Telegram Web Link
#ምኞት፥ ስለ መጪው አሮጌ ዓመት 🌼

አዲስ ሆኖ ይምጣ፤ መጪው አሮጌ ዐመት
ሰው በውድ ይገመት
እህልና ሲሳይ በርካሽ ይሸመት።
በጦም በፍስክም፥ ዱላ ለምንጠግብ
ጨቅላ ልጅ አስርበን፥ ጆፌ ለምንመግብ
ሰላም ይለግሰን
ከለታት አንድ ቀን፥ የሰው ወግ ይድረሰን።
ያርሶ በሌ ልጆች
በእንግዳ ሰው እጆች
ሳናረጅ ከመጦር፥
ይሰውረን ከጦር
-ያስጥለን ከበቀል
እንደ ድንኳን ችካል
አመሻሽ ተተክሎ፤ ጠዋት ከመነቀል።
በእልህ ምትክ መላ
ልባችንን ይሙላ።
ጉልበቱን ለሚያመልክ ፤ ጉልበቱን ያቅልጠው
ለደግ ሰው አክሊል
ለክፉ ልብ ይሰጠው።
ይፍለቅ ከየመስኩ
የርህራሄና የማስተዋል ጠበል
ቃል ምግባር ይወልዳል፤ አሜን! ይሁን እንበል!
* * *
(በእውቀቱ ስዩም)

* * * 💜
@wubaroma

👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/firstpray
https://www.tg-me.com/firstpray

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/yemaledasink
https://www.tg-me.com/yemaledasink
https://www.tg-me.com/yemaledasink

ለሌሎች እንዲደርስ #SHARE!
🙏🙏🙏
Problem Solved !
htts://www.tiktok.com/@ezanamesfin00
Live stream started
Live stream finished (2 minutes)
2025/06/29 03:58:44
Back to Top
HTML Embed Code: