Telegram Web Link
በ<ሙጀሲም> ዙሪያ የሙጅተሂዶች አቋም ምንድን ነው?


➀ [መልስ አንድ]፦ በዓሊምነታቸው በነብያዊ ሐዲስ የተመሰከረላቸው የኢማሙ ማሊክ ተማሪ ሻፊዒይ እንዲህ አሉ፦
【المجسم كافر ـــ وكذا من قال إنه قاعد فوق العرش】

ትርጉም፦ <አላህን በአካል የሚገልፅ ሙጀሲም ሙስሊም አይደለም። እንደዚሁም አላህ ከዓርሽ በላይ ይቀመጣል ያለ።>

ይህንንም ኢብኑል ሙዐሊም አል ቀረሺይ «ነጅሙል ሙህተዲ ወረጅሚል ሙህተዲ በተሰኘው ኪታባቸው ከ"ቃዲ ሑሰይን" በማስተላለፍ ዘግበውታል።



➁ [መልስ ሁለት]፦ የሻፊዒይ እውቅ ተማሪ እና መልካም ጓደኛቸው ኢማም አህመድ ቢን ሐንበል እንዲህ አሉ፦
【من قال الله جسم لا كالأجسام فقد كفر】

ትርጉም፦ <አላህ አካል ነው ነገር ግን አካላትን አይመስልም ያለ ሰው በርግጥም ከፍሯል ክዷል።>

ይህንንም «ሷሒቡል ኺሷል» ከ«አዝ'ዘርከሺ» በመያዝ አስተላፎልናል።

<ተሽኒፉል መሳሚዕ> በተሰኘው ኪታባቸው ጥራዝ አራት ገፅ [4/648] ላይ ጠቅሰውታል።

~
ኢማሙ አህመድ ቢን ሐንበል የዘመኑ ሙጀሲማ የሆኑት ወሀቢያ እና የቀደምት ሙጀሲማ የኛ ናቸው በማለት በውሸት ይለጥፉባቸው እንደነበረ ይታወቃል። እርሳቸው ግን «ሙጀሲም» ካፊር መሆኑን በማያሻማ መልኩ አስረግጠው አለፉልን።
~
ከዚያ በተጨማሪ ለማምታቻ "አካላትን ሳይመስል" በማለት ተጅሲምን የሚረጩ ወሀቢያ እና መሰሎቻቸው የሚሄዱበትን አካሄድ ተችተው፣ አውግዘው የለየለት ክህደት መሆኑን አስረግጠውልን አለፉ።

[መልስ ሶስት]፦ አል በያዲይ «ኢሻራቱል መናም» በተሰኘው ኪታባቸው የኢማሙ አቡ ሐኒፋን ንግግር ሸርሕ ሲያደርጉ እንዲህ አሉ፦
【 وفيه إشارات.. الأولى: أن القائل بالجسمية والجهة منكر وجود موجود سوى الأشياء التي يشار إليها حسا، فمنهم منكرون لذات الإله المنزه عن ذلك فألزمهم الكفر لا محالة وإليه أشار بالحكم بالكفر. الثانية من أطلق التحيز والتشبيه وإليه أشار بالحكم المذكور لمن أطلقه】

ትርጉም፦ <የአቡ ሐኒፋ ንግግር አመላካች ነገሮች አሉት። አንደኛው፦ አላህን በአካል እና በአቅጣጫ የሚገልፅ በገሃድ የሚጠቆም ከሆነ ነገር ውጭ ባለ ነገር የማያምን ነው፤ ከነሱም ከሚሉት ነገር የተጥራራው አላህን መኖር የሚክዱ ናቸው፤ ይህም ያለ ምንም ጥርጥር ካፊርነታቸውን ያስይዛል፤ ይህንንም ነው አቡ ሐኒፋ ኩፍር ክህደት ነው ሲሉ የጠቆሙት።

🈴JOIN🈴

https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ክፍል ②

#የኢስተዋዕ_ማብራሪያ!!

በኢማሙ-ማሊክ ኢብኑ ኣነስ ረድየሏሑ ተዓላ ኣንሁ!!!!
_______
#ሀፊዝ_ኢብኑ_ሓጀር_ፈትሁል_ባሪ ውስጥ የኢማሙ ማሊክን ንግግር በዚህ መልኩ ዘግበውታል።

#ይህ አገላለፅ የኢማሙ ማሊክ ብቻ ሳይሆን የሶሐብይቱ ኡሙ ሰለማ እና የረቢዓተ ብኑ አቢ አብዱረህማን ንግግር ጭምር ነው።
«الإستواء معلم والكيفية غير معقول»

•ዋህብያዎች በዚህ በኡሙ'ሰለማ ንግግር ሰዎችን ለማታለል ይሞክራሉ። ይህ ንግግር የሷ ብቻ አይደለም አንዳንድ ሰለፎችም ተናግረውታል።

☞ ይህ ንግግር ለነሱ መረጃ ሊሆናቸው አይችልም ይልቁንስ በነሱ ላይ ነው መረጃ የሚሆነው!

#ንግግሯን ብንመለከት
<الإستواء معلم>
{ኢስተዋዕ የሚለው የቁርዓን አንቀፅ መምጣቱ የታወቀ ነው}
በቁርዓን ውስጥ መጠቀሱ ማነም የማይክደው ነው።

<والكيفية غير معقول>
{ነገር ግን ከይፍያ/ዕንዴት/ የሚለው ጥያቄ ለአሏሕ አይገባም የሚገለፅበትም አይደለም፥ አእምሮም አይቀበለውም}

والكيفية في اللغة كل ماكان من صفات المخلوق
#እንዴት /ከይፍያ/፦ማለት ማንኛውም የፍጡር ባህሪ ሁሉ ከይፍያ /እንዴት/ ይባላል።
      ፦ተደላደለ፣ ተቀመጠ፣ ከፍ አለ፣ አቅጣጫ፣ ቦታ፣ መውረድና መውጣት ወ.ዘ.ተ.   #ከይፍ ተብሎ ይጠራል።

#ስለዚህ የኡሙ ሰለማ ንግግር የሚያስረዳን የዚች የቁርዓን አንቀፅ ተቀመጠ ፣ተደላደለ፣ከፍ አለና ወረደ ተብሎ እንደማይተረጎም እና ዕነዚህ ነገራቶችን ፍጡራን የሚገለፁበት ለአሏሕ የማይገቡ አእምሮ የማይቀበለው መሆኑን ነው ።

ምክንያቱም አሏሕን በፍጡራን ባህሪያት እንደማይገለፅ በቁርዓንን ነግሮናል።
قال الله تعالى【ليس كمثله شىء】
#ትርጉሙ፦ {እርሱን {አሏህን} የሚመስል ነገር የለም}
✘✘✘ ✘✘✘✘✘✘✘✘
『ስለዚህ አሏህን በቦታና በአቅጣጫ መግለፅ ቁርዓንን በግልፅ መካድ ነው』


https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
🌾 ሲሳይን [ሪዝቅን] ከሚጨምሩና ከሚያበዙ ነገራቶች መካከል🌴

ክፍል


🍂
➀ ►▸◦ አሏሕን መፍራት..!
ومن يتق الله يجعل له مخرجا - ويرزقه من حيث لايحتسب طلاق ٢-٣
[ አሏሕንም ለሚፈራ ሰው ለእርሱ መውጫን ያደርግለታል፥ ከሚያስበው በኩል ሲሳይን ይሰጠዋል። ]
🍂
➁ ►▸◦ ኢማን...!
وَلَوْ أَنَّ أَهْلَ الْقُرَىٰ آمَنُوا وَاتَّقَوْا لَفَتَحْنَا عَلَيْهِم بَرَكَاتٍ مِّنَ السَّمَاءِ وَالْأَرْضِ وَلَٰكِن كَذَّبُوا فَأَخَذْنَاهُم بِمَا كَانُوا يَكْسِبُونَ الأعراف ٩٦
[የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፡፡ ግን አስተባበሉ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው፡፡]
🍂
➂ ►▸◦ አሏሕን ማሀርታ መጠየቅ [ኢስቲጝፋር ማድረግ]
فَقُلْتُ اسْتَغْفِرُوا رَبَّكُمْ إِنَّهُ كَانَ غَفَّارًا نوح - ١٠
«አልኳቸውም፡- ጌታችሁን ምሕረትን ለምኑት፡፡ እርሱ በጣም መሐሪ ነውና፡፡
يُرْسِلِ السَّمَاءَ عَلَيْكُم مِّدْرَارًا - ١١
«በእናንተ ላይ ዝናብን ተከታታይ አድርጎ ይልካል፡፡
وَيُمْدِدْكُم بِأَمْوَالٍ وَبَنِينَ وَيَجْعَل لَّكُمْ جَنَّاتٍ وَيَجْعَل لَّكُمْ أَنْهَارًا -١٢
«በገንዘቦችና በልጆችም ይለግሰላችኋል፡፡ ለእናንተም አትክልቶችን ያደርግላችኋል፡፡ ለእናንተም ወንዞችን ያደርግላችኋል፡፡»
🍂
#ይቀጥላል....🙏

መልካም እለት ተመቸሁላችሁ...🙏

JOIN US

https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ክፍል ③

#በኢማሙ_ማሊክ_ኢብኑ_ኣነስ ረዲየሏሁ ዓንሁ ተናግረዋል ተብሎ ከተዋሸባቸው ንግግር መካከል በመረጃ አስደግፈን ከንግግሩ የፀዱ መሆናቸውን እናስቀምጣለን...!
------------------------------------------------------

ትክክለኛ በሆነ ሰነድ ከኢማሙ ማሊክም ሆነ ከሌሎች ሰለፎች የሚቀጥለው ንግግር አልተረጋገጠም፦
لم يثبت من حيث الإسناد عن مالك ولا عن غيره من السلف أنه قال "الإستواء معلوم والكيفية مجهولة"
«ኢስቲወዕነቱ የታወቀ ነው እንዴት እንደሆነ ግን ከይፍያው አይታወቅም።»


•በወሃብዩችና በሙጀሲሞች ዘንድ ኢስተዋዕኑቱ የታወቀነ ነው ሲሉ ከፍታው ነው የተፈለገበት ይላሉ እንዴት እንደሆነ ከፍታው ግን አይታወቅም ብለው ተጅሲማቸውንና ተሽቢሀቸውን ለማለባበስ ይሞክራሉ፥

➦ከስር ከመሰረቱ ይህ ንግግር በትክክለኛ ሰነድ ከአንድም የሰለፍ ኦለማዎች አልተረጋገጠም እና ለእምነት መገንቢያ ተደርጎ በጭራሽ አይወሰድም፥ ምንም እንኳን በኣንዳንድ እውቅና ካላቸው አሊሞች ዘንድ በኪታባቸው ውስጥ ቢያስቀምጡትም።


•ንግግሩ እውቅና ያላቸው አሊሞች በኪታባቸው እንደጠቀሱት የሚታወቅ ጉዳይ ነው፥ ታድያ መጥቀሳቸው ለምን ጉዳይ ነው?፥ በምን ኣይነት መልኩ ተረዱት? ከተባለ እንደሚከተለው ኦለሞች ገልፀውታል።
"الإستواء معلوم والكيفية مجهولة"
°ኣል-ኢስቲዋዑ መዕሉም ማለት፦ “በቁርዓን ውስጥ መጠቀሱ ማነም የማይክደው የተረጋገጠና የታወቀ ነገር ነው።”

°ወል-ከይፍየቱ መጅሁለቱን ማለት፦ “ነገር ግን የኢስተዋዕ ትርጉም/ትንታኔ/ ከብዙ ሰዎች ዘንድ ድብቅ/የማይታወቅ/  ነው።”

©ከይፍ ማለት እውነታው በሚል ትርጉም ይመጣል፥ እናም እዚህ ንግግር #ከይፍ የተባለው የፍጡራንን መገለጫ የሆነውን የቦታ ከፍታንና መደላደልን ለማንፀባረቅና ለመግለፅ አይደለም።
•••
#ገጣሚው እንድህ ይላል፦
#كيفية المرء ليس المرء يدركها       فكيف #كيفية الجبار في القيدم

“የሰውዬውን እውነታ እራሱ ሰውዬው አይደርስበትም፥    ታድያ እንዴት ጅማሪ የሌለውን የፈጣሪን እውነታ ሊደርስበት ይችላልን? አይችልም።”

#ከይፍ እዚህ ግጥም ውስጥ ሀቂቃ ወይም እውነታ በሚለው ትርጉም እንደምትመጣ ያስረዳናል።


ይቀላቀሉ..🙏
ይማሩበታል‼️

https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ክፍል ④
🍂
በኢማሙ ማሊክ ኢብኑ ኣነስ ረዲየሏሁ ዓንሁ ተናግረዋል ተብሎ ከተዋሸባቸው ንግግር መካከል በመረጃ አስደግፈን ከንግግሩ የፀዱ መሆናቸውን እናስቀምጣለን....!

ከእኛ ጋ ይሁኑ...!🙏
------------------------------------------------------
ኢማሙ ማሊክ ተናግረውታል ብለው ከሚያስጠጉት ንግግር ውስጥ አንድኛው ይህ ነው።

ንግግሩም እንደዚህ ይላል፦
«አሏሕ ከሰማያት በላይ ነው፣ ከእውቀቱ ምንም ነገር አይደበቅበትም።»
واما القول المنسوب لمالك وهو قول « الله في السماء وعلمه في كل مكان لايخلو منه شىء» 
🍂
ይሄም ንግግር ትክክለኛ በሆነ ሰነድ ከኢማሙ ማሊክ አልተገኘም፥ ወሬ ብቻውን መረጃ ሊሆን አይችልም።
🍂
•ይሄን ንግግር ካወሩት ሰዎች መካከል ኣብዱሏሕ ኢብኑ ናፊዕ ይገኛል።

ኣብዱሏሕ ኢብኑ ናፊዕ ደግሞ ፥ ኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሀንበል እንድህ ብለውታል፦
«ይህ ሰው የሀድስ ባለቤት አይደለም፥ ድክመት ያለበት ሰው ነው።»

©ኢብኑ ጀማዓ ኢዷሁ ደሊል በሚባል ኪታባቸው

#JOIN_US
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ክፍል ①

#የኢስተዋዕ_ማብራሪያ!!
በኢማም ሙሀመድ ኢብኑ እድሪስ ኣሻፊዕይ ረድየሏሁ ዓንሁ
🍂
#ኢማሙ ሻፊዕይ በፊልስጤን ሀገር ጛዛ በምትባል ቦታ በ150 ኣመተ-ሒጅራ ተወልደው በ204 ኣመተ-ሒጅራ ያረፉ ታላቅ ኣሊም ናቸው።

#ነብዩና_ሙሀመድﷺ ስለ እነርሱ እንድህ ብለዋል፦ “የቁርይሽ ኣሊም በእውቀቱ ምድርን ይሞላታል።”

በዚህ ሀድስ ዙሪያ የተለያዩ ኦለሞች ሀሳባቸውን ሰንዝረው ኣስቀምጠዋል፥ ወደ ዋናው ዝርዝር ባንገባም ኢማሙ ሻፊዕይን እንደተፈለገበት ያመላክታል፥ ምክንያቱም ኢማሙ አሻፊዕይ ከቁረይሽ የዘር-ግንድ ይመዘዛሉ። ረዲየሏሁ ኣንሁ!

ስለ ኢስተዋዕ በተጠየቁ ጊዜ መልሳቸውን እንድህ በማለት ኣስቀምጠዋል፦

"أمنت بلا تشبه وصدقت بلا تمثيل" ذكره الإمام أحمد الرفاعي في البرهان المؤيد
“ያለምንም ማመሳሰልና እንድህ ይመስላል ሳልል አምኛለሁ።”

የንግግራቸው ትርጉም ማብራሪያ
•『ፍጡራኖችን በጭራሽ በማይመስለው፣ በፍጡራን ባህሪያት በማይገለፀውና ከጉድለት ባህሪያት በተጥራራው ጌታዬ አምኛለሁ፥ ባወረዳቸውም የቁርዓን አንቀፆች ያለምንም መቀየር፣ ማመሳሰልና መካድ አምኛለሁ።』


قَالَ الإمامُ الشَّافعيُّ رَضِيَ اللهُ عَنْهُ: "ءامنْتُ بما جَاءَ عنِ اللهِ على مُرادِ اللهِ وبما جَاءَ عنْ رَسُولِ اللهِ صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ على مُرادِ رَسُولِ اللهِ"،

#ኢማሙ_ሻፊዕይ እንድህ አሉ፦
“ከአሏህ በመጡ ነገራቶች ሁሉ እርሱ (አሏሕ) በፈለገበት አምኛለሁ፥ #ከነብዩና_ሙሀመድﷺ በመጡ ነገራቶች ሁሉ ነብዩ ﷺ በፈለጉበት አምኛለሁ።”


© ኣል-ሀፊዙል-ሁስንይ
#ደፍዑ_ሹበሕ_መንሸበሀ_ወተመረድ!

يعني رَضِيَ اللهُ عَنْهُ لا علَى ما قد تذهَبُ إليه الأوْهَامُ والظُّنُونُ من المَعاني الحِسّيَّةِ الجِسْمِيَّةِ التي لا تَجُوزُ في حَقِّ الله تعالى.

°ኢማሙ ሻፊዕይ ንግግራቸው የሚያስረዳን «የእኔ ማመን ሀሳቦችና እስትንታኔዎች በሚሄዱበት መንግድ አይደለም፥ የኣካልና የስሜት ህዋሳት የሆኑ ለአሏሕ ተገቢ ያልሆኑ ነገራቶችን በማፅደቅ አይደለም።»

ኢማሙ ሻፊዕይ #ነጂሙል_ሙሕተድ በሚባለው ኪታብ ዕንድህ አሉ፦
“አሏሕን ከአርሽ በላይ ነው ብሎ የገለፀ ሰው ካሐዲ ነው።”

قال الشافعي رضى الله عنه
"من اعتقد أن الله جالس على العرش فهو كافر"
~•~•~•~•~•~•~
➣ JOIN_US
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ክፍል ②

በኢማሙ ሙሐመድ ኢብኑ ኢድሪስ ኣሻፊዕይ ረዲየሏሁ ዓንሁ ተናግረውታል ተብሎ የተቀጠፈባቼውን ንግግር በመጥቀስ ከንግግሩ የፀዱ መሆናቸውን በመረጃ አስደግፈን እናስቀምጣለን!!
---------------------------------------------------------------
•ተናግረውታል ተብሎ ከተዋሸባቼው ንግግሮች ውስጥ፦
قيل "القول في السنة التي أنا عليها ورأيت أصحبنا عليها أهل الحديث الذين  رأيتهم وأخذت عنهم مثل سفيان ومالك وغيرهما الإقرار بالشهادة أن لاإله إلا الله وأن محمد رسول الله وأن الله تعالى على عرشه في سمائه يقرب من خلقه كيف يشاء وأن الله ينزل إلى السماء الدنيا كيف يشاء ...." وذكر سائر فاسد كاسد الإعتقاد
©ዘሐብይ ሙኽተሶር ዑሉው ላይ ጠቅሶታል!!

የዚህ መልስ ጥርት ያለ ቅጥፈት ነው!!፥ ምክንያቱም በሰነዱ ውስጥ አቡ ሐሰን አል-ሐካርይ አለበት፥ ይህ ሰው ደግሞ ዘሐብይ ሚዛኑል-ኢዕቲዳል በሚባል ኪታብ ውስጥ እንድህ ብሎ ተናግሯል፦
“አል-ሐፊዝ አቡልቃሲም ኢብኑ አሳኪር እንድህ አሉ፥ የሚታመንበት ሰው አይደለም፥ ኢብኑ ነጃርም እንድህ አሉ፥ ሀድስ ወድዕ በማድረግ ሰውዬው ይታወቃል።”


•እንደዚሁም በተጨማሪ አቡ-መሐመድ ኣል-መቅድስ በሰነዱ ውስጥ ይገኝበታል፥ ይህ ሰው ደግሞ አል-ሐፊዝ  አቡ-ሻማህ አል-መቅዲሲይና ሌሎችም ኦለሞች ሙጀሲማ መሆኑን ገልጸዋል
አዚሉ ዓላማ ረውዶተይኒ
ተራጂሙ ሪጃል!! በሚባል ኪታብ!!

•እንደዚሁም ከኢማሙ-ሻፊዕይ ይዞ አውርቷል ተብሎ የሚጠራው ሰው #አቡ_ሹዓይብ ይባላል።

ይህ ሰው ዒማሙ ሻፊዕ ካለፋ ከሁለት አመት በኋላ የተወለደ ነው፥ ኢማሙ ሻፊዕይ በሐያት ኣለገኘም!!
ምንጭ
📚ታሪኩል-ባግዳድ ተመልከቱ

ማጠቃለያ ነጥብ!!

የዒማሙ ሻፊዕይ አቂዳ ተብሎ በተጠራው ኪታባቸው በሰነዳቸው ውስጥ ሙጀሲሙ አል’መቅዲሲይ፣ አል-ወዷዑ [ዋሾው] ሀካርይ፣ ኢብኑ-ካድሽ፣ ዓሽሻርይ ይገኙበታል፥ ከዕነዚህ ሰዎች የተወራው መቀበል አይቻልም አይበቃም ሐራም ነው።
📚ምንጭ
© ተብዲሉ ዞላሙል-ሙኸየም!! የሙሐዲሱ አል-ከውሰርይን ኪታብ ይመልከቱ!!

#JOIN_US 🍂
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ክፍል ①
🍂
የኢስተዋዕ ማብራሪያ በኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሐንበል ረዲየሏሁ ዓንሁ....!!!
-------------------------------------

ኢማሙ አህመድ በረቢዒል አወል ወር 164 ዓ.ሒ በባግዳድ ተወለዱ፥ 241ዓ.ሒ ዓረፋ ረዲየሏሁ ዓንሁ !!

➦ አንድ ሚሊየን ሐድሶችን በአእምሯቸው መሐፈዝ የቻሉ ታላቅ የኢልም ሙህር ነበሩ። #ሙስነድ አዘጋጅተዋል🙏

ስለ ዒስተዋዕ ትርጉም ማብራሪያ በተጠየቁ ጊዜ እንድህ በማለት መልስ ሰጥተዋል፦
إستوى كما أخبر لاكما يخطر للبشر
“የዒስተዋዕ አንቀፅ ትርጉም አሏሕ ’ራሱን እንደገለፀበት እንጂ በሰው ልጅ ልብ ውል እንደሚልበት አይደለም።”

ምንጭ📚
© አል-ሐፊዙል ሁስንይ ደፍዑ ሹበህ በሚባል ኪታብ ጠቅሰውታል።

#የዒስተዋዕ ትርጉም ለሰው ልጅ ዉል የሚልበት መቀመጥ፣ ከፍ ማለት፣ መውረድና መውጣትን ይመስላል በሚባል መልክ አይደለም፥ አሏሕ ከቦታ ከፍታና መውረድ ሙሉ ጥራት የተገባው ጌታ ነው።

📚 እንደዚሁም ኢዕቲቃዳቱ አህመድ ኢብኑ ሐንበል በሚባል ኪታብ ይህን ንግግር ተጠቅሷል፦
قال الإمام أحمد بن حنبل "والله تعالى لا يلحقه تغير ولا تبدل ولا تلحقه الحدود قبل خلق العرش ولا بعد خلق العرش"
ኢማሙ አህመድ ብኑ ሀንበል እንድህ አሉ፦
«ጥራት የተገባው አሏሕ አርሽን ሳይፈጥር በፊትም ሆነ ከፈጠረም በኃላ መቀያየርም ሆነ መለዋወጥ በአካል መገለፅ አያመችበትም»


ማስጠንቀቂያ!!

ከኢማሙ አህመድ ኢብኑ ሐንበል ረዴየሏሁ ዓንሁ “ አረዱ ዓለል ጀህምያ ሆነም ሪሳላ” የሚባሉ በትክክለኛ ሰነድ ከእነሱ የተገኙና የተፃፋ ኪታቦች አይደሉም።

ይልቁንስ በስማቸው ቀጣፊ የቀጠፈው ኪታቦች ናቸውና እንዳትሸነገል እንዳትሸወዱ።

ለዚህም ሐፊዙ ዘሐብይ ሲየሩ ዓዕላሙ ኑበለዕ 11 ጥራዝ ላይ የተዋሹ መሆናቸውን የኢማሙ አህመድ ኪታቦች አይደሉም ብለዋል።

#JOIN_US🍂
~•~•~•~
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
🌾 ሲሳይን [ሪዝቅን] ከሚጨምሩና ከሚያበዙ ነገራቶች መካከል🌴

ክፍል


🍂
❹►▸◦ አሏሕን ማመስገን፥ አመስጋኝ መሆን [አሹኩር]
وَإِذْ تَأَذَّنَ رَبُّكُمْ لَئِن شَكَرْتُمْ لَأَزِيدَنَّكُمْ ۖ وَلَئِن كَفَرْتُمْ إِنَّ عَذَابِي لَشَدِيدٌ -ابراهيم ٧
ጌታችሁም «ብታመሰግኑ በእርግጥ እጨምርላችኋለሁ ብትክዱም (እቀጣችኋለሁ) ቅጣቴ በእርግጥ ብርቱ ነውና» በማለት ባስታወቀ ጊዜ (አስታውሱ)፡፡
🍂
❺►▸◦ ለጋሽ መሆን፥ መስጠት
وَمَا أَنفَقْتُم مِّن شَيْءٍ فَهُوَ يُخْلِفُهُ ۖ وَهُوَ خَيْرُ الرَّازِقِينَ سبإ ٣٩
«ከማንኛውም ነገር የምትለግሱትን እርሱ ይተካዋል፡፡ እርሱም ከሲሳይ ሰጪዎች ሁሉ በላጭ ነው» በላቸው፡፡
🍂
❻►▸◦ በአሏሕ መንገድ ላይ መሰደድ
۞ وَمَن يُهَاجِرْ فِي سَبِيلِ اللَّهِ يَجِدْ فِي الْأَرْضِ مُرَاغَمًا كَثِيرًا وَسَعَةً ۚ  النساء ١٠٠
በአላህም መንገድ የሚሰደድ ሰው በምድር ውስጥ ብዙ መሰደጃንና ምቾትን ያገኛል፡፡
🍂
❼►▸◦ ጋብቻ ፥ ትዳር...!
وَأَنكِحُوا الْأَيَامَىٰ مِنكُمْ وَالصَّالِحِينَ مِنْ عِبَادِكُمْ وَإِمَائِكُمْ ۚ إِن يَكُونُوا فُقَرَاءَ يُغْنِهِمُ اللَّهُ مِن فَضْلِهِ ۗ وَاللَّهُ وَاسِعٌ عَلِيمٌ النور ٣٢

ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ፡፡ ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን (አጋቡ)፡፡ ድኾች ቢኾኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል፡፡ አላህም ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው፡፡

ይቀጥላል...!

መልካም ሌሊት ተመኘሁላችሁ..🙏

#JOIN_US😎
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
🌾 ሲሳይን [ሪዝቅን] ከሚጨምሩና ከሚያበዙ ነገራቶች መካከል🌴

ክፍል

❽►▸◦ ቤተሰብን ሶላት እንድሰግዱ ማድረግና ማዘዝ...!
وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصْطَبِرْ عَلَيْهَا ۖ لَا نَسْأَلُكَ رِزْقًا ۖ نَّحْنُ نَرْزُقُكَ ۗ وَالْعَاقِبَةُ لِلتَّقْوَىٰ طه ١٣٢
ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፡፡ በእርሷም ላይ ዘውትር፤(ጽና)፡፡ ሲሳይን አንጠይቅህም፡፡ እኛ እንሰጥሃለን፡፡ መልካሚቱ መጨረሻም ለጥንቁቆቹ ናት፡፡
🍂
➈►▸◦ በሸሪዓ ህግ መተዳደርና በእሱም ላይ መፅናት...!
وَلَوْ أَنَّهُمْ أَقَامُوا التَّوْرَاةَ وَالْإِنجِيلَ وَمَا أُنزِلَ إِلَيْهِم مِّن رَّبِّهِمْ لَأَكَلُوا مِن فَوْقِهِمْ وَمِن تَحْتِ أَرْجُلِهِم ۚ مِّنْهُمْ أُمَّةٌ مُّقْتَصِدَةٌ ۖ وَكَثِيرٌ مِّنْهُمْ سَاءَ مَا يَعْمَلُونَ المائدة ٦٦
እነርሱም ተውራትንና ኢንጂልን ከጌታቸውም ወደ እነሱ የተወረደውን መጽሐፍ ባቋቋሙ (በሠሩበት) ኖሮ ከበላያቸውና ከእግሮቻቸው ሥር በተመገቡ ነበር፡፡ ከእነሱ ውስጥ ትክክለኞች ሕዝቦች አልሉ፡፡ ከእነሱም ብዙዎቹ የሚሠሩት ነገር ከፋ!
🍂
⓾►▸◦ ዝምድናን መቀጠል...!
قال رسول الله ﷺ من سره أن يبسط له في رزقه أو ينسأ له في أثره فليصل رحمه - متفق عليه
የአሏሕ መልክተኛ ﷺ እንድህ አሉ፦ «'ርዚቁ እንድሰፋለት የፈለገ ወይም እድሜ እንድገፉ እንድረዝም የፈለገ ዝምድናን ይቀጥል።»
🍂
⓫►▸◦  ለደካሞች መልካምን መዋል..!
قال رسول الله ﷺ هل تنصرون وترزقون إلا بضعفائكم - البخاري
የአሏሕ መልክተኛ ﷺ እንድህ አሉ፦ «የምትታገዙና የምትሰጡ አይደላችሁም በደካሞቻችሁ ቢሆን እንጂ።»
🍂
⓬►▸◦ እውነት መናገርና ነውርን መግለጽ
قال رسول الله ﷺ البيعان بالخيار مالم يتفرقا أو قال حتى يتفرقا فإن صدقا وبينا بورك لهما في بيعهما وإن كتما وكذبا محقت بركة بيعهما - متفق عليه 
የአሏሕ መልክተኛ ﷺ እንድህ አሉ፦ [ሻጭና ገዥ ምርጫ አላቸው እስከ’ልተለያዩ ድረስ እውነት፥ እውነት ከተናገሩና ነውርን ግልጽ ካደረጉ ግብይታቸው በረካ ይኖረዋል፥ ከደበቁና ከዋሹ ደግሞ በረካው ይነሳል።]

ይቀጥላል..!

መልካም ሌሊት ተመኘሁላችሁ..!

#JOIN_US😊
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
🌾 ሲሳይን [ሪዝቅን] ከሚጨምሩና ከሚያበዙ ነገራቶች መካከል🌴

ክፍል

⓭►▸◦ ሀጅና ዑምራን ማብዛት፥ ማድረግ...!
قال رسول الله ﷺ تابعوا بين الحج والعمرة فإنهما ينفيان الفقر والذنب كما ينفي الكير خبث الحديد - النسائي
የአሏሕ መልክተኛ ﷺ እንድህ አሉ፦ ዑምራና ሀጅን አስከታትሉ [አዘውትሩ ] ሁለታቸውም ድህነትንና ወንጀልን ያስወግዳሉ፥ ወናፍ የብረትን ዝቃጭ እንደሚያስወግደው።
🍂
⓮►▸◦ ሰበቦችን ከመፈፀም ጋር በአሏሕ መመካት ተወኩል ማድረግ...!
قال رسول الله ﷺ لو كنتم توكلون على الله حق توكله لرزقتم كما يرزق الطير تغدو خماصا وتروح بطانا - الترمذي
የአሏሕ መልክተኛ ﷺ እንድህ አሉ፦ [እናንተ ትክክለኛ የሆነን መመካት በአሏሕ ብትመኩ ኑሮ በራሪ ወፍን ርዚቅ እንደሚሰጠው ይሰጣችሁ ነበር፥ ጧት በባዶ ሆዷ ትወጣለች ማታ ሆዷን ሞልታ ትመለሳለች።]
🍂
⓯►▸◦ ለእውቀት ፈላጊዎች መስጠት፥ መለገስ...!
كانَ أَخَوانِ على عَهدِ النّبيّ صلى الله عليه وسلم فكَانَ أحَدُهما يَأتي النّبيَّ صَلّى الله عليه وسلم والآخَرُ يَحتَرِفُ – أي يَعمَلُ – فشَكَى المحتَرِفُ أخَاهُ إلى النّبيّ فقَال النبيُّ صلى الله عليه وسلم: "لَعَلَّكَ تُرْزَقُ بِهِ"، قال التّرمِذِيُّ: هَذا حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ.
[ሁለት ወንድማማቾች በነብያችን ﷺ ዘመን ነበሩ፥ አንድኛው ወደ ነብያችን ﷺ እየመጣ ትምህርትን ይቀስም ነበር፥ መንድሙ ደግሞ የሙያ ባለቤት ነውና ስራን በመስራት የተጠመደ ነበረ። ወንድሙም በስራ አያግዘውም ነበርና ወደ ነብያችን ﷺ መጥቶ እንደማያግዘውና በስራ እንደማይረዳው ብሶቱን አዋያቸው‼️
ነብያችንም ﷺ እንድህ ብለው አሉት፦ [ሲሳይን የምታገኘው በሱ ምክንያት ይሆናል።]


ይቀጥላል...!

#JOIN_US
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ሰይዳችን ﷺ ከሞቱ በኋላ ሰዪዱና ቢላል ኢብኑ ረባሕ [ረዲየሏሁ ዓንሁ] መድናን ለቀው በሻም ሐገር ኑሯቸውን ይገፋ ጀመሩ።
🌸
ከእለታት አንድ ቀን ሰዪዱና ቢላል [ረዲየሏሁ ዓንሁ] ሰይዳችንን ﷺ በህልም ያያሉ፥ ከዛም ሰይዳችን ﷺ [ ቢላል ሆይ! በጣም እራቅከን አልናፈቅም ወይ?] አሉት።
🌸
ሰይዱና ቢላልም [ረዲየሏሁ ዓንሁ] በጧት ወደ ወደ መዲና እየከነፈ ሔደ!
🌱
መዲና ላይ እንደደረሰም ሰዪዱና ቢላል ረዲየሏሁ ዓንሁ አዛን ማድረግ ጀመረ ልክ "አሽሀዱ አነ ሙሐመደን ረሱሉሏህ" ላይ እንደ ደረሰ ሰዪዱና ቢላል [ረዲየሏሁ ዓንሁ] አልቻለምና ለቅሶውን ለቀቀው፥ የመድና ሰዎች የሰይዱና ቢላልን [ረዲየሏሁ ዓንሁ] ድምፅ በሰሙ ጊዜ መቋቋም አቃታቸው ከተማዋ በለቅሶ ትርምስ ተዋጠች ...!
🍂
ኢሽተቅናክ ያረሱለሏህ ﷺ
ናፍቀውናል አንቱ የአሏሕ መልክተኛ ሆይ ﷺ በህልም ይታዩን🙏


#JOIN_US 🌺

https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ዛሬ ስለሀገራችን ታላቅ ሙጃሂድ የሀገር ባለዉለታ የአፍሪካ ቀንድ #የሙስሊሞች ኩራት ኢማም አህመድ አልጋዚ ታሪክ በወፍ በረር ቅኝት በቻናላችን ይለቀቃል ይቀላቀላሉን..🙏
🗡 ታላቁ ሙጃሒዱ ኢማሙ አህመድ አል'ጋዚ..! ⚔️

🌀ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል'ጋዚ  ረዲየሏሁ ዓንሁ 🌸

PART ⓵

ዛሬ ስለ ሀገራችን ታላቅ ሙጃሂድ፥ የሀገር ባለዉለታ፥ የአፍሪካ ቀንድ #ሙስሊሞች ኩራት ኢማም አህመድ አልጋዚ ታሪክ በወፍ በረር ቅኝት ጀባ አልናችሁ..🙏

ከብዙ ምዕተ ዓመት ወደ ኋላ የሙስሊም ሱልጣኔቶች ተራ በተራ ተደምስሰዋል። የነሱን የነፃነት ጥያቄ ያነሳ ሁሉ ጥቃት ሲያስተናግድ ቆይቷል።

እጣው የደረሳቸው የመጨረሻው ኢማም #ኢማም_ማህፉዝ ነበሩ። ሙስሊሙ የባህል ወረራ የኢኮኖሚና የስነ ልቦና ጥቃት ሰለባ ሆኗል። ሁለገብ ጥቃት በየአቅጣጫው ሀይሏል።

በዚህ ሁሉ ጭንቅ መሀል #በ1506 አህመድ ኢብኑ ኢብራሂም ይህቺን ምድር ተቀላቀለ። የተወለደው ሀረር አቅራቢያ " #ሁበት" በተባለ ስፍራ ልዩ ስሙ " #ዘእካ" በተባለ መንደር ነው

ኢማም ማህፉዝ ሲገደሉ ኢማሙ አህመድ ገና የ 10 አመት ታዳጊ ነበር። የልጅነት ጊዜውን በሁበት ከተማ አሳለፈ። አባቱ ኢብራሂም ከባርነት ቀንበር ነፃ ባወጡት አዶሊ በተባለ ሰው ጥበቃና ቁጥጥር ስር አደገ። አዶሊ በአህመድ ስብእና ላይ ተፅእኖ ፈጣሪ ነበሩ። አህመድ በወጣትነታቸው በተደጋጋሚ በጥቃት የተዳከመቸውን አዳልን በማረጋጋትና ሙሐረማትን [ክልክላትን] በመዋጋት ከጋራድ አቡን ጋር ተሰለፈ።
በገራድ አቡን ጦር ውስጥም ፈረሰኛ ሆኖ ትግሉን ጀመረ። በኢማሙ አህመድ አርቆ አሳቢነትና ቆራጥነት የተደመመው ገራድ አቡን እጅግ አቀረበው። በወቅቱ የነበረው የሱልጣን አቡበከር አስተዳደር የሙስሊሙን ባህል በመጠበቁ ረገድ ተዳከመ። ኢስላማዊ ያልሆኑ ባእድ ባህሎች ወደ ሙስሊሙ በስፋት መቀላቀል ጀመሩ። ገራድ አቡን ለሶስት አመታት በአካባቢው የተከሰተውን መጥፎ ገፅታ ለመለወጥ በመልካም ማዘዝና ከመጥፎ መከልከል ጀመረ። ቁማርን አገደ፥ ሽፍቶችን በቁጥጥር ስር አዋለ፥ የሙዚቃ መሳሪያዎችን ከለከለ፥ ኡለሞችንና መሻይኮችን አስጠጋ።
🗡
ሱልጣን አቡበከር የአያቶቹን ዝና በመጠቀም የአዳልን ዋና ከተማ ከደካር ወደ ሀረር አዞረ። በዚህም ከነ ገራድ አቡን ጋር ግጭት ውስጥ ገባ። የገራድን አካሄድ ፈፅሞ አልወደደም። ሱልጣን አቡበከር ገራድን በሽፍቶች አስገደለው ። ማክሰኞ 7 ሻእባን መግሪብ ላይ በ931 ነበር። ገራድ አቡን ይቆጣጠር የነበረውን አካባቢ በግዛቱ ጨመረ። ሽፍቶችም ዳግም ተመለሱ። አስካሪ መጠጥ በብዛት ተንሰራፋ፥ ፍትህ ጠፋ፥ ቀመኛ በዛ። ጉልበት ያለው ጉልበት የሌለውን ይጨቁን ጀመር። ሱልጣን አቡበከርን ታላላቅ ሰዎች የቁርአን መምህራንና ኡለሞች ተግባሩን በማውገዝ ገሰፁት።

ወዳጁ ገራድ አቡን የተገደለበት ኢማሙ አህመድ የሱልጣን አቡበከር ጦር ከቁርአንና ከሱና መንገድ መውጣቱ በጣም አበሳጨው። የአላህን ህግ ባለ መጠበቁ ተናደደ። ወደ ትውልድ መንደሩ ሁበት ተጓዘ። ጦር ያደራጅም ጀመር። ከመቶ በላይ ፈረሰኛ ጦር አሰባሰበ። ለሙስሊሞች ነፃነት ሲታገሉ የተሰውትን የኢማም መህፋዝን ልጅ ባቲ ድል ወንበሯ የተሰኘችዋን ልጃገረድ አገባ።  "ኢማም" የሚል የማእረግ ስያሜ ተሰጠው .......!

ኢንሻ አሏህ ይቀጥላል...!

🈴JOIN
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
🗡ታላቁ ሙጃሒድ ኢማሙ አህመድ አል'ጋዚ⚔️

🌀ኢማም አህመድ ኢብን ኢብራሂም አል'ጋዚ🌸

PART ➁

#ፋኑኤል የተሰኘ ክርስቲያን የጦር መሪ ከደዋሮ አቅጣጫ ወደ ሁበት ከተማ ሠራዊቱን ይዞ ዘመተ። ወታደሮቹ ሙስሊሙን አጠቁ፥ ሴት ወንዶችን ያለ ርህራሄ ገደሉ፥ ሀብት ንብረት ዘረፉ።

"የሚቋቋመን ማን አለ?! ጀግና ነኝ የሚል ሙስሊም ይውጣ" በሚል ስሜት ሙስሊም ሕጻናትንና ሴቶችን ማርከው ይዘው ሄዱ፥ በአቅራቢያው ለነበረው ኢማም #አሕመድ ወሬው ደረሰ፥ የራሱን ሠራዊት ይዞ የፋኑኤልን ጦር ተከተለ። "ዓቂም" (አማሬሳ) የሚል ስያሜ በተሰጠው ወንዝ ጋር ተገናኙ።

በመካከላቸው ከፍተኛ ውጊያ ተደረገ። ኢማሙ መሀል ገብቶ ሠይፉን ከአፎቱ መዞ ከጠላት ጦር ጋር ገጠመ። ሌሎች በግራ አቅጣጫ የፋኑኤልን ጦር አጠቁ። ከራሱ ላይ የብረት መከላከያ ባጠለቀው ፋኑኤል የተመራው ጦር በቀኝ ክንፍ ባሉ ሙስሊሞች ላይ ጥቃት ከፈተ።

ኢማሙ አሕመድ የመጀመሪያው የሆነውን ጂሐድ በድል አድራጊነት ተወጣ። ከመስቀላዊያን የአፄዎች የጠላት ወገን 60 ፈረሰኞችና በርካታ እግረኞች ተማረኩ። በርካቶችም ተገደሉ። የጦር መሣሪያም ማረኩ። የተማረኩትን ሙስሊሞች አስለቅቀው በድል አድራጊነት ወደ ዚፋህ ከተማ ገቡ። የኢማሙ ገድልና ዝና ናኘ፥ ተሰራጨ።

በአቅራቢያው የነበረው ሱልጣን አቡበክር ከአካባቢው ሸሸ። ኢማሙ አህመድ ባገኘው ድልና ምርኮ ተናደደ።
ሱልጣን አቡበከርና ኢማሙ አህመድ ጦርነት ገጠሙ፥ ሱልጣኑ ተሸንፎ ሸሸ።

ኢማሙ ወደ ሐረር ከተማ ገባ። ሱልጣኑ በርካታ ሠራዊት መልምሎ ኢማሙ አህመድን ለማጥቃት ተመመ። ኢማሙ ደግሞ ሐረርን ለቅቆ ወደ ሁበት ሸሸ። የሱልጣኑ ጦር ተከተለው። ኢማሙ በሁበት ተራራ ላይ ወጣ። የሱልጣኑ ጦር ተራራውን ከበበ። ለሁለት ሳምንታት አላንቀሳቅስ አለ። በዚህ የተሰላቸው የኢማሙ ጦር በማታ ከተራራው ወረዶ ጦርነት ገጠሙ። ከኢማሙ አህመድ ጦር ውስጥ አሚር የነበረው ዑመረዲን ተገደለ። ኢማሙና ተከታዮቹም ወደየቀያቸው አቀኑ።

በኢማም አሕመድና በሱልጣን አቡበክር መካከል በዑለሞች አማካኝነት ስምምነት እንዲፈጠር ተደረገ። በስምምነቱ መሠረት ኢማሙና ሠራዊቱ የሱልጣኑን ጦር እንዲቀላቀሉ ተደረገ። ሱልጣኑም ሸሪዓን ሊጠብቅ ተስማሙ። ሆኖም ስምምነቱ ከጥቂት ቀናት በላይ አልዘለቀም።

ሱልጣን አቡበክር ኢማም አሕመድን ለመግደል ማሤር ጀመረ። ስምምነቱ በሱልጣኑ ተጣሰ። ሱልጣኑ ኢማሙ አህመድን ሊገድል በመፈለግ ያለበትን ለማወቅ በየስፍራው ሰላዮችን ላከ። ዛዕካ መኖሩን ሰምቶ ጦር ላከበት። የኢማሙን ቤት አቃጠሉ። ንብረቱንም ዘረፉ። ሆኖም ኢማሙ አህመድን ሊያገኙት አልቻሉም።
|
JOIN AND SHARE
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ሒጅራ🌸

ከመካ ጀምሮ እስከ መድነቱል-ሙነወራ ብዙ ክስተቶች፥ ታሪኮች፥ ገጠመኞችንና ትምህርቶችን አቅፋ ይዛለች፥ የነብያችንም ﷺ ጉዞ ባጢል ሰዎችን ለመዋጋት ፈርተው አይደለም፥ ይልቁንስ የአሏሕን ትዕዛዝ ለመፈፀምና ለመተግበር ነበር።

✍️ ሙሉውን ለማገኘት .....! ወደ ቻናላችን ጎራ ይበሉ....!
🌸ክፍል አንድ🌸

ሒጅራ ማለት ነብያችን ﷺ ከሚወዷትና ከተወለዱባት ሀገር ተነስተው ወደ መድቱል-ሙነወራ ያደረጉት ጉዞ ነው። ይህ ጉዞ ትልቅ ትምህርትን አቅፎ ይዟል።

رَوى البُخاريُّ في الصّحيحِ عنِ ابنِ عبّاسٍ رضيَ الله عنهُما قال " بُعِثَ رسولُ الله صلّى اللهُ عليه وسلّم لأربَعينَ سنةً فَمَكثَ  بمكّةَ ثلاثَ عشْرةَ سنة يُوحَى إليه، ثمَّ أمِرَ بالهجرةِ فهاجَرَ عشْرَ سِنين وماتَ وهوَ ابنُ ثلاثٍ وستّينَ سنة " صلّى الله عليه وسلّم.

ኢማሙል’ቡኻሪ በሶሒሓቸው ከዓብዱሏሕ ኢብኑ ዓባስ በዘገቡት ሀድስ አብዱሏሕ ኢብኑ ዓባስ [ረዲየሏሁ ዓንሁማ] እንድህ አሉ፦ [በ40 ዓመታቸው መለኮታዊ ረዕይ ወረደላቸው ከዛም 13 ዓመት በመካ ውስጥ ወህይ [ረዕይ] እየወረደላቸው ቆዩ፥ ከዛም ወደ መድና ጉዞ እንዲያረጉ ታዘዙና ከ10 ቆይታ በኋላ በ63 ዓመታቸው አለፋ።]

إِلَّا تَنصُرُوهُ فَقَدْ نَصَرَهُ اللَّهُ إِذْ أَخْرَجَهُ الَّذِينَ كَفَرُوا ثَانِيَ اثْنَيْنِ إِذْ هُمَا فِي الْغَارِ إِذْ يَقُولُ لِصَاحِبِهِ لَا تَحْزَنْ إِنَّ اللَّهَ مَعَنَا ۖ فَأَنزَلَ اللَّهُ سَكِينَتَهُ عَلَيْهِ وَأَيَّدَهُ بِجُنُودٍ لَّمْ تَرَوْهَا وَجَعَلَ كَلِمَةَ الَّذِينَ كَفَرُوا السُّفْلَىٰ ۗ وَكَلِمَةُ اللَّهِ هِيَ الْعُلْيَا ۗ وَاللَّهُ عَزِيزٌ حَكِيمٌ

[(ነቢዩን) ባትረዱት እነዚያ የካዱት ሕዝቦች የሁለት (ሰዎች) ሁለተኛ ኾኖ (ከመካ) ባወጡት ጊዜ አላህ በእርግጥ ረድቶታል፡፡ ሁለቱም በዋሻው ሳሉ ለጓደኛው አትዘን አላህ ከእኛ ጋር ነውና ባለ ጊዜ አላህም መረጋጋትን በእርሱ ላይ አወረደ፡፡ ባላያችኋቸውም ሰራዊት አበረታው፡፡ የእነዚያንም የካዱትን ሰዎች ቃል ዝቅተኛ አደረገ፡፡ የአላህም ቃል ለእርሷ ከፍተኛ ናት፡፡ አላህም አሸናፊ ጥበበኛ ነው፡፡]
🍂
ከመካ ጀምሮ እስከ መድነቱል-ሙነወራ ብዙ ክስተቶች፣ ታሪኮች፥ ገጠመኞችንና ትምህርቶችን አቅፋ ይዛለች፥ የነብያችንም ﷺ ጉዞ ባጢል ሰዎችን ለመዋጋት ፈርተው አይደለም፥ ይልቁንስ የአሏሕን ትዕዛዝ ለመፈፀምና ለመተግበር ነበር።

በራዕ [ረዲየሏሁ ዐንሁ] እንድህ ይላሉ፦
{ ወሏሒ እኛ ’ኮ ጦርነቱ በጣም የበረታ ጊዜ በነብያችን ﷺ እንጠለል ነበር።}

📚 ምንጭ
© ሙስሊም ዘግበውታል
🍂
🌀ኢማሙ ኣን’ነወውይ [ረዲየሏሁ ዐንሁ] እንድህ ይላሉ፦ {ይህ ሐድስ የነብያችን ﷺ ጀግንነት፥ በአሏሕ ያላቸውን የቂንነትና ተወኩልነት ያመላክታል።}

⚠️ የነብያችንም ﷺ ከመካ ወደ መድና ያደረጉት ጉዞ እርጋታን፣ እረፍትን፣ ዱንያን ፈልገውም  አልነበረም።
🍂
♻️የኛ ነብይ ﷺ ቲርሚዝይ በዘገቡት ሀድስ እንድህ ያሉ ናቸው ፦ [ እኔ በዱንያ ላይ ከአንድት ዛፍ ጥላ ስር እንዳረፈና ትቷት እንዴ ሄደ ተጓዥ ነኝ።]
🍂
♻️ይህ ጉዞ ትልቅን አላማ ያዘለና የቋጠረ ነበር፥ የሙስሊሞችን ወንድማማችነት ለማጠናገር፣ የእስልምና ባድራ ከፍ ለማድረግና እስላማዊ አስተዳደር እንድቋቋም ነበር።

🌀ነብያችን ﷺ ከመካ ወደ መድና የተጓዙት ከሰዎች ዘንድ በስልጣንንና በደረጃን መታወቅንና የበላይ መሆንን ፈልገው አልነበረም። ለዚህማ የቁረይሽ ታላላቅ መሪዎች እና ኋብታሞች እንድህ ብለው ጥያቄ አቅርበውላቸው ነበር።
«በዚህ በምታደርገው ጥሪ ሀብታም መሆን ፈልገህ ከሆነ ’ኛ ከገንዘባችን ሰብስበን ከ’ኛ የበለጠ ሀብታም እናደርገሀለን፣ ስልጣንን ፈልገህ ከሆነ አንተን በ’ኛ መሪያችን አድርገን እንሾመሃለን !! ይሔን ጥሪህ ተው ለትዕዛዝህ ታዛዥ እንሆናለን።»

🌀ይሔን እንዳደርስ የተላከው መልክተኛ አጎታቼው አቡ'ጧሊብ ነበርና እንድህ ብለው መለሱለት ነብያችን ﷺ ፦
«አንተ አጎቴ ሆይ እንኳን ይሔን ቀላሉን ነገር ቀርቶ ሰማይን በቀኝ እጄ ጨረቃን ደግሞ በእግራ እጄ ቢያኖሩልኝም ከዚህ ጥሪዬ አሏሕ ግልፅ እስኪሚያደርገው ወይም ስሞት በቀር አልተውም።»

⚠️ #ይቀጥላል...!
||
#JOIN_US 🌸
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
🌸ክፍል ሁለት🌸

የሐጅ ወቅት በደረሰ ጊዜ የተለያዩ የዐረብ ጎሳዎች ይሰባሰባሉ፥ አንድ ቀን ነብዩና ሙሀመድ ﷺ ከመድና ከመጡ ሰዎች ጋር ተገናኝተው ወደ እስልምና ጥሪ አቀረቡላቸው። እነርሱም ጥሪውን ተቀብለው ወደ እስልምና ገቡ፥ እንድህም አሉ “እኛ ወደ ሀገራችን መድና ተመልሰን ሰዎችን ወደ እስልምና እንጠራለን።” በማለት ለነብያችን ﷺ ቃል ገቡ።
🍂
ወደ መድና ሀገራቸው ከተመለሱ በኋላ የመድና ሰዎችን ወደ እስልምና መጣራት ጀመሩ፥ ከእነርሱም ከመድና ነዋሪዎች ከፊሎቹ ወደ እስልምና እምነት ገቡ። እነርሱም አንሷሮች {አጋዦች} ይባላሉ
🍂
♻️ የቀጣዩ ዓመት የሐጅ ወቅት ሲደርስ ከአንሷር አስራሁለት ሰዎች መጡና ለነብያችን ﷺ ቃልኪዳን {ቃለመሐላን} ፈፀሙ።  [ቃልኪዳኑም ፦ ከአሏሕ ውጭ ሌላን ጉኡዝ ላያመልኩ፥ የሰውን ንብረት ላይሰርቁ፥ ዝሙትን ላይፈፅሙ፥ ልጆቻቸውን ላይገድሉ፥ ቅጥፈትንና ውሸትን ላይቀርቡ ነበር፤ ሲመለሱም ከእነርሱ ጋር ሙስዓብ ኢብኑ ዑመይርን [ረድሏሁ ዓንሁ] የእስልምና እውቀትን እንዳስተምራቸው ላኩት፥ እስልምና መድና ውስጥ በየቤቱ ገባ፥ አንኳኳ።
🍂
🌀 በቀጣይ አመት የሐጅ ወቅት በደረሰ ጊዜ ወደ ሰባ [70] የሚደርሱ አንሷሮች ወደ ነብያችን ﷺ መጡና ቃል መሐላን ፈፀሙ።
🍂
♻️ የሒጅራ ትዕዛዙ በመጣ ጊዜ..!!
የመካ ቁረይሾችም ለነብያችን ﷺ ቃልኪዳን መፈፀማቸውን እና ሶሀባዎች ወደ መድና ጉዞ ለማድረግ መዘጋጀታቸውን አወቁ።

⚠️ በዚህን ጊዜ ቁረይሾች ነገሩ የከፋ ይሆናል ብለው ፈሩና ተደናገጡ፥ የፈሩበትም ምክንያት ሙሐመድ ﷺ ሀይል ካደረገ ስልጣናችን ይወገዳል፣ ክብራችን ይገፈፋል፣ በመድና አድርገን ወደ ሻም የሚያዳርሰን የንግድ መንገድም ይቋረጣል ብለው ነበር።

ቁረይሾችም ዳረ'ነድዋህ ከሚባል ቤት ተሰባስበው ተንኮል፣ ሴራና ደባን መጠንሰስ ጀመሩ፥ የተሰባሰቡት ቀንም የውመ’ዙህማህ በመባል ይጠራል።

በዚህም ተንኮል ጥንሰሳ ጊዜም ዒብሊስ [የአሏሕ እርግማን ይውረድበትና] የሽማግሌ ቅርፅ በመላበስ ከነጅድ እንደመጣ ሁኖ ከበሩ ላይ ቆመ በዚህን ጊዜ ከበሩ ላይ የቆመው ማነው በማለት ጠይቀው ምንነቱን ከነገራቸው በኋላ ትልቅ ሽማግሌ ነው በማለት በአማካሪነትና አስታራቂነት አቀረቡት፥ ከዛም የተነለያዩ ሀሳቦች ተሰነዘሩ በዚህ ጊዜ ኢብሊስ [ነዐለቱሏሂ ዐለይሒ] ሐሳባቸውን ውድቅ አደረገው፣  መጨረሻ ላይም ከተለያዩ የዐረብ ጎሳዎች ወጣቶችን በመሰብሰብ በአንዴዬ መትተው እንድገደል ወሰኑ፥ ኢብሊስም  [ነዐለቱሏሒ ] ጥሩ ሀሳብ ነው ብሎ ተቀበለ፥ ተስማማ።

⚠️ #ይቀጥላል..!
||
#JOIN_US 🌸
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ሸይክ ሐጅ ኑራድስ ወሎ-መርሳ [ረሒመሁሏሁ]
🌀
🗣 ስለሙጀሲማ ምን አሉ?
👂 አብረን እናዳምጥ


⚠️ ሙጀሲማዎችን ተከትሎ መስገድ አይበቃም ‼️

JOIN
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
2025/07/01 20:02:14
Back to Top
HTML Embed Code: