Telegram Web Link
መድሃኒት አለው አልያም ማስታገሻ 💔💔ለተሰበረ ልብ'ስ??💔💔
ይቀጥላል.......
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
🙋@yebezawit2 🙋
" የገንዘብ ትልቁ ኀይሉ የኪስን ድህነት ማጥፋቱ ሳይሆን የአእምሮን ራቁትነት ማጋለጡ ላይ ነው ። "

👉ገንዘብ ኖሮክ አሰተዳደሩን ወይም አጠቃቀሙን ካላወቅክ የገንዘብ ሀያልነት አንተ ላይ ሲሰራ ይታያል እንድትገዛበት (እንድትገበያይበት) የተፈጠረው ነገር አንተን ሲገዛ ይገኛል ያኔ ገንዘብክ የአምሮክን እርቃንነት ልትሸፍነው በማትችለው መልኩ ይገለጣል ይህ ደግሞ አጠቃቀምን አለማወቅ ነው ክፋቱ ያንተ ታውሮ የሌሎችንም ማሳወሩ ።
👉ገንዘብ ኖሮክ ደግሞ አጠቃቀሙን ስታውቀው ግን ገንዘብ መጠቀሚያ እንጂ የአምሮ ወይም የአሰተሳሰብ ልዕልናክን አሊያም ዝቅጠትን የሚያጋልጥ ሳይሆን አንተን የሚያገለግል ስለሚሆን አንተን ጠቅሞ ሌላውን ይጠቅማል።

👉ስለዚህ ገንዘብ በራሡ ነፃ (neutral) ነገር ነው። የማንም የአእምሮ ራቆትነት ብሎም የአስተሳሰብ ልዕልናን አያሣይም ሠውየው ስለ ገንዘብ እና አጠቃቀሙ ያለው እስተሳሰብ እንጂ ገንዘብ ከመጠቀሚያነት ያለፈ ሀይል ያለው ነገር ሆኖ አይደለም።

ዶ/ር ምህረት ደበበ
የተቆለፈበት ቁልፍ
@yebezigetmoch
@yebezawit2 🙋🙋

💔💔💔ሰባራ ልቦች ምሽት ይጠብቁ💔💔💔
😭😭ለሁሉም መድሃኒት አለው አልያም ማስታገሻ 💔💔ለተሰበረ ልብ'ስ??💔💔
ይቀጥላል.......
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
🙋@yebezawit2 🙋
💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔
ክፍል አስራአራት

#ብጫቂ_ገፅ
💔💔💔

ስልኩን ዘግቼ እድልን አየኋት እሷም "ምነው ምንድነው?" አለችኝ። እኔም ብነግራት ፍቅሯን እሷነቷን ላጣው ነውና "አይ ምንም አይደለም የሆነ ፋይል ተገኝቷል መሰለኝ እንሃድ" አልኳት ፈገግ አለች ውበቷ አነፀባረቀብኝ መኪናውን በፍጥነት ሳበር ከሆስፒታሉ ደረስን 'ላጣት ነው....ሰምሃል ትሆን የላከቻት...ምንድነው የምሆነው?...አምላኬ አላየኸኝም እንዴ?' ከራሴ ጋር እሟገታለሁ። ወደ ዶክተር ዘውዱ ክፍል አቀናን እና ትንፋሼን ሰብስቤ በሩን አንኳኳሁ ደገምኩኝ እና ሲጥጥ አድርጌ ከፈትኩት ዶክተር ዘውዱ በፈገግታ ተቀበለን እና ወንበሩ ላይ አረፍ አለን።እድል ጣቶቿን እየፈተለች "እእ ዶክተር ተገኘ" አለችው። ዶክተሩም ዶክመንቱን አገላብጦ "ዶክተር ሊገባኝ ባይችልም ያየሁትን ነገር አስደንግጦኛል" አለኝ ዘውዱ አይኔን እየተመለከተ። "ምንድነው ንገረኝ" አልኩ እድል ሰረቅ አድርጌ እያየኋት የገመትኩት ነገር እውነት ከሆነ ምን እንደማደረግ አላውቅም ጨነቀኝ በቃ የመጣውን ልቀበል ብዬ ስተነፍስ ልቤን ደግሞ ያፍነኛል።
.....ሰምሃል ከልቤ ገብታ ከልቤ የቀረች ሴት ነበረች። ነበረች የምለው ዛሬ እድል ሁሉንም ስለቀየረች ነው በእሷ ባልወደድ እንኳን በመውደዴ እንዳልቆጭ እና እንዳላዝን ፍቅሯ እንድቆጭ እድል የሚባል አልሰጠኝም በቃ በየምክንያቱ እያሰብኳት አፈቅራታለሁ።ምን ያህል ውስጤ ፈርሶ ዳግም እንደተሰራ ማንም ሊረዳኝ አይችልም የሚረዳኝ ቢኖር አፍቅሮ የተለየ እና እውነት የካሰው ነው ፍቅር ግን ፍቅር ነው!💕
"ተመልከተው ፎቶው ያንተ ነው" ዘውዱ ዱብዳ አወረደብን። ታወሰኝ ወደኋላ መርከቤን አንስቼ ስቀዝፍ ታወሰኝ ገና ተመርቀን ስንቀጠር ሰምሃል እና እኔ በፍቅር አብደን ነበር እና የአደጋ ጊዜ ተጠሪ ተብሎ አክሊል ብላ እኔን ሞልታኛለች እኔም ስሟን አስመዝግቤ ነበር የማያውቅ አልነበረም ሲቀጥል በእያንዳንዱ እንቅስቃሴ ፊርማዎቿ ሌሎች ስራዎቿ አክሊል ነው የምትለው እና ልዩ ያደርጋት ነበር። መልህቄን ጥዬ ቆምኩኝ እድል ወረቀቱን አተኩራ እያየች እንባዋን ወደ መሬት ትፈጠፍጣለች "አ...አ..አንተ ነህ..አ..ክ..ሊ..ል?" ጠየቀችኝ። "አዎ ማለት ምን መሸለሽ?" ሳታስጨርሰኝ በእንባ እንባዋን እያረሳች "እኔ ስንት መከራ ሳይ ቢያንስ ከታሪኩ ለምን አልተረዳህም አምኜህ ነበር ከሰዎች ሁሉ ተለይተህ የረዳኸኝ መስሎኝ ነበር ግን ነበር እሺ ቢያንስ ለእኔ እንኳን አታስብም ከእህቴ...." ሳትጨርሰው ከክፍሉ እየሮጠች ወጣች። ብትጨርሰው ለእኔ ደስታ ይሆን ነበር አልኩ በልቤ ወይ ጉድ ደግሞም ስትበሳጭ ውበቷ እንደ ፀሀይ ጮራ ይዋጋል "እድል እድል" ሮጬ ተከተልኳት እና እጇን ያዝኳት "ምን እስኪ ንገረኝ አንተ እኮ አክሊል ነህ ለእህቴ አክሊሏ ለእኔ ደግሞ የመውደዴን እውነት ማሳያ ከጎኔ ነበርክ ታውቃለህ ስለአንተ ማሰብ መጀመሬን ስለአንተ መጨነቄን አታውቅም ብታውቅም ትርጉም የለውም...በቃ ልቀቀኝ አክሊል ዋጋ የከፈልኩት ለእህቴ ነውና እሷ ጋር ሂድ የምታፈቅራት ጋር የማትሸፍትባት ሰምሃል ጋር" ስሟን ጠራቻት "እኔንም አድምጭኝ ቆይ ስሟን ነግረሽኛል አንቺ ስታስቢኝ እኔ ደግሜ አስቤሻለሁ ስትስቂ ነው የሳኩት በአንቺ ምክነያት ነው ከቤተሰቤ የተታረኩት ግን አላውቅም አልነገርሽኝም" ጮሁኩባት።
"ለፍርድ ቀላል ነው ግን አንተስ ታሪክህን ያፈቀርካትን ልጅ ብትረሳ ትዝታዎችህን እንዴት ትረሳለህ አፈቅራታለሁ ካልክ እንዴት አልገመትክም በቃ ተወው ይቅር የእኔና የአንተ ነገር ለፍርድ አይመችም ከቻልክ ነገ አብረን ሄደን እህቴን እያት ቁስሏን በአይኖችህ አክምላት በእጆችህ ዳብሰህ አስረሳት እኔን ግን ተወኝ" እጇን ከእጄ አስለቀቅ እየሮጠች ወጣች። እዛው ወለሉ ላይ ተቀመጥኩ እንባዬን እንደ ክረምት ዶፍ እያዘነብኩ በእግሮቼ መሀል ተደብቄ ዝም አልኩኝ ዝም....
ይቀጥላል
💕💕ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ💕💕
ድምፅ ስጡ!!!
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezawit2 🙋
የመጨረሻው ክፍል እየደረሰ ነው
🙋ሰላም!!

💔ሰባራ ልቦች💔 በቀጣይ #ብጫቂ_ገፅን ይዞላችሁ ይቀርባል!!
💕💕💕መልካም ንባብ💕💕
💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔
👉 #ብጫቂ ገፅ👈
ክፍል አስራአምስት 💕💕💕
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezawit2
...........ነገሮች እኔ እንደፈለኩት መሄድ አልቻሉም እናም እንደምንም ከወደኩበት ተነስቼ በድን ሰውነቴን እየጎተትኩ ወደ ቤቴ ገባሁኝ እናቴ ግን ከእኔ ኋላ እድል ስትጠብቅ ነበርና "የለችም" አልኳት እና ተወርውሬ አልጋው ላይ ተኛሁ ተንሰቀሰኩ....ዛሬን አያድርገውና በፊት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስማር ወንዶች ሲያልቅሱ ካየሁ ውሸት ነበር የሚመስለኝ ከልብ ለካ ህመም ሲመነጭ እንባም ያነሳዋል።ሰምሃልን አልክድም ወድጃታለሁ ግን እንድኖርባት ሳይሆን እንድማርባት የተሰጠተችኝ ነበረች። ከእሷ ጋር ያላሳለፈነው አንድም መልካም ነገር የለም።ተጣልተን ተኮራርፈን እንኳን እጅ ለእጅ ተያይዘን ነበር የምንሄደው የሆነ ቀን አስታውሳለሁ አንድ መልከመልካም ወጣት ወደእኔ ስትመጣ ይለክፋት እና እሷም ስትስቅ ተመልክቼ ደሜፈላ አቅፌ ሰላም ብያት እጆቿን ይዤ ወደምዝናናበት ቦታ ቃል ሳይወጣኝ ደረስኩ ሰምሃልም ስለገባት ንዴቴ ይቅርታ ብላ ተማፀነችኝ አውቃለሁ ሰምሃል ሳቋ ቦታ የለውም ግን እኔም ምን ያህል እንደምቀና ታውቃለች እና እንዲህ በመሆኗ ተናድጄ ነበር።

ዛሬ ግን መናደድን አለመኖርን ትቼ መኖርን መርጫለሁ አለማፍቀርን ሳይሆን ፍቅርን መርጫለሁ💕ፍቅርን ለትልቆች እና ለእድለኞች የሚሰጣቸውን ነው የመረጥኩት ያውም ልቧ አንደ እናቴ ነጠላ ስስ የሆነ እንደ ንፃቱ አስተሳሰቧ የደመቀ ድርድር ጥርሶቿ የጠዋቷን ጮራ ከመሰሉት ከውቧ ከትሁቷ ከዝምተኛዋ እና ከተጫዋቿ ከእድል አስቀርቶኛል ከፍቅሯ ውሃ አስምጦኝ ለመውጣት እንኳን እንዳልመኝ አድርጎኝ አየር ማጣቴ ቢያሰቃየኝም ደስ እንዲለኝ አድርጎኛል። እድል ለእኔ በልብወለድ እና በፊልም የማውቃት ናት። ለእኔ ስለስብራቴ ስለድክመቴ እና ስለሀዘኔ የተሰጠችኝ የክፉ ቀን ሽልማቴ የጨለማዬ ማብሪያ ጧፌ ናት።
"የት ጥለሀት ነው?" እድልን የወደደቻት እናቴ ጠየቀችኝ።
"በቃ አትመጣም" መለስኩኝ።
"በዛች ከንቱ ነው እሷንም ጥለህ የመጣህ ምን አደረገችህ?" የእናቴ መልስ አበሳጨኝ።
"ተይኝ እማዬ በቃ እድል ማለት ጤነኛ እና ቤተሰብ ያላት ናት በዛ ላይ ከንቱ ላልሻት እህት ናት እኔን ፍለጋ አዲስአበባ መጥታ ነው የተሰቃየችው እማዬ እባክሽ ተይኝ" በጩኸት ተናገርኩ አባዬ ከእናቴ ኋላ ሆኖ ተመለከተኝ።
ከአይኔ የሚወርደው እንባና ከአፍንጫዬ የሚወጣው ቀጭን ንፍጥ ገፄን አበስብሶታል "ወደድኳት ድጋሜ ሰው መሆን ፈለኩ ድጋሜ ልጃችሁ ሆኜ ላኮራችሁ ነበር ግን አልሆነም ድጋሜ የሀዘን በትር ልቤን ገረፈው" ተደፍቼ የአልጋዬን አንሶላ ማራስ ጀመርኩ።ማንም ምንም አላለኝም ዝም ብለውኝ ሄዱ እዛው ተደፍቼ እያለሁ ሰዓቱ መንጎዱ ሳይገባኝ የአእዋፋት ዜማ ተሰማኝ ቀና አልኩኝ ጭንቅላቴ ለአንገቴ ከበደው አይኖቼ ሊፈርጥ የደረሰ ቲማቲም መስሏል እንደምንም ስልኬን አብርቼ ተመለከትኩ መልእክት ደርሶኝ ነበር አዲስ ቁጥር ነው
"አውቶቡስ ማዞሪያው ጋር ቆሚያለሁ እስክትመጣ አልሄድም እድል ነኝ" ይል ነበር እንዴት እንደተነሳሁ አላውቅም ፊቴን በውሃ ሳላብስ ትላንት ዶክተር ዘውዱ ያመጣልኝን መኪና እያከነፍኩ ካለችኝ ቦታ ደርሼ በአይኔ አማትሬ ፈለኳት። አየኋት ከሰው መሀል ድንጋይ ላይ ተቀምጣ በያዘችው ደረቅ እንጨት መሬት ስትጭር ከመኪናው ወርጄ ፊቷ ተደነቀርኩ በሃሳቤ ዘላ ስታቅፈኝ አንገቴ ስር ገብታ በጠረኗ ልቤን ስታዘልል አሰብኩና ፈገግ አልኩኝ ስመለስ ግን አይደለም።"እድል" አልኩኝ ካቀረቀረችበት ቀና ብላ አየችኝ እሷም በእንባ እና በእንቅልፍ እጦት ፊቷ ገርጥቶ ነበር ብድግ አለችና "እንሂድ" አለችኝ። "ሰላም አትይኝም" ሰላምታዋን ናፍቄ። "ሰላም እንዳልሆንክ አውቃለሁ ጠይቀህ ደግሞ..." በድፍረት አቀፍኳት። ያሳለፍናቸው ጊዜያት በአይኔ ውልውል አሉ። ከእቅፌ ከቆየች በኋላ "ልዑል አይሆንም በቃ ይቅር" አለችኝ። ለቀኳት እና አየኋት "እርግጠኛ ነሽ ይቅር አትወጂኝም?" ጠየኳት ራስ ወዳድነቴን እየታዘብኩ። "አልወድህም አላልኩም ግን ልክ አልነበርኩም አንተ ማለት ለእህቴ ፍቅሯ ነህ የእህቴ ፍቅር ለአንተ ፅድቅ የሌላው ደግሞ ሀጢያት ነው" አለችኝ በሀዘን ተሰብራ። "አንቺ ግን እህቷ አይደለሽም አንቺንም በድላሻለች እኮ" መለስኩላት እሷ ግን ጥላኝ ወደመኪናው ገባች እኔም ተከተልኳት እና ሞተሩን አስነስቼ ለእሷ ደስታ ወደ ጅማ ጉዞ ጀመርን። በስሱ የከፈትኩት የፀጋዬ እሽቱ ዘፈን(እንክት ይበል ድቅቅ ጎኔን አይመቸው መቼም ያለወዳጅ አይደላም የለ ሰው...) እየሰማን የአዲስአበባ ምድርን ጥለን ወጣን። "ልዑል" ስሜን ስጠራው አፏ ላይ ከማር ይጥማል ሰምሃል አክሊሌ ስትለኝ እንዲህ አይሰማኝም ነበር ልጅ የሆንኩ ያህል ይሰማኛል። "ወዬ" አልኳት የምትለኝም ልሰማት ዝግጁ እንደሆንኩ እንድታውቅ ሰርቄ እያየኋት "ታውቃለህ ሳገኝህ ከዶክተር አሊ ሌላ ጥሩ ሰው ስላይታየኝ የምትረዳኝ አልመሰለኝም ነበር ብዙ ጊዜ ስታወራኝ እና ሀሳብህን ስታጋራኝ ውስጤ እወቂው ቅረቢው ይለኝ ነበር...እእእ..ይሄን የምነግረህ ውስጤ ያለውን አውርቼ እንዳወጣው ነው። ከሁሉም ነገር በላይ እናትህ ለእኔ ሲጨነቁ አንተም ደውለህ ስለእኔ ስትጨነቅ ታውቃለህ የማረሳው ቀን የልቤን ደውል የደወልከው መቼ እንደሆነ..." ጠየቀችኝ። ለመስማት ጓጉቼ "መቼ ነው" አልኳት። በመስኮቱ የሚገባው ንፋስ ፀጉሯን እየረበሸ ወደፊቷ የመጣውን ወደኋላ እየመለሰች "እናትህ የእጅ ስራ ዳንቴል አስተምረውኝ ከብዙ ሙከራ በኋላ ሲሳካልኝ አንተ ቲቪ ከአባትህ ጋር እያየህ ከደስታ ብዛት መጥቼ ሳሳይህ እንኳን ይሄን ሌላም የሰራል ውብ እጅሽ ብለህ እጆቼን ሳምካቸው...ለሊቱ ሙሉ እጄን ሳየው ነበር ያደርኩት በቃ ለምን እንደሆነ ግን አላውቅም " እንቧ ቀደማት የዚን ያህል ቦታ ልቧ ላይ አግኝቼ ማጣት የእግር እሳት ነው አይ ሰምሃል...አልኩኝ በልቤ። ጅማ ደረስን። ከጅማ ወደ መቱ መሄድ አለብን እና "ምግብ እንብላ" አልኳት። "እህቴ ከሞት ጋር ተቃጥራ እየጠበቀችኝ ነውና መብላት አይደለም መቆም አልፈልግም" አለችኝና ርሃቤን ገደለችው ከመኪናዬ የማይጠፋውን ውሃ ተጎንጭቼ ወደ መቱ መንገድ ቀጠልን መቱ ልንደርስ ትንሽ ሲቀር ጀምበር አዘቀዘቀች እኛም መቱ ላይ ሆቴል ይዘን አረፍን።ነገ የመጨረሻ ቀን ነው ሰምሃልን ላያት ነው እድልን ደግሞ ልሸኛት......ጨለማውን ባይነጋ ብዬ ረገምኩት....😭😭😭😭

ቀጣይ ክፍል ነገ ምሽት ይጠብቁ!!
💔💔ሰባራልቦች ብጫቂ ገፆች💔💔💔
ደራሲ 👉ቤዛዊት የሴትልጅ👈
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
👉 @yebezawit2 👈
💔ሰባራ ልቦች💔
#ብጫቂ_ገፅ
ክፍል አስራስድስት
ደራሲ ቤዚ የራጉኤል ልጅ
@yebezawit2
💔💔

............ግን ፃድቅ አይደለሁምና ለሊቱ ተገፎ የማለዳዋ ጮራ ፈነጠቀች እድል ውጪ ነበር የጠበቀችኝ ሳያት ደነገጥኩ ለሊቱን ባትተኛ እንጂ ብዬ አሰብኩ.."ደህና አደርሽ" አልኳት "ደህና" መለሷ ውስን ነው"ቁርስ እንብላእና እንሄዳለን" አልኳት። "አንተ ብላ እኔ በልቻለሁ" አለችኝ መልሷ የእውነት አሳቀኝ እንኳን ልትበላ ከክፍሏ አልወጣችም ነበር"ውሸት አትችይም" አልኳት እና እጇን ጎትቼ ወደ መመገቢያ አዳርሹ ገባን ቀላጣፋው አስተናጋጅ ሲመጣ ለቁርስ የሚሆን ቀለል ያለ ምግብ አዘን ተመለሰ።"የውሸት ንፃት ግን ይለያል" አልኩ መሀላችን የነገሰው ዝምታ እያሰፈራኝ።"መሬት ወድቆ ነው ያገኘሁት" አለች እድል የጠረጴዛውን ጨርቅ እየነካካች።"ታውቃለህ ለሊቱ ከመርዘሙ ብዛት ሁለት ለሊት ነው የሆነብኝ" አለችኝ ቀጥላ።"በእርግጥ እኔም አልተኛሁም ታዲያ ለምን እኔ ጋር አልመጣሽም ማለት አልጠራሽኝም" አልኳት።ፈገግ ብላ አየችኝና "ደረቅ" አለች።ፈገግታዋ ልብን ደስ በሚያሰኝ ስሜት ይወጋል አይኖቿን እያየሁ ባረጅ ብዬ ተመኘሁኝ በአርምሞ እያየኋት ብኖር በታደልኩ።አስተናጋጁ ምግቡን ጠረጴዛው ላይ ደረደረው እና "መልካም ቁርስ" ብሎ ተመለሰ።....

ምግብ በልተን ከጨረስን በኋላ ወደ መኪናዬ ገብተን ጉዞ ወደ መቱ ጀመርን።ዳርዳሩን በትላልቅ ዛፎች የታጠረው መንገድ አረንጓዴነቱ ልዩ ውበት ሰጥቷል በመስኮቱ በሚገባው ቀዝቃዛ ንፋስ እየታጀብን መንገዱን ጨርሰን ከትንሿ እና ታሪካዊቷ የጎሬ ከተማ ደረሰን።የጠዋቷ ፀሀይ ወደቤቷ ለመመለስ እያዘቀዘቀች ነውና ማደሪያችንም አሳስቦኛል ከዛ በላይ ግን ምን ማድረግ እንዳለብኝ አስጨንቆኛል። ሰምሃልን እድልን ባየሁባት አይኔ ልመለከታት ነው። "ልዑሌ እዚህ ጋር አቁመው" አለች እድል። ልዑሌ ስትለኝ ምን ያህል ደስ እንዳለኝ ቢያደርግልኝ ኖሮ ለመዝናናት ነበር ከእሷ ጋር መምጣት ነበር። የመኪናውን ሞተር አጥፍቼ ከመኪናው ወረድን እና ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያንን ለመሳለም ተጠጋን ቆሜ መላ ሰውነቴን እያማተብኩ እድል የሚያውቋትን አባት አግኝታ ጉልበት ስማ ሰላምታ ሰጠቻቸው ይበልጥ ውበቷ እና ስነስርዓቷ ታየኝ "የኔ ልጅ የት ተሰውረሽ ነው" አሏት አቀፈው እንደ ልጅ እየተመለከቷት።"አዲስ አበባ ነበርኩ አባቴ" እድል መለሰችላቸው። "አይ የኔ ልጅ ብትጠፊ ጊዜ ስንት ወገን ተራበብሽ መሰለሽ" አሉ በሀዘን አቀርቅረው። እድል ዝናብ ሊዘንበብ ሲል የሚሰማውን መብረቅ የሰማች ይመስል ክው አለች።"አባ ይቅር ይበሉኝ ጥቅሜን አብልጬ መሄዴ አግባብ አይደለም ግን የእህቴ ነፍስ በሰላም እንድታርፍ ብዬ ነው" አለች አይኗን እንባ ሞልቶት።"ተይ የኔ ልጅ እንዲህማ አትበይ መጥፋትሽ ነው እነሱንም ያሳሰባቸው እንጂ ረሃቡስ እንዲያው አልፈውታል..ይልቅ ተሳካልሽ" አሏት። እድልም እኔን ዘወር ብላ አየችኝና "አዎ ፈረሰኛው ጊዮርጊስ አድርጎልኛል" አለቻቸው። እሳቸው "እሰይ ምን ይሳነዋል..በይ የኔ ልጅ አላስቁምሽ እኔም ልጄ ጋር ነው የምሄድ ነገ እንገናኛለን" አሏት እና በያዙት መስቀል ባረኳት እሷም ጉልበታቸውን ስማ ደግማ የደረቁ እጆቻቸውን ስማ ወደ እኔ መጣች። "ይቅርታ አባ እኮ..." ሳላስጨርሳት "ደስ የምትይ ክርስቲያን ነሽ" አልኳት ኮረብታማውን መንገድ እየተጓዝን። "ምን አድርጌ ባክህ በነገሬ ሁሉ ክርስቲያን ብመስልም እምነት የጎደለኝ ንፁህ እኮ አይደለሁም" አለኝ መልሷ ይጠጥራል። "ግን ኮርቼብሻለሁ" አልኳት እጄን ኪሴ ውስጥ እየከተትኩ። የከሰአቷ ፀሀይ ግንባራችንን እየለበለች ነው እናም ኮፍያዬን አውልቄ ለእድል አደረኩላት እና "እድሌ ግን ትምህርት ተምረሻል አልኳት።"ብዙም ባልገፋም አዎ ተምሪያለሁ እስከ አስር ያውም ከመጨረሻ አንደኛ ነበር የምወጣው" አለች እየሳቀች። "ሰነፍ አታነቢም ማለት ነው" አልኳት። "ወይ ጉድ አባቴም እኮ ያለ እኔ ጥናት አልወድም ከክላስ ፎርፌ እንዳውም ቤተክርስቲያን ነበር የምውለው" አለችኝ። "ይገርማል ሰው ይዝናናል አንቺ ቤተክርስቲያን" አልኳት። "ነፍስህ ሰላም ከሆነች ተዝናናህ ማለት ነው" አለችኝ እና "በነገራችን ላይ ይሄ ጥምቀተ ባህሩ ነው እዚህ ጋር ድንኳን ተጥሎ ነው የምናድረው...ይሄ ምንጭ ደግሞ መቼም የማይደፈርስ ውብ ነው" ብላ ምንጩን አሳየችኝ የተፈጥሮ ውበት የተቸራት ጎሬ እጅግ ትለያለች። "ዋው በጣም ያምራል" አልኳት። እጇን ወደ አንድ ግቢ እየጠቆመች "እዛ ግቢ የሚኖሮ ሼህ አሉ እናም ደግ እና ፍቅር ናቸው ብታይ እዚህ ለበዓል ስናድር ሲጨነቁልን" ብላ በሃሳብ ቆማ ተከዘች። "ደስ የሚል ትውስታ አለሽ" አልኳት እድልም "አይመለስም እንጂ" ብላ ትልቁን ለምለሙን ሜዳ ማቋረጥ ጀመርን። "ይሄ ሜዳ በነገራችን ላይ አውሮፕላን ማረፊያ ነበር" አለችኝ።...ወዲያው ግን ሰማዩ ጉም አዝሎ ዝናብ ማካፋት ጀመረ። "ወይኔ የህንድ ፊልም ልንሰራ ነው" አልኳት አቅፊያት በቶሎ እየተራመድን። "አታስብ ደርሰናል" አለችኝ እውነትም ትንሽ ዝናብ ካበሰበስን በኋላ አንድ በር የሌለው በጫካ የተከበበው ግቢ ደረስን ወንድነቴ ክዶኝ ጉልበቴ ተብረከረከ መተንፈስ እስኪያቅተኝ አየር አጠረኝ መላ ሰውነቴን ላብ አጠመቀው የምሆነው ሁሉ ግራ ገባኝ እና እድልን አየኋት ላቤ ከዝናቡ ውሃ ተደባልቆ አያስታውቅም "ልዑሌ የእውነት ልፋቴን ከተረዳኸኝ እባክህ ሰሚን እንዳታሳዝናት በእግዚአብሔር እጅ ላይ ናት" አለችኝ። "ፈራሁ እድልዬ ግራ ገባኝ እንዴት ነው የምሆነው ምንድነው የምላት እኔ እኮ አንቺን.." ተጠምጥማ አቅፋኝ ተንሰቀሰቀች እና "ለእኔ ብለህ አድርገው በቃ እኔን እርሳኝ እሺ" ብላ ጥላኝ ከፊቴ በዝናቡ እየራሳች መራመድ ጀመረች ከጎጆው ቤት የሚወጣው ጭስ ከደመናው ጥቁረት ጋር ሌላ ገፅ ሰጥቶታል እንባዬን ጠርጌ እድልን ተከተልኳት "እማማ" ብላ እድል ጮክ ብላ ተጣራች።"ማነው?" ብላ እናቷ አንገታቸውን ብቅ አደረጉ እኔም ደንግጬ ከእድል ኋላ ዝናብ ውስጥ ቆሜ ቀረሁ።.....ሁለተኛ የፍቅር ህመም ያውም በአንድ ገፅ ላይ ከፋኝ የእናቴ ማህፀን ሳለሁ በሞትኩ ብዬ ተመኘሁ በልቤም አብዝቼ ሰምሃልን ረገምኳት እንዳዛ እየወደድኳት ያለምክንያት ጥላኝ መሄዷ ሳያንስ ዛሬም ሰው መሆኔን ዳግም በጠበጠችው በህይወት ሳለች ገድላኝ በሞቷ ልትቀብረኝ ነው ምን አይነት እርግማን ነው? አልኩኝ በልቤ ሰማዩም ከእኔ ጋር አብሮ እያነባ የእድልን እናት አተኩሬ ተመለከትኳቸው።.....
😭😭😭ይቀጥላል💔💔💔
💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔
አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ
👉ምድር ላይ ያለ ክፉ ነገር በፍቅር ይሻራል ህመም በፍቅር ይድናል ጨለማ በትዕግሥት ይገፈፋል ብርሃን በፍቅር ይደምቃል አብሮነት በመከባበር ይጠነክራል በፍቅር ደግሞ ይሰምራል!😍የዚህ አይነት መከራስ በምን ይሻራል? የመለያየትን ባህር በምን ይከፍሉታል? ፍቅር አሻጋሪ እንዳይሆን ተከፍሏል...የተከፈለ ፍቅር በምን ይጠገናል???
💔💔ሰባራ ልቦች የመጨረሻዎቹ ክፍሎችን ለማግኘት ድምፅ ይስጡ💔💔💔
👉ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ💀
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
👉 @yebezawit2 👈
💔💔ሰባራ ልቦች 💔💔
📚በዛሬው ዕለት ባለመኖሩ እጅግ ትልቅ ይቅርታ እየጠኩኝ በነገው እለት ሁለት ክፍሎችን ወደ እናንተ የማቀርብ መሆኔን በታላቅ ትህትና አሳውቃለሁ!
💕💕 ስለምትሰጡኝ ሃሳብ አስተያየት ፍቅር እና ክብር አመሰግናለሁ💕💕
@yebezawit2
@yebezigetmoch
ቤዛዊት የሴትልጅ
💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
💕 #ብጫቂ_ገፆች
ክፍል አሰራሰባት 😍



"የኔ ጎሳ" ብለው ደርባባዋ የእድል እናት ወደ ደረታቸው አስጠግተው አቀፏት እና እኔን ተመለከቱኝ።እድልም ከእቅፏቸው ወጥታ እኔን ዘወር ብላ አየችኝ እና "ምን ሁነህ ነው ና እንጂ" አለችኝ ደረቄ መቆሜን ተመልክታ።እኔም ቀስ ብዬ ወደ በረንዳው ተጠጋሁ እና ለእናቷ እጅ ነስቼ ቆምኩኝ።እናቷም በስስት እና በፍቅር አይን አያዩኝ "ማነው እድሌ" አሉ። እድልም "እሱን ነገ ጠዋት ታውቃላችሁ ለዛሬ ግን የእኔ እንግዳ ነው" አለቻቸው እና ወደ ውስጥ ይዘውኝ ዘለቁ ቤቱ በሚነደው እንጨት ሞቋል በግራ በኩል የታሰሩት ሁለት ጥጆች ተቀምጠዋል።"ልብስ እስከማመጣልህ እዚህ ጋር አረፍ በል" ብላኝ እድል ወደ ማጀቱ ዘለቀች። እኔም ከላይ እስከታች የገጠሯን ጎጆ ቃኘኋት ደርባባዋ እናትም ከማጀቱ ሆነው ምግብ እያዘጋጁ እንደሆነ የገባኝ "አንቺ ልጅ እንዲያው በባዶ ቤት ታመጫቢኛለሽ አይደል አሁን ይሄን ይበላል" ሲሏት ነበር።እኔም ምግቡ ምን እንደሆነ እያሰብኩ እድል ልብሱን ይዛልኝ መጣች የማን እንደሆነ ባይገባኝም ቁምጣና ቲሸርት ከቡልኮ ጋር ነበር ያመጣችልኝ።እኔም ልብሱን ቀይሬ ልብሴን በረንዳው ላይ አስቀምጬ ብሉኮዬን ደርቤ ተቀመጥኩኝ እድልም ረጅም ቀሚሷን ለብሳ ከፊቴ ተቀመጠች እና አይኔን መመልከት ጀመረች።አይኖቿ አይኔን ሲመለከቱ ያለሁበት ቤት የአማቼ እንዲሆን ተመኘሁኝ።"ሀገራችን እንዴት ናት?" አለች እጆቿን እርስበርስ እያፋተገች "አንቺ ያለሽበት ቦታ ሁሉ ውብ ነው" አልኳት።ፈገግ አለችልኝ እና "ልዑሌ ነገ ሰምሃል ትመጣለች እና አደራ እሺ እኔን ሳይሆን እሷን አስባት" አለችኝ።እኔም ፀጉሬን ዳበስ አድርጌ "እሺ ግን አንቺን አለማሰብ ለእኔ የማላውቀውን ሀገር እንደመናፈቅ ይሄን ካወቅሽልኝ ሌላው ቀሪ ነው" አልኳት።እሷም "ግን የእህቴ ፍቅር ባትሆን አገብቼህ እራስህን የመሰሉ ልጆች ነበር የማሳቅፍህ" አለችኝ ድምጿን ቀንሳ።"ስንት ልጆች" አልኳት ከዚህ ጨዋታዋ እንዳትወጣ "ያው መንታ ሁለት ልጆችን" አለችኝ እና ብድግ ብላ ወደ ማጀቱ ገባች።እኔም በሀሳቤ ኑሮዬ ከእሷ ጋር ቀለስኩኝ ወዲያው እድል ከማጀቱ የጣት ውሃ ይዛልኝ መጣች። እናቷም ገበታውን ከፊቴ አቀረቡት እና "እንዲያው በባዶ ቤት ይዛህ መጣች ይህቺ ቀዥቃዣ" አሉ ስጋወጡን ፊቴ እየጨለፉ።ፍቅር ደግነትን አየሁባቸው።"ብላ የኔ ጌታ" አሉ ቆረሰው እንጀራውን እየቀመሱ እኔም ከእድል ጋር አብሬ መብላት ጀመርኩ እሳቸውም ቡናውን እያፈሉ "እነ ኮከብም እህትሽ ነገ ነው የሚመጡት" አሉ እድልን እያዩ እድልም "ይሁን እናቴ ሰምሃል ግን ደህና ናት" አለቻቸው እና ልብ ምቴን ቀየረችው።"ደህና ናት ይኸው ዛሬ ማርያም ጸበል ከገባች ሰባት ቀን ሆናት ነገ ይመጣሉ አብረው ነው የገቡ እኔም የእርሻው ነገር ቢያሳስበኝ ነው የቀረሁ" አሏት በሰባራው ሸክላ በገል ቡናው እየቆሉ።"ጎበዜ የለም እንዴ" አለች እድል የሚያወሩት ባይገባኝም ግን አይኖቼን እያማትርኩ እሰማቸው ነበር።"ብላ የኔ ልጅ እድሌ ብላ በይው እንጂ" አሉ እድልም በእናት አይኗ እየተመለከተችኝ "አንተ ብላ አርፈህ" አለችና ፈገግ አለች።"ጎበዜማ አያቱ ታመው ሄዷል" አሉ ገሉን እያወረዱ። እኔም ምግቡን ጥግብ አድርጌ በልቼ ገበታው ከፍ አለ።

ቡናው ተፈልቶ እጣኑ ተጫጭሶ ቤቱ ደምቋል ጎረቤቶችም ተሰባሰባዋል መጨነቄን ከአይኖቼ የተመለከተችው እድል በአይኖቿ ምልክት ሰጥታኝ ወደ ውጪ ወጣሁኝ።"የሚያጫውትህ ጠፋ አይደል....ተረዳቸው የሰብላቸው ነገር አሳስቧቸው ነው" አለችኝ እና ከድንጋይ ካብ ላይ ተቀምጠን የምሽቱን ውበት መመለከት ጀመርን። "ታዉቃያለሽ በዚህ ሁኔታ ከአዲስአበባ እወጣለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም" አልኳት። እድልም "እድሜ ለእኔ ሰው አደረኩህ" አለችኝ እና "ስማኝማ ልዑሌ" አለች ስሜን በማር አንደበቷ እየጠራች እኔም "ሁሌ ነው የምሰማሽ" አልኳት "እእ አላውቅም መልስህን ማወቅ ስለፈለኩ ነው" አለች "ማወቅ ያለብሽ ነገር ከሆነ ጠይቂኝ የምደብቅሽ ነገር አይኖርም" አልኳት። "እሺ አሁን ሰምሃል አብረን እንሁን ብትልህ..." ጥያቄዋ ስለገባኝ ዝም አሰኘኋት እና "በፊት ቢሆን ደስታዬ ልነግርሽ አልችልም እድል አታምኚኝ ይሆናል ሰምሃልን ከመናፈቄ ብዛት በለሊት አብረን ተቀምጠን ካወጋንበት ቦታ ሄጄ አውቃለሁ አንዳንዴማ አይኔን ጨፍኜ ስገልጥ አጠገቤ ባገኘኋት እል እና ተንበርክኬ በጸሎት ተንበርክኬ እለምነው ነበር። ሰምሃልን ያጣኋት በሃጢአት ብዛት ነው ብዬ ፍቅርን ረግሜ ራሴን ተጸይፌ ነበር ግን እግዚአብሔር ይሄንን አይቶ አልተወኝም ከእብድ መለስ አርጎ አቁሞኛል። በዛ ጊዜ ነፍሴ የምትፈልገው ከሞት የሚያድናት ሳይሆን የሚገላትን ነበር ግን አንቺ መጣሽ ደስተኛ እና ተስፈኛ አድርገሽ ዳግሜ በሂሶጵ እንደተረጨ በደለኛ ዳግም ነፃው ፊቴ ፈካ የእምዬን ፈገግታ አየሁብሽ የአባቴን ፍቅር አገኘሁብሽ ግን ይኸው አሁንም ላጣሽ ነው መሰለኝ ፈርቻለሁ ግን መለሴ አይሆንም ነው" አልኳት እና ከድንጋዩ ላይ ተነስቼ "ወደ ቤት እንግባ" አልኳት እድልም ዘላ አቅፈችኝ እና "ምን አለ ባላውቅህ ምን አለ ባልወድህ" አለች።


💔💔💔ሰባራ ልቦች💔💔💔
😭አሳዛኝ የፍቅር ታሪክ💕💕💕

ይቀጥላል.....
#ብጫቂ_ገፅ
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezawit2
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
በኔትወርክ ምክንያት በመጥፋቴ ይቅርታ እጠይቃለሁ!! መልካም ንባብ🙏💕
💕🌹ሰባራልቦች💔💔💔
🌿ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ🌿
🌹ክፍል አስራስምንት🌹

#ብጫቂ_ገፆች
.
.
.
.
..ከመደቡ ላይ እየተንጠራራሁ ተነሳሁ የረበሸኝ የከብቶቹ ድምፅ ነበር እነሱ ግን ለምደውታል በለሊት መነሳት እንደምንም ተነስቼ ወደ ውጪ ወጣሁኝ የማለዳዋ ፀሀይ እንደ ህፃን ልጅ ፈገግታ ውብ ነች በረንዳው ላይ ቁጭ አልኩኝ እና አገጬን በእጄ ላይ አስደግፌ በሀሳብ መነንኩኝ። የእድል እናት ከብቶቹን ሜዳ ላይ አውጥተው ሲለመሱ ተመለከቱኝ እና "ደህና አደርክ የኔ ልጅ" አሉ መቀነታቸውን ጠበቅ እያደረጉ።"እግዚአብሔር ይመስገን ደህና አደሩ" አልኩ። ካለሁበት ሀሳብ ለመውጣት እየተንቦጫረኩ።"መኝታህ ተመቸህ"አሉኝ እኔም "ተመችቶኛል ጥሩ ነው" ብዬ እንቅልፍ ማጣቴን ሸሸኩኝ።"መልካም በል ና ቁርስ ላቅርብልህ" አሉኝ በእናትነት ፍቅር። እኔም "አይ እቆያለሁ እድል የት ሄዳ ነው" አልኳቸው። እሳቸውም "እድል አባ ኪዳንን ልታገኝ ቤተክርስቲያን ሄዳለች።መች እሷ ትቀመጣለች" አሉኝ። እኔም ብድግ ብዬ "ጊዮርጊስ ነው የሄደችው" አልኳቸው። "አዎ" አሉ ደርባባዋ የእድልእናት። እኔም የታጠበልኝን ልብሴን ለብሼ ወደ ቤተክርስቲያኑ ሄድኩኝ። የእድል እናት ወ/ሮ እልፌ ብቻዬን እንዳልሄድ ቢፈልጉም አውቀዋለሁ ብያቸው ነበር የወጣሁት ሜዳውን አንዴ በሩጫ ሲለኝ በእርምጃ አቋርጬ በኮረብታው ደረስኩኝ ብቻዬን ሳወራ እጄን ሳወናጭፍ ለተመለከተኝ ጀማሪ እብድ ነበር የምመስለው። ከቤተክርስቲያኗ ስደርስ መላ ሰውነቴን ሶስት ጊዜ አማትቤ ወደ ግቢው ገባሁ።የዛፎቹ ርዝመት እና ስፋት እያየሁ ከቤተክርስቲያኗ እድል ፈለኳት ግን የለችም ከአንድ ዛፍ ስር ቁጭ አልኩ። በዛ ጋር የሚያልፍ ሁሉ እየተሳለመ ይማፀናል ይለምናል። እኔም በርከክ አልኩኝ ከተቀመጥኩበት ሸርተት ብዬ "ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሆይ...."ምን እንደምፀልይ ግራ ገባኝ ሀሳቤ በንፋስ የተበታተነ ወረቀት ሆነብኝ። "እድል እኮ" መልሼ ተውኩት እና ድንጋዩ ላይ ተመልሼ ተቀመጥኩኝ መረፋፈዱ የገባኝ ቅዳሴ ማለቁን ስረዳ ነበር "እንዴ ልዑሌ" የሚል ድምፅ ከኋላዬ ተሰማኝ ውቧ እና ተወዳጇ እድል ናት። ፈገግ ብዬ አየኋት እና "ማዘር ናቸው እዚህ መሆንሽን የነገሩኝ" አልኳት የምላትን አጥቼ። "ውይ ትቼህ ጠፋሁኝ አይደል ግን እንኳን መጣህ በል ና" ብላኝ ቀድማኝ ተራመደች ምን አለ ግን ሰምሃል ብትሞት አልኩኝ(ይቅር ይበለኝ) ግን ደግሞ የእድልን ሀዘን ማየት አልፈለኩም እና መልሼ ይሄን ሀሳብ ነፍሴ እንድትፀየፍ አረኳት። እድልም ከአንድ ከፈራረሰ ጭቃ ቤት ይዛኝ ገባች ብዙ ህፃናት አሉ ውበታቸው በድህነት እና በማጣት ተሸሽጎ ልብ ይነካል። ከደቀቀ ወንበር ላይ እንድቀመጥ ጋበዘችኝ እና "ልጆች እሱ ልዑል ይባላል ዶክተር ነው እናም ዛሬ እናንተን ለማየት ነው የመጣው እስኪ በመዝሙር እንኳን ደህና መጣህ በሉት" አለቻቸው በፍቅር እያየቻቸው የገረመኝ ግን የልጆቹ አስተያየት ነበር እንደ እኔም በፍቅሯ የተወጉ ነበር የሚመስሉት እነሱም በልጅ በሚጥም አንደበታቸው የቤተክርስቲያን ዝማሬ አቀረቡልኝ እድልም ከየት እንዳመጣችው ሳይገባኝ ነጠላ አምጥታ አለበሰችኝ እና "ክርስቲያናዊ አለባበስ ግድ ነው" አለችኝ።ልጆቹ በሙሉ የሚጠይቁኝ ሁሉ ንፅህናቸውን ነበር የነገረኝ ደስ የሚል ጊዜ አብሪያቸው አሳለፍኩ ምግብም አብረን በላን። "አዲስአበባ ስሄድ ደግሞ የምትፈልጉትን እልክላችኋለሁ" ብዬ ቃሌን ሰጠኋቸው። የእውነት ደስታቸው ከንዘብ እና ከአለም ኮተት የከበረ ነበር።ወደ ከሰአት ከእድል ጋር ወደ ቤት ተመለስን።"አደከምኩህ?" አለችኝ ሜዳውን እየተጓዝን።"ኧረ አላዳከምሽኝም የእውነት ደስ ብሎኛል የእውነት አመሰግናለሁ " አልኳት እሷም "በጣም ነው የምወዳቸው ሁሉም ወላጆቻቸውን ያጡ ናቸው እናም በዚህች ቤተክርስቲያን ስር ነው የሚረዱት እኔም ሁሌ እየሄድኩ እጠይቃቸዋለሁ የሚገርምህ እጅህን ሳይሆን ልብህን ነው የሚያዩት እንደ እነሱ ንፁሕ ብሆን ነው ምኞቴ እና ህልሜ" አለችኝ ንፁሕ መሆኗ ያልታወቃት ምስኪኗ እድል። ከቤት ደርሰን ስናወጋ ቆየን። ሰአቱ ነጉዶ ደንገዝገዝ ያለው ምሽት ምድሪቷን ወርሷታል "እማይ እማይ እነ ሰምሃል መጡ" አለች እድል ከውጭ ሆና። ጣዕረ ሞት እንዳየ ሰው ደርቄ ቀረሁ መላ ሰውነቴ በላብ ተጠቀመ የምሆነውን አጣሁ ትንፋሼ ቁርጥ ቁርጥ ሲል ታወቀኝ። ደንገዝገዝ ባለው ሰማይ ላይ በረህ ጥፋ ጥፋ አሰኘኝ።
😭😭😭ሰባራ ልቦች💔💔💔


ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezawit2
🍃🌿🍃የግጥም መንደር🍃🌿🍃🌿

💚💛💚💛💚💛
ከፍቅር......
ያለፈ ህመም ዛሬም ጉዳት አለው....ውስጥ ድረስ የሚሰማ የማይረሳ ጠባሳ💕💕 ፍቅር ፈተና ሳይሆን ፀጋ ነው ብልሆች ያጌጡበታል ብልጦች ግን ይወድቁበታል...💚ፍቅር ብልጥ በመሆን አይገኝም የምትወዳት ፀሀይ ለማየት ከቤትህ እንደምትወጣው የምትወደውንም ሰው ለማግኘት አትከተለው!!ከጎኑ ሁንለት ፍቅር ይሄ ነው....🌿ህመም እስኪሰማህ ውደድ አፍቅር💕 ፍቅር መልሶ ያድንሃል💛💛💛 ሰባራ ልብህን በፍቅር ሙላው💚💚💚በፍቅርህ ተስፋ አትቁረጥ!!የተረጋጋ ነፍስ ይኑርህ!🌹 የምትወደውን ለማግኘት ታገስ!🌿 በዝግታ ተራመድ!አትጣደፍ!አስተውል😊 መልካም እና ተወዳጅ ለመሆን #ቅን ሰው ሁን!!
💛💚

🌿የግጥም መንደር በቤዚ የራጉኤል ልጅ🌿
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የሰው_ልጅ_የጥበበኛነት_መንገድ_ትርጉም[email protected]
31.5 MB
የሰው_ልጅ_የጥበበኛነት_መንገድ_ትርጉም.pdf

@yebezigetmoch
📖📖📖መልካም ንባብ📚📚📚
╔══❖•ღڿڰۣ🇪🇹ڿڰۣღ •❖══╗​​​
💔💔ሰባራ ልቦች💔
​​╚══❖•ღڿڰۣ💝ڿڰ ۣღ•❖══╝​​​​
.
••●🍃🌹🍃●•
🌹🌹🌹🌹🌹
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
🌹🌹🌹🌹🌹
@yebezawit2
😊ክፍል አስራዘጠኝ
#ብጫቂ_ገፅ

... አይኖቼ ከበሩ ላይ እንደተተከሉ ሰምሃል በዊልቸር ተወስና ስትገባ አየኋት ሁለታችንም ፊት ለፊት ተፋጠን ቀረን።ወ/ሮ እልፌም ወደ ውስጥ ገፍተው አስገቧት እና "ኮከቤ ግቡ በሉ" አሉ ወይዘሮ እልፌ ኮከብ የተባለችውን ተከትላ ሆስፒታል ያየኋት ሴት ገባች ምህረት ናት። ሁሉም ፍርሃት ከውስጡ ይነበባል እኔም ብሎን ምላሴ ከላንቃዬ ጋር ተጣብቆ ማውራት ተስኖኛል። እራት ከተበላ እና ማዕዱ ከፍ ካለ በኋላ እድል ጉሮሮዋን ጠረግጠረግ አድርጋ ለማውራት ልትጀምር ስትል በሩ ተንኳኳ ቀድሞ ነገር አይኗ ወደ ውጪ ሲቅበዘበዝ ሰው እየጠበቀች መሆኗ ገብቶኝ ነበር። ተነስታ ስትከፍት አባ ኪዳን ነበሩ ወደ ውስጥ በሰላምታ ዘለቁ ሁሉም ተነሳላቸው ከሰምሃል ውጪ። እሳቸውም አክብረው ተቀመጡ እድል አሁን ድፍረት ያገኘች ትመስላለች። "እህቴ...አውቃለሁ ብዙ ባደርግ አታምኚኝም የጊዮርጊስን በር ከፍቼ እየዘጋሁ ብምልልሽም ልብሽ ለእኔ አይደነግጥ ይሆናል ግን ቢያንስ ይሄ ካረካሽ ብዬ ነበር በደልኩት ብለሽ ያዘንሽለትን ሰው ፍለጋ አዲስአበባ የሄድኩት መከራው በዝቶ ቢሆንም አግኝቼዋለሁ።እማይ ልዑል የሰምሃል ፍቅረኛ ነበር" አለች። ክው አልኩ።የእድል እናትም ደንገጠው ነው የሚዩኝ። ምን ልናገር ምን ልበል? ደግሞስ ምን ማለት እችላለሁ? የሰምሃል እንዲህ መሆን ሊገባኝ አልቻለም ጊዜ ለካ ይሽራል ይሾማል። እንኳን በዚህ ሆኔታ ላስባት ለአንድ ቀን የሚከፋት አይመስለኝም ነበር። "እሱ ግን አሁን አይወደኝም" አለች ሰምሃል በዝምታ። እኔን ሁሉም እያየኝ ነው እድልን አየኋት አቀረቀረች። "እእእ..." ሰምሃል አስቋረጠችኝ። "አክሊሌ አውቃለሁ አዝነህብኛል እኔን ስትል ያጣኸው ብዙ ነው እኔም ግን ያጣሁት ነገር አለኝ የጎደለኝ ብዙ ነው በእርግጥ አሁን ላይ ለመሞት የቀረኝ ጊዜ ትንሽ ነው ግን ደግሞ ለፍቅር አይረፍድም እና ልክስህ ነው የምፈልገው አብረኸኝ እንድትሆን" ብላ ዊልቸሯን ገፍታ ከፊት ለፊቴ ተደነቀረች እና እጇን ፊቴ ላይ አሳረፈች እንደ አባጨጓሬ ተፀይፌ እጇን ወደ ራሷ መለስኩት እና ተነስቼ ወደ ውጪ ወጣሁኝ። ወደ እናቴ ስደውል ስልካቸው አይሰራም በጸሎትሽ አስቢኝ ለማለት አልቻልኩም። ሀዘን ቤቱን ሰራብኝ።እንደሰው ለሰምሃል አዝኛለሁ ግን ለእሷ የሚሆን ፍቅር የለም። "የኔ ልጅ ና ግባ ባይሆን ሲነጋ እናወራለን" አሉ የእድል እናት እኔም ግንባሬን ቀርጭም አድርጌ መደቤ ላይ ተጠቅልዬ ተኛሁኝ። ምን ሰአት አባ ኪዳን እንደሄዱም አላውቅም አድልም ተከፍታ በጊዜ ነው የተኛችው። መፍትሔ ባጣ እንኳ ሰምሃልን ለማቀፍ እጄ አይታዘዝም።

የከብቶቹ እና የአእዋፋቱ ዜማ ከእንቅልፌ አነቃኝ። ፊቴን ታጥቤ ከእድል እናት ጋር ቤት ላለመቀመጥ ወንዝ ወረድን። "የኔ ልጅ እድልን ወደሀታል" አሉኝ። ውሃውን እየቀዱ። "ብወዳትስ ትርጉም አጥቷል" አልኳቸው። "ሰምሃል ግን ትወድሃለች ለአንተ ነው የምትሞተው" አሉኝ። ተናደድኩ ስለ እደል ብቻ እንዲጠይቁኝ ነበር የፈለኩት።"እኔ ግን አልችልም በእሷ ተጎድቻለሁ ይቅር ብላትም አብሪያት ልሆን ቀርቶ ላስባት አልችልም" አልኳቸው በመረረ ድምፅ "ብትክስህም " አሉ። "እማማ ይቅርታ ግን እኔ ላፈቅራት አልችልም።" አልኳቸው ና ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ መቆጣቴን ያዩት እናት እልፌ ዝም አሉ።አቀበቱን እየወጣን ደርባባዋ እናት ደግመው ጠየቁኝ "የሰምሃልን ይቅርታ ልትጥለው ነው?" አሉኝ።በእርግጥ እንደ እኔ ላልተጎዳ ሰው ነገሩ ቀላል ይመስላል ነገርግን ቀላል አይደለም በሁለት እህትማማቾች መሀል መቆም በምርጫ መጠመድ ከባድ ነው።የሰምሃል እንደዛ ልቧ ተሰብሮ እና ተጎድቶ ማየት አስቸጋሪ ነው። "እቀበላታለሁ ግን" ንግግሬን ከአፌ ነጥቀው"ይሁን ይሁን" አሉኝ። ከቤት ስንደርስ ሰምሃል በረንዳው ላይ ተቀምጣ ነበር ስታየኝ እንደ ልጅ ፈገግ አለች።"ምነው በጠዋት ተነሳህ" አለችኝ።ድምጿን ላለመስማት ጆሮዬ ቢደፈን ብዬ ተመኘሁ(ብቻ አብዝቶ ይቅር ይበለኝ)።"እዚህ ጋር ተሸመጥ ቡና እስኪፈላ" አለችኝ ጎኗ ያለውን ኩርሲ እየጠቆመችኝ።ይሉኝታ ባይዘኝ ምን አለ እያልኩ ተቀመጥኩ የእድል እናትም ወደማጀታቸው ዘለቁ። "አክሊሌ"ሰምሃል ጠራችኝ።"አክሊሌ ሳልሆን ልዑል ነኝ ትላንት ተስፋውን እና ፍቅሩን ረግጠሽ የሄድሽው ያ ላንቺ ትንሹ ርካሹ የሆንኩት ልዑል ነኝ ልዑል!" በቁጣ መለስኩላት።"አሁንም አዝነህብኛል" ጥያቄዋ ይበልጥ ያናድደኝ ጀመር"አዝኜብሽ ነበር አዎ አንተ ለኔ አትመጥንም አንተ እና እኔ አብረን አንሆንም ስትይ አዝኜ ነበር ይበልጥ ልቤን የሰበረው የሰርግ ወረቀትሽን ስትልኪልኝ ነው።እኔን ልታገቢ ነበር ግን ነገር ሁሉ ተገለበጠ ዛሬ ግን ደስተኛ ነኝ ሁሉም የሆነው ይመስለኛል ለኔ እግዚአብሔር አስቦ ነው አንቺን እንዳላገባ።" ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ።"ስሚኝ በቃ ይቅር ብዬሻለሁ ግን አብሬሽ መሆን አልችልም ከስንት አመት በኋላ መጥተሽ ፍቅር ብትይኝ እጎዳሻለሁ እንጂ አልጠቅምሽም ነገ ደግሞ ጥለሽኝ እንደማትሄጂ በምን አውቃለሁ ልብሽ ሁሌም ስደተኛ ነው ስለዚህ ተይኝ በቃ ነገ ወደ መጣሁበት እመለሳለሁ" ብዬ ወደ ውስጥ ልገባ ስል ንግግሯ አድርቆ አቆመኝ።"እድልን ወደሀታል?" አለች።ቀስ ብዬ ዞሬ አየኋት "እንዳትዋሽ አይኖችህ ይናገራሉ መላ ሰውነትህ እሷን ነው አይደል የሚፈልገው አሁን እሷ ከእኔ የተሻለ ነገር ኖሯት ነው?እሷ ከእኔ በልጣ....."
"ዝም በይ!" እንደ መብረቅ ጮሁኩባት። ከቤት ያሉት እድልን ጨምሮ ወጡ።"ዝም በይ አንቺ የጠላሽው እኔነቴን ታግሳ የቀየረችው አንቺ አፈር ያደረግሽው ሰውነቴን ሰው ያደረገችው እሷ ናት ቢገባሽ ለአንቺ ስትል እብድ ሆና ሆስፒታል ነበረች እስኪ ንገሪኝ ማነው ለበደል ፍቅር የመለሰ አንቺ ነሽ ወይስ እሷ ለነገሩ ፍቅር አይገባሽም ከዚህ በኋላ ስለእሷ ክፉ አታውሪ እኔንም ተይኝ ስለአንቺ ቀንለሊት የምትጸልይ እህትሽ ናት እሱንም አታውቂም ተጎሳቁላ እንዲደላሽ ነበር እኔን ያመጣችኝ።ብወዳት ደግሞ የሚገባት ናት የሚወደድ ነፍስ ያላት ሴት ናት...." እነ እድልን ገፍትሬ ወደ ውስጥ ገብቼ ሻንጣዬን ይዤ ወጣሁኝ። "ራስ ወዳድ ነህ ልዑሌ" እድል እያለቀሰች። "አዎ ነኝ ማንም ግን አይገባውም" አልኳት። "ስትመጣ ልትንከባከባት ቃል ገብተሀል" አለች "አልችልም እድል እኔም እኮ ሰው ነኝ የራሴ የህይወት ህግ አለኝ ተይኝ መልካሙን እመኝልሻለሁ" በጥፊ ፊቴን አጋየችው። "ሰው መስለኸኝ ነበር! ሰው ብትሆን ህግህን በፍቅር ትሽር ነበር" ጥላኝ ወደ ቤት ሮጠች እኔም ሰምሃልን ዞር ብዬ ስመለከታት ፊቷ እንደ ተጨማደደ ግንባሯ እንደተቋጠረ ነው ምንም ሳልል በተሰበረ ልብ ከግቢው ወጥቼ መጓዝ ጀመርኩ።ለሁለተኛ ጊዜ የምወደውን ነገር ተቀማሁ እድል የኔ ላትሆን ጥላኝ ሮጠች የልቤን ሀዘን በጭፍን ፈረደችብኝ።እውነት ነው ህግ በፍቅር ይሻራል ይሄ ግን ለእኔ ከባድ ነው ሰምሃልን አቅፌ እድልን አሻግሬ ማየት አልፈልግም።እንዲሁ እንደቆሰልኩ ድኜ ተደስቼ ሳላበቃ ዳግም ነፍሴ አዘነች ማቅ ቀድጄ አመድ በራሴ ላይ ብነሰንስ ሀዘኔን አይገልፀውም። "ልዑል" ከኋላዬ የሰማሁት ድምፅ መሀል መንገዱ ላይ አቆመኝ ወደ ፊትም ወደኋላ ሳልል ባለሁበት ቆሜ ቀረሁ።......😭ይቀጥላል😭
💔ፍቅር ሰብሮ አያውቅም ፍቅር አይሰብርም ፍቅር አይጥልም ፍቅር አይሸነፍም እውነተኛ ፍቅር ሃኪም ነው
ቅር አዳኝ ነው💚ፍቅር ፈዋሽ እንጂ ገዳይ አይደለም🌿🌿 ፍቅር ውበት ነው በልብ የሚሸሽጉት🌹🌹ፍቅር ስጦታ ነው በገንዘብ የማይመነዝሩት💕 ፍቅር ምግብ ፍቅር ሰላም ነው😊
💔💔የዳኑበትን ፍቅር ማጣት ዳግም መሞት ብቻ አይደለም መሀል መንገድ የቆመ ፍቅር ምርጫው ከባድ ነው💔💔 የምትወዱትን ፈጣሪ ይምረጥላችሁ

💔ሰባራ ልቦች💔
🌹ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezawit2

@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
🔥 ••●◉Join us share 🔥
የደግ ሴት እድሏ ያማረ ነዉ፤
እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰዉንም ወደ እድሉ ታደርሰዋለች፤
መጽሐፈ ሲራክ 26:1~3
#አታግባ
የህይወት ምንነት ሳታዉቅ👉 አታግባ
የትዳርን ምንነት ሳታዉቅ👉አታግባ
የትዳር አጋርህን ሀቅ (መብት) ሳታዘጋጁ 👉አታግባ
በችግር ሰዓት ህይወትን አብረህ ልትገፋ ምትችል ሴት ሳታገኝ👉 አታግባ
ኃላፊነትህን እንደት መወጣት እንዳለብህ ሳታቅ አታግባ
ለልጆችህ ተምሳሌት መሆን ሳትችል አታግባ

#ትዳር
ትዳር ማለት 1ወንድ አንድ ሴት
ትዳር ማለት 1 እምነት አንድ እዉነት
ትዳር ማለት 1 እሳት አንድ ዉሃ
ትዳር ማለት 1 ሙሉ አንድ ጎዶሎ
ትዳር ማለት 1 አንድ መጥፎ አንድ ጥሩ
ትዳር ማለት 1ጉልቻ አንድ ድስጥ
ትዳር ማለት 1ወንዝ አንድ ዉሃ የሚቀዳ ቢሆንም ካልተንከባከብዉና ካልተቻቻልንበት ሊደርቅ የሚችል ወራጅ ወንዝ ነዉ።

ደግ ሴትን ባሏ ያመሰግናታል፤
የህይወት ዘመኑም እጥፍ ይሆናል፤
ቅን ሴት ባሏን ደስ ታሰኘዋለች፤
ዘመኑንም በሰላም ይጨርሳል፤

በፍቅር ያማረ ትዳር ሠላም ያለዉ እዉነተኛ ፍቅር ይስጣችሁ
💚ፈጣሪ የምትወዱትን ያድላችሁ💚

@yebezawit2
😊 @yebezigetmoch
😊 @yebezigetmoch
😊 @yebezigetmoch
አስተማሪ አጭር ታሪክ .!


አንድ ቤተሰብ ውስጥ አባት ከሞተ በኋላ የሚመገቡት እስኪያሳስባቸው ድረስ ይቸገራሉ ። አንድ ጌጣጌጥ መሸጫ ሱቅ ያለው ዘመድ አላቸው እና እናትየው ለልጇ ያላትን ለረጅም ጊዜ የተቀመጠ የአንገት እና የጣት ዳይመንድ ጌጥ ሰጥታው እዛ ሱቅ ሄዶ እንዲሸጠው ትሰጠዋለች፡፡

ልጁ የተባለው የዘመድ ጌጣ ጌጥ ሱቅ ሄዶ እናቱ እንደላከችው አስረድቶ እንዲገዛው ይጠይቃል፡፡ ሰውየውም ከመረመረው በኋላ "አሁን ገበያው ወድቋል ትንሽ ግዜ ጠብቀን በጥሩ ዋጋ
እንሸጠዋለን፡፡" ብሎ ይመልስለትና የተወሰነ ገንዘብ ከሰጠው በኋላ ለልጁም እስከዛው በየጊዜው እየመጣ እዛው ሱቅ ስራ እንዲሰራ ያደርጋል ።

ልጁ በየግዜው እየሄደ የጌጣጌጥአሰራር ጥበብ ተካነ ፡፡ የገበያም እውቀት አካበተ በስራውም ታዋቂም ለመሆን ቻለ ፡፡

ይሄኔ ባለሱቁ "የሆነ ግዜ ልትሸጠው አምጠተኸው የነበረውን ጌጥ አሁን አምጣው አሁን ገበያው ጣራ ነክቷል እና ታተርፋላችሁ ፡፡ ብሎ ይልከዋል ፡፡ ልጁ እንደተባለው እቤት ሄዶ ጌጣጌጡን በአይኑ በማየት ብቻ አርቴፊሻል ሆኖ ያገኘዋል፡፡

ወደ ሱቅ ይመለሳል ፡፡ባለቤቱ ይጠይቃል "ዳይመንዱስ ?" ልጁም "አርቴፊሻል ነው ግን እያወክ ያን ጊዜ ለምን አልገርከኝም ?አሁንስ ለምን ላከኝ?ሲል ጠየቀው፡፡ ዘመዱም "ያን ጊዜ ለረጅም ዘመን ዳይመንድ ነው ብላችሁ ያመናችሁትን ነበር ይዘህ የመጣኸው ፡፡ያለምንም እውቀት፤ ባዶህን እና በሙሉ እምነት ብቻ ! በሰዓቱ ባለህበት ሁኔታ ልክ ያልሆነ ነገር ለማስረዳት ይከብዳል፡፡ ምናልባት ላታምኑኝ ትችሉ ነበር ፡፡ምናልባትም ባለመግባባት የሚፈጠሩ የቃላት ልውውጥ አሁን ላይ መጥፎ ስሜት ሊያሳድርብን በቻለ ነበር ።" ብሎ በትህትና መለሰለት፡፡

እንዲህ ያለ የላቀ ስብዕና ባለቤትና ነገሮችን
በብዙ አቅጣጫ የምናይበት ህሊና ይስጠን፡፡
💚💛 በቅንነት የምንደምቅ ቅን ኢትዮጵያውያን ያድርገን💚💛

@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊
ደህና እደሩ🕊🕊🕊🕊
የሰላም ምሽት ይሁንላችሁ 💋💋💋
ሰባራ ልቦች ይቅጥላል❤️❤️
ገመና_ረጅም_ልብ_ወለድ_በ_ሰለሞን_ሹምዬ_.pdf
2.8 MB
መልካም ንባብ📖

🌹ቤዚ የራጉኤል ልጅ
(🌿ቤዛዊት የሴትልጅ 😊)
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
የሚወዱህን መጥላት ሰይጣናዊነት ፣ የሚወዱህን መውደድ ሰብአዊነት ፣ የሚጠሉህን መውደድ መንፈሳዊነት መሆኑን ተረዳ ። የሚወዱህን መውደድ ሳትችል የሚጠሉህን መውደድ አትችልም ። ሰብዐዊነት መሰፋፈር ነው መንፈሳዊነት ግን አምላክን እያዩ ማፍቀር ነው

ከፍቅር
💚💛
💚💛
💚💛
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
💕ሰባራ ልቦች💕

🍃🍃የመጨረሻ ክፍል መዳረሻ🌿🌿
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ 💕
@yebezawit2

🌹🌹ሰባራ ልቦች💔💔💔
....የሰማሁት ድምፅ የሰምሃል ነበር ፊቴን ሳላዞር ቆምኩኝ።"አትሂድ በቃ እውነቱ ያየኸው ሳይሆን በልብህ ያለው ነው" እንባ ባነቀው ድምፀት አወራች እኔ ግን ከቆምኩበት ወደ ፊት መንገዴን ቀጠልኩኝ። ሲሞላ አላየሁም የልቤ ሲሆንልኝ እናም በቀጠሮ ሳይሆን አሁን ዛሬ ኋላዬን ሳላይ መሄድን ፈለኩኝ መራቅ ከእድል አይን ስር መሸሽ አውቃለሁ ለእኔ ባለ ሰባራ ልብ ከባድ ነው ግን ግድ ነው መሄድ መምጣት ነው አሉ እንጂ መሄድ መሞት ነው የሚወዱትን ማጣት ከቃል በታች መውደቅ ስቃይ ነው። እግሬን እየተከተልኩ ሜዳውን መቋራጥ ስጀምር ከፊቴ ነጭ ኩታ የደረቡ ሁለት አባቶች እና አንድ ደርባባ ሴት ተመለከትኩ ቆምኩኝ ወደ ኋላ ላለማየት ራሴን ገዝቻለሁ ከወንድነት ወኔዬ እና ጉልበቴ አልፎ የሚዘረገፈውን እንባዬን በእጄ እየዳበስኩ አተኩሬ አየኋቸው "ልጅ ልዑል" አሉ በስተቀኝ ያሉት ባለ ነጭ ሽበት አዛውንት። አንገቴን አቀረቀርኩ እና ዝም አልኩ ። "ስጠራህ አቤት አትልም" አሉ መልሰው እኔ ግን ቃል አላወጣሁም ለምን? ምን ማለት እችላለሁ ዝም ብቻ ነው የኔ ድርሻ። "እስኪ ዘወር ብለህ ተመልከት" አሉ ደርባባዋ እናት ቀና ብዬ ደም በመሰለው አይኔ ተመለከትኳቸው እና " ልሄድ ነው አላይም...ይቅር በሉኝ" መንገዴን ልቀጥል ስል። "ታዛዥ አልነበርክም እንዴ" መሃል ላይ ያሉት አባት ጠየቁኝ።እኔ ግን ሰውነት ናፍቆኝ ሰው አድርጋኝ የራቀችኝን እድልን ላለማየት ነበር ራሴን የገዘትኩት ግን አባቶቹ ለምን እንደፈለጉ አልገባኝም እና በሰባራ ልቤ እያነባሁ ወደ ኋላ ዘወር አልኩኝ እና ተመለከትኩ። አይኖቼ ያጭበረበሩኝ መስሎኝ ጨፍኜ ዳግም ገለጥኩ ግን እውነት ነው ውሸት የለውም ፈገግ አልኩኝ እና ማልቀሴን ጀመርኩ።ሜዳው ላይ እግሬን ዘርግቼ ተቀመጥኩኝ እና እናቱን እንዳጣ ጨካኝ ወታደር በእግሮቼ መሃል አንገቴን ቀብሬ መራራ ለቅሶን አለቀስኩ።ሰምሃል ከዊልቸሩ ተነስታ ነበር የተመለከትኳት ይሄ ለእኔ የቀን ቅዥት ነበር የሆነብኝ ግን እውነት ነው። "እድል" ሰምሃል ወደ እኔ እየመጣች ተጣራች "ምን አሁን ምን ቀረሽ" እድል እየተመናጨቀች ስትወጣ እሷም እንደ እኔ ካለችበት ደርቃ ቀረች። "ልዑሌ ይቅርታ ለማለት የሚበቃ ሞራል የለኝም" ብላ እጇን ዘረጋችልኝ እና ይዣት ከተቀመጥኩበት ተነሳሁ። ከአዛውንቶቹ ጋር ወደ ቤት ገብተን ተቀመጥን እና የሆነው ሁሉ ሊተረክልኝ እንግዶች ይጠሩ ተባለ።እኔ ግን ሰምሃል ከወዲያ ከወዲህ ስትል ማየቱ እንግዳ ነገር ሆኖብኝ በስስት አያታለሁ እድልም በእናቷ እግር ላይ ተኝታ ገጿን በእንባ በዝምታ ታርሳለች። "ግቡ ግቡ " ሰምሃል ከውጪ የሚገቡትን ሰዎች በሚያምር ትህትና ጋበዘቻቸው። የኔው ጉዶች ነበሩ እናቴ አባቴ ወንድሜ እና አሊሾ ከእነሱ ውጪ ቂም ይዤበት የማዝንበት የድሮ ፍቅሬን የቀማኝ ዶክተር ማርቆስ ነበር።የሚሆነው ነገር ስላልገባኝ ዝም ብዬ መመልከት ጀመርኩ ሰምሃልም ከትንሿ ኩርሲ ላይ ተቀምጣ ታወጋን ጀመር። "ልዑሌ አንተን ትቼህ ስሄድ ልክ ላልመስልህ እችላለሁ ግን ልክ ነበርኩ የምወደው ሰው ነበር እስሱም ማርክ ነበር ማርክን ለማግኘት ነው አንተን የቀረብኩህ በእርግጥ አንተ የግቢው ታዋቂ ብትሆንም እኔ ግን ያለ ምክንያት የምወደው ማርክን ነበር ሳየው ሁሉ በፊቱ ፈገግታ እጠግባለሁ ብቻ ትቼህ ሄጄ ረስቼህ ነበር ግን ማርክ ሁሌም ስለአንተ ያስብ ነበር ስፈልግህ አጣሁህ እናም እርጉዝ እያለሁ በገጠመኝ የጤና እክል ሁለት ልጅ አጣሁኝ ብቻ ህይወት ጨልማ ጎስቋላ ሆንኩኝ እናም በደሌን ተናዝዤ ንስሃ ልገባ አሰብኩ ግን ይቅርታችሁን ፈልጌ እየናፈኩ አዲስአበባ መጣሁ እና ልደታ ቤተክርስቲያን መጥቼ ስሳለም አጋጣሚ እናትህን አገኘኋቸው ሳያቸው ነበር ወዲያው ያወኳቸው የሆነው ሁሉ አጫወቱኝ እናም ከእኔ ከተለየህ ጀምሮ የጊዜ መቁጠሪያህ መቆሙን ስትነግረኝ ወልጄ አለመሳሜ ምክንያቱ ገባኝ። አታምኑኝ ይሆናል ግን በየቀኑ እየመጣሁ አይህ ጀመር ቤተሰቦቼ አዲስአበባ መሆኔን አያውቁም እና እንደምንም አሊሾን አውርቸው ካሳመንኩት በኋላ ያንተን ጉዳይ ጨርሴ እድል እህቴን አሰብኳት እሷም በእኔ ግፍ ተጎድታለች።በእርግጥ መኖር አላቆመችም በእግዚአብሔር ጸንታ ታግላ ለበደሌ ጸልያ ለጥላቻዬ ፍቅርን ሰጥታኝ አክብራኝ አሸንፋኛለች እና ደካማ ጎኗን ስለማውቅ ነበር ጉዳት ደርሶብኛል ብዬ የመጣሁት እሷም አንተን ፍለጋ ወጣች በየቀኑ ግን አሊሾ ይከታተላት ነበር" አለችኝ።
የምታወራልኝ ሁሉ የሆነ ልብወለድ መሰለኝ ግን ደግሞ በሁለት አይኖቼ እየተመለከትኩ ነውና ውሸት ነው ብዬ መኬድ ከበደኝ። "እና ልዑሌ እድልዬ እግዚአብሔር በእናንተ ከካሰኝ ብዬ እንድትተዋወቁ ድራማ ሰራንባችሁ ያንቺ ሙላት እሱን ሞላው ያንተ መጥቆር እና ማዘን እሷን አበርትቶ አንተን ደገፈችህ እና ላትለያዮ እጅ ለእጅ ተያያዛችሁ።ስደተኛ እና ሰባራ ልብህ በእድል ልብ አረፎ ሲፅናና አየሁት የእውነት ልዑሌ ስትስቅ ሳይህ ደስታ ምድሬን ሞላችው እናም በቃ ይሄን ሰራንላችሁ" አለች እድልን እያየች እድልም በዝምታ ካደመጠች በኋላ "በቃ ይሄ ነው" አለች። ሁሉም ደንግጦ ይመለከታት ጀመር። "አንተስ የሰራኸው ድራማ የለም" አለችኝ ወደ እኔ አይኗን አፍጥጣ።ደነገጥኩ "አድል እኔ አላውቅም እንደ አንቺ እንግዳ ነኝ።" በጩኸት ንግግሬን አቋረጠችው። መሃል ላይ እየተንጣጣ የሚነደው እሳት ቤቱን አሞቆታል። "ተንኮል ነው ታውቅ ነበር አውቃለሁ እኔ ላይ መጫወት አይሰለቻችሁም ግን ቆይ ምን አረኩህ እስኪ አንተ ንገረኝ ህመም አይተህ አታውቅም እና ነው እኔን እንደዚህ አይኔ ስር የተጫወትከው እስኪ አሁን ታምነኛለች ብለህ ነው እንደዚህ የምታወራው።" ከተቀመጠችበት ከመነሳቷ ከእሳቱ ዳር እራሷን ስታ ተዘርራ ወደቀች። ሁሉም በጩኸት ጎጆ ቤቷን አተረማመሰው......

🌹🌹🌹ይቀጥላል🌹🌹🌹

ፍቅር የሚያወሩት ሳይሆን የሚኖሩት እውነት ነው! ማጭበርበር ውሸት የሌለበት ንፁህ ለሚወዱት ብቻ የሚሰጡት በስስት የሚያኖሩት ልዩ በረከት ነው💚የሚታደሉትም ጥቂቶች ናቸው😍 ያገኙት ጥለውት ያገኙት ሲያከብሩት የሚጎዱ ብዙዎች አሉ💕ያ ህመምም በፍቅር ይታከማል🌹 ውበት እና ሃብት ፍቅር የሚያመጣው እንጂ ፍቅርን የሚያመጡ አይደሉም😘😘😘

ይቀጥላል...ብጫቂ ገፆች
ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
( በላይ በቀለ ወያ )

.
.
እኖር ብዬ ብታረድም ፣
ለመኖር ስል ብሰደድም
እኖር ብዬ ብጨነቅም ፣ እኖር ብዬ ብዋረድም
ዘጠኜ ሞቴን ብሞተው…
አንዴ እንደመኖር አይከብድም!
መኖር ከመምት አይልቅም
ሞት እንደሕይወት አይጨንቅም፡፡
።።።
የሞተ ‹‹እሞታለሁ›› ሲል…
በጭራሽ አያውቅም ፈርቶ፡፡
ያልኖረ አያውቅም ሞቶ።
።።።።
መኖር እንጂ የሚያስፈራኝ
መኖር እንጂ የሚያስገፋኝ
መኖር እንጂ የሚያስከፋኝ
መኖር እንጂ የገደለኝ
መኖር እንጂ የበደለኝ
ሞት አያምም ካቆሰለኝ
ምት አያምም ከገደለኝ!

( በላይ በቀለ ወያ )
2025/07/04 09:27:38
Back to Top
HTML Embed Code: