Telegram Web Link
ሰይዱና ኢብኑ ዑየይና ረዲየሏሁ ዐንሁ እንድህ አሉ፦
[ደጋግ የአሏሕ ሰዎችን ማውሳት ረህመት ያወርዳል።]
🍂
ሙሃመድ ኢብኑ ዩኑስ የሚባሉት ደግሞ እንድህ በማለት ገልፀዋል፦ [ ደጋግ የአሏሕ ሰዎችን ከማውሳት የበለጠ ለቀልብ ጠቃሚ ነገር አላየሁም።]

📲 JOIN
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ሙሉ ባህሪያቶቹ የአላህ ሲፋዎቹ
አስራ ሶስት ናቸው ዋናዋናቹ
🍂
ማወቁ ግድ ነው ሁሉንም ነገር
በተራ በተራ እስኪ ልዘርዝር
🌀
አንደኛው ውጁድ ነው የአላህ መኖሩ
ብቻውን የኖረ ሳይገኝ ፉጥሩ
ያለ ነው ሲባልም አላህ የኛ ጌታ
አያካብበውም አቅጣጫና ቦታ
ማመኑ ግድ ነው እሱን ያለ እንዴታ
ከዚህ ነው አይባል አይደለምም ፍጡር
ያለ ቦታ ነበር ፍጡርን ሳይፈጥር
🌀
ሁለተኛው ደግሞ አላህ አንድ ነው 
እሱን የሚመስል አጋርም የለው    
አንድ ነው ሲባልም አይደለም በቁጥር
በጌትነቱ ነው በሌለው አጋር    
በማይገኝለት ቢጤና ወደር
🌀
ቀዳሚነቱ ነው ደግሞ ሶስተኛው
ኻሊቁ ጌታችን ጅማሬም የለው
ቀድሙ ሰታሩ ዘላለም ቢኖርም
ዘመናት በሱ ላይ አይሸጋገርም
🌀
አራተኛው ደግሞ አል በቃእነቱ
ዳኢም የሚኖር ነው ውሸት ነው መጥፋቱ
ማሊኩ ጌታችን ዘላለም ነዋሪ
መኽሉቁ ሲጠፋ እሱ ብቻ ቀሪ
ያረጃል አይባል ወይም ይሞታል
አያመችበትም መጥፋት ለጀሊል
🌀
አልቂያሙ ቢነፍሲህ ነው አምስተኛው
ከሌላ አይከጅልም የተብቃቃ ነው
ፍጡርን ፈጣሪ ሁሉንም አስጠጊ
ከፈጠረው ፍጡር አይደለም ፈላጊ
የተብቃቃ  ጌታ ጥቅምን አይፈልግም
ከፍጡር በጭራሽ
ከትንሿም ዘራ ከትልቁም አርሽ
🌀
ስድሰተኛው ደግሞ ቁድራ ቻይነቱ
ሁሉን ነገር ሰሪ በችሎታነቱ
ማንም መፍጠር አይችል ኸይርም ሆነ ሸር
ትንሿን እንኳ አንድቷን ፀጉር
ከሶመድ በስተቀር ከአላህ ከጀባር
ሁሉን በየ አይነቱ ሲፈጥረው እሱማ
የሚያቅተው የለም አይደለም ደካማ
🌀
ሰባተኛው ደግሞ ይባላል ኢራዳ
ቢፈጠር ቢጠፋ ሀሉም ከአላህ ዘንዳ
መግደሉም ማዳኑም በአዘል ተፈርዶ
የሚያሰራው የለም እሱን አስገድዶ
አይቀያየርም ፍላጎቱ ጀሊል
የፈጠረው ነገር አንድ ጊዜ በአዘል
🌀
ስምንተኛው ደግሞ መሆኑ አል'ከላም
ያለ ሀርፍ ያለ ድምፅ ተናጋሪ ዳኢም
በቋንቋ በፊደል በድምፅ አይናገር
ያለአንዳች መሳሪያ ያጅባል የሱ ነገር
🌀
ዘጠነኛው ደግሞ አሰሚዕነቱ
መሳሪያ አይጠቀም ጌታችን በእውነቱ
ረሂሙ ጌታ ሲሰማ ነገር
አያሰፈልገውም የጀሮ ታምቡር
🌀
አስረኛው ደግሞ የሚያይ ነው በሲር
ማየት አይሳነው ድብቅን ነገር
በጨለማ ምድር ብትሄድ ጉንዳን
ጭራሽ አይጠፋውም ያያታል እሷን
ያለ አንድ መሳሪያ ያለ አይን ብሌን
🌀
አሊም መሆኑ ነው አስራ አንደኛው
በዳኢሙ እውቀቱ ሁሉን የሚያውቀው
አይጠፋውም ለሱ በሰው ልብ ያለው
እውቀቱ አይጨምርም ደግሞም አይቀንስ
የፍጡር አይመስል የመላኢኮችን የጅንም የኢንስ
አይጠፋም እውቀቱ የአላህ የቁዱስ
🌀
አስራ ሁለተኛው ሀይ ነው ሶመድ
የአላህን ሀይነት ማመን ይላል ግድ
በስጋና በደም አይደለም በነፍስ
የፍጥሩን አይመስልም ሃይነቱ እሱስ
በአጥንትም አይባል እንድሁም በአካል
ከሁሉም ተጥራራ ረበል ጀሊል
አይሞት አይታመም ዘላለም ነዋሪ
ለመኽሉቃቶቹ አዛኝና ማሪ

ለአሏህ ለቀውዩ ዛት አለው ሲባል
እውነታው ማለት ነው አይደለም አካል
ጨለማና ብርሃን ሌሊትና ቀኑ ሰማይና ምድሩ
ያመላክትሃል የአላህን እውነታ እሱ ለመኖሩ
🌀
አልሙኻለፋቱ ሊልሀዋድስ አስራ ሶስተኛው
የፍጡራንን ባህርይ አለመምሰል ነው
መደላደል ይሁን ወይም መረጋጋት
መንቀሳቀስና  መውረድም መውጣት
ይህን መሰልና ሌሎች ባህሪያት
የፈጣሪ ሳይሆን ናቸው የፍጥረት
የአላህ ባህሪያቶች አስራ ሶስቱ ሁሉ
ጎደሎ አይባሉም ናቸው ሙሉ ሙሉ
🍂
ሁስነልኺታሚ ወፍቀን ጀሊሉ
ጌታየ አታስወጣን ከረህመትህ ዘንዳ
በኢማን ዘይነህ አኑረን በሰዓዳ
መጨረሻም ስንሞት ግጠመን ሽሃዳ

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
⭕️ ይባላል ➲ አንድ ሰው የሞተን ውሻ ከሙስሊሞች መቃብር ቀበረ፥ በዚህን ጊዜ ሰዎች ወደ ቃዲው ዘንድ ሄዱና ክስ አቀረቡ።

ቃዲውም ሰውዬውን ጠራውና “ሰዎች ከሙስሊሞች መቃብር ውስጥ ውሻ ቀብረሃል” ብለው ከሰወሃል አለው

ሰውይውም «አዎ በርግጥም ቀብሬዋለሁኝ ሲሞት ኑዛዜ ነበረው ኑዛዜውንም ፈፅሚያለሁኝ» በማለት መለሰ

ቃዲውም “ወዬውልህ በእኛ ላይ ታሾፋለህን?” በማለት ጠየቀው

ሰውዬውም ቀጠል አደረገና “ውሻውም ለቃዲው አንድ ሺ ወርቅ እንድሰጥ ተናዞ ነው የሞተው” አለና ሰጠው

ቃዲውም “ሟችን ውሻ አሏሕ ይዘንለት” አለ

ክርክሩን ሲሰሙ የነበሩ ሰዎችም ቃዲው በፍጥነት ሁኔታው መቀየሩን ሲያዩ በጣም ተገረሙ!

ቃዲውም ለሰዎቹ እንድህ አላቸው፦ «አትገረሙ በዚህ ጥሩ ውሻ ላይ ብዙ አስቢበታለሁ፥ መርምሪያለሁ እሱም ከአስሃቡል'ከህፍ ውሻ ዘር መሆኑን ደርሼበታለሁ»
〰️
የሁላችንም ሁኔታ ይሄን ይመስላል!

አንዳንድ ሰዎች አቋማቸውን አስር ጊዜ ይቀያይራሉ

ስህተትንም ይናገራሉ ለስህተታቸውም ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ሲሉ ይከላከላሉ፥ ሌላም ስህተት ይጨምራሉ።

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
◌ የዘንድሮው መውሊድ ሺዐር [መፈክር]

📢ሸውቃህ!

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ሰይዱና ሐሰኑል'በስርይ ረሒመሁሏሁ እንዲህ አሉ፦
[የአደም ልጅ ሩሕ ከሰውነቱ አትወጣም በሶስት ነገሮች ተፀፅቶ ቢሆን እንጂ፥
በሰበሰበው ነገር ባለመጥገቡ፥
❷ምኞቱን ባለማሳካቱ እና
❸ወደፊት ለሚሔድበት ሐገር ስንቅ ባለማስቀደሙ።


የአደም ልጅ ሆይ የቀናቶች ስብስብ ነህ ቀናቶች በሔዱ ልክ የሰውነትህ ከፊል ይሔዳል።]

〰️
📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
من كنوز التدبر
●➊● ✍️
🍃‏"قَالَتِ امْرَأَةُ الْعَزِيزِ الْآنَ حَصْحَصَ الْحَقُّ "
የዐዚዝ ሚስት «አሁን እውነቱ ተገለጸ፥ እኔ ከነፍሴ አባበልኩት እርሱ ከእውነተኞቹ ነው» አለች።
قد تنام الحقيقة طويلًا ،، لكنها لا تموت !

እውነት ልትደበቅ ትችላለች ነገር ግን አጠፋም..!


●➋●✍️
🍃‏"اقتلوا يوسف أو اطرحوه أرضاً يخلُ لكم وجهُ أبيكم "
ዩሱፍን ግደሉ፥ ወይም በሩቅ ምድር ላይ ጣሉት። የአባታችሁ ፊት ለእናንተ የግል ይኸናልና።
ماعلموا أن الحبّٓ لايغادر مع الأجساد ..!!

ፍቅር በአካል በመራቁ እንደማይወገድ፥ እንደማይጠፋ  አላወቁም ነበር።


●➌●✍️
🍃‏﴿ إذ قالوا ليوسُفُ وأخوه أحبُّ إلى أبينا منّا ﴾
“ወንድሞቹ ባሉጊዜ አስታውስ ዩሱፍና ወንድሙ ብንያም ወደ አባታችን ከእኛ ይበልጥ የተወደዱ ናቸው።”
لم يحسدوه على المال !
በገንዘብ፥ በሀብት አይደለም የተመቃኙት..!
عطايا القلب أثمن من عطايا اليد ..

የቀልብ ስጦታ ከእጅ ስጦታ የበለጠ ነው።

●➍●✍️
🍃تكرر القميص في قصة يوسف-عليه السلام-٣مرات:
በዩሱፍ عليه السلام ታሪክ ላይ ቀሚሱ ሶስት ጊዜ ተመላልሷል።
فكان سبباً للحزن، ودليلاً للبراءة، وبشارة فرح.
“ለሀዘን ምክንያት ነበር፥ ለንፅህና መረጃ ነበር፥ ለደስታም ብስራት ነበር።”
ما يُحزنك اليوم قد يكون سبَبَ سُرورك غداً.

«ዛሬ የሚያስከፋህ ነገር ነገ የደስታህ ምንጭ ሊሆን ይችላል።»


●➎●✍️
🍃" وَاستَبَقا البَاب "
በሩንም ተሽቀዳደሙ...!
قَد تَسيران فِي دربٍ وَاحد .. لكِن النّوايَا مُختلِفة .!

“በተመሳሳይ መንገድ ልትጓዝ ትችላለህ.. ነገር ግን ፍላጎታችሁ ይለያያል።”

🌀ይቀጥላል.....!

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
✍️ ክፍል ①
〰️
📍አብዘሀኛው የወሃብያ እምነት ተከታዮች ለዚህ ለተበላሸ እምነታቸው እንደመረጃ ከሚያቀርቡት መካከል አንድኛው  የኢስተዋ አንቀፅ ነው። ወደ ትርጉሙ ሳንገባ በፊት በአረብኛ ቋንቋ ስንት ትርጉም እንዳለው ከመረጃ ጋር እናያለን!
🌀
◈ ኢስተዋ የሚለው ቃል በአርብኛ ቋንቋ ①⑤ ትርጉም አለው። ይህንንም የሐድሱ ሊቅና የቋንቋው ምሁር አቡበክር ኢብኑል'ዐረብይ ረሒመሁሏሁ ጠቅሰውታል፥ እንደዚሁም ሙሀመድ ኢብኑ ጀሪር'ኣጦበርይ በተፍሲራቸው በከፊል ጠቅሰውታል።
♻️
◌ የኢስተዋ ቃላት ፍች !!!
كلمة استوى في لغة العرب لها خمسة عشر معنى، منها:
የዒስተዋ ቃል በአረብኛ ቋንቋ አስራ አምስት ትርጉም አላት። ከነዚህም መካከል

1- التمكن والاستقرار:
ومنه قوله تعالى في سورة هود: "وَاسْتَوَتْ عَلَى الْجُودِيِّ" أي أن سفينة نوح عليه السلام استقرت على جبل الجودي
◈① መደላደል
በቁርዓን ውስጥ በዚህ ትርጉም ከመጣልን መካከል በሱረቱል ሁድ-44 አሏሕ አንቀፅ ላይ እንድህ ይላል፦
«ጁድይ በሚባልም ተራራ ላይ መርከቢቱም ተደላደለች።» ማለትም የነብዩሏሂ ኑህ ዓለይሂ ሰላም ሰፊና ጁድይ ከሚባል ተራራ ላይ ተረጋጋች ማለት ነው

ويقال: استوى الرجل على ظهر دابته أي استقر عليها، قاله اللغويون وغيرهم.
◉ እንደዚሁም በተጨማሪ የቋንቋ ሊቃውንቶች እንድህ ብለዋል፦ «ሰውየው በእንስሳይቱ ጀርባ ላይ ተደላደለ [ተቀመጠ]።»

2- الاستقامة والاعتدال:
ومنه قوله تعالى في سورة الفتح: "فَاسْتَوَى عَلَى سُوقِهِ" أي الزرع، والمراد بالاستواء في هذه الآية الاستقامة التي هي ضد الاعوجاج.
◈② ቀጥ ማለት
በቁርዓን ውስጥ በዚህ ትርጉም ከመጣልን መካከል በሱረቱል-ፈትሕ-29 አንቀፅ ላይ አሏሕ እንድህ ይላል፦ «በአገዳዎቹ ላይ ተስተካክሎ እንደቆመ አዝመራ ነው።» °በዚህ የቁርዓን አንቀፅ ኢስቲዋዕ በማለት የተፈለገው ምንም አይነት መወላገድ የሌለው መስተካከልን [ቀጥ ብሎ መቆምን] ነው።

قال المفسر أبو حيان في تفسيره (البحر المحيط ج8 / 103) ما نصه: "فاستوى أي تم نباته على سوقه جمع ساق كناية عن أصوله" ا هـ
◉ታላቁ ሙፈሲርና የቋንቋ ምሁር የሆኑት አቡ'ሓያን አል'አንደሉስይ በተፍሲራቸው (በህሩል-ሙሒጥ 8ጁ/103 ) “ኢስተዋዕ ማለት አበቃቀሉ ሞላ፣አገዳው በስሮቹ ጠነከረ፥ ባጠቃላይ የአገዳው ስር መስደድና መጠንከር”  በማለት ገልፀዋል። 

وقال البيضاوي في تفسيره ما نصه (أنوار التنـزيل م2/ج5/ص 86): "فاستقام على قصبه جمع ساق" ا هـ
◉በይዿዊይ እንደዚሁ በተፍሲራቸው (አንዋሩ ተንዚል) «አዝዕርቱ በአገዳው ላይ ቀጥ አለ።»

يقال استوى صار سَوِيًّا أي مُستقيمًا. وهذه من المعاني التي تليقُ بالمخلوقات.
◉ኢስተዋ ይባላል እኩኩል ለሆነና ለተስተካከለ ነገር ይህም በፍጡር ላይ የሚገለፅ ባህሪ ነው።

3- التمام:
ومنه قوله تعالى في سورة القصص: "وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ وَاسْتَوَى" أي تمت قوته الجسدية .

◈③ ሞላ
በቁርዓን ውስጥ በዚህ ትርጉም ከመጣልን መካከል በሱረቱል-ቀሶስ-14 አንቀፅ ላይ አሏሕ እንድህ ይላል፦«ብርታቱንም በደረሰና በተስተካከለ (ሞላ) ጊዜ....» የሰውነቱ ጥንካሬ ብርታት በሞላ ጊዜ

ففي (القاموس) (ص1673): "واستوى الرجل: بلغ أشده" ا هـ،
◉ቃሙስ ውስጥ «ኢስተዋ'ረጁሉ: ይባላል ጥንካሬው በደረሰ ጊዜ።»

قال الحافظ محمد مرتضى الزبيدي شارح القاموس (ج10/189): "فعلى هذا قوله تعالى في سورة القصص: "وَلَمَّا بَلَغَ أَشُدَّهُ وَاسْتَوَى" ا هـ.
አልሐፊዙ ሙሃመድ ሙርተዶ'ኣዘቢድይ ቃሙስን ሲያብራሩ እንድህ አሉ፦ «በዚህም ንግግር አሏሕ በሱረቱል-ቀሶስ ላይ ጠቅሷል።»

ويقال "استوى القمر بدرًا" أي تَمَّ.
°«የበድር ጨረቃ ሞላ።» ይባላል!!!!

🌀 ይቀጥላል...!

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ዊላዳው
የውልደትሁ ዜና ከሰማይ የላቀ
ይገኛል ወይ እስኪ አንቱን ያልናፈቀ
በዳና በጫሊ ገብቶ ያልቦረቀ

በየት በኩል ልሂድ ሙሀባን ፈርቄ
አንቱን ልገልፀዎት በቃላት ጨምቄ

ቀናትን ስቆጥር ሀድራን እየናፈኩ
በተስፋ ስኳትን ራብሳን እያሰብኩ
ይህው ሶፈር ገብቶ በሩጫ ከነፈ
አንቱን የማይወድሁ ፍሬው ረገፈ

በሙሂቡ ዳኒ …………
ሼር… ……
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
⭕️ሱፍይነት.!
🍂
ሰዪዱና ኢማሙ አሕመድ ኢብኑ ሐንበል ረዲየሏሁ ዐንሁ ወደ ሰዪዱና አቡ-ሐምዛ አል’ባግዳዲይ ረዲየሏሁ ዐንሁ ደብዳቤን ይልኩ ነበረ።

በደብዳቤያቸውም እንድህ ይሉት ነበር፥ እስኪ በዚህ መሳዓላ [ጥያቄ] ላይ አንቱ ሱፍይ ሆይ መልስ ስጡበት..!
🍃
ይህ ብቻ አይደለም ለልጃቸውም እንዲህም እያሉ ምክርን ይለግሱት ነበር፦ [ከሶፍዮች ጋር መዘውተርን አብዛ፥ አብረህ ተቀማመጣቸው።  እነሱ በኢኽላስ እኛ ያልደረስንበትን ደረጃ ደርሰዋል።]
🍃

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
«የሚፋታው በዛ»

ሙሀባ የሚሉት እራቀን ትርጉሙ
ማግባት ከጀመሩ ሴቶች ከድርሀሙ
ሴት ለብር ኖረ መላው ጠፍቶብናል
ዶክተሩ ጠፍቶ እንጂ እጂጉን ታመናል

ብር ሳታካብት በትዳር ላይ ገብተህ
ፍቅርህ ተሰደደ በረካ አጣህ ለፍተህ
አይደል?
በችኮላ ሰክረን ጠፍቶብን እርጋታው
ሆይሆይታ አሸንፎን የስሜት ጋጋታው
አልገባን እያለ የመውደድ ስጦታው
ከሚጋባው ይልቅ በዛ የሚፋታው


በሙሂቡ ቀለም
ሼር
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
Audio
ርዕስ የሱፍዬች ገድል
=========
ክፍል…01

«የኛ መሪ ኢማም»

👉መንሱር አልበይዷዊ(ረሒመሁሏህ)

ጡወር በተባለ ስፍራ ተወለዱ
ከኢማሙ ቱስቱር እውቀትን ወሰዱ



ሙሂቡ ቀለም
🀄️ጥላል ሼር
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
ክፍል ❶
〰️
የዒስተዋ ቃል ፍች!!
♻️
قال الله تعالى
{إِنَّ رَبَّكُمُ ٱللَّهُ ٱلَّذِى خَلَقَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ وَٱلْأَرْضَ فِى سِتَّةِ أَيَّامٍ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ يُغْشِى ٱلَّيْلَ ٱلنَّهَارَ يَطْلُبُهُۥ حَثِيثًا وَٱلشَّمْسَ وَٱلْقَمَرَ وَٱلنُّجُومَ مُسَخَّرَٰتٍۭ بِأَمْرِهِۦٓ أَلَا لَهُ ٱلْخَلْقُ وَٱلْأَمْرُ تَبَارَكَ ٱللَّهُ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِين}
◈ትርጉሙ፦ [ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም (ስልጣኑ) በዐርሹ ላይ ተደላደለ፡፡ (አላህ) ሌሊትን በቀን ፈጥኖ የሚፈልገው ሲኾን ይሸፍናል፡፡ ፀሐይንና ጨረቃንም ከዋክብትንም በትእዛዙ የተገሩ ሲኾኑ (ፈጠራቸው)፡፡ ንቁ! መፍጠርና ማዘዝ የእርሱ ብቻ ነው፡፡ የዓለማት ጌታ አላህ (ክብሩ) ላቀ፡፡] ሱረቱል አል አእራፍ 5፣ዩኑስ 3፣ፉርቃን 59 ፣ሰጀዳ 4 ፣ሃድድ 4

♯እንደዚሁም በሱረቱ ረዕድ 4
{ٱللَّهُ ٱلَّذِى رَفَعَ ٱلسَّمَٰوَٰتِ بِغَيْرِ عَمَدٍ تَرَوْنَهَا ثُمَّ ٱسْتَوَىٰ عَلَى ٱلْعَرْشِ}
◈ትርጉሙ፦ [አላህ ያ ሰማያትን የምታዩዋት አዕማድ ሳትኖር ያነሳት ከዚያም በዐርሹ (ዙፋኑ) ላይ (ስልጣኑ) የተደላደለ።]

♯እንድሁም በሱረቱ ጧሃ 5
ٱلرَّحْمَٰنُ عَلَى ٱلْعَرْشِ ٱسْتَوَىٰ
◈ትርጉሙ፦ {(እርሱ) አልረሕማን ነው በዐርሹ ላይ (ስልጣኑ) ተደላደለ፡፡}

🌀የጥመት ባለቤቶች እነዚህና ሌሎች አሻሚ የሆኑ  የቁርዓን አንቀፆች በመከታተል አሏሕ ያለገለፀበትን፥ ነብዩ ﷺ ያላስተማሩትን፥ ከደጋግ ሰለፎች ያልተገኘን ቁርዓን ያለ አግባብ በመተርጎም ፈጣሪን በፍጡር ባህሪ ይገልፃሉ። ይህም #የተሽቢህ ጥመት ነው።
〰️
⭕️ኢስተዋ ማለት ከፍ አለ ማለት ነው ይላሉ! በከፊሎቹ ዘንድ ደግሞ ተደላደለ! ማለት ነው ይላሉ። ይህ የተሳሳተ የኩፍር እምነት ነው።
〰️
☞በነሱ ተፍሲር አካሔድ  <ጌታችሁ ያ ሰማያትንና ምድርን በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አላህ ነው፡፡ ከዚያም ከፍ> አለ ይሆናል ይህ ማለታ ሰማያት እና ምድርን ሳይፈጥር ከአርሽ ዝቅ ያለ ከበታች ነበር ማለት ያሲዛል ይህ ደግሞ ለአሏሕ የማያመችን ባህሪ ማፅደቅ ነው።

◌በተጠቀሱት የቁርአን አንቀፆች ላይ ታላላቅ ሙፈሲሮች እና የተውሒዱ ኦለሞች የተፈለገበትን ሲያብራሩ ኢስተዋ ማለት ተቆጣጠረ ማለት ነው ብለው በግልፅ ያስቀምጣሉ።
:
🌀ነገር ግን አንዳንድ የአእምሮ ዝቅጠት ያለባቸው ሰዎች ይህ ነገር አይዋጥላቸውም እንደውም ይህ ነገር ለማስተባበል ሲፍጨረጨሩ ይታያሉ።
:
🌀ከሚያቀርቡት ማስተባበያ መካከል ፦ ተቆጣጠረ ማለት የአሏን ስልጣን መገደብ ነው ምክንያቱም ተፎካካሪ ነበረው እና አሸንፎ ተቆጣጠረን ያሲዛል ይላሉ።

☞ታድያ እንደነሱ አባባል ይህን ምን ይሉት ይሆን?
قال الله تعالى في سورة الرعد
{قُلِ ٱللَّهُ خَٰلِقُ كُلِّ شَىْءٍ وَهُوَ ٱلْوَٰحِدُ ٱلْقَهَّٰرُ}
◈ትርጉሙ፦ { በል፤ «አላህ ሁለመናውን ፈጣሪ ነው፡፡ እርሱም አንዱ ተቆጣጣሪው ነው» በል፡፡}

♯ በዚህ የቁርዓን አንቀፅ ውስጥ የአሏሕ ስልጣንን መገደብ አለበትን?
♯ ለዚች ዓለም ሌላ ተፎካካሪ ነበራትን? አሸንፎ ነው የተቆጣጠረው?

በዚች የቁርዓን አንቀፅ ስልጣኑን መገደብም ሆነ ተፎካካሪ እንደሌለው ሁሉ አሏሕ አርሽን መቆጣጠሩ ስልጣኑ የተገደበ አይደለም ተፎካካሪም ነበረው የሚለውን አያመላክትም።

وكذلك في قوله تعالى {لمن الملك يوم}
#እንደዚሁም አሏሕ የውመል ቂያማ እንድህ ይላል፦
{ዛሬ ንግስና የማነው?}
በዱንያ ላይ ንግስና የሌላ ነበር እንዴ?

⭕️አዩሓል ዋህብያ!!!!

≈ኢስተዋን ኢስተውላ ብሎ መተርጎም ተዕጢል /ጥመት/ነው ብሎ ማለት ይህ የለየለትና ግልፅ የሆነ ኩራፋት ነው!!!

⭕️ ታላላቅ እውቅና ያላቸው አሊሞችን በጥመት መፈረጅ ይሆናል። ኦለማዎችን በጥመት መፈረጅ ደግሞ የእሱ እምነተ መጤ ለመሆኑ ግልፅ የሆነ መረጃ ነው። ምክንያቱም ለሚናገረው ንግግር ወይም እምነት ሰነድ የለውም ወደ ነብዩ የሚደርስ ማለት ነው።
🌼
📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ርዕስ ረቢዒን ናፋቂ
☞ገጣሚ ሙሂቡ ዳኒ

    ★☞አቅራቢ ራዲያ

    ★☞ኤዲት ኢብኑ ናፊዕ

ስላንቱ እየገጠምኩ ቃላት ባላረቅም
ከበያኑ ይልቅ ድልዙ ቢደምቅም
ጃሂል ነኝ አቃለሁ ምንም አወ አላቀም
መግጠም ሱሴ ሆኗል እሱን ደግሞ አለቅም

ይጠብቁን ሼር
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
የተዋበ ስነምግባር ❷

አቡ'ሁረይረተ እንድህ አሉ፦ ነብዩ ﷺ ምግብን አነውረው አያውቁም። ካሰኛቸው ይበሉታል፥ ካልፈለጉት ይተውታል።

🍃ጁማዐቱኩም ሙባረክ

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
◈ኢማሙ አ'ሻፊዕይ ረዲየሏሁ ዐንሁ ከዚህ ዐለም በሞት ከተለዩ በኋላ አንድ ተማሪያቸው በህልም አያቸውና እንድህ በማለት ጠየቃቸው፦“አሏሕ እንዴት አደረገዎት ኢማማችን ሆይ?”

«በአሏሕ እምላለሁ አሏሕ ማረኝ፥ አዘነልኝ እንደሙሽራም ተደርጌ ወደ ጀነትም ተሸኘሁ።» አሉት

ተማሪውም፦ “በምንድን ነው ይሄን እድል ሊያገኙ የቻሉት ኢማማችን ሆይ?” በማለት ጠየቃቸው

“አር'ሪሳለ በተሰኘው ኪታቤ መግቢያ ላይ በፃፍኩት ፅሁፍ ነው” አሉት

ተማሪውም ወዳው ከእንቅልፋ ባነነ፥ ከህልም አለምም ነቃና ኪታቡን ፈልጎ ከፈተና መግቢያው ላይ ይሄን አገኘ።

[አሏሑመ'ሶሊ ዐላ ሙሃመድ ወዐላ አሊ ሙሃመድ ኩሉማ ዘከረከ ዛኪሩን ወጕፈለ ዐን ዚክሪከል'ጓፊሉን]

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
ለኢኽዋኖች መንጋ

ብቁ እኔ ነኝ ብለህ መጅሊሱን ቀምተህ
ዛሬስ አቋምህን እርግፍ አርገህ ትተህ
ሰወችን በስሜት በጥመት አርክተህ
             መውሊድን
ቢዳአ ነው እያልክ ስንት እዳላወራህ
ሙሽሪክ ናቸው እያልክ ስንት እዳላዘራህ
ሀሰናት መሆኑን ዛሬ ማን አቀራህ?
                አጅብ
ምን አይነት ንግድ ነው ትርፍ የሌለው ልፋት
በሰለፍያ ስም ሰለፍያን ማጥፋት
በሱፍዬች ማሊያ ኹራፋት ማሥፋፋት
                 ተውጂ
በማስመሰል ጥበብ በሂክማ መደበቅ
ቢዳዓና ሱና ሳይለዩ መድረቅረቅ
አስመስሎ መኖር የትም አያደርስም
ካላከበራችሁ ብለንም አንከስም
             ሸህ ኢብራሂም ቱፋ
የምን መውተርተር ነው ልክ እንደ ሰካራም
ሰው ስታጭበረብር አላህን አትፈራም
መለየት አታቅም ሀላልና ሀራም

መውሊድ ቢዳዓ ነው ብለህ ተናግረሀል
ባቋምህ ፅና እንጂ ምን ይመልሰሀል
           ሸህ ኢብራሂም ቱፋ
ማን ነው ያስተማረህ አስመስሎ መኖር
ሀቅን እያጠፉ ወንበር ላይ መዘመር
           ኢኽዋኖች
ብትመለሱ እንጂ እኔ ምመክራችሁ
እኔስ መቸ ጠፋኝ መሪው አባታችሁ
        ሰይድ ቁጥቡ
ግብፅ ነው መነሻው እውቀት ያላተተ
መቶ አመት ያልሞላው ከተመሰረተ
ውሸትና ቅጥፈት በደንብ የተጋተ
መረጃ የሌለው የተርበተበተ
             ነው
ዲንጋ ዳቦ ነው ባይ ሀቅ የማይረዳ
የተፈላፈለ ኢስላምን ሊጎዳ

እሱ ነው አባትህ አለም ሁሉ ያቃል
ለአሻኢርያ  መቸ ይደበቃል
ማን ያስተውልሀል መች ትታመናለህ
አምና ሀራም ነው አልክ አሁን ትፈቅዳለህ
ሰለፍይ ስታገኝ እሱን ትመስላለህ
ከዚያ ሀዳድ ስታይ ከሱ አለሁ ትላለህ

አንተን አስታውሸ ስንኝ መፃፌ
አዝናለሁ በራሴ ብዕር ማንከርፈፌ

ግን ደግሞ የዋሆች ያልተጠነቀቁ
የሚከታተሉህ ጉዲህን ሳያውቁ
በአንተ ፊክር ገብተው የተጨማለቁ
እድጠነቀቁ
ባለማወቅ ዘመን ወዳንተ የመጡ
ዛሬ እስኪ ይወቁህ ካንተ ጋ እሚሮጡ
ለነርሱ ነው እኔ የምለቀልቀው
የነ ጃክን ሴራ ሁሉም ሰው እንዲያውቀው

የሙሂቡን ግጥም
አብረን እናጣጥም

Join ሼር ሼር Join
https://www.tg-me.com/byetiLhadorat
ረሱላችንን ስታወድሱ ለምን ድቢ ትመታላችሁ ?
ወዲያ ወዲህ መወዛወዙንስ ማን ፈቀደው? ብሎ ለጠየቀን!
✦✦✦

መንዙማ እያሉ ድቤ መምታትና ወዲያ ወዲህ መወዛወዝን የፈቀዱት ራሳቸው ነብዩ ናቸውﷺ።አዎ! በጭፍን ከመቃወምህ በፊት ተከታዩን ሐዲስ ልብ ብለህ አንብብ!

1. ኢማም አሕመድ ሙስነዳቸው ላይ፣ኢብኑ ሒባን ሶሒሓቸው ላይ አነስ ኢብኑ ማሊክን ጠቅሰው እንዲህ ይላሉ።
كانت الحبشة يزفنون بين يدي رسول الله ويرقصون يقولون محمد عبد صالح.
"ሐበሻዊያን ከአላህ መልእክተኛ ፊት ለፊት ሆነው እየተወዛወዙ
"ሙሐመዱን ዓብዱን ሷሊሕ" ሙሐመድ ደጉ ሰው በማለት ያዜሙ ነበር።

2. ታላቁ የሐዲስ ሊቅ ኢማሙ ነሳኢይ "ሱነኑል ኩብራ" ላይ በአቢ ሰለማ በኩል የተላለፈውን ሐዲስ እናታችን አዒሻ እንዲህ ማለታቸውን በሶሒሕ ዘገባ አስፍረዋል።
دخل الحبشة يلعبون فقال لي ياحميراء أتحبين أن تنظري إليهم ؟فقلت نعم ،فقام بالباب وجئته فوضعت ذقني على عاتقه فأسندت وجهي إلى خده ، قالت ومن قولهم يومئذ "أبا القاسم طيبا"
ሐበሾች እየተጫወቱ ገቡ፣ነብዩም "ሑመይራእ ሆይ ልታያቸው ትፈልጊያለሽን" አሉኝ።እኔም አዎን አልኳቸው።በሩ ላይ ቆሙ፤እኔም አገጬን አንገታቸው ላይ፣ፊቴን ወደ ጉንጫቸው አስደግፌ መመልከት ጀመርኩ። ያኔ [ሐበሾቹ]ይሉት የነበረው[መወድስ] "አበል ቃሲሚ ጦይይባ" "ደጉ የቃሲም አባት" የሚለውን ነበር" አለች።

3. ኢብኑ ማጃህ ሱነናቸው ላይ፣ጦበራኒ ሙዕጀሙ‐ሶጊር በተሰኘ ኪታባቸው ላይ አነስ ኢብኑ ማሊክን ጠቅሰው እንዲህ ብለዋል።
ነብዩﷺ መዲና ላይ በሆነ ቦታ ሲያልፉ የተመለከቷቸው የመዲና እንስቶች ድቢያቸውን እየደለቁ በሚያምር ዜማ
نحن جَوار من بني النجاري
ياحبذا محمدٌ من جار
ነሕኑ ጀዋሪን ሚን በኒ ነጅጃሪ፣
ያ ሐበዛ ሙሐመዱን ሚን ጃሪ።

"እኛ ከበኒ ነጃር ጎሳ የሆንን እንስቶች ነን፣የሙሐመድ ጎረቤት መሆን ምንኛ መታደል ነው?!"በማለት ማንጎራጉሩ ያዙ።ይህን የተመለከቱት ነብዩም ﷺ በምላሹ
الله يعلم إن لأحبكن
"አሏህ ያውቃል እኔም እወዳችኋለሁ።" አሉ

✦✦✦
ይሄው ነው ወንድሜ! ነብዩ አይተው ያፀደቁትን ነገር እንዴት አንተ ሥላልተመቸህ ብቻ ልትቃወመው ውስጥህ ፈለገ? ነብዩ ይሁን ያሉትን አንተ አይሆንም የምትለው አንተ ማነህና? የተቃወምከው ባለማወቅ ከሆነ ያውና ከዚህ ጀምሮ እወቀው።ሐዲሱን እያወቅክ ከሆነ ግን በቀጥታ የምትቃወመው ረሱልን ይሆናል። ይሄ ደግሞ አደጋ ላይ ይጥልሃል።

በርግጥ አደብና ለዛ ባለው መልኩ አድርጉት ብሎ መምከርን ማንም አልከለከለህም። ዘለህ ሐራም ነው፣ገለመሌ ነው፣ሽርክ ነው የማለት አቅም እንደሌለህ ግን ማወቅ ይኖርብሃል።ረሱል ከፈቀዱ አበቃ!

ለምሳሌ ይሄ የረቢዕ መቀበያ የዒሽቅ ፕሮግራም ስርአት ያለውና ውብ ነው ማሻአላህ
الصلاة والسلام عليك ياسيدي وياسندي يارسول الله يا علم الهدى

#copy ✍️በኡስታዝ ሙሃመድ ዐረብ
📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
እኝህን ድንቅ ሐበሻዊ ሸይኽ ለመረዳት በቅድሚያ...
✦✦✦
✺ቢያንስ ቢያንስ በትንሹ...

➢ለመከራከር ሳይሆን ለማወቅ አእምሮን ዝግ ከማድረግ ይልቅ ዝግጁ ማድረግን ይጠይቃል።

➢እኔ ብቻ አውቃለሁ፣ እኔ ብቻ ትክክል የሚል የጀህልን ድሪቶ አውልቆ መጣል ያሻል።

ቲፎዞ ከሚሉት ከንቱ በሽታ መላቀቅ ያስፈልጋል። [በተለይ ይሄ ሊሰመርበት ይገባል።ምክንያቱም ዲነል'ኢስላም
ከነብዩ አደም እስከ የውመል ቂያማ አሸናፊነቱን ጠብቆ የሚዘልቀው በማስረጃና በማስረጃ ብቻ እንጂ በቲፎዞነት አይደለም። ቲፎዞነት ብቻውን በውጭ ሲታይ ግዙፍ የሚመስል ነገር ግን ግልብና ዘላቂነት የሌለው የገለባ ክምር ነው።]


➢ሰው ምን ይለኛል ከሚል እርባና ቢስ ምክንያት ለመውጣት የሚያስችል የሞራል ልእልና ያስፈልጋል።

⭕️[ይህች ነጥብ👆መንጋው በፈጠረው ቅጥፈት እንደ ገበታ ውኃ የሚዋልሉ ሰዎች ስላሉ ጥሩ ጥቆማ ትመስለኛለች😁]

✺ከፍ ሲል ደግሞ!

እኚህን ክንደ ብርቱ ሸይኽ ለመረዳት አራቱን መዝሃብ አብጠርጥሮ መረዳትን፣ ኩቱበ ሲታን እና አሉ የተባሉ የሐዲስ ኪታቦችን እስከ ሰነዳቸው መሸምደድን፣ ከባባድ የሉጛ[ወሳኝ የአረብኛ ቋንቋ] ኪታቦች መሐፈዝን፣ የሙጅተሂድነትን መስፈርት ማሟላትን እና ሌሎች ወሳኝ መመሪያዎችን ጥንቅቅ አድርጎ ማወቅን ይጠይቃል!

ሸይኽ ዓብዱሏህ አንድ ሸይኽ ነበሩ፣ እንደ ማንኛውም ተራ ሰው ናቸው ከሚል አባዜ ካልወጣህ ፈፅሞ ልትረዳቸው አትችልም።

📍 ወዳጄ! ምንም ማጋነን ሳያስፈልገው ሰውየው በጣም ከባድ ሸይኽ ናቸው!

⭕️በእርግጥ ይሄን ስል ፊታቸው በንዴት የሚቀላ፣ አይናቸው በብስጭት ደም የሚሞላ ኮስማናዎች አይጠፉም ይሆናል።😄

ስማቸውን ደጋግመን የምናነሳው ግን በአለም ዙሪያ ተሰራጭቶ የሙስሊሞችን ክብር አስጠብቃለሁ በሚል የሙስሊሞችን አንገት ላስዳፋውና ሙስሊሞችን ከጀርባ በጠላቶች እያስመታ ለሚገኘው መንጋ በጥልቅ ዒልማቸው ከባድ የራስ ምታት በመሆናቸውና ክብርም ስለሚገባቸው ጭምር ነው!!

በጣም የሚገርመው ኢትዮጵያዊ በመሆናቸውም "እንዴት አንድ የሀበሻ ሰው እኛ አረቦችን ይበልጠናል" በሚል በቅናት የሚነዱ አንዳንድ የውጭ ሰዎች ነበሩ፣ አሁንም አሉ። ነጂና!

አዎ! ለሐበሻ መሻይኾቻችን የሚገባቸውን ክብር ልንሰጣቸው ይገባል!
ምክንያቱም ክብሩ ለኛ ነውና!

✦✦✦
رحمكم الله سيدي مولاي! አል‐ፋቲሐ

#copy

📲 JOIN & SHARE ይበሉ!
https://www.tg-me.com/+XBeaC-I2mctmNjE8
2025/06/27 07:27:31
Back to Top
HTML Embed Code: