Warning: mkdir(): Permission denied in /var/www/bootg/function.php on line 101

Warning: file_put_contents(aCache/detail/y/e/g/n/yegna_mastaweshaa.txt): Failed to open stream: Permission denied in /var/www/bootg/function.php on line 103
y_m ፎቶ ኤዲቲንግ - Telegram Web
💔
ስማኝ ባትሰማኝም😶


በበጋ መብረቅ ላይ ተደናግጬ ሳይ
በወፎቹ ግጥም ስመሰጥ ከሰማይ
ትኖራለህ ብዬ ፍለጋ ብወጣ
አንተን በመፈለግ እኔነቴን ሳጣ
ድረስልኝ ብዬ ራሴን ስቀጣ

የታዘበኝ ሁሉ ምራቅ ከተፋብኝ
በማያዉቀው ፍቅር ፈራጅ ከሆነብኝ
በመሄድክ መንገድ መቶ የሳቀብኝ
መተህ ንገራቸው ይህን ይወቁልኝ


አንተ ከሄድክ ወዲህ ብቻዬን እያለው
ማንም በሌለበት ብቻዬን እስቃለው
በአዋራ ሜዳ ላይ እንቅፋት ፈርቼ ልዘል አስባለው
የማላውቀውን ሰው ባንተ ስም እጠራለው
አቤት ማይለኝን ልሳን የሌለውን ውሻ አናግራለው
ሰሚ በሌለበት ብቻዬን እጮሀለው

አንተ ባትሰማኝ መተህ ላትረዳ
ልቤ ላንተ አድልቶ አደረገኝ ባዳ

ስለዚህ የኔ አለም

ምንም ባይገባቸው የልቤን እውነታ
ትመጣለህ ብዬ ልንገር በስሞታ
በትናንት ትዝታ ላንተ ራሴን ባጣ
ምትመጣ ከሆነ ዘላለም ልቀጣ







@K0555555



ተፃፈ በቃል አበበ
👦 አንተ ሁሌ ትልቅ እንደሆንክ አታስብ። እኔ ብቻ አቃለው እኔ ብቻ እችላለሁና እበልጣለሁ አትበል። 😮 ምናልባት ምትሻልበት መንገድ ቢኖርም ሌላኛውም ሰው ካንተ ሚሻልበት የራሱ የሆነ ነገር አለው።😐 ስለዚ ሰውን አትናቅ፤ ከቻልክ አንተ ለሱ የበለጠ ክብርና ፍቅር ስጠው።😉 ምናልባት ካንተ በምን እንደሚሻል (እንደ ሚበልጥ) ስታውቅ ትማርበት ይሆናል!!😁😁

አስቴር የእናቷ ልጅ 🙏 🙏
ማሩኝ 🙏

እኔን ብላቹ እዚህ የተገኛቹ
በዝምታዬ ያስከፋኋቹ
ማሩኝ በእናታቹ !!

✍️ @itzmeastu2

ብእሬ ነጥፎ ነበር አሁን ግን ለመመለስ እየጣርኩ ነው ። እስኪ አበርቱኝ ወዳጆቼ አለንልሽ በሉኝ 🙏😊
ባንተ ምክንያት ሞታለች ካሉህ እመናቸው !

መኖርን ካለመኖር መለየት ተስኖኝ ውስጤ ከእለት እለት እንደ አለት እየፈረሰብኝ የህይወትን ትርጉም ከዘነጋሁ ቆየሁኝ። አዎ መተንፈስ መኖር ከሆነ አለሁኝ መብላት መጠጣት መሄድ መራመድ አለች አልሞተችም ካሰኘ አዎ አልሞትኩኝም። ግን ፍቅር እመነኝ። ከእለት እለት እየሞትኩ ነው። ነብሴ በናፍቆት ተጨንቃ ትንፋሽ እስኪያጥረኝ አንተን ያሰኘኛል። ለመኖር እና ለማኗኗር ስል ብቻ መተንፈስ ይኖርብኛል። ግን ያላንተ እና ላንተ የማይደረጉ ነገሮች ሁሉ አስቀያሚ ናቸው። ጥቂት ደስታ ብዙ ሀዘን የነገሰባቸው። እናልህ ውዴ የለሁም ሞቻለሁ በናፍቆትህ ከሰውኛነት ተራ ወጥቻለሁ። በአካል ከሰው መሀል ብቀመጥም ነብሴን እና ደስታዬን ካንተ ጋር አጥቻለሁ። አዎ የምተነፍስ ግኡዝ የምበላ ድንዝዝ የምጠጣ ግን የማረካ አለት ሆኛለሁ። መምሰል እንጂ መሆን ተስኖኛል። የእውነት መኖር ታክቶኛል። አፈር አለብስኩም እንጂ በቁሜ ሞቻለሁ። ስለእውነት ስልህ በቃላችን መሰረት አንተን ሳጣ በመጣብኝ ጣጣ እራሴንም አጥቻለሁ።


@itzmeastu2
ክፋት በቆንጆ ሴት ያምራል። ምክንያቱም የብዙ ፈተና ውጤት ናት። መሰበር መገፋት መዋረድ መቀማት ማጣት መደሰት ስሜት አልባ ሆነው ብርቅ የማይሆኑባት አይነት ሴት አለች። ብዙ ውድቀቶች ለነገ መነሻ ናቸው። ብዙ ሀዘኖች ለነገ መሰረት ይሆናሉ። ብዙ ያለቀሰች ሴት ሀዘን ምኗም አይደለም። ተደስታ ደስታዋ ያረጋላት እንስት ደስታ መከታዋ ሆኖ አያውቅም።

በብዙ ውጣ ውረድ ያለፈች ትላንቴ አለፈ ነገዬ የት እና ምን ላይ ይሆን እያለች ማሰብ የጀመረች ሴት ጥሩ ለመሆን እየጣረች ያለች ችግሮቿ ካነፆት ማንነት ለማምለጥ እየጣረች ያለች ብርቱ ሀይል ያላት ፍጡር ናት። ለመዳን ለማገገም እየጣረች እንጂ ዙሪያዋን በበቀል መረብ የተያዘች ምስኪን እርግብ ለማምለጥ ምትጥር በጭቃ መረብ ተይዛ በነጭ ልብዋ የምትተጋ ውብ ናት።

ክፉ ላለመሆን እየጣርን እንጂ ክፉ ሳንሆን ቀርተን አይደለም። ሁሉም ማንነታችን የሚታነፀው በተሰጠን ልክ ነው። የተሰጠንን ለመቀየር የማስተዋያ ጊዜው እስኪደርስ ሁላችንም የህይወት መንገድ ላይ ያጋጠሙን የእይቶቻችን ውጤት ነን። እንደ ብረት በእሳት የተፈተነች ሴት እሳት መትፋቱ ሊከብዳት አይችልም። እንደ ፀሀይ ጊዜውን በጨለማ የተቀማች ሴት የደስታ መጨረሻ መሆን ተስኗት አያቅም። እንደ አንበሳ በትንሹ ጉንዳን የተቆነጠጠች እንስት ነገዋ ላይ መድረስ አያቅታትም። ጥሩ ለመሆን እየጣርን ነው እንጂ ህይወታችን በመጥፎ አጋጣሚ እና እይታዎቻችን ቆንጅዬ አውሬ አርገውናል።

ፈተና ያስውባል። ጥንካሬን ለእኔን እና እችላለሁን ያላብሰናል። መስበር መጣል መግደል ቀላል እንደሆነ ተረድተናል። በብዙ እሳት የተፈተነ ወርቅ ነው ማስጌጫ። በትኩሱ ፈሳሽ እሳት እፉ ነው። እሷም ያው ናት ፈተናዎቿ ያነፆት ውበትን ከእራስ መተማመን ጋር ያላበሷት ቆንጆ ጥሩ ሰው ለመሆን የምትጥር ናት። ከነኳት ችግር ከቀረቧት አለም የምትሆን ውብ ፍጥረት እንስት ናት።

👩 ክብር በችግር ውስጥ እያለን ከትላንታችን አልፈን ዛሬላይ ላለን እንስቶች 🙏🙏🙏

ከአስቴር @itzmeastu2
መንገዳችን ሲለያይ አብሮነታችን ሲያበቃ
ያቀድናቸው ነገሮች ሁሉ ቁጭ ብለን በፀሀይና ጨረቃ
አከተመ አበቃልን ብለን በአንድነት
አንድላይ አለመሆንን ብናውጃት
በውስጥህ እረግመኸኝ ነበር እንዴ?
የሄደችበት አይቅናት ብለህ አቂመህ ነበር እንዴ
የምትወደው አይውደዳት እጄ ላይ ይጣላት
የነካችው ሁሉ አይድላት
አለም ትክፋባት ብለህ ነበር?
አዲስ ፊልም /Music Video/ ሊሰሩ አሰበዋል

በምን እናግዞዎት
Locetion
Material
ማማከር

እርሶዎ ሰራዎት ይስመር እንጂ እኛ ጋር ሁሉም አለ
ፊልም መስራት ካሰቡ
ወጪ በሚቀንስ መንገድ እኛው production እንመራለን ሳይሳቀቁ ውጪ በዛ ብለው እራሶትን ሳይዙ እኛው አመጣጥነን  ፍጥም ።
በተጨማሪ ፊልሜ ማጀቢያ ይኑረው ካሉ ከፊልሞዎ ታሪክ ጋር በተዋቀረ ግጥም አንጀት በሚበረብር ዜማ አዋዝተን በገበታ በሚዎዳጁንን አቀናባሪዎች አካራክመን እነሆ ባይዮች ነን።

ለስራዎት ግባአት ፈለጉ ?

ምን  ?
ቀንጡ መኪና
የአባቶቻችን መዘነጫዎች የነበሩትን
እነ ቮልስ  ቮልቮ ንቫ ላዳ. .........
ሞተር ሳይክል
ብስክሌት
ኧረ ቡዙ አለ  ብቻ የአዘጋጆትን/Director አይን ግልጥ ያድርግ እንጂ  አለን።

ለቀረፃ የሚሆን ቦታስ ምን ዓይነት ፈለጉ ?

ቅንጡ መኖሪያ ቤት
የድሮ ቤት
ሜዳ
መዋኛ ቦታ
እልም ያለ ጫካ
የድሮ ሙሴ ባቡር ሀዲድ
ድልዲያ
ማማ
የአበባ መንከባከቢያ
የገበያ ማዕከል....
በክልል ቢሉ
በዚችው በመዲናችን
ሁሉ ዝግጁ ነው

ኧረ ቡዙ አለ  ብቻ የአዘጋጆትን/Director አይን ግልጥ ያድርግ እንጂ  አለን።

ሙዚቃ ጨርሰው ለቀረፃ እየተዘጋጁ ነው ጎሽ እንኳን አለቀ !

ምን እናግዞዎት ታዲያ

የትዕይንት ምስል ታሪክ/story እንፃፍሎት
ምስል ታሪክን ወደ/screen playe እንቀይርሎት ?
እናዘጋጅሎት ?

ዘጋቢ ፊልም/Docmentry ልሰሩ ነው
ይቅናዎት
  ምን እንርዳዎት
ጥናት/Resreach ፈለጉ
አለ
ተዋናይ ማቅረብ

ሰዓት ማክበር

የአዘጋጁን /Director ምናብ በእውን

ማሳየት ሳይሰለቹ መታዘዝ መለያችን ነው
እንደ ልጅ ታዘኖዎት
በዕውቀትዎ ይሰራሉ ።
ቲዩበር ከሆኑማ
የበሽበሽ  ብዛቱ ተወዳጅና ተጠባቂ  አጫጭር ድራማዎችን ከፁሁፍ እስክ ዘግጅት  Dramatic Music video ማዘጋጀት ..........ኧረ ብዙ ነው በሻይ ወጪ ሰራዎትን ጨርሰው የድግስ ያተርፋሉ።
ብቻ ይደውሉ 0943191983
Telegram @Sebezzfilm
Email sebezfilm@gmail.com
2024/04/29 11:05:01
Back to Top
HTML Embed Code: