Telegram Web Link
የተዋበ ስነምግባር ❷

አቡ'ሁረይረተ እንድህ አሉ፦ ነብዩ ﷺ ምግብን አነውረው አያውቁም። ካሰኛቸው ይበሉታል፥ ካልፈለጉት ይተውታል።

🍃ጁማዐቱኩም ሙባረክ

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
◈ኢማሙ አ'ሻፊዕይ ረዲየሏሁ ዐንሁ ከዚህ ዐለም በሞት ከተለዩ በኋላ አንድ ተማሪያቸው በህልም አያቸውና እንድህ በማለት ጠየቃቸው፦“አሏሕ እንዴት አደረገዎት ኢማማችን ሆይ?”

«በአሏሕ እምላለሁ አሏሕ ማረኝ፥ አዘነልኝ እንደሙሽራም ተደርጌ ወደ ጀነትም ተሸኘሁ።» አሉት

ተማሪውም፦ “በምንድን ነው ይሄን እድል ሊያገኙ የቻሉት ኢማማችን ሆይ?” በማለት ጠየቃቸው

“አር'ሪሳለ በተሰኘው ኪታቤ መግቢያ ላይ በፃፍኩት ፅሁፍ ነው” አሉት

ተማሪውም ወዳው ከእንቅልፋ ባነነ፥ ከህልም አለምም ነቃና ኪታቡን ፈልጎ ከፈተና መግቢያው ላይ ይሄን አገኘ።

[አሏሑመ'ሶሊ ዐላ ሙሃመድ ወዐላ አሊ ሙሃመድ ኩሉማ ዘከረከ ዛኪሩን ወጕፈለ ዐን ዚክሪከል'ጓፊሉን]

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ለኢኽዋኖች መንጋ

ብቁ እኔ ነኝ ብለህ መጅሊሱን ቀምተህ
ዛሬስ አቋምህን እርግፍ አርገህ ትተህ
ሰወችን በስሜት በጥመት አርክተህ
             መውሊድን
ቢዳአ ነው እያልክ ስንት እዳላወራህ
ሙሽሪክ ናቸው እያልክ ስንት እዳላዘራህ
ሀሰናት መሆኑን ዛሬ ማን አቀራህ?
                አጅብ
ምን አይነት ንግድ ነው ትርፍ የሌለው ልፋት
በሰለፍያ ስም ሰለፍያን ማጥፋት
በሱፍዬች ማሊያ ኹራፋት ማሥፋፋት
                 ተውጂ
በማስመሰል ጥበብ በሂክማ መደበቅ
ቢዳዓና ሱና ሳይለዩ መድረቅረቅ
አስመስሎ መኖር የትም አያደርስም
ካላከበራችሁ ብለንም አንከስም
             ሸህ ኢብራሂም ቱፋ
የምን መውተርተር ነው ልክ እንደ ሰካራም
ሰው ስታጭበረብር አላህን አትፈራም
መለየት አታቅም ሀላልና ሀራም

መውሊድ ቢዳዓ ነው ብለህ ተናግረሀል
ባቋምህ ፅና እንጂ ምን ይመልሰሀል
           ሸህ ኢብራሂም ቱፋ
ማን ነው ያስተማረህ አስመስሎ መኖር
ሀቅን እያጠፉ ወንበር ላይ መዘመር
           ኢኽዋኖች
ብትመለሱ እንጂ እኔ ምመክራችሁ
እኔስ መቸ ጠፋኝ መሪው አባታችሁ
        ሰይድ ቁጥቡ
ግብፅ ነው መነሻው እውቀት ያላተተ
መቶ አመት ያልሞላው ከተመሰረተ
ውሸትና ቅጥፈት በደንብ የተጋተ
መረጃ የሌለው የተርበተበተ
             ነው
ዲንጋ ዳቦ ነው ባይ ሀቅ የማይረዳ
የተፈላፈለ ኢስላምን ሊጎዳ

እሱ ነው አባትህ አለም ሁሉ ያቃል
ለአሻኢርያ  መቸ ይደበቃል
ማን ያስተውልሀል መች ትታመናለህ
አምና ሀራም ነው አልክ አሁን ትፈቅዳለህ
ሰለፍይ ስታገኝ እሱን ትመስላለህ
ከዚያ ሀዳድ ስታይ ከሱ አለሁ ትላለህ

አንተን አስታውሸ ስንኝ መፃፌ
አዝናለሁ በራሴ ብዕር ማንከርፈፌ

ግን ደግሞ የዋሆች ያልተጠነቀቁ
የሚከታተሉህ ጉዲህን ሳያውቁ
በአንተ ፊክር ገብተው የተጨማለቁ
እድጠነቀቁ
ባለማወቅ ዘመን ወዳንተ የመጡ
ዛሬ እስኪ ይወቁህ ካንተ ጋ እሚሮጡ
ለነርሱ ነው እኔ የምለቀልቀው
የነ ጃክን ሴራ ሁሉም ሰው እንዲያውቀው

የሙሂቡን ግጥም
አብረን እናጣጥም

Join ሼር ሼር Join
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
ረሱላችንን ስታወድሱ ለምን ድቢ ትመታላችሁ ?
ወዲያ ወዲህ መወዛወዙንስ ማን ፈቀደው? ብሎ ለጠየቀን!
✦✦✦

መንዙማ እያሉ ድቤ መምታትና ወዲያ ወዲህ መወዛወዝን የፈቀዱት ራሳቸው ነብዩ ናቸውﷺ።አዎ! በጭፍን ከመቃወምህ በፊት ተከታዩን ሐዲስ ልብ ብለህ አንብብ!

1. ኢማም አሕመድ ሙስነዳቸው ላይ፣ኢብኑ ሒባን ሶሒሓቸው ላይ አነስ ኢብኑ ማሊክን ጠቅሰው እንዲህ ይላሉ።
كانت الحبشة يزفنون بين يدي رسول الله ويرقصون يقولون محمد عبد صالح.
"ሐበሻዊያን ከአላህ መልእክተኛ ፊት ለፊት ሆነው እየተወዛወዙ
"ሙሐመዱን ዓብዱን ሷሊሕ" ሙሐመድ ደጉ ሰው በማለት ያዜሙ ነበር።

2. ታላቁ የሐዲስ ሊቅ ኢማሙ ነሳኢይ "ሱነኑል ኩብራ" ላይ በአቢ ሰለማ በኩል የተላለፈውን ሐዲስ እናታችን አዒሻ እንዲህ ማለታቸውን በሶሒሕ ዘገባ አስፍረዋል።
دخل الحبشة يلعبون فقال لي ياحميراء أتحبين أن تنظري إليهم ؟فقلت نعم ،فقام بالباب وجئته فوضعت ذقني على عاتقه فأسندت وجهي إلى خده ، قالت ومن قولهم يومئذ "أبا القاسم طيبا"
ሐበሾች እየተጫወቱ ገቡ፣ነብዩም "ሑመይራእ ሆይ ልታያቸው ትፈልጊያለሽን" አሉኝ።እኔም አዎን አልኳቸው።በሩ ላይ ቆሙ፤እኔም አገጬን አንገታቸው ላይ፣ፊቴን ወደ ጉንጫቸው አስደግፌ መመልከት ጀመርኩ። ያኔ [ሐበሾቹ]ይሉት የነበረው[መወድስ] "አበል ቃሲሚ ጦይይባ" "ደጉ የቃሲም አባት" የሚለውን ነበር" አለች።

3. ኢብኑ ማጃህ ሱነናቸው ላይ፣ጦበራኒ ሙዕጀሙ‐ሶጊር በተሰኘ ኪታባቸው ላይ አነስ ኢብኑ ማሊክን ጠቅሰው እንዲህ ብለዋል።
ነብዩﷺ መዲና ላይ በሆነ ቦታ ሲያልፉ የተመለከቷቸው የመዲና እንስቶች ድቢያቸውን እየደለቁ በሚያምር ዜማ
نحن جَوار من بني النجاري
ياحبذا محمدٌ من جار
ነሕኑ ጀዋሪን ሚን በኒ ነጅጃሪ፣
ያ ሐበዛ ሙሐመዱን ሚን ጃሪ።

"እኛ ከበኒ ነጃር ጎሳ የሆንን እንስቶች ነን፣የሙሐመድ ጎረቤት መሆን ምንኛ መታደል ነው?!"በማለት ማንጎራጉሩ ያዙ።ይህን የተመለከቱት ነብዩም ﷺ በምላሹ
الله يعلم إن لأحبكن
"አሏህ ያውቃል እኔም እወዳችኋለሁ።" አሉ

✦✦✦
ይሄው ነው ወንድሜ! ነብዩ አይተው ያፀደቁትን ነገር እንዴት አንተ ሥላልተመቸህ ብቻ ልትቃወመው ውስጥህ ፈለገ? ነብዩ ይሁን ያሉትን አንተ አይሆንም የምትለው አንተ ማነህና? የተቃወምከው ባለማወቅ ከሆነ ያውና ከዚህ ጀምሮ እወቀው።ሐዲሱን እያወቅክ ከሆነ ግን በቀጥታ የምትቃወመው ረሱልን ይሆናል። ይሄ ደግሞ አደጋ ላይ ይጥልሃል።

በርግጥ አደብና ለዛ ባለው መልኩ አድርጉት ብሎ መምከርን ማንም አልከለከለህም። ዘለህ ሐራም ነው፣ገለመሌ ነው፣ሽርክ ነው የማለት አቅም እንደሌለህ ግን ማወቅ ይኖርብሃል።ረሱል ከፈቀዱ አበቃ!

ለምሳሌ ይሄ የረቢዕ መቀበያ የዒሽቅ ፕሮግራም ስርአት ያለውና ውብ ነው ማሻአላህ
الصلاة والسلام عليك ياسيدي وياسندي يارسول الله يا علم الهدى

#copy ✍️በኡስታዝ ሙሃመድ ዐረብ
📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
እኝህን ድንቅ ሐበሻዊ ሸይኽ ለመረዳት በቅድሚያ...
✦✦✦
✺ቢያንስ ቢያንስ በትንሹ...

➢ለመከራከር ሳይሆን ለማወቅ አእምሮን ዝግ ከማድረግ ይልቅ ዝግጁ ማድረግን ይጠይቃል።

➢እኔ ብቻ አውቃለሁ፣ እኔ ብቻ ትክክል የሚል የጀህልን ድሪቶ አውልቆ መጣል ያሻል።

ቲፎዞ ከሚሉት ከንቱ በሽታ መላቀቅ ያስፈልጋል። [በተለይ ይሄ ሊሰመርበት ይገባል።ምክንያቱም ዲነል'ኢስላም
ከነብዩ አደም እስከ የውመል ቂያማ አሸናፊነቱን ጠብቆ የሚዘልቀው በማስረጃና በማስረጃ ብቻ እንጂ በቲፎዞነት አይደለም። ቲፎዞነት ብቻውን በውጭ ሲታይ ግዙፍ የሚመስል ነገር ግን ግልብና ዘላቂነት የሌለው የገለባ ክምር ነው።]


➢ሰው ምን ይለኛል ከሚል እርባና ቢስ ምክንያት ለመውጣት የሚያስችል የሞራል ልእልና ያስፈልጋል።

⭕️[ይህች ነጥብ👆መንጋው በፈጠረው ቅጥፈት እንደ ገበታ ውኃ የሚዋልሉ ሰዎች ስላሉ ጥሩ ጥቆማ ትመስለኛለች😁]

✺ከፍ ሲል ደግሞ!

እኚህን ክንደ ብርቱ ሸይኽ ለመረዳት አራቱን መዝሃብ አብጠርጥሮ መረዳትን፣ ኩቱበ ሲታን እና አሉ የተባሉ የሐዲስ ኪታቦችን እስከ ሰነዳቸው መሸምደድን፣ ከባባድ የሉጛ[ወሳኝ የአረብኛ ቋንቋ] ኪታቦች መሐፈዝን፣ የሙጅተሂድነትን መስፈርት ማሟላትን እና ሌሎች ወሳኝ መመሪያዎችን ጥንቅቅ አድርጎ ማወቅን ይጠይቃል!

ሸይኽ ዓብዱሏህ አንድ ሸይኽ ነበሩ፣ እንደ ማንኛውም ተራ ሰው ናቸው ከሚል አባዜ ካልወጣህ ፈፅሞ ልትረዳቸው አትችልም።

📍 ወዳጄ! ምንም ማጋነን ሳያስፈልገው ሰውየው በጣም ከባድ ሸይኽ ናቸው!

⭕️በእርግጥ ይሄን ስል ፊታቸው በንዴት የሚቀላ፣ አይናቸው በብስጭት ደም የሚሞላ ኮስማናዎች አይጠፉም ይሆናል።😄

ስማቸውን ደጋግመን የምናነሳው ግን በአለም ዙሪያ ተሰራጭቶ የሙስሊሞችን ክብር አስጠብቃለሁ በሚል የሙስሊሞችን አንገት ላስዳፋውና ሙስሊሞችን ከጀርባ በጠላቶች እያስመታ ለሚገኘው መንጋ በጥልቅ ዒልማቸው ከባድ የራስ ምታት በመሆናቸውና ክብርም ስለሚገባቸው ጭምር ነው!!

በጣም የሚገርመው ኢትዮጵያዊ በመሆናቸውም "እንዴት አንድ የሀበሻ ሰው እኛ አረቦችን ይበልጠናል" በሚል በቅናት የሚነዱ አንዳንድ የውጭ ሰዎች ነበሩ፣ አሁንም አሉ። ነጂና!

አዎ! ለሐበሻ መሻይኾቻችን የሚገባቸውን ክብር ልንሰጣቸው ይገባል!
ምክንያቱም ክብሩ ለኛ ነውና!

✦✦✦
رحمكم الله سيدي مولاي! አል‐ፋቲሐ

#copy

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
👍1
ርዕስ የቲም አይደለንም

ግጠም ሲለኝ ደርሶ ሰአት አልጠብቅም
እናንተን ለመምታት እውቀት ባላረቅም
መረጃ የላችሁ የጃሂል ጥርቅም
ዝቅ ብለህ ቅራ ካላወክ አታቅም

እንደ ሱፍይ የለም ለሀቅ የሚታመን
ለድኑ የቆሙ ባለንበት ዘመን
ቅረብና እያቸው እንድንተማመን
              ጃል
ይመልሱላሀል ጠይቅ ተጠግተህ
ፊትና ማራገቡን ማጭበርበሩን ትተህ
ውሸት አታሰራጭ ፌስቡክ ላይ ተኝተህ
የጥመት ቀስት ነሁ የዘመኑ አንበሳ
ኢኽዋን ያቃዠዋል ስማቸው ሲነሳ
     ሸህ አቡበክር ሰለይማን   
መረጃ ቢነግሩት ላኪን አይረዳም
ንፁህ ከሀይቅ እንጂ ከኩሬ አይቀዳም
       ሙሸቢሁ ሁላ       
እረቢዕ ሲደርስ አትነጫነጩ
መረጃ አልባ ተረት ሁሌ አታሰራጩ
ኢብሊስ ጋር ሂዱና ፀጉር ተነ ጫጩ
              እና ለዚ
ስወዱም ስጠሉም ይኑራችሁ ሚዛን
የነብዩ መውሊድ ቢሸጥ እንገዛን
ቀነስነው ስትሉ የበለጠ በዛን
              ሀየ ሀየ
እርግጥ ከናንተ ጋር ይበዛል ውዳቂው
አጨብ ጫቢ ሁላ የገንዘብ ደማቂው
የሷለሆች መንገድ አሏህ ነው ጠባቂው
            ብትለፉም
ፊትና ለመቀስቀስ ምንም ብትለፉም
ውሸትን ቅጥፈትን ብታቀላጥፉም
ከሚዲያ ጩኸት ከፌስቡክ አታልፉም
             ሀሀሀሀሀሀ
ዊላዳው አብቧል ፈፅሞ አልተነካም
ተስፋ ቁረጡ እንጂ ፊትናው አልተሳካም
ሁሌ የሚውጥ ሰው የጥመትን ክኒን
በርዘንጅ ሲሰማ ይሆናል መጃኒን
           ሀበሻ
የሊቃውንት ሀገር የውቀት መናገሻ
ዳሩል ሒጅረተይኒ ነችና ሀበሻ
የነዚያ ሶሀቦች መጠጊያ መሸሻ
የተቀበለችው ሆና መዳረሻ

የእውቀት ጠበብቶች የአሊሞች ሀገር
የፅናት ተምሳሌት ግርግዳና ማገር
ብዙ ሊቆች አሉን ሁሉን ብንናገር
         እንግዳሳ
ሀቅን ያስተማሩ አረብ ከሀበሻ
አጧዕ ኢብኑ ረባህ የኢልሙ ወጌሻ
እወቀቱ ባህር ነው የለው መዳረሻ
የጥመትን ህንፃ ደማሚት ማፍረሻ
              ናቸው
መጠኑን በዝርዝር ጠንቅቄ ባላውቅም
ስንት አሊም አሉ አያጠያይቅም

እነማንስ ናቸው አይንህን ገልጠህ እይ
ኢትዮጲያዊ ናቸው ኢማሙ ዘይለዕይ
ሙፍቲ የነበረው ኢማሙ አጣኢይ
ኸረ ሌላም አሉ ኢማሙ አድ ረዕይ
         ውዶቼ
የሀበሻ አሪፍ ስማቸው ሲነሳ
እነ አህመዱ ዳንይ የቃጥበሬው ኢሳ
እነ ዓሊ ጎንደር አልጀበርቲ ሙሳ
የቲም አይደለንም ፈፅሞ እንዳትረሳ

   በሙሂቡ ቀለም
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
እደዚ ያሉ ምርጥ ምርጥ ግጥሞችን ለማገኘት
ይቀላቀሉን ሼር ማድረግም አይርሱ
ረቢዕ አንድ አለ

ለነብዩ መውሊድ ዛሬ እንተሳሰብ
በየ መሳጂዱ ሀያ እንሰባሰብ
አሽቀን ይመልከት ይሄ ህብረተሰብ
         
እየተነዛነዝን ያለ እድሜ ከማርጀት
አንድ ሶስት ሆነን ቡድን ከማበጀት
ለማይረባ ነገር ወጭን ከመበጀት
እስኪ ለረቢዑ እንሰብስብ ባጄት
ሐያ እንሳፈረው ያንን የገራም ጀት
   እናንተን አይጠቅስም
በሙጀሲማ ስም የተወሸቃችሁ
የምትበጠብጡ እውነቱን አውቃችሁ
እየሸተተን ነው  የሀሳብ ጭቃችሁ

ምንድን ነው ማንንም በነገር መሸኘት
ሰው ሀቅ እንድረዳ ነው እንጂ መመኘት
የምን መድረቅረቅ ነው ሹህራ ለማግኘት
         ስንት አለ መሰለህ……
የሙጀሲም ጋሪ ሳይሰራ አንድ ፋይዳ
በየሽርኩቻው ስር ነገር እየነዳ
ማንንም መቃወም እውቀት የሚመስለው
ቀርበው ሲጠይቁት መረጃ የሌለው
         ስንት አለ መሰለህ……
በሱ አስተሳሰብ ዱዓት የሚሰፍር
ለመሀይምነት ፈፅሞ እማያፍር
         ስንት አለ መሰለህ…
እውቅና እሚመስለው ፊትና ማቀጣጠል
ጀመዓ እሚበትን ቆርጦ በመቀጠል
አህባሾች እያለ ምቾት ለመዘንጠል
ፓርቲ የሚያቋቁም ውስጡን በተናጠል
ጀግንነት ነው ለሱ ዑለማን ማብጠልጠል
        ስንት አለ መሰለህ………
የትላንቱ ፊትና ያላስተማራቸው
ከነሱ ሀሳብ ውጭ ሌላ እማይገዛቸው
          ስንት ሰው አየሁኝ…
ማታ ሚቀየሩ ጧት ከኛ ጋር መጥተው
ሳምንት የማይቆዩ ባቋማቸው ፀንተው
ለገንዘብ ነው እንጂ ለህዝብ የማያዝኑ
ሰውን ባለባበስ ብቻ እሚመዝኑ

እሬትና ማርን የሚቀላቅሉ
ሙዝ ተከልን ብለው እሾህ የሚያበቅሉ
አቋመ ብልሹ ብዙ ሰወች አሉ
            ይልቅ……
ቂል ከሚሆን ምርቱ ስሜት እየዘራህ
ሐያ ከኛጋ ሁን መውሊዳቸው ይምራህ

በሙሂቡ ቀለም💚❤️💚 ١٤٤٦ حجرا
ሼር ሼር ሼር
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
በፓኪስታን ውስጥ ያሉ ሁሉም የመንግስት እና የግል ትምህርት ቤቶች ለነብያችን ሙሀመድ መውሊድ እንዲደሰቱ ለሶስት ቀናት ትምህርት ቤቶች ዝግ ይደረጋሉ በማለት አስታዉቋል።

#ረቢዕ   #ሚላድ   #ነብዩሰዐወ   #ደስታ
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
ላንቱ የፃፍኩቱ………

በትንሽ መዳፌ በቁንፅል መፃፌ
ማቅለም ጀምሪያለው ቃላትን ሰልፌ

የውበቱን ረጋ በባዕድ እሚያትቱ
የዛን የደግ ሰው  አንደበተ ሩቱ
     መፃፍ ጀምሪያለው………
ማውጫ የለው መግቢያ ሽፋን የለው ጥራዝ
ሉል ንግግሮቹ ተወዳጅ ከአልማዝ
ብራናው ኹሙል ነው ማለቂያ የለው ገፅ
በሙሂቡ ዳኒ ታሪኩ ሲገለ'ፅ
   መፃፍ ጀምሪያለው………
ስላንቱ እየገጠምኩ ቃላት ባላረቅም
ከበያኑ ይልቅ ድልዙ ቢደምቅም
ጃሂል ነኝ አቃለሁ ምንም አወ አላቀም
መግጠም ሱሴ ሆኗል እሱን ደግሞ አለቅም
   መፃፍ ጀምሪያለው……………
የመልክሁ ቁንጅና ኢንታሃው እርቋል
የፀጉርሁ ዘለላ ሀሩ ተንጠቅ ጥቋል
ጨረቃ ለሁለት ሰማን ተሰንጥቋል
የዊላዳሁ ብርሀን እስከ ሻም ፈንጥቋል
ሳዋ ያለው ባህርም ባለበቱ ደርቋል
የቴምሩ ዛፍም ናፍቆት ተሰቅ ስቋል
    መፃፍ ጀምሪያለው………
ሲገጥሙ አይቼ ስንኝን መደርደር
ራሴን ሳላጠና ሳልቆም በመንደርደር

በሸውቅ ጋልቤ ካለሁበት ጓዳ
መግባትን ተመኘሁ ያመናረል ሁዳ
ወዳጅሁ ሙሂቡ

ስነጫነጭ መዋል አመሌ ገርሽቶ
ምን ሆነሀል?  ሲሉኝ
በመጤው ባሀሪየ ሰዉ ተመልክቶ
አላውቅም ምንድነው?
ልገልፀው አልቻልኩም የፊቶትን ቀመር
ሸፍጥ ሆኖብኛል መስማት ብቻ ኸበር

ላንቱ ገብቻለሁ ሁሉንም ከድቼ
እንቅልፍ ትቻለው ዳግም ብየ ዝቼ
ለተመልካች ሁሉ
እኔ አንቱን በመውደድ አሳበቀ ልቤ
ካንቱጋ አድራለው በሩሄ ተስቤ
ሙሂቡ
አብልጨ ልወደድሁ ከሰላማን ከቢላል
ላንቱ ይድረስልኝ ግጥሜ ይቀጥላል

እስኪ ሼር አድርጉት ነቢን የምትወዱ
እንዲ ዳረስልኝ ግጥም ለሚወዱ

በሙሂቡ ቀለም

https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
Join
ዳና

መኪና ባታገኝ ተስበህ እንደ እባብ
በነቢ ውደታ በሚደንቅ ድባብ
በራችን ክፍት ነው ግባ ባሰኘህ ባብ
ዳና እንገናኝ ተዘጋጅ ያሸባብ


በmuhib ቀለም
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
1
እዳላስተምር

ቀርቼማ ነበር
በገጠር ዑለሞች ተጉዤ በእግሬ
ዳገቱን ሜዳውን ወንዙን ተሻግሬ
ሁሉን ቻል አድርጌ አንጀቴን አስሬ

       ቀርቼማ ነበር
ያውም እየተራብኩ በብዙ ሀሪማ
በራያ በየጁ አቦ ተውኝማ
በቃሉ አውራጃ በኮቻ ከተማ

አለሁኝ እንደ አለሁ በነገ በዛሬ
አስተምራለሁ ስል አቂዳን ተምሬ
ይሄው እገኛለሁ ሰንፌ ጠንክሬ

ግን ምን አደርጋለሁ

የማይታገሉት ባላንጣ ጥሎብኝ
ሁሌ በአዕምሮ እየተደፋብኝ
ንፁሁ ሀሳቤን እያፈረሰብኝ
የመከራ ናዳ የህይወት ውርጅብኝ
ቂራአት መውደዴ ዕድሜየን ፈጀብኝ

መፍትሄው የራቀ አስቸጋሪ ነገር
    አይጋፉት ድንበር
    አይሰርዙት መስመር
እምቢኝ ብሎኝ ቀረ ለማቆም ሲጀመር
ተጣብቆ አለቅ አለኝ ደሜ ሲመረመር

ስተቴን እንደ ቅርስ እያስተረጎመ
እምቢኝ ባይ ልሳኔ እንደተለጎመ
እንደ ደረቅ ቅጠል ከቀን ዛፍ ይረግፋል
ባየሩ ሽውታ በቅፅበት ይጠፋል
ሌላ መሻይኽ ሳይ ባድስ ይጠለፋል

እንደ ባህር አረግ የስቃየ ክምር እየተሰደደ
የግጥሞቼን ማማ የተስፋየ ፍሬ ነገን እየናደ
ሁሉም እረገጠው ሁሉም ጠቀጠቀው
የማይረባ እያለ አልፎ ሂያጁም ናቀው
      ነፋሴ ብቻ ነው
ምንድነህ" እያለ ደፍሮ ያልጠየቀው

ይገርመኛል የኔ ጀህልን አለማለፍ
እራመዳለሁ ስል ሁሌም ስጠላለፍ
          
ለሰው የማይገባ በርቀቱ የሚያምር
#ሙሂቡ_ተብየ_ቀለሜን ስቀምር
ወደ መልካም ነገር ጉዞየን ስጀምር
እንቅፋት የሆነኝ ሀቅ እንዳላስተምር
     እርሱ ነው ጠላቴ
የዱንያ ውደታ የመከራ ክምር

       

@yedanawecuchannnneel@
👍2
2025/07/13 21:12:45
Back to Top
HTML Embed Code: