Telegram Web Link
#አንሶላ_እንዴት_ናቀው?

ከታምራት በላይ
በታምር አድርጎ እኛን ሲከልቀን
አለም ትደምቃለች ለሰከንድ ስቀን
አናኮርፍም እንጂ
እኛ ካኮረፍን ያውም ለአንድ ቀን
ፉጡራን በመሉ
ተጠናውቶት ያድራል እልፍ አዕላፍ ሰቀቀን

ከንጋት ከምሽት
ኩርፊያና ሳቃችን እንዲ እያስደነቀ
እኛን እያፀና ዘመኑ ካለቀ
የኛ መፈቃቀር
ንፁ ሆኖ ሳለ በነገር ያልሸሸ
ተኝተን ስነቃ
ለምንድነው ?ታዲያ አሶላው ቆሸሸ

የነካን ይቅርና ያየን በፀደቀው
ንፁ ፍቅራችንን አንሶላ እንዴት ናቀው

ቶፊቅ መሀመድ ( #አዲብ )
@Tufaw_muhe
አልባሌ ነገር አታስቡ አሏቹ ደግሞ 😝

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
የተበላ ቁማር
.
.
በዛሬያችን ስሌት ባሁናችን ቀመር
መቆም ሆኖ ቀረ መጣል ምርኩዝ መስበር።
ባይገባን ነው እንጂ ወርቁ ቢመሳጠር
ጅምር ያልነው ትላንት ፍፃሜያችን ነበር።

ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
: መልካም : ክፉዎች #፪

አይጋሩት: ለሊቴን : ቀኔን : ይሻሙታል
ለቀን : ቅዠታቸው : ህልሜን ይቀሙታል_
ሲስቁ : በመሳቅ : ሲያለቅሱም በመሳቅ
ብዙ : ሞክርያለሁ : ከእነሱ : ለመራቅ_
ለመኖር : እያሉ : ከኑሮ ተጣልተው
ከራስ : ጋር : ተኳርፈው : ካለመኖር ታርቀው
ክፋት :,አየራቸው : ስድብ ትንፋሻቸው_
:*: * :*:
እንባቸው : የአዞ : ከአዞም : የባሰ
ከአይናቸው : ጉርፎ : እንኳን: የሰው ልጅን : ውቅያኖስ : ያጨሰ
በረዶ : እሚያነድ : የባህር : ላይ : እሳት
እየፆሙ : መስባት : እየበሉ : ክሳት
መቆሚያቸው : ገደል : መኝታቸው : እሾህ
/*ይባስ/
ምግባቸው : አመድ : ቀበቷቸው : እባብ
መሬታቸው : ረመጥ : ቡቃያቸው : ርሀብ

/ናታን ኤርሚያስ/
@UniqueDy

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
እንጨዋወት
.
.
እስቲ እንጨዋወት እንቃርም ጨዋታ
መሳቅ ያማረው ጥርስ ይዛል በፈገግታ።
ላፍታ ሰብሰብ እንበል መራራቅ ይገታ
ቀንዳም ሽልብ ሰይጣን ሉሲፈር ይረታ።
ድንበር አጥር ይፍረስ
እንጣል ያንድነት ዳስ
ምሬት ያደረቀው
የፊታችን ቆዳ
በሳቅ እንባ ይራስ።

ዘረኝነት ጥበት
ጎሰኝነት ዝቅጠት
መዳረሻ ይጣ
በአንድነት ማእበል
በመውደድ ነበልባል
ይወዝወዝ ይቀጣ።
ስጋህ ከስጋዬ
ደምህ ከደሜ ጋር
ይዋሀድ ይቀየጥ
የፍቅራችን ድርሰት
እልቆ መሳፍር ገፅ
ዝንት አለም ይገለጥ።

ይመታ ይወገር
የሕብረታችን ማገር
በአንድ ይሰናሰን
ኑሯችን ይመስጥር።
በዚች በአሁኗ
በሽራፊ ሰአት
በስባሪ ሰከንድ
ነገያችን ይቀመር።

እንጂማ
ምን ሊበጅ ጠበንጃ
ምን ሊበጅ ምንሽር
ቁና እህል ላይሰፍር
ምን ሊበጀን መንደር
ምን ሊበጀን ሰፈር
አጥር ሰው ላይቀብር።

እስቲ እንጨዋወት እንቃርም ጨዋታ
መሳቅ ያማረው ጥርስ ይዛል በፈገግታ።
ላፍታ ሰብሰብ እንበል መራራቅ ይገታ
ቀንዳም ሽልብ ሰይጣን ሉሲፈር ይረታ።

ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
#አርፎ_ልፊያ

አካሌ ደካክሞ ዝለት እንዳራደው
እንቅልፍ ይሉት ጉልቤ ጠቅልሎ ወሰደው
ጠራኝ ተከተልኩት አንቺን አስከትዬሽ
መንገድ አይሰኝም ብሄድ ተነጥዬሽ

ይኸው
ካንቺ ጋራ እየሄድኩኝ
ለማህሌት በሌ'ት ቆምኩኝ
ህልም አልለው ወይም ቅዠት
አይን ከድኖ እንደማየት
ብርሀን የለ ወይም ፅልመት
ከምንም ላይ ለመመፅወት

ከፅልመቱ መገፋፋት
ከራስ ጠቦ ፣ ከራስ አንሶ፣ ካአንቺ መስፋት
አጀብ ...
ወይ መታደል ወይ መታጀብ
ከሁካታው፣ ከጫጫታው፣ ርቆ ማምለጥ
በአንድ አካል በአንድ ልብ ነፍስን ማድመጥ

ደስታን ይዞ ለመቀየኘት
አርፎ ልፊያ
መገዳደር መሰቃየት

ተሰቃይቶ ደስታ ማትረፍ
ተዛዝሎ ብርታት መቅጠፍ
አንቀላፍቶ ለሊት መንቃት
የነቁ ለት አንቺን ማጣት

ያጡሽ ለታ
መበሳጨት ፣ መናደድ ፣ መጋጋል
እንዲ እያለ ሌት ይነጋል
"ነጋ ደግሞ ጎህ ቀደደ"
ህልሜ ርቆኝ ተሰደደ
ላልደርስበት ተከትዬ
ከራሴ አለም ተነጥዬ

አንቺን ማየት አንቺን ማፈር
አንገት ሰገግ አይን ሰበር
ሌት ጠብቆ አንቺን ማስገር
ሲነጋ ጋ ደግሞ ማፈር

እንዳይነጥቀኝ...
የመአልቱን ድንቅ ቅሪት
የተፈጥሮ ኡደት ይዙር
አይንጋልኝ ይኼ ለሊት

ቶፊቅ መሀመድ ( #አዲብ )
@Tufaw_muhe

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ1442ኛው የዒድ አል- አድሀ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

መልካም በዓል!!!
ሹመቴን መልሱ
.
.
ጎራው ያለ እንደሆን ባላምባራስ ደስታ
ዘራፍ ያለ እንድሆን ባላምባራስ ደስታ
ጠላት ይጠፋዋል መደበቂያ ቦታ።
.
ፊታውራሪ ፍላቴ
ግራዝማች በሃፍቴ
አዛዥ ለጥ ይበሉ
ቀኝ አዝማች ባካሉ
ዣንጥራር ባያሌው
ደጃዝማች እንዳለው
እንዲህ ነው ካልቀረ አንጀት አርስ ሹመት
ለድል የሚያበቃ ጦር ይዞ ቢዘመት።
.
የጣሊያን ጄነራል ኮኮቡን ደርድሮ
በሊጋባ ሞዜር ስንት አሳሩን ቆጥሮ
ድል አድርጎት የኛ ሰው ፎክረን በኩራት እንደተመለስን
ስልጣኔ መስሎን የሱን ስም ወረስን።
.
ሟቹ ጀኔራል ነው ገዳይ ፊታውራሪ
ስም እንዴት ይዋሳል ደፋር ሰው ከፈሪ?
በጠላት ሬሳ ላይ ቆመን እያቅራራን
በድላችን ማግስት የኛን ሹመት ንቀን ከሆንን ኔተራል
ባናውቀው ነው እንጂ የዛን ቀን ሙተናል።
.
ኮረኔል አይበሉን ያገሩን አርበኛ
ጀኔራል አይበሉን ሀበሻ ነን እኛ።
.
የሟች ስም አይደለም የገዳይ ሰው ምሱ
በደም ተበላሽቷል ባለ ኮኮብ ልብሱ
ገድዬው ሳበቃ ባስታጠቁኝ ወኔ
በሱ ስም አይጥሩኝ ቆሞ እንዲሄድ በኔ።
ጀኔራል ድል ሆኖ ስላለፈች ነፍሱ
ይበሉ ጃንሆይ ሹመቴን መልሱ።
.
ፊታውራሪ ካታካምባ
ሊጋባ ዴሊቦ
አዛዥ ለጥ ይበሉ
ቀኝ አዝማች አካሉ
ዣንጥራር አበጋዝ
አንዲህ ነው አንጀት አርስ ሹመት።
.
ፍቃድዎ ከሆነ ግርማዊ ተፈሪ
እንዳገሬ ሹመት በሉኝ ፊታውራሪ
በሟች ከመጠራት ስለሚሻል እሱ
ይበሉ ጃንሆይ ሹመቴን መልሱ።

(ቴዲ አፍሮ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
#የሀቅ_መንገድ_ችቦ

በጨቅላ እድሜው
ከመከራ ችጋር ጠልቆ የተፈተነ
አንዱን እያነሳ አንዱን እያመነ
ለልቡ ላይ መሻት ጠልቆ እየመነነ
በጥያቄ ናዳ ሰርክ ሲብሰለሰል
በትንሿ ልቡ ሀቂቃ ለማከል
ሰው ይሄ ሰው
ይሄ በኒ አደም ላፍታ ቢስተካከል
የከረረውን ገመድ ጨብጦ
ተሰዶ ነበር ወዳጅህ
ተሶዶ ነበር ከሊልህ - ኢብራሒም አባ መውደድ
የሃቋን መንገድ ችቦ - ዳግም ለኩሶ ለማንደድ

ይገርማል የጀሊሉ ስራ
ከሰው መርጦ ለሹመት እንዲሉ
የዘጠኝ አመት ልጅ ገዝፎ ሲንጠራራ
ሁሉ ገፍላ ውስጥ ባለበት
ልጅ እግር ለትግል ሲጠራ

አዎን - በልጅነት እድሜ በጨቅላ አይምሮ
ዛሬው ላይ ሲፀና ነገን አሳምሮ

ያላንዳች ፍራቻ
ያላንዳች መታከት
እጆቹን ለፊጥኝ
እግሩን ለትኩሳት አሳልፎ ሲሰጥ
ሀቅን ተመርኩዞ ቢጣልም ከረመጥ

ካአንድ አንተ በስተቀር
ከቶ ማያሻርክ ችሎ ማያጋራ
ከሳት ቢወረውር አልበገር ያለው
ኢብራሒም ነበረ የነብያት አውራ
ኢብራሒም አባ መውደድ
የሃቋን መንግድ ችቦ - ዳግም ለኩሶ ለማንደድ

የወዱዱን የውዱን እርዳታ ያለው
ብትገባው ነው ያቺ ሃቅማ
የጅብሪልን ክንፍ አሻፈረኝ ብሎ
የአሏህን እርዳታ ብቻ ያስባለውማ
አዎን ' ያ ናሩ ኩኒ በርደን ወሰላማ ' ያስባለለትማ

አንተ በሰጠኸው በአደልከው ትልቅ ዲን
ብቻውን የቆመ ካለም ሁሉ ጎዲን
በጥቂት ልቡ ላይ በአደልከው በረካ
ስንት ገድል ፅፏል ባንተ እየተመካ
የአንድ ልጇን ሂወት ጥራ ለማስቀጠል
ከበርሀው ሁዳድ ገብታ ስትቃጠል
አሰብኳት ሀጀራን ባልሆንም እንደናት
አምጣ ብቶልድም ቃልህ እንዳፀናት
እዝነትህን ሽቶ
ስንቱ የገረጣ አካል በቃልህ ሲወዛ
የአንድ ልጁን ሂወት
አርግፎ እንደቅጠል አረጥቦ እንደጤዛ
ኢብራሂም ለብቻው እንደሺ ሲበዛ

ኢስማኢልስ ያባቱ ልጅ
በልጅነት እድሜ ማስተዋል ሳያንሰው
በቃልህ ፀንቶ ነው
ከገዛ አባቱ ካራ የተዋሰው
እናትየው አሚን
አባትየው አሚን በዱአህ የፀኑ
ከሩሀቸው በላይ ላንተ ደጅ የጠኑ
አጀብ ነው እርዚቅህ
ብርቱ ነው መኽሉቅህ
ከራሱ ተዋድቆ አንተን የሚያልቅህ
አያልቅም እዝነት እስቲ እኔን ጠብቀኝ
እንደልቤ ኖሬ በስምህ እንድቀኝ
አጥምቀው ቅኝቴን ባንተ ቃል ባንተ ስም
ዱንያ ሲገፋኝ ብርታት እንድቀስም

ቶፊቅ መሀመድ ( #አዲብ )
@Tufaw_muhe
#ኢድ_ሙባረክ

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
#ደስታና_ይሉኝታ

ተመልከች እንግዲ
ከመሄድ ላይ ሆኜ ለመሄድ ስታትር
የመድረሻዬን ጥግ ስለካ ስመትር
እንዳሰሩት ነገር በገመድ ጠርንፈው
የአይንሽ ጨረር ብቻ እግሬን አናቀፈው

የአሳሰርሽው ገመድ በውል አይታይም
መሄድ እሄዳለሁ መንገድ አይገታኝም
አካሄዴ እንጂ ውሉ ያልታወቀ
መድረሻዬ እንጂ ስጠጋው የራቀ
መሄድ እሄዳለሁ መንገድ መች አለቀ
አይተሽ እንዳላየ
ሰምተሽ እንዳልሰማ ሆነሽ እያለፍሽኝ
ለመነሳት ስጥር ስንት ግዜ ጣልሽኝ
ማጣቴን አምኜ
መንገዴን ስጀምር ሽንፈቴን ስቀበል
ጠረንሽን ይመጣል
አካልሽን ብዬ ስር ስርሽ ስከተል
አየች አላየችኝ
ሀሳብ አውጠንጥኜ ለመደበቅ ስሸሽ
አይታያለች ብዬ
ከፍርሀት ጋራ ደስታን ስምነሸነሽ
የአይንሽን ጨረር ስፈልግ ስርቀው
በአንቺ መታየቴ
ደስታና ይሉንታ ልቤን አስታጥቀው
ህመምተኛ ልቤን
እኔ በልጥ እኔ በልጥ
የሚል ሙግት ይዞ እየተናነቀው
ሊቆም ሲል ተፈታ ሲሮጥ የታጠቀው
ትጥቁን አያበጃጅ ወይ መቆሙን አይተው
መንገዱን ሲዋቀስ እግሩ እየጎተተው
ከእግሩ ሲዋቀስ አካሄዱን ሳተው
አይንሽ ፍላጋ
አካሄድ ሲያጠና ለመራመድ ሲጥር
እንዴት ይሻገረው የአይንሽን አጥር

ቶፊቅ መሀመድ ( #አዲብ )
@Tufaw_muhe

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
አታውቂም
.
.
አታውቂም
ከጠረንሽ ጋራ ሱባኤ እንደገባሁ
አታውቂም
ወንድ አይደለም እንዴ
እስከሚሉኝ ድረስ ቁጭ ብዬ እንዳነባሁ፡፡
አታውቂም ባገኘሁት ዘፈን ሆድ እንደሚብሰኝ
አታውቂም
ስላንቺ ለማሰብ ዘመን እንደሚያንሰኝ፡፡
አታውቂም
ከለበስሸው ጋራ መቀመጥ ማምሸቴን
አታውቂም
እኩያ እስከማጣ ብቻዬን መቅረቴን፡፡
አታውቂም
:
አታውቂም
:
ብታውቂም አትመጭም
አትመጭም አታውቂም
ምን ብዬ ልፀልይ ከህይወት ይዤ ቂም፡፡

(ኤልያስ ሽታሁን)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
ክብሯን ወዳጆቼ ነገ ባማረው ቅዳሜያቹ ከኔ ጋር እንድትሆኑ በታላቅ ፍቅርና ትህትና አስገድዳቹሀለው 😍
ነገ ከ6:00 እስከ 8:00 ባሉት ድንቅ ጊዜዎች አይኖች ሁሉ ወደ #አፍሪ_ሄልዝ ይተማሉ 🙏

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
ምን?ነበር ውላችን
.
.
ምን ነበር? ውላችን
የገባሽልኝ ቃል
የገባሁልሽ ውል፥
ማንም እንዳይሰማ
ገለን የቀበርነው
በኔና አንቺ መሀል።
ምን? ነበር መሀላው
መፅሐፍ ቅዱስ ይዘን
በተራ በተራ የተቀባበልነው።

ልትከጂኝ ልከዳሽ
ልጠይኝ ልጠላሽ
በሳለ ክፋት ጦር
ወግቼ ላደማሽ?
ትተሺኝ ልትነጉጂ
ማንም ምንም ሆነሽ
ወዴትም ልትሄጂ?

ትላንት ላይ ወዳጅ
ዛሬን ጠላት ልንሆን?
ያ ሁሉ መዋደድ
ያ ሁሉ ፍቅራችን
እንደጤዛ ሊተን?

ዝም አትበይኝ እንጂ

ምን ነበረ ስሙ
እስቲ ስጪኝ ምላሽ
ከረሳሁ አስታውሺኝ
ከረሳሽ ላስታውስሽ!!!

ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
መልስ አልባ ጥያቄ
.
.
ምነው ምን ነክቶን ነው
መውደድ አልሆን ያለን
ፍቅር አልሆን ያለን
ተጣመርን ባልን
በዛች ሰአት ቅፅበት
ሁለት የሚያረገን

ምንድነው ነገሩ፥
በኔና አንቺ መሀል
የመጣረስ ችግኝ
ስሩ መጠንከሩ
ጣፋጭ ያልነው እለት
ላፍታ ተለውጦ
ጎምዝዞ መምረሩ

ምንድነው ሁኔታው
ምንድነው ሚስጥሩ
አልገለጥ አለኝ
ቅኔ ሆኖ ነገሩ።

ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
ለፅድቅ : ፍትሀት : ሀጥያትን : ካረገ፣
መርገምን : በረከት : አርጎ : ከፈለገ፣
መሰዋዕት : አርጎ : እጣን : አሽቀንጥሮ : ቆሻሻ እያጨሰ፣
ገነትን : እያለ : ሲኦል : ከፈለሰ፣

......
በየቱስ : አምክሮ : ሞገስን : ይስባል፣
በነገር : ጎዳና : አቡዋራ : ያቦካል፣
ምሳሌውን : ንቆ : ፈጣሪው : ጋር : ቀርቦ፣
እንዲህ : ጠየቀ : አሉ : ጥጋብን : ተርቦ፣
አሳ : ስጠኝ : አለው፣
ዳቦ : ስጠኝ : አለው፣
እግዜርን : በእግዚአብሔር: ብሎ : እየለመነው፣
ፈጣሪም : ሊቀልድ : ይህን : አሰበና፣
ይሁን : ብሎ : ቸረው : ድንጋይ : እና : እባብ፣
ለንቀቱ : ክብር : ለጥጋቡ : ርሀብ፣

❗️ማሳሰቢያ የመጨረሻው አንጓ ላይ ያሉት ቃላቶች መልካም ክፉዎች ከሚለው ከሌላኛው ግጥሜ ጋር ቢመሳሰሉም። ፍፁም የተለያየ ሀሳብን ይዘዋል ።
ናታን ኤርምያስ
@UniqueDy

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
#አውቆ_አለማወቅ

እርግጥ ነው አፌን ፈትቼ መናገር አልቻልኩም።
በውስጤ ግን ቃል መሆን ያልቻሉ ካለመሆን የታበዩ እልፍ እላፍ ጩኸቶች አይምሮዬን ሰንገው ይዘውታል።
እያንዳንዱን ጩኸት ላድምጣቸው ብል እራሴን አግንቼ ማጣው ይመስለኛል። እራሴን ካለማግኘት ደግሞ እራሴን አግንቼ ማጣቱ ይበልጥ ይጎዳኛል በማለት ዝምታዬ ያዘላቸውን እልፍ አዕላፍ ጩኸቶች ባለማድመጥ ውስጥ ሆኜ አደምጣቸዋለው። ግን እራሴን እሸውደው ይሆን?
አላቅም። አለም ላይ እራስን እንደመሸወድ ያለ ከባድ ነገር ይኖራል ብዬ አላምንም። ግን ድርጊቱ ሚያመጣውን ተፅዕኖ በማሰብ ድርጊቱ እንዲሆን አለመፍቀድ እራስን ከመሸወድ ይልቅ ብልሀት ይመስለኛል። ምክንያቱም አንዳንዴ ማወቅ ብዙ ነገሮችን በአመክንዮ ለማየት የሚደረግ ጥረት ቢሆንም ያን ጥረት ማድረግ ደግሞ ደስታ የተባለ የሂወትን ፍሬ በገዛ ፍቃድ መሬት ላይ በትኖ ለመልቀም እንደመታተር ተደርጎ ይወሰዳል።ነገሮችን ላፍታም ያህል ቆሞ ብለን ካስተዋልናቸው ደግሞ አለም ላይ ደስታን ከሚፈጥሩ ቁልፍ ነገሮች መካከል አለማወቅ ግንባር ቀደሙ ነው። የማወቅ ጉዞ ባያበቃም ሽንፈትን መቀበል ድል እንደመደገስ ይቆጠራል። ከዚ ሁሉ ውጥረት ከባዱ ግን አውቆ አለማወቅ እንደሆነ ጥርጥር የለኝም !።

ቶፊቅ መሀመድ ( #አዲብ )
@Tufaw_muhe

@Am_in_love
@Am_in_love
@Am_in_love
አወይ አንቺ
.
.
በጠመቅሽው ጠላ በጣልሽው አረቄ
አወይ የወንዱ ልጅ ቀረኹኝ ወድቄ።
ወርቁን አመሳጥረሽ ድገም ድገም ያልሺኝ
ለካስ ኋላ ኖሯል ጋን ልታሳቅፊኝ።

ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
አትፅናኝ
(መዘክር ግርማ)
.
.
ሞትን አንመልሰዉ፣ እናውቃለን አይሸሽ
ስንት ጥፍራም ኀዘን አይተናል መሰለሽ!
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማቀይር አምነን
ስንት ጥፍራም ኀዘን፣ እንደማይቀር አምነሽ፤
ዳሩ ታውቂዋለሽ።

አቀጣጡ ክፋት፤
አመጣጡ ም‘ፃት፤
ግን ከሄደው ሁሉ፣ ከተመላለሰዉ
ምን ይባላል ይኼ፣ ባንቺ የደረሰዉ?!
ምን ይባላል ይኼ? አንቺስ ምን ልትባይ?
እኩይ ነዉ እታለም፣ ሽንገላ እንደ ሥራይ።

በእድፋም ጥፍሩ፣ ቧጦሽ ጥፍራም ኀዘን
መፅናናት መመኘት፣ ምንድነዉ መማፀን?
ምንድን ነዉ ዕንባ አባሽ?
ምንድን ነዉ ማገገም?
ዕንባሽን ማድረቂያ፣ አልሰጥሽም ማ‘ረም።
እሪ በይ!
ቢል በይ!
ኩርምት በይ–ዋኔ!
ላንቺ መፅናናትን፣ አልመኝም እኔ።
ወይኔ በይ!
ወዮ በይ!
ተይ አልልም ጭራሽ፤
አለመፅናናት ነዉ፣ አንቺን የሚያፅናናሽ!

@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
Forwarded from የትዝታ ወልዴ ግጥሞች (Tizita21)
ስትመጪ ጊዜ
የተናገርሻቸዉ እሾህ መርዝ ቃልሽ
የለፈለፍሻቸዉ ለከት ያጣዉ ስድብሽ
ለዛ የማያቀዉ ጭቃ አንደበትሽ
ዉስጤን አንቶግቱጎ
አንቺን ለማስከፋት ዉስጤ ቂም ሰንጎ
ነይ ብዬ ስቀጥርሽ
ስትመጪ ጊዜ ቁስሌ ተሻረልሽ።
ደሜ ሙቀቱን ለልቤ ሰጠና
ምት ሆኖ አረፈዉ አንቺን ሲያይሽ ገና
እንኳን እኔ ቀርቶ
አንቺ ስትመጪ
ሰማዩ ዳምኖ ጠቁሮ እንዳልነበረ
ካፊያዉን ሊያዘንበዉ
ፀሀይ ተደባልቆ ጅብ ወለደ አሉ ትርጉሙ ያልገባዉ
.......እናምልሽ ዉዴ
እነዛ ከዋክብት በጉም ተሸፋፍነዉ የተደባበቁ
አንቺን ለማየት ግን ድል ነስተዉ ደመቁ።
እንኳን እኔ ቀርቶ
መከፋቴን አይታ ያዘነች ጨረቃ
አንቺን ስታይ ጊዜ አየዋት ቦርቃ
እና ምን አለፋሽ
ቁጣዬ ንዴቴ ጥፋትሽ ሲለካ
ባንቺ ፊት ሲመዘን ምንም ነበር ለካ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ተፃፈ በትዝታ ወልዴ
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
ልቤ አለ ዳመራው
.
.
ለመስከረም ችቦ ለመስቀል ዳመራ
ይኸው ልቤ አለልሽ እንደጉድ ሚያበራ።
አትፈልጊ ክብሪት ጭረሽ ልታነጂው
ዛሬም ሲነድ አለ አምና እንደለኮሺው።

ዘመንሽን አፍኪው እኔን እያከሰልሽ
አጠቅምም ብለሻል በዚ እንኳን ልጥቀምሽ።
ይሄ ሞኙ ልቤ ስንት እንዳላለመ
ህልሙ ቅዠት ቢሆን ችቦ ሆኖ አከተመ።

መልካም በአል ይሁንላችሁ!!!

ማይክል ሰለሞን
(የቡዜ ልጅ)
@yegetemmender
@yegetemmender
@yegetemmender
2025/07/04 09:47:16
Back to Top
HTML Embed Code: