ጣቶቹን ፀጉሬ ውስጥ ሰዶ ወደራሱ አስጠጋኝ። ይበልጥ ሲቀርበኝ ከመቃወም ይልቅ ልስመው ፈለግኩ። በሌላኛው እጁ እንባዬን ከጉንጬ ላይ ጠራረገው። ከንፈሩ ከንፈሬን የሚነካበት ሰዓት ረዘመብኝ። መጠበቅ አቃተኝ። ሳምኩት። ነፍስ በሚያሳርፍ መሳሙ ለደቂቃዎች ሳመኝ።
"ምንም ይሁን ንገሪኝ፣ አንድም ሳታስቀሪ የተሰማሽን ንገሪኝ፣ አንቺ ራስሽን ከምትረጂው በላይ እረዳሻለሁ። እንባሽ ከመጣ አልቅሺ ብቻ ልስማሽ!" አለኝ መረጋጋቴን ሲያይ
"አሁን እኮ መሽቷል። ሌላ ቀን ላውራህ?"
"ማደር ካለብኝ እየሰማሁሽ አድራለሁ።"
አውርቼ የማላውቃቸውን ብዙ ነገሮች ነገርኩት። ሳለቅስ አያባብለኝም። እጄን እየደባበሰ ይሰማኛል። ስለቤተሰቦቼ ሁሉንም ነገርኩት። አያቴ ሲሞት ከልጅነቴ ጀምሮ ምርኩዙ ሆኜ ስላደግኩ ያለውን ንብረት ሁሉ ተናዞልኝ ነበር የሞተው። በንብረቱ ሳቢያ ዘመዶቼ ሁሉ በፊት ይጠሉኝ ከነበረው በብዙ እጥፍ ጠሉኝ።
የደበቅኩት የለም ሁሉንም ነገርኩት። ያልሰማኝ የለም። ያለፍትን ውሳኔዎቼን በሙሉ ቆም ብዬ እንዳይ አደረገኝ።
"ከኢሳያስ ጋር ያለሽ ክፍተት ከፍቅርሽ ይበልጣል? ወይስ ከክብርሽ? ክፍተታችሁ ከፍቅርሽ ከበለጠ ችግር ውስጥ ነሽ!! ካልሆነ ግን አስቢበት!" ነበር ያለኝ ስለትዳሬ ሳወራው
እቤቴ ስገባ እንደሌላው ቀን ኢሳያስ የሌለበት ወና ቤት አላስጠላኝም። አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ ከራሴ ጋር አወራሁ።
"በራስሽ መተማመን ካለብሽ ራስሽን እወቂው። ጠንካራ ጎንሽን እና ድክመትሽን ለዪ፣ ድክመትሽን በጠንካራው ነገርሽ ለመሸፈን አትሞክሪ፣ ተጋፈጪው ማሻሻል ያለብሽን አሻሽዪ፣ ያለፈ ቁስልሽን ተቀበዪው እመኚው እንጂ አትሽሺው።" ያለኝን የሲሳይ ንግግር አሰብኩት። ደስ ብሎኝ ተኛሁ።
★ ★ ★
በጠዋት ወደስራ ስገባ ሲስተር ቀለምን ቀድማኝ አገኘኋት ። ጠርቻት ለልጆቿ የሆነ ነገር እንድታደርግ የተወሰነ ገንዘብ ሰጠኋት። እጄን እያገላበጠች ስትስም እንባዋ ነካኝ። አቀፍኳት። እስከዛሬ ልረዳት ባለመቻሌ ራሴን ረገምኩት። እቤቷ ሄጄ ልጆቿን ላይላት ለሳምንቱ መጨረሻ ቀጥርያት ስራ ጀመርን።
በህይወቴ ከመቼውም ጊዜ በላይ ደስተኛ ነኝ። ግን ደግሞ መንታ መንገድ ላይም ነኝ። ሲሳይና ኢሳያስ!!
የብዙ ዓመት አለሁሽ ባዬ ግን በራሴ ትህምክትና ፍራቻ ያልተረዳሁት ኢሳያስ
ሳልነግረው የማስበው እና የሆንኩት የሚገባው ሲሳይ
መወሰን ነበረብኝ። ማናቸውንም መምረጥ ህመም አለው። ፈሪ ግን አይደለሁም። አልሸሽም።
★ ★ ★
ውሳኔዬን መጀመሪያ ለሲሳይ ማሳወቅ ፈለግኩና አገኘሁት። ነገርኩት።
"እርግጠኛ ነሽ?" አለኝ መጀመሪያ ግራ እየተጋባ
"አዎን። መቼም እንደዛሬ እርግጠኛ የሆንኩበት ውሳኔ የለም። " መለስኩለት
"አሁን ነው የገረዝሽኝ። ያማል።" አለኝ ድምፁን ዝግ አድርጎ
"አዝናለሁ። አንተ በህይወቴ ፈጣሪ የላከልኝ መልዓክ ነህ። ባልጎዳህ በወደድኩ። " አልመለሰልኝም። ግንባሬን ሳመኝ። ለመጀመሪያ ጊዜ ሲከፋው አየሁት። ሊሄድ መንገድ ከጀመረ በኋላ መለስ ብሎ እንዲህ አለኝ
"ኢሳያስን እድለኛ መሆኑን ንገሪው!!"
★ ★ ★
አሁን ጨረስን።
(ሲስን ማፅናናት የምትፈልጉ ቺኮች ሊንኩን ከላይ አስቀምጬላችኃለሁ!!! ትረካውን ስሙት ሃሃሃሃ)

👍23❤5😢2
ጌታ በሶስተኛ ሚስት ስለባረከኝ ... አመስግኑልኝ!!
አንዱ ዘመዴ ነው (ደቡቤው ).... ዼንጤ ሆኖ ወጥረው ሲያስተምሩት ከርመው!! በጋብቻ ላይ ጋብቻ ዝሙት ነውን እኮ ለብዙኛ ጊዜ ገርበውለታል🤣🤣
የምስክርነት ሰዓት ላይ ምስክርነት አለኝ ብሎ ቆመና
"ጌታ ውለታው ለኔ ብዙ ነው!! (ሁለት ዘለላ እንባ ጠብ ጠብ) ትላንት በሶስተኛ ሚስት ባረከኝ!! ጌታ ሲረዳኝ ሳታስቸግር ነው ወደ ቤት የገባችው(ጠልፎ እኮ ነው🤪) ... ከሁለቱ ሚስቶቼ ጋር ፕቅር በፕቅር ሆናለች!! ጌታ ገና በብዙ ይባርከኛል አመስግኑልኝ!!" (በኛ ለዛ ይነበብልኝ)
ኸረ ወዮዮዮዮዮዮዮዮዮ 🤣🤣🤣
ምን ለማለት ነው?
ሀይማኖተኛ ሀይማኖተኛ እያጫወታችሁ ደሞ በጎን
የኔ ብሄር ይድመቅ
የእገሌ ብሄር ይድቀቅ...
የምትሉ ዘመዶቼ እንዴት ናችሁ???
(ሁለቱንም አንድ ላይ ማስኬድ ጠዋት ለብልፅግና ከሰዓት ለኢዜማ የድጋፍ ሰልፍ እንደመውጣት ነው!!)

👍11😁4
እናንተ ግን ካልማልኩ አታምኑኝም እንጂ
አንድ የባሌ ጏደኛ ሚስቱ ከድታው ለ18 ዓመት ያቆመውን መጠጥ ጀምሮ(አልክሆሊክ ነው) ለ2 ሳምንት ቀን ከሌት ሲጠጣ ቆይቶ ባሌ ከስራ ቦታ ደውሎልኝ 'ከመሞቱ በፊት እባክሽ ተቋም ውሰጂው' ብሎኝ እቤቱ ሄድኩ::
ቤቱ ከጏዳ እስከ ሳሎን የሞላው የቢራ ቆርቆሮ ... ወተት ... እና የፒዛ ካርቶን
"ለመሆኑ ትተኛለህ?" አልኩት ... መጠጡ አልቆበት ይንቀጠቀጣል
"ትንሽ ደቂቃዎች እተኛለሁ!"
(ደሞ ወጉ ፊልም ከፍቷል)
"ፊልም እያየህ ነው?" አልኩት ለራሴ የማወራው ግራ ገብቶኝ! ምን ቢለኝ ጥሩ ነው?
"አዎ ይሄ ፊልም በጣም ቆንጆ ነው! ስንቴ አየሁት መሰለሽ?"
"ስለምንድነው?" እለዋለሁ
"እኔንጃ አላስታውሰውም! ያው ሰክሬ ስለማየው ታሪኩ ትዝ አይለኝም! እያደጋገምኩ የማየው ለዛ ነው!" ......

😁12👍8
ትህትና ወንበር እያለ መሬት መቀመጥ አይደለም!! አንተ ወንበር ላይ ተቀምጠህ ካንተ ይልቅ ሊቀመጥ የሚያስፈልገው ሰው ወንበር አጥቶ ሲቆም ወንበርህን መልቀቅ እንጂ!!
🙏🏽🙏🏽 ይሄ ኢሞጂ በየቦታው ስጠቀመው ምርር ብሎት ነው መሰለኝ ቅድም 🙌🏽 ይሄን እየሆነ አስቸገረኝ!! (ያለአግባብ ተጠቀምሽኝ ነገር መሰለኝ::)
ቅድም አንዱ ሙልጭ አድርጎ የሰደበኝ ስር እራሱን button ደጋግሜ ስነካው ስክሪኑ ላይ የሚመጣው 👎🏽👎🏽👎🏽 ይሄ ነው!!
ጭራሽ መጨረሻ ላይ አልባሌ ጣት ገጭቶኝ ወጣ🤣🤣 (አታሽቃልጪ የምን አጉል ትሁት መሆን ነው ተበሳጭተሻል ለማለት ፈልጎ መሰለኝ)
ሰዎችዬ ትሁት መሆን ምርጥዬ ነገር ነው:: መናደድና መቆጣታችንም ግን ሰው እንጂ የሚያደርገን ሌላ የለውም!!

👍6🙏1
የትዳር አጋራችንን እግዜር ነው የሚሰጠን ብላችሁ የምታምኑ ሰዎች .... እስኪ አንዴ ጠጋ በሉ! የምራችሁን ነው?
እግዜር ለአዳም ሄዋንን የሰጣትኮ ሴት በምድር ስላልነበረ ነው!
ምድር በሰው ዘር ከሁለቱም ወገን ተሞልታ ራስሽን ፈልገሽ አጊንተሽ የሚስማማሽን ባል ፈልገሽ የምትመርጪበት ማሰቢያ እና ልብ ሰጥቶሽ .... አሁን ቤተሰብ እንኳን ለልጁ ሚስት ወይ ባል በማያጭበት ዘመን እግዜርን ማስቸገር አግባብ ነው?
እኔ የምሬን ነው እሺ አግብተሽ ... ተፋታሽ ... ከዛ እግዜር ሰጠ እግዜር ነሳ ልትዪ ነው ወይስ የሰይጣን ስጦታ ነበር ልትዪ?
አንተኛው ራሱ አስር ገርል ፍሬንድ ጠብሰህ እግዜርን ራሱ አምታተኸው ስታበቃ .... አስራ አንደኛዋን እግዜር ሰጠኝ ልትል ነው? (አስሮቹ ሳምፕል ናቸው?😜)
ስናገባ 'እግዜር ነው የሰጠኝ' ስንጣላ 'ይሄ የተረገመ ሰይጣን!!' (ሰይጣን ራሱ እኮ ግራ ገባው)
እስኪ እቤታችሁ ቁጭ በሉና ሄዋን አንኳክታ ትመጣ ከሆነ ጠብቁ.... ድህነት ብቻ ነው የሚያንኳኳባችሁ!!
አንቺም ወንድ በደረሰበት አትድረሺና 'ባሌ በመኪና ይምጣ' 🤪ብለሽ ፀልዪ እስኪ .... ተው እንጂ ....
ደሞ አንዳንዶች አለን እንጂ "እገሌን የእኔ ካደረግክልኝ!" ብለን የምንፀልይ ... ከዛ ደግሞ በአመቱ ሌላ እገሌ .... ፈጣሪ ራሱ ዝርዝሩ ብዝት ብሎበት .... ለፈርኦን እንዳለው 'ኸረ ህዝቤን ልቀቂ!' ነው የሚለው !!
አታፍሩምኮ ንጉስ ሰለሞንን በ700 ሚስቶች እና በ300 እቁባቶች ጌታ ነው የባረከው ትሉኝ ይሆናል😜😜😜
ከሆነ በጊዜ ንገሩኝ እስኪ ... በቀረው የእርጅና ዘመኔ አንድ አስሩን ላደራጃቸውና ተስማምተው በፍቅር እንዲያስተዳድሩኝ ፆም ፀሎት ልግባ 🤣🤣🤣🤣
እህህ የምር እረፉኣ? ስለ ሚስት ራሱ 700 ሚስትና 300 እቁባት የነበሩት ጠቢቡ ሰለሞን ያለውን ጥቅስ እየጠቀሳችሁ ..... ብልህ ሚስት ... አስተዋይ ሚስት....
ከ1000 ውስጥ የትኛዋ ነበረች አስተዋይዋ? በስማቸውስ ያውቃቸው ይሆን እንኳን በስብእናቸው?
ንግስተ ሳባ ናታ በሉ ደሞ ...

👍6🥰2❤1
እየቀለድኩ አይደለም ባለፈው ሀኪሙ
"እድሜሽ እየገፋ ስለሆነ የአመጋገብ ባህልሽን አስተካክዪ እንደ ወጣቶቹ ስኳር .. ጣፍጭ ነገር መብላትሽን አቁሚ!" አይለኝም ይሄ ከንቱ ... ደሞኮ ቸኮሌቴን እያላመጥኩ ገብቼ ነው::
"አንተ ይኸው በ65 ዓመትህ(ግምት ነው) የሰው ሞራል እየንካህ መንግስት ደሞዝ ይከፍልህ የለ? መቼ አረጀህ አሉህ?" ልለው ነበር!!
አንድ ወዳጄ ደግሞ ይባስ ብላ "እውነቱንኮ ነው በኛ ህገመንግስት የወጣቱን ዞን አልፈሻል" ብላ
ይኸው ቆሌ እንደራቀኝ ነው:: በዚህ ምክንያት ትክክለኛው የእድሜዬ ቁጥር ስለጠፋኝ .... ሀያ ቤት ስጠራ ካጋጠማችሁ እለፉኝ!!🤪🤪 እየተላለፍን!!
አንድ ወዳጄ እኮ ናት የስልኳ ፓስዋርድ የተወለደችበት ዓ.ም ነበር:: 'ሌላ ነገር ጠፍቶ ነው?' እላታለሁ ምን አለች:: 'እንዳይጠፋብኝኮ ነው!ይሄ 28 የምለው ነገር ሲደጋገም እውነት መስሎኝ ዋናው እንዳይጠፋኝ ብዬ ነው!" ብላኝ እርፍ ...
ቆይ ቀድሞ ነገር እኔ እንደአብዛኛው አርቲስቶቻችን 21 ላይ መገገም አቅቶኝ ነው?
መጀመሪያውኑ ሀያ ቤትን መልቀቅ አምሮኝ ነው?
ፀጊ(ልጄ) "ኸረ ማሚ እኔ ራሱ ሀያ ቤት ልገባ ነው! እየተላለፍን!" ብላኝ እንጂ 🤪🤪

👍9🥰3😁3
በቀደም አንዷ ሀበሻ የሆነችውን ጉድ ልንገራችሁ::
ከሆነኛው ፊልም ላይ ያየችውን ማርገዟን ሰርፕራይዝ ልታደርገው ... የእርግዝና መመርመሪያውን ኬክ ውስጥ አድርጋ ሳሎን አስቀምጣለታለች (ሲቆርስ እንዲያገኘው መሆኑ ነው) ... ምስኪን ወንድሜን ቆርሶ በልቶ ሲያበቃ ነው ጫፉን አይቶ ሲጎትተው ነገርየውን ያገኘው ...
ይኸው ሽንትሽን የሸናሽበትን አስበላሽኝ ብሎ ተጣልተው ሽምግልና ላይ ነን 🤣🤣🤣🤣
ኸረ ተው ግን የምንኮርጀውን ነገር እንለይ?🤪🤪

😁8👍4❤1🥴1
ቅድስቲቷ ሀገሬ አንጀቴን ትበላዋለች!!
(እስኪ አስኮሳትሩኝ ... የምሬን ነው!!)
"መብራት የቆጠረውን ቼክ አድርጊና ኦንላይን ክፈዪ" ይለኛል ባልዬ
"እህ ቆይ እነሱ ቼክ የማያደርጉ ከሆነ ቁጥሩን አሳንሼ ትንሽ ብር ብከፍልስ?" እላለሁ እኔ
"እህ ለምን ብለሽ ታታልያለሽ?"
"እህህ ትንሽ ለመክፈል ነዋ?"
"ይሄ እኮ ወንጀል ነው! ለምን ብለሽ ?"
"እህህ ይሄ ሰው.... ከአመት ዓመት እየመጡ ቼክ ካላደረጉ: አምነው የቆጠረውን ሙዪ ካሉኝ ትንሽ መሸቀብ ..ምናለበት?" አላልኩትም ... በልቤ ነው ያልኩት
..................2
ሰብሰብ ብለን ከከተማ ወጣ ስንል መንገድ ላይ ድንች : እንቁላል ... ታሽጎ ታሽጎ ዋጋው እላዩ ላይ ተለጥፎበት ተቀምጧል:: ... አጠገቡ ካርቶን አለ:: እቃውን ትወስዳለህ! የተለጠፈውን ብር ካርቶኒ ውስጥ ታስቀምጣለህ! መልስ ካለህ ከካርቶኒ ውስጥ ትወስዳለህ?
"ባለቤቱስ?" እላለሁ እኔ የማላርፈው ነገሬስ
"ማታ ሂሳቡን ሊሰበስብ ይመጣል:: ጠዋት እቃውን ሊያስቀምጥ ይመጣል::"
"እህህህ ቆይ ብሩን አሁን ይዘንበት ብንሄድስ? ወይም ሳንከፍል እቃውን ብንወስድበትስ?"
"ለምን ብለን?"
"እኚህ ሰዎች ምንድነው ችግራችሁ:: እኔ ሳውቅ በሀገሬ እንኳን ጥለህ ሄደህ ህእ ኪስህንም አንቀህ መጅራትህ ይታነቃል!" ... አላልኳቸውም .... በልቤ ነው ይሄንንም ያልኩት
.................... 3
አንድ ወዳጄ የመኖሪያ ፈቃድ አጊንታ በጣም ደስ ብሎኝ እያወራሁላቸው ነው! በፖለቲካ ኬዝ ነው ምናምን ብዬ ስቀላምድ
"ፖለቲከኛ ነበረች?" አሉኝ
"እይይ እናንተ ደግሞ ለኬዝ ነው እንጂ እሷማ ፊዚክስ አስተማሪ ነበረች"
"እና ምን ልታደርጊ ነው?"
"ስለምኑ?"
"ሪፖርት ማድረግ አለብሻ! ውሸቷን ነው! መንግስትን አታላለች"
"ኸረ በመድሃንያለም? ጭራሽ ራሴው ሪፖርት ላድርግ? ኸረ ንቀሉ...."
እንደተባባሪ ታይቼ አለፍኩት::
...,........................4
የአክስቴ ልጅ መንጃ ፍቃዱን ተምሮ ለፈተናው አንድ ሳምንት ሲቀረው ቀድሞውኑም ኢትዩዽያ ይነዳ ስለነበር ብዙም ሳያካብድ ለእራት የጋበዛቸውን የስራ ባልደረቦቹን ጠጥተው ስለነበር በዚህ ምሽትማ አልተዋችሁም ብሎ ሁሉንም በመሸኘት:: ብቸኛ ያልጠጣው እሱ ነበር:: መንገድ ላይ አንዱ
"እንኳን ደስ አለህ መንጃ ፈቃድህን ተቀበልክ!" ሲለው
"እሱ እንኳን ገና በሚቀጥለው ሳምንት ነው የምቀበለው" በማለት ሲያቀብጠው
ሁሉንም አድርሶ ወደቤቱ ሲመለስ በሩ ላይ ፖሊስ እየጠበቀው ነው:: አንዱ ደውሎ ምናለው
"ላንተው ብዬ ነው የደወልኩብህ:: ወንጀል ነውኣ? ለጋበዝከኝ እራት አመሰግናለሁ:: ጥዑም ነበር::"
.....................
እኚህ ሰዎች ... ኖርዌዥያን ሀይማኖት የሌላቸው ይበዛሉ:: ስነስርዓታቸው እና ታማኝነታቸው ... ሰው ምን ቢሆን ነው እዚህኛው ደረጃ ላይ የሚደርሰው ያስብሉኛል::
...........
በቅን ልቤ መቼ ነው ሀገሬ እንዲህኛው ሀቀኝነት ላይ የምትሆነው እላለሁ!!! ቅድስቲቷ ሀገሬ ..... ዋቴዋ ነፍፍፍፍፍፍ በእግዜር ስም የምንሰራው ሸፍጥ ........ በሃገር ፍቅር ስም የምንሰራው ማጅራት መምታት .... በሀይማኖት ጥላ ተከልለን ስራችን እምነት የለሽ ግብዝ ....ሜዬ ተይ ግን ንፅፅር ተይ ግን ተይ ትነቅያለሽ!!

👍21❤2😁1
የምር እናውራ ከተባለ ይሄ ትውልድ (ከቀደዳ ባለፈ) የአድዋ ድል ምኑ ነው?
መቼም በአንዲት አርቲስት ቂጥ ቀለም ሁለት ጎራ ለይቶ የሚፋለምን ሰው እንዴት በአድዋ ጎራ ትለያለህ ማለት ከባድ ነው። ይሁንና ከዓመት ዓመት የሚሳቡት የነገር ሰበዞች ቀጥነው ቀጥነው ወላ የአድዋ ጀግኖችን መከፋፈል ይዘናል። እሰይ የሚያስብል ነው ምጡቅነታች🙈🙈
'ከድሉ መሃል በእንዲህኛው ቀን በእንዲህኛው ሰዓት የተኮሰው የእኔ ብሄር ስለሆነ የዚህ ደቂቃ ድል የሚገባው ለእኔ ነው የሌላው ቀን ውጥንቅጥ ገደል ይግባ'
'ይህን ያህል ሬሳ ይገባኛል ምክንያቱም የዚን ያህል ነጫጭባ የገደለው የእኔ ብሄር ወታደር ነው' ዓይነት የታሪክ ክፍፍል የትምኮ አልታየም!
እኔ የማስበውን ልንገርህ (አስምርበት እኔ የማስበውን ነው ያልኩት) እስማማለሁ ስትል አስምርበት አልስማማም ስትል በጨዋ ደንብ ሀሳብህን አስረዳ ለምን እንዲህ አሰብሽ ብለህ ልትንበራጨቅ ካሰብክ ተጣላኝ አስቀድመህ
እኔ ኳስ በመሬት ባይ ነኝ
አድዋ ዛሬ ላይ መበሻሸቂያ አድርገን ፅንፍ ለይተን የምንቧችርበት ዓይነት ታሪክ ብቻ አይደለም።
1) ታሪክ ብቻ ነው ብለህ:: በቃ! ብለህ ልታጣጥል አትጋጋጥ
አድዋ ስነ ልቦና ነው።
በጣም በቀላል ምሳሌ ላስረዳህ አንድ ኢትዮጵያዊና ሌላ በቀኝ የተገዛች አፍሪካዊት ነጮች የተሰበሰቡበት ቦታ ሲገቡ እሷ የምታስበው 'ጥቁር ስለሆንኩ ነው የሚያዩኝ'
ኢትዮጲያዊቷ እንደእኔ ጥጋበኛ ከሆነች 'ቆንጆ ስለሆንኩ ነው ወይም ጨበሬዬ ከይፏቸውኮ ነው።'
ነጭነት ለሀበሻ የቀለም ልዩነት እንጂ የክላስ ልዩነት አይደለም። እውነት ነው የኛ ትውልድ አብዛኛው ነጭ ስናይ ጭራችንን እንቆላለን። ሀቅ ነው! ነጭ ስለሆነ አይደለም ሀብታም ነው ብለን ስለምናስብ ነው በቀለሙ ሳይሆን በኪሱ ነው። ባሪያም ቢሆን ሀብታም ከሆነ እንደምናሽላላው! ድህነት አፈር ይብላና!
ስለዚህ አድዋ የአንድ ወቅት ያለፈ ታሪክ ነው አትበለኝ። ዛሬም ደሜ ውስጥ ያለ ድል ነው።
2) አድዋ ድላችን ስለሆነ ራሳችንን ከመላዕክት እናጠጋጋም አትበለኝ።
የአብዛኛው ሌላ አለም ከሌላው ጥቁር ለይቶ አያይህም። ሞላጫ እከካም ድሃ ነህ ለእነሱ! ሲያይህ ትዝ የሚለው የደረት አጥንቱ የሚቆጠር ርሃብተኛ ችጋራም ነው። ታሪክህን እንኳን የሚያውቅ ጥቂት ነው። እነሱ የአፍሪካን ጥሩ ነገር ማውሳት ስለማይወዱ ነው ምናምን ብለህ ራስህን የምታፅናናበትን እውነት የሚመስል ማስተባበያህን ተው አትንገረኝ።
ምን ያውሩልህ? ዛሬም በ2021 የገዛ ወገንህን ሬሳ እየጎተትክ የድል መዝሙር የምትዘምር መሆንህን? አንደኛው መሃል ከተማ ጥጋብ ወጥሮት ለአንዲት እራት 36,000 ብር ውስኪ እየጠጣ ወገንህ እየተራበ ነው ሲባል 'ብሄሩ ምንድነው' ብለህ እንደምትጠይቅ? ይሄን ስልጣኔህን ያውራልህ?
ዓለም ዛሬ ላይ የሚያውቅህ ባለፈው ዓድዋ አይደለም! በዛሬው ዓድዋ ነው። የዛሬዋ አድዋ የት ናት? ጦርነት አንካሳ አድርጓት ህዝቦቿ እርዳታ የሚሰበሰብላት (እዚህጋ በመድሃንያለም ይዤሃለሁ የፖለቲካ ትንተናህን እናዳታመጣብኝ) ልጁን በብሽቅ ፖለቲካ ውርርድ ቀብሮ ሀዘን ያቆራመደው አባት ...... እንባ አይኖቿን ያሞጨሞጨው እናት....
እኔስ?
አድዋ የሰጠኝኝ ነፃነት ...አንድነት ... የሀገር ፍቅር ወዴት አደረስኩት? ወደየትም!
የምኖረው ዴንማርክ 400 ዓመት አንቀጥቅጣ ቀኝም ግራም ገዝታው የነበረ ሀገር ስለሆነ ለቀደዳው ይመቻል። 'ምንድነው በሀገራችሁ ወንድ አልነበረም እንዴ 400 ዓመት እንዴት ነው ጭጭ ምጭጭ የምትሉት?' ብዬ ለማብሸቅ የምመዘው ካርድ ነው::
ደስ ይላልኮ ደረትህን ነፍተህ 'የኔ አባቶችኮ እንቢ ብለው ...' ምናምን ብለህ ደረትህን ስትነፋ
ከዛ በተረፈ እኔ በአባቶቼ ጀግንነት ላይ ያከልኩበት ምናምኒት ጀግንነት አለ?
ለዛ ነው በበኩሌ ለብሽሽቅ ብቻ ብለን እዚህና እዚያ ጫፍ ባንጠረቅ ብዬ የማምነው።
ክብር ለአድዋ ጀግኖች🙏🏽🙏🏽🙏🏽🙏🏽

👍8
እኔ ነኝ ጤነኛ እነሱ?
ሬሳ በቀብር ፈንታ ሲቃጠል አይታችሁ ታውቃላችሁ ወይ?
እኔ ግን አይቻለሁ:: አጅቤ ወስጄ አስቃጥዬ ... አመዱን አጅቤ ... ምን አቻኮላችሁ ልነግራችሁ አይደል?
እኔ ሁለት ቀን ነው ያየሁት ... እቤታችን መጥቶ ... ለበዓል ... ተጫዋች .. ወጣት ነው! እነሱ
ቤተሰቦቹ ናቸው...
"ጆናስ እኮ ሞተ" ብሎ የሚነግረኝ አባቱ ራሱ ነው:: እኔን ነው ማየት ... ነጠላዬን አቀብሉኝ አልኩ:: እሱ እቴ ... ውስኪዬን አቀብሉኝ ብሎ በላይ በላዩ ይጨልጠዋል::
"ምን ሆነሽ ነው ኸረ ተረጋጊ!" አባትየው ነው በድጋሚ ..... የልጁን ሞት የረሱት መስለው ከወንድሙጋ ሌላ ወሬ ያወራሉ....
ልጁ
ይሄ ከተራራ ላይ ገመድ ወገባቸው ላይ አስረው የሚሽቀነጠሩትን ነገር ታውቁት የለ? እንደሱ ሲምዘገዘግ ነው ተፈጥፍጦ ...ትንሽ ቀን ሀኪም ቤት ተኝቶ የሞተው...
(እኔ ሀበሻ ነኝ! ምንም ሆኖ ይሙት ... ሰው ሞተ ከተባለ 'ወየው ልጄን... ወንድሜን ... አጎቴን ..." ነው! እነሱ 'እረፍ ስንለው አልሰማ ብሎ' ይላሉ:: 'ኸረ ሙት አይወቀስም ተው' እላለሁ በሆዴ ... (በነሱ ቆንቃ ማለት ስለማልችል ነው)
የቀብሩ ቀን ... (የመቃጠሉ ቀን ) ሬሳው በስነስርዓት በሳጥን ተደርጎ ጥቁር ሱፋችንን ግጥም አድርገን ቤተ ክርስቲያን ሄድን!! ... እንደማንኛውም ሬሳ የፀሎት ስነስርዓት ተደረገለት... ወላ ሀሌሉያ የሚለውን እንግሊዝኛ መዝሙር ዘመርኩላቸው ... (ሚስማር ሊያዘንቡብኝ ሆ! የመዝሙሩ ግጥምኮ ከእግዜር ጋር ፀብ አለው! )
የሆነው ሆኖ ሬሳው መቃጠያ ስፍራ ከመሄዱ በፊት ተሰናበቱት ሲባል ... የልጁ አያት አበባ ሊያስቀምጡ በሄዱበት ከእናቱጋ ተደጋግፈው ማልቀስ ጀመሩ.... ድምፄን እንዴት ልዋጠው? ህቅቅ ብዬ መነፋረቅ...
እናት የምመስለው እኔ ነኝ!! ሰው 'ምኑ ናት? ' እየተባባለ የሆነ ፊልም ይመስል ያፈጡብኛል:: ... ስንት ነገር አለ? ህእ ... ሀበሻኮ በአንድ ለቅሶ ለአንድ ሞት ብቻ አያለቅስም ... እነሱ ይሄን ያውቃሉ? አያውቁም!! ... የዛሬ 20 ዓመት የሞተ ወንድሜ... የዛሬ 14 ዓመት የሞተ አያቴ .... የዛሬ 6 ዓመት የሞተ ጏደኛዬ ... በእዛ እንባ ውስጥ ይሄ ሁሉ ሀዘን መኖሩን ያውቃሉ? አያውቁም....
ስንወጣ ሰው እናትና አባቱን ትከሻቸውን ጨበጥ እያደረገ ካለፈ በኃላ እኔጋ ሲደርሱ አበክረው ያፅናኑኛል::
የሚቃጠልበት ቦታ ሄደን ተቃጥሎ እስኪበቃና እስኪቀዘቅዝ ጊዜ ስለሚፈጅ ተመልሳችሁ ኑ ተብለን ሲለኮስ አይተን ሄድን!!
(በነገራችሁ ላይ ... ሬሳዬ እንዳይቀበር ይቃጠል ያለው ራሱ ሟች ነው:: እናትና አባቱ እንቢ ብለው ነበር ... እህቱ ቃሉ መከበር አለበት:: ብላ በዛ ላይ 18 ዓመት ስላለፈው መብቱ ነው ተብሎ ነው::)
ልናርፍ በሄድንበት እህትየው የባሰውን አመጣችው!!
"አመዴን ከወደቅኩበት ተራራ ላይ ወስዳችሁ በትኑት ብሏል:: እዛው ወስደን ነው የምንበትነው!"
አባትየው ምርር ብሎት
"በህይወት እያለም እረፍት ሰጥቶኝ አያውቅም! ይኸው ሞቶም ያንከራትተኛል! ምን አይነት የተረገመ ልጅ ነው?" (ልጁ ራሱ ግፉ)
እኔ አይኔን በልጥጬ ደንግጬ አያቸዋለሁ!! እነሱ ያፅናኑታል
"አይዞህ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ነው!! ቃሉን እናድርግለት"
አመዱን በሚያምር እቃ አስቀምጠው ሰጡን!! አመድ አጅቤ ትንሽ መንገድ ከሄድኩ በኃላ እኔ ወደቤቴ ተመለስኩ.... እነሱ አመድ ብተና ወደተራራው ተጏዙ....

👍13😁3🥴2❤1
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አወቅኩ!! (ርዕስ ነው)
"አታውቂም ነበር እንዴ?" ብለው የሚያዩኝ አስተያየት ራሱን ሊያጠፋ የነበረው ልጃቸው ሳይሆን እኔ የሆንኩ በሚያስመስል ሀዘኔታ አይን ነው።
"ምኑን? ምኑን ነው የማውቀው?"
"bipolar እንደሆነ አልነገረሽም?"
"ባይፖላር ምንድነው?"
እናቱና ወንድሙ 'ውይ ምስኪን አታውቅም!' የሚል አስተያየት ተያዩ። ያሉት ነገር ትርጉሙ ሳይገባኝ ግን ፍቅረኛዬ እንደ እርጅና የሚያስፈራ ነገር(ለእኔ ከእርጅና በላይ አስፈሪ ነገር የለኝም) እንደደበቀኝ ገባኝ።
ፍቅረኛዬ ነው! አብረን መኖር ከጀመርን ሶስት ወራችን! ማታ ከእንቅልፌ ስነቃ ከአጠገቤ አልነበረም። ለደቂቃዎች ጠበቅኩት። አልተመለሰም። አንዳንዴ እንቅልፍ ሲያስቸግረው እንደሚያደርገው ሳሎን ከሆነ ብዬ ሄድኩ። አልነበረም! የሳሎኑ ወደ ጓሮ የሚያስወጣ በር ክፍት ነው። እግሬ በደመነፍስ ተራመደ።
ቤታችን (ቤቱ) ውሃ ዳር ነው። የሳሎኑ ወደጓሮ የሚያስወጣ በር ወደ ውሃው ነው የሚመራው። ጨረቃዋ ፏ ብላ ምሽቱ የእኩለቀን ድምቀት ደምቋል። ዙሪያ ገባውን ቃኘሁ። በስሱ ከሚያፏጨው ንፋስ በቀር ምንም ተንቀሳቃሽ ነገር የለም። ዓይኔን ወደውሃው ላኩት። ውሃው ውስጥ የሚንቀሳቀስ ነገር ያየሁ መስሎኝ አተኮርኩ። ማመን አልፈለግኩም ወይም ባይሆን ተመኘሁ እንጂ ያየሁት የሰው ጭንቅላት ነበር። ከደቂቃዎች በኃላ ራሱ መሆኑን አረጋገጥኩ። ፍቅረኛዬ ነው!! ውሃው ውስጥ እየተራመደ ነገር ........ ውሃው አንገቱጋ ደርሷል::
እኔ ምን ነበር ያደረግኩት? ቆምኩ! ደነዘዝኩ! ተጣራሁ
"ፔር! ሀኒ..."
ውሃው ውስጥ ልገባም ጀመርኩ:: ከነየቤት ጫማዬ ..... የውሃው ቅዝቃዜ እርሱጋ ሳልደርስ የሚገድለኝ አይነት ነው:: እየገባሁ ደጋግሜ ተጣራሁ።
"ፔር ! ፔር! " እንደሀበሻነቴም 'እሪሪሪሪ ..... ኸረ ወየው ኡኡኡኡኡኡ.... የሰው ያለህ' ማለትም ያምረኛል።
የጎረቤታችንን ስም እየጮህኩ ተጣራሁ አንዴ የፍቅረኛዬን ..... አንዴ የጎረቤታቸንን ስም ... እጮሃለሁ! የምይዘው ግራ ገባኝ .... የእሳት አላርማቸው ራሱ እንደእኔ መጮሁን እንጃ ጎረቤት መብራት ሲበራ እሪታዬን ከበፊቱ አብልጬ አቀለጥኩት። መጥተው እሱን ሲያወጡት እኔ ግማሽ ውሃ ውስጥ እንደገባሁ ደንዝዤ ቆሚያለሁ። እግሬ መንቀሳቀስ አቃተው። ድንጋጤው ...... ከዜሮ በታች የሆነው የውሃው ቅዝቃዜ ....... ጭንቅላቴ ውስጥ አሁንም አሁንም የሚያቃጭለው ሀሳብ 'ራሱን ሊያጠፋ ነበር?' አማተብኩ። መጥተው እጄን ይዘውኝ ከውሃው ወጣሁ!!
ሀኪም ቤት ከደረስን በኋላ ተደውሎላቸው የመጡት ቤተሰቦቹ 'እንዴት አታውቂም?' ብለው ይገረሙብኛል።
የፍቅረኛዬ ህመም ምን እንደሆነ ሊያስረዱኝ ሳይንሳዊ ማብራርያ ይነግሩኛል። በግልብ ሀበሽኛ ቋንቋ ፍቅረኛዬ መለስተኛ እብድ ነው። ይኸው ነው!! የአዕምሮ አለመረጋጋት!
"በሆነ መንገድ ትሪትመንት ይኖረዋልኣ? የሚድን ነገር ነው?" አልኩት ዶክተሩን። እሱም እንደቤተሰቦቹ እንዴት አታውቂም በሚል ሀዘኔታ እያየኝ(መሰለኝ)
"በሚያሳዝን ሁኔታ አይደለም! ... እ እ ከስንት አንዴ በራሱ የመጥፋት ነገር አለው። ጨርሶ ባይድንም በመድሃኒትና በትሪትመንት ግን ኖርማል ቀን ይኖራቸዋል።" ብሎኝ ምን ማድረግ እንደሚገባኝ ይነግረኛል። ማድረግ አለብሽ ብሎ የሚነግረኝን ነገር ማድረግ መፈለጌን እንኳን ሳያውቅ
ልንጋባ ቀን ቀጥረናልኮ!
ምንድነው የማደርገው?
ክፉ ሴት ነኝ? ፍቅረኛዬ ራሱን ሊያጠፋ ከመሞከሩ ከሰዓታት በኋላ ያሳሰበኝ ቪዛዬ ነው! ካላገባሁት ወደሀገሬ ልመለስ ነው።
በለሊት ተነስቶ ራሱን ለማጥፋት የሚሞክር እብድ ከመሆኑ ውጪኮ ጥሩ ሰው ነበር።
አንዳንዴ ልክ እንደጦዘ ሰው እየተቅለበለበ አንዱን ቃል ከአንዱ እየደረበ ከማውራቱ ውጪኮ ደህና ሰው ነበር።
አንዳንዴ በጣም ከመደበሩ የተነሳ እቤት ውስጥ ሲንቀሳቀስ ሰው ሰራሽ ሮቦት እንጂ ስጋና ደም ያለው ሰው አይመስልም ነበር እንጂ ደህና ሰው ነበርኮ
ለሊት ለሊት ብዙ መተኛት ስለማይችል ግማሽ ለሊቶችን ብቻዬን ተኛለሁ እንጂ ደህና ሰው ነበርኮ!
አንድ ቀን የጦፈ ልፋት ላይ ሆነን ድንገት የሆነ ራዕይ እንደተገለጠለት ነገር አክሱሙን ነቅሎ እንደተንጋለልኩ ጥሎኝ እርቃኑን ከመኝታ ቤት ወጥቶ ሲሄድ ምን ሆኖ ነው ብዬ ብከተለው ምንም እንዳላቋረጠ መጠጥ ቀድቶ ሳሎን ቢቀመጥም ..... ደህና ሰው ነበርኮ
ይሄ ሁሉ የህመሙ ምልክት መሆኑን የማውቀው ዛሬ ነው። ሀበሻ ነኛ .... የአእምሮ መታወክ ... አለመረጋጋት ... እያለ ከማያለዝብ ማህበረሰብ ነው የመጣሁት!! ... እብደት እብደት ነው የማውቀው!! በደረጃና በምልክት ተከፋፍሎ አንድ ሀገር ስም እንዳለው አላውቅም!! ከአዕምሮ ጋር የተያያዘ ምንም ነገር ከተፈጠረ ... ፀሎት ... ፀበል ... ጠንቋይ ቤት ... ባስ ካለ እና ትንሽ ከዘመኑ ሀኪም ቤት .... ትንሽ ትንሽ ያለመረጋጋቱን 'እገሌ እኮ ወሰድ ያደርገዋል' እየተባለ በሳቅ የሚታለፍ ነው!
የተወሰኑ ቀናት ሆስፒታል ከቆየን በኋላ ወደ ቤት ተመለስን! ፈራሁት! በተራዬ የማልተኛው እኔ ሆንኩ! እሱን ጥበቃ ገባሁ!
እንደፈራሁት ገብቶታል።
"You are free to leave me" አለኝ የሆነ ቀን!
ምን ማለት ነው? ማንን ነው የሚያስኮንነው? ደሞስ ቪዛዬስ? ቀድሞስ የያዘ ይዞኝ እንጂ አካሄዱ መች ጠፋኝ? ሰበር ሰካ እያልኩ እፈተለከው!
ግን ከዛስ?
አልጨረስንም ............

👍13🥰2❤1
እኔ መቼም ገመናዬን አልደብቃችሁም አይደል? ለምን በሙዚቃ ተስፋ እንደቆረጥኩ ልንገራችሁ.......
The voice of norway ሁሉ ተመዝግቤ የነበርኩ ሰው ነኝ ... no joke
70 ዓመት ሆኖኝም ቢሆን ለ ሳይመን የመዝፈን እቅድ የነበረኝ ሰው ነኝ... which I kind of still dream 🤣
እናላችሁ በሰዓት 450kr ከፍዬ ቮካል መስራት ጀመርኩ ....
አስተማሪው መጀመሪያ ቀን በጣም በድምፄ ተደምሞ ... "You r unbelivable ... ur voice is out of this world " (for real)
ምናምን ሲለኝ በቃ ... the voice ነሽ ... AGT .... ጎልድ ሲዘንብብኝ ታየኝ ....
በነገታው በሙዚቃ መሳሪያ ታጅበን ስንሰራ ቆየንና ... ምን አለኝ? ለካ ሪትም የለ ምን የለ እያንበጫረቅኩ አስቸግሬዋለሁ
"You r completely deaf to music instrument"
በቃ ምንም ምንም የሌለው ደንቆሮ ነሽ 🤣🤣🤣🤣🤣🤣 ያለምኩት ጎልድ ጉድጏድ ገባ ስላችሁ...
አስተማሪው መረረው! መልክ ብቻ እንደሚባለው ... ድምፅ ብቻ! አለኝ በጣም እያዘነ ሃሃሃሃ
በቃ ተስፋ ቆረጥኩ ስላችሁ
ሀ ብለሽ አንደኛውን የሙዚቃ መሳሪያ ካልተማርሽ አትልፊ ብሎ ነው ወሽመጤን የቆረጠውኮ 🤣🤣🤣🤣🤣
ይኸው ፒያኖ መማር ጀምሬያለሁ:: እንደአያያዜ ከሆነ ከዘራ መያዣዬ ላይ ቅኝት በደንብ ይገባኛል!! በከዘራ ሄጄም ቢሆን ለሳይመን ዘፍናለሁ 🤣🤣🤣

👍9🥰2
'በመስጠት የደኸየ የለም' ይላል ሀበሻ ...
'10 ድሃ ዘመድ ያለው ሀብታም በመጨረሻ ራሱ ድሃ ይሆናል' ይላል ራሱ ሀበሻ መልሶ (ቅኔ የሆነ ህዝብ)
እስኪ ይሄን አጭርዬ ድራማ እዩት ... ደሞ እስኪ አትሰስቱ ሰብስክራይብ አድርጉ...
https://youtu.be/PbBsloOZmZ4

YouTube
ሁሉም እውነተኛ ባይሆንም ሁሉም ውሸታምም ግን አይደለም!
ውድ ተመልካቾቼ ይህ ሀሙስ ሀሙስ በተለያየ ሀሳብ ዙሪያ ለውይይት መነሻ የሚሆን አጭር ድራማ ይዘንላችሁ የምንቀርብበት «የሜሪ ሀሳቦች» የተሰኘ ፕሮግራማችን ነው። እንደምን ከረማችሁ!!
ሁሌም እንደምንለው ሁላችንም በተለያየ ሃሳብ ዙሪያ የተለያየ አይነት እይታ ይኖረናል። ቤተሰብ በመሆን የናንተንም ሀሳብ ብታጋሩን ደስታችን እጅግ የበዛ ነው።
በዚህ ቻናል ቢያንስ ለአንድ ሰው መነሳት ምክንያት ይሆናል ብለን…

👍4
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አወቅኩ (ክፍል ሁለት)
"ተሻለህ? እንዴት ነው የሚያደርግህ?"ይባላል?
"እንደ እብድ እንደእብድ ነው የሚያደርገኝ!" እንዲለኝ ነው?
እንደእውነቱ ከሆነ የሚያደርገውስ እኔ እነደማውቃቸው እብዶች አይደለም። የሚያደርገው ብቸኛ ነገር ጉልበቱን አቅፎ መተኛት ነው።
በግድ ይጎርሳል ..... ተፈጥሯዊ ግዴታ ስለሆነ እግሩን እየጎተተ ሽንት ቤት ይሄዳል። በቀን ውስጥ ከጥቂት ቃል ያለፈ ከአፉ አይወጣም።
ከሱ እንዲህ መሆን በላይ ልፋት ማቆማችን አሳሳቢ ነገር ሆኖ ባይሆንም እስከመቼ እንደምፆም ማወቁም አይከፋምኮ🤪 አብሯት ብዙ አልባሌ ነገር እንዳደረገ ሰው ሳይሆን ዛሬ እቤቱ እንደመጣች እንግዳ ነው የሚያየኝ። ቀኑ መርዘሙ ለሊቱ ደግሞ መባሱ ከአጠገቤ ዞር ሲል ካለማመኔ ሽንቱን ሁሉ ቆሜ ላሸናው ምንም አይቀረኝም።
የዛን ያህል ክፉ ሴት አታድርጉኝ! ፍቅረኛዬ ባይሆን ..... አብሬው ባልተኛ ......ወደፊቴን አብሬው ባላስብ ..... በአንድ ጣራ አብሬው ባልኖር ...... ይሄ ሁሉ ባይሆን እናንተ ስታነቡት እንዳዘናችሁለት እኔም አዝኛለሁ። ቤተሰቦቹ ; ጎረቤቱቹ ; ጓደኞቹ መጥተው 'እንዴት ነው?' ብለው ጠይቀውት እንደሚሄዱት፣ ስልክ እንደሚደውሉት እንደሱኮ እኔም የዛን ያህል ሀዘኔታና ፍቅር አለኝኮ
ግን ቀሪውን ዘመኔን ልሰጠው? በትዳር ስም ራሴንም ምንም የማያውቅ ልጄንም የየእለት ሰቀቀን ውስጥ ለመክተት የሚያስደፍር ቸርነትም ፍቅርም የለኝም። የዛን ደረጃ ፍቅር ማፍቀር የሚችለው ማፍቀሪያዬ ቆይቷል ከጥቅም ውጪ ከሆነ ......
ኸረ እንደእውነቱ ከሆነ በየትኛውም መጠን የሚሆን ፍቅር የለኝም!
አዎ ላገባው ነው። አዎ አብሬው እየኖርኩ ነው። አብረን ከመኖራችን በፊትም ለአንድ አመት የኔ ፍቅር የኔ ህይወት ተባብለናል። አላፈቅረውም ማለት እጠላዋለሁ ማለት አይደለም? 🤷🏽 መሃል ላይ የሆነ ስሜት አለ አይደል? ደስ ይለኛል! ከዛ ባለፈ ግን መሽለኩያዬ ነው። ማምለጫዬ ነው! ማለቴ ነበር!
እሱ ዛሬ ብድግ ብሎ ሰርጉን ሰርዤዋለሁ ቢል አንደኛ አይገርምም ያመዋላ!
ሁለተኛ ኖርዌጅያን ነው። እንኳን ሰርጉን ራሱንም በፈቃዱ ከመኖር ቢሰርዝ ከአንድ ቀን ቀብር ያለፈ ግርግር የለውም።
እኔስ?
እኔ እሱን ሳገባ ለእርሱ የሁለት ሰው ጥምረት እንደሆነው አይደለም ለኔ።
እሱ ቤት ስገባ የልጄን የወደፊት ህይወት ... የቤተሰቤን ድህነት ..... ያቺ የምወዳት ጎረቤቴን የበዓል ወጪ ሳይቀር በትከሻዬ አዝዬ ከነብዙ ጓዜ ነው የማገባው!
እሺ እኔስ በቃ ሰርጉን ሰርዝኩት አልኩኝ 'ልጄ ቀስ ብላ ትከፍላለች' ብሎ በብድር መሬት የገዛ አባቴን ምንድነው የምለው?
'ልጄን ሰው ካደረግክልኝ ሙክት አስገባለሁ!' ብላ ለመድሀንያለም የተሳለች እናቴን ምንድነው የምላት?
ለሚያውቃቸው እኩዮቹ ሁሉ 'እናቴ ውጪ ሄደች መጥታ ፈረንጆቹጋ ትወስደኛለች!' ብሎ የተቀደደ ልጄን ምንድነው የምለው?
'አይዞሽ እህታለም እኔ አለሁልሽ የግል ትምህርት ቤት አስገባሻለሁ' ያልኳትን ታናሽ እህቴን ምንድነው የምላት?
ለእነሱ መክፈል ያለብኝ መስዋዕትነት ከእብድ ጋር መኖር ከሆነ የምገባበትን ማጥ በወጉ ማወቅ ስላለብኝ ስለህመሙ ጎግል ማድረግ ጀመርኩ። ሳልዋሻችሁ መጀመሪያ የጎለጎልኩት ካገባሁት በኋላ እንደለመደው ራሱን ሊያጠፋ ቢሞክርና ቢሳካለት የኔ እጣ ፋንታ ምን እንደሚሆን ነው። ቋሚ የመኖርያ ፈቃድ ለማግኘት 3 ዓመት አብሬው የመኖር ግዴታ አለብኝ።
እንደክፉ ሴት አትዩኝ። እሺ በቃ ትንሽ ትንሽ ክፉ ነኝ። ከሞተ ወረቀቴን ይሰጡኛል። ለሆነ ሰከንድ ቢሞት ሁሉ ምንም እንደማይመስለኝ አሰብኩ። አምኛለሁ እሺ በደንብ ክፉ ነኝ!
በአለም ላይ 45 ሚሊየን ህዝብ የባይፖላር ህመም ተጠቂ መሆኑን ሳነብ በተመሳሳይ ምልክቶች የማውቃቸውን ሰዎች ሁላ እጠረጥር ጀመር። ራሴን ሁላ ስሜቶቹ ተሰምተውኝ ከሆነ ፈተሽኩ 'እብድ እኮ ለራሱ አይታወቀውም'ብዬ ተውኩት
በአለማችን ታዋቂ የሆኑ በዚህ ህመም ተጠቂ የነበሩና የሆኑ ሰዎችን ስም ዝርዝር ሳነብ የእብዶች ዓለም ነውሳ ዓለማችን?
በጣም ጥቂቶቹን ላስቆጥራችሁ ከመሪዎች የአሜሪካውን አብርሃም ሊንከን Abraham Lincoln የእንግሊዙን ዊንስተን ቸርችል (Winston Churchill)
ከሙዚቀኞች በፍቅር የምወዳት ኒና ስሞንን ጨምሮ Nina Simone, Selena Gomez,,Mariah Carey , Amy Winehouse, Demi Lovato ዘፋኞቹ ላይ ይበረታል ልበል? ብዙ ናቸው
በቁጠኝነቱ የሚታወቀው ታዋቂው ቦክሰኛ mike tayson
ታዋቂው የፊልም ፀሃፊ ዳይሬክተርና ተዋናይ Mel Gibson የዘመኔ ወንድ ልጆች እንደሱ ለመሆን ካራቴ የሚማሩለት አክተር ቫንዳም Claude Van Damme
እሺ ማነው ጤነኛ? የእብዶች ዓለምማ ነው!
ዶክተሩጋ ደውዬ ላገኘው እንደምፈልግ ነግሬው አገኘሁት። ይሄ ደግሞ ክፋቴን ሲያበዛው
"አንቺ ወደህይወቱ ከመጣሽ በኃላ ደስተኛ እንደሆነው ደስተኛ ሆኖ አያውቅም። ለ20 ዓመት ህክምናውን የምከታተለው እኔ ነኝ። አንቺን ካገኘ በኋላ ድኛለሁ ብሎ ለራሱ ስላመነ መድሃኒቱን አቋርጦ ነው" ይለኛል!!
ምን ውስጥ ነው ራሴን የዘፈቅኩት?
አሁንም አልጨረስንም ......

👍16❤1
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አወቅኩ (ክፍል ሶስት)
(ተፋፍረን እንጂኮ ሁላችንም አብደናል)
እንዴ የፈረንጅ አማች ሲከፋ ከሀበሻ ይብስ የለ እንዴ?
"በሱ ፋንታ ምናለ አንቺን ቢያቆራምድልኝ!" አንሾካሽካለሁ
"Pardon?" ትላለች ወደ አፌ ጆሮዋን አሹላ
"እዚሁ ነው እናቴ እዚሁ ነው!"
"Excuse me?"
ኡፈይ እቺ ደግሞ አላስተነፍስ ልትለኝ ነው እንዴ? እህቱኮ ናት! ወንድሟን አለሁልህ ልትለው ለተወሰነ ቀን መጥታ ልትደፋኝ በነገር። ቀድሞውኑም እንደማላፈቅረው ገብቷታል። 'እሰይ የታባሽ !' አይነት ሙድ ታሸሙራለች። የኔ መጨናነቅ ደስ ያላት ነው የምትመስለው።
'በላሁ ብለሽ ተቆረጠምሽ!' አይነት የነገር ዳርዳርታ
ጨዋታ ትጫወታለች::
"ስለሰርጉ ተነጋገራችሁ?"
"አልተነጋገርንም ምናልባት ቀኑን መቀየር ሊኖርብን ይችላል" አልኳት
"ሀሳብሽን የምትቀይሪ መስሎኝ ነበር።" እና ይህቺ የሀበሻ አማች አይደለችም?
"ለምን ብዬ?"
"አይ ያለበት ሁኔታ ከከበደሽ ብዬ ነው።" (ከባዱን ይስጥሽ እላታለሁ በልቤ)
የሰርጉን ቀን ላልተወሰነ ቀን አራዘምነው። እሱም መድሀኒቱን መቃም ቀጠለ። ከቀን ወደ ቀን ድባቴው ለቀቅ እያለለት መጣ።
የሆነኛው ቀን ከእህቱ ጋር እቤት ትቼው ወጣሁ እና አንዲት የምግባባት ታይላንዳዊት ጋር ሄድኩኝ። የማሳጅ ቤት አላት። የተፈጠረውን ነገር አንድ በአንድ ነገርኳት። እኔን ክፉ ናት አላችሁ? በሷ ሂሳብ እኔ ለመላዕክትነት እቀርባለሁ።
"ምን ትሰሪያለሽ ታዲያ? መድሀኒቱ ህመሙ የሚነሳበትን የጊዜ ጋፕ ያረዝምልሻል እንጂ ዘላለምሽን ወይም ሶስት ዓመት ከእብድ ጋር ነው የምትኖሪው ይልቅ በቀረሽ ጊዜ ዞር ዞር ብለሽ የሚያገባሽ ፈልጊ!" አለችኝ። ባል ከምስር ውስጥ የሚለቀም ጠጠር ነው ወይ ፈለግ ፈለግ ተደርጎ የሚገኘው? በዛ ላይ አብዛኛው ኖርዌጅያን አግባ ከሚባል ሲኦል ግባ ቢባል ኪሱ ውስጥ እጁን ከቶ እያፏጨ ይገባል።
"ከየት ነው የምፈልገው?"
"ቲንደር አካውንት ክፈቺ (የታወቀ የዴቲንግ ሳይት ነው) ወንዱ እዛ አፉን ከፍቶ አይደል እንዴ የሚውለው? ከፈለግሽ ደግሞ ማሳጅ ቤት እየመጣሽ እኔጋ ዋዪ ሀብታሞቹ ይመጣሉ::"
"ከዛስ? በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ አግባኝ ብለው ማን ይሰማኛል?"
"አንቺ (እንዴት ያለሽው እንከፍ ነሽ አይነት አስተያየት ከፀጉሬ እስከጥፍሬ እያየችኝ) ይሄን የመሰለ ሰውነት ይዘሽ .... ቆንጆ ነሽ ... በዛ ላይ ስማርት ነሽ ...ጨዋታውን ተጫወቺ (አባባሏ ስድድድ ያለ ስድነት አለው ) አጊንቶ ነው። ካላገባኸኝ ቪዛዬ ሊያልቅ ስለሆነ ልሄድብህ ነው ትዪዋለሽ አለቀ!"
"እሺ ባይለኝስ? ከሁለት ያጣ ሆንኩ ማለት አይደል?"
"አንቺ (አሁንም አጠራርዋ እንዴት ያለሽው ገንገበት ነሽ አይነት ነው) አንድ አምስቱን አጫውቺ ከአምስቱ አንዱ ይፈርምልሻል!"
"መድሀንያለምዬ አምስቱን እያጫወትኩ ተመልሼ ፍቅረኛዬ ቤት ነው የምገባው?"
"ምን? ከቤት ስትወጪ ምልክት ያደርግበታል? ወይስ ይለካዋል?"
"እኔ ለሱ አይደለም ለራሴ? ጭንቅላቴ አይቀበለውም!"
"እንግዲህ ምርጫው ያንቺ ነው!"
እቤት ስገባ እሱ ከእህቱ ጋር ሳሎን ቁጭ ብለዋል።
"እንኳን ወጣሽ ከኔ የባሰ ድብርት ውስጥ ገባሽ!" አለኝ። ዛሬ ደግሞ በደንብ ነቃ ያለ ይመስላል።
"እ ለለውጥ አሪፍ ነው!" አልኩት።
ዶክተሩ እንዳስረዳኝ ይሄን የድባቴ ጊዜ ካለፈ መድሀኒቱን በስርዓት ከወሰደ ደህና ይሆናል። ላልታወቀ ያህል ጊዜ..... ደግሞ ድጋሚ እስኪነሳበት ....
ህመሙ ከገነት ሲኦል አይነት የስሜት ለውጥ ነው። እጅግ ከፍተኛ የሆነ የፈንጠዝያ ስሜት ከብዙ ተያያዥ ስሜቶችና ቅዠቶች ጋር ለቀናት ወይም ለሳምንታት ይቆይና ከዛ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የድብርት ስሜት ራስን እስከማጥፋት የሚያስደርስ ራስን መጥላትና አለመፈለግ ስሜት ለቀናት ለሳምንታት ይከተላል
"ይቅርታ! " አለኝ እህቱ ስትሄድ ጠብቆ "ስላልነገርኩሽ ይቅርታ"
"እሺ ለምንድነው ግን ያልነገርከኝ?"
"አንቺ ዓይኖች ውስጥ ብቻ ነው ጤንነቴን የማየው። አንቺ ስታዪኝ ብቻ ነው ሙሉነት ... እንደማንኛውም ሰው ጤንነት ይሰማኝ የነበረው። ሌሎች በዙሪያዬ ያሉ ሰዎች ሲያዩኝ አይናቸው ውስጥ አቅም አልባነቴን አየዋለሁ። ተስፋ ቢስነቴን አየዋለሁ። አንድ ምንም እንዳልጎደለሽ አድርጎ የሚያይሽ ያውም የምታፈቅሪው ሰው በህይወትሽ ሲኖር ደስ ይላል። ለመኖር ፈለግኩ .... ዓይንሽ ተስፋ ሰጠኝ .... ለመኖር ጓጓሁ .... አለመናገር መረጥኩ!" አለኝ። አይኑ ሳያነባ ድምፁ እያለቀሰ።
ግራ ገባኝ .... የምር ግራ ገባኝ። ልጄ አልቅሶ ሲያበቃ እንቅልፍ ሲወስደው በእንቅልፍ ልቡ ህህቅ ብሎ ሲቃ ሲያሰማ አንጀቴ እንደሚላወሰው አንጀቴ ተላወሰብኝ። አጠገቡ ሄጄ አቀፍኩት ትከሻው ላይ አገጬን አድርጌ ግራ የገባው ሀሳብ ሳስብ ከቆየሁ በኃላ
"መቼ ነው ለመጀመሪያ ጊዜ ያወቅከው?" እንዴት ብዬ እንደምጠይቀው ግራ ገባኝ ብቻ ገብቶታል። አይኑን ቡዝዝ አድርጎ
"ከአባቴ ሞት በኋላ አባቴን እንደገደልኩት ሳስብ ለሳምንታት ዲፕረስድ ሆንኩ::" እያለኝ እህቱ መጣች
ምንድነው ያለው? አባቴን ገድዬው ነው ያለው? ገድዬው ሲጥ ገድዬው?
አሁንም በድጋሚ አልጨረስንም

👍28❤1
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አወቅኩ (ክፍል አራት)
"አባትህን እንዴት አድርገህ ነው የገደልከው?" እንዲህ ተብሎ አይጠየቅም! "ቅድም አባቴን ገደልኩት ነው ያልከኝ?" ይሄም ያው ነውኮ! "ቅድምኮ እንዴት መጀመሪያ እንዳወቅክ እየነገርከኝ ...." ኤጭ ምንድነው የምቀባጥረው?
ወደ መኝታ ከመሄዴ በፊት ሽንት ቤት ሆኜ ጥርሴን እየፋቅኩ ነው ፊልም ላይ እንደሚያወሩት ብቻዬን የማወራው። የራሱ ጉዳይ በቃ "አባትህ ምን ሆነው ነው የሞቱት?" እለዋለሁ። እሱ አፉን ሞልቶ አባቴን ገድዬ ሲል ያልተሳቀቀ እኔ ምን ያሳቅቀኛል? ውይ እሱ ወሰድ ያደርገዋል ለካ!
"ስለአባታችን እባክሽ እንዳታነሺበት!" ትለኛለች ይህቺ ደግሞ ከሽንት ቤቱ ስወጣ ጠብቃ
"ለምን?" ያልኳት እንደመጣልኝ ነው
"ለእሱ እጅግ በጣም መጥፎ ትዝታው ነው። ሰላም እደሪ!" ብላኝ እብስ ልትል .... አባቴን ገድዬ ካለኝ ሰውዬ ጋር ደግሞ እንዳታነሺበት ብላኝ ደህና እደሪ ? ቀልድ ነው?
"እሺ አንቺ ንገሪኛ? አባቴን እንደገደልኩት ሳስብ እኮ ነው ያለኝ!"
"ኦ ኖ ኖ እንደሱ አይደለም! (ዘገነናት) ፔር ማንም ላይ እጁን የሚያነሳ ሰው አይደለም! ኦህ ማይ ጋድ ጭራሽ አታውቂውም አይደል? (ቆይ እዚህ ቤት ታዲያ ምን ትሰሪያለሽ? በውል እንኳን የማታውቂውን ሰው ነው አገባዋለሁ ብለሽ ቀን የቀጠርሽው? የሚል ለዛ ነው ድምፅዋ ያለው።) በጥቂቱ አፈርኩ። የምርም አላውቀውም!
"ስለዛ ቀን ለማንም አውርቶ አያውቅም በትክክል በቦታው የተፈጠረውን ከግምት ውጪ ማናችንም አናውቅም። ፔር በ20 ዓመቱ የዩንቨርስቲ ተማሪ እያለ ነበር። አባታችን ከጓደኞቹጋ አሳ ሊያጠምዱ ሲወጡ አብሬ ካልሄድኩ ብሎ ወጣ ስምንት ሆነው ነው የሄዱት። መጥፎ ወጀብ ነበር። መርከባቸው ከዓለት ጋር ተጋጭታ ተሰባበረች። እኛ የምናውቀው የእርዳታ ሰጪ ሰራተኞቹ ሌሎቹን ማትረፍ ሲችሉ አባቴን ማትረፍ አለመቻላቸውን ነው። 'ላድነው እችል ነበር ገደልኩት' እያለ ይቃዥ ነበር። ከዛ ውጪ ለማንም ቃል ተንፍሶ አያውቅም።" አለችኝ
ዝም አልኩ። መተንፈሴን የሚያስጠረጥር ዝምታ ዝም አልኩ። የሆነ ነገር የተጫነብኝ ቁመቴ ሁሉ ያጠረ መሰለኝ።
"እንደማታፈቅሪው አውቃለሁ። እውነት ለማውራት እኔም አልወድሽም! ግን እባክሽ ወንድሜ በቂ ስቃይ በህይወቱ የተሰቃየ ሰው ነው። አትጨምሪበት! ደህና እደሪ!!" ብላኝ በቆምኩበት ጥላኝ ወደ ክፍሏ ሄደች። እግሬን እየጎተትኩ መኝታ ቤታችን ገባሁ። በጎኑ ተኝቶ ኩርምት ብሏል። ቶሎ አልጋው ላይ አልወጣሁም።
"እባክሽ እንደሱ አትዪኝ" አለኝ በዛ እንባ ሳይወጣው ለቅሶ ባለው ድምፁ
"እንዴት አድርጌ አየሁህ?" አልኩት ቅስስ እያልኩ አንሶላውን ገልጬ እየገባሁ
"ልክ ጊዜውን ጠብቆ እንደሚፈነዳ ፈንጂ .... ከጥፋት ውጪ ምንም ፍፃሜ እንደሌለው።"
"እንደሱ አልነበረም ያየሁህ!" አልኩት ልክ እንደሱ በጎኔ ፊቴን ወደሱ አዙሬ እየተጋደምኩ።
"እኔ እስከማውቀው ከራስህ አልፈህ ለሀገርህ የምትተርፍ ጂኒየስ ነህ! አንተ በሰራሃቸው ሶፍትዌሮች ምክንያት ብዙ ስርአጥ ስራ አጊንቷል። ብዙ ድርጅት አትርፏል። የብዙ ሰዎችን ህይወት አቅልለሃል አንተን ከጥፋት ውጪ ሌላ ፍፃሜ እንደሌለው ሰው ማየት እንዴት ይቻላል?"
(በሙያው IT ኢንጂነር ነው። የምሬን ነው ያልኩት ከIT ቴክኖሎጂጋ ተያይዞ ያለው እውቀትና ፈጠራ የምርም ለሀገር የተረፈ ነው።)
"ውሃው ቀዝቃዛ ነበር። ጨለማ ነበር። ሁላችንም የእርዳታ ሰራተኞቹ እስኪደርሱልን ነፍሳችንን ለማትረፍ እየታገልን ነበር። እንደምንም በህይወት ለመቆየት ጭንቅላቴን ከውሃው በላይ አድርጌ እየዋኘሁ ነበር። እሱም ነፍስ ይዞት ለመትረፍ ሲፍጨረጨር እግሬን ይዞኝ ለመትረፍ መታገል ጀመረ። እግሬን በጎተተኝ ቁጥር እኔም እየዘቀጥኩ ለመሞት መሽቀዳደም ሆነ። እግሬን አስለቅቄው ነፍሴን ለማዳን መዋኘት ጀመርኩ። በሰዓቱ ራሴን ከማዳን ውጪ ስላለው ነገር አላሰብኩም። በኋላ ላይ እግሬን ያስለቀቅኩት አባቴ መሆኑን አወቅኩ።"
ይሄን እያወራኝ ይበልጥ ኩምትር አለ። እንባው ትራሱ ላይ ተከታተለ። አቀፍኩት። ድምፅ ሳያሰማ ህቅ ሳይል ሰው ይሄ ሁሉ እንባ እንዴት ይወጣዋል? አብሬው አለቀስኩ።.... ለምን እንዳለቀስኩ እንኳን ሳይገባኝ ፍቅፍቅ ብዬ አቅፌው አለቀስኩ .....
አሁንም በድግምጋሚ አልጨረስንም

👍18❤3
ሴትነት እና ሙያችን
ማርች 8 አይደል?
በመሰረቱ እኔ አብሲት ማን ይቀቅል? እንቁላል ማን ይጥበስ ዓይነት ነገሮች በፆታ የተመደቡበት ቤተሰብ ውስጥ አላደግኩም:: እኛ ቤት የቤቱ ራስ ማሚ ናት!! (እርግጥ ከመጀመሪያውም እንዲህ አልነበረም ትላለች ማሚ ... እሱ የቤት ገመና ነው ይለፋችሁ)
ሆ ስንፈራትኮ በጅምላ ነበር .... ሁለቱም መንግስት ቤት ሰራተኞች ስለነበሩ እናም ስለበርዬ አውርቻችሁ የለ? ለሱ ተብሎ ሲደመር ማሚ ሴቶች ጉዳይ አልነበር የምትሰራው...🤣🤣🤣
በቃ በብዙ ምክንያት እቤት ውስጥ የቤቱን ስራ የሚሰሩ ልጆች ይኖራሉ... ማሚ የፃታ ስብጥሩን ላለማዛባት ... እቤት ሁላ ወንድም ሴትም ነው የሚቀጠረው (ጌታን የምሬን ነው!!)
ስወዳትኮ ..... ጅንን ያለች ሴትዮ ❤️❤️
ከኔ ቀድሞ ዶሮ መስራት ወንድሜ ነው የቻለው ... እንጀራ መጋገርም ... እንደእውነቱ እቤት ውስጥ አስቸጋሪም ... ቀበጥም ... አመፀኛም እኔ ነበርኩ:: ሌሎቹ የተባረኩ የጌታ ልጆች ናቸው ሃሃሃሃ
እናላችሁ .... አገባሁኛ !! ያውም በ18 ዓመቴ ህልመኛ አፍቃሪ ነበርኩ ... (ቤት አለው? መኪና አለው ያልኩ እንዳይመስላቸው ሃሃሃ ሳይክል ነው የነበረው ሃሃሃ ...) ፍቅር ቅልብልብ አድርጎኝ .... እሱን ካላገባሁ ከልጅነት መዝገብ ሰርዙኝ ብዬ.... አገባሁ!! ...
(እኔኮ ዘመኔን ሳስበው የአንድ ሰው ብቻ ህይወት የኖርኩ አይመስለኝም የምለው በምክንያት ነው::)
የሆነው ሆኖ አናቴ እስኪጨስ ባሌን እወደው ስለነበር ለእርሱ ምግብ ማብሰል ደስ ብሎኝ የምሰራው ነገር እንጂ 'ወጥ ቀቃይ ነኝ ወይ?' ብዬ የምመናቀርበት ርእስ ሆኖ አያውቅም!! ...
አንድ ቀን እንጀራ የሚጋግሩልኝ ሴትዮ ሳይመጡ ቀሩና እኔ እንጀራ ልጋግር እሳት አያያዝኩ ... ፀግዬን እርጉዝ ነኝ!! ... በእሳት እንጀራ ጋግሬ አላውቅም🤣 ስለው ግማሽ ሊጥ ሆኖ ይወጣል ... ስለው ምጣዱን እንቅ .... ግማሹ ሊጥ እንኩሮ ሆነ!! ቁጭ ብዬ ሊጡጋ ማልቀስ ... ሆርሞኑም አለኣ .... ባልዬ ከስራ ለምሳ ሲመጣ ... ኩሽና ቁጭ ብዬ እነፋረቃለሁ:: ሲያየኝ ሳቁ መጣ... ልብሱን ቀይሮ መጣና ለሁለት እንሞክረው ብሎኝ .... ሊጡ ላይ ለሁለት ቀለድንበት ... 🤣🤣🤣🤣 በየመሃሉ አልባሌ መነካካቶች ስንነካካም ስለነበር አንድም የረባ እንጀራ ሳይወጣ ሊጡ አለቀና ... ውጪ ወጥተን ምሳችንን በላን....
(አልባሌ ነገሩን ብቻ አትያዙብኝ .... 🤣🤣 ወደ ነጥቤ ልግባው?)
ከ6 ዓመት በኃላ .... ሴት አይደለሽ? በሚሉ ብዙ ተለጣፊ ነገሮች ሰበብ .... እንደሴት ብቻ ሳይሆን እንደሰው ራሴን አጥቼው .... ያቺ በ18 ዓመቷ የምትበር ባለክንፏ ሜሪ ጠፍታ .... ዝምምምም ያለችው ሜሪ ነበርኩ:: ልብ አድርጉ ከነዚህ ውስጥ አሁንም ምግብ ማን ይስራ አይስራ ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ነገር ሆኖ አያውቅም!! ጊቢ አድሬ ስመጣ ቁርስ ሰርቶ የሚቀበለኝ ባል ነው የነበረኝ .... እርግጥ ስመጣ አጭር ቀሚስ ከሆነ የለበስኩት በቦክስም ይቀልበኛል🤣🤣🤣
የሴት ልጅ መብትና እኩልነት ርእስ ሲነሳ .... ብዙ ጊዜ ወንዱ ገብቶ አብሲት ይቀቅል አይነት እሰጣ ገባ ውስጥ ቀድመን እንገኛለን..... እኔ በበኩሌ እንደሜሪ .... ከዛ በላይ የሚሰብረው እንደሰው ራሴ ላይ እንድወስን እድል የማትሰጡኝ ነገር ነው::
ቅድሚያ እንደሴት ብቻ ሳይሆን እንደሰው ሙሉ ትሁንበት .... መማር ቅብጠት አይሁንባት... የምታገባውን መምረጥ ቅብጠት አይሁንባት ... የምትፈልገውን ትምህርት መምረጥ ቅብጠት አይሆንባት ....
ማህበረሰብ እንድትሆን የሚፈልገውን ሳይሆን ራሷ መሆን የምትፈልገውን ትሁንበት!!
ቀድማ ብታገባ ... ዘለፋ ... ዘግይታ ብታገባም እንዲሁ ... ባታገባም አይቀርላትም
ባትወልድ ዘለፋ ... ወላ ፈጣሪ ለፍሬ ባያድላት ሁላ ... ከጋብቻ ውጪ ብትወልድ አበሳ ... የወለደችው ጤነኛ ባይሆን ዘለፋ ...
የአልጋ ልፋቱን ባትችል ቀዝቃዛ ናት ... ካስላበችው ብዙ የቀመሰች ዱርዬ ናት ...
አጭር ብትለብስ ዘለፋ ... ረዥም ብትለብስ ጎታታ ...
ሴትነት ጌጧ እንጂ መሸማቀቂያዋ አይሁን!! ሴትነት መኩሪያዋ እንጂ መዘለፊያዋ አይሁን!! ሴት ስለሆንሽ ተብሎ በውስጠ ታዋቂነት 'አትችዪም' የምትባልበት ሳይሆን .... እንደሰው የምትፈተንበት ህይወት ይኑራት ....
ወየው ደከምኩ.....
አግዙኝ እስኪ....
(በነገራችሁ ላይ ርእሱ ከፅሁፉ ጋር ምንም አይያያዝም 🤣🤣🤣🤣 )

👍18❤4
የሴቶች ቀን ከማክበራችን በፊት (ለሴቶች ብቻ! ወንዶች ይለፋችሁ የሴት ገመና ነገር ነው!)
የሴቶችን ቀን ከማክበራችን በፊት እኔን አክብሪኝ! አንቺኝ ላክብርሽ! ራሳችን እንከባበር!
የሴቶች ጓደኝነት ሲባል የምንታወቀው እኮ በመቀናናት፣ በመጠላለፍ ፣ እፍፍፍ ብለን ተዋደን እፍፍፍ አድርገን አቧራ አጭሰን በመጣላት ፣ በመተማማት ነው። ውሸት ነው?
ብዙ እሩቅ ሳትሄጂ በአንዲት ሴት ዙሪያ በተቀለደ ፐርሰናል ህይወቷን በሚነካ የጅል ቀልድ ዙሪያ የሚሰጡ ኮመንቶች አንብቢ ባለመውለዷ የምታለግጥ፣ ባለማግባቷ የምታለግጥ ፣ በእድሜዋ የምታፌዝባት ስራዋን የምታጣጥልባት ብዙም ብዙም አብዛኛው እጅግ የሚሰብር ኮመንት የሴቷ ነው።
ሌላኛው የዓለም ሀገር ተሰዳ አረብ ሀገር የተሰደደች እህቷ ላይ የምትመናቀረው ማናት?
እንግሊዝኛ ስለቻለችና ሁለት ቀሚስ ስለቀየረች ገጠር የምትኖር ቂቤ የምትቀባ : እበት የምትጠፈጥፍ እህቷ ላይ የምትበሻቀጥ ማናት?
አንዲት ሴት ተደፈረች ቢባል ቀድሞ ሲሰድባትና ሲያብጠለጥላት የሚገኘው ማነው? ከመደፈሯ ህመም ይልቅ ለመደፈሯ ምክንያት የሚሰበስብ ማነው?
አንዲት ሴት አሲድ ተደፋባት፣ ተደበደበች ሲባል ከሚታየው የእህቷ ጉዳት በላይ ምን አድርጋው ነው ብላ ያልታየ የሱን ህመም ለመታመም የምታጣጥር ማናት?
አንዲት ሴት በየትኛውም ሙያ ብቅ ስትል አናት አናቷን ቀጥቅጦ አቅመቢስነት እንዲሰማት የምታደርግ ማናት?
አንቺኮ እኮ እኔ ነሽ!! አንቺ ያላከበርሽኝን ወንድ ሳያከብረኝ ሲቀር እንዴት ትገረሚያለሽ?
ተጋግዘሽ ብትቆሚ ተበረቻለሽ! አትሰበሪም!
ስወድቅ ብታግዢኝ : ስትደክሚ ባበረታሽ እኔ ላንቺ አንቺ ለእኔ ብንቆም ብዙ ነን። ያኔ በሁሉም ቀን እንደምቃለን!!
በከፍታሽ ስደሰት ከፍታዬ ይመጣል! ስወድቅ እንዳልነሳ ከምትሰብሪኝ ልታነሺኝ እጅሽን ብትልኪልኝ ተያይዘን እናድጋለን!!
አንቺ ያላመመሽን ህመሜን እንዴት እሱ አልታመመም ብዬ እወቅሰዋለሁ? አንቺኮ እኔ ነሽ!

👍14
ልንጋባ ሁለት ሳምንት ሲቀረን እጮኛዬ ጤነኛ እንዳልሆነ አውቅኩ (ክፍል አምስት)
አንድ ህቅታ ሳያሰማ እቅፌ ውስጥ ሆኖ ትኩስ እንባው ክንዴን ያርሰኛል። ለምን እንዲህ ሆድ እንደባሰኝ አላውቅም። የሚያስለቅሰኝ የሱ ለቅሶ ይሁን የራሴ ውጥንቅጥ ሁላ አላውቅም። ግን መቼ እንዳለቀስኩ የማላስታውሰውን ለቅሶ ከሱ የባሰ ተንፈቀፈቅኩ።
ምን አለ ሀላፊነት ባይኖርብኝ? ምናለ ጠዋት ተነስቼ ጨርቄን ማቄን ሳልል መጥፋት ብችል? ምናለ ድሀ ባልሆን? ምንለ የሆንኩትን ሁላ ባልሆን? ምናለ ከነጭራሹኑ እኔን ባልሆን?
“የቱ ይብሳል? " አልኩት ሁለታችንም ከለቅሷችን ጋብ እንዳልን
"ከምኑና ከምኑ?"
"ከሜኒያው እና ከዲፕረሽኑ?" (የበሽታው ሁለቱ የስሜት ፅንፍ ኢፒሶዶች ናቸው)
"ሁለቱም ያው ናቸው። አንደኛው አይንሽን የሚያጠፋ ብርሃን ሌላኛው የሚያደናብር ድቅድቅ ጨለማ ናቸው። ሁለቱንም ጊዜ ራሴን አይደለሁም። የማታዢበት ጭንቅላትና ሰውነት መያዝ ምን ያህል ዋጋ ቢስነት ነው?" አለኝ ከእቅፌ ሸሽቶ በጀርባው እየተኛ ፊቱን ወደኔ መልሶ አይን አይኔን እያየ።
ለደቂቃዎች ዝም አልኩ። እንባውን ለመዋጥ ሲታገል የሚንቀጠቀጥ ከንፈሩን ልስመው ፈለግኩ ግን ደግሞ የባሰ የሚታዘንለት ፍጥረት እንደሆነ እንዲሰማው አልፈለግኩም።
"ግንኮ በብርሃንህ ወቅት ብዙ ነገር ትሰራለህ። እራሱን እንደማይቆጣጠር ሰው አይደለህም።" አልኩት ከልቤ
"አ..ዎ...ን (ዝቅ ባለ አቅመ ቢስ በሆነ ስሜት አይኑን ቡዝዝ አድርጎ) ችግሩ የቱጋና መቼ ከልክ በላይ እንደሚሆን አታውቂውም። የሆነኛው ቀንና ቦታ ላይ የልኩን መስመር አልፋለሁ።" አለኝ
በማንባት ያበጡ አይኖቹን ተራ በተራ ሳምኩለት። ከንፈሩን ልስመው ከንፈሬን ሳንቀሳቅስ የእንባው ጨው ጨው የሚል ጣዕም ምላሴ ላይ ደረሰ። እንባውን ነው የቀመስኩት .....ሀዘኑን ነው በምላሴ ያጣጣምኩት ..... የዘመናት ሰቀቀኑን ነው ከምራቄ አዋህጄ ምላሴ ላይ ያጣጣምኩት .... .....እናም የዋጥኩት .... እናም የተዋሃድኩት ....... ሆዴ እርብትብት አለብኝ።
ከንፈሩን በስሱ ስሜው ደረቱ ላይ ጋደም አልኩ። የቀመስኩት ሀዘን ..... የዋጥኩት ሰቀቀን ..... ያጣጣምኩት እንባ ....... ድጋሚ ያነፋርቀኝ ጀመር። በተራው እሱ ደግሞ ደረቱ ላይ በሁለቱም እጆቹ አቅፎኝ ለኔ ይሁን ለራሱ እንባውን አብሮኝ አፈሰሰው። ደክሞን እንቅልፍ በዛው ይዞን ሄደ።
እንዲህ እንደሚሆን ባውቅ ላገባው እወስን ነበር? እንዲህ እንደሚሆን ባውቅ ወደ ኖርዌይ እመጣ ነበር? እንዲህ እንደሚሆን ባውቅ የግብዣ ወረቀቱን ልላክልሽ ሲለኝ እሺ እለው ነበር? እንዲህ እንደሚሆን ባውቅ ኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ ሊያየኝ ሲመጣ ቤተሰቤን አስተዋውቀው ነበር? ልጄን አሳየው ነበር? እንዲህ እንደሚሆን ባውቅ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊያየኝ ሲመጣ ለጓደኞቼ አስተዋውቀዋለሁ? ኸረ ቀድሞውኑ እንዲህ እንደሚሆን ባውቅ ስልኬን እሰጠው ነበር?
ዱባይ ነው የተዋወቅነው። እሱ ከሆነ ሶፍትዌር ካምፓኒ ጋር የስራ ውል ኖሮት። እኔስ? እቁብ ጥዬ ተጣጥዬ በአንዲት ጓደኛዬ ምክር እና ምሪት ከዱባይ እቃ አምጥቶ ለመሸጥ ተከትያት ሄጄ!
ስንሸማምት ውለን የሆነኛው ቦታ ቡና ልንጠጣ ባረፍንበት። ቡናውን ከምትቀዳው ሴትዮ ተቀብዬ በቁሜ ስኳር ስጨምር
"ኦውውው .." የሚል ድምፅ ሰምቼ ዘወር አልኩ።
"ይሄ ሁሉ ስኳር ለአንድ ብርጭቆ ቡና ገርሞኝ ነው ይቅርታ" አለኝ። ፈገግ ብዬ ዝም አልኩት።
በሚቀጥለው ቀን አንደኛው ሞል ውስጥ ከጓደኛዬ ጋር ክልው ክልው ስል ድጋሚ ተገናኘኝ።
"Ohh hey Sugar lady" አለኝ
አለ አይደል ጓደኛህን አጊንተህ "አንተ ከንቱ አለህ በናትህ ?" ምናምን እንደምትለው አይነት ምን የሚሉት አጠራር ነው አሁን ይሄ
"ሄይ" አልኩት ቆም ብዬ ... በእጄ አንድ ሀገር እቃ ተሸክሚያለሁ። 'ላግዛችሁ?' ብሎ የተወሰነ እቃ ተቀበለን። ማታ እራት ሊጋብዘኝ ሲጠይቀኝ እንደሀበሻ ሴት መግደርደር አልነበረብኝም? ቢያንስ ላስብበት አይባልም?
አይባልም! የፈረንጅ ቆንጆ ነው .... በዛ ላይ ሰውነቱ.... በዛ ላይ ..... ምንም ምክንያት አያስፈልገውም። በቃ አብሬው እራት መብላቱን ፈልጌዋለሁ!!
እራት ስንበላ ስለብዙ ነገር አወራን። ስለስራው .... ስለሀገሩ .... ሀገሩ ስለሚያመርተው brown cheese ሳይቀር አወራልኝ። (የትኛውም ኖርወጅያን ይሄን ካልጠቀሰላችሁ የተወጋ ኖርዌጅያን ነው)።
ጨዋነቱ ደስ ሲል ..... በረራው የዛኑ እለት እኩለ ለሊት ነበር።
"እንዴት ላግኝሽ?" ሲለኝ ስልኬንም ... ሜሴንጀሬንም ... ዋትስአፔንም .... የሰይጣን ነገር አይታወቅም እሱም ባይሰራ የቤት ስልክ ... ድንገት ሰይጣን እጅግ ሲከፋና ይሄም ካልሰራ ፖስታ ሳጥን ቁጥሬም ሳይቀር ሰጠሁት።
ለወራት በርቀት ስናወራ ፎቶ ስንለዋወጥ ከቆየን በኋላ ሊያየኝ መጣ።
የአዲስ አበባ አስፓልቶች ላይ ተመናቀርኩ። ድህነት ላይ ዘበጥኩበት። ብቸኝነት ላይ ተቁላላሁበት ::
አስቡት ፈረንጅ ሆኖ ቆንጆ .... ቆንጆ ሆኖ ሀብታም ... ሀብታም ሆኖ ውጪ የሚወስድ ያውም ከነ ልጅሽ ልንከባከብሽ የሚል ..... ዋናው ነጥብ የአልጋው ልፋት ላይ ሌላ የማያስመኝ ለፊ ... በምንም የማይገኝ ስብጥርኮ ነው።
ህም .......
ስብጥሩ እብደት እንደሚቀላቀልበት ባውቅ ኖሮ ይሄን ሁሉ እርቀትስ እሄድ ነበር?
በነገራችሁ ላይ አሁንም አልጨረስንም

👍22❤2