Telegram Web Link
.          ልቤን መልስልኝ

😐ልትሄድ ከሆነ ላይቀር መለየቱ😐
😔ቢበቃኝ ይሻላል ባንተ መጎዳቱ😔
🚶ቀልብህ ካላረፈ እግረኛ ሆነህ🚶
🏃መጓዝህ ካልቀረ ከእኔ መራቅህ🏃
💔ለምን አስፈለገ ልቤን መስረቅህ ?💔
​​​​​​.
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 9

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺



እሱዋን አመስግኜ ዘግቼ ማክ ጋር በድጋሚ ስደውል አነሳ የኔ ፍቅር ይቅርታ አሁን ነው የጨረስኩት ልደውልልሽ እያሰብኩ በአጋጣሚ እህቶቼ ደውለው እያወራው ነበር አለኝ ፍፁም መረጋጋት አይታይበትም እሺ ግን ሰላም አልመሰለኝም ድምፅህ ምን ተፈጠረ ለመስማት እየጓጓው ማሬ እየደረስኩ ነው ስመጣ እነግርሻለው ግን አታስቢ ምንም አልተፈጠረም አለኝ እኔም እስከሚደርስ በጉጉት እንደምጠብቀው ነግሬው ምሳ ምን እንደተሠራ ላይ ወደ ኪችን ሄድኩኝ ማክ ሲመጣ ግን በጣም ተረጋግቶል ምሳ እየበላን ሄዋኔ ከእኔ ጋር የትም ለመሄድ ዝግጁ ነሽ አለኝ አዎ የኔ ማር እስከአለም ጥግ ድረስ አልኩት ተነስቶ እቅፍ አርጎ ሳመኝ በቃ ወደ አውስትራሊያ እንሂድ እዛ በሰላም እንኖራለን ሁሉንም ወደ ኃላ ትተሽ ከእኔ ጋር ተጋብተን አዲስ ህይወት እንኖራለን አንቺን የሚመስሉ ቆንጆ ልጆች ትወልጅልኛለሽ ከልጆቻችን ጋር ደስተኛ ቤተሰብ መስርተን በሰላም እንኖራለን አለኝ ምንም እንኳን በማክ ሀሳብ ብስማማና ብደሰትም ያለናት ብቻውን ያሳደገኝን አባቴን ለሽፈራው አሳልፌ ልሰጠው አልፈቀድኩም በርግጥ አባቴ ለኔ ጥሩ አልነበረም አባት እያለኝ አባት እየናፈቀኝ ነው ያደኩት እሱ ለኔ መጥፎ ቢሆንም ለኔ አባቴ ነውና ክፋቱን በክፋት ልመልስለት አልፈልግም ምን አልባት የሰራው ወንጀል እንደሽፈራው አባባል አባቴን ክፋ ችግር ላይ የሚጥለው ከሆነ ፀፀቱን አልችለውም
አይሆንም ማክዬ አባቴን ጥዬ መሄድ አልችልም አልኩት ልመና በተቀላቀለበት አንደበት ተነጋግረን ቃል ገብተሽልኛል
አሁን ለምን ሀሳብሽን ቀየርሽ አባትሽ ምንም አይሆንም ከዚህ አገር ከወጣን አባቢ እንደማያገኚሽ ስለሚረዳ ምንም እንኳን አባትሽ ላይ የሆነ ማስረጃ አለኝ ቢልም ምንም አያደርገውም አትጨነቂ
ሄዊ በቃ ወስኚ አይዞሽ እስከዛሬ ህይወትሽን ያለደስታ ኖረሻል አሁን ጥሩ ህይወትን የምትኖሪበት ጊዜ ነው ጠንካራ ሁኚ ወደኋላ አትመልከች አለኝ እኔ ያባቴ ነገር ምንም ሊሆንልኝ አልቻለም ጊዜ ወስጄ እንዳስብበት ለምኜው ዛሬ አባቱ ምን እንዳለው ጠየኩት ሄዊ የኔ ውድ በቃ ዛሬ ሁሉንም ነገር ለመስማት ሞክሪ
ምንም የተለየ ነገር አላወራንም ያው ሚስቱን ከቤት ይዤበት ስወጣ ምን ሊያስብና ሊናገር እንደሚችል መገመት አይከብድም በቃ ትንሽ ተጣላን መጣው አለኝና ርዕስ ማስቀየር ጀመረ ያባቴና የሽፈራው ሚስጥር አስጨንቆኛል በምን መንገድ ማወቅ እንደምችል እያሰብኩ ነው ማክን ላለማስጨነቅና እንዳይከፋው ለማድረግ ደስተኛ ለመሆን እየጣርኩ ነው፡፡ያባቴ የመጨረሻው ንግግርና የሽፈራሁ ጋር ሊኖረው የሚችለው ሚስጥር ሰላሜን ነስቶኛል ማክ አባቱ እያፈላለገኝ ስለሆነ ከቤት እንዳልወጣ አስጠንቅቆኛል ግን ያባቴን ሚስጥር የሚያውቅ ሌላ ተጨማሪ ሰው ማን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ጀመርኩ
ማወቅ አለብኝ ከዛ በኋላ አባቴን ከችግሩ የሚወጣበትን መንገድ አመቻችቼ ከማክ ጋር አዲስ ህይወት መስርቼ በሰላም መኖር ይሄን ካላደረኩ ግን ደስተኛ ሆኜ መኖር እንደማልችል አውቃለሁ አንድ ቀን ጠዋት አዙ ጋር ስደውል አባቴ ከሽፈራው ጋር ሲጨቃጨቁ ቆይተው አሁን እንደወጣ ነገረችኝ የተነጋገሩትን ነገር ሰምታ እንደሆነና እንዳልሆነ ስጠይቃት ሽፈራሁ በገዛ ልጅህ አማካኝነት ወቀመቅ እንድትወርድ ነው የማደርግህ ሲለው እንደነበርና አባቴ በጣም  ሲለምነው እንደነበር ነገረችኝ ሌላ ተጨማሪ ነገር ሰምታ እንደሆነ ስጠይቃት አይ ይኼን ብቻ ነው የሰማሁት አለችኝ ከኔ ጋር ሊያገናኘው የሚችለው ነገር ምንድነው ለምንስ በኔ ያስፈራራዋል በቃ በጭንቀት እራሴ ሊፈነዳ ደረሰ ለማክ ነገርኩት፡፡
ማክ ምንም አልተገረመም ነበር ምነው ማክ የምታውቀው ነገር አለ አልኩት በጥያቄ አስተያየት እያየሁት እ.....


        

✎ ክፍል አስር ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
       
​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 10

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺



አይ የለም ምን ይኖራል በቃ ይኼ ነገር ስለሰለቸኝ ነው አለኝ እኔ ግን ላምነው አልቻልኩም ምክንያቱም አባቱ ጋር ደርሶ ከመጣ በኃላ ወሬው ሁሉ ይችን አገር ለቀን እንውጣ ሆኗል እንዴት እንዳደኩና ማን ስለእናቴ የሚያውቀው ነገር ካለም በተደጋጋሚ እየጠየቀኝ ነው፡፡ ማክ አላመንኩም ባለፈው ከአባትህ ጋር ያወራችሁትን ንገረኝ ምንድነው ከእኔ የምትደብቀው ነገር አልኩት? ሄዊ እኔ ከአንቺ የምደብቀው ነገር የለም ምንም አልደበኩሽም አለኝ ባላምነውም እሺ በቃ ተወው አልኩት ግን ባባቴ እና ባባቱ መካከል ያለውን ሚስጥር እንድደርስበትና ሊነግረኝ እንደማይፈልግ ሁኔታው ያስታውቅ ነበር፡፡ እኔም ባባቴ ሚስጥርና በሁኔታቸው እዚህ መሆን ደስታ አጥቻለሁ ቀን ከሌሊት የማስበው ይኼ ሆኗል ማክ እኔ ወደቀድሞ ደስታዬና ማንነቴ እንድመለስ የማያደርገው ነገር የለም ከጎኔ በመሆኑ እድለኛ ነኝ ወደኋላ ተመልሼ አስተዳደጌንና አባቴ ለኔ የነበረው አመለካከት ማሰብ ጀመርኩ አባቴ ለኔ ግድ የለሽና በራሴ ጥረት ጎበዝ ተማሪ እንደነበርኩ ከማስታወስ ውጪ አዲስ ነገር ማስታወስ አልቻልኩም ከቤት ከወጣን ወራትን አሳልፈናል ማክም የራሱን ስራ እዚህ ጀምሯል እኔና ማክ አንድ ላይ ብንኖርም እስካሁን በመካከላችን የተፈጠረ አንድም ነገር የለም ግን አንዳችን በአንዳችን ደስተኞች ነን አንድ ቀን ማክ ሳላስበው የንጋባ ጥያቄ አቀረበልኝ ጥያቄው ቢያስደስትም ከአባቱ ጋር የፍቺ ውል አልፈፀምኩም እንዴት እንጋባለን የሚለው ነገር አስጨነቀኝ ማክ የፍቺ ጥያቄ እንዳቀርብ ነገረኝ እንደዚህ ካደረኩ አባቴን አቶ ሽፈራው እንደማይተው ለማክ ነገርኩት
መጀመሪያ ባባቴ ጉዳይ ላይ መፍትሄ ማግኘት እንዳለብን ስነግረው ሀሳቤን ባይወደውም ተስማማ የማክ በዚህ ጉዳይ ላይ ግድ የለሽ መሆን ይበልጥ የሚያውቀው ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነኝ የአባቴ ሁኔታ አስጨንቆኛል እንዴት መፍትሄ እንደማገኝ አሰብኩኝ ቀናቶች ተቆጥረው ሳምንታትን ወለዱ አንድ ቀን ሰኞ ማክን ወደስራ ከሸኘሁ በኋላ ወደ አባቴ ሰፈር ሄጄ የእናቴን የቅርብ ጓደኛ አግኝቼ እናቴ ከመሞቷ በፊት ስለአባቴ ያጫወተቻቸው ነገር ካለ ጠየኳቸው
የናቴ ጓደኛ በጣም ነበር በጥያቄ የደነገጡት ምንም እንደማያውቁና በባሏና በሷ መካከል ያለ ሚስጥር ነግራቸው እንደማታውቅና ለምን እንደፈለኩት ጠየቀችኝ ዝም ብዬ ስለአባቴ ማወቅ ፈልጌ እንደሆነና ካስታወሱ እንዲደውሉልኝ ቁጥሬን ሰጥቻቸው ካለ ምንም መፍትሔ ወደቤቴ ተመለስኩ በማግስቱ ጠዋት በማላውቀው ቁጥር የአባትሽን ሚስጥር ከሆነ የምትፈልጊው በዚህ አድራሻ ነይና እንነግርሻለን የሚል የፅሑፍ መልዕክት ነበር ደጋግሜ ስልኩን ስሞክር አይነሳም ቴክስትም ባደርግ አይመልስም የማደርገው ነገር ጨነቀኝ ለማክ ብነግረው ለምን እንደዚህ አደረግሽ ብሎ ይጣላኛል ደሞ ብሄድ እራሴን አደጋ ላይ የምጥል ስለመሰለኝ ፈራሁ በዚህ ውጥረት መሀል እያለሁ የናቴ ጓደኛ ከዚህ ሚስጥር ጋ ምን እንደሚያያይዛቸውና ድንጋጥያቸው ትዝ አለኝ ደግሜ እንዳላገኛቸውም ፈራሁ በዚህ ሁኔታ እስከመቼ እንደምዘልቅ ሀሳብ ሆነብኝ የማክ ሁሉን እረስተን የንጋባ ጥያቄው አቶ ሽፈራው አባቴና የናቴ ጓደኛ ወይዘሮ እልፍነሽ ግንኙነት ሀሳብ ሆኖብኛል
ጠዋት ቁርስ እየበላን ማክ ዛሬ አባትህን ፊት ለፊት ማናገር ወስኛለሁ የመጣው ይምጣ መናገር አለብኝ ይሄ ህይወት ሰልችቶኛል አልኩት ማክ እንደማይሆንና እሱ በራሱ መንገድ አባቱ ጋር ያለውን ማስረጃ የሚያገኝበትን መንገድ እየፈለገ መሆኑንና ትንሽ ጊዜ እንድታገሰው ነግሮኝ ወደ ስራ ሄደ እኔ ግን ከዚህ ሚስጥር ጀርባ ያለውን ነገር ከዚህ በላይ ታግሶ የመጠበቅ ትግስቴ አልቋል እስከመቼ እንደምታገስ ባላውቅም ትንሽ ጊዜ እንድታገስ ለራሴ አሳመንኩት ስራ መስራት እንዳለብኝና ቤት መቀመጥ እንደሰለቸኝ ለማክ ነግሬው ከሱ ጋር ስራ ጀምሬአለሁ ትንሽ ቢሆንም ከቤት እየወጣው ስራ ላይ መዋሌ ጭንቀቴን ቀንሶልኛል ከማክ ጋር ያለን ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና ተጋብተን እንደማንኛውም ጥንዶች ህይወትን የመኖር ፍላጎታችን እየጨመረ ነው፡፡
ማክና አባቱ ጭራሽ ተቆራርጠዋል አባቱም እኔን መፈለጉን አቁሞ አባቴ ተረኛ ፈላጊዬ ሆኗል ከስራ ስገባም ሆነ ስወጣ ከማክ ውጪ አልንቀሳቀስም የትም ስንሄድ አብረን ነው፡፡ አንዳንዴ አዙ ጋር እየደወልኩ ያለውን ሁኔታ እከታተላለው አባቴና አቶ ሽፈራው ሁሌም ይገናኛሉ ሁሌም ይጨቃጨቃሉ፡፡ አንድ ቀን ስደውልላት አባቴ እኔን አግቶ አሳምኖ ወደቤቴ ካልመለሰልኝ ሲዲውን ለኔ እንደሚሰጠኝና በኔ በልጁ እጅ እንደሚጠፋ እንደነገረው ነገረችኝ በጭንቀት ልፈነዳ ምንም አልቀረኝም እየሮጥኩ የማክ ቢሮ ሳላንኳኳ ዘልዬ ስገባ ስብሰባ ላይ ነበር ይቅርታ ጠይቄ ተመልሼ ስወጣ ማክ ተከትሎኝ ወጣና የሆንኩትን ጠየቀኝ ሲጨርስ ላገኘው እንደምፈልግና ማውራት እንዳለብን ነግሬው ወደ ቢሮዬ ተመለስኩ። ምንም መረጋጋት አልቻልኩም ነበር የማክ ይበልጥ ያባቴ ነገር እና ከኔ ጋር የሚያያይዘው ነገር ሰላም ነሳኝ ተረጋግቼ መቀመጥ አልቻልኩም ድንገት ከወራት በፊት የተላከልኝን ቴክስት አስታወስኩ ስልኬን አንስቼ ቁጥሩን መፈለግ ጀመርኩ መልዕክቱ ስልኬ ላይ የለም አጥፍቼው እንደሆነ ለማስታወስ ሞከርኩ ግን አላጠፋሁትም ማን ሊያጠፋው ይችላል?? ማክ እንኳን ስለዚህ የስልክ መልዕክት የሚያውቀው ነገር የለም እኔም እንዳላጠፋሁት እርግጠኛ ነኝ
ታዲያ ማን ሊያጠፋው ይችላል?.....


       
✎ ክፍል አስራ አንድ ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።

••●◉Join us share
​​​​.
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 11

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


ምንም ማስታወስ አልቻልኩም የማስታውሰውም ነገር የለም ምክንያቱም እኔ እንዳላጠፋሁት እርግጠኛ ስለሆንኩ
በዚህ ሀሳብ ላይ ሆኜ ማክ በር አንኳክቶ ገባ ማሬ ምን ሆነሽ ነው ሰላም አይደለሽ አለኝ አዙ የነገረችኝን ቴክስቱን ማን እንዳጠፋው ሳላውቅ ልነግረው አልፈለኩም እ..... ..ደና አይደለሁም ማክ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላውቅም የደበቅኩህ ነገር ነበር አልኩ እየተንተባተብኩ ንገሪኝ ምን ደብቀሽኝ ነበር አለ በተጨነቀ አይነት ስሜት እያየኝ ማክዬ እንዳትቆጣኝ አልኩት አልቆጣም ንገሪኝ ምን ተፈጠረ ምንድነው የደበቅሽኝ
ማክ ከየት እንደምጀምርልህ አላውቅም ጥፋት ይሁን መልካም ላንተ ሳልነግርህ ከወራት በፊት የናቴ ጓደኛ ጋር ሄጄ ነገር
ብዬ ቀና ብዬ አየሁት ቀጥይ በሚል አስተያየት ሲመለከተኝ ከናቴ ጓደኛ ጋር እንዳወራንና በማግስቱ በማላውቀው ቁጥር ቴክስት እንደተላከልኝ አሁን    ቴክስቱን ላገኘው እንዳልቻልኩም ጭምር ነገርኩት ምንም ባለመገረም ስሜት ነበር የሚያዳምጠኝ ስጨርስ ምን እንደሚለኝ ለመስማት በጉጉት እጠብቀው ጀመር
ሄዊዬ ቆይ ይሄ ነገር ለምን አይቀርብሽም ለምን አዲስ ህይወት "ሀ" ብለን አንጀምርም? በርግጥ የእናትሽ ጓደኛ ጋር እንደሄድሽ አላውቅም ግን ሌላ ተጨማሪ ቴክስት ካንድ አይነት ቁጥር ተልኮልሽ ነበር አንቺ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ነበርሽ በወቅቱ ከፍቼ ሳየው አባቴ አንቺን የሚያገኝበት አጋጣሚ እየፈለገ እንደሆነ ስለተረዳው አጠፋሁት ቁጥርሽን ከየት እንዳመጡ ልጠይቅሽ ነበር ግን የባስ እንዳላስጨንቅሽ ስላሰብኩ ተውኩት
አንቺም ከዛ በኋላ የረሳሽው መስሎኝ ነበር ስላልጠየቅሽ እና አሁን በምን በምን ትዝ አለሽ አለኝ በውስጤ ተመስገን ማክ ከኔ ጋር ነው ምንም አልዋሸኝም አልኩኝ ለደቂቃ ምንም ሳልናገር ቆየሁ በያ ንገሪኝ አለኝ ማክ ምንድን ነበር ሁለተኛው መልዕክት አልኩት "ይሄ የመጨረሻ እድልሽ ነው ያባትሽን ሚስጥር ማወቅ ከፈለግሽ በላክንልሽ አድራሻ ጠዋት 4 ሰዓት ነይ" ነበር የሚለው ይሄን መልዕክ ብታይ ኖሮ በርግጠኝነት ሄደሽ እራስሽን አባቴ መዳፍ ላይ ትጥይ ነበር አለኝ ማክ መሄድ ነበረብኝ ሁኔታው ከምታስበው በላይ አሳሳቢ ነው ዛሬ አዙ ጋር ደውዬ ሚስጥሩን የያዘው ፋይል ሲዲ እንደሆነ ነግራኛለች ይሄ ሲዲ ደግሞ እኔ እጅ ከገባ አባቴን እኔ ራሴ እንደሆንኩ የምበቀለው ሲያወሩ ሰምታለች፡፡ እኔ እዚህ ሲዲ ውስጥ ምን እንዳለ ሳላውቅ እንቅልፍ አይወስደኝም ምንድነው ሚስጥሩ እራሴ ሊፈነዳ ነው እባክህ አግዘኝ የኔ ፍቅር አልኩት ማክ ከተቀመጠበት ተነስቶ አቅፎ ያፅናናኝ ጀመር በቃ መፍትሄ አናጣም ትንሽ ብቻ ታገሺ እራስሽን ለማረጋጋት ሞክሪ ምን ይመስልሻል ትንሽ እንድትረጋጊ ሁኔታዎችንም ተረጋግተን ለማሰብ አንድ ሳምንት ወጣ ብለን ብንመጣ አለኝ ሀሳቡ ጥሩ መስሎ ታየኝ ወዴት እንሂድ አልኩት አሁንም ግራ እንደተጋባሁ ነኝ ዱባይ ደርሰን እንምጣ እስከዛ ነገሮችን በደንብ የምናስብበት ጊዜ ይኖረናል በዛውም ካለንበት ጭንቀት ትንሽ እናርፋለን አለኝ በሀሳቡ ተስማማሁ ከሳምንት በኃላ ዱባይ ሄደን በጣም አሪፍ የሚባል ጊዜ እያሳለፍን ነው ለጊዜውም ቢሆን ሁሉንም ነገር እረስቼዋለሁ ማክ ወደበፊቱ ማንነቴ በመመለሴ በጣም ደስተኛ ሆኗል ድንገት አየሽ አይደል ሁሉንም ነገር  ጥለን ወደ አውስትራሊያ ብንሄድ ሁሉን ነገር መርሳት እንደምንችል አለኝ ማክዬ ለጊዜው መርሳት ስለፈለኩና አንተም ማስከፋት ስላልፈለኩ እንጂ እስከመጨረሻው ማንነቴንና ያባቴን የተደበቀ ማንነት እረስቼ መኖር አልችልም
በተለይ ጉዳዩ ከኔ ጋር እንደሚያያዝ ካወቅኩ በኃላ ይበልጥ የማወቅ ፍላጎቴ ጨምሯል ይህን ጉዳይ እልባት ካገኘሁለት በኃላ የፈለክበት እንሄዳለን አልኩት ማክ ይሄን ሲሰማ ሀሳቤን እንደማልቀይር ስላወቀ በቃ እሺ እኔም ይሄ ነገር ሰላም እየነሳኝ ነው ስለዚህ ወደኢትዮጵያ ስንመለስ አብረን መፍትሄ እንፈልጋለን ግን አንድ ነገር ቃል ትገቢልኛለሽ አለኝ ምንድነው ማክ የፈለግከውን አልኩት በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮኝ እንደሆነ ሲነግረኝ በመደሰት
ያባትሽ ሚስጥር ምንም ሆነ ምን ጠንካራ እንደምትሆኚና ምንም ለማድረግ እንደማትሞክሪ እንደዛ ሲለኝ ማክ የሆነ የምታውቀው ነገር እንዳለ ይሰማኛል አልኩት ሄዊዬ እንደዛ ማለቴ አይደለም ግን ያው ከሁኔታዎች አንፃር ጉዳዩ እንደሚከብድ በመጠርጠር ነው ብሎ አቅፎ ሳመኝ ነገሩ ባይዋጥልኝም ከማመን ውጪ አማራጭ አልነበረኝም
የዱባይ ቆይታችንን ጨርሰን እንደተመለስን.......


          ꧁༺༒༻꧂


✎ ክፍል አስራ ሁለት ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
   ​ 
━━━━━━━✦✿✦━━━━━
⇘የኔ ሱስ💘

እንዴትና ለምን እንዳፈቀርኩሽ😍 አላውቅም
ብቻ ሳላስበው ባልጠበቅኩት መንገድ
ልቤ ውስጥ ገባሽና ህይወቴን ብሩህ
አደረግሻት ።ድሮ ድሮ ፍቅር አለ ሲሉኝ  ውሸት ነው  እል ነበር ፤ አሁን ግን ስለመኖሩ አልጠራጠርም💞በህይወቴ ብዙ ስጦታና ገጠመኞ አይቻለሁ አንቺ ከሁሉም የገዘፈ ስጦታዬና አስደሳች ገጠመኘ ነሽ፤እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ❤️አፈቅርሻለሁ።
ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.
ምዕራፍ 2
                  ♥️ ክፍል 12

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


በሁለተኛው ቀን ለአዙ ደወልኩላት ባባቴና በሽፈራው መሀል ምንም አዲስ ነገር እንደሌለና ግን ሽፈራውን ለማግኘት አንድ ሴትዮ መጥተው እንደነበረና ስለኔ ስም ሲያነሱ ገና ሽፈራው አዙ እንድትሰማ ስላልፈለገ እንዳስወጣትና ብቻቸውን ለእረጅም ሰዓት አብረው እንደቆዩና እንደሄዱ እሷ ምንም መስማት እንዳልቻለች በር ላይ ሆነው ግን በቃ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ አሳውቅሀለሁ ሲሉት ብቻ እንደሰማች ነገረችኝ መቼ እንደነበር የተገናኙትና ደግመው መጥተው እንደሆነ ስጠይቃት ደግመው እንዳልመጡና እንዳሉትም ከሁለት ቀን በኃላ ሹፌሩ አንድ ትንሽ ፖስታ አምጥቶ ሲሰጠው እንዳየችው ሹፌሩን ስጠይቀው ከሁለት ቀን በፊት የመጡት ሴትዩ እንደሰጡት ነገረችኝ አዙ ሲዲው እንዳይሆን ታዲያ ያስቀመጠበትን ወይ ደሞ ምን እንዳረገው አላየሽም ስላት ምን አውቄ አለሜ ጋሽዬ ጥንቁቅ እንደሆኑ እያወቅሽ አለችኝ ስልኩን ከዘጋው በኃላ የናቴ ጓደኛና ሽፈራው ምን እያደረጉ ነው
ምኑንስ ነው በሁለት ቀን ውስጥ የሚያሳውቁት ስለምንስ ነው ረጅም ሰዓት ወስደው ሲያወሩ የነበሩት ሹፌሩስ ለሽፈራው ምንድነው አምጥቶ የሰጠው?
በነዚህ ሀሳቦች ተጠምጄ እያለሁ ድንገት ስልኬ ጠራ የእናቴ ጓደኛ ነበሩ ልቤ ሲመታ ይታወቀኛል ስልኩን እያየሁት ለማንሳት ጊዜ ወሰደብኝ ላንሳው አላንሳው በሚል ሀሳብ ተወጥሬ ስልኬን አይን አይኑን እያየሁት ስልኩ ዘጋ በድጋሚ ሲጠራ እንደምንም ራሴን ተቆጣጥሬ ሄ...ሄሎ አልኩኝ እየተንተባተብኩ ሄዋኔ እንዴት ዋልሽ አሉኝ ምላሽ አልነበረኝም ምን ሊሉኝ ነው ጥያቄ ውስጤ ተወጥሯል ሄሎ ሄዋኔ አሉኝ ደግመው አ....አቤት እማዋ አልኳቸው በተቆራረጠ ድምፅ ስንጠራቸው እማዋ እያልን ነው፡፡ ምነው ደህናም አደለሽ አሉኝ ...እንደምንም ራሴን ለማጠንከር እየሞከርኩ ደና ነኝ እማዋ እንዴት ነዎት አልኳቸው ምነው ጠፋሽ ባለፈው ከመጣሽ በኃላ ድምፅሽ ጠፋ እኔም እደውላለሁ እያልኩ ያው እንደምታውቂው የልጆች ነገር ከሰሞኑ ብደውልም ስልክሽ አይሰራም አሉኝ የማዋ ባለቤት የሞቱት ከናቴ ጋር በተቀራራቢ ወቅት ነበር እንደውም አስታውሳለሁ ያኔ የ9 አመት ልጅ ነበርኩ
የማዋ ባል ባልታወቀ ሰው ተገድሎ ነው የሞተው ያው ዱርዬዎች ለመዝረፍ ብለው ገድለውት ይሆናል በሚል ሰበብ ነገሩ ተረሳ እንጂ እናቴና እኔ ለቅሶ ቤት ደርሰን ስንመጣ አባቴ ከናቴ ጋር በጣም እንደተጣሉ አስታውሳለሁ ምክንያቱን እረስቼዋለሁ ኧረ እንደውም በግርግር አባቴ አንድ ጥፊ አቅምሶኛል ከዛ የማዋ ባል ከሞተ ሳምንት ሳይሞላው እናቴ በድንገት አረፈች፡፡ ይገባኛል እማዋ አይመችም አልኳቸው አዎ ልጄ አይመችም አሉ ስለኑሮ ምናምን ሲጠይቁኝ ቆይተው በመጨረሻም እናቴ ስላባቴ የነገረቻቸው ነገር ካለ ካስታወሱ እንዲደውሉልኝ እንደነገርኳቸውና ትዝ ያላቸው ነገር ስላለ ለዛም ሲሉ እንደወሉልኝ ነገሩኝ ስለሳቸው ምንም ያላወቀ በመምሰል ውይ እማዋዬ ምን አስታወሱ አልኳቸው ለመስማት የጓጓሁ እንዲመስል አድርጌ አይ ሄዋኔ በስልክ አይሆንም እንደው ከተመቸሽ ወደከሰዓት ብትመጪና ያቺ የምትወጃትን ሽሮ ስርቼልሽ ቡናም አብረን ጠጥተን ተጫውተሽ ትሄጃለሽ አሉኝ ምን አይነት ወጥመድ እንደተዘጋጀልኝ ባላውቅም ግን አንድ ነገር እንዳሰቡ ግልፅ ነው፡፡ ስልኩን ከዘጋው በኃላ ማክ ጋር ሄጄ ሁሉንም ነገር ነገርኩት ልትሄጂ አስበሽ እንዳይሆን ብቻ አለኝ...ማክዬ አላሰብኩም ግን ሹፌሩ ለአባትህ የሰጠው ሲዲው እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ ስለዚህ ማግኘት አለብን አልኩት ማክ እንድረጋጋ እየለመነኝ እሱ በየትኛውም መንገድ ሲዲውን እንደሚያመጣውና እስከዛ ምንም እንዳላደርግ አስጠነቀቀኝ ማክን በደስታ አቅፌ ሳምኩት ከስራ ወጥተን ውጪ ትንሽ ዘና ብለን ወደቤት ከተመለስን በኃላ በሀሳብ ብወጠርም ደስ የሚል ቀን አሳለፍን፡፡ እማዋ ደጋግመው ደውለው ነበር እንደነቃውባቸው እንዳያውቁ ትንሽ ራሴን ስላመመኝ ሰሞኑን ከስራ መልስ እንደምመጣ አሳውቂያቸዋለሁ ማክ አንድ ሀሳብ እንደመጣለት ነገረኝ ምን ስለው ሁሉም የቤት ሰራተኞች በኛ ሳይድ ስለነበሩ በተለይ ላባቱ በጣም ቅርብ የሆነው ሹፌሩ ብር ሰጥቶ ፋይሉን እንዲሰርቅ ማድረግ ምክንያቱም እሱ ስለሆነ ካባቴ ጋር ብዙን ጊዜ የሚያሳልፈው ብዙ ነገር ያውቃል አለኝ
ማክ የፈለገ ቅርብ ቢሆን ትልቅ ሚስጥር ላያውቅ ይችላል አልኩት እኛ እንሞክር ካልሆነ ከወር በኃላ ወንድሜ ስለሚመጣ ሁሉንም ነገር ስለነገርኩት እሱ ይረዳናል አለኝ የወንድሙ ሀሳብ ጥሩ ቢሆንም ወር ሙሉ እሱ እስከሚመጣ የሚያቆይ ትግስት እንደማይኖረኝ ስለማውቅ በማክ በመጀመሪያ ሀሳብ ተስማምተን ማክ ላባቱ ሹፌር ደውሎለት በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ......
​​  ሄ ዋ ን 🌺
            :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 13

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


ማክ ለአባቱ ሹፌር ደውሎለት በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ እስኪነጋ እንቅልፍ ባይኔ አልዞረም ጠዋት ቁርስ ላይ ለማክ አባቴ በጣም እንደናፈቀኝና ልደውልለት እንዳሰብኩኝ ስነግረው ጥሩ ሀሳብ አለመሆኑን ነገሮኝ ባልደውልለት የተሻለ እንደሆነ አስጠነቀቀኝ ቢሮ ከገባሁ በኃላ ግን ደጋግሜ አባቴን ማሰብ አላቆምኩም
የመጣውን ለመቀበል ራሴን አሳምኜ አባቴ ጋር ደወልኩ ገና ድምፄን ሲሰማ ነበር አንቺ መድረሻ ቢስ ምን ይሁን ብለሽ ደወልሽ አታገኘኝም ነው ... እ ... እንደናቅሽኝ እየነገርሽኝ ነው? ይኼውልሽ እናትሽ የገባችበት ጉድጓድ ብትገቢ አታመልጭኝም መድረሻ ቢስ ሰላም እንደነሳሽኝ እንደዶሮ አንቄ ለሽፈራው ካልሰጠሁሽ ወንድ አይደለሁም አለኝ
ይሄንን ሁላ ሲያወርድብኝ አንድም ቃል አልተናገርኩም ብቻ ባይሆን ድምፁን ስለሠማው ትንሽም ቢሆን ደስ ብሎኛል ወይ አባ ምን ብትደብቅ ነው ሰላም አተህ ሰላም የነሳኸኝ አልኩ ለራሴ ስልኩን ዘግቼ ማክን ከሹፌሩ ጋር ሲገናኙ አብረን ብናገኘውስ ብዬ ልጠይቀው ስላሰብኩ ወደሱ ሄድኩ ማክ ቢሮ አልነበረም... ፀሀፊውን ስጠይቃት ተቻኩሎ እንደወጣ ነገረችኝ ደወልኩለት ስልኩን አያነሳም ሱማክ የትም ቢሄድ ለኔ ሳይነግረኝ አይሄድም ስልኩን አለማንሳቱ ይበልጥ አስጨነቀኝ ተረጋግቼ መቀመጥ አልቻልኩም ደጋግሜ ብደውልም አይነሳም... በጭንቀት ራሴ ተወጠረ ማክ ከቢሮ ከወጣ 4 ሰዓታት ተቆጠሩ በዛ ሁኔታ ቢሮ ምንም ስለማልሰራ ወደቤት ሄድኩ... ለተጨማሪ 1 ሰዓት ጠበኩ ምንም የለም የማክ ስልክ አይነሳም... በመጨረሻም ሁሉም የማክ ጓደኞች ጋር ደወልኩ ከማንም ጋር አልተገናኘም መልሶ ካልደወለ እንድደውልላቸውና ለፖሊስ እንደምናመለክት ነገሩኝ ሁለቱ ጓደኞቹ እንደሚመጡ ነግረውኝ ስልኩን እንደዘጋሁ ስልኬ ጠራ ማክ ነበር
ማክ የኔ ፍቅር የት ሆነህ ነው ለምንድነው የማታነሳው በጭንቀት ልትገድለኝ አስበህ ነው... የጥያቄ መዓት አደራረብኩበት...
የኔ ቆንጆ ስላስጨነኩሽ ይቅርታ እየመጣሁ ነው አለኝ በደከመ ድምፅ ማክ የት ነህ የሆንከው ነገር አለ ድምፅህ ልክ አይደለም ምንድነው የተፈጠረው ያለህበት ልምጣ አልኩት እያለቀስኩ አያስፈልግም ማሬ እየደረስኩኝ ነው ትንሽ ታገሺኝ አለኝ ልቤ በሀይል ይመታል በጣም እያለቀስኩ ነው ምን እንደማደርግ ግራ ተጋብቼ ግቢ ውስጥ ወዲያና ወዲህ እያልኩ የማክን መምጣት መጠባበቅ ጀመርኩ ከግማሽ ሰዓት በኃላ የመኪና ድምፅ ስሰማ እየሮጥኩ ወደበሩ ስሄድ የማክ ጓደኞች ነበሩ ... አዲስ ነገር ካለ ሲጠይቁኝ የሆነውን ነግሬያቸው ማክን አብረን መጠበቅ ጀመርን ትንሽ ቆይቶ ሌላ የመኪና ድምፅ ስንሰማ ሁላችንም ወጣን ዘበኛው በሩን ሲከፍተው መኪናው ውጪ እንደቆመ ነው ማንም ጋቢና የለም እየሮጥኩ ወጥቼ ሳይ ማክ በደም ተነክሮ ከኃላ ተኝቷል እየጮህኩ ጓደኞቹን ለርዳታ ጠራኻቸው ወደሆስፒታል ንዳው ብዬ አንዱ ጓደኛው ላይ ጮህኩኝ... ማክ በደከመ ድምፅ ደህና ነኝ የኔ ፍቅር አለኝ ማክ ማነው እንደዚህ አድርጎ አምጥቶ የጣለህ ማክ ክፉ ሰው ነው አንተ ላይ እንደዚህ ያደረገው እያልኩ ያለማቋረጥ አለቅሳለሁ እሱ እንደዛ ሆኖ እኔን ለማፅናናት ይሞክራል ጓደኞቹም እንድረጋጋ እየለመኑኝ ሆስፒታል ደረስን ህክምና ተደረገለት የማክ እጁ ላይ ቅጥቅጥና ግንባሩ ላይ ጉዳት ከመድረሱ ውጭ የከፋ ነገር እንደሌለውና ግንባሩ መሰፋት እንዳለበት ዶክተሩ ነግሮኝ ወጣ
ከሰዓታት በኃላ ወደቤታችን ተመለስን የማክ ጓደኞች ተሰናብተውን ከሄዱ በኃላ ማክን በጥያቄ አጣድፈው ጀመር... ሄዊ የኔ ቆንጆ ተረጋጊ አባቴ ነው በቃ እንደዚህ ያደረገው ሹፌሩ ከኛ ጋር መሆን አልቻለም ከኔ ጋር ቀጠሮ እንዳለው ላባቴ ነግሮት ነው አባቴ ከሱ ምን እንደፈለግን አውቋል በር ላይ ጥሎኝም የሄደው ሹፌር  የሱ ነው አሁን መኖሪያችንን አውቋል መጠንቀቅ አለብሽ ግን አንቺን በአካል ማግኘት ነው የሚፈልገው ይሄን ደግሞ እኔ አልፈቅድም አለኝ እና እንዴት ልጁን ጨክኖ እንደዚህ ያደርጋል በጣም ተናዶብኛል ሰዎቹ ሲደበድቡኝ እንኳን ለማየት አልደፈረም ውጪ ቆሞ ነበር አንቺን እንድመልስሽ ለማስፈራራት እንጂ ሌላ ነገር ማድረግ ቢፈልግ ይችል ነበር አሁን እሱን እርሽው የኔ ማር የምትፈልጊውን ነገር በየትኛውም መንገድ አደርጋለሁ አንቺ ግን ራስሽን አደጋ ላይ የሚከት ተግባር እንዳትፈፅሚ
አባቴ ቢያገኝሽ አንዴ እጁ ከገባሽ አይለቅሽም እስረኛው ነው የምትሆኚው እኔም ላድንሽ አልችልም ቢቻል ራስሽን አሳምነሽ ከዚህ አገር እንውጣ ካልሆነ ግን ታገሽ አለኝ የማክ ንግግር ጠንካራ ነበር፡፡ እኔም ያለኝን እንደማደርግ ቃል ገባሁለት ከዛን ቀን በኃላ ለሳምንት ስራ አልገባንም ነበር በጣም ደስ የሚል የፍቅር ጊዜ እያሳለፍን ነው፡ የሁለታችንም ፍቅር ጨምሯል ፍቅር እንጂ እኛ ጋር ፀብ የለም ከማክ ጋር በጣም ነው የምንዋደደው ሁለታችንም ደስተኞች ነን... ዛሬ የማክ እውነተኛ ሚስት የመሆን ፍላጎቴ ጨምሯል የምንጋባበት ጊዜ ገና ገደብ የለውም ሽፈራው እስከሚፈታኝ ከታገስን ልናረጅ ነው ብቻ በቃ ከፍቅረኝነት የሚስትነት ህይወት አማረኝ ..እኔና ማክ እንደባልና ሚስት አንድ ላይ እንኑር እንጂ ገና መጋባታቸውን የሚጠባበቁ ፍቅረኛሞች ነን እኔና ማክ ለመጋባት የሚከለክለን የአባቱ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ደሞም ለማክ አባት የወረቀት ሚስት እንጂ የእውነት የትዳር አጋሩ አይደለሁ ይሄንንስ አምላክ ከሀፂያት ይቆጥርብኝ ይሆን አልኩ ለራሴ
አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ እየተፋቀርን አንተን ፈርተን እስካሁን ቆይተናል አሁን ግን የትግስቴ ጥግ ላይ ደርሻለሁ አንተ ማረኝ አልኩ በልቤ በጣም ጣፋጭ እራት በራሴ እጅ አዘጋጅቼ ቤቱን ሮማንቲክ አደረኩት.....
የፍቅር ጥቅሶች 💖 pinned «​​  ሄ ዋ ን 🌺             :¨·...............:¨·.                   ♥️ ክፍል 13   ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 Written by Estifanos tekka ማክ ለአባቱ ሹፌር ደውሎለት በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ እስኪነጋ እንቅልፍ ባይኔ አልዞረም ጠዋት ቁርስ ላይ ለማክ አባቴ በጣም እንደናፈቀኝና ልደውልለት እንዳሰብኩኝ ስነግረው ጥሩ ሀሳብ…»
ሄ ዋ ን 🌺
            :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 14

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺

ሮማንቲክ አደረኩት አሁን የቀረኝ ነገር ማክን መቀስቀስ ነው ክፍላችን ስገባ ጥልቅ እንቅልፍ ወስዶታል እንደሁል ጊዜው ለረጅም ደቂቃዎች በዝምታ ስመለከተው ቆየሁ ማክን ተኝቶ እንደማየት የሚያስደስተኝ ነገር የለም ብዙ ነገሮች አስባለሁ ለምሳሌ ያህል እድለኛነቴን ፍቅራችንን፣ መልካም ሰው መሆኑን ፣ የዋህነቱን ፣ በተለይ ደሞ እሱ ህይወቴ ውስጥ ባይፈጠር ምን ልሆን እችል እንደነበር በቃ ይሄን ሁሉ ነገር አንዳንዴ ከዚህም በላይ ስለማክ አስባለሁ ከጥቂት ዝምታ በኃላ ከንፈሩን ስስመው ተገልብጦ ተኛ ማክዬ የኔ ፍቅር ተነስ ብዙ ተኛህ ማታ የት ልታድር ነው አልኩት ፀጉሩን እየደባበስኩት እናቴም የማክም እናት የሞቱት ገና ሳንጠግባቸው በልጅነታችን ነው፡፡
ለማክ የእናትን ያህል እንክብካቤ መስጠት ባልችልም ግን የቻልኩትን ሁሉ አደርጋለሁ ሁሌም ጥረቴ እሱን ለማስደሰት ነው አሁን ደግሞ ልጆች እንዲኖሩንና ደስተኛ የሆነ ቤተሰብ እንዲኖረን ጥልቅ ፍላጎት አለኝ የፍላጎቴ መጠን ያማልፍ ይመስለኛል ካባቱ ጋር በግድ ያስተሳሰረኝን ቃልኪዳን ሳላፈርስ የማክ እውነተኛ ሚስት ለመሆን የቆረጥኩት ማክ ከተነሳ በኃላ ባየው ነገር እጅግ ደስተኛ ነበር ደስ የሚል የፍቅር ጊዜ አሳለፍን #የመጀመሪያዬንም የሚስትነት ሌሊት በማክ እቅፍ ውስጥ አሳለፍኩ፡፡ እንደእብድ ከምወደው የኔ ማክ ጋር በራሳችን ፍቃድ "ሀ" ብለን የትዳር ህይወትን ጀመርን ይሄ ለኛ ልዩ ስሜት ነበረው ምክንያቱ አንድ ነው ያባቱ ሚስት ነበርኩኝ  ደሞም አሁንም ነኝ ጠዋት ስነሳ አልፎ አልፎ እንደሚያደርገው ማክ ነበር ቁርስ ያዘጋጀው ማክን ሳየው የማላውቀው አይነት ስሜት ተሰማኝ አይኑን ለማየት ህፍረት ተሰማኝ ሲቀሰቅሰኝ ቀና ብዬ ላየው አልደፈርኩም እሱም ይሄን ሳይረዳ አልቀረም እንደህፃን ልጅ አባብሎ አስነስቶኝ አቅፎ መታጠቢያ ቤት ወስዶ የምለብሰው ልብስ አቀበለኝና ቁርስ ላይ እንዳልቆይ አስጠንቅቆኝ ወደሳሎን ሄደ ለደቂቃዎች ውሀ ውስጥ ቆየሁ ያሳለፍነውን ለሊት እያሰብኩ ብቻዬን ፈገግ እላለሁ አንዳንዴ ኮስተር ህመሙን ሳስበው ህልም ነበር የሆነብኝ በዚህ መሀል ነበር የማክ ጥሪ ከሀሳቤ ያነቃኝ  ሄዊዬ ዛሬ ከውሀ ውስጥ ላለመውጣት ወስነሻል ወይስ ባልሽ እንዲናፍቅሽ ሙከራ እያደረግሽ ነው? ባልሽ ??? እውነትም ባሌ ማክና እኔን ማንም እልል ብሎ ሳይድረን ተጋባን በራሳችን የፍቅር ቃልኪዳን አሰርን "ባልና ሚስት" ለራሳችን የሰየምነው የክብር ስያሜ ቁርስ ላይ ሆነን ማክ እ...ተጨማሪ የሳምንት እረፍት ሳያስፈልገን አይቀርም አለኝ በፍቅር እያየኝ በሀሳቡ በደስታ ተስማማሁ ከከተማ ወጥተን  አራት የሚገርሙና የተዋቡ ቀናቶችን አሳለፍን ወደ አ/አ በተመለስን ሁለተኛ ቀን አባቴ ደውሎ ሆስፒታል እንደገባ ነገረኝ አባቴ ደም ግፊት አለበት ካልሄድኩኝ ብዬ ማክን አስቸገርኩት ማክ መሄድ ካለብኝ መጀመሪያ እኔ ነኝ የምሄደው አባትሽ አንቺን ለማግኘት ሆን ብሎ ይሆናል አለኝ እንደዛ ሲለኝ ትንሽ እራሴን ለማረጋጋት ሞከርኩ ማክም እንዲሄድ አልፈለኩም ሰው ለመላክ ወሰንን የማክን ጓደኛ አባቴ ተኛሁ ያለበት ሆስፒታል ሄዶ ሲያጣራ እውነትም በዛ ሰው ስም የተኛ ሰው እንደሌለ ተነገረው አባቴ አሁንም ሊያጠቃኝ እየሞከረ ነው ግን ለምን አልኩ ለጥቂት ቀናት እረስቼው የነበረውን ያባቴን ሚስጥር ማወቅ ዳግም እንደ አዲስ አገረሸብኝ ግን እስካሁን ምንም መፍትሄ አላገኘውም ያባቴ የስልክ ጥሪ አንዳንዴ እማዋ ለማክም አባቱ ማስፈራሪያና ሲለውም ሰው ይልክበታል በዚህ ሁኔታ ሁለት ወራቶች ተቆጠሩ ቁርስ ልንበላ ገና ቁጭ ከማለቴ ነበር የማቅለሽለሽ ስሜት ተሰማኝ ወደመታጠቢያ ቤት የሮጥኩት ማክ ተከትሎኝ መጥቷል ምን ሆነሽ ነው ሄዊዬ አለኝ በስስት አላውቅም ማክ ትላንትም እንደዚህ አይነት ስሜት ነበረኝ አልኩት በይ ወደሆስፒታል እንሄዳለን አለኝ ለባብሼ ቅርባችን ወዳለው ሆስፒታል አመራን ከምርምር በኃላ የሰማነውን ውጤት ማመን አልቻልንም ተቃቅፈን አለቀስን ተደሰትን ዘለልን በቃ የምንሆነውን አጣን በርግዝናዬ ምክንያት ማክ በጣም ነበር የሚሳሳልኝ ስራ እንዳቆም አድርጎ  በቃ እቤት ውስጥ እንደሚሰበር እንቁላል ነበር እንክብካቤው ከስራ እስከሚመጣ ስልኬ ሰላም የለውም እቤት ከመጣ በኃላ ራሱ ነበር እያበሰለ ምግብ የሚያበላኝ አንዳንዴ በጣም ከመጨናነቁ የተነሳ በእንክብካቤ እስከመማረር እደርሳለሁ በዚህ ሁኔታ ሶስተኛ ወር ላይ ገብቻለሁ አንድ ቀን ማክ ስራ ሄዶ እኔ እቤት መቀመጥ ስለሰለቸኝ ግቢ ውስጥ ዝም ብዬ ወዲያና ወዲህ እያልኩ ነው ድንገት የግቢያችን በር ተንኳኳ......


✎ ክፍል አስራ አምስት ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል..
                     ┏━ 🦋 ━━━━ 🦋 ━┓
                 
​​    ሄ ዋ ን 🌺
            :¨""""""""""""""¨:

               " ምዕራፍ ሁለት🌺 "

                  ♥️ ክፍል 15

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka

   
አንድ ቀን ማክ ስራ ሄዶ እኔ እቤት መቀመጥ ስለሰለቸኝ ግቢ ውስጥ ዝም ብዬ ወዲያና ወዲህ እያልኩ ነው ድንገት የግቢያችን በር ተንኳኳ... ከደቂቃዎች በኀላ ዘበኛው ፖስታ ይዞልኝ መጣ "ለሄዋን መኮንን" በእጅ የሚሰጥ ይላል የላኪ ስም አልተገለጸም እጆቼ ተንቀጠቀጡ ለተወሰነ ደቂቃ ካለሁበት ሳልነቃነቅ በጄ የያዝኩትን ፖስታ ፈዝዤ ተመከትኩት ምን እንደማደርገው ግራ ገባኝ እየሮጥኩ ወደቤት ገባሁ እርግጠኛ ነኝ እስከዛሬ በጉጉት ስጠብቀው የነበረው ፋይል ነው ግን እጄ ላይ ሲደርስ ለማየት አቅም አነሰኝ ልከፍተው አስቤ ተውኩና ለማክ ልደውልለት ስልኬን አነሳሁ መልሼ ተውኩት በቃ ግራ ተጋብቼ ፈዝዤ እንደቆምኩ ነኝ እጆቼ አሁንም ይንቀጠቀጣሉ አምላኬ ሆይ እርዳኝ አልኩኝ እና እንደምንም እራሴን ለማረጋጋት ቁጭ አልኩኝ ከፖስታው ጋር ተፋጠናል በዛ ግራ መጋባት ውስጥ እያለሁ ስልኬ ሲጮህ ከተቀመጥኩበት በድንጋጤ ተነሳሁ ማክ ነበር እንደምንም አየር ስቤ ስልኩን አነሳሁ ሄ....ሄሎ አልኩኝ በተቆራረጠ ድምጽ የኔ ፍቅር ምነው አመመሽ እንዴ አለኝ እ..ደ..ደህና ነኝ ማክ አልኩት አሁንም በተቆራረጠ ድምጽ አጠገቤ ከተቀመጠው ፖስታ ጋር አሁንም ተፋጠናል ደህናማ አደለሽም ምንድነው የሆንሽው አትደብቂ ንገሪኝ የተፈጠረ ነገር አለ አሞሻል ወይስ ምንድነው አለኝ የኔ ፍቅር ደህና ነኝ ትንሽ ቆይቼ ልደውልልህ ብዬ ስልኩን ዘጋሁት
ያስቀመጥኩትን ፖስታ አንስቼ በድፍረት ስቀደው ውስጡ ፎቶና አንድ ፍላሽ አለ..... ፎቶውን ገና ከማየቴ አቅለሸለሸኝ ወደመታጠቢያ ቤት እየሮጥኩ ሄድኩኝ ሲያዞረኝ ይታወቀኛል ከዛ በኋላ የሆንኩትን አላስታውስም ስነቃ ማክ እና
ዶክተሬ አጠገቤ ቆመው ስለኔ ጤንነት ያወራሉ ዙሪያዬን ስቃኝ ሆስፒታል አልጋ ላይ ተንጋልያለሁ ሆዴን ዳበስኩኝ ማክ ል....ልጄ ብዬ ስጮህ እየሮጠ መጥቶ አቀፋኝ ልጃችን ደህና ነው ተረጋጊ የኔ ፍቅር አለኝ ኡፈይይይ... ብዬ ተነፈስኩ....
ተስፋ በሌለው ባዶ ስሜት ውስጥ ሆኜ እነዛን ፎቶዎች ዳግም አስታወስኩኝ.....
አባቴ እንዴት ይሄንን ይፈፅማል አይሆንም አልኩና ካልጋ ለመውረድ ከማክ ጋር መታገል ጀመርኩኝ ማክ በግድ አረጋግቶ አስቀመጠኝ አንገቱ ስር ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ማክ ምድር ላይ ያለኝ ብቸኛው ሰውገዳዩ አባቴ ነው የማዋን ባል የገደለው አባቴ ነው እያልኩ ሳለቅስ በግድ እንድረጋጋ ዝም እንድል ያባብለኝ ጀመር ትዝ ሲለኝ ፍላሹ ውስጥ ምን እንዳለ ገና አላየሁም ማክ ፍላሹስ ፍላሹ የታል አልኩት አሁንም ማልቀሴን ሳላቆም የኔ ፍቅር ተረጋጊ...እቤት ነው አሁን ለልጃችን ብቻ አስቢ አለኝ እንደህፃን እያባበለኝ በዚህ በተዘበራረቀ ስሜት ውስጥ ሆኜ ቀናቶች ተቆጠሩ ማክ ካጠገቤ ለሴኮንድ መራቅ ፈራ ያንን ፎቶም ሆነ ፍላሽ ዳግም አላየዋቸውም ግን አንዴ ውስጤ የተቀረጸው አባቴ የገዛ ጓደኛውን ሲገል የሚያሳየው ምስል ከውስጤ አልጠፋም ተኝቼም ያባንነኛል ሙሉ ሚስጥሩን የማዎቅ ፍላጎቴ በረታ
ማክ ከያንዳንዷ እርምጃዬ ጎን ነው ያንን ለማድረግ እድሉን አልሰጠኝም ነበር.... ድንገት የማክ የበፊት ሁኔታዎች ታወሱኝ ማክ ታውቅ ነበር አደል ስለዚህ ጉዳይ ለዛም ነበር ስትከላከል የነበርከው አልኩት ስለዚህ ጉዳይ ምንም እንደማያውቅ ምሎ አረጋገጠልኝ ቆይ ቢያውቅስ ምን ለውጥ አለው አባቴ እንደው አንዴ ሰው ገድሏል ምን የሚመጣ ለውጥ አለ ግን ያባቴን ወንጀል ተለባብሶ እንዲቀር አልፈቅድም ተለባብሶ የሚቀር ምንም ነገር መኖር የለበትም ለሱ ሀፂያት እዳ መክፈያ እኔን መስዕዋት ማድረጉ ጭራሽ እንድጠላውና እንድፀየፈው አደረገኝ የማዋ ካባቴ ጋር በሰላም መኖርና ከሽፈራሁ ጋር የሚያገናኛቸው ሚስጥርስ ምንድነው ሰው እንዴት ከደመኛው ጋር ፍቅር ይሆናል የማይመለስ ጥያቄ ውስጤ ተጫረ..... ድንገት ፍላሹ ትዝ አለኝ ምን አልባት የዚህ ጥያቄዬ መልስ እዛ ፍላሽ ውስጥ ይኖራል ማክ በኔ ቅዠትና በየደቂቃው ከንቅልፌ መንቃት ምክንያት እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር አድሮ አሁን ሸለብ አድርጎታል ቀስ ብዬ ካጠገቡ ተነሳሁ.....


          ꧁༺༒༻꧂

✎ ምዕራፍ ሁለት🌺 ክፍል አስራ ስድስት ከ90 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
​​​​​​.
                      ሄ ዋ ን 🌺
            :¨""""""""""""""¨:

               " ምዕራፍ ሁለት🌺 "

                  ♥️ ክፍል 16

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka

   
ድንገት ፍላሹ ትዝ አለኝ ምን አልባት የዚህ ጥያቄዬ መልስ እዛ ፍላሽ ውስጥ ይኖራል ማክ በኔ ቅዠትና በየደቂቃው ከንቅልፌ መንቃት ምክንያት እንቅልፍ ባይኑ ሳይዞር አድሮ አሁን ሸለብ አድርጎታል ቀስ ብዬ ካጠገቡ ተነሳሁ ማክ እቤት ውስጥ ለስራ የሚጠቀመው ክፍል ገብቼ መፈለግ ጀመርኩ ምንም አልቀረኝም ላገኘው አልቻልኩም ድንገት ከኀላዬ ሄዊዬ ምን ጠፍቶብሽ ነው የሚል ድምጽ ተሰማኝ ማክ ነበር ማክ እባክህ ምን እንደምፈልግ ታውቃለህ እናም ከደበቅክበት አውጥተህ ስጠኝ አልኩት
እጄን ይዞኝ ከክፍሉ እየወጣ የኔ ቆንጆ አሁን ማሰብ ያለብን አንድና አንድ ነገር ብቻ ነው ስላንቺ ጤና ብቻ ለኔ ካላዘንሽልኝ ለምን ለልጃችን አታስቢም በኀላ ጭንቀታም ልጅ ልትወልጂ ነው አለኝ እየቀለደ ማክ ስለልጃችን ብቻ አደለም ስላንተም አስባለሁ ግን እስከመቼ ነው በዚህ አይነት ሁኔታ የምንቀጥለው እኔ በጭንቀት ልሞት ነው ሁሉንም ያባቴን ሚስጥር አውቄ ለህግ ካላቀረብኩት ሰላም አይኖረኝም እባክህ ማስረጃዎቹን ስጠኝ አልኩት እያለቀስኩ የኔ ቆንጆ ያባቴም ፍላጎት ይሄ ነው አንቺ አባትሽን አሳልፈሽ እንድትሰጪ ግን የሱን ፍላጎት እንድታሟይ አልፈቅድለትም አባትሽ ባደረገው ነገር መቀጣት ካለበት ወንጀሉን ሲፈፅም የተተባበሩትም ሰዎች አብረው መቀጣት አለባቸው ይሄን ደሞ የሚያደርገው ሰው አንቺ ሳትሆኚ እኔ ነኝ አባትሽም ሆነ ሌላውን ሰው ለቅጣት ለማቅረብ እኔ አለሁኝ ቃል እገባልሻለሁ ግን ምን አልባት ያባትሽ ጥፋት ብቻ ላይሆን ስለሚችል እስከማጣራ አንቺ ተረጋጊ እስከዛ እራስሽንና ልጃችንን ብቻ ለመንከባከብ ቃል ግቢልኝ አለኝ ማክ እንዴት ነው አባቴ ጥፋተኛ ላይሆን የሚችለው እኔ ባይኔ እኮ ነው ፎቶውን ያየሁት እንዴት ይሆናል አልኩት አሁንም እያለቀስኩ ባይንሽ አይተሻል እንዴትስ እንደተፈጠረ የምታውቂው ነገር አለ አለኝ ማክ እንባዬን እየጠረገልኝ እኮ የሁሉም ነገር መፍቻ እኮ ምን አልባት ፍላሽ ውስጥ ይኖራል ማክዬ ፕሊስ ስጠኝና ልየው ከዛ በኋላ ባልከኝ ሁሉ እስማማለሁ አልኩት በምንም መልኩ ማክ ፋይሉን ሊሰጠኝ አልፈቀደም እኔም ከቀን ወደቀን እየተሻለኝ ቢመጣም ያባቴ ስራ ከፊቴ መጥፋት አልቻለም እርግዝናውም እየከበደኝ ሲመጣ ማክ የገባልኝን ቃል እስኪፈፅም ከመጠበቅ ውጪ ምንም አማራጭ አልነበረኝም ቀናቶች ወራቶችን ወልደው የምወልድበት ጊዜ ደረሰና የምታምር ቆንጅዬ ሴት ልጅ በሰላም ተገላገልኩ ስሟን ስጦታ አልኳት ማክና ስጦታ ለኔ የህይወት ገጸበረከቶቼ ናቸው ውሎዬ አዳሬ ሁሉ ነገሬ ከልጄ ጋር ሆነ ያም ሆኖ ያባቴ ነገር አሁንም ውስጤ አለ ማክ በኔ ደስተኛነት በጣም ደስተኛ ሆኗል በጣም የሚያስቀናና ደስተኛ ቤተሰብ አለን አሁን የማክ እህት ዎንድሞችም ሊያዩኝ የደስታችን ተካፋይ ሊሆኑ መጥተዋል ሁሉም በኛ ደስተኞች ናቸው ከማክ ካንዷ እህቱ በስተቀር በቃ ደስ የሚል ቤተሰባዊ ጊዜን እያሳለፍን ነው ብቻዬን አድጌ በሰው መከበቤ እንደአዲስ የተወለድኩ አይነት ስሜት ፈጥሮብኛል ስጦታ ሁለት ወር ሞልቷታል ሙሉ ጊዜዬን ለማክና ለስጦታ መስጠት ከጀመርኩ ሰነባብቻለሁ አንድ ቀን አባቴ እቤት ድረስ አንኳክቶ መጣ ማክ አጋጣሚ ስራ ነበር እኔም ስጦታን እያጫወትኩ ውጪ ነበርኩ ዘበኛው ጠርቶኝ ስወጣ ገና ሳየው አንቀጠቀጠኝ ፈራሁኝም እሱ ግን ፍፁም ተረጋግቶና አሳዛኝ ሆኖ ነበር እባክሽ ልጄ አንድ እድል ስጪኝ ላናግርሽ ነው የመጣሁት እባክሽ እያለ ይማጸነኝ ጀመር ድንገት ያ ፎቶ ፊቴ ድቅን አለብኝ ማናገር እንደማልችል ነግሬው ወደውስጥ እየሮጥኩ ገብቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ማክ ሲመጣ የሆነውን ስነግረው ባባቴ እቤት ድረስ ደፍሮ መምጣት በጣም ተናደደ ማክን እንደዛ ሲሆን አይቼው አላውቅም.... ስጦታን ለሞግዚቷ እንድሰጣትና የሱ የስራ ክፍል እንድከተለው ነገረኝ ማክ በጣም አስተዋይና ታጋሽ ነው የዛሬው ሁኔታው ግን የተለየ ነበር በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ ያለኝን ፈፅሜ ስመጣ....
እንድቀመጥ ወንበር ስቦ አስቀምጦኝ የሚነግረኝን ማንኛውንም ነገር በፀጋ እንድቀበልና ምንም አይነት እርምጃን ከሱ ውጪ እንደማልፈጽም ቃል አስገባኝ......

                                 ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
የፍቅር ጥቅሶች 💖 pinned «​​​​​​.                       ሄ ዋ ን 🌺             :¨""""""""""""""¨:                " ምዕራፍ ሁለት🌺 "                   ♥️ ክፍል 16   ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 Written by Estifanos tekka     ድንገት ፍላሹ ትዝ አለኝ ምን አልባት የዚህ ጥያቄዬ መልስ እዛ ፍላሽ ውስጥ ይኖራል ማክ በኔ ቅዠትና…»
​​​​.
                      ሄ ዋ ን 🌺
            :¨""""""""""""""¨:

               " ምዕራፍ ሁለት🌺 "

                  ♥️ ክፍል 17

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 ነገ የመጨረሻው ክፍል ይቀርባል።
🥀🥀🥀🥀🥀🥀🥀❤️❤️❤️❤️
ማክ ሲመጣ የሆነውን ስነግረው ባባቴ እቤት ድረስ ደፍሮ መምጣት በጣም ተናደደ ማክን እንደዛ ሲሆን አይቼው አላውቅም.... ስጦታን ለሞግዚቷ እንድሰጣትና የሱ የስራ ክፍል እንድከተለው ነገረኝ ማክ በጣም አስተዋይና ታጋሽ ነው የዛሬው ሁኔታው ግን የተለየ ነበር በድንጋጤ ውስጥ ሆኜ ያለኝን ፈፅሜ ስመጣ እንድቀመጥ ወንበር ስቦ አስቀምጦኝ የሚነግረኝን ማንኛውንም ነገር በፀጋ እንድቀበልና ምንም አይነት እርምጃን ከሱ ውጪ እንደማልፈጽም ቃል አስገባኝ
እኔም በሁኔታው ስለተደናገጥኩም ለዓመታት ስጠብቀው የነበረውንም ሚስጥር ለመስማት ስለጓጓሁ ቃል ገባሁለት ሄዊዬ የኔ ፍቅር የምነግርሽ ነገር እንደሚከብድሽ አውቃለሁ ግን እንደምትረጋጊ ቃል ገብተሽልኛል እኔና ልጃችን ካላንቺ ባዶ ነን እና እባክሽ ምንም አይነት የተሳሳተ ነገር እንዳታደርጊ ካሁኑ እለምንሻለሁ....ቃላቶቹ ይበልጥ ቢያስፈሩኝም እንደገና ቃል ገባሁለት አንቺ ገና ልጅ እያለሽ ነው በናትሽ ጓደኛ እና ባባቴ መካከል የፍቅር ግኑኝነት ነበር እናም የናትሽ ጓደኛ ባለትዳር ስለነበሩ አባቴ ወደሳቸው ሲመጣ አባትሽ ስራ ስለሚውሉ የሚገናኙት እናንተ ቤት ነበር...አንድ ቀን እንደተለመደው አባቴ እናንተ ቤት ሆኖ ፍቅረኛውን ሲጠብቅ ያባትሽ ጓደኛ ለናትሽ መልዕክት ሊነግራት ሲመጣ አባቴን እናንተ ቤት ያየዋል
በዚህ መሀል ምንም ሳይናገር ሄዶ ላባትሽ ሲነግረው እሱም እብድ ሆኖ ወደቤት ይመለሳል በዛን ሰአት ግን አባቴ እቤት አልነበረም....አባትሽ በሰማው ነገር ተናዶ ሰለነበር እናትሽን ይደበድባታል...
እናትሽም የሆነውን ነገር ለባሏ ልታስረዳ ብትሞክር የራስሽን ስራ ሰው ላይ አታላኪ በሚል ሊሰማት ፍቃደኛ አልሆነም ከዛን ጊዜ ጀምሮ እናትሽን አባትሽ በጣም ይመታት ጀመር አዎ አስታውሳለሁ አልኩት እያለቀስኩ ከዛን እናትሽ በጣም ትማረርና ሽማግሌ ሰብስባ ሁሉንም ትናገራለች በዛ ምክንያት ከጓደኛዋ ጋር እንደበፊቱ መሆን አልቻሉም አባትሽም እናትሽን ማመን አልፈለገም መምታቱን አላቆመም ነበር ብዙ ጊዜ እየሰከረም ነበር የሚገባው አባቴና የናትሽ ጓደኛም በውጪ መገናኘታቸውን አላቆሙም ነበር
ግን ባላቸው እናትሽ ያለችውን ነገር አምኖ ነበርና የት ወጣሽ የት ገባሽ በሚል አላስቀምጥ ሲላቸው እሱን ለመገላገል ካባቴ ጋር ሆነው ተንኮል መጠንሰስ ይጀምራሉ እናም አባትሽ አባቴን ባካል አያውቀውም ነበርና አንድ ቀን አባትሽ የሚጠጣበት መጠጥ ቤት ሆን ብሎ ያገኘውና ጓደኛው ያደርገዋል። ከጊዜ ወደ ጊዜ መቀራረብ በኋላም እናትሽ ከጓደኛዋ ባል ጋር እየማገጠችበት እንደሆነና ከዚህ በፊት የነገረው ታሪክ ስለራሱ እንደነበር በደንብ ያሳምነዋል።
እሱም እናትሽ የነገረችው የጓደኛዋ ታሪክ አላሳመነውምና አባቴን በቀላሉ ያምነዋል
አባትሽም ጓደኛው ባላደረገው ነገር ቂም ይይዘበትና አልፎ አልፎ ላጣልት ይጀምራሉ ከጊዜ በኻላም ያባትች ቂም ውስጡ እያደገ ይሄድና ወደበቀል ይቀየራል ካባቴም ጋር ቅርበታቸው ጠብቆ ነበርና ሊገድለው እንደሚፈልግ ላባቴ ያማክረዋል እነሱም ይሄ ነበር አላማቸውና ይበልጥ አባትሽን ያበረታታዋል ሊገድለው ባቀደበት ወቅት ካባቴ ጋር ሲጠጡ አምሽተው ይለያያሉ ግን አባቴ ወደቤቱ አልተመለሰም ነበር አባትሽን ተደብቆ እየተከታተለው ስለነበር ጓደኛውን ሲገድለው ፎቶ ያነሳዋል ያው በጥንቃቄ ስለነበር የገደለው ፖሊስ ምንም አይነት መረጃ ማግኘት አልቻለም ዱርዬዎች ሊርዘፉት አስበው እንገደሉት ተወራ። በወቅቱ በበቀል የተሞላው እና ያባቴ አበረታችነት ያልተለየው አባትሽ በዚህ አላበቃም ትንሽ ብሎ በረጅሙ ተንፍሶ ንግግሩን አቆመ ማክ ቀጥል ትንሽ ምን አልኩት በንባ እየታጠብኩኝ.፣
ተፂዬ መቀጠል አቃተኝ አለኝ.....ኖ ማክ ትቀጥላለህ ሁሉንም መስማት እፈልጋለሁ አልኩት እየጮህኩ....
እሺ ግን ቃልሽን እንዳታጥፊ አለኝ አጠገቤ እየተነረከከ እባክህ ማክ ቀጥል አልኩት እያለቀስኩ ረጅሙ ተንፍሶ....

✎ ምዕራፍ ሁለት🌺 ክፍል አስራ ስምንት ወይም የመጨረሻው ክፍል ነገ ከ80 ሠው አድድ♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
​​​​​​.
                      ሄ ዋ ን 🌺
            :¨""""""""""""""¨:

               " ምዕራፍ ሁለት🌺 "

                  ♥️ ክፍል 18

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 የመጨረሻው ክፍል።
Written by Estifanos tekka

   
በረጅሙ ተንፍሶ ትንሽ ቆይቶ ያባትሽ ብትር እናትሽ ላይ አረፈ ...እንዴት እኔ ይሄንን አላምንም ብዬ ጮህኩ ሄዊ ተረጋጊ አለኝ ተንሰቅስቄ አለቀስኩ ራሴን ማረጋጋት ፍፁም ተሳነኝ በር ዘግቼ ማልቀስ ሆነ ስራዬ አልበላም አልጠጣም አባቴን ሄጄ ብገለው ደስታዬ ነበር ግን የማክ ቁጥጥር አደለም ከቤት መውጣት ስልኬን እስከመቀማት ደርሶ ነበር ማክ ከስጦታ ጋር ጊዜዬን እንዳሳልፍና ነገሮችን እንድረሳ የማይጥረው ነገር አልነበረም ከቀን ወደቀን ትንሽ እየተሻለኝ ቢመጣም ግን የእናቴ አሟሟት መርሳት አልቻልኩም ትዝ ይለኛል እናቴ በጣም ሳቂታና ተጫዋች ነበረች ሁሌም እሷ ነበረች ከትምህርት ቤት የምታመጣኝ ጠዋት
ት/ት አድርሳኝ ባልተለመደ ሁኔታ በጣም አቅፋ ስማኝ ነበር፡፡ ታዲያ ወደቤት ስመለስ ብቻዬን ነበር ሰው ሁላ ቤታችን ተሰብስቧል እናቴን በዛ ትርምስ ውስጥ ስፈልግ ያየኝ ሁሉ ልጅ አይደለች ምኑን አውቃው እያሉ በሀዘኔታ ከንፈራቸውን ይመጡልኛል፡፡ እኔ በወቅቱ ምንም አልገባኝም ነበር እናቴ ላትመለስ አሸልባለች ባልሰራችው ሀፂያት ተቀጥታለች ከናቴ ድንገተኛ ሞት በኃላ አባቴ ይባስ ጨከነብኝ ለኔ ጭራሽ ግድ አልነበረውም አንዳንዴ እማዋ ቤት እንኩዋን ሳድር የት ገባች ብሎ አይፈልገኝም በራሴ ጥረትና በጎረቤት ፍርፋሪ ነው ያደኩት ይኸው በመጨረሻም ለወንጀሉ ተባባሪ ለሆነው ሰው ሸጦኝ እሱም አልበቃ ብሎት ሲያሳድደኝ ነበር የእናቴን ገዳይም ሆነ ተባባሪ ለህግ አሳልፌ ሳልሰጥ እንቅልፍ እንደማይወስደኝ ለራሴ ቃል ገባሁ ማክን ጠርቼ እነዚህን መረጃዎች ከየት እንዳመጣና ተልኮልኝ የነበረው ፋይል የት እንደሆነ ጠየኩት ሄዊዬ ቃሌን ፈፅሚያለው እስክትረጋጊ ነበር የጠበኩሽ እንጂ ሁሉም በህግ ስር ከዋለ ሳምንት አልፏቸዋል አለኝ እንዴት ማክ አልኩት  በአድናቆት እያየሁት በመጀመሪያ ነበር
አባትሽ እናትሽን እንደገደላት ያወኩት እንደውም ካስታወሽ መጀመሪያ አባቴን ላናግረው የሄድኩኝ ቀን አስታወሽ አለኝ አ....አዎ እንደውም ቆይተህብኝ ተጨንቄ አዙ ጋር የደወልኩት ሰዓት አልኩት ለመስማት እየጓጓው እክል እንደሚገጥምሽ ገመትኩ ከዛ ያለውን ነገር ሁሉ አንቺ እንዳትገቢበት እየተከላከልኩ አጣራሁ ለዛ ነበር ይሄን ክትትል እንዳቆም አባቴ አስደብድቦኝ የነበረው ከዛም እኔ የሆነ የተደበቀ ነገር እንዳለ ይበልጥ ስለጠረጠርኩ በክትትሌ ገፋሁበት እናም በመጨረሻም የናትሽ ጓደኛ ጋር እንደሄድሽና በማግስቱ በማታውቂው ቁጥር ቴክስት እንደመጣልሽ የነገርሽኝ አስታወስኩ የሚስጥሩ መፍቻ ቁልፍ እሳቸው እንደሆኑ ተረዳው እናም ሆነ አለኝ እና ይሄን ሁላ ነገር የነገሩህ እሳቸው ናቸው አልኩት አሁንም ማልቀሴን ማቆም አልቻልኩም ....አዎ ያው በመጀመሪያ ተቸግረን ነበር በኃላ ግን በልጆቻቸው ስናስፈራራቸው አመኑ ሁሉንም ነገር ተናገሩ ታዲያ እናቴ እንዴት ሞተች አልኩት ያው እራሷን እንዳጠፋች ነበር ተደርጎ የተወራው ግን አንቺ ልጅ ስለነበርሽ ፊት ለፊትሽ አልተወራም ለዛ ነው ያላስታወሺው ለማንኛውም አሁን ዝግጁ ከሆንሽ ፖሊስ ጣቢያ ሄደሽ ቃል ትሰጫለሽ ብሎ አቅፎ ሳመኝ የናቴ ጉዳዮች ለፍርድ በመብቃታቸው ብደሰትም እናቴን ግን ለዘላለም አጥቻታለሁና መርሳት አልቻልኩም እንዴት ልረሳት እችላለሁ ለዛውም በግፍ ያለሀፂያትዋ የተቀጣችው እናቴን አሁን ወደ ስራዬ ተመልሻለሁ ስጦታም እያደገች ነው ቤተሰቤ ደስ የሚል ፍቅር አለው ዛሬ የስጦታ ሶስተኛ አመት የልደት ቀን ነው የማክ ወንድምና እህቱ እዚሁ ናቸው፡፡ ወንድሙ ጠቅልሎ ከመጣ አመት ያልፈዋል ከሳምንት በኃላ በአባቱ ቤት ይሞሸራል ማክ በጣም ደስተኛ ሆኗል ዛሬ ደግሞ የምነግረው አስደሳች ዜና አለኝ ማክና ስጦታ የኔ የህይወቴ መጀመሪያ ስጦታዎቼ ናቸው፡፡ ማክ አልኩት ወዬ ሄዊዬ የኔ ፍቅር አለኝ በቅርቡ ሌላ የቤተሰብ አካል ቤተሰባችንን ይቀላቀላል እርጉዝ ነኝ አልኩት ማክ እራሱን መቆጣጠር አልቻለም በደስታ መጮህ ጀመረ ሚስቴ ሄዊ እርጉዝ ናት ብሎ ለታዳሚው ጮሆ ተናገረ እኔና ስጦታን አቅፎ የደስታ  እንባ አነባ...
የመጀመሪያዬ ፍፃሚዬም ሆነ እስከለተሞቴ ላልለየው ፅኑ ቃል♥️ አለኝ፡፡


✎ ቤተሰቦች ታሪኩን እንዴት አገኛችሁት መቼም የማይረሳ ጣፋጭ የፍቅር ታሪክ እንደሰነቃቹ አልጠራጠርም በሌላ ድርሰት እስከምንገኛኝ ድረስ ባላችሁለት ሰላማችሁ ይብዛልን አስተያየታችሁ  አድርሱኝ መልካም ጊዜ።🌺
      ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
       ❤️🩵❤️🩵❤️🩵
          ማነው የተረዳኝ
ማነው የተረዳኝ የገባው ስሜቴ
እኔ በሱ ፍቅር እንቅልፍ ማጣቴ።
ታዲያ እስከ መቼ አፍኜው እኖራለሁ
አንድ ቀን በይፋ ግልፅ አወጣዋለሁ።
እስከዛች ደቂቃ እስከዛች ቀን ድረስ
ይህንን ሚስጥሬን ለማንስ ልተንፍስ።
እሱ ኩራተኛ ፍቅር የማይገባው
የፍቅርን ትርጉም የማይረዳው
መልክና ቁመናው ልብ የሚነዛው
ሳቁና ፈገግታው መንፈሰ የሚያድሰው
ከሁሉ ተግባቢ ያ ቆንጆ ሰው
የኔን ልብ ሰርቆ ወዴት ሰወረው?
እባክህ ተረዳኝ አስብልኝ አንዴ
እኔ ባንተ ፍቅር ተቃርቧል ማበዴ
ሌላ ሴት ጋር ሳይህ እቀናለሁ ባነዴ
ይህን እወቅልኝ እባክህን ውዴ።
አንተ ፈገግ ስትል እኔ የምስቀው
አንተ ስትከፋ እኔ አዝኜ የምውለው
እባክህ ተረዳኝ ስለወደድኩህ ነው።

        ‌‌‌‌‌‌  
~~~
ላንተም/ላንችም ቀን ይወጣል !

ፀሀይ እና ጨረቃ እኩል አይወጡም ፤  ሁለቱም የየራሳቸው ሰዐት አላቸው ስለዚህ ወንድሜ/እህቴ አንተ/አንቺ የምታበራበት ቀን መቼ እና የት እንደሆነ አታውቅም እና ዝም ብለህ/ሽ ራስህን አዘጋጅ የሚጠበቅብህን ነገር ጥግ ድረስ አድርግ ያኔ ያልጠበቅከው ድል ያላሰብከው ብርሀን አንተ/አንቺ ላይ ሲፈነጥቅ ታየዋለህ/ሽ !
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
​​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ 🌹


             ♥️ክፍል 1♥️

...🖊ቃልኪዳን እባላለሁ የምኖረው ከእናት እና ከህቴ ጋር ነው አባቴን ገና በልጅነቴ ነው ያጣውት ያባትነት ፍቅር እንዲሁ እየናፈቀኝ ነው ያደግከት በ3 አመት የምበልጣት ታናሽ እህት አለችኝ ቀይ እና ቆንጆ ምትባል ናት እኔ ደግሞ የቀይ ዳማ ነኝ ብዙ ሰዎች እናትሽን ቁልጭ ትመስያለሽ ይሉኛል እኔም ደስ ይለኛል ደሞ ማሚ ወጣት ነገር ናት እና ለጎደኞቼ ከማወራው ይልቅ ከናቴ ጋር ማወራው ይበልጣል በኑሯችንም ቢሆን መካከለኛ ከሚባሉት መካከል ነን ቢሆንም የሚያስፈልገን ነገር በሚያስፈልገን ጊዜ ይደረግልናል እኔ የ12 ክፍል ውጤት በጥሩ ሁኔታ አልፌ ተወልጄ ባደግኩበት 4 ኪሎ አዲስ አበባ ገባው ምንም እንኳን ተወልጄ ባድግበትም ከ 5 አመት በፊት ድሬ አዲስ ከተማ በምትባል መንደር ውስጥ መኖር ከጀመርን በኃላ ሙሉ በሙሉ የዛ ሀገር ተወላጅ ነው ምመስለው በጣም ሳቂታና ተጫዋች ነኝ ነገር ግን በሩቁ ላየኝ ሰው እጅግ ጢባራም እና ምናገር አልመስልም ግን እኔ በተቃራኒው ነኝ አሁን ግን አዲስ አበባ ስመጣ ልክ እንደመጀመሪያዬ ድንግርግር ነው ያልኩት ገና ግቢ ስገባ ከአንዲት የተደናበረች ልጅ ጋር እጋጫለው ከዛ ልጅቷም በጣም ይቅርታ የኔ እህት አላወኩም ነበር ብላኝ ምላሼን ሳጠብቅ የሄደችው ይቅርታ ባጠይቀኝ እዛው ባጋጫት ደስ ይለኝ ነበር ገና በመጀመሪያው ቀን እንዲህ ከደበረኝ ትንሽ ከቆየው እንደማብድ እያሰብኩ ወደ ዶርሜ ሄጄ ማስቀመጥ ያለብኝን ነገር ቦታ ባታ እያስያስኩ በጣም የሚያስጠላ የስላቅ ድምፅ ሰምቼ ስዞር የቅድሞ ልጅ ናት በስልክ ከማን ጋር እንደምታውራ ባላቅም ዝም ብላ ታገጣለች ደሞ እዚም ተከተልሽኝ እያልኩ በውስጤ ምን ልትሰራ መጣች እላለው ከዛም ስልኩን አውርታ እንደጨረሰች ሀይ ሜሮን እባላለው ስትለኝ ቃልኪዳን አልኳት ከዛም ለቅድሙ ይቅርታ ተቻኩዬ ነበር ምናምን ብላ ብዙ አወራች ግን በቅጡ አንዱንም አልሰማዋትም ከዛም ከዚህ በኃላ ጓደኛሞች ነን አለችኝ ምላሼን ሳትሰማ ስልኳን መጎርጎሯን ጀመረች በጣም ሲበዛ ችኩል ናት ግን ለኔ ጥሩ ነው ጓደኛ በዚህ ፍጥነት እገኛለው ብዬ አላሰብኩም ነበር...

                ይቀጥላል...✍️

┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️
​​​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ


             ♥️ክፍል 2♥️

...🖊ጓደኛ በዚህ ፍጥነት አገኛለው ብዬ አላሰብኩም ግን ቀን ቀናትን እየውለዱ ግማሽ ሴሚስተር ደረሰ እኔ እና ሜሮንም በጣም ጓደኛማቾች ሆንን ሜሮን ምንም እንኳ ችከል ብትሆን በጣም ጥሩ ደስ ምትል ልጅ ናት ከዛም እረፍት ቤተሰብ ጠይቀን ወደ ትምህርት ተመለስን ይሄ አመት ብዙም ሳይደብረኝም ሳያስጠላኝ አልፈ እረፍትን ከቤተሰቦቼ ጋር ድሬ በመዝናናት እሳለፍኩ ሜሮንም የሀዋሳ ልጅ ናት ግን ድሬን ማየት ትፈልግ ስለነበር እኛ ጋር 2 ሳምንት ተቀምጣ ሄደች መምጣቱ አይቀር መስከረም መጣ ከዛም ግቢ ስደርስ ሜሮን ቀድማኝ ደርሳ ነበር እናም ከሆነ ልጅ ጋር ቆማ ታወራለች ከነሱ ትንሽ ተገንጥሎ የቆመ አንድ ቀላ ያለ ፀጉረ ሉጫ ቆንጅዬ ልጅ ቆሟል እና ሜሮን አይታኝ ስለነበር በእጇ ወድ እርሷ እንድመጣ ጠራችኝ ከዛም ደርሼ ሰላም አልኳት እና አማን ይባላል ጓደኛዬ ነው ተተዋወቂው አለችኝ እሺ ቃልኪዳን ስለው አማን አለኝ ከዛም አቤል ና ተቀላቀል አለው ትንሽ ተገንጥሎ ስለነበር ከዛም አማን አቤል ይባላል ተዋወቂው ሲለኝ ቃልኪዳን ብዬ እጄን ዘረጋውለት ከዛም እጄን ልክ ሲጨብጠኝ ሙሉ አካሌን ሲነዝረኝ

ይሰማኛል ከዛም ወድያው ስሙን ነግሮኝ እጁን ከእጄ ሲያወጣው ምነው ዘላለም ብትይዘኝ ብዬ ተመኘው ከዛም ግን በቃ እንሂድ ብላ ሜሮን ልክ ስንቀሳቀስ አንዴ ዞሬ ሳየው ተነጋግረን ይመስል እርሱም ወደኔ ያያል ደንግጬ ዞርኩ ዶርም ከገባን በኃላ ለምን እንደሆነ ባላውቅም እጄን አስር ጊዜ እመለከተውና ስለ አቤል ማሰብ ጀመርኩ ግን ሜሮን በወሬ ወሬ አረሳችኝ ከዛ ጊዜ ጀምሮ ግቢው ውስጥ እፈልገዋለሁ ግን ብዙ ጊዜ አይታይም እንዲሀ እንደለመደብኝ ዛሬም ስፈልገው ውዬ ላገኘው ስላልቻልኩ ተበሳጭቼ ወደ ዶርም ስገባ ሜሮን የት ነበርሽ እስካሁን አማን ደውሎ ነበር ዛሬ ሁለታችንንም ምሳ ሊጋብዙን ፈልገዋል ስትለኝ በውስጤ አቤልም በመጣ እያልኩ እያሰብኩ እያለ ሰላም ምን ያፈዝሻል ምሳ እኮ ነው የተባልነው ተንቀሳቀሽ እያለች እያጣደፈች ይዛኝ ወጣች ለምን እንደሆነ ባላውቅም በጣም ደስ ብሏታል እና እኔም ዝም ብዬ ሄድኩ ካፌው ልክ ስንደርስ ግን...

                ይቀጥላል

┄┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
​​​♥️✿የተራራቀ ልብ✿♥️

        አጓጊ እና ልብ አንጠልጣይ የፍቅር ታሪክ



             ♥️ክፍል 3♥️

...🖊ስንደርስ ግን አቤል እና አማን አንድ ላይ ቅልጥ ያለ ወሬ ይዘው ማንንም አይሰሙም ከዛም እማን ቀና አለና ሜሪ ብሎ ከመቀመጫው ብድግ አለ እስዋም አማን ብላ እየተፍለቀለቀች ወደ እርሱ ሄዳ ጥምጥም አለችበት ከዛ እኔ ደግሞ አቤልን በእጄ ብቻ ሰላም ብዬ ፈገግ አልኩኝ እርሱም አፀፍውን ለመመለስ ያክል በትንሹ ፈገግ አለ ከዛም አማንን ሰላም  ካልኩት በኃላ አማን አጠገቡ ካለ ወንበር ሳብ አድርጎ ነይ እዚህ ጋር ተቀመጭ አለኝ ሜሪ እንደነገረችኝ ከሆነ አማን ተጫዋችና የብዙ ሴቶች ቀልብ የሚስብ ልጅ ነው አማን የጠይም ቆንጆ ነው ግን ሴት አታራማሽ ነው በርግጥ እነርሱ ሲመጡበት እንጂ ተላካፊ እይደለም ምላሳም ስለሆነ ብዙ ሴቶች ይወዱታል አቤል ግን ዝምታ የሚያበዛ ጉረኛ ቢሆንም ሲግባቡት ግን ምርጥ ልጅ ነው እና እሺ ብዬ ወንበሩ ላይ ተቀመጥኩ አሁን ምን አለ ከአቤል ጎን ብቀመጥ ውስጤ እየተናደደም ቢሆን ከርሱ አጠገብ ሄጄ ተቀመጥኩአማን የባጥ የቆጡን እያነሳ ያወራል አቤል እና ሜሪ ደግሞ የራሳቸው አለም ውስጥ ናቸው እኔ አማን የሚያወራውን አንዱንም አላዳምጥም አቤል ምን እያላት ይሁን ወይም እርሷ ምንድነው ምትለው እያልኩ ውስጤ ያብሰለስላል መልሼ ለራሴ የፈለገችውን ብትለውስ ምን አገባኝ ቆይ ከመች ጀምሮ ነው ስለወንድ መጨነቅ የጀመርሽው ለዛውም አንድ ቀን ላወቅሽው እሱም በቅጡ ሳታወሪ ብዬ ለራሴ እያወራው ሳለ ቃል ኧረ ቃል ተመለሽ ወዴት ሄድሽ የሚል ድምፅ ካለውበት የሀሳብ ባህር ፈልቅቆ አወጣኝ አማን ነበር ዉይ ይቅርታ አላሰብኩትም ስለው ኧረ ችግር የለውም ማናባቱ ነው እንዲህ እንድታስቢ የሚያረግሽ ሲለኝ እነ ሜሪ ወሪያቸውን ትተው የኔን ምላሽ መጠበቅ ጀመሩ አቤልም ምላሽ ስጪ እንጂ የሚል አስተያየት ያየኛል ከዛ ኧረ ዛሬ ማም አልደወለችም አሳስቦኝ ነው አልኳቸው አፌ ላይ የመጣውን ግን እውነት ነው ዛሬ ማም አልደወለችም ነበር ከዛም አማን እና ለምን አሁን አደውይላቸውም ከምትጨናነቂ ሲለኝ አይ ችግር የለውም ስወጣ ደውላለው ብያቸው አንዴ አቤልን ሰረቅ አድርጌ አየውት ግን እርሱም እያየኝ ስለነበር በጣም ደንግጬ አንገቴን አቀረቅርኩ

ከዛም የመጣልንን ምግብ በልተን ሊሸኙን ተነሱ ከዛም እየወጣን አማን ስልክ እንለዋወጥ አለኝ እና ስልኬን ሰጥቸው ከሜሪ ጋር ወደ ዶርማችን ተመለስን ከዛም ከነ አማን ጋር በተደጋጋሚ መገናኘት ጀመርን በጣም ጓደኛማቾች ሆንን በትምህርታችንም አሪፍ ውጤት እያስመዘገብን የመጨረሻ አመት ተማሪ ሆንን ከአቤል ጋርም ሚገርም ጓደኝነት ፈጥረናል ሜሪ ይሄን ሰሞን ተቀያይራብኛለች ትፈዛለች ትነጫነጫለች ከዛም አጥብቄ ምን እንደሆነች ጠየኳት...

      ✎  ክፍል አራት እንዲቀጥል
Like ማረግ አይርሱ❤️

┉┉✽‌»‌🌹🌹»‌✽‌┉┉┄
             
 ╔═══❖•🌺•❖═══╗
         ❤️#ፍቅር_ያሸንፋል❤️

‌‌‌‌‌‌‌‌
 
                   #እውነተኛ ስሜት

ቻናላችንንይቀላቀሉ
@yefeker_tiksoche
@yefeker_tiksoche
ከወደዳችሁት ❤️

2024/06/16 05:10:05
Back to Top
HTML Embed Code: