Telegram Web Link
መጎዳቴ ለበጎ ነበር
ትኩረቴን እንዳስተካክል ጠቅሞኛል።
ሁሉም ነገር በጊዜው ይቀየራል!!

አንተ በሙሉ አቅምህ እየለፋህ ነገሮች አንተ በፈለከው መንገድ ላይሄዱ ይችላሉ ፤ ሰዎች ላይረዱህ ፣ ሁኔታዎች ሊያናድዱህ ይችላሉ ፤ ራስህንም እየጠለኸውም ይሆናል።

ስለዚህ...ወዳጄ ከዚህ ስሜት መውጣት ከፈለግክ "የምችለውን ለመቀየር ሁሌም እጥራለው ፤ የማልችለውን ፈጣሪ እንዲቀይረው ለሱ አስረክባለው" ብለህ ለራስህ ቃል ግባ!! ከዛ ሳትጨነቅ በየቀኑ ካንተ የሚጠበቀውን ሁሉ አድርግ።
በፍፁም አልተውህም የሚሉኝ ሰዎች
እንደዛ እያሉ የተውኝን ሰዎች
ያስታውሱኛል!
ስታጠፋ ይቅርታ ጠይቅ እንጂ
ስህተትህን የሚያበረታታ ጥቅስ
አትፈልግ።
​​

⇘እናት ፍቅር ታስተምርና ከፍቅርም
   ጋር ይቅርታን ታስተምራለች......
   ምክንያቱም ማፍቀር ማለት ይቅር
   ማለትም ነውና።

@yefiker_bet11
እያንዳንዱ ስቃይ ትምህርት ይሰጠናል
እያንዳንዱ ትምህርት ደሞ እኛን ይለውጠናል
ህይወት እንደዚህ ናት።
ንዴትና ስሜትህን ስትቆጣጠር ደካማ ጎንህ ይደበቃል።
            🖤 ግን ለምን 🥺

የውስጤን ዘርግፌ,,,,,,
  እኔነቴን ብሰጥሽ
ምኞት፣ፍላጓቴን,,,,,,,,
  ገልጬ ብነግርሽ፣
ፍቅሬን አጣጥለሽ,,,,,,,
   ዝቅ አርገሽ ገመትሽው
መውደዴን አርቀሽ,,,,,,,,,
     ማፍቀሬን ጠላሽው።
        
መውደዴን,,,,,,,,አርክሰሽ፣
   ማድነቄ ,,,,,,,,አቅልለሽ፣
መቅረቤን,,,,,,,,አውግዘሽ፣
   እንዳልነበር,,,,,,,አርገሽ፣
ከጓዳና ወጠሽ,,,,,,,,,
    አጋልጠሽ ሰጠሽው፣
ማፋቀሬን,,,,,,,ገደልሽው።
አልበቀላቸውም ግን
እንዲፀፅታቸው አደርጋቸዋለሁ።
••ዝምብያለሁኝ••


ስም ላውጣልሽ ብዬ
ቃላትን ባሰላ
አጣሁልሽ ፊደል
ሚሄድ ካንቺ ጋራ
ፍቅሬ እንዳልልሽ
ከፍቅር አልፈሻል
ህይወቴ እንዳልልሽ
በጣም ያንስብሻል
ስም ልሰጥሽ ብዬ
ቃላት ስላጣሁኝ
በቃ የኔ ፍቅር
ዝም ብያለሁኝ።
◆━━━✎✦✎━━━◆
                
ሼር አደራ🙏
መልካም የእናቶች ቀን ይሁንልን!

በኮሜንት ላይ ሁላችሁም የእናታችሁን ስም
እየገለፃቹ መልካም ምኞት ተመኙ
😞 ደህና ነኝ

ደህና መሆን ማለት በስቃይ ላይ ስቃይ በህመም ላይ ህመም ማለት ከሆን እውነት ነው ደህና ነኝ ። ደህና መሆን ማለት እየሳቁ መስሎ ማልቀስ ተደብቆ ማንባት ከሆነ የምር ደህና ነኝ ። ደህና መሆን ማለት ሰው ሁሉ እያለ እየከፋኝ መደበቅ ከሆነ እውነት ስላቹ ደህና ነኝ ። ደህና መሆን ማለት ውስጥ እያለቀሰ ልብ እየደማ ከላይ መሳቅ ከሆነ እመን ደህና ነኝ ። 100 ሚሊዮኖች በሞሉበት ሀገር የልብን ሚጋራ የውስጥን ሚረዳ አንድ ሰው እንኳን ማጣት ደህና መሆን ከሆነ ደህና ነኝ ። ግን እውነት ደህና አደለሁም ደህና ነኝ ደህና ነኝ ያበዛሁት ቢያንስ ደህና አለመሆኔ ከገባቹህ ብዬ ነበር...... ግን ሚገባቹ አይመስለኝም
እስኪ እንደኔ ደህና የሆናችሁ ደህና ነኝ በሉ
               
                    . . .
#ፍቅርሽ_ነው . . .

            እሳት ነው ፍቅርሽ ልቤን አነደደው
         የንፋሱ ድምፅሽ ቀልቤን የወሰደው

     በውሁው ማእበልሽ ያመጣኝ አንሳፎ
          ብርሀን ያሳየኝ ጨለማውን አሳልፎ

          ፍቅርሽ ነው ደመና ያራሰኝ በዝናብ
        ጥማቴን አስታግሶ ያወጣኝ ከረሀብ

   አዎ ፍቅርሽ ነው እስትንፋሴ የልብ ምቴ
         ነብሴን ያቆየልኝ ፍቅርሽ ነው እናቴ፡፡

      ♥️
#እናቴ_ሁሌም_ወድሻለው! ♥️
ስንፍና ባንተ አያምርም

ወጣት ሆነህ ካልተለወጥክ መቼ ልትለወጥ ነው?አቅም ባለህ ሰዓት ካልሰራህ መቼ ልትሰራ ነው? ካልዘራህ እኮ አታጭድም

ከ 10 ዓመትም በኋላ ከሰው መጠበቅ ነው የምትፈልገው? ከራስህ አልፈህ የምትወዳቸውን ቤተሰቦችህን መቀየር አትፈልግም?እርግጠኛ ነኝ ትፈልጋለህ!

ስለዚህ ተነስ! የምትችለውን ሁሉ አድርግ! ቁጭ አትበል! የማይጠቅምህን ፕሮግራም አትይ! ጊዜ ቆሞ አይጠብቅም ንቃ ወዳጄ! ስንፍና ባንተ አያምርም
          ~_~_~ 'አፋልጉኝ' ~_~_~
.
ልቤ አካሉን ነስቶ  መኖር ከጀመረ ፣
በትዝታ አክናፍ  በሀሳብ ከበረረ ፣
አመታት ነጎዱ  ዘመን ተቆጠረ ፡፡
.
ስደተኛዉ  ልቤ ፣
ምፃተኛዉ  ልቤ ፣
እንደወጣ ቀርቷል  ቤት አልተመለሰም ፣
'ራቁቱን ነበር  ምንም አልለበሰም ፡፡
ከሀገሩ ቆንጆ  አንድም አልቀመሰ ፣
በፍቅር ነበልባል  ቅንጣት አልታመሰ ፣
እዛች ጋር አልሄደ  እዚህ አልደረሰ ፡፡
.
ይሄ ታማኝ ልቤን.. .. ..
ከአፍቃሪዉ አካል ጋር   ወስዶ ላገናኘዉ ፣
የልቡ ባለቤት   ወሮታ ከፋይ ነዉ ፡፡
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ባትለኝ
ንገሪኝ ካልክ ዛሬም እንደዛው ነኝ

የኔ ደህና መሆን ምን
#ያሳስብሀል
ፍቅር ነው እንዳልል
#ትተከኝ ሂደሃል😔
ደግሞ ድንገት መጠክ
#አዛኝ ያደርግሀል
እንዴት ነሽ እንዴት ነሽ ባትለኝ
ንገሪኝ ካልክ ግን
አንተን እያሰብኩኝ ዘመናት ቆጠርኩኝ
እኔነቴን ትቼ ባንተ ውስጥ አለሁኝ

አመታቶች አልፈው ዘመናት ቢመጣ
አንተን
#ከማፍቀር ውጭ ለውጥም አላመጣ
ህመሜን ብነግርህ መተህ
#ላታድነኝ
ድንገት እየመጣህ ምነው
#ባታደማኝ
🔥
እንደተለመደው ምርጥና አጓጊ የፍቅር ታሪክ ለመጀመር አስበናል vote በማድረግ አብራችሁን ሁኑ
Anonymous Poll
39%
ደስ ይላል
61%
ቶሎ ይጀምር
​​  ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 1

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by yohannis 

     
    ገና በልጅነቴ ነበር አባቴ ለሀብታም ጓደኛው እኔን እንደሚድረው ቃል የገባለት
እኔ ባባቴ ሀሳብ ባልስማማ አማራጭ አልነበረኝምና ባልፈልገውም ሁለተኛ ጀረጃ ትምህርቴን እንደጨረስኩ ያባቴ ጓደኛ ከዚህ በኃላ እንድማር ባለመፍቀዱና ካባቴ ጋር በመስማማታቸው እንዳገባ ተወሰነ .....
ድል ያለ ሰርግ ተደግሶ አለሜን ሳላይ አለምሽ ተብሎልኝ ተጋባን...ለመጀመሪያ ቀን ባሌ ቤት ስገባ የእስር ቤት ህይወት አንድ ብዬ መጀመሬን ለራሴ አሰብኩት...

መረረኝም ጣፈጠኝም አማራጭ አልነበረኝምና የቤት እመቤትነት ኑሮ ሳልፈልግ አንድ ብዬ ጀመርኩት.. ..
ቀናቶች ተቆጥረው ወራትን ወለዱ ባሌ ትልቅ ሰው ከመሆኑ ባሻገር ለኔ መልካም ለመሆንና ካለሀብት የሀዘን ኑሮ ሊያወጣኝ ይጥራል... እውነት ለመናገር ክፋ የሚባል አይነት ሰው አይደለም አንዳንዴ ፈገግ ብዬ ካየኝ በደስታ የሚሆነውን ነው የሚያጣው......
የሚጎድልብኝ አንድም ነገር የለም ባዶ የሚባል አይነት ኑሮ ልኑር እንጂ ማንኛዋም ሴት የምትመኘው አይነት የድሎት ህይወት ነው የምኖረው፡፡
ያልኩትንም ነገር በመፈፀም ሆነ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች በማሟላት ወደኋላ አይልም ግን እኔ ከአባቴ እኩያ ጋር በፍቅር አብሮ መክነፍ የማላስበው ሆነ...በቃ ጭራሽ የሚሆንልኝን ነገሮች አባት ለልጁ የሚያደረገው እንክብካቤ አድርጌ እስከመቁጠር ደርሻለሁ .....

ከባለቤቴ አቶ ሽፈራው ጋር እስካሁን አንሶላ አልተጋፈፍንም ለየብቻ ነው የምናድረው እንዲህ ፍላጎቴን ማሟላት ከዚህ ከባድ መስዕዋትነት ይጀምራል እኔ ፍቃደኛ ባለመሆኔና ለዚህ ነገር ዝግጁ እስከምሆን እንዲታገሰኝ ስነግረው ቅር ቢለውም ፍላጎቴን አልተቃወመም ለዛም ነው ጥሩ ሰው መሆኑን ባንደበቴ የምመሰክረው ..... ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ አውቃለሁ እንደሚወደኝ... አንድ ቀን አባቴ ሊጠይቀኝ ሲመጣ እኔ ሌላ ክፍል እንደምተኛ አውቆ በጣም ተበሳጨ..... ይህን አይነት ወርቅ ህይወት ሰጥቼሽ ምን ፈልገሽ ነው እንደዚህ የምትሆኚው አለኝ...... ያባቴ እንደዛ መበሳጨት አልገባኝም......

✎ ክፍል ሁለት  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
  
​​​​​​
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 2

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


    ባለቤቴ እንኳን የሱን ያህል አልተማረረብኝም ነገሮችን ገና መቀበል እንዳልቻልኩና ትንሽ ጊዜ እንዲታገሰኝ ለባሌ ነግሬው መስማማቱን ስነግረው....
እስከመቼ ነው የሚታገስሽ አመት ሊሞላችሁ ምን ቀረ ባይሆን ውለጂና ይሄን ሀብት የሚወርስ ልጅ ሰጥተሽ አስደስችው አለኝ እኔ ብወልድ ሀብቱ የሱ የሚሆን ይመስል ነገሮችን እንደማስተካክል ቃል ገብቼለት ከስንት ጭቅጭቅ በኃላ አሳመንኩት ባሌ ደውሎ የመጨረሻ ልጁ ነገ ከአውስትራሊያ እንደሚመጣ እና የሚያስፈልግ ነገር ካለ ለሰራተኞች ነግሬ እንዲያስተካክሉ በትህትና ጠየቀኝ ፡፡ ሁሉን እንደማሟላና እንዳያስብ ነግሬው አመስግኖኝ ስልኩ ተዘጋ.....ዛሬ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶኛል! በጠዋት ተነስቼ ቤቱ መስተካከልና አለመስተካከሉን ቼክ አደረኩ ፡፡
ምሳ ምን መዘጋጀት እንዳለበት ነግሬያቸው ተጣጥቤ ፀጉሬን ልሰራ ወደፀጉር ቤት ሄድኩ... ከፀጉር ቤት እንደጨረስኩ የምፈልጋቸውን ነገሮች ገዛዝቼ እቤት ስገባ ነበር ባየሁት ነገር ባለሁበት ደርቄ የቀረሁት... ሀይ እንዴት ነሽ ሄዋን አለኝ ደስ የሚል ቃና ባለው ጎርናና ድምፅ.. .. እ..እንኳን ደህና መጣህ  ማክቤል?? አሀ ማክቤል ብሎ ለሰላምታ እጁን ዘረጋልኝ.... ለደቂቃዎች እጁን ሳለቅ ፈዝዤ በቆምኩበት ቀረሁ... ዋው አባቴ ሚስቱ ቆንጆ እንደሆነች ቢነግረኝም እንደዚህ አልጠበኩሽም ነበር አለ እጁን ከጄ እያላቀቀ...
እ...አመሠግናለሁ እባክህ አረፍ በል መኝታ ቤት ገብቼ መጣሁ ብዬው የመሮጥ ያህል ካጠገቡ ጠፋሁ....
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተኝቼ የማክቤልን ውበት ከፎቶ ይበልጥ በአካል እንደሚያምርና የኔ ሳየው መደንገጥ እያሰብኩ ነበር ድንገት በሬ የተንኳኳው... ሄዋን... የባሌ ድምፅ ነበር...አቤት አልኩት በድንጋጤ ካልጋዬ እየተነሳው ...
ነይ እንጂ ምሳ እየጠበቅንሽ ነው አለኝና ወደታች ወረደ .... ሊያምርብኝ የሚችለውን ቀሚስ በመምረጥና እራሴን በማስዋብ ጊዜ ወሰደብ...  ልክ ወደ ታች ስወርድ ማክቤል ፊት ለፊት ነበር የተቀመጠው እግሬ ሲተሳሰር ታወቀኝ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ስላስቆየኃቹ ይቅርታ ብዬ ከባሌ አጠገብ ተቀመጥኩ....ባሌ ዛሬም እንደሁልጊዜው አምሮብሻል አለኝ እጄን እየሳመኝ ... ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንዲ ሲያረግ !
ደንግጬ እጄን ከእጁ መነጨኩትና የማክቤልን ገፅታ ተመለከትኩ ምንም አልመሠለውም.... ሚስትህ ቆንጆ ናት አባዬ ለራስህ ታውቅበታለህ አለው እየቀለደ.... ለምን እንደሆነ ባላውቅም በንግግሩ ተናደድኩ ብሽቅ አልኩ በውስጤ.... ምን ነካሽ ሄዋን አንቺ ያገባሽ ሴት ነሽ...አልኩ ለራሴ
ምሳ ተበልቶ እንዳለቀ ማክቤል ማረፍ እንደሚፈልግ ተናግሮ ወደክፍሉ ገባ ሳላስበው ባይኔ ተከተልኩት... ቆሞ ሁኔታዬን ሲመለከት የነበረው ባሌ ....
"ዛሬ ደስ ያለሽ ትመስያለሽ "....አለኝ የባሌ ድምፅ ነበር ከሀሳቤ ያነቃኝ ... ... ም ..ምምን ተገኝቶ ያው እንደበፊቱ ነኝ.... ል....ልግባና ልረፍ ትንሽ እራሴን አሞኛል አልኩት እየተርበተበትኩ ... ...
መድሀኒት ውሰጅ ምን አልባት ፀጉርሽን ስለተሰራሽ ይሆናል አለኝ ይሆናል ልግባና ልረፍበት ብዬው ወደክፍሌ ሄድኩ.....
አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ነኝ .... የማላውቀው የተዘበራረቀ ስሜት ይሰማኛል ደጋግሜ ማክቤልን አስብና ፈገግ እላለሁ.....


          ꧁༺༒༻꧂


✎ ክፍል ሶስት ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
   ​ 
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
#የኔ አዳም❤️

ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል😘
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ🤗
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም #ወዴት ነህ?🤷‍♀


           ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
2024/05/18 01:09:19
Back to Top
HTML Embed Code: