Telegram Web Link
​​  ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 1

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by yohannis 

     
    ገና በልጅነቴ ነበር አባቴ ለሀብታም ጓደኛው እኔን እንደሚድረው ቃል የገባለት
እኔ ባባቴ ሀሳብ ባልስማማ አማራጭ አልነበረኝምና ባልፈልገውም ሁለተኛ ጀረጃ ትምህርቴን እንደጨረስኩ ያባቴ ጓደኛ ከዚህ በኃላ እንድማር ባለመፍቀዱና ካባቴ ጋር በመስማማታቸው እንዳገባ ተወሰነ .....
ድል ያለ ሰርግ ተደግሶ አለሜን ሳላይ አለምሽ ተብሎልኝ ተጋባን...ለመጀመሪያ ቀን ባሌ ቤት ስገባ የእስር ቤት ህይወት አንድ ብዬ መጀመሬን ለራሴ አሰብኩት...

መረረኝም ጣፈጠኝም አማራጭ አልነበረኝምና የቤት እመቤትነት ኑሮ ሳልፈልግ አንድ ብዬ ጀመርኩት.. ..
ቀናቶች ተቆጥረው ወራትን ወለዱ ባሌ ትልቅ ሰው ከመሆኑ ባሻገር ለኔ መልካም ለመሆንና ካለሀብት የሀዘን ኑሮ ሊያወጣኝ ይጥራል... እውነት ለመናገር ክፋ የሚባል አይነት ሰው አይደለም አንዳንዴ ፈገግ ብዬ ካየኝ በደስታ የሚሆነውን ነው የሚያጣው......
የሚጎድልብኝ አንድም ነገር የለም ባዶ የሚባል አይነት ኑሮ ልኑር እንጂ ማንኛዋም ሴት የምትመኘው አይነት የድሎት ህይወት ነው የምኖረው፡፡
ያልኩትንም ነገር በመፈፀም ሆነ የሚያስፈልጉኝን ነገሮች በማሟላት ወደኋላ አይልም ግን እኔ ከአባቴ እኩያ ጋር በፍቅር አብሮ መክነፍ የማላስበው ሆነ...በቃ ጭራሽ የሚሆንልኝን ነገሮች አባት ለልጁ የሚያደረገው እንክብካቤ አድርጌ እስከመቁጠር ደርሻለሁ .....

ከባለቤቴ አቶ ሽፈራው ጋር እስካሁን አንሶላ አልተጋፈፍንም ለየብቻ ነው የምናድረው እንዲህ ፍላጎቴን ማሟላት ከዚህ ከባድ መስዕዋትነት ይጀምራል እኔ ፍቃደኛ ባለመሆኔና ለዚህ ነገር ዝግጁ እስከምሆን እንዲታገሰኝ ስነግረው ቅር ቢለውም ፍላጎቴን አልተቃወመም ለዛም ነው ጥሩ ሰው መሆኑን ባንደበቴ የምመሰክረው ..... ግን አንድ ነገር እርግጠኛ ሆኜ አውቃለሁ እንደሚወደኝ... አንድ ቀን አባቴ ሊጠይቀኝ ሲመጣ እኔ ሌላ ክፍል እንደምተኛ አውቆ በጣም ተበሳጨ..... ይህን አይነት ወርቅ ህይወት ሰጥቼሽ ምን ፈልገሽ ነው እንደዚህ የምትሆኚው አለኝ...... ያባቴ እንደዛ መበሳጨት አልገባኝም......

✎ ክፍል ሁለት  ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
  
​​​​​​
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 2

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


    ባለቤቴ እንኳን የሱን ያህል አልተማረረብኝም ነገሮችን ገና መቀበል እንዳልቻልኩና ትንሽ ጊዜ እንዲታገሰኝ ለባሌ ነግሬው መስማማቱን ስነግረው....
እስከመቼ ነው የሚታገስሽ አመት ሊሞላችሁ ምን ቀረ ባይሆን ውለጂና ይሄን ሀብት የሚወርስ ልጅ ሰጥተሽ አስደስችው አለኝ እኔ ብወልድ ሀብቱ የሱ የሚሆን ይመስል ነገሮችን እንደማስተካክል ቃል ገብቼለት ከስንት ጭቅጭቅ በኃላ አሳመንኩት ባሌ ደውሎ የመጨረሻ ልጁ ነገ ከአውስትራሊያ እንደሚመጣ እና የሚያስፈልግ ነገር ካለ ለሰራተኞች ነግሬ እንዲያስተካክሉ በትህትና ጠየቀኝ ፡፡ ሁሉን እንደማሟላና እንዳያስብ ነግሬው አመስግኖኝ ስልኩ ተዘጋ.....ዛሬ ለምን እንደሆነ ባላውቅም ደስ የሚል ስሜት ተሰምቶኛል! በጠዋት ተነስቼ ቤቱ መስተካከልና አለመስተካከሉን ቼክ አደረኩ ፡፡
ምሳ ምን መዘጋጀት እንዳለበት ነግሬያቸው ተጣጥቤ ፀጉሬን ልሰራ ወደፀጉር ቤት ሄድኩ... ከፀጉር ቤት እንደጨረስኩ የምፈልጋቸውን ነገሮች ገዛዝቼ እቤት ስገባ ነበር ባየሁት ነገር ባለሁበት ደርቄ የቀረሁት... ሀይ እንዴት ነሽ ሄዋን አለኝ ደስ የሚል ቃና ባለው ጎርናና ድምፅ.. .. እ..እንኳን ደህና መጣህ  ማክቤል?? አሀ ማክቤል ብሎ ለሰላምታ እጁን ዘረጋልኝ.... ለደቂቃዎች እጁን ሳለቅ ፈዝዤ በቆምኩበት ቀረሁ... ዋው አባቴ ሚስቱ ቆንጆ እንደሆነች ቢነግረኝም እንደዚህ አልጠበኩሽም ነበር አለ እጁን ከጄ እያላቀቀ...
እ...አመሠግናለሁ እባክህ አረፍ በል መኝታ ቤት ገብቼ መጣሁ ብዬው የመሮጥ ያህል ካጠገቡ ጠፋሁ....
አልጋዬ ላይ በጀርባዬ ተኝቼ የማክቤልን ውበት ከፎቶ ይበልጥ በአካል እንደሚያምርና የኔ ሳየው መደንገጥ እያሰብኩ ነበር ድንገት በሬ የተንኳኳው... ሄዋን... የባሌ ድምፅ ነበር...አቤት አልኩት በድንጋጤ ካልጋዬ እየተነሳው ...
ነይ እንጂ ምሳ እየጠበቅንሽ ነው አለኝና ወደታች ወረደ .... ሊያምርብኝ የሚችለውን ቀሚስ በመምረጥና እራሴን በማስዋብ ጊዜ ወሰደብ...  ልክ ወደ ታች ስወርድ ማክቤል ፊት ለፊት ነበር የተቀመጠው እግሬ ሲተሳሰር ታወቀኝ እንደምንም እራሴን አረጋግቼ ስላስቆየኃቹ ይቅርታ ብዬ ከባሌ አጠገብ ተቀመጥኩ....ባሌ ዛሬም እንደሁልጊዜው አምሮብሻል አለኝ እጄን እየሳመኝ ... ለመጀመሪያ ጊዜ ነው እንዲ ሲያረግ !
ደንግጬ እጄን ከእጁ መነጨኩትና የማክቤልን ገፅታ ተመለከትኩ ምንም አልመሠለውም.... ሚስትህ ቆንጆ ናት አባዬ ለራስህ ታውቅበታለህ አለው እየቀለደ.... ለምን እንደሆነ ባላውቅም በንግግሩ ተናደድኩ ብሽቅ አልኩ በውስጤ.... ምን ነካሽ ሄዋን አንቺ ያገባሽ ሴት ነሽ...አልኩ ለራሴ
ምሳ ተበልቶ እንዳለቀ ማክቤል ማረፍ እንደሚፈልግ ተናግሮ ወደክፍሉ ገባ ሳላስበው ባይኔ ተከተልኩት... ቆሞ ሁኔታዬን ሲመለከት የነበረው ባሌ ....
"ዛሬ ደስ ያለሽ ትመስያለሽ "....አለኝ የባሌ ድምፅ ነበር ከሀሳቤ ያነቃኝ ... ... ም ..ምምን ተገኝቶ ያው እንደበፊቱ ነኝ.... ል....ልግባና ልረፍ ትንሽ እራሴን አሞኛል አልኩት እየተርበተበትኩ ... ...
መድሀኒት ውሰጅ ምን አልባት ፀጉርሽን ስለተሰራሽ ይሆናል አለኝ ይሆናል ልግባና ልረፍበት ብዬው ወደክፍሌ ሄድኩ.....
አልጋዬ ላይ ጋደም እንዳልኩ ነኝ .... የማላውቀው የተዘበራረቀ ስሜት ይሰማኛል ደጋግሜ ማክቤልን አስብና ፈገግ እላለሁ.....


          ꧁༺༒༻꧂


✎ ክፍል ሶስት ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
   ​ 
━━━━━━━✦✿✦━━━━━━━
#የኔ አዳም❤️

ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል😘
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ🤗
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም #ወዴት ነህ?🤷‍♀


           ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​​​​​
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 3

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


በራሴ የባህሪ ለውጥ ግራ ብጋባና ማክቤልን ላለማሰብ ብሞክር ሊሆንልኝ አልቻለም ቀን ከለሊት እሱን ብቻ ነው የማስበው በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለው ቀናቶች ተቆጠሩ፡፡ ማክቤል ያሉት ጓደኞች ውስን በመሆናቸውና እነሱም ከስራ ውጪ ብቻ ስለሚያገኙት አብዛኛውን ጊዜ ብቻውን ነው የሚያሳልፈው አንድ ቀን ታዲያ ወደ ውጭ ስወጣ ስፖርት ሰርቶ ደክሞት በጀርባው መሬት ላይ ተኝቷል በላብ የራሰው ሰፊ ደረቱና ተክለ ሰውነቱ ከከለሩ ጋር ታይቶ አይጠግብም እዛው እንደተኛ ቀና ብሎ እያየኝ እንደምን አደርሽ አለኝ፡፡
ሰላም እንዴት አደርክ ደክሞህ ነው አልኩት አዎ ትንሽ አለ ለመነሳት እየሞከረ በናትሹ በድብርት እኮ ልሞት ነው ላባቴ ልንገረውና ከፈቀደ ምን ይመስልሻል ዛሬ ከእንጀራ እናቴ ጋር ምሳ ውጪ አብረን ብንበላ አለኝ አባባሉን ስላልወደድኩት ቀና ብዬ አይቼው ወደ ውስጥ ልገባ ስል እየሮጠ መጥቶ እጄን ያዘኝ ልቤ በሀይል ሲመታ ይታወቀኛል ፕሊስ እንዳይከፋሽ ለመቀለድ ያህል ነው ይቅርታ እሺ በልምምጥ እሺ ግን ሁለተኛ እንዳትደግመው አልኩት አልደግመውም እና ተስማማሽ አባቴን ላስፈቅደው አለኝ እሱ እንደምንሄድበት ቦታ ይወሰናል አልኩት ቁርስ ላይ ተቀምጠን አባዬ ዛሬ ሚስትህን ባስኮበልልብህስ እቤት መቀመጥ ሰልችቶኛል ብቻዬን ደግሞ ምንም አላውቅም ምሳ አብረን ብንበላና አንዳንድ ነገሮችን አብረን ብናይስ አለው ባለቤቴ ቀና ብሎ ሲያየኝ ምንም አይነት ቅር የመሰኘት ነገር የለብኝም እንደውም ፈገግ ሁላ ብያለሁ ባይሆን የሱ ገፅታ ተቀያይሯል ግን ምንም ማለት ስላልቻለ ባይፈልግም ጥሩ ግን አትቆዩ አለው በውስጤ ደስታዬን መቆጣጠር አልቻልኩም  እረ ፊቴ ላይ ሁላ ያስታውቃል የማክቤል ውበቱ እርጋታውና ስርአቱ ከቀን ወደቀን ልቤን እየገዛው ነው፡፡ ቁርስ በልተን ስንጨርስ ባለቤቴ ተሰናብቶን ወደቢሮው ሄደ ማክቤልም እስከምንወጣ ጓደኞቼን በስካይፕ ላውራ ብሎኝ ወደ ክፍሉ ገባ እኔም ወደ ክፍሌ ገብቼ የምለብሰውን ልብስ መምረጥ ጀመርኩ የቁምሳጥኑ ልብስ አንድ አልቀረኝም በየተራ ሁሉንም ሞከርኩት በመጨረሻ ያመንኩበትን አዘጋጅቼ ሰአቱ እስከሚደርስ አላስችል ስላለኝ ልዋኝ ወደውጪ ሄድኩ በደስተኝነቴ አደለም ባለቤቴ ሰራተኞቹ ተገርመዋል፡፡ ሁሌም ካጠገቤ የማጠፋውና የሚሠማኝን ሁላ የማልደብቃት አዛለች ሄዋንዬ አለችኝ የሚጠጣ ይዛልኝ እየመጣች ከሷ ጋር ማውራት ደስ ይለኛል እንደ እናት ነው የምታዝንልኝ ወዬ አዙ አመሠግናለሁ አልኳት ብርጭቆዬን እየተቀበልኳት አለሜ ምን ተገኝቶ ነው እንደዚህ በደስታ የከነፍሽው አለችኝ በደስታዬ መደሰቷ ፊትዋ ላይ እያስታወቀ አዙ ብነግርሽ አታምኚም አልኩዋት ከገንዳው ወጥቼ አጠገቧ እየተቀመጥኩ አቤት አቤት ንገሪኝ ልስማው ታዲያ አለች እንደናት እየደባበሰችኝ ከማክ ጋር ለምሳ ልንወጣ ነው አልኳት እንደህፃን እየፈነደቅኩ ኧረ ቆይ ..ቆይ ..ቆይ ..እንዴት ሆኖ አለች ፊቷን ፈታ ኮስተር እያረገች.....


ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
         
🤷‍♂🤷‍♂አዳም ግራ ገባው🤷‍♂🤷‍♂


ሜላትን በfacebook ሞትኩልሽ እያለ
ቅድስትን በviber ባፉ እያታለለ
ሓናንን በSkype ሁሌ እያማለለ
ሳባን በwhat's up እያቀማጠለ
ከለታት ባንዱ ቀን እንዲህ ተፈጠረ...
*
ሜላት ልትመጣ ነው ወዳለበት ስፈራ
ቅድስት ተዘጋጀች ልትሆን ሙሽራ
የሓናን ቤተሰብ አድምቀው ጭፈራ
ጫጉላዋን ለማድመቅ ተዘጋጀች ሳባ
አዳም ግራ ገባው የትኛዋን ያግባ
የሚያደርገው ሲያጣ እኛ channel ገባ
😂😂😂😂😂😂😂

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌ ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​​​​​.
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 4

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


  አዙ ሆነ ማክ ሽፈራውን አስፈቀደ እሱም ተስማማ ደስ አይልም አልኳት እረ እኔስ ምኑም ደስ አላለኝም ሄዋንዬ ምን አስበው እሺ አሏችሁ ጋሼ ለማንኛውም ተጠንቀቂ አለሜ ብላ ወደ ውስጥ ገባች፡፡ እኔም ተመልሼ መዋኘቴን ጀመርኩ ግን የአዛለችን ንግግር እያሰብኩ ነበር የዛሬው ደስታዬ ምንም ነገር እንዲያጠወልገው አልፈልግም እቤት ገብቼ መዘገጃጀት ጀመርኩ
አንዲት ሙሽራ እንኳን ለሰርጓ እኔ ያባከንኩትን ሰአት አታባክንም በጣም ለማማርና ቀልቡን ለመሳብ የቻልኩትን ያህል ለፋሁ ልክ እንደጨረስኩ በሬ ተንኳኳ ማክቤል ነበር  አልጨረሽም አለኝ ኧረ ጨርሻለሁ አልኩት መኪናው ጋር እጠብቅሻለሁ እሺ መጣው አልቆይም አልኩት የት መሄድ እንደምፈልግ ጠይቆኝ በኔ ምርጫ ወደ አንድ ሬስቶራንት እየሄድን ነው ስትዋኚ ጎበዝ ነሽ አለኝ ድንገት ነበር የተናገረው አባባሉ አስደነገጠኝ እ...የት አየኸኝ አልኩት እንደማፈር እያልኩ ቅድምም ሌላም ቀን አይቼሻለሁ ማን አስተማረሽ አለኝ ትምህርት ቤት እያለን አንድ ዋና በጣም የምትወድ ጓደኛ እንደነበረችኝና እሷ እንዳስተማረችን ነገርኩት አሪፍ ነው እኔም ዋና እወዳለሁ አለኝ እንደዚህ እያወራንና ስለግል ታሪኬ አንዳንድ ነገሮችን እየተጫወትን ደረስን ከመኪናው ወርዶ በር ከፍቶ እጄን ይዞ አወረደኝ
ማክቤል ስርአቱ በጣም ነው የሚገርመው ምሳ እየበላን ድንገት ለምንድነው አንቺና አባዬ የተለያየ ክፍል የምትኖሩት አለኝ ጥያቄው ድንገተኛ ስለሆነ የጎረስኩት ትን አለኝ እንዴ ምነው ጥያቄዬ የዚህን ያህል ያስደነግጣል አለኝ  ውሀ እያቀበለኝ አ..አይ እንደሱ ማለቴ አይደለም አልኩት እና እንዴት ነው አለኝ ለመስማት የጓጓ በሚመስል ድምፅ?
እስኪ ሁሉንም ነገር ንገሪኝ አለኝ ተመቻችቶ እየተቀመጠ ያለውን ነገር በግልፅ ነገርኩት ላባቱ የሚሰማኝ ነገር አባት ለልጁ ከሚያደርገው እንክብካቤ ያልዘለለ እና የኔም እዛ ቤት ኑሮ ከስር ቤት ያልተናነሰ መሆኑንም ጭምር በሀዘኔታ እያየኝ አይዞሽ እሺ አለኝ ከዚያ ሌላ እኔን የሚያፅናናበት መንገድ የለምና እሺ አልኩት አንገቴን ደፍቼ እንዴ ከድብርት እንድታሶጭኝ ይዤሽ ብመጣ ጭራሽ ልታስደብሪኝ ነው እንዴ አለ ለመቀለድ እየሞከረ ይቅርታ አልኩት ፈገግ ብዬ ታዲያ አሁን የት እንሂድ ዛሬ በአንቺ ምርጫ ነው አለኝ ዛሬ የምትለዋ ቃል ሌላም ጊዜ አብረን እንደምንወጣ ተስፋ ሰጠችኝ ከዛን ቀን በኃላ አባቱን እያስፈቀድን አንዳንዴ ዝም ብለን እየወጣን መዝናናቱን ተያያዝነው ሲለንም እያመሸን መግባት ጀመረናል በቃ የማንሄድበት ቦታ የለም ከማክ ጋር ስሆን ሁሉን ነገር እረሳለሁ ህይወቴ በደስታ ተሞላች ቅልጥ ያለ ፍቅር ይዞኛል ቀንም ሌሊትም የማስበው ስለማክ ብቻ ሆኗል
ማክም ፍቅር ሳይዘው አይቀርም......



✎ ክፍል አምስት ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
#የኔ አዳም❤️

ካወኳቸው ሁላ ልቤ አንተኑ መርጧል
ማንነትህ ማርኮት ማፍቀሩን አጋልጧል😘
ምን ቆንጆ ቢሞላ ቢትረፈረፍ በዝቶ
አይኔም ሌላን ላያይ ምሏል ተገዝቶ🤗
እግሮቼም ካንተ ውጭ ከቶውን ላይሄዱ
ወስነው ቆርጠዋል ተዘግቷል መንገዱ
ከንግዲህ ለኔ ጎን ያለኸው አንተ ነህ
ብዬ ምፅፍልህ የኔ አዳም #ወዴት ነህ?🤷‍♀

           ┄┅┅┄┅✶♥️✶┅┄┅┅┄
              ‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌
​​​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 5

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


  የምገዛቸውንም ሆነ የምለብሳቸውን ልብሶች የሚመርጥልኝ የፀጉር ስታይሌን የሚመርጥልኝ እሱ ሆኗል የማክ አባት ጭራሽ ባሌ መሆኑን እረስቼዋለሁ አንድ ቀን አምሽተን ከውጪ እንደገባን ከመኪና ሳንወርድ ሄዋኔ ብሎ ጠራኝ ወዬ ማክ አልኩት በፍቅር እያየሁት ነይማ የሆነ ነገር አለ ፀጉርሽ ላይ አለኝ ወደኔ እየተጠጋ ወደሱ ስቀርብ ድንገት ሳመኝ በደስታ ልሞት ምንም አልቀረኝም ጉንጮቼ ቀሉ ሲያልበኝ ይታወቀኛል ክፍሌ ገብቼ በደስታ አልጋዬ ላይ ዘለልኩኝ ወንድ ሲስመኝ የመጀመሪያዬ ነው እሱም ብቻ ሳይሆን እኔ የምወደው ቀን ከሌሊት የማስበው ማክ እኮ ነው የሳመኝ!!! በደስታ የምሆነውን አጣው ልብሴን ቀይሬ ለመተኛት ብሞክር አልቻልኩም የማስበው ማክንና የማክን የመጀመሪያ ኪስ ብቻ ነበር ድንገት መደወልና ድምፁን መስማት ፈለኩ ልደውል ስል ደውዬ የምለው ነገር ግራ ገባኝ ስልኬን ይዤው ለብዙ ደቂቃዎች ማሠብ ጀመርኩ በመሀል ስልኬ ጠራ ማክ ነበር ሴኮንድ አላባከንኩኝም ማክ አልኩት ወዬ አልተኛሽም እንዴ አለኝ እንቅልፍ እንቢ አለኝ አልኩት ለምን ምን እያሰብሽ አለኝ አንተን አልኩት ድንገት ከአፌ ያመለጠ ቃል ነበር ስለኔ ምን አለኝ አፍሬ ዝም አልኩት እኔም ስላንቺ እያሰብኩ ነበር
የዛን ቀን ለረጅም ሰአታት አወራን ሌሊቱ አላልቅ ብሎኝ እንቅልፍ በአይኔ ሳይዞር ማክን እያሰብኩ ሊነጋጋ ሲል እንቅልፍ አሸለበኝ ጠዋት የአዙ ድምፅ ነበር ያነቃኝ  ሄዋንዬ ዛሬ ተኝተሽ ልትውይ ነው እንዴ አለችኝ መጋረጃውን እየከፈተች በይ ተነሽ አለችኝ የለበስኩትን እየገለጠች በግድ አይኔን ገልጬ እንዴት አደርሽ አዙ አልኳት ለመነሳት እየተንጠራራው እግዛሄር ይመስገን ጎሽ ተነሽ! ጋሽዬ ለቁርስ እየጠበቁሽ ነው አለች ልነሳ የነበረው እንደዛ ስትለኝ ተመልሼ ተኛሁ በግድ አስነሳችኝ ወደመታጠቢያ ቤት እየሄድኩ ትላንት የሆነውን እየፈነደኩ ነገርኳት
አንቺ ልጅ እኔ አላማረኝም አለች የመከፋት ፊት እየተነበበባት እኔ ንግግሯን ከምንም ሳልቆጥር አዙ ደግሞ ዝም ብለሽ ታካብጂያለሽ አልኳት የምለብሰውን እየመረጥኩ አዙ ይሄ ያምራል ወይስ ይሄ አልኳት በሁለት እጆቼ የያዝኩትን ልብስ እያማራጥኳት ኤዲያ እኔ ምኑም አላማረኝም አንዱን ልበሽና ይልቅ ተከተይኝ አታስጠብቂያቸው ብላኝ ጥላኝ ወጣች እኔ እየዘፈንኩና በደስታ እንደ ህፃን እየፈነደኩ ወደታች ስወርድ የማክ አባት ፊት ተቀያይሯል ምነው ደና አይደለህም እንዴ አሞሀል አልኩት መልስ የለም ዛሬ ከቤት እንዳትወጪ አለኝ ማስጠንቀቂያ በሚመስል ድምፅ እንዴ ለምን አልኩት ግራ እየተጋባው ባልሽ መሆኔን ላስታውስሽ አለኝ ቀና ብሎ ያልተለመደ ፊት እያሳየኝ በዚህ መሀል ነበር ማክ እንደምን አደራቹ እያለ የወረደው የማክ አባት ምንም ሳይመልስ ከተቀመጠበት ተነስቶ ያልኩሽን እንዳትረሺ መልካም ቀን ብሎኝ ወጣ
ማክ ግራ በመጋባት እያየኝ ምን ሆኖ ነው ተጣለቹ አለኝ ያለኝን ነገርኩት ማታ ስስምሽ አይቶ ይሆን እንዴ አለኝ ባባቱ ሁኔታ ግራ እንደተጋባ እ ይሆናል አሁን ምን እናድርግ አልኩት ትንሽ እስከሚረጋጋ በቃ አንወጣም ነገሮችን እናስተካክላለን አይዞሽ አለኝ ተነስቶ በድጋሚ እየሳመኝ ከዛን ቀን በኃላ አባቱ እስኪረጋጋ ከቤት ባንወጣም ግን አንድ ላይ ሆነ የምናሳልፈው ሁለታችንም በፍቅር ከንፈናል አባቱ ሲመጣ ፊት ለፊቱ እንደበፊቱ እናወራለን ግን በቃ ቤቱን በአንድ እግሩ ስናቆመው ነው የምንውለው የቤቱም ሰራተኞች በእኛ ሳይድ ነበሩና ማንም ለማን ምንም አይናገርም ነበር እኛ በድብቅ ፍቅራችንን እያጣጣምን ነው ከማክ ጋር ከመሳሳም ውጪ ምንም አናደርግም ሲውል ሲያድር በድብቅ አንድ ቀን እኔ ጋር ሌላ ቀን እሱ ጋር ነው የምናድረው እስከምንጋባ ምንም ላናደርግ ወስነናል በቃ በጣም የሚያስቀና ፍቅር ውስጥ ገብተናል ማክ ወደ አውስትራሊያ ላለመመለስ ከተመለሰም አብረን እንደሆነ ወስኗል
አንድ ቀን እሁድ የማክ አባት እንደሚፈልገኝ በአዙ በኩል ልኮብኝ ስሄድ በረንዳ ላይ አኩርፎ ተቀምጧል ሄዋን አለኝ የሆነ ቁጣ ባዘለ ድምፅ አቤት አልኩት ምን ሊለኝ ነው በሚል ፍራቻ እንደተጋባን ዝግጁ አይደለሁም ምናምን በሚል ተራ ምክንያት እስካሁን ለብቻሽ እየተኛሽ ነው እኔም ስለምወድሽና ስሜትሽን ላለመጋፋት ታግሼሻለሁ አሁን ግን የሚበቃ ይመስለኛል የማሰቢያ ሳምንት ሰጥቼሻለሁ ካልሆነ ግን ወደ ነበርሽበት ህይወት ትመለሻለሽ አለኝ ዛቻ ባዘለ ድምፅ ንግግሩ አናዶኝ ልሄድ ስል አልጨረስኩም አለ ቆጣ ብሎ ከልጄ ጋር ያለውን ነገር የማላውቀው እንዳይመስልሽ ከዚህ ቤት ብወጣ እሱ አለልኝ ብለሽ ከሆነ እንዳታስቢ ሁሉን ነገር አሰቤበታለው ደግሞ ማክቤል ለአንቺ የሚሆን ልጅ አይደለም አባትሽን በማታገኚው ነገር ላይ ተማምነሽ እንዳታሳዝኚው የአባትሽ ከባድ ሚስጥር በእጄ ላይ ነው አለ አንቺ አይሆንም የምትይ ከሆነ ባባትሽ ፈርደሽ ነው አለኝ.....

✎ ክፍል ስድስት ️ ......  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 6

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


ምን እንደማደርግ ግራ ገባኝ አምላኬ ሆይ አንተ ትግስቱን ስጠኝ አልኩኝ በውስጤ ደስታዬ ላይ ውሀ ቸለሰበት ክፍሌን ዘግቼ ስቅስቅ ብዬ አለቀስኩ ምንድነው የማረገው አሁን ለማክ ልንገረው ወይስ ይቅር እያልኩ ሳስብ ማክ ደወለ ሄዋንዬ እስካሁን ተኝተሻል እንዴ አለኝ ገና መነሳቱ ነበር አይ ቆየው አልኩት ምን እንደሆንኩ ጠየቀኝ በስልክ አይሆንም ናና እናወራለን አልኩት ደቂቃ አልፈጀበትም ነበር አባቱ ያለውን ስነግረው በጣም ደነገጠ ምን ማድረግ እንዳለብን እያሰብን በቃ አይዞሽ አንቺ ብቻ አትከፊ መፍትሔ አናጣም አለኝ
ድንገት ለምን አባትሽ እና አባቴን የሚያስተሳስራቸውን ነገር አባትሽን አጠይቂውም ከዛ በምንችለው መንገድ ዶክሜንቱን መውሰድ ከዛ በኃላ ያለውን ነገር እንጋፈጣለን አለኝ አባቴ ለነገሮች ድብቅና ሀይለኛ እንደሆነ ባውቅም በማክ ሀሳብ ተስማማው ጥሩ በቃ ዛሬ ከአባቴ ጋር እናወራለን አልኩት ተነስቼ እንድተጣጠብና አባቴ ጋር አብረን እንደምንሄድ እሱ ውጪ እንደሚጠብቀኝ ተነጋግረን እሱም ወደ ክፍሉ ሄደ፡፡
በተባባልነው መሠረት ወደ አባቴ ጋር ለመሄድ ስንወጣ የማክ አባት ወዴት ነው አለን ከላይ መኝታ ቤቱ በረንዳ ላይ ቆሞ
እንዴ አባዬ አለህ እንዴ አለው ወደ አባቱ እየተመለከተ አዎ አለው ወዴት ነው አለ ደግሞ እየጠየቀ ምን ትላንት ለሰው መስጠት የነበረብኝ እቃ ነበር ቦታውን ስላላወኩት አሁን ሄዋንን አሳይኝ ብያት እሺ ብላኝ እየሄድን ነው እንዳለህ አላወኩም ነበር አለው ጥሩ ቶሎ ተመለሱ አለው ፊቱ ሳይፈታ ዋናው መፍቀዱ ነው አልኩ ተመለሽ የሚለኝ መስሎኝ በጣም ፈርቼ ነበር ከግቢ እንደወጣን ተረጋጊ የኔ ቆንጆ ብሎ ሳመኝ
ማክ ፈራሁ አልኩት እጁን አጥብቄ ይዤ
አትፍሪ ምንም አይመጣም መቼም አንለያይም ካልሆነ እንጠፋለን አለኝ ለመቀለድ እየሞከረ እስኪ አትቀልድ ለራሴ ጨንቆኛል አልኩት አይዞሽ የኔ ቆንጆ ሁሉም ይስተካከላል አለኝ አባቴ ቤት ደረስን አናግረሻቸው ነይ አለኝ ማክ እሱም ጨንቆታል አባቴ ቁጭ ብሎ ስልኩ ላይ ካርታ ይጫወታል አባዬ አልኩት እንዴ ሄዋኔ ምን እግር ጣለሽ ለምን መጣሽ አለኝ ቀና ብሎ እየሳመኝ እንዴ እንደዚህ ይባላል እንዴ አልናፍቅህም አልኩት አይ እንዴት ሳትነግሪኝ ብዬ ነው አለኝ ምንም ሳይመስለው አባቴ ለኔ ግድ የለውም ሁሌ ይገርመኛል እናቴ ከሞተች በኃላ ብቸኝነት እየተሰማኝ ነው ያደኩት
ፈልጌህ ነበር አባ አልኩት አሁንም ቀና ብሎ ሳያየኝ ምነው በሰላም አለኝ  አዎ ምንድነው አቶ ሽፈራው አንተን የሚያስፈራራበት ሚስጥር ምንድነው አልኩት የሰማውን ማመን አልቻለም በጣም ደንግጦ ከተቀመጠበት ብድግ አለና አንቺ እንዴት አወቅሽ ሊመታኝ በሚመስል ሁኔታ አፍጥጦ እንዴ አባ የዚህን ያህል ከባድ ሚስጥር ነው እንዴ ለኔ ለልጅህ የማይነገር ?? አልኩት ልጅ ያሳጣሽ ዝም በይ ብሎ ጮኸብኝ ሁኔታው በጣም ነበር የሚያስፈራው ምንም ሳልተነፍስ ጥጌን ይዤ ቁጭ እንዳልኩ ነኝ አባቴ በንዴት ቤቱን እየዞረው ነው ድንገት ቆም ብሎ ቆይ አንቺ በመሀላችን ሚስጥር እንዳለ በምን አወቅሽ አለኝ ስሩ እስጊገተር እየጮኸ
እ ....ያው ሽፈራው ነው የነገረኝ አልኩት እየተንቀጠቀጥኩ እኮ እንዴት አለኝ አይኑን እንዳፈጠጠ እ ...አብረን መተኛት አለብን ነው የሚለው አልኩት ቃላቱን ለመጨረስ እየፈራው ያባቴ ንዴት ይባስ ጨመረ እና ለምን አተኝም ታዲያ ያገባሽ የቤቱ ጌጥ ሊያረግሽ ኖሯል አንቺን ቤቱ አስቀምጦ የሚቀልብበት ምንም እዳ የለውም ትሰሚኛለሽ ምንም ጊዜ ሳታባክኚ አሁኑኑ ሄደሽ ይቅርታ ጠይቀሽ የሚልሽን ካለምንም ድርድር ፈፅሚ አለኝ ቁርጥ ባለ ድምፅ ጌታዬ ሆይ መፍትሔ ፍለጋ መጥቼ ጭራሽ አጣብቂኝ ውስጥ ልግባ አልኩኝ ለራሴ፡፡ አሁን ማጉረምረሙን ትተሽ ዳይ ወደ ባልሽ ደሞ ከኔ ጋር እንዳወራንም ሆነ እንደመጣሽ እንዳትነግሪው አለኝ
ቦርሳዬን አንሴቼ ሳልሰናበተው እንኳን እየሮጥኩ ወጣሁ......


✎ ክፍል ሰባት ከ50 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 7

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺

ማክ በሩቅ ሁኔታዬን አይቶ ከመኪናው እየወረደ ምነው ፍቅር ምን ሆንሽ ተረጋጊ እንጂ ታውቆሻል እንዴት እንደሆንሽ ብሎ አቀፈኝ ማክ እባክህ አርቀህ ከዚህ ውሰደኝ አልኩት ምን እንደሚል ግራ ገብቶት ካስገባኝ በኃላ ወዴት እንደሚሄድ እንኳን ሳያውቅ ነዳው መንገድ ከጀመርን በኃላ ነበር ወዴት ልንዳው ብሎ ጠየቀኝ ደስ ወዳለህ ግን በቃ ፀጥ ያለ ቦታ አልኩት በሚያስገርም ፍጥነት ከከተማ የሚያስወጣውን መንገድ ያዘ፡፡ እኔ ዝም እንዳልኩኝ ነኝ ማክ አልፎ አልፎ ምን እንደሆንኩ እየጠየቀኝ ነው ማልቀስና ዝም ብቻ የሆነ ጭር ያለ ቦታ ላይ ስንደርስ አቆመ ምንድነው የኔ ቆንጆ በጭንቀት ልትገይኝ እኮ ነው አለኝ ማክ ሁሉም ነገር ተስፋ የለውም አልኩት እያለቀስኩ በጭንቀት እያየኝ የሆንኩትን ጠየቀኝ አባቴ ያለውን ስነግረው ለደቂቃዎች ዝም ብሎ ባባቢና ባባትሽ መካከል ያለው ሚስጥር ከባድ ነው ማለት ነው አለኝ አዎ በትክክል አልኩት
ስለዚህ አባትሽ ለሱ ሚስጥር ብሎ ለሚስጥሩ ከሸጠሽ አንቺ ለምን ተባባሪው ትሆኛለሽ ከኔ ጋር ነሽ በሀሳቤ ትስማሚያለሽ አለኝ በቆራጥነት የአባቴ የጭካኔ ፈተና ሁኔታው ታወሰኝ አዎ ማክ ከአንተ ጋር ነኝ አልኩት እንግዲያውስ ነይ ብሎ መኪናውን አዙሮ ተመለሠ ማክ ምን ሰልታደርግ ነው አልኩት አባቴን ላናግረው ነው እንደምንዋደድ ነግሬው ያመጣውን ያምጣ ካስፈለገውም ቤት ለቀን እንወጣለን አለኝ ማክና አባቱ በእኔ ምክንያት እንዲጣሉ አልፈልግም ማክን በስንት ልመና አባቱ የሰጠኝ ገደብ ስላለ እስከዛ ተረጋግተን መፍትሔ እንፈልጋለን አሳምኜ ሀሳቡን አስቀየርኩት ወደ ቤት ስንመጣ የማክ አባት ቤት አልነበረም እንደምንም ወደ በፊት ደስታችን ለመመለስ ሞከርን ምሳ እየተሳሳቅን በፍቅር በላን ትንሽም ቢሆን ካለንበት ሙድ ወጣን ማክ ሻወር እስከሚጨርስ ያባቴን ንግግር ማሰብ ጀመርኩ ምንድነው የአባቴ ከባድ ሚስጥር
ለምንስ እንደዛ ደነገጠ የኔ የልጁ ሚስጥሩን ማወቅ ቢረዳው እንጂ ምንድነው ጉዳቱ ይሄን እያብሰለሰልኩ ማክ በሩን ከፍቶ ወጣ ማክዬ ይሄን ደረት እንዴት እንደምወደው እኮ አልኩት ከንፈሩን እየሳምኩ አስቀናሽኝ እኔንስ አለ እየቀለደ አይ ....አይ አንተንኳን አይመስለኝም አልኩት በዚህ እየተቃለድን ቤቱን ስንዞረው አዙ ድንገት በሩን በርግዳ ገባች ጋሽዬ መጡላችሁ አለችን ማክም እኔም ወደየክፍላችን እሮጥን ይሄ የቃቃ ጨዋታ መቼ እንደሚያልቅ ጨነቀኝ
ያባቴ የክፋት ፊትና የሽፈራው ዛቻ ሳስበው እንባዬ ሳይታወቀኝ ሲወርድ ተሰማኝ አባቴ ለኔ ግድ የለውም ቢሆንም እኔ ግን አባቴ ነውና እወደዋለው፡፡ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ የአባቴንም ሆነ የኔን ህልውና ልታደግ የምችልበት መፍተሄ እንዴት እንደማገኝ ማሰብ እንዳለብኝ ወሰንኩ ያባቴ ለኔ ያለው ጥላቻና ግዴለሽነቱ ምንነቱን በማላውቀው ሚስጥር ምክንያት እንዲጎዳው መፍቀድ እንደሌለብኝ ወሠንኩ፡፡ ያባቴ ሚስጥር ምንም ሆነ ምን አሳልፌ ልሰጠው አልፈቅድም፡፡ ምንም ቢሆን አባቴ ነዋ......!! ግን በዚህ ባንድ ሳምንት ውስጥ ምን አይነት ተአምር መፍጠር እና ከዚህ ችግር ማምለጥ ይቻላል ግራ ተጋብቻለሁ ይህን እያሰብኩ ሌሊቱን ያለ እንቅልፍ አሳለፍኩ ማክም እኔም በጭንቀት የማይገፋ ለሊት አሳለፍን
በማግስቱ ጠዋት ሁላችንም ለቁርስ ተሰብስበናል ድንገት የማክ አባት......


✎ ክፍል ስምንት ከ100 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
🚫#​​እሱን_ተይው ..... 🤦‍♀

ስትወጅው ካልወደደሽ
ስትቀርቢው ካልቀረበሽ
ስትጠጊው ካልተጠጋ
ስለፍቅር ካላወጋ
   
      💓አይሆንሽም እሱን ተይው
      አትድከሚ ላታገኚው
      ማፍቀርሽን እያወቀ
      በፍቅራችሁ ካልፀደቀ💔

💞በቃልሽ ላይ ካላመነ
ጥርጣሬ ከሰፈነ
በመውደድሽ እየኮራ
የውሸት ፍቅር ከሚሰራ
ልብሽ ይቁረጥ እሱን ተይው
ላንች ላይሆን አትወትውችው💞💔💘

━━━━━━🌹✦✗💔✦━━━━━━━
  
​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 8

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
  ❦መንታ ልቦች❦


የማክ አባት ለማክ ወደ አውስትራሊያ መቼ ልትመለስ አሰብክ አለው ማክ አባቱ ቶሎ ሊገላገለው መፈለጉን ቢረዳም እንዴ አባዬ ሰለቸውህ እንዴ አለው በቀልድ መልክ አይ ነገሩን ነው ለእህቶችህ የምትወስደውን ነገሮች እንድናዘጋጅልህ ነው አለው ለመሄድ እየተነሳ ሽፈራው እንደወጣ ካረጋገጥን በኃላ እኔና ማክ ልክ ከተገናኘን የቆየን ይመስል ተናንቀን ተሳሳምን ማክ ይሄ የድብቅ ህይወት ማብቃት አለበት አልኩት ልክ ነሽ የኔ ፍቅር እኔም እያሰብኩበት ነው አለኝ
ግን እንዴት እንደሆነ ለሁለታችንም ግራ ገብቶናል ማክ ቤት መቀመጥ ሰለቸኝ ለምን አንወጣም አልኩት አዎ እንደውም ልወስድሽ ያሰብኩበት ቦታ አለ ዛሬ አለኝ
የት አልኩት እንደህፃን እየተቁነጠነጥኩ
እሱማ ሰርፕራይዝ ነው ባይሆን ተነሽ ልበሽና እንውጣ አለኝ ጊዜ አላባከንኩም እየፈነደኩ ወደ ላይ ስወጣ ማክ በግርምት ቆሞ ያየኛል ልብሴን ለመልበስ ጊዜ አልፈጀብኝም ነበር ለባብሼ ከመቅፅበት ወጣው አቤት ፍጥነት ይሄኔ ሰርፕራይዝ ባይሆን ባመትሽም አትወጪም ነበር አለኝ ከእቅፉ እያስገባኝ
ታዲያ ሁሌ ቶሎ እንድወጣ ለምን ሰርፕራይዝ አታዘጋጅም? አልኩት እየሣምኩት እኔና ማክ ብቻችንን ስንሆን አለምን እንረሳለን በቃ ምንም ትዝ አይለንም አሁን እንኳን እንደዚህ አይነት ችግር ውስጥ እያለፍን እንኳን በኛ ፍቅር መካከል ምንም የተቀየረ ነገር የለም
እንደውም ፍቅራችን በጣም እያማረበት ነው አንዳችን ካላንዳችን መኖር እስከማንችል እስከሚመስለን ድረስ ፍቅር ጨምረናል ልክ ማክ ያለኝ ቦታ ልንደርስ ስንል አይኔን እንድጨፍን ነገረኝ
ማክዬ ቸኮልኩ አልኩት ደርሰናል ብሎ መኪናውን ሲያቆም ተሰማኝ አይኔን እንደጨፈንኩ በማክ መሪነት ወደሚገርመው የማክ ሰርፕራይዝ አመራን አይኔን ማመን ነበር ያቃተኝ እኔ አላምንም ብዬ ማክ ላይ ተጠምጥሜ የደስታ እንባ አነባሁ ማክ ወደገዛው አስደናቂና ውብ ቤት ስንገባ እንኳን ደህና መጣሽ የኔ ልዕልት የሚል በሰፋፊው ተፅፏል ቤቱ በሚያማምሩ የቤት እቃዎችና አበባዎች አሸብርቋል፡፡
ደስታዬ ወደር አጣ የምናገረው ጠፋብኝ ማክ ላይ ተጠመጠምኩበት እንደኔ የታደለች ሴት አለም ላይ የለችም እኮ አልኩት እየሳምኩት እኔም እድለኛ ነኝ አባቴ አንቺን ስላመጣልኝ አለኝ ወዲያው ደስታዬ ጠፋ የረሳሁትን ነገር አስታወሰኝ
ማክ የፊታችን ገፅታ መቀያየር አይቶ አትዘኝ የኔ ማር የምታዝኚበት ቀን አብቅቷል አለኝ እንዴ ማክ አልኩት ሽሽሽ....አለኝ ወዳንገቱ ስር እያስገባኝ
በቃ አብቅቷል አለኝ ያባትና የልጅ ፍልሚያ ተጀመረ የዛን ቀን ለመጀመሪያ ጊዜ ውጭ አደርን፡፡ ሽፈራው ደጋግሞ ቢደውልም አላነሳንም ማክ ሁሉንም ነገር ተዘጋጅቶበት ነበር እኔ ሳላውቅ ከአዙ ጋር   ተመካክረው ጠቃሚ የምላቸውን ነገሮችና ልብሶች በሻንጣ አዘጋጅተዋል
እሱም እንደዛው በሁኔታው መገረሜን እስካሁን አላቆምኩም ሁሌም የማክ መልካምነት ይገርመኛል ቤታችን የመጀመሪያዋን ለሊት አሳለፍን የነፃነት ትንፋሽ እየተነፈስኩ አደርኩ ከማክ ውጪ የነበርኩዋቸው አስቀያሚ ትርጉም አልባ ጊዜቶች ሳስታውስ ይበልጥ ነፃነት ታወቀኝ ማክን እንደተኛ ይበልጥ እቅፍ አደረኩት ማክ በእንቅልፍ ውስጥ ሆኖ አትተኛም እንዴ የኔ ውድ አለኝ ደረቱን ተደግፌ አሸለበኝ ዛሬ ሶስተኛ ቀናችንን አስቆጥረናል ከቤት ከወጣን ሽፈራውና አባቴ እያፈላለጉን እንደሆነ አዙ ነግራናለች ማክ አባቱን ማናገር እንዳለበትና ነገሮችን በዚህ ሁኔታ መቀጠል እንደማይችሉ ነግሮኝ ከቤት ወጣ፡፡ ማክ አባቱን አናግሮ እስከሚመጣ በጭንቀት ሞትኩ በተደጋጋሚ ስደውልለት አያነሳም ሲጨንቀኝ አዙ ጋር ስደውል ማክና አባቱ ለረጅም ሰዓት ሲጨቃጨቁ ቆይተው በመጨረሻም ተጣልተው እንደተለያዩ እና ከቤት ከወጣም እንዳልቆየ ነገረኝ......


✎ ክፍል ዘጠኝ ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
.          ልቤን መልስልኝ

😐ልትሄድ ከሆነ ላይቀር መለየቱ😐
😔ቢበቃኝ ይሻላል ባንተ መጎዳቱ😔
🚶ቀልብህ ካላረፈ እግረኛ ሆነህ🚶
🏃መጓዝህ ካልቀረ ከእኔ መራቅህ🏃
💔ለምን አስፈለገ ልቤን መስረቅህ ?💔
​​​​​​.
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 9

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺



እሱዋን አመስግኜ ዘግቼ ማክ ጋር በድጋሚ ስደውል አነሳ የኔ ፍቅር ይቅርታ አሁን ነው የጨረስኩት ልደውልልሽ እያሰብኩ በአጋጣሚ እህቶቼ ደውለው እያወራው ነበር አለኝ ፍፁም መረጋጋት አይታይበትም እሺ ግን ሰላም አልመሰለኝም ድምፅህ ምን ተፈጠረ ለመስማት እየጓጓው ማሬ እየደረስኩ ነው ስመጣ እነግርሻለው ግን አታስቢ ምንም አልተፈጠረም አለኝ እኔም እስከሚደርስ በጉጉት እንደምጠብቀው ነግሬው ምሳ ምን እንደተሠራ ላይ ወደ ኪችን ሄድኩኝ ማክ ሲመጣ ግን በጣም ተረጋግቶል ምሳ እየበላን ሄዋኔ ከእኔ ጋር የትም ለመሄድ ዝግጁ ነሽ አለኝ አዎ የኔ ማር እስከአለም ጥግ ድረስ አልኩት ተነስቶ እቅፍ አርጎ ሳመኝ በቃ ወደ አውስትራሊያ እንሂድ እዛ በሰላም እንኖራለን ሁሉንም ወደ ኃላ ትተሽ ከእኔ ጋር ተጋብተን አዲስ ህይወት እንኖራለን አንቺን የሚመስሉ ቆንጆ ልጆች ትወልጅልኛለሽ ከልጆቻችን ጋር ደስተኛ ቤተሰብ መስርተን በሰላም እንኖራለን አለኝ ምንም እንኳን በማክ ሀሳብ ብስማማና ብደሰትም ያለናት ብቻውን ያሳደገኝን አባቴን ለሽፈራው አሳልፌ ልሰጠው አልፈቀድኩም በርግጥ አባቴ ለኔ ጥሩ አልነበረም አባት እያለኝ አባት እየናፈቀኝ ነው ያደኩት እሱ ለኔ መጥፎ ቢሆንም ለኔ አባቴ ነውና ክፋቱን በክፋት ልመልስለት አልፈልግም ምን አልባት የሰራው ወንጀል እንደሽፈራው አባባል አባቴን ክፋ ችግር ላይ የሚጥለው ከሆነ ፀፀቱን አልችለውም
አይሆንም ማክዬ አባቴን ጥዬ መሄድ አልችልም አልኩት ልመና በተቀላቀለበት አንደበት ተነጋግረን ቃል ገብተሽልኛል
አሁን ለምን ሀሳብሽን ቀየርሽ አባትሽ ምንም አይሆንም ከዚህ አገር ከወጣን አባቢ እንደማያገኚሽ ስለሚረዳ ምንም እንኳን አባትሽ ላይ የሆነ ማስረጃ አለኝ ቢልም ምንም አያደርገውም አትጨነቂ
ሄዊ በቃ ወስኚ አይዞሽ እስከዛሬ ህይወትሽን ያለደስታ ኖረሻል አሁን ጥሩ ህይወትን የምትኖሪበት ጊዜ ነው ጠንካራ ሁኚ ወደኋላ አትመልከች አለኝ እኔ ያባቴ ነገር ምንም ሊሆንልኝ አልቻለም ጊዜ ወስጄ እንዳስብበት ለምኜው ዛሬ አባቱ ምን እንዳለው ጠየኩት ሄዊ የኔ ውድ በቃ ዛሬ ሁሉንም ነገር ለመስማት ሞክሪ
ምንም የተለየ ነገር አላወራንም ያው ሚስቱን ከቤት ይዤበት ስወጣ ምን ሊያስብና ሊናገር እንደሚችል መገመት አይከብድም በቃ ትንሽ ተጣላን መጣው አለኝና ርዕስ ማስቀየር ጀመረ ያባቴና የሽፈራው ሚስጥር አስጨንቆኛል በምን መንገድ ማወቅ እንደምችል እያሰብኩ ነው ማክን ላለማስጨነቅና እንዳይከፋው ለማድረግ ደስተኛ ለመሆን እየጣርኩ ነው፡፡ያባቴ የመጨረሻው ንግግርና የሽፈራሁ ጋር ሊኖረው የሚችለው ሚስጥር ሰላሜን ነስቶኛል ማክ አባቱ እያፈላለገኝ ስለሆነ ከቤት እንዳልወጣ አስጠንቅቆኛል ግን ያባቴን ሚስጥር የሚያውቅ ሌላ ተጨማሪ ሰው ማን ሊሆን እንደሚችል ማሰብ ጀመርኩ
ማወቅ አለብኝ ከዛ በኋላ አባቴን ከችግሩ የሚወጣበትን መንገድ አመቻችቼ ከማክ ጋር አዲስ ህይወት መስርቼ በሰላም መኖር ይሄን ካላደረኩ ግን ደስተኛ ሆኜ መኖር እንደማልችል አውቃለሁ አንድ ቀን ጠዋት አዙ ጋር ስደውል አባቴ ከሽፈራው ጋር ሲጨቃጨቁ ቆይተው አሁን እንደወጣ ነገረችኝ የተነጋገሩትን ነገር ሰምታ እንደሆነና እንዳልሆነ ስጠይቃት ሽፈራሁ በገዛ ልጅህ አማካኝነት ወቀመቅ እንድትወርድ ነው የማደርግህ ሲለው እንደነበርና አባቴ በጣም  ሲለምነው እንደነበር ነገረችኝ ሌላ ተጨማሪ ነገር ሰምታ እንደሆነ ስጠይቃት አይ ይኼን ብቻ ነው የሰማሁት አለችኝ ከኔ ጋር ሊያገናኘው የሚችለው ነገር ምንድነው ለምንስ በኔ ያስፈራራዋል በቃ በጭንቀት እራሴ ሊፈነዳ ደረሰ ለማክ ነገርኩት፡፡
ማክ ምንም አልተገረመም ነበር ምነው ማክ የምታውቀው ነገር አለ አልኩት በጥያቄ አስተያየት እያየሁት እ.....


        

✎ ክፍል አስር ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
       
​​ሄ ዋ ን 🌺
:¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 10

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺



አይ የለም ምን ይኖራል በቃ ይኼ ነገር ስለሰለቸኝ ነው አለኝ እኔ ግን ላምነው አልቻልኩም ምክንያቱም አባቱ ጋር ደርሶ ከመጣ በኃላ ወሬው ሁሉ ይችን አገር ለቀን እንውጣ ሆኗል እንዴት እንዳደኩና ማን ስለእናቴ የሚያውቀው ነገር ካለም በተደጋጋሚ እየጠየቀኝ ነው፡፡ ማክ አላመንኩም ባለፈው ከአባትህ ጋር ያወራችሁትን ንገረኝ ምንድነው ከእኔ የምትደብቀው ነገር አልኩት? ሄዊ እኔ ከአንቺ የምደብቀው ነገር የለም ምንም አልደበኩሽም አለኝ ባላምነውም እሺ በቃ ተወው አልኩት ግን ባባቴ እና ባባቱ መካከል ያለውን ሚስጥር እንድደርስበትና ሊነግረኝ እንደማይፈልግ ሁኔታው ያስታውቅ ነበር፡፡ እኔም ባባቴ ሚስጥርና በሁኔታቸው እዚህ መሆን ደስታ አጥቻለሁ ቀን ከሌሊት የማስበው ይኼ ሆኗል ማክ እኔ ወደቀድሞ ደስታዬና ማንነቴ እንድመለስ የማያደርገው ነገር የለም ከጎኔ በመሆኑ እድለኛ ነኝ ወደኋላ ተመልሼ አስተዳደጌንና አባቴ ለኔ የነበረው አመለካከት ማሰብ ጀመርኩ አባቴ ለኔ ግድ የለሽና በራሴ ጥረት ጎበዝ ተማሪ እንደነበርኩ ከማስታወስ ውጪ አዲስ ነገር ማስታወስ አልቻልኩም ከቤት ከወጣን ወራትን አሳልፈናል ማክም የራሱን ስራ እዚህ ጀምሯል እኔና ማክ አንድ ላይ ብንኖርም እስካሁን በመካከላችን የተፈጠረ አንድም ነገር የለም ግን አንዳችን በአንዳችን ደስተኞች ነን አንድ ቀን ማክ ሳላስበው የንጋባ ጥያቄ አቀረበልኝ ጥያቄው ቢያስደስትም ከአባቱ ጋር የፍቺ ውል አልፈፀምኩም እንዴት እንጋባለን የሚለው ነገር አስጨነቀኝ ማክ የፍቺ ጥያቄ እንዳቀርብ ነገረኝ እንደዚህ ካደረኩ አባቴን አቶ ሽፈራው እንደማይተው ለማክ ነገርኩት
መጀመሪያ ባባቴ ጉዳይ ላይ መፍትሄ ማግኘት እንዳለብን ስነግረው ሀሳቤን ባይወደውም ተስማማ የማክ በዚህ ጉዳይ ላይ ግድ የለሽ መሆን ይበልጥ የሚያውቀው ነገር እንዳለ እርግጠኛ ነኝ የአባቴ ሁኔታ አስጨንቆኛል እንዴት መፍትሄ እንደማገኝ አሰብኩኝ ቀናቶች ተቆጥረው ሳምንታትን ወለዱ አንድ ቀን ሰኞ ማክን ወደስራ ከሸኘሁ በኋላ ወደ አባቴ ሰፈር ሄጄ የእናቴን የቅርብ ጓደኛ አግኝቼ እናቴ ከመሞቷ በፊት ስለአባቴ ያጫወተቻቸው ነገር ካለ ጠየኳቸው
የናቴ ጓደኛ በጣም ነበር በጥያቄ የደነገጡት ምንም እንደማያውቁና በባሏና በሷ መካከል ያለ ሚስጥር ነግራቸው እንደማታውቅና ለምን እንደፈለኩት ጠየቀችኝ ዝም ብዬ ስለአባቴ ማወቅ ፈልጌ እንደሆነና ካስታወሱ እንዲደውሉልኝ ቁጥሬን ሰጥቻቸው ካለ ምንም መፍትሔ ወደቤቴ ተመለስኩ በማግስቱ ጠዋት በማላውቀው ቁጥር የአባትሽን ሚስጥር ከሆነ የምትፈልጊው በዚህ አድራሻ ነይና እንነግርሻለን የሚል የፅሑፍ መልዕክት ነበር ደጋግሜ ስልኩን ስሞክር አይነሳም ቴክስትም ባደርግ አይመልስም የማደርገው ነገር ጨነቀኝ ለማክ ብነግረው ለምን እንደዚህ አደረግሽ ብሎ ይጣላኛል ደሞ ብሄድ እራሴን አደጋ ላይ የምጥል ስለመሰለኝ ፈራሁ በዚህ ውጥረት መሀል እያለሁ የናቴ ጓደኛ ከዚህ ሚስጥር ጋ ምን እንደሚያያይዛቸውና ድንጋጥያቸው ትዝ አለኝ ደግሜ እንዳላገኛቸውም ፈራሁ በዚህ ሁኔታ እስከመቼ እንደምዘልቅ ሀሳብ ሆነብኝ የማክ ሁሉን እረስተን የንጋባ ጥያቄው አቶ ሽፈራው አባቴና የናቴ ጓደኛ ወይዘሮ እልፍነሽ ግንኙነት ሀሳብ ሆኖብኛል
ጠዋት ቁርስ እየበላን ማክ ዛሬ አባትህን ፊት ለፊት ማናገር ወስኛለሁ የመጣው ይምጣ መናገር አለብኝ ይሄ ህይወት ሰልችቶኛል አልኩት ማክ እንደማይሆንና እሱ በራሱ መንገድ አባቱ ጋር ያለውን ማስረጃ የሚያገኝበትን መንገድ እየፈለገ መሆኑንና ትንሽ ጊዜ እንድታገሰው ነግሮኝ ወደ ስራ ሄደ እኔ ግን ከዚህ ሚስጥር ጀርባ ያለውን ነገር ከዚህ በላይ ታግሶ የመጠበቅ ትግስቴ አልቋል እስከመቼ እንደምታገስ ባላውቅም ትንሽ ጊዜ እንድታገስ ለራሴ አሳመንኩት ስራ መስራት እንዳለብኝና ቤት መቀመጥ እንደሰለቸኝ ለማክ ነግሬው ከሱ ጋር ስራ ጀምሬአለሁ ትንሽ ቢሆንም ከቤት እየወጣው ስራ ላይ መዋሌ ጭንቀቴን ቀንሶልኛል ከማክ ጋር ያለን ፍቅር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረና ተጋብተን እንደማንኛውም ጥንዶች ህይወትን የመኖር ፍላጎታችን እየጨመረ ነው፡፡
ማክና አባቱ ጭራሽ ተቆራርጠዋል አባቱም እኔን መፈለጉን አቁሞ አባቴ ተረኛ ፈላጊዬ ሆኗል ከስራ ስገባም ሆነ ስወጣ ከማክ ውጪ አልንቀሳቀስም የትም ስንሄድ አብረን ነው፡፡ አንዳንዴ አዙ ጋር እየደወልኩ ያለውን ሁኔታ እከታተላለው አባቴና አቶ ሽፈራው ሁሌም ይገናኛሉ ሁሌም ይጨቃጨቃሉ፡፡ አንድ ቀን ስደውልላት አባቴ እኔን አግቶ አሳምኖ ወደቤቴ ካልመለሰልኝ ሲዲውን ለኔ እንደሚሰጠኝና በኔ በልጁ እጅ እንደሚጠፋ እንደነገረው ነገረችኝ በጭንቀት ልፈነዳ ምንም አልቀረኝም እየሮጥኩ የማክ ቢሮ ሳላንኳኳ ዘልዬ ስገባ ስብሰባ ላይ ነበር ይቅርታ ጠይቄ ተመልሼ ስወጣ ማክ ተከትሎኝ ወጣና የሆንኩትን ጠየቀኝ ሲጨርስ ላገኘው እንደምፈልግና ማውራት እንዳለብን ነግሬው ወደ ቢሮዬ ተመለስኩ። ምንም መረጋጋት አልቻልኩም ነበር የማክ ይበልጥ ያባቴ ነገር እና ከኔ ጋር የሚያያይዘው ነገር ሰላም ነሳኝ ተረጋግቼ መቀመጥ አልቻልኩም ድንገት ከወራት በፊት የተላከልኝን ቴክስት አስታወስኩ ስልኬን አንስቼ ቁጥሩን መፈለግ ጀመርኩ መልዕክቱ ስልኬ ላይ የለም አጥፍቼው እንደሆነ ለማስታወስ ሞከርኩ ግን አላጠፋሁትም ማን ሊያጠፋው ይችላል?? ማክ እንኳን ስለዚህ የስልክ መልዕክት የሚያውቀው ነገር የለም እኔም እንዳላጠፋሁት እርግጠኛ ነኝ
ታዲያ ማን ሊያጠፋው ይችላል?.....


       
✎ ክፍል አስራ አንድ ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።

••●◉Join us share
​​​​.
                       ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 11

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


ምንም ማስታወስ አልቻልኩም የማስታውሰውም ነገር የለም ምክንያቱም እኔ እንዳላጠፋሁት እርግጠኛ ስለሆንኩ
በዚህ ሀሳብ ላይ ሆኜ ማክ በር አንኳክቶ ገባ ማሬ ምን ሆነሽ ነው ሰላም አይደለሽ አለኝ አዙ የነገረችኝን ቴክስቱን ማን እንዳጠፋው ሳላውቅ ልነግረው አልፈለኩም እ..... ..ደና አይደለሁም ማክ ምን ብዬ እንደምነግርህ አላውቅም የደበቅኩህ ነገር ነበር አልኩ እየተንተባተብኩ ንገሪኝ ምን ደብቀሽኝ ነበር አለ በተጨነቀ አይነት ስሜት እያየኝ ማክዬ እንዳትቆጣኝ አልኩት አልቆጣም ንገሪኝ ምን ተፈጠረ ምንድነው የደበቅሽኝ
ማክ ከየት እንደምጀምርልህ አላውቅም ጥፋት ይሁን መልካም ላንተ ሳልነግርህ ከወራት በፊት የናቴ ጓደኛ ጋር ሄጄ ነገር
ብዬ ቀና ብዬ አየሁት ቀጥይ በሚል አስተያየት ሲመለከተኝ ከናቴ ጓደኛ ጋር እንዳወራንና በማግስቱ በማላውቀው ቁጥር ቴክስት እንደተላከልኝ አሁን    ቴክስቱን ላገኘው እንዳልቻልኩም ጭምር ነገርኩት ምንም ባለመገረም ስሜት ነበር የሚያዳምጠኝ ስጨርስ ምን እንደሚለኝ ለመስማት በጉጉት እጠብቀው ጀመር
ሄዊዬ ቆይ ይሄ ነገር ለምን አይቀርብሽም ለምን አዲስ ህይወት "ሀ" ብለን አንጀምርም? በርግጥ የእናትሽ ጓደኛ ጋር እንደሄድሽ አላውቅም ግን ሌላ ተጨማሪ ቴክስት ካንድ አይነት ቁጥር ተልኮልሽ ነበር አንቺ መታጠቢያ ቤት ውስጥ ነበርሽ በወቅቱ ከፍቼ ሳየው አባቴ አንቺን የሚያገኝበት አጋጣሚ እየፈለገ እንደሆነ ስለተረዳው አጠፋሁት ቁጥርሽን ከየት እንዳመጡ ልጠይቅሽ ነበር ግን የባስ እንዳላስጨንቅሽ ስላሰብኩ ተውኩት
አንቺም ከዛ በኋላ የረሳሽው መስሎኝ ነበር ስላልጠየቅሽ እና አሁን በምን በምን ትዝ አለሽ አለኝ በውስጤ ተመስገን ማክ ከኔ ጋር ነው ምንም አልዋሸኝም አልኩኝ ለደቂቃ ምንም ሳልናገር ቆየሁ በያ ንገሪኝ አለኝ ማክ ምንድን ነበር ሁለተኛው መልዕክት አልኩት "ይሄ የመጨረሻ እድልሽ ነው ያባትሽን ሚስጥር ማወቅ ከፈለግሽ በላክንልሽ አድራሻ ጠዋት 4 ሰዓት ነይ" ነበር የሚለው ይሄን መልዕክ ብታይ ኖሮ በርግጠኝነት ሄደሽ እራስሽን አባቴ መዳፍ ላይ ትጥይ ነበር አለኝ ማክ መሄድ ነበረብኝ ሁኔታው ከምታስበው በላይ አሳሳቢ ነው ዛሬ አዙ ጋር ደውዬ ሚስጥሩን የያዘው ፋይል ሲዲ እንደሆነ ነግራኛለች ይሄ ሲዲ ደግሞ እኔ እጅ ከገባ አባቴን እኔ ራሴ እንደሆንኩ የምበቀለው ሲያወሩ ሰምታለች፡፡ እኔ እዚህ ሲዲ ውስጥ ምን እንዳለ ሳላውቅ እንቅልፍ አይወስደኝም ምንድነው ሚስጥሩ እራሴ ሊፈነዳ ነው እባክህ አግዘኝ የኔ ፍቅር አልኩት ማክ ከተቀመጠበት ተነስቶ አቅፎ ያፅናናኝ ጀመር በቃ መፍትሄ አናጣም ትንሽ ብቻ ታገሺ እራስሽን ለማረጋጋት ሞክሪ ምን ይመስልሻል ትንሽ እንድትረጋጊ ሁኔታዎችንም ተረጋግተን ለማሰብ አንድ ሳምንት ወጣ ብለን ብንመጣ አለኝ ሀሳቡ ጥሩ መስሎ ታየኝ ወዴት እንሂድ አልኩት አሁንም ግራ እንደተጋባሁ ነኝ ዱባይ ደርሰን እንምጣ እስከዛ ነገሮችን በደንብ የምናስብበት ጊዜ ይኖረናል በዛውም ካለንበት ጭንቀት ትንሽ እናርፋለን አለኝ በሀሳቡ ተስማማሁ ከሳምንት በኃላ ዱባይ ሄደን በጣም አሪፍ የሚባል ጊዜ እያሳለፍን ነው ለጊዜውም ቢሆን ሁሉንም ነገር እረስቼዋለሁ ማክ ወደበፊቱ ማንነቴ በመመለሴ በጣም ደስተኛ ሆኗል ድንገት አየሽ አይደል ሁሉንም ነገር  ጥለን ወደ አውስትራሊያ ብንሄድ ሁሉን ነገር መርሳት እንደምንችል አለኝ ማክዬ ለጊዜው መርሳት ስለፈለኩና አንተም ማስከፋት ስላልፈለኩ እንጂ እስከመጨረሻው ማንነቴንና ያባቴን የተደበቀ ማንነት እረስቼ መኖር አልችልም
በተለይ ጉዳዩ ከኔ ጋር እንደሚያያዝ ካወቅኩ በኃላ ይበልጥ የማወቅ ፍላጎቴ ጨምሯል ይህን ጉዳይ እልባት ካገኘሁለት በኃላ የፈለክበት እንሄዳለን አልኩት ማክ ይሄን ሲሰማ ሀሳቤን እንደማልቀይር ስላወቀ በቃ እሺ እኔም ይሄ ነገር ሰላም እየነሳኝ ነው ስለዚህ ወደኢትዮጵያ ስንመለስ አብረን መፍትሄ እንፈልጋለን ግን አንድ ነገር ቃል ትገቢልኛለሽ አለኝ ምንድነው ማክ የፈለግከውን አልኩት በዚህ ጉዳይ ላይ አብሮኝ እንደሆነ ሲነግረኝ በመደሰት
ያባትሽ ሚስጥር ምንም ሆነ ምን ጠንካራ እንደምትሆኚና ምንም ለማድረግ እንደማትሞክሪ እንደዛ ሲለኝ ማክ የሆነ የምታውቀው ነገር እንዳለ ይሰማኛል አልኩት ሄዊዬ እንደዛ ማለቴ አይደለም ግን ያው ከሁኔታዎች አንፃር ጉዳዩ እንደሚከብድ በመጠርጠር ነው ብሎ አቅፎ ሳመኝ ነገሩ ባይዋጥልኝም ከማመን ውጪ አማራጭ አልነበረኝም
የዱባይ ቆይታችንን ጨርሰን እንደተመለስን.......


          ꧁༺༒༻꧂


✎ ክፍል አስራ ሁለት ከ80 Vote♥️ በኋላ ይቀጥላል...  ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like♥️ ማድረግ አይርሱ።
           
   ​ 
━━━━━━━✦✿✦━━━━━
⇘የኔ ሱስ💘

እንዴትና ለምን እንዳፈቀርኩሽ😍 አላውቅም
ብቻ ሳላስበው ባልጠበቅኩት መንገድ
ልቤ ውስጥ ገባሽና ህይወቴን ብሩህ
አደረግሻት ።ድሮ ድሮ ፍቅር አለ ሲሉኝ  ውሸት ነው  እል ነበር ፤ አሁን ግን ስለመኖሩ አልጠራጠርም💞በህይወቴ ብዙ ስጦታና ገጠመኞ አይቻለሁ አንቺ ከሁሉም የገዘፈ ስጦታዬና አስደሳች ገጠመኘ ነሽ፤እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ❤️አፈቅርሻለሁ።
ሄ ዋ ን 🌺
           :¨·...............:¨·.
ምዕራፍ 2
                  ♥️ ክፍል 12

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


በሁለተኛው ቀን ለአዙ ደወልኩላት ባባቴና በሽፈራው መሀል ምንም አዲስ ነገር እንደሌለና ግን ሽፈራውን ለማግኘት አንድ ሴትዮ መጥተው እንደነበረና ስለኔ ስም ሲያነሱ ገና ሽፈራው አዙ እንድትሰማ ስላልፈለገ እንዳስወጣትና ብቻቸውን ለእረጅም ሰዓት አብረው እንደቆዩና እንደሄዱ እሷ ምንም መስማት እንዳልቻለች በር ላይ ሆነው ግን በቃ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ አሳውቅሀለሁ ሲሉት ብቻ እንደሰማች ነገረችኝ መቼ እንደነበር የተገናኙትና ደግመው መጥተው እንደሆነ ስጠይቃት ደግመው እንዳልመጡና እንዳሉትም ከሁለት ቀን በኃላ ሹፌሩ አንድ ትንሽ ፖስታ አምጥቶ ሲሰጠው እንዳየችው ሹፌሩን ስጠይቀው ከሁለት ቀን በፊት የመጡት ሴትዩ እንደሰጡት ነገረችኝ አዙ ሲዲው እንዳይሆን ታዲያ ያስቀመጠበትን ወይ ደሞ ምን እንዳረገው አላየሽም ስላት ምን አውቄ አለሜ ጋሽዬ ጥንቁቅ እንደሆኑ እያወቅሽ አለችኝ ስልኩን ከዘጋው በኃላ የናቴ ጓደኛና ሽፈራው ምን እያደረጉ ነው
ምኑንስ ነው በሁለት ቀን ውስጥ የሚያሳውቁት ስለምንስ ነው ረጅም ሰዓት ወስደው ሲያወሩ የነበሩት ሹፌሩስ ለሽፈራው ምንድነው አምጥቶ የሰጠው?
በነዚህ ሀሳቦች ተጠምጄ እያለሁ ድንገት ስልኬ ጠራ የእናቴ ጓደኛ ነበሩ ልቤ ሲመታ ይታወቀኛል ስልኩን እያየሁት ለማንሳት ጊዜ ወሰደብኝ ላንሳው አላንሳው በሚል ሀሳብ ተወጥሬ ስልኬን አይን አይኑን እያየሁት ስልኩ ዘጋ በድጋሚ ሲጠራ እንደምንም ራሴን ተቆጣጥሬ ሄ...ሄሎ አልኩኝ እየተንተባተብኩ ሄዋኔ እንዴት ዋልሽ አሉኝ ምላሽ አልነበረኝም ምን ሊሉኝ ነው ጥያቄ ውስጤ ተወጥሯል ሄሎ ሄዋኔ አሉኝ ደግመው አ....አቤት እማዋ አልኳቸው በተቆራረጠ ድምፅ ስንጠራቸው እማዋ እያልን ነው፡፡ ምነው ደህናም አደለሽ አሉኝ ...እንደምንም ራሴን ለማጠንከር እየሞከርኩ ደና ነኝ እማዋ እንዴት ነዎት አልኳቸው ምነው ጠፋሽ ባለፈው ከመጣሽ በኃላ ድምፅሽ ጠፋ እኔም እደውላለሁ እያልኩ ያው እንደምታውቂው የልጆች ነገር ከሰሞኑ ብደውልም ስልክሽ አይሰራም አሉኝ የማዋ ባለቤት የሞቱት ከናቴ ጋር በተቀራራቢ ወቅት ነበር እንደውም አስታውሳለሁ ያኔ የ9 አመት ልጅ ነበርኩ
የማዋ ባል ባልታወቀ ሰው ተገድሎ ነው የሞተው ያው ዱርዬዎች ለመዝረፍ ብለው ገድለውት ይሆናል በሚል ሰበብ ነገሩ ተረሳ እንጂ እናቴና እኔ ለቅሶ ቤት ደርሰን ስንመጣ አባቴ ከናቴ ጋር በጣም እንደተጣሉ አስታውሳለሁ ምክንያቱን እረስቼዋለሁ ኧረ እንደውም በግርግር አባቴ አንድ ጥፊ አቅምሶኛል ከዛ የማዋ ባል ከሞተ ሳምንት ሳይሞላው እናቴ በድንገት አረፈች፡፡ ይገባኛል እማዋ አይመችም አልኳቸው አዎ ልጄ አይመችም አሉ ስለኑሮ ምናምን ሲጠይቁኝ ቆይተው በመጨረሻም እናቴ ስላባቴ የነገረቻቸው ነገር ካለ ካስታወሱ እንዲደውሉልኝ እንደነገርኳቸውና ትዝ ያላቸው ነገር ስላለ ለዛም ሲሉ እንደወሉልኝ ነገሩኝ ስለሳቸው ምንም ያላወቀ በመምሰል ውይ እማዋዬ ምን አስታወሱ አልኳቸው ለመስማት የጓጓሁ እንዲመስል አድርጌ አይ ሄዋኔ በስልክ አይሆንም እንደው ከተመቸሽ ወደከሰዓት ብትመጪና ያቺ የምትወጃትን ሽሮ ስርቼልሽ ቡናም አብረን ጠጥተን ተጫውተሽ ትሄጃለሽ አሉኝ ምን አይነት ወጥመድ እንደተዘጋጀልኝ ባላውቅም ግን አንድ ነገር እንዳሰቡ ግልፅ ነው፡፡ ስልኩን ከዘጋው በኃላ ማክ ጋር ሄጄ ሁሉንም ነገር ነገርኩት ልትሄጂ አስበሽ እንዳይሆን ብቻ አለኝ...ማክዬ አላሰብኩም ግን ሹፌሩ ለአባትህ የሰጠው ሲዲው እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ ስለዚህ ማግኘት አለብን አልኩት ማክ እንድረጋጋ እየለመነኝ እሱ በየትኛውም መንገድ ሲዲውን እንደሚያመጣውና እስከዛ ምንም እንዳላደርግ አስጠነቀቀኝ ማክን በደስታ አቅፌ ሳምኩት ከስራ ወጥተን ውጪ ትንሽ ዘና ብለን ወደቤት ከተመለስን በኃላ በሀሳብ ብወጠርም ደስ የሚል ቀን አሳለፍን፡፡ እማዋ ደጋግመው ደውለው ነበር እንደነቃውባቸው እንዳያውቁ ትንሽ ራሴን ስላመመኝ ሰሞኑን ከስራ መልስ እንደምመጣ አሳውቂያቸዋለሁ ማክ አንድ ሀሳብ እንደመጣለት ነገረኝ ምን ስለው ሁሉም የቤት ሰራተኞች በኛ ሳይድ ስለነበሩ በተለይ ላባቱ በጣም ቅርብ የሆነው ሹፌሩ ብር ሰጥቶ ፋይሉን እንዲሰርቅ ማድረግ ምክንያቱም እሱ ስለሆነ ካባቴ ጋር ብዙን ጊዜ የሚያሳልፈው ብዙ ነገር ያውቃል አለኝ
ማክ የፈለገ ቅርብ ቢሆን ትልቅ ሚስጥር ላያውቅ ይችላል አልኩት እኛ እንሞክር ካልሆነ ከወር በኃላ ወንድሜ ስለሚመጣ ሁሉንም ነገር ስለነገርኩት እሱ ይረዳናል አለኝ የወንድሙ ሀሳብ ጥሩ ቢሆንም ወር ሙሉ እሱ እስከሚመጣ የሚያቆይ ትግስት እንደማይኖረኝ ስለማውቅ በማክ በመጀመሪያ ሀሳብ ተስማምተን ማክ ላባቱ ሹፌር ደውሎለት በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ......
​​  ሄ ዋ ን 🌺
            :¨·...............:¨·.

                  ♥️ ክፍል 13

  ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺
Written by Estifanos tekka


ማክ ለአባቱ ሹፌር ደውሎለት በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ እስኪነጋ እንቅልፍ ባይኔ አልዞረም ጠዋት ቁርስ ላይ ለማክ አባቴ በጣም እንደናፈቀኝና ልደውልለት እንዳሰብኩኝ ስነግረው ጥሩ ሀሳብ አለመሆኑን ነገሮኝ ባልደውልለት የተሻለ እንደሆነ አስጠነቀቀኝ ቢሮ ከገባሁ በኃላ ግን ደጋግሜ አባቴን ማሰብ አላቆምኩም
የመጣውን ለመቀበል ራሴን አሳምኜ አባቴ ጋር ደወልኩ ገና ድምፄን ሲሰማ ነበር አንቺ መድረሻ ቢስ ምን ይሁን ብለሽ ደወልሽ አታገኘኝም ነው ... እ ... እንደናቅሽኝ እየነገርሽኝ ነው? ይኼውልሽ እናትሽ የገባችበት ጉድጓድ ብትገቢ አታመልጭኝም መድረሻ ቢስ ሰላም እንደነሳሽኝ እንደዶሮ አንቄ ለሽፈራው ካልሰጠሁሽ ወንድ አይደለሁም አለኝ
ይሄንን ሁላ ሲያወርድብኝ አንድም ቃል አልተናገርኩም ብቻ ባይሆን ድምፁን ስለሠማው ትንሽም ቢሆን ደስ ብሎኛል ወይ አባ ምን ብትደብቅ ነው ሰላም አተህ ሰላም የነሳኸኝ አልኩ ለራሴ ስልኩን ዘግቼ ማክን ከሹፌሩ ጋር ሲገናኙ አብረን ብናገኘውስ ብዬ ልጠይቀው ስላሰብኩ ወደሱ ሄድኩ ማክ ቢሮ አልነበረም... ፀሀፊውን ስጠይቃት ተቻኩሎ እንደወጣ ነገረችኝ ደወልኩለት ስልኩን አያነሳም ሱማክ የትም ቢሄድ ለኔ ሳይነግረኝ አይሄድም ስልኩን አለማንሳቱ ይበልጥ አስጨነቀኝ ተረጋግቼ መቀመጥ አልቻልኩም ደጋግሜ ብደውልም አይነሳም... በጭንቀት ራሴ ተወጠረ ማክ ከቢሮ ከወጣ 4 ሰዓታት ተቆጠሩ በዛ ሁኔታ ቢሮ ምንም ስለማልሰራ ወደቤት ሄድኩ... ለተጨማሪ 1 ሰዓት ጠበኩ ምንም የለም የማክ ስልክ አይነሳም... በመጨረሻም ሁሉም የማክ ጓደኞች ጋር ደወልኩ ከማንም ጋር አልተገናኘም መልሶ ካልደወለ እንድደውልላቸውና ለፖሊስ እንደምናመለክት ነገሩኝ ሁለቱ ጓደኞቹ እንደሚመጡ ነግረውኝ ስልኩን እንደዘጋሁ ስልኬ ጠራ ማክ ነበር
ማክ የኔ ፍቅር የት ሆነህ ነው ለምንድነው የማታነሳው በጭንቀት ልትገድለኝ አስበህ ነው... የጥያቄ መዓት አደራረብኩበት...
የኔ ቆንጆ ስላስጨነኩሽ ይቅርታ እየመጣሁ ነው አለኝ በደከመ ድምፅ ማክ የት ነህ የሆንከው ነገር አለ ድምፅህ ልክ አይደለም ምንድነው የተፈጠረው ያለህበት ልምጣ አልኩት እያለቀስኩ አያስፈልግም ማሬ እየደረስኩኝ ነው ትንሽ ታገሺኝ አለኝ ልቤ በሀይል ይመታል በጣም እያለቀስኩ ነው ምን እንደማደርግ ግራ ተጋብቼ ግቢ ውስጥ ወዲያና ወዲህ እያልኩ የማክን መምጣት መጠባበቅ ጀመርኩ ከግማሽ ሰዓት በኃላ የመኪና ድምፅ ስሰማ እየሮጥኩ ወደበሩ ስሄድ የማክ ጓደኞች ነበሩ ... አዲስ ነገር ካለ ሲጠይቁኝ የሆነውን ነግሬያቸው ማክን አብረን መጠበቅ ጀመርን ትንሽ ቆይቶ ሌላ የመኪና ድምፅ ስንሰማ ሁላችንም ወጣን ዘበኛው በሩን ሲከፍተው መኪናው ውጪ እንደቆመ ነው ማንም ጋቢና የለም እየሮጥኩ ወጥቼ ሳይ ማክ በደም ተነክሮ ከኃላ ተኝቷል እየጮህኩ ጓደኞቹን ለርዳታ ጠራኻቸው ወደሆስፒታል ንዳው ብዬ አንዱ ጓደኛው ላይ ጮህኩኝ... ማክ በደከመ ድምፅ ደህና ነኝ የኔ ፍቅር አለኝ ማክ ማነው እንደዚህ አድርጎ አምጥቶ የጣለህ ማክ ክፉ ሰው ነው አንተ ላይ እንደዚህ ያደረገው እያልኩ ያለማቋረጥ አለቅሳለሁ እሱ እንደዛ ሆኖ እኔን ለማፅናናት ይሞክራል ጓደኞቹም እንድረጋጋ እየለመኑኝ ሆስፒታል ደረስን ህክምና ተደረገለት የማክ እጁ ላይ ቅጥቅጥና ግንባሩ ላይ ጉዳት ከመድረሱ ውጭ የከፋ ነገር እንደሌለውና ግንባሩ መሰፋት እንዳለበት ዶክተሩ ነግሮኝ ወጣ
ከሰዓታት በኃላ ወደቤታችን ተመለስን የማክ ጓደኞች ተሰናብተውን ከሄዱ በኃላ ማክን በጥያቄ አጣድፈው ጀመር... ሄዊ የኔ ቆንጆ ተረጋጊ አባቴ ነው በቃ እንደዚህ ያደረገው ሹፌሩ ከኛ ጋር መሆን አልቻለም ከኔ ጋር ቀጠሮ እንዳለው ላባቴ ነግሮት ነው አባቴ ከሱ ምን እንደፈለግን አውቋል በር ላይ ጥሎኝም የሄደው ሹፌር  የሱ ነው አሁን መኖሪያችንን አውቋል መጠንቀቅ አለብሽ ግን አንቺን በአካል ማግኘት ነው የሚፈልገው ይሄን ደግሞ እኔ አልፈቅድም አለኝ እና እንዴት ልጁን ጨክኖ እንደዚህ ያደርጋል በጣም ተናዶብኛል ሰዎቹ ሲደበድቡኝ እንኳን ለማየት አልደፈረም ውጪ ቆሞ ነበር አንቺን እንድመልስሽ ለማስፈራራት እንጂ ሌላ ነገር ማድረግ ቢፈልግ ይችል ነበር አሁን እሱን እርሽው የኔ ማር የምትፈልጊውን ነገር በየትኛውም መንገድ አደርጋለሁ አንቺ ግን ራስሽን አደጋ ላይ የሚከት ተግባር እንዳትፈፅሚ
አባቴ ቢያገኝሽ አንዴ እጁ ከገባሽ አይለቅሽም እስረኛው ነው የምትሆኚው እኔም ላድንሽ አልችልም ቢቻል ራስሽን አሳምነሽ ከዚህ አገር እንውጣ ካልሆነ ግን ታገሽ አለኝ የማክ ንግግር ጠንካራ ነበር፡፡ እኔም ያለኝን እንደማደርግ ቃል ገባሁለት ከዛን ቀን በኃላ ለሳምንት ስራ አልገባንም ነበር በጣም ደስ የሚል የፍቅር ጊዜ እያሳለፍን ነው፡ የሁለታችንም ፍቅር ጨምሯል ፍቅር እንጂ እኛ ጋር ፀብ የለም ከማክ ጋር በጣም ነው የምንዋደደው ሁለታችንም ደስተኞች ነን... ዛሬ የማክ እውነተኛ ሚስት የመሆን ፍላጎቴ ጨምሯል የምንጋባበት ጊዜ ገና ገደብ የለውም ሽፈራው እስከሚፈታኝ ከታገስን ልናረጅ ነው ብቻ በቃ ከፍቅረኝነት የሚስትነት ህይወት አማረኝ ..እኔና ማክ እንደባልና ሚስት አንድ ላይ እንኑር እንጂ ገና መጋባታቸውን የሚጠባበቁ ፍቅረኛሞች ነን እኔና ማክ ለመጋባት የሚከለክለን የአባቱ ጉዳይ ብቻ ነው፡፡ ደሞም ለማክ አባት የወረቀት ሚስት እንጂ የእውነት የትዳር አጋሩ አይደለሁ ይሄንንስ አምላክ ከሀፂያት ይቆጥርብኝ ይሆን አልኩ ለራሴ
አምላኬ ሆይ ይቅር በለኝ እየተፋቀርን አንተን ፈርተን እስካሁን ቆይተናል አሁን ግን የትግስቴ ጥግ ላይ ደርሻለሁ አንተ ማረኝ አልኩ በልቤ በጣም ጣፋጭ እራት በራሴ እጅ አዘጋጅቼ ቤቱን ሮማንቲክ አደረኩት.....
የፍቅር ጥቅሶች 💖 pinned «​​  ሄ ዋ ን 🌺             :¨·...............:¨·.                   ♥️ ክፍል 13   ◈ አጭር እውነተኛ የፍቅር ታሪክ🌺 Written by Estifanos tekka ማክ ለአባቱ ሹፌር ደውሎለት በማግስቱ ለመገናኘት ቀጠሮ ያዙ እስኪነጋ እንቅልፍ ባይኔ አልዞረም ጠዋት ቁርስ ላይ ለማክ አባቴ በጣም እንደናፈቀኝና ልደውልለት እንዳሰብኩኝ ስነግረው ጥሩ ሀሳብ…»
2024/06/01 08:35:47
Back to Top
HTML Embed Code: