Telegram Web Link
﴿ ﷽ ﴾﴿ إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ﴾

قال رسول الله ﷺ :

أَكثِروا الصَّلاةَ عليَّ يوم الجمعةِ
وليلةَ الجمعة فمن صلَّى عليَّ صلاةً صلَّى اللَّهُ عليْهِ عشرًا ."

اللَّهُمَّ صَلِّ وَسَلِّمْ وَبَارِكَ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ
በቅኔ ሙሃባ ተቀብተን ነበር
ከዳና እስከ አብሬት ቅኔ በመዘመር

ደረቅ ብእር ይዤ ህይወትን ፍጀራ፤
እና ምን ዋጋ አለው፤
ወደ ሆላ ሳበኝ፤የማይረባ እንጀራ።

እንደ ዳናው ሚስባህ:
ተሰጥተን ነበር :

የቅኔ ብርሀን ጨለማ ሚያነጋ:
አስሮ ያዘኝ እንጂ:
በየጉራንጉሩ እንጀራ ፍለጋ።

ለነፍስ ነው እንጂ ጥማትና ረሀቡ:
ስጋማ ሞኝ ነው
ቆሎ የበላ ቀን ጋብ ይላል ረሀቡ።

        በ አወል ዳና
شرح_عقيدة_المسلمين_الطبعة_الثانية_ملون.pdf
30.7 MB
ኪታብ: የአቂደቱል’ሙስሊም ሙሉ ማብራሪያ ባለ ከለር ...!
:
መጠን: 30.7mg
:
ወሳኝና ጠቃሚ የሚባሉ መሳዓላዎችን ያካተተና በመረጃ የተደገፈ ኪታብ ነው፥ ከሁላችንም ሊገኝ የሚገባ....
:
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
Audio
ጁማዱል'ዐወል 3-1444ሒ.
መውሊድ በሐራ.!
:
JOIN
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
●► #ሰለፈ_ሷሊህ  አሻሚ በሆኑ ቁርዓንና ሃድሶች ላይ ሁለት አይነት ማብራሪያ አላቸው።

①ኛው- ጠቅለለ ባለ መልኩ ያብራሩታል ማለትም እውቀትን ከ’ነሱ አርቀው ወደ #አሏህ ያስጠጋለሁ፥ ተዕዊሉል-ኢጅማልይ ይባላል።

ይህን ሲሉ ደግሞ ለአሏህ አካል፣ ቦታ፣ አቅጣጫ፣ ይወርዳል የሚለውን ነገር #ለአሏህ ተገቢ አይደለም ብለው ያምናሉ፥  በ’ነዚህ ባህሪያት አሏሕን መግለፅ የተሳሳተ መንገድ ነው፥ ነብዩ ﷺ አላስተማሩትም ብለው ያምናሉ።

#የሰለፎች እምነት ስምምነት በፀደቀበት ኪታብ ዓቂደቱ-ኣጧሃውይ እንድህ ብለው አስተላልፈዋል፦
ومن مصف الله بمعنى من معني البشر فقد كفر
«አሏን በሰው ባህሪዎች በአንድ ባህሪ የገለፀ በርግጥም ክዷል»
ከሰዎች ባህሪ መካከል፦ መቀመጥ፣ መውረድ፣ መምጣትና በቦታና በአቅጣጫ መገለፅ ነው።

②ኛው- ዝርዝራዊ ማብራሪያ ይህ ደግሞ ሃድስም ይሁን ቁርዐን  የተፈለገበትን በአረብኛ ቋንቋ በሚያሲዘው ይናገራሉ።

➧ለምሳሌ፦
ኢማሙ አህመድ ስለአንድ የቁርአን አንቀፅ እንድህ ብለዋል።
قال الإمام أحمد في قوله تعالى( وجاء ربك والملك صفاصفا)
#የጌታህ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ብለዋል።

•ይህ የቁርዐን አያት በግልፁ ካየነው «ጌታ በመጠ ጊዜ መለይኮች ሶፍ ሶፍ ሰርተው» ይላል።
#ነገር ግን ኢማሙ አህመድ እንደዚህ አይነት ተፍሲር አሏህን በፍጡር ባህሪ መግለፅ  ስለሆነ አሏህ በፍጡር ስለማይገለፅ።
#ትክክለኛውን ትርጉም ሰጡት «የጌታህ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ » ብለው።

#ሁለቱም ጠቅለል ባለመልኩ እና በዝርዝር  ትርጉም መስጠት ከሰለፎች ተገኝቷል ይህም  ትክክለኛ ነው።

#ሁለቱም አካሔድ ለአሏህ ቦታና አቅጣጫ አያስፈልገውም ብለው ይናገራሉ።
በቦታና በአቅጣጫ የሚገለፅ ፍጡር ነው፥ ፈጣሪ አይደለም።

:
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
በኳታር በሚደረገው የአለም የእግር ኳስ ጨዋታ ከታዳሚዎች መካከል አንዱ የመላ እስልምና ተከታዮች እምነት የሆነውን አሏህ ያለ ቦታ ያለ ነው የሚለውን እንቁ ንግግር በዚህ መልኩ ለታሪክ አስቀርቶልናል።

አሏህ የዐርሽ ፈጣሪ ነው።
አሏህ የቦታ ፈጣሪ ነው።
አሏህ የአቅጣጫ ፈጣሪ ነው።
ነብዩ በሐዲሳቸው "አሏህ ነበር(በአዘል) ከእርሱ ሌላ ምንም አልነበረም"ቡኻሪይ እንደዘገቡት።
ይህ ማለት አሏህ ነበር(በአዘል) ቦታ አልነበረም።
አሏህ ነበር(በአዘል) አቅጣጫ አልነበረም።
አሏህ ነበር(በአዘል) ሰው፣ጅን፣መላኢካ በአጠቃላይ ፍጥረታት አልነበሩም።
ቦታን ሳይፈጠር በፊት አሏህ ያለ ቦታ ነበር(በአዘል)።
አሏህ ከቦታ ፈላጊ አይደለም።አሏህ ቦታን ከፈጠረ በኋላ ያለ ቦታ ያለ ነው፡፡
ይህ የመላኢኮች የነቢዮች የወሊዮች እምነት ነው፡፡

አሏህ በዚህ ላይ ያፅናን::ኣሚን
:
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ተንዚህ ክፍል2
ኢብኑ ናፊዕ
ሼር ማድረግን አትርሱ በዚህ ሰበብ ማን እንደሚስተካል አናቅምና።

ክፍል 1👇 ለማገኘት ይጫኑ።
https://www.tg-me.com/istefid/6249
ለኢልያስ አህመድ መልስ
ሸይኽ ሷሊህ
ምሳ ለፊርአውን እውን አሏህ በሰማይ ነው በለውታልን?



https://www.tg-me.com/istefid/6249
#ምነው!..........
አንድ ቀን ፈግግ ብላችሁ፣
ምኞቴ ነበር ብመለከታችሁ።
#ሐቢቢ_ረሱሉሏሕ
••• ••• ••• ••• ••• •••
አሏሕ ሆይ ምኞቴን ለወዳጆቼም ለ’ኔም አሳካልኝ!!
:
http://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
[ከዝምታ ሀቅ መናገር በላጭ ነው፥ ስህተት ከመናገር ዝምታ በላጭ ነው፥ ከብቸኝነት መልካሞች ጋር መቀመጥ በላጭ ነው፥ ከመጥፎ ጓደኛ ብቸኝነት በላጭ ነው።]
© አቡዘር ኣልጚፋሪይ ረዲየሏሁ ዓንሁ..!

||
http://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
•ከእለታት አንድ ቀን #ሸይኽ_ኣብዱል-ቃዽር ጀይላኒ በኸለዋቸው ውስጥ እያሉ ይህ የተረገመ ሸይጧን ሊያጠማቸው #ሀዋዑን የሞላ የሆነ ብርሀን ተመስሎ ወደ ሸይኽ ተጠጋና እንድህ አለ፦

فقول: يا عبدي يا عبد القادر أحللت لك المحرمات ورفعت عنك الفرائض،

አንተ ባሪያዬ አብዱል-ቃዽር ሆይ ክልክላቶችን ፈቀድኩልህ፤ ግዴታዎችን ደግሞ ተውኩለህ፥ አነሳሁልህ አላቸው።

{ ●ነገር ግን #ሸይኽ_አብዱል-ቃዽር ስለ «አሏህ አንድም አምሳያ እንደሌለው፣ በአንድም ነገር ውስጥ እንደማይሰፍር (ያልተወለደ)፣ ከአንድ ነገር የሚወጣ እንደላደለ(የማይወለድ) አሏሕ ከነዚህ ከተጠቀሱት ባጠቃላይ የተጥራራ መሆኑን  ስለሚያቁ፤ ይህ ብርሀን ደግሞ አካል እንደሆነና ለሱ ቅርፅ ያለው፣በርቀት የሚገለፅ፣ በቦታና በአቅጣጫ ያለ መሆኑን ሲመለከቱ ፍጡር እንጅ ፈጣሪ አለመሆኑን አወቁ።

● ሁለተኛ ደግሞ አሏሕ ለሚወድው እንኳን ባሪያው ለነብዩ ሙሀመድ (ሶለሏሑ አለይሂ  ወሰለም) ግዴታዎች አላነሳለትም፤ ክልክላቶችንም አልፈቀደለትም ታድያ ለምርጡ ባሪያው ይህን ያላደረገ ለኔ እንዴት ይሆናል ይህ ሽይጧን ነው። በማለት በእውቀታቸው አሸነፉት።}


•ሸይኽ አብዱልቃድርም አንድህ አሉ
:خسئت يا لعين
«አንተ የተረገምክ እርኩስ ተዋረድክ»

°በዚህን ጊዜ ያ ሀዋዑን የሞላው ብርህን ወደ ጨለማ ተቀይሮ ጠፋ ሸይጧን እንድህ ብሎ አናገራችው #ሸይኽ_አብዱል-ቃዽርን

يا عبد القادر غلبتني بعلمك ومعرفتك فلقد أغويت سبعين رجلًا من أهل الطريق بهذا قبلك.
«አንተ አብዱል-ቃዽር በእውቀትህ አሸነፍከኝ እኔ ከአንተ በፊት 70 የጦሪቃ ባለቤቶች ከመንግድ አስወጥቻቸዋለሁ (አሳስቻለሁ)።»
||
http://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
መልካም ሚስት ሁኚ
ኢብኑ ናፊዕ
ምክሩ ትዳር ላይ ላሉ ሴቶች ነው
ያላገባም ቢሰማው ይጠቀማል።

ሼር ማድ ግን አትርሱ።



https://www.tg-me.com/istefid/6273
[ከጁማዓ ቱርፋቶች መካካል]
:
قال رسول الله صلى الله عليه وسلم:
"ما من مسلم يموت ليلة الجمعة أو نهارها وقاه الله فتنة القبر" رواه الترمذي

“በጁማዐ ቀንም ሆነ ለሊት የሚሞት ሙስሊም የለም አሏሕ ከቀብር ቅጣት የጠበቀው ቢሆን እንጅ።”
•••
||
http://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ሶሓባዎች ለነብዩ ﷺ ያላቸው ውዴታ...!

#ረቢዐተ_ኢብኑ_ካዕብ አልአስለምይ!! እንድህ ይላሉ፦ “እኔ ሁልጊዜ ለነቢዩ  ﷺ ውዱእ የሚያደርጉበት ውሃና ሌላም 
የሚፈልጓቸውን ነገሮች ማታ ማታ አቀርብላቸው ነበር፡፡


አንድ እለት የአሏህ መሌእክተኛ (ﷺ) እንዱህ አሉኝ፡- “የምትፈልገውን ነገር ጠይቀኝ!” እኔም እንድህ አልኳቸው፡-“እኔ ከእርስዎ ጋር በጀነት አብሬ መሆን ነው የምፈልገው፡፡”

ነቢዩ  (ﷺ) ይህን እንደሰሙ እንድህ አሉ፦ “ሌላስ የምትጠይቀኝ ነገር የለህም?”

#እኔም “ይህን ብቻ ነው የምፈልገው”  አልኳቸው፡፡

ይህን እንደሰሙ እንድህ አሉኝ፡-
“እንደዚያ ከሆነ ሱጁድ በማብዛት እርዳኝ፡፡” አሉት..! (ሙስሉም)

||
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
2025/07/04 07:21:52
Back to Top
HTML Embed Code: