መኖር አንደማትችል ተረዳ።
:
√መኖር የምትችለው የሚያስፈልግህን እንጂ የምትፈልገውን ሁሉ እንዳልሆነ አስብ።
:
"ሁሉ በአንተ እንዲኖር እንጂ ፣ አንተ በሁሉ ውስጥ ለመኖር አትሞክር!"
:
►ሁሉ ወደ አንተ የሚመጣበትን መንገድ ይኑርህ።
:
►አንተ ወደ ሁሉ ለመሄድ አትሞክር።
:
►ሁሉ ለአንተ ተፈጠረ እንጂ አንተ ለሁሉ እንዳልተፈጠርክ እወቅ።
:
►የሚጠበቅብህን ህይወት ኑር አንጂ፣ የምትፈልገውን ሁሉ ለመሆን አትጠብቅ::
@yebezdebdabewoch
መኖር ግን ምንድነው? እንጃ መኖርማ መኖር ነው ይላሉ አንዳንዶች ሌሎች ደግሞ መኖር መታወስ ነው ፣ በሰዎች ልብ ውስጥ መገኘት ፣ ሳይገኙ መገኘት አልፎ አለመረሳት ፣ ሰው መሆን... መኖር መለወጥ ነው ፣ መኖር የራስን ስሜት መግደል ነው ይሉናል ግን እውነት ማነው የሌሌችን ህመም የሚታመመው ማነውስ እራሱን ገሎ ሌሎችን የሚያኖር? ኧረ እኔጃ አለመኖርስ ምን ይሆን? በቃ አለመኖርማ አለመኖር ነው አለመታወስ ፣ አለመገኘት ወይ ደግሞ እየኖሩም መሞት ብቻ ብዙ ይሉናል....
@yebezdebdabewoch
ርዕስ፡(እንዳንድ ፅሁፎች ርዕስ የላቸውም)

አንዳንድ ጊዜ መኖር ካለመኖር ፣ መሄድ ከመቆየት ፣ ከመግባት መውጣት የተሻለ ነው። አዎ አንዳንዴ ወርቅ ነው ካልነው ዝምታ ይልቅ ህመም ያለው ንግግርን አልማዝ የሚያደርጉ የህይወት ዑደቶች አይጠፉም። ህይወት እንደዚህ ናት እንዳንድ ቀናቶቿ ላይ ከአዎንታ አሉታን ፣ ከአዎ አይን፣ ከነው ነበር የመሳሰሉ ብዙ አሉታዎች ተመራጭ ይሆኑባታል። ለዛም ነው የሰው ልጅ ይህን ውጥንቅጡ የወጣን ዑደት ቃላት ደርድሮ ስንኝ ሰድሮ መግለፅ ሲሳነው "ህይወት እንደዚህ ናት" ብሎ በቃላት አስውቦ የተዛባ እሱነቱን፣ ያልተፈታ ህልሙን፣የተወሳሰበ ማንነቱን ፣ የተተራመሰ ሰውነቱን ፣ ያልተገራ ስሜቱን ፣ የከሸፈ ራዕዩን ሊገልፅ ሲታትር የሚስተዋለው።
እውነት ነው በቃ ሌላ ምንም የለም...
"ህይወት እንደዚህ ናት"
@yebezdebdabewoch
Forwarded from 💝 የፍቅር_ደብዳቤዎች💝 (in To the dag👈📴ሃበን)
😔ከህመሜ አልዳንኩም😔
አሞኛል ህመሜ ደግሞ አንተ ነህ
አዎን በድለኸኛል በሰጠውህ ክብር እጥፉን ንቀኸኛል .....

[ 📥Comment @Dpapi ]

╔═══✿💌💌✿═ ══╗
☞ join & share ☜
@yepkil@yepkil
╚═══❀💌💌❀═ ══╝
🌿#Morning_Motivation

ፅናት!

"በዓለም ላይ የፅናትን ቦታ የሚተካ ምንም ነገር የለም። ብቃትም አይደለም። እንደውም ብቃት ያላቸው ስኬታማ እንዳልሆኑ ብዙ ቁጥር ያለው የለም። የረቀቀ ዕውቀትም አይደለም እንደውም ሰዎች እንደማወቃቸው ስኬታማ አለመሆናቸው ቢታይ አስገራሚ ትዕይንት ነው። መማርም አይደለም። ዓለማችን በተማሩና በማይሰሩ ሰዎች የተሞላች ናት። ጽናትና ቁርጠኝነት ግን ሁሉንም ነገሮች ናቸው። የአላማ ፅናት ያላቸው ሰዎች ከየትኛውም ቦታ ተነስተው ያሰቡት ቦታ ለመድረስ ሊያቆማቸው የሚችል ምንም ነገር የለም።" -ካልቬን ኮሌጅ

"እያንዳንዱ ታላላቅ የስኬት ታሪክ የትልልቅ ውድቀቶች ውጤት ነው ። ልዩነቱ ተሸናፊዎች በወደቁበት ተኝተው ሲቀሩ አሸናፊዎች ግን ከያንዳንዱ ውድቀታቸው በኀላ ዳግመኛ በታላቅ ብርታት መነሳተቸው ነው" -ፊዮዶር ዶስቶቭስኪ

መልካም ቀን!
════❥━━━❥═════
@yebezdebdabewoch
አብጄ ይሆን እንዴ!

ምን ነበር ያልከኝ እኔ እና አንቺ ልክ እንደ መርፌ እና ክር ነን ልጠግንሽ ስፈልግ የምቀድሽ ልታድሺኝ ስፈልጊ የምትበሺኝ አዎ እንደዛ ነበር ያልከኝ። እኔ እና አንቺ ልክ እንደ ጫማ ሰፊ ነን። መጠገን ካለብን አንዳችን እምንዳችንን የምንቀድ የነፍስ ሀኪሞች። ትዝ ይልሀል አደል ምድር ላይ የኛ ብቻ የምትመስለን ቦታችን ላይ ከመቅደስ የምናገዝፋት ከመኖር የምንረቅባት የና እና ያንተ መናገሻ ላይ ቁጭ ብለን የጠየኩህ። " ቆይ ድንገት ብለይህስ ብሄድስ ምን አልባት አንድ ቀን ህይወት እዛ ላይ እንድንቆም ብትፈርድብንስ ስልህ ያልከኝ ትዝ ይልሀል አደል? ጉልበት የሚያሳጡኝ አይኖችህን አይኔ ላይ ተክለህ ከአለም በሚያስመንኑኝ እጆችህ አቅፈህ ያልከኝን አረሳውም አደል? አስታውሳለሁ እንዲ ነበር ያልከኝ "እናት መለየትን የሚፈሩ ቀድሞውንም አንድ ያልነበሩ ናቸው" ማብራሪያ አላስፈለገኝም እኚ ቃላትህ በቂ ነበሩ። ዛሬም ድረስ ለሰዎች የሚታያቸው መሄድህ ስህተት እንደሆነ የሚያበስሩኝ የነፍስህ ቃልኪዳን ስለሆኑ መሰል ነፍሴን የብቸኝነት ንፋስ ሊያዝላት የመለየት መርዶ ሊያብረከርካት ሲሻ በአምላኩ ፍቅር የተሰበረ ባርያ ያለ መሰልቸት ሲደግመው አንደሚውለው ዳዊት ለነፍሴ ሳነበልብላት እውላለሁ። አይገርምህም መውደዴ ህይወት ትላንት የፈራሁት ቦታ ላይ አቁማናለች አነዛ ከአይን ያውጣቹ ያሉን ከናፍርት ለሽሙጥ ተሽቀዳድመዋል ፣ ስለ ፍቅራችን ቃል መደርደር ስንኝ መሰደር ዜማ ማርቀቅ ያምራት የነበረች አለም እኛነታችንን ተፀይፋ ስለ መሄድህ ልደሰኩርልኝ ያሻት ጀምሯል። ሰሚ አጣች እንጂ። ህይወቴ ምን ግርም እንዳለኝ ታውቃለህ አዝነውልኝ ይሁን መጎስቆሌ አስደስቷቸው ባይገባኝም ቀን ከሌት እየመጡ እረስቼህ አዲስ ህይወት እንድጀምር የሚወተውቱ እልፎች አጋጠሙኝ። ያለሱ ምን ህይወት አለኝና ልላቸው እፈልግና እተወዋለሁ። ከሽሙጥ ሳቃቸው የዘለለ ምን ሊሰጡኝ። ሲደክሙ! አንዳንዴማ " ሶሲ ንቂ እንጂ እሱ እኮ ሌላዋን ደርቦብሽ ነጉዷል " ይሉኛል። ወይ ግሩም የተያዘ ስፍራ ሌላ ለመደረብ ምን ይቀረውና እላቸዋለሁ ህልመኛ! ብለውኝ ይነጉዳሉ። ነቅቼ የሚሉኝን ከማምን እንቀላፍቼ ባገኝህ እንደምመርጥ ማን በነገራቸው። አንዳንዴማ የእናቱን ቀሚስ መልቀቅ እንደማይፈልግ ጨቅላ ችክ ሲሉብኝ ይህን እላቸዋለሁ " ያልሄደ ከወዴት ይመጣል ያልጠፋስ ይፈለጋል ወይ የነፍሴ መላክ የልቤ ንጉስ አልሄደም።እናንተ ያ ቢታያችሁም እሱ ሁሌም አብሮኝ ነው። መሄድ የመሰላቹ እውነቱ መምጣቱ ቢሆንስ" መከራከሩ ዋጋ እንደሌለው ሲገባቸው ይሄዳሉ። አልሳትኩም አደል? " አዎ አንዳንዴ ማፍረስም መስራት መሄድም መምጣት ነው " ያልከኝ አንተው አደለህ። አንዳንዴማ ቃሉ ከሚያልፍ ሰማይና ምድር ቢያልፋ ይቀላል ልላቸውም ይቃጣኛል።



አሁንስ እውነትም አበድኩ መሰል ጃል ኪኪኪኪ😂
@yebezdebdabewoch
@DayeBT
አውቃለው ጠፍቻለው የጠፋውትም አንዳንድ ስሜቶች ለብእር እጅ አይሰጡም አሁን ላይ ግን ተመልሻለው ከነገሮች ሁሉ በላይ ሆኜ ላጠፋውት ጊዜ ይቅርታ ጠይቃለው 🙏
አስተያየት ካላቹ👉 @DayeBT
@yebezdebdabewoch
አዎ አጥፍቻለው አንቺም ተከፍተሻሻል
ልቤም አንቺን ብሎ ይቅርታሽን ይሻል
በይ ማሪኝ እና ይመቸኝ ት ራሴ
ይቅርታ አርገሽልኝ ልታረቅ ከራሴ
😉😉😁😁
@yebezdebdabewoch
ምንድነው ቢሉኝ ህመምስ በሽታ
መቼ አውቅ ነበር ካንተ ሳልሆን ለታ
ለካስ ናፍቆት ነው ከህመም ህመም
መዳኒት የሌለው ቶሎ እማይታከም
@yebezdebdabewoch
@DayeBT
2024/05/17 05:43:53
Back to Top
HTML Embed Code: