❤
💖🌿💖🌿💖🌿💖💐
⇣
⇣⇣ 💖ክርስቶቤል💖
⇣⇣
🍃🌹🍃.........✍
🔥ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ፨🔥
💥 ❤😭ክፍል ዘጠኝ🙏
..... አይኖቼ በስስት እያያት ልቤም ላያወርዳት ደግሞ ቀብቶ አነገሳት።ኤዲ ለመሳፈሪያ እንዲሆናት የሰጠኋትን ብር ለእኚህ አዛውንት ስትሰጥ አየኋት። ከእሳቸው ይልቅ እሷን እያስፈለጋት እሷ ግን ከኪሷ ማኖርን አልወደደችም። ደግነት ይሄ ነው ልክ እንደ ኤደን ልቤም ያነገሳት በምክንያት መሆኑ ገባኝ። የተጎሳቆሉት ሽማግሌ አባትም በአባት አይን አይተዋት አለቀሱ። ኤደንም አቅፋቸው "ፀልይልኝ አባ....ነገ አዲስ ፀሐይ ስትወጣ እናቴን ይዣት እንድመጣ አደራ.." ብላ የተስፋ ቃሏን ሰጥታቸው አዛውንቱም "የኔ ልጅ እምነትሽን የሚያይ ፈጣሪ ይከተልሽ እረፍት ግን አድርጊ አንቺም ተጎሳቅለሻል" አሏት እና በመቁጠሪያቸው ጸሎት አድርገው ዳበሷት። ኤደንም በፍቅር ተሰናብታቻቸው ወደ ታክሲ መያዣው ጋር ተመለሰች። ደግነት ተላብሳ የተሸሸገች ልዩ ሰው።.....መከተሌን እንዳታውቅ በላዳ ታክሲ ወደ ሆስፒታል አቀናሁ። ቀድሚያት ስለገባሁ መከተሌን አልገባትም ያለፉትን ሰአታት እና ቀናት ረስታ ሌላ ሰው ሆናለች። አዲስ የተስፋ ወኔ ታጥቃለች.."በቃ እስከ አሁን ቆይታችኋል ነገ ትመጣላችሁ ጓደኞቼ" አለችን ኤደን የፀሀይን ማዘቅዘቅ ተመልክታ። ናታንም "ኧረ ኤድዬ ውለታ አታስመስይው ባይሆን አንቺ ወደቤት ሄደሽ እረፍት አድርጊ እኛ ለማደር ነው የመጣነው" አላት። ጓደኞቼም ቢሆኑ ወደዋታል።የኔንም ጭንቅ የእሷንም መጎሳቆል ተመልክተዋል።ኤደንም " ውለታ ሆኖብኝ ሳይሆን...በቃ እኔ እናቴን ትቼ መሄድ አልፈልግም"አለች። እኔም "ነገ እኮ እንመጣለን እሺ በይ ኤዲ በእማማ ሞት" አልኳት ሀሳቧን ለማሸነፍ በእናቷ ሞት ተማፀንኳቴ። በእረፍት እጦት ሊከደን የደረሰው አይኗን አፍጥጣ አየችኝ እና"ሁለተኛ እንደዚህ እንዳትለኝ" አለችኝ እኔም በአውንታ እራሴን ነቀነኩላት። ምርጫ ስለሌላት ከተቀመጠችበት ተነስታ "ደውሉልኝ በናታችሁ" ብላ ለእነ ናታን አደራ ብላ እኔና እሷ ተያይዘን ከሆስፒታሉ ወጣን......
"ግን እኮ ብቻዬን እዛ ቤት እፈራለሁ እኛ ቤት ታድራለህ?" አለችኝ። ልቧ በንፅህና አምኖኝ።እኔም "እእ እሺ ችግር የለውም" አልኳት። ውስጤ እያዘነላትም እየተደሰተ።...ዘመም ያለው ቤት ከውጪ ሲታይ ሰው የሚኖርበት አይመስልም። ከትንሹ ቤት በሩን ከፍታ ወደ ውስጥ ዘለቅን።መሬት የተነጠፈው ያለቀ ፍራሽ ጫፍ ላይ ተቀመጥኩኝ እና ቤቱን በአይኔ መቃኘት ጀመርኩ። ግድግዳው ላይ የተለጣጠፈው ጥቅስ ፈገግም ኮስተርም ያደርጋል በመጋረጃ ተጋርዶ ሁለት ክፍል መሆኑ ደንቆኛል። ይህ አለም ሌላ አለም ነው። እኔ ያደኩበት ቤት እና ያየሁት ህይወት ሁሉም ሰው የሚያሳልፈው ይመስለኝ ነበር። ኤደን ፊቷን ታጥባ መጋረጃ ከተጋረደበት ክፍል ወጣች እና "ምግብ ትበላለህ" አለችኝ። የተዝረከረከውን ልብስ እያስተካከለች።"አንቺ ከበላሽ" አልኳት።..."እኔ አልበላም ግን አንተ...." ሳላስጨርሳት "ተይው በቃ አልበላም" አልኳት። ኤደንም ምንም ሳትለኝ ያረጀ ማንደጃው ላይ ከሰል ጨመራ ማያያዝ ስትጀምር እኔም ለማገዝ በለቅሶ ሽንኩርት መላጥ ጀመርኩኝ ሁኔታዬን እያየች ከልቧ ሳቀች። የእሷ ሳቅ እኔ ላይ ተንፀባርቆ እኔም እስከ ዛሬ ስስቅ ያለተሰማኝን ስሜት እየተሰማኝ ሳኩኝ።አብሪያት መሆኔን ልቤ እንደምን እንደቆጠረው ሳይገባኝ ጦርነት እንዳሸነፈ ወታደር በደስታ ተፍነከነኩ። በመከራ ተልጦ በለቅሶ የተከተፈውን ሽንኩርት ድስት ውስጥ ጨምራ ከሰሉ ላይ ጣደችው እና "አዝናናኸኝ እውነት...ሰርተህ አታውቅም" አለችኝ። እንዴት ልንገራት እኔ ያደኩት በሰራተኛ የምፈልገው ምግብ እየተሰራ። ጤናዬ በግል ዶክተር እየተጠበቀ። በግል ሹፌር ከተማ እየዞርኩ። ብነግራት በኑሮዋ ላይ የምሳለቅ መስሎ ስለተሰማኝ ብቻ ዝም አልኳት።....በትንሹ የከፈተችውን ራድዮ እያደመጥን ሽሮአችን ለመበላት ደረሰች። እንጀራውን በሳህን አድርጋ አቀረበች። ሳላስበው ውስጤን አንዳች ነገር እረበሸው። ደስታ ሀዘን ውስጤ ተመሰቃቀለ አማኑኤልን የተማፀንኩት ነገር ታውሶኝ ፈገግ ብልም ጊዜዋን መካፈሌ ቢያስደስተኝም በመጥፎ ሰአት መሆኑ አስከፋኝ።"ብላ እንግዲህ እናቴ ብትኖር በሽልጦ በቡና ትቀበልህ ነበር" አለችኝ ወጡን ጨልፋ እያወጣች። እኔም "ሽልጦአቸው ይጥማል ማለት ነው" አልኳት የጠቀለልኩትን ላጎርሳት እጄን ዘርግቼ። ኤደንም ከተቀመጠችበት ተስፈንጥራ ተነስታ አስደነገጠችኝ ጉርሻዬ ረበሻት እጄን ሰብስቤ "ምነው " አልኳት ኤደንም እንደምንም እራሷን አረጋግታ "ጉርሻ አልፈልግም " አለችኝ ግንቧሯን ቋጥራ።እኔም ይቅርታ ብያት ደግማ እንድትቀመጥ አደረኳት።የበላንበትን ሳህን አንስታ "እስኪ ለጓደኞችህ ደውልላቸው" አለችኝ። እኔም ለእነ ናታን ደውዬ ምንም አዲስ ነገር እንደሌለ እና ሰላም መሆኑን አሰማኋት።.........ፍራሹ ላይ ከጎኔ እየተቀመጠች "ግን እንዴት አወቃችሁኝ....ማለት ለምን ተንከባከባቹኝ?" አለችኝ መልሴን ለማወቅ እየጓጓች እኔም "እስኪ እናጣራለን እሱን አሁን ተኚ.." አልኳት ፈገግ እያልኩ። ኤደንም "እኔ ያናገርኩት እና እንዲዚህ የቀረብኩት ሰው የለም እና እምነቴን እንዳትጎዳ ልቤንም እንዳትሰብር " ንግግሯ አንዳች ነገር የፈራች እንደሆነ ግልፅ አድርጎልኛል። አይኖቿን ትኩር ብዬ አይቼ "እምነትሽን ልብሽ በስህተት ሳላውቅ ብጎዳ መቼም ይቅር አትበይኝ " ንግግሬን ሳልጨርስ "ህፃኑን በለኝ እስኪ" ብላ ውብ መዳፏን ዘረጋችልኝ እኔም የልቤን ፍቅር በልቤ አዳፍኜ እንደ ወንድም ልጠብቃት እንደ አባት ልንከባከባት መዳፏን መትቼ ቃል ገባኋላት።"እኔ ምኑ ጋር ነው የምተኛው" አልኳት። "እዚሁ ነዋ እኔ ከግርጌ ነው የምተኛው ግን ..." አለችኝ እኔም "ችግር የለም ኤዲ እሺ ደግሞ ወንድምሽ ሆኛለሁ በህፃኑ ምዬልሽ አልዋሽሽም" ብያት ፍራቻዋን እንድትተው ነገረኳት። እሷም እንደ ልጅ በንፁህ ልቧ አምናኝ ተሸፋፍና ተኛች። እኔ ግን እንኳን እንቅልፍ ሊወስደኝ ለማሰብም አይኔን መክደን አቅቶኛል ከማንም አጠገብ ተኝቼ የማላውቅ ዛሬ በህይወት አጋጣሚ ከኤዲ ጋር ያውም በማይመች ቦታ። ስንት አመት በእንደዚህ አይነት ህይወት ኖራለች.............. የቤቱን ጥቅስ እያነበብኩ ድንገት አይኔ አንድ የድሮ ፎቶ ላይ አረፈ ፎቶው አዲስ አልሆነብኝ የለበስኩትን ብርድልብስ ከላዬ ላይ አንስቼ ለማየት ስነሳ ኤዲ ነቃች "እስከ አሁን አልተኛህም" አለችኝ። እኔም"አይ ድምፅ ሰምቼ ነው" አልኳት። "አይጥ ይሆናል ባክህ ተኛ" ብላ የደከመ ሰውነቷን ለማሳራፍ አይኗን ጨፈነች። እኔም ፎቶውን የት እንደማውቀው እያሰብኩ ከስንት የሀሳብ ውጣ ውረድ በኋላ እንቅልፍ ወሰደኝ።....ይቀጥላል!❤
🌿ክፍል አስር
❤ እንዲደርሶ አብሮነታችሁን @yebezawit2 💌ቅርጫታችን ላይ ሀሳብ በመስጠት ያሳውቁን!!😘
"በመሀል ለተፈጠረ የቃላት ግድፈት ይቅርታ እጠይቃለሁ"
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
❤የግጥም መንደር በቤዛዊት💟
😍ክርስቶቤል🌹
❥❥________⚘_______❥❥

🌸🌺ከእናንተው የተላከልኝን የይቅርታ መልዕክቶች በነገው ዕለት የማቀርብ መሆኑን እየገለፀኩ #ክርስቶቤልን አንባብችሁ የተለመደ አስተያየታችሁን @yebezawit2 ቅርጫቴ ላይ ጫር ጫር አድርጉልኝ💌💌💌
💚💛❤️ መልካም ንባብ💚💛❤️
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
💚💛❤️ መልካም ንባብ💚💛❤️
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
Forwarded from 𝚂𝙰𝙾𝙻𝙿𝚁𝙾𝙼𝙾
┄┄✽̶»̶̥🌺ህይወቴ🌺🌺̶̥✽̶┄┄
✍በጉጉት ስትጠብቁት የነበረው❤ህይወቴ❤️ የተሰኘው ምርጥ የፍቅር ታሪክ ይዤላቹሁ ከች ብያለው፡፡ምንም ሳያመልጣችሁ ከመጀመሪያ ጀምሮ ለማንበብ ከታች 🌺ክፍል 1️⃣ 🌺የሚለውን ምርጫ ይጫኑት
እንዳያመልጣችሁ በተለይ ለጥንዶች┄┄✽̶»̶̥🌺

Forwarded from Арбитражница dooradas (🦋ሱራ ቢራቢሮ 🦋)
የጉንጭ ላይ ዥረት
🦋 ተ 🦋
🦋 ፃ 🦋
🦋 ፈ 🦋
በሱራፌል ጌትነት (ሱራቢራቢሮ🦋)
ሲፍገመገም -- ሲውሸለሸል
ለመፋጀት ወላፈኑ ሲንቀለቀል
የእሳት ሰይፍ በክናዱ
ተዛመተ ከአንዱ ወደ አንዱ
አስሰውት ሳይነካቸው የነካኩት
ባልጠፋ የእህል ዘር ስጋውንም ገፈው በአፋቸው አዋሉት
በአክ-እንትፍ አርሰን
ምናወርድ በአርጋኖን
ምን ህመሙ አይሎ እጅግ ተባብሶ
ወደ ቅዬ ገባ ከእባብ ለስልሶ
ሽቅቡን አንጋጠሽ በለሆሳስ ቃና
እጆችሽን ዘርጊ ይምርሻልና
ኢትዮጵያ ታበፅዕ እደዊሀ ሀበ እግዚአብሄር
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🦋🦋👇🦋🦋
https://www.tg-me.com/sufafel
🦋🦋👆👆🦋🦋
✅ ✍ @surabirabiro ✍🦋
🦋 ተ 🦋
🦋 ፃ 🦋
🦋 ፈ 🦋
ከሱራ🦋ቢራቢሮ 🦋
🦋 ተ 🦋
🦋 ፃ 🦋
🦋 ፈ 🦋
በሱራፌል ጌትነት (ሱራቢራቢሮ🦋)
ሲፍገመገም -- ሲውሸለሸል
ለመፋጀት ወላፈኑ ሲንቀለቀል
የእሳት ሰይፍ በክናዱ
ተዛመተ ከአንዱ ወደ አንዱ
አስሰውት ሳይነካቸው የነካኩት
ባልጠፋ የእህል ዘር ስጋውንም ገፈው በአፋቸው አዋሉት
በአክ-እንትፍ አርሰን
ምናወርድ በአርጋኖን
ምን ህመሙ አይሎ እጅግ ተባብሶ
ወደ ቅዬ ገባ ከእባብ ለስልሶ
ሽቅቡን አንጋጠሽ በለሆሳስ ቃና
እጆችሽን ዘርጊ ይምርሻልና
ኢትዮጵያ ታበፅዕ እደዊሀ ሀበ እግዚአብሄር
🇪🇹🇪🇹🇪🇹
🦋🦋👇🦋🦋
https://www.tg-me.com/sufafel
🦋🦋👆👆🦋🦋
✅ ✍ @surabirabiro ✍🦋
🦋 ተ 🦋
🦋 ፃ 🦋
🦋 ፈ 🦋
ከሱራ🦋ቢራቢሮ 🦋
❤
💖🌿💖🌿💖🌿💖💐
⇣
⇣⇣ 💖ክርስቶቤል💖
⇣⇣
🍃🌹🍃.........✍
🔥ደራሲ ቤዛዊት የሴትልጅ፨🔥
💥 ❤😭ክፍል አስር🙏
በስተምስራቅ በኩል የወጣችው የማለዳዋ ፀሐይ በቤቱ ቀዳዶች ብርሃኗን አሳልፋ ቤቱ ደምቋል።"አንተ ተነስ....." የሚል ድምፅ ከእንቅልፌ አነቃኝ። ኤዲ ነበረች "ትቼህ ልሄድ ነበር ግን አሳዘንከኝ" አለችኝ በሩን እየከፈተች። እኔም "አታደርጊውም ነበር" አልኳት ስልኬን እያየሁ "በወንድሜ መጨከን አልችልማ" አለችኝ ወንድሜ የሚለው ቃል ልቤን ቢያሳምመውም ከእሷ ጎን ለሁልጊዜ ለመሆን ብቸኛው መንገድ ነው ወንድም መሆን ደግሞም ፀሎቴ ነው የእሷ መሆን እንጂ የምሻው የግድ እሷ የእኔ እንድትሆን አልፈልግም።"እሺ እህቴ" አልኳት እየከበደኝ። "ለምን ምግብ ሰርተን አንሄድም" የሚል ሀሳቤን ቀጠልኩላት። "አይ ደህና መሆኗን ሳላይ አልበረታም ቢያንስ አንዴ አይኗን እንዲያሳዩኝ ልለምናቸው" አለችኝ በሀዘን ፊቷን ቋጥራ እኔም ከአለቀችው ፍራሽ ላይ ተነስቼ "ግድ የለሽም ዛሬ ሊያስወጧት ይችላሉ" አልኳት። እነ ናታን በመልዕክት እናቷ ደህና እንደሆኑ ከከፍተኛ ክትትል ወጥተው ሰላም መሆናቸውን ከሰአት እንደሚወጡ ስለነገሩኝ ነበር። ኤደንም"ጥሩ ህልም አይተሀል መሰለኝ" ፀጓሯን እያስያዘች በአግራሞት አየችኝ። እኔም አዲሱ ወንድምነቴን ተጠቅሜ ቤቱን አፅድተን ምግብ አዘጋጅተን ቡና አቀራርበን በሩን ዘግተን ወደ ሆስፒታል አቀናን። ኤደንም ወደ ከፍተኛ ክትትል ክፍሉ ልትሄድ ስትል እጇን ይዤ እናቷ ወደ ተኙበት ክፍል አስገባኋት....በደስታ እንደ ጠዋት ፀሐይ ፊቷ ደምቆ እናቷ ላይ ተጠመጠመች። እኔም ከእነ ናታን ጋር ተያይዘን ከክፍሉ ወጣን ናታንም "በጣም ታሳዝናለች" አለኝ እኔም "በጣም ግን ጨንቆኛል " አልኳቸው የልቤን ልነግራቸው ዘኪም "ምንድነው አቡሻ ችግር አለ እንዴ " አለኝ። እኔም " አላውቅም በቃ እኔጃ እንደዚህ ሆኜ አላውቅም..." ተንተባተብኩ። ናታንም በረጅሙ ስቆ " አፈቀርኳት ልትለን ነው" ብሎ ቃላት ከመጎት ገላገለኝ። እኔም " አዎ ግን እንዴት ልንገራት ወንድምሽ ነኝ ብዬ ትላንት ማታ ማልኩላት " አልኳቸው። ዘኪም " አቡሻዬ ታዲያ ምን ችግር አለው የአንተ ምንነተ ስትረዳ እና ሲገባት ሁሉንም ታስረዳታለህ ይሄ ቀላል ነው።" አለኝ እኔም ቀላል ቢሆን ብዬ በልቤ ተመኘሁ የኤዲ ነገር ለእኔ ስውር ቅኔ ነው ናታንም "ማዘሯ ግን እንዴት ረሃ እንደሆኑ...ልክ እናንተ ስትሄዱ ነው እኮ ያስወጧቸው" አለኝ እኔም "ጭንቀቷ በጣም ቢያስጨንቀኝም ይሄን ፈገግታዋን ለማየት ብዬ ሳልነገራት ነው የመጣኋት" አልኳቸው። ዘኪም " ግን አቡሻዬ በጣም ጭንቀት አለባቸው እና የሆነ ነገር ብናደርግላቸው" አለኝ። ጓደኛ በክፉ ቀን ጥላ በድካም ጊዜ ማረፊያ በደስታ ቀን ማድመቂያ ስጦታ ነው ከላይ ሲሆን ሽልማቱ ተድላ ነው ጓደኞቼ ስሜቴን ፍላጎቴን ሁሉንም ነገር ሲረዱኝ ምን ያህል እንደ ሚደንቀኝ። ተመልሰን የኤደን እናት የተኙበት ክፍል ስንገባ እናት እና ተቃቅፈው እየተላቀሱ ነበር የእኛን መግባት ተመልከተው ተላቀቁ እና "አንተ ግን አውቀህ ነበር አ ያልንገርከኝ?" አለችኝ እኔም "ማን ይሄን ደስታ ይሰጠኛል?" አልኳት ጥያቄዋን በጥያቄ እየመለስኩላት። መጥታ ዘላ ተጠመጠመችብኝ። እኔም እየተንቀጠቀጥኩ አቀፍኳት።........ለመውጣት ዶክተሩን ማናገር አለብን እና እኔ ኤዲ ሆነን ዶክተሩ ጋር ሄድን ዶክተሩ ግን በሀዘን ነበር የተቀበለን "ምንድነው ዶክተር" አልኩት። "አሁን ላይ ወ/ሮ ተዋቡ ያሉበት ጤና መልካም ቢሆንም ግን...." ዶክተሩ እስኪጨርስ አልጠበቀችም "ግን ምን?" ኤደን ዶክተሩ ላይ አፈጠጠች። "ከጨንቀት ካልራቁ እና በቂ ዕረፍት ካላደረጉ ተመጣጣኝ ምግቦችም ካልተመገቡ ለወደፊቱ እጅግ አሳሳቢ ነው ከእኛ አቅም በላይ ሊሆን ይችላል..." የኤደን እንባዎች መዘርገፍ ጀመሩ። ደነገጥኩኝ "የሚረዳን የለም እኔም ስራ ብስራ እሷን ከጭንቀት ላድን አልችልም እኮ እናቴ ማጣት አልችልም ዶክተር ለእኔ ከባድ ነው" አሳዘነችኝ ዶክተሩም " ለምን እሳቸውን የሚያዝናና ስራ አትሰጫቸውም" አላት ወጣቱ ዶክተር ኤደንም "ምን ልስጣት ለእሱም ሌላ ወጪ በቃ እኔማ ተረግሜ ነው አይለፍልሽ ተበይ ነው" "ኤዲ በቃ መፍትሄ ይኖረዋል" አልኳት። ዶክተሩም "እንኪ ለጊዜው" ብሎ በዛ ያለ ብር ሰጣት ውስጤ በቅናት በብስጭት ነደደ "አልፈልግም እሱን ዶክተር ግን እባክህ" ከተቀመጠችበት ተነስታ ወደ ዶክተሩ ተጠግታ "እናቴን አንዳንዴ እየመጣህ እይልኝ ገንዘብ ሳገኝ እከፍልሃለሁ" አለችው ወጣቱ ዶክተርም "ችግር የለም አድራሻዬን እሰጥሻለሁ ስትፈልጊኝ ደውይልኝ" ብሎ አድራሻውን ሰጣታ። እኔም በውስጤ ቅናት እያንጨረጨረኝ ከክፍሉ ወጣን........ከኤዲ ጋር እናቷን ይዘን ወደ ቤት አቀናን እናቷም የቤቱን መፅዳት ተመልክተው "ልጄ ያለኔ ሰርቶ ለመብላት በቃችልኝ" አሉ ባለቀችው ፍራሽ ጋደም እያሉ ኤዲም " ኧረ ይሄ እኮ ነው ካልሰራን ብሎ" ብላ ወደእኔ ጠቆመች። እኔም ጓደኞቼም እስከ ምሽት እንደ ቤተሰብ ተጫውተን የግድ ወደ ቤት መመለስ አለብን እና ኤዲንም እናቷንም ተሰናብተን ከቤቱ ወጣን። ወደ አስፓልት የሚወስደውን መንገድ ከጓደኞቼ ጋር በጨዋታ እየገፋነው "አቡሻ አቡሻ" ኤዲ ነበረች ቆሜ ጠበኳት "አንተ አስረሳኸኝ አይን አይንህን እያየው" አለችኝ ደነገጥኩኝ አይኖቼን አፍጥጬ ተመለከትኳት "ኧረ ስቀልድ ነው ደግሞ በደስታ እንዳትሞት" አለችኝ እውነት ቢሆን ምን ያህል እንደምታደል አላወቀችም። ወንድ ሁሉ ያለችው ሴት አይደለችም ወንድ ሁሉ የሚመኛት እንጂ እኔጃ ስትጫወት ጭንቀት ታርቃለች ስታለቅስ የሌላውንም ልብ ታስነባለች ፈገግታዋ ደግሞ በቃ ቃላት ይግለጿት ቢባል ገና ትህትናዋን ሊገልፁ ሲሉ ያልቃሉ ደግነቷንማ እኔም በአይኔ አይቼዋለሁ። በየሰአቱ ፍቅሬ ቢጨምርም ምርጫ የለኝም ለጊዜው ዝምታን መርጫለሁ እስከ መቼ እኔጃ እኔም አላውቀውም። እጇ ያለውን እስካርፕ አንገቴ ላይ አደረገችልኝ እና "እንዳይበርድህ ነው ለአንተ የሚሆን ጃኬት ስለሌለኝ ነው ደግሞ ይመለሳል" አለችኝ። ለካ በቲሸርት ነኝ ብርዱን ያስታወሰችኝ እንዳይበርድህ ስትለኝ ነው። በድፍረት አቀፍኳት። "በቃ እንዳይመሽባችሁ" ብላ ቻው እንኳን ሳትለኝ እየሮጠች ወደቤት ተመለሰች። ራቅ ብለው የሚጠብቁኝ ጓደኞቼ ጋር ስደርስ "ኧረ አቡሻ ግን ሴቶችን ምን ብታስነካቸው ነው ጠብ እርግፍ የሚሉልህ" አለኝ ናታን። "ጠብ ብዬ እኔ ቀድሜ የእሷ እንዲህ መሆን ይገርምሃል እንዴ" አልኩት የሰጠችኝን እስካርፕ እያየሁት። ዘኪም "ኧረ ቅድም ዶክተሩ ምን ብላቹሁ ነው ኤደን ስትመለስ ፊቷ የተለወጠው" አለኝ እኔም ያለንን ስነግራቸው በሀሳብ ተከዙ "እኔ ግን ሀሳብ አለኝ" አልኳቸው እነሱም ፊታቸውን ቀደ እኔ አዙረው ሲያዩኝ ቀጥል መሆኑ ስለገባኝ " እናቷ ሽልጦ መጋገር እንደሚሆንላቸው ነግራኛለች እናም እሳቸውን የምታግዝ ሰራተኛ ቀጥረን እሱን ቢሰሩ" አልኳቸው "አንተ አስበኸዋል ምጣድ አለ ለልጅቷም ይከፈላል ዱቄትም አለ እኮ..." አለ ናታንም። "ለአባዬ ብነግረው ሳያቅማማ ነው የሚረዳኝ እኛ ብቻ የምታግዛቸውን ሰራተኛ እንፈልግ" አልኳቸው። ይሄን እያወጋን አስፓልቱ ጋር ደረስን እኔም ለሹፌራችን ለያዕቆብ ደውዬ ጠራሁት እና በሌላ ታክሲ ጓደኞቼን ሸኘኋቸው። ያዕቆብ ብዙም ሳይቆይ መጣ እኔም ወደቤቴ ተመለስኩኝ አጎቴንም ቻው ሳልልው። ቤት ስደርስ እናቴ በስስት ነበር የተቀበለችኝ። "አቡሻዬ ደህና ነህ" አለችኝ "ደህና ነኝ ማም" አልኳት ሶፋው ላይ እየተቀመጥኩ "ዳዲ የት ነው" አ

ልኳት እናቴም "ላይብረሪ ነው" አለችኝ እኔም ተነስቼ የቤቱን ደረጃ ወጥቼ ወደ አባቴ ላይብረሪ አንኳኩቼ ገባሁ "የኔ ጀግና ልጅ" አለኝ "ዳዲ" ብዬ ተጠመጠምኩበት በአባት መዳፉ ፀጉሬን ዳብሶኝ"ሰላም ተመለስክ ተረጋጋህ" አለኝ እኔም "አዎ አስጨነኳችሁ" አልኩት ፊቱ ካለው ወንበር ላይ እየተቀመጥኩ። "ለእኛ ሳይሆን ለራስህ አስብ" አለኝና የከፈተውን መፅሐፍ እየዘጋ "እሺ ምን ልታዘዝ" አለኝ። "ዳዲ የእናንተ ማህበር እርዳታ ሊያደርግላት የሚገባ ልጅ አለች" አልኩት። አባቴ ከተወሰነ አመታት በኋላ በራሱ ፍቃድ ስራውን ለቆ የበጎ አድራጎት ስራ ላይ ተሰመርቷል። "የት ናት ምን እንርዳት" አለኝ እኔም "የእኛ ግቢ ተማሪ ናት " አልኩት አባቴም "አቡሻ ታዲያ ትምህርቷ ላይ ነው ድጋፋችን" አለኝ። እኔም ያለውን ነገር በተወሰነ መልኩ ነግሬ ሰራተኛ ምጣድ ዱቴት እንደሚያስፈልገን ነገርኩት። አባቴም ፈገግ ብሎ አይቶኝ "ታዲያ ይሄን ማህበሩ ሳይሆን እኛ እንፈታዋለን እሺ " ብሎኝ ቼክ አውጥቶ ብር ፅፎ ሰጠኝ አባቴን አመስግኜ እኔም ወደ ክፍሌ ገባሁ። የቤት ልብሴን ለቤሼ እስካርፖን ግን ከአንገቴ ላይ ማውላቅ አልፈለኩም ለጓደኞቼ ደውዬ ስለገንዘቡ ሰነግራቸው ናታንም ብር እንዳገኘ ነገረኝ። ነገ ላየው እየጓጓሁ ወደ ናፈቁኝ ቤተሰቦቼ ጋር ተቀላቅዬ የጀመሩትን ፊልም ማየት ጀመርኩ።.......ይቀጥላል!
🌿ክፍል አስራአንድ 💖
❤ እንዲደርሶ አብሮነታችሁን @yebezawit2 💌ቅርጫታችን ላይ ሀሳብ በመስጠት ያሳውቁን!!😘
💖ድምፅ ይስጡ💖
"በመሀል ለተፈጠረ የቃላት ግድፈት ይቅርታ እጠይቃለሁ"
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
❤የግጥም መንደር በቤዛዊት💟
😍ክርስቶቤል🌹
❥❥________⚘_______❥❥
🌿ክፍል አስራአንድ 💖
❤ እንዲደርሶ አብሮነታችሁን @yebezawit2 💌ቅርጫታችን ላይ ሀሳብ በመስጠት ያሳውቁን!!😘
💖ድምፅ ይስጡ💖
"በመሀል ለተፈጠረ የቃላት ግድፈት ይቅርታ እጠይቃለሁ"
╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
╚═══❖•🌺🌸•❖═══╝
❤የግጥም መንደር በቤዛዊት💟
😍ክርስቶቤል🌹
❥❥________⚘_______❥❥
:(
እኔም ብሆን ደስታን ፍለጋ ስኳትን ነው የተከፍሁት…ደስታን ስፈልግ ነው ያን ሀዘንን በመንገዴ ያገኘሁት…አሳልፈኝም ብዬ ተማፅኜውም ነበር…
✍🏽 ፊሊሞን የማርያም ልጅ ✍🏽
ግን ምን ዋጋ አለው አይሰማም
ማስከፋት ነው የእሱ አለም😔
ይሁንለት በእኔ ደስ ካለው
መንገዴን ዘግቶ አካሌን ቢያርቀው
ልቤ እንደው ከእሷ ጋር ነው።
✍ቤዚ የራጉኤል ልጅ✍

ብቸኛ ስለሆንኩ አይደለም ያፈቀርኩህ
ሰው አጥቼም አይደለም የመረጥኩህ
እናም ሳትዘጋጅ ቀርበህ አታሳምመኝ
መድሃኒት ባትሆነኝ በሽታ አትስጠኝ!
✍ቤዛዊት የሴት ልጅ✍
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
❤🔥ከፍቅር❤🔥
ሰው አጥቼም አይደለም የመረጥኩህ
እናም ሳትዘጋጅ ቀርበህ አታሳምመኝ
መድሃኒት ባትሆነኝ በሽታ አትስጠኝ!
✍ቤዛዊት የሴት ልጅ✍
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
❤🔥ከፍቅር❤🔥
ከእብዷ ቤዚ ገፅ_1❤
...........ይመጣል.....አይመጣም......ይመጣል .....እያልኩ ከሀሳቤ ጋር ተጣልቼ ደግሞ ታርቄ ስጠብቅህ ነበር.....ምን ዋጋ አለው መጠበቅ ኪሳራ ነው እንዴ ማፍቀርስ?............እኔጃ እኔ እንደሆን እቆጥራለሁ....ይመጣል....❤....አይመጣም.....እያልኩኝ.....#እብድም አይደለሁ? ለሚያየኝ ግድ የለኝም............ለሊትም ቀን እቆጥራለሁ...."በቃሽ ልጄ" እስኪለኝ አባቴ.........🌞አዲስ ፀሐይ ስትወጣ በቃ ተቀየረ......ይመጣል ስል ወዲያው ይጨልም እና ጨረቃ🌛 ብቅ ትላለች ከዛም ፈገግ ስል.......አይመጣም ትለኛለች.......ለካ አትመጣም...... ረስቼው ነው........እብድ ዛሬን ኖሮ ትላንትን የሚረሳ ነገን የማያመልክ ነውና እንደ'ኔ መስለኸኝ ነበር.............ግን አይደለህም....🙄 ሲገርም🙄.........እንዲህ እየለፈለፍኩ እኔው ራሴ ነኝ"ቤዚ በቃሽ ተኚ" ብዬ ራሴን የማስተኛው😂 እውነትም አብጃለሁ...........🌞ፀሐይ ጨረቃ🌛.........ኧረ ልተኛ በቃ🙄
✍ቤዛዊት የሴት ልጅ ✍
@yebezigetmoch
🍃 በሰላም እደሩ🙏
ሰላም እደሪ እናት ሀገሬ ኢትዮጵያ 🇪🇹

💥 ❤😭ክፍል አስራ አንድ 🙏
..................ፊልሙ ላይ የተመሰጥኩ መስዬ እኔ ግን ባለፉት ቀናት ከኤዲ ጋር ያሳለፍኳቸውን ጊዜያት በምናቤ ደግሜ እያየኋቸው ነበር። "ነገ ትምህርት አለህ?" የእናቴ ጥያቄ ወደ ራሴ መለሰኝ።"አዎ ጠዋት ነው ያለኝ...ምነው ማም ፈልገሽኝ ነው?" አልኳት እናቴም "አይ በቃ ተወው" ብላኝ ፊልሙን ማየት ቀጠለች እኔም "በቃ ልተኛ ደህና እደሩ" ብያቸው ወደ ክፍሌ ገባሁኝ። ነገ ትምህርት አለ ባልሄድ በተደሰትኩ ግን ከትምህርቴ ጋር መኮራረፍ አልሻም።.................ለማግሰኞ የማይለቅ ሰኞ የለም እና ለሊቱ በብርሃን ድል አድራጊነት ተጠናቋል። እንደሁልጊዜው ቁርሴን በልቼ ወጣሁኝ። ሹፌራችን ያዕቆብም "ልጅቷ እሺ አለችህ እንዴ ፊትህ ተመለሰ" አለኝ በመስታወቱ እያየኝ። እኔም "ታውቃለህ ለሴት ቦታ እንደ ሌለኝ" አልኩት ግንባሬን ቋጥሬ ያዕቆብም የትራፊክ መብራቱን 🚦 አይቶ መኪናውን እያቆመ "ኧረ አቡሻ እኔን አትዋሸኝ ስትሄድ የነበረህ እና ስትመለስ ያለህ ገፅታ ሌላ ሆኗል" አለኝ። "ኦ እኔ ምን አስዋሸኝ ይልቅ ቶሎ ግቢ አድርሰኝ" አልኩት። ያዕቆብ የከፈተው ሙዚቃ ቀልቤን ሰረቀው...........
⏪⏪⏪ልሒድ ደግሞ አይኗንም ልየው⏩⏩⏩
⏪⏪⏪የደንቡን ላድርስ⏩⏩⏩❤❤❤
⏪⏪እፎይ ብዬ እንዳድር የልቤም ባይደርስ⏩⏩
ፈገግ አልኩኝ። ለእኔ አስቦ ይሆን እንዴ የዘፈነልኝ አልኩኝ። የኮሌጁ በር ጋር ስንደርስ "በቃ ሰላም ዋል" ብዬ የመኪናውን በር ከፍቼ ልወርድ ስል ያዕቆብ ዞር ብሎ እየተመለከተኝ "የሚጠቅምህን እና የሚጎዳህን አንተ ታውቃለህ....እንደ ወንድም ግን የደስታዋ ምንጭ ባትሆን እንኳ ለሀዘኗ ምክንያት እንዳትሆን" አለኝ። ለምን እንደዚህ አልከኝ ብዬ ከጠየኩት የካድኩትን እውነት ሊያውቅብኝ ነው ፍቅር አልያዘኝም ብዬዋለሁ። "አንተ ብዙ ታወራለህ....ስወጣ እደውልልሀለሁ" ብዬው ወረድኩኝ። ያዕቆብ መኪናውን አዙሮ ሲመለስ እኔም ወደ ግቢ ገባሁኝ። ምን ዋጋ አለው ቀበጧ ሜሪ ተቀበለችኝ" ምን ሁነህ ነው አቡሻ ስደውል ስልክህ ዝግ ቴክስት አትመልስ?" አለችኝ። "ደህና ነኝ.....አሁን ክላስ ልገባ ነው" አልኳት ከፊቴ ገለል እንድትል። "ናፍቀኸኛል እኮ" ንግግሯ ቀፈፈኝ። "እስኪ ሴት ሁኚ" ብዬ አልፊያት ጥያት ሄድኩኝ። አርፍጃለሁ እና አስተማሪው ገብቶ ነበር። በሩን ሁለቴ አንኳኩቼ ቆምኩኝ። "እስከ አሁን የት ነበርክ" የሚወደኝ መምህር በላይ ነበር። "መንገድ ዝግ ሆኖ ነው" አልኩት። አስተማሪው አስገባኝ እኔም ከኋላ ወንበር ሄጄ ተቀመጥኩኝ።............የትምህርት ሰአት አልቆ አስተማሪው ስም ጠርቶ ወጣ። የክፍላችን ተማሪ ሎዛ ወደ እኔ ዞራ "አምሮብሃል" አለችኝ። ወይ ጉዴ እኔ ብቻ ነኝ እንዴ የምታያቸው አልኩኝ። ጓደኞቼ ሲመጡ ተያይዘን ወደ ኤደን ጋር አቀናን።..........የኤደን ቤት ደርሰን የግቢው በር አንኳኳን "ማነው? እያንኳኳ የሚሳደበው" እያለች አንድ የሴት ድምፅ ከውስጥ ተሰማን እኔና ጓደኝቼ ተያይተን ፈገግ አልን። ኤደን ነበረች "እናንተ እንዴት ብትደፍሩ ነው በሩን የምትደበድቡት" አለች። ናታንም "እእ እስክሪኑ እምቢ ሲለን ነዋ" አላት ኤደንም " እእእ ታዲያ በድንጋይ አትፈነክቱትም" ብላ ሳቀች። "ኧረ ቆምን እኮ"አላት ዘኪ ኤዲም ሰላም ብላ አስገባችን የኤደን እናትም ውጪ አጠር ያለ ዱካ ላይ ተቀምጠዋል። "የኔ አንበሶች" ብለው በእናት ፍቅር ተቀበሉን። ወደ ውስጥ ዘልቀን ስናወጋ ቆይተን......"የኤደን እናት ያው እርሶ አሁን ትንሽ እረፍት ስለሚያስፈልጎ...." "አረጀሽ እያልከኝ ነው ልጄ?" አሉኝ ንግግሬን ሳያስጨርሱኝ። እኔም ፈገግ ብዬ "አይደለም ገና ኖት ግን ለጊዜው እንዲያርፉ ብለን እኔና ጓደኞቼ ሰራተኛ ልንቀጥርሎ ነው" አልኳቸው። ናታንም " ሽልጦም መጋገር እንደሚወዱ ስላወቅን እሱንም ከእሷ ጋር ሁነው ይሸጣሉ" አላቸው። ኤደን "ምንድነው አቡሻ ቀልድ አይደለም አአ" አለችኝ "አይደለም ኤዲ አንቺም ትማሪያለሽ እሳቸው እረፍት ያደርጋሉ" አልኳት ተነስታ ተጠመጠመችብኝ። እናቷም "የኔ ልጆች ተባረኩ......አሁን ህፃኑ ቂርቂቆስ አደመጠኝ ፀሎቴን ልጄ ብቻ ትማርልኝ ሌላውስ ተዉት" አሉን። ዘኪም "እናታችን ከዚህ በኋላ አያስቡ ተጋግዘን እናልፈዋለን" አላቸው።
እኔና ኤዲ ዱቄት ለመግዛት ከቤት ወጣን። ወደ ሱቁ እየወሰደችኝ "አቡሻ" አለች ቀና ብላ እያየችኝ። ስሜ አፏ ላይ ጣፈጠኝ። "ወዬ" አልኳት በግራ መጋባት የሚያዩኝን አይኖቿን እያየኋቸው። "የምር አትጎዳኝም አይደል የላከህ ሰው የለም አአ" አለችኝ እኔም "አንቺን ለመጉዳት ብላክ እንኳን አልችልም" አልኳት "ብሩን ከየት አመጣኸው የሀብታም ልጅ ነህ?" አለችኝተ "አይ ሀብታም ሆኜ አይደለም ግን ከጓደኞቼ ጋር አዋጥተን ነው" አልኳት "እሺ ግን እናንተ ለ'ኔ እንዲህ ሆናችሁ እኔ ለእናንተስ?" አለች። "አትራቂን እሱን ብቻ አድርጊልን" አልኳት ኤዲም በረጅሙ ስቃ "በእኔ ሰልችታችሁ ካልሄዳቹ እንጂ እኔ እንደ ሙጫ ነው የምጣበቅባቹ ወንድሜ" ብላ ከስሬ ተሸጎጠች። ዱቄቱን ገዝተን ለቤት አስቤዛ የሚሆነውንም ነገር ሸምተን ተመለስን።......ከቀናት በኋላም አዲስ ሰራተኛ ተቀጠረች ኤዲም ትምህርት ጀመረች። እናቷም ሁሌ ለእኔም ለጓደኞቼ ሽልጦ ይልኩልናል። እውነትም እጅግ የሚጥም ነው። ጠዋት ጠዋት እሱን በሻይ በልተን ወደ ክፍል እንገባለን የእኔ ብቻ ስለሆንኩ ከእነሱ ጋር የማልማረው እኔ ክላስ ሲኖረኝ ተሰብስበው ይጠብቁኛል። ክላስ ባይኖርም ግቢ ተገናኝተን እናጠናለን። ከዛ ኤዲን ሸኝተናት ወደ የቤታችን እንከተታለን። ዛሬ ግን ናታንም ዘኪም አይመጡም። ለእኔ ብለው እንድነግራት ስለሚፈልጉ።....ክላስ አልነበረንም እና ያገኘኋት ሰፈሯ ሄጄ ነበር። ብታወልቀው ብዬ የምመኘው ማቋ ይኸው እስከ ዛሬ ከሰውነቷ ላይ አልወጣም። አቅፌ ሰላም አልኳት እና "ዛሬ እነ ናታን እኮ አይመጡም?" አልኳት በተስፋ እንዳትጠበቅቸው። "ኧረ...ሲያስጠሉ እኔ ደግሞ የሆነ ቦታ ልወስዳቹ ነበር....በቃ እኔና አንተ አብረን እንሄዳለን" አለችኝ። እኔም "እሺ ግን የት ነው?" አልኳት። "ሰርፕራይዝ ነው" ብላ እጄን ጎትታ መንገዱን አስጀመረችኝ። የእውነት በዚህ ሁኔታ አያታለሁ ብዬ አስቤ አላውቅም በዚህን ደረጃ መቀራረባችንም ደንቆኛል። ይበልጥ ደግሞ ከናታን ጋር ሆና ሳቅ ሲፈጥሩ ምን ያህል ደስ እንደምትል። እኔጃ ስለ ኤዲ ለማውራት ለመናገር ባህር ቀለም ሆኖኝ ምድርም ሸራ ቢሆኑኝ ከመጀመሬ ያልቃሉ ለእሷ ያንሳሉ።.......ከታክሲ ወርደን ወደ ሆነ ከፍታ ቦታ ወሰደችኝ ተራራው ዙሪያውን በዛፍ ተክልሎ በወፎች ዜማ ተውቧል። "ወይኔ ሲያምር ኤዲ" አልኳት ተፈጥሮን እየቃኘሁ። "ማን መሰልኩህ ኤዲ እኮ ነኝ...ና እንቀመጥ" ብላ ለእኔ ለእሷ ብቻ የተዘጋጁ የሚመስሉ ድንጋዮች ላይ ተቀመጥን ከፊት ለፊታችን ባህር የሆነችው አዲስ አበባን እናያታለን። "ወደድከው" አለችኝ። እኔም "አንቺ መርጠሽው እንዴት አልወደውም?" አልኳት ጥያቄዋን በጥያቄ እየመለስኩ። "ባትወደው ግን አልቆልህ ነበር" ብላ ትከሻዬ ላይ ተደገፈች። "ታውቃለህ አቡሻ ስለአወኩህ እድለኛም ደስተኛም ነኝ" አለችኝ። ከእኔ በላይ ግን እንደማይሆን ልነግራት ብዬ ድፍረት አጣሁ። መልሴን ዝምታ አድርጌ በተፈጥሮ ውበት መደመሜን ቀጠልኩኝ። ስናወራ ቆይተን "እስኪ ዝፈንልኝ" አለችኝ። "እኔ ዘፈን አልችልም" አልኳት። እውነትም ዘፈን

ዛሬ ሰምቼው ነገ እረሳዋለው ጎበዝ አድማጭ አይደለሁም። "እሺ መዝሙር" አለችኝ። "ኤዲ እኔ ደምፄ አያምርም ባይሆን አንቺ ዝፈኚልኝ" አልኳት። ኤዲም "ኧረ በእኔ ልትስቅ ነው" አለች እኔም "ካሳቅሽኝ" አልኳት። ኤደንም ጉሮሮዋን ጠርጋ።
⏪⏪⏪ክብሬ ሞገሴ ነሽ እምዬ እናቴ⏩⏩⏩
እንባ አነቃት እና ዝም አለችኝ ቀጠል አርጋም ሲቃ ባነቀው ድምጿ
⏪⏪⏪መከራ እና ችግር ተፈራርቀውብሽ⏩⏩⏩
⏪⏪⏪የኑሮ ውጣ ውረድ አሳሩ በዝቶብሽ⏩⏩⏩.............ተንሰቅስቃ አለቀሰች። "ምንድነው ኤዲ" አልኳት በአንዴ የስሜቷ መለወጥ አስደንግጦኝ። "እናቴ ዛሬ ስትስቅ አየኋት......እናቴን ዛሬ ያለ እንባ አየኋት....." አቅፊያት ዝም እንድትል ብሞክርም እሷ ግን ስለእናቷ ማውራቷን ማቆም አልፈለግችም። እንባዋን በእጆቿ ዳብሳ ጥቁር ሻርፗ ላይ የቋጠረችውን ፈታ አወጣች እና ወደ እኔ ዞራ እያየችኝ "ከዚህ በላይ ብሰጥህ ደስ ይለኛል.....ግን የለኝም ስለሌለኝ ነው....እንባዬ የሚፈሰው በደስታ ብዛት ነው። አቡሻ ከሰው እንዳላንስ ብላ ምስኪኗ እናቴ አንሳለች እኔ እንዳልጠቁር እሷ ጠቁራለች እኔ እንዳላዝን እሷ አዝናለች ህመሟን ሸሽጋ ሰው እንድሆን ተሰቃይታለች።ከጎኔ ማንም የለም ስል እግዚአብሔር ለእኔ የላከህ መልዓክ ነህ አንተም ጓደኞችህም የነፍሴን በረሃ በእናቴ ሳቅ አርሳችኋታል። ምንም ልልህ አልችልም ታውቃለህ....." የምታወራው ግራ ገብቶኛል "ምንም አትበይኝ ኤዲ ይሄ እኮ ምንም ነው" አልኳት ውለታ መስሏት እንዳትጨነቅ። "ለእናንተ ነው ምንም የሆነው ለኔ ግን እኔን ነው ምንም ከመሆን የመለሳችሁኝ.....እንዳትጎዳኝ እንደ ወንድሜ እያየሁ እንዳትሰብረኝ እሞታለሁ ተጎድቶ ድጋሜ ማገገምን አላስብም እና...." እጇ ላይ ያለውን ሀብል አሳየችኝ "አባቴ የሰጠኝ የድሮ ስጦታ ነው ስለምወደው ነው የምሰጥህ ከልብህ አዝነህብኝ ስትጠላኝ ከአንገትህ ላይ አውልቀው" ብላ በእንባ ገጿን እያራሰች በአንገቴ ላይ አሰረችልኝ። ምን ልበላት ይበልጥ አቅርባ እንዳራቀችኝ አልገባትም። እኔም አቅፊያት "መቼም አልጎዳሽም አንቺን ለመጎዳት ወኔው የለኝም" አልኳት። ማፍቀሬን ልነግራት ብሄድም ግን እሷ ወንድምነቴን በእምነት በቃል አፅንታዋለች። ዝም.......በቃ ዝም.......ምርጫ የለኝማ።.......
ክፍል አስራ ሁለት #በምዕራፍ ሁለት ይመለሳል....
💖💖ታሪኩ እንዲቀጥል ድምፅ ይስጡ!!!💖💖

😍ውድ የግጥም መንደር ቤተሰቦች እንዴት አመሻችሁ.....ለቀናት በመጥፋቴ 💖 ይቅርታ እጠይቃለሁ....ላሳያቹኝ ፍቅር እና ደግነት ግን በእግዚአብሔር ስም አመሰግናለሁ 😍 ሁሌም ፈጣሪ በፍስሃ ያኑራቹ!!!
#ክርስቶቤልን በምዕራፍ ሁለት ይዤላችሁ እመለሳለሁ.....
መልካም ንባብ...
🙏ስለ ሐገራችን ስለ አለም እንፀልይ 😭
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
#ክርስቶቤልን በምዕራፍ ሁለት ይዤላችሁ እመለሳለሁ.....
መልካም ንባብ...
🙏ስለ ሐገራችን ስለ አለም እንፀልይ 😭
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
ከእብዷ ቤዚ ገፅ #1
..........ነጋ እኮ አንቺም ወጣሽ 🌞ፀሐይ.........ግን ማንም የለም.....ሊጠይቀኝ የመጣ የለም.........ለነገሩ ልክ ነሽ......ለሰው መድሃኒቱ እራሱ ነው.......ግን ሰው እንዴት ቀሏል..........በቃ ተንኮል መሸረብ......ወጥመድ ማጥመድ.......ሰው ወድቆ ሲያይ ሰልፊ መነሳት.......🙄🙄ሁሉም ለካ ራሱን ስቷል.......ዝና ክብር ገንዘብ...ልቡን አውሮታል...ይታይሽ ፀሐይ....
ዛሬስ ግን ይመጣል??.....ለካ ደግሞ አይመጣም.....የሚጨክን አይመስለኝም ይመጣል....🌞ውይ አንቺ ደግሞ ሙባረክን ነዋ ጓደኛዬ ወንድሜን....እውነት ስልሽ ወንድሜ ነው!🙄ሰውም እንዳንቺ ጠርጥሮኛል.....ግን ይመጣል?😭...... ተይ ተይ የሞተ ሰው አይመጣም አትበይ.....🙄 እሱ እኮ እኔ አስከፍቼውም ይቅርታ ሊለኝ ይመጣል.....ሁፍፍ ዛሬ ግን ጨክኗል.....🌛ከመቼው ወጣሽ ደግሞ
ጨረቃ.....ይመሻል....ይነጋል....ምንድነው...ግን እንዲህ የሚያፈጥነው...? አዎ ደህና ነኝ ግን አይደለሁም😢........ሙቤን እኮ እየጠበኩት ነው.....እእህ አታውቂም የኔን ሙባረክ🌛 እኮ እሱን ማን ይረሳል.....ስለ እሱ ንገሪኝ..? አላቆምም ከጀመርኩኝ.....ደግሞ ሊነጋ ነው መሰለኝ ልተኛ በቃ🌛ደህና እደሪ ጨረቃ🌛
#ገፅ 2 ❤
...ግን ቆይ ጨረቃ ስሚኝ.....አንተ ማለት ለእኔ ሙቤ.....ከአንተ በፊትም ከአንተ ኋላ ማንም ከአንተ ጋር አይወዳደርም....❤...❤...❤ ለካ እንደዚህ ነው መለያየት.....ምን ትዝ አለኝ መሰለህ...."ቤዚ ዛሬን ኑሪ" የሚል ደረቅ ቃልህ ትዝ አለኝ😁........ሁሌ ስትመክረኝ እኔ ሳበሳጭህ.......😂እንደ እኔ ጨጓራህን የላጠ እኮ የለም.....💀ካስታወስክ ያን ጊዜን........የማይሆን ቃል ተናግሬህ አበሰጫጭቼህ........አለፍ ብሎም አስለቅሼህ.......😭 ቤት ድረስ መጥተህ በኔው ጥፋት ይቅርታ አልከኝ........ለካ ከጥፋቴ እኔ በልጬብህ ነው..........ፈቲያ እንኳን እንዴት እንደምትቀናብን....🙄🙄ያ ጊዜ ለካ ውድ ነበር........አይ ዛሬማ እንደ አንተ የሚወደኝም የለም......እውነት ስልህ.......😭 በሆነ ተአምር ከመቃብር ብትወጣ ብዬ እመኛለሁ......ግን አትመጣም? ትመጣለህ.....ጨረቃን እያየሁ🌛 ፀሐይን🌞 እያማከርኩ እየጠበኩህ ነው..!.....ልለው ነበር አንቺ ጨረቃ🌛 ....ግን አይሰማኝም......ብዙ ካወራሁ እኮ እንዴት እንደሚከፋኝ.......በቃ አጠይቂኝ ጨረቃ.....🌛ተከድኖ ይብሰል ልተኛ እኔም በቃ....
ገፅ 3 🌞
🌞ፀሐይ እኔም አንዴ እንደ አንቺ ከፍ ብዬ ማየት ብችል.........ብዙ የማየው ሰው ነበር.......ግን አልታደልኩም......እኔ ሰው ነኝ.....😂 ለካ ሰውነቴን ቀምተው #እብድ ነሽ ብለውኛል .....#ተመስገን ነው። ዛሬ ከነጋ ምን አየሁ መሰለሽ........በፌስታል ሙሉ ዳቦ ተሸክሞ ወደ ቤቱ እየሄደ አንዱ በላተኛ..........ማስቲሽ የሚመጠውን ህፃን እያየው አላለፈውም መሰለሽ😭😭😭...........ምን አለ ግማሽ ቢሰጠው??......እኔማ #እብድ ነኝ ምንም የሌለኝ ያለኝ ወሬ ነው እናም አወራለሁ ስለ እሱ............ፍቅር ተፈትኗል.......ፍቅርን ያዋረዱ መስሎአቸው እነሱ እየተዋረዱ ነው......ግን ማንም አይሰማኝም.....ያበደን ማን ይሰማዋል.....ጠባቂን ማን ያደምጠዋል......ማን ማንን ያክበራል....ሁሉም ተናንቋል😭🙄🙄🙄.....አንቺስ ምን ታዘብሽ.......ውይ እሱንማ ተይው በውድ ዋጋ በገዛዋ መኪና....😭የራሱን ውድነት ረስቶ....በቆርቆሮ ሰውን ይለውጣል.....🌞አይ ፀሐይ አንቺም ብዙ ታዝበሻል🌞..........ደግሞ ይሄ ዘፈን ሙቤን ሲያስታውሰኝ...😭ልራቅ ወይስ ልጠብቅ እስኪዘጉት.....😢😢....🙆🙆ይሄ ዘፈን ሙቤን ከልቡ ያሳዝነዋል....ግን ከእሱ ታሪክ ጋር ምንም አይያያዝም....😂 ደረቅ እብድ እኮ ስለሆነ ነው..."ከአንቺ ባላገኝ የልጅ ፍሬ አልቀይርሽም በሰው ወሬ...ሚዛን ደፍቷል ፍቅሬ.." ጥበቡ ወርቅዬ እኮ ነው። 😢አጥፉት አጥፉት!! የሚሰማኝ ግን የለም ባክሽ ልራቅ 🚶🚶..... እስከ ዛሬ ስላበሳጨሁት ነገር እኮ #ይቅርታ 🙏 ብዬዋለሁ ግን አልመጣም💖 የቀረኝ የሚወደውን ፒዛ🍕🍕ማምጣት ነው። እብድ እኮ ነበር እኔ ሳውቀው እናም እብድ ይረሳል.......ይስቃል......ያለቅሳል......ይፈነክታል.......ይጠፋል......ከዛ ተመልሶ ይመጣል🏃🏃........🙄🙄🙄 እሱ ቀረ በቃ አይመጣም ማለት ነው.......አይ ይመጣል....😍🙏...........
ገፅ 4 😘
......🌛 አትረበሽ ብለው እምቢ አለኝ ሆዴ.....ምን ተሻለኝ ጨረቃ......😢.....ይመጣል እያልኩ ስጠብቅ.........ለካ አይመጣም......ግን እኮ ይመጣል.....እመጣለሁ ብሎ አይቀርም...💑.........ተስፋ አደረኩ...ጠበኩ...ጠበኩ....ግን አይመጣም.....አልመጣም....🌛ምን ልሁን ጨረቃ🌛.......ረመዳን እኮ ነው እሱ አይቀርም......... እውነትሽን ነው ፈጣሪ ጋር ነው ያለው........ግን አሁንም ይወደኛል አይደል....?😢.......... ቀበጧ ነበር እኮ የሚለኝ........እማማ ወርቄ እሱ የሚረዳቸው እናት ናቸው😍.......እናቴ ናት ነው የሚለው.......ሁሌ እዛ ይወስደኝ ነበር....😂ምን ዋጋ አለው መጨረሻ ላይ እንዳበሳጨሁት ነው......🌛አንቺ እራስሽ ስንቴ በጎዳናው ላይ አይተሽናል🌛......ከወንድምነት ያለፈ ረቂቅ ፍቅር💖.....💖...💖....ያ ጊዜማ ተይው....🌞ፀሐይም እኮ አታምንም......እየመከረኝ እንዲያው እንደ ለመደው ጥርሴ ብቅ ሲል እና ሳልሰማው ስቀር.......🙆 ጆሮዬን አንጠልጥሎ ነበር የሚሸኘኝ......ከዛ ደግሞ በጠዋት መጥቶ ያገኘኛል.....❤አሁን አንቺስ አልናፈቀሽም....❤ የዛን ቀንስ አስታወሽ🌛ጨረቃ........ቸኮሌቴን እረስቶ መጥቶ ያስመለስኩት.....እና ደግሞ ይዞልኝ የመጣው...... ክፉ እኮ ነኝ🙆🙆🙆 እንደ ልጅ እኮ ስለሚያቀብጠኝ ነው.....😂😂😂አሁንማ ተይው.....ሳላረጅ አስረጅተውኛል...ደግሞ እንደ አባት ምግብ ብይ አልበላም ተባብለን የምንጨቃጨቀውስ❤😭....ውይ ግን በሆነ መንገድ ብመልሰው እመኛለሁ....እኔ እኮ እሱን የምወደው ቀሚሷን ይዤ እንዳሳደገችኝ እህቴ ነው.....አንዳንዴ ስራ በዝቶበት እኔ ሱቁ ጋር ሄጄ የምበጠብጠውስ...ለካ መውደድ ቀበጥ ያደርጋል....እኔጃ ከአለም ላይ ጥቂቶች ንፁህ ወንድም ልዮ ጓደኛ ያገኛሉ ያውም ደረቅ እብድ....ከእነሱ መሀል አንዷ እኔ ነኝ🙏😘....ታድዬ😁.....🌛ውይ ጨረቃ ግን ተይ ሆዴን ባዶ አታስቀሪው🌛....እስኪ አንቺም ተኚ...💖😘.......
ገፅ #5 ❤❤
...........ዛሬ እኮ አገኘሁት መጣ....🌞ፀሐይ አየሁት ሙቤን.....ለካ ልቤ ውስጥ ነበር.....አላየሁትም እንጂ ሀሳቤ ውስጥ ጭንቅላቴ ውስጥ ነው.....😂ኧረ ተይ ፀሐይ..🌞.....እራሱ ነው እንጂ የጠራኝ....ግን ኮራሁበት....😂 ደግሞ እንዲያቀብጠኝ ነዋ........ለካ የምንወዳቸው ሰዎችን ልባችን💖 ውስጥ ነው የምናኖራቸው...........💑አሁንም ትቀብጫለሽ.........አለኝ 😘 እንዴት እተዋለሁ......ምን ትዝ አለኝ መሰለሽ.....ከትምህርት ቤት ወጥቼ እየጠበኩት......ዘግይቶብኝ🙆..ያስከፋኝ ዕለት.....የቀጣሁት ቅጣት እኮ....😂😂 ትንሽ

ደቂቃ ላስጠበቀኝ ያዘፈንኩት ዘፈን......ያስደነስኩት ዳንስ.......ያስጮውኩት.....ጩኸት....😂........ዛሬ እንደዚህ ልጠብቀው😢.....😢....😢...😢......ግን እንዳታለቅሺ ስታለቅሺ እኮ.......... የአራስ ቤት ህፃን ነው የምትመስይው..........ስለሚለኝ አላለቅስም.......ደግሞ ይቅርታዬን አልፈልግም አለኝ🙄........ስታበሳጪኝ ነው የምወድሽ እናም እንደምትወጂኝ የማውቀው አለኝ......🌞 ደስ ብሎኛል.....አይመጣም......አይመጣም........ይመጣል....ይመጣል.....እያልኩ እኮ ነው.....የመጣው💑💖.........
........❤ በመጨረሻም ልቤ ውስጥ ያለው.....ሙባረክ እንዲህ አለኝ.............. ሁሌም ፈገግ በይ.........ለሰው ኑሪ......ፍቅርን አክብሪ.......ክፋትን ቅበሪ.....ሰው ሁኚ!.....ስናፍቅሽ ወደ ልብሽ ሰማይ ገብተሽ ብረሪ ......ታይኛለሽ.....አለኝ......😘🌞🌛
😘ከእብዷ ቤዚ ገፆች የተወሰደ😍
ሙቤ የኔ እንዴት አርጎሀል አንተስ ናፍቆቱ
አይታይህም ወይ አብሮ መብላቱ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️🌸🌸🌸🌸🌸🌸

እቴ አንቺ ፍረጅኝ
.
.
ልዕልናን ጭነሽ የፊት ገፅ ወዘናሽ አድሮ እየማረከ
ንዋይ የታደለ ፣ የወንበር ሹመኛ ከተንበረከከ
እንደ ገብስ ቆሎ ለመዝገን ሲሻቸው
አቅሙ ባይሰጠኝ ቆሜ ባልጥላቸው
የኔነትሽን ረስተው የነሱ ሊያደርጉሽ
በፍቅር ጎጆ ውስጥ ለዘመን ቢመኙሽ
እኔ ምን አቅም አለኝ
ስጋየን ሊሰቅሉ ለፍርድ ቢያቆሙኝ
ግን...
በመውደድ ልሳንሽ ፍቅርን ባስተማረኝ
ልሙትም ልዳንም እቴ አንቺው ፍረጅኝ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አማኑኤል ደርበው(አማን)
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
❤❤❤❤ከፍቅር❤❤❤❤❤
.
.
ልዕልናን ጭነሽ የፊት ገፅ ወዘናሽ አድሮ እየማረከ
ንዋይ የታደለ ፣ የወንበር ሹመኛ ከተንበረከከ
እንደ ገብስ ቆሎ ለመዝገን ሲሻቸው
አቅሙ ባይሰጠኝ ቆሜ ባልጥላቸው
የኔነትሽን ረስተው የነሱ ሊያደርጉሽ
በፍቅር ጎጆ ውስጥ ለዘመን ቢመኙሽ
እኔ ምን አቅም አለኝ
ስጋየን ሊሰቅሉ ለፍርድ ቢያቆሙኝ
ግን...
በመውደድ ልሳንሽ ፍቅርን ባስተማረኝ
ልሙትም ልዳንም እቴ አንቺው ፍረጅኝ
°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°°
አማኑኤል ደርበው(አማን)
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
@yebezigetmoch
❤❤❤❤ከፍቅር❤❤❤❤❤