Telegram Web Link
Audio
#ደጅ_ጠናሁ   

ደጅ ጠናሁ ቆይቼ ኪዳነ ምህረትን
ተፅናናሁኝ ረሳሁ ሀዘኔን
የአምላክ እናት እመቤታችንን
ሞገስ ሁኚኝ ቀሪው ዘመኔን

የመከራው ዘመን አለፈ እንደዋዛ
አንቺን ተጠግቼ የአለሟን ቤዛ
የልጅሽ ቸርነት የአንቺ ደግነት
ባርያሽን ሰውሪኝ ከአስጨናቂው ሞት
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ
#አዝ
ልቤ ባንቺ ፀና ከፍ ከፍም አለ
በጠላቶቼ ላይ አፌ ተናገረ
በማዳንሽ ስራ ባሪያሽ ደስ ብሎኛል
የኃያላኑን ቀስት ልጅሽ ሰብሮልኛል
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ የታበሰ ሰላም ለኪ
#አዝ
እጄ ባዶ ሲሆን ወዳጆቼም ሸሹኝ
በመርገም ምክራቸው ሊለያዩን ሲሹ
እርሱ የሰጠኝን እሱ ወሰደ አልኳቸው
እመቤቴ አለችኝ ብዬ አሳፈርኳቸው
እናቴ ስምሽን ሰጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ በአንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ
#አዝ
በአውደ ምሕረቱ ሆኜ ስጠራት
ዘንበል ብላ አየችን ኪዳነ ምህረት
ሀሳብሽን ምንም የለም የሚመስለው
እረፍት ያገኘሁት እናቴ ባንቺ ነው
እናቴ ስምሽን ስጠራ አለፈ ያሁሉ መከራ
እምባዬ በፊትሽ ፈሰሰ
እምዬ ባንቺ እየታበሰ ሰላም ለኪ

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን
ይዘምሩ ፤ ለተዋሕዶ እንጋደል
👇👇👇👇👇👇👇👇
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
እናት አለኝ
ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
እናት አለኝ

እናት አለኝ የምታብስ እንባ
አያታለው ስወጣ ስገባ
ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት

ሔዋን ሰጥታኝ ከበለሱ ፍሬ
እራቆቴን ብቆምም አፍሬ
ልብሴን ይዘሽ ወደ እኔ ቀርበሻል
ደጓ እናቴ ቤቴን አድምቀሻል

ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ለዘላለም ንጽህይት በመሆኗ
ከኔ ጋር ነው ህያው ቃልኪዳኗ
ደስተኛ ነኝ ሀዘኔን አልፌ
አጽናኝ ሆናኝ የመስቀል ስር ትርፌ

ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

ከጥፋቱ ውሀ ማረፊያዬ
መርከቤ ነሽ ከሞት ማምለጫዬ
የአምላክ እናት ምልጃሽ ሆኖኝ ክብሬ በህይወት አለው ጥልቁን ተሻግሬ

ኪዳነ ምህረት /3/ አንባ መጠጊያ ናት/

አዝ፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠፠

በእናትነት ህይወቴን ጎብኝታ
ልቤ አረፈ ተነቅሎ በሽታ
ሰንሰለቴ ከእጄ ተቆረጠ
መራራዬ በልጅሽ ጣፈጠ
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን
ይዘምሩ ፤ ለተዋሕዶ እንጋደል
👇👇👇👇👇👇👇👇
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
ወገን ዘመድ ማንም እረዳት በሌለበት ዘ...
ሰላማዊት ኪዳነ ምህረት
ወገን ዘመድ ማንም ረዳት በሌለበት ዘመን
ደርሰሽልኛል ድንግል ማርያም
ውለታሽን አልረሳም።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን
ይዘምሩ ፤ ለተዋሕዶ እንጋደል
👇👇👇👇👇👇👇👇
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
"በንጹሕ ደሙ አዳነን" - ዘማሪ ገብረ...
ቤተ ቅኔ - Bete Qene
በንጹሕ ደሙ ያዳነን።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን
ይዘምሩ ፤ ለተዋሕዶ እንጋደል
👇👇👇👇👇👇👇👇
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
ዘማሪ ገብረ አምላክ ኤፍታህ በለኝ መዝ...
ዝማሬ መላእክት
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን
ይዘምሩ ፤ ለተዋሕዶ እንጋደል
👇👇👇👇👇👇👇👇
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
"ሲከፋኝ መጽናኛዬ" - ዘማሪ ገብረአም...
ቤተ ቅኔ - Bete Qene
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን
ይዘምሩ ፤ ለተዋሕዶ እንጋደል
👇👇👇👇👇👇👇👇
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
✞ኪዳነምህረት እመቤት✞
♡የመዝሙር ግጥሞች♡
✞ኪዳነምህረት እመቤት✞

ኪዳነ ምህረት እመቤት እመቤት(፪)
ነይልን ነይልን ካለንበት (፪)

ከሰማያት በላይ /ካለው ከማደሪያሽ/(፪)
ዝማሬ ከሞላው ከዘላለም ቤትሽ
የምድር ፍጥረታት /ማርያም ማርያም ሲሉሽ/(፪)
የቃል እናት እመቤቴ /ነይ በሰረገላሽ/(፪)
አዝ= = = = =
ከጸጥታ ወደብ /ከፍቅር አውድማ/(፪)
ከሰላሙ መንደር ከእውነት ከተማ
ሰዐሊ ለነ ቅድስት /ውዳሴሽ ሲሰማ/(፪)
ከሚካኤል ከገብርኤል ጋር /ነይልን ከራማ/(፪)
አዝ= = = = =
ዘርፋፋው ቀሚስሽ /ይውረድ ከሰማያት/(፪)
እንባችን ይታበስ ባንቺ አማላጅነት
የጽዮን ዝማሬ /ተሞላች ነፍሳቸን/(፪)
ንዒ ንዒ ንዒ እንበል /እንደ አባቶቻችን/(፪)
አዝ= = = = =
ፍጥረታት ሊድኑ /በአማላጅነትሽ/(፪)
የዘላለም ኪዳን አማኑኤል ሰጠሽ
ትውልድ ይህን አምኖ /ብፅይት ይልሻል/(፪)
እናቴ መመኪያዬ /ምርኩዜ ሆነሻል/(፪)
አዝ= = = = =
የልብን ሲያዋዩሽ /ሰምተሽ ዝም አትይም/(፪)
ችግረኛን አይቶ ልብሽ አይጨክንም
ከአይን ጥቅሻ /ፈጥነሽ ትደርሽለታለሽ/(፪)
ከሐዘን ከመከራ /ታሳርፊዋለሽ/(፪)

መዝሙር
ለምለም ከበደ

"ከመረጥሁት ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ"
                  መዝ፹፱፥፫
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞
ቻናላችንን በመቀላቀል አብረውን
ይዘምሩ ፤ ለተዋሕዶ እንጋደል
👇👇👇👇👇👇👇👇
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
@yemezmurdebiter
Forwarded from YHWEH LESS THAN 1K
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💯አዲስ ዝማሬ " ከእግዚአብሔር በላይ ማንም " ሊቀ መዘመራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
Forwarded from YHWEH LESS THAN 1K
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💯አዲስ ዝማሬ " የኪዳን ሁሉ ራስ" ዘማሪ ፍቅሩ ንጉሴ
Forwarded from YHWEH LESS THAN 1K
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💯አዲስ ዝማሬ " ማርያም ኀሪት" መዝገበ ምህረት ሰንበት ትምህርት ቤት
Forwarded from YHWEH LESS THAN 1K
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💯አዲስ ዝማሬ " ፊደል ናት " ዘማሪ አባ ብርሀን ኢየሱስ ሽመልስ እና ዘማሪ ዲያቆን ጥበቡ ከበረ
Forwarded from YHWEH LESS THAN 1K
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💯አዲስ ዝማሬ " መንክር ግርማ " ዘማሪ ቀሲስ ብርሀን እሸቱ
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
# መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል

❖  ከ7ቱ ሊቀነ መላእክት አንዱ ነው።

❖ ገብርኤል ማለት የስሙ ትርጉም የእግዚአብሔር ልጅ የሚመስል የእግዚአብሔር ሰው ማለት ሲሆን
ት.ዳን 3+25ሕዝ 9፥2 በተጨማሪም መጋቤ ሐዲስ( የሐዲስ ኪዳን አስተማሪ) እግዚእ ወገብረ (እግዚአብሔር አደረገ ) ማለት ነው።

❖ ብስራታዊ (አብሳሪው) መልአክ ነው። እመቤታችንንና ዘመዷ ኤልሳቤትና አብስሮአልና።

❖ ቅዱስ ገብርኤል አርባብ የተበለው ነገደ መላእክት አለቃ ነው።

❖ በመጀመሪያው የመላእክት ጦርነት ጊዜ አምላካችንን እስክናውቅ ባለንበት ፀንተን እንቁም በማለት መላእክት ያፀናቸው ቅዱስ ገብርኤል ነው።
❖ ተራዳዩ መልአክ ነው።

ዳን ፫፥፲፱-፳፯፣ዳን ፰፥፲፭ ዳን፱፥፳፩-፳፯
❖ ቅዱስ ገብርኤል ከ፯ቱ ሊቃነ መላእክት አንዱ ነው።

❖ በጎ በጎውን የምንሰማበት መልካም መልካሙን የምናደርግበት መልካም ቀን ይሁንልን።

🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

#መልካም እለተ ይሁንልን

ባለ ማዕተቦችን ወደዚህ
ግሩፕ ይጋብዙ

ለመቀላቀል
https://www.tg-me.com/dmse_tewado
ኦ ፍጡነ ረድኤት
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
#ኦ_ፍጡነ_ረድኤት

ኦ ፍጡነ ረድኤት ፍጡነ ረድኤት
የእግዚአብሔር አገልጋይ ቅዱስ ሰማዕት

ሰላም ለአንተ ይሁን - - - ፍጡነ ረድኤት
የልዳው ፀሐይ - - - ፍጡነ ረድኤት
በጨካኝ ንጉሥ ፊት ቆምክ አደባባይ
ታማኝ አገልጋይ ነህ - - - ፍጡነ ረድኤት
ስቃይ ያልበገረህ - - - ፍጡነ ረድኤት
አክሊልን አገኘህ መከራን ታግሠህ
#አዝ
የፈጣሪውን ስም - - - ፍጡነ ረድኤት
ስለመሰከረ - - - ፍጡነ ረድኤት
ጊዮርጊስ ሰማዕት በሰይፍ ተመተረ
የስቃይ መሣሪያ - - - ፍጡነ ረድኤት
ያላዘናጋህ - - - ፍጡነ ረድኤት
መንፈሳዊ አርበኛ ጊዮርጊስ አንተ ነህ
#አዝ
ለጌታ ተጋዳይ - - - ፍጡነ ረድኤት
ታማኝ ወታደር - - - ፍጡነ ረድኤት
ቢነገር አያልቅም የተሰጠህ ክብር
ስቃይ ቢያደርሱብህ - - - ፍጡነ ረድኤት
በመታገስህ - - - ፍጡነ ረድኤት
ሲወሳ ይኖራል ዘለዓለም ስምህ
#አዝ
ለሰማው ይደንቃል - - - ፍጡነ ረድኤት
የአንተ ሰማዕትነት - - - ፍጡነ ረድኤት
ምሳሌ ይሆናል ለሁሉ ፍጥረት
ገድልህ ይናገራል - - - ፍጡነ ረድኤት
ክብር እንደተሰጠህ - - - ፍጡነ ረድኤት
ጊዜ የማይሽረው ምግባር ሃይማኖት ነው


              💚  💛  ❤️
   
https://www.tg-me.com/natanimube
https://www.tg-me.com/maetebe_kbrenew
https://www.tg-me.com/dmse_tewad
https://www.tg-me.com/zmaredawt_zeortodocs
https://www.tg-me.com/zmaredawt_zeortodocs
https://www.tg-me.com/orthodoxswi_eywet
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️
"#ጾምን ውደደው " #ማር ይስሐቅ
‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️‼️

#ጾም ማለት መተው ፣ መከልከል፣ መጠበቅ ፣ በታወቀ ጊዜ ከምግብ መከልከል ማለት ነው።

ሌላው በፍትሐ ነገስት አንቀጽ 15 ላይ እንዲህ ይላል
" ጾምስ በሕግ ውስጥ በታወቀው ጊዜ የሰው ከምግብ መከልከል ነው ፤ ሰው በደሉን ለማስተስረይ ዋጋውን ለማብዛት የፈቲሁን ኃይል ( በምኞትና ባምሮት መያዝ) ለማድከም የሚጠቀምበት ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ ትታዘዝ ዘንድ የምታደርግ ናት"።


👉 ስለዚህ ሰው በደሉን ለማስተስረይ ዋጋውን ክብሩን ለማብዛት የፈቲሁን ( በምኞትና ባምሮት መያዝ) ኀይል ለማድከም እና ፈቃደ ሥጋን ለፈቃደ ነፍስ ለማስገዛት በታወቀ ጊዜ ውስጥ ከምግብ መከልከል ነው::

👉 ጾም ከመንፈሳዊ ተጋድሎዎች አንዱ ነው ፤ ጾም ለሥጋ መንፈሳዊ ልጓም ነው ማለትም ጸዋሚ ሰው ፈቃደ ሥጋውን እየገታ ከእግዚአብሔር ጋር ለመኖር የሚበቃበት ለወዲያኛው ዓለም ረብሕ ያለው ስንቅ የሚይዝበት ነው ፤ (።)

👉 ጾም የነፍስን ጠላት ለማድከም የምታግዝ መሆኗን ቅዱስ ዮሐንስ ሐፂር ሲናገር "የጠላቱን ከተማ ለመቆጣጠር የዘመተ ንጉሥ አስቀድሞ የውኃውን መንገድ የእህሉንም መግቢያ ሁሉ ይዘጋል ፤ ያን ጊዜ ጠላቶቹ ይራባሉ ፣ ይጠማሉ በመጨረሻም እጃቸውን ይሰጣሉ ይሰጣሉ ምርኮኛም ይሆናሉ ፤ የነፍስን ጾር ለማሸነፍም በተመሳሳይ መንገድ መጠቀም ተገቢ ነው ፤ የሥጋን ፈቃድ የሚያበዛው ድሎት ምቾት ነው ስለዚህ የነፍስን ጾር ለማሸነፍ ትክክለኛው መንገድ ጾም ነው፤ አንድ ሰው በጾም ከጸና  የነፍሱ ጠላቶች ይደክማሉ። "


👉 ማር ይስሐቅም ጾም ገንዘብ ያደረጓትን መንፈሳዊ ሥራ የምታሠራቸው መሆኗን ሲገልጥ
" ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ ፣ ( ፤ ) ኃይለ ፍትወትን የምታደክም ፣ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ ፣ ከእግዚአብሔር ጸጋን የምታሰጥ ፣ የወንጌልን  ሥራ መጀመሪያ  ፣ የጽሙዳን ክብራቸው፣ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው ፣ የንጽሕና መገለጫ ፣ የጸሎት ምክንያት እናት ፣ የዕንባ መገኛ መፍለቂያዋ ፣ አርምሞን የምታስተምር ፤  ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ ና ሰውነትን በእግዚአብሔር ፊት በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት።"
በዚህም ጾም የበጎ ነገር ሁሉ መገኛ መከማቻ ናት ማለት ነው።

👉 ሰው የሚጾመው ምግብ ባለ መብላቱ እግዚአብሔር የሚደሰት ስለሆነ አይደለም ፤ ዲያቢሎስ በልቶ አያውቅም ፤ ስለዚህ ሰው የሚጾመው ፈቃዳተ ነፍሱን ለመፈጸም ፤ከሞት ያዳነውን  አምላኩን በተገቢው መልኩ ለማገልገል  ፤ንጽሕናን ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ ይጾማል።
ጾም ከሰይጣን ሥራዎች ሁሉ ርቆ ስለ ራስና ስለ ሕዝብ ስርየተ  አበሳ ፤ ሰላምንና በረከትን ለመለመን ፊትን ወደ እግዚአብሔር ማቅናት ነው።


👉 ጾም ከእኅቶቿ ከጸሎት እና ከምጽዋት ጋር የተጋመደችና በአግባቡ የተፈጸመች እንደ ሆነ ወደ ጽድቅ መንገድ ትመራለች፤  ጾም የምግባራት ሁሉ ንግሥት ነች። ይህን ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ሲናገር "የመልካም ሕይወት ምግባር ሁሉ እናት የማስተዋልና የሌሎች ምግባራት ሁሉ ንግሥት የምትሆን ጾም ናት"
ይህች የምግባራት ሁሉ በር የሆነችው ጾምን ልንቀበላት የሚገባው የልቡናችንን በር ከፍተን ራሳችንን ለንስሓ አዘጋጅተን በቀናው መንገድ ለመጓዝ ቆርጠን መሆን አለበት።


👉 የጾም ዓላም ዓላማ ለተወሰኑ ጊዜያት ከምግብ መከልከል አይደለም ፤ በመንፈሳዊ ሕይወታችን  አንድ ወይም ሁለት ደረጃዎችን ለመውጣት የተዘጋጀልን ነው ።ጾም በሕይወታችን ለውጥ የሚያመጣ የበረከት በር ነው። ጾም የማንጸልይ ከነበረ እንድንጸልይ ፤ የማንመጸዉት ከነበረ እንድንመጸውት ፤ የማናስቀድስ ) ከነበረ እንድናስቀድስ ፤ የማንቆርብ  ከነበር  እንድንቆርብ የሚያበረታን የሕይወት በር ነው።
በተለይ በጾም ወቅት ርቀነው የነበረውን መቅደስ በይበልጥ የምንቀርብበት ነው ። አንድ ኦርቶዶክሳዊ አምልኮትን መፈጸም ( ማስቀደስ) ( ማስቀደስ አምልኮትን መፈጸም ተብሎ መተርጎም ይችላል? )ግዴታው ( ምን ለማለት ነው ? ) ነው ፤  ስለዚህ በዚህ ጾም ብንችል የዘውትር ( የዘወትር ) ቀናትን  እና የሰንበትን ቅዳሴን ለመሳተፍ ( ዘወትር ማለት ከሰኞ እስከ እሑድ ያሉትን ቀናቶች ስለሚያካትት እና ብሎ መጨመሩ አስፈላጊ አይደለም። ) መሞከር ካልቻልን ግን  በሰንበተ ክርስቲያን (እሑድ) ቅዳሴን መሳተፍ ይገባናል። 

👉 ሌላው በጾም መቃረብያ ጊዜ የምናደርገውን የቅበላ ሥርዓታችንን መመልከት ይኖርብናል ። ቅበላ በክርስትና ውስጥ ያገኘነውን ምግብ መመገብ ፤ ያገኘነውን መጠጥ መጠጣት አይደለም ፤ ቅበላ ራስን ለጾም ማዘጋጀት ሲሆን ይህም በቅዳሴ ፣ በተመስጦ ፣ በምስጋና እና ከንስሐ አባት ጋር ተነጋግሮ መንፈሳዊ ሥራዎች በመሥራት ነው። የቀደሙ አባቶች ጾምን በመጾም ይቀበሉ ነበር ። እኛስ?
ስለዚህ ጾምን በመንፈሳዊነት ተቀብለን በመንፈሳዊነት ጾመን መዳረሻችን ንስሐ ገብተን ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን መቀበል መሆን አለበት።

👉 ጾም አያደክምም ንቁ ያደርጋል እንጂ። በጾም የሚደክም ፍትወተ ሥጋ ነው። በጾም ወቅት የመግደፊያ ሰዓቱ ሳይደርስ የሚርበን ከሆነ ቆም ብለን ራሳችንን መመርምር ይገባናል። ነፍሳችን ካልተራበች የሆድ ባዶ መሆን ሊያስጨንቀን አይችልም።

ክቡር ዳዊት ግን ሁልጊዜም በአምላኩ ደስ ይለው ነበር። ጾም ስለ  ኀጢአታችን እንድናዝን የሚረዳን መሆኑንም ከእርሱ ሕይወት እንማራለን። “እንዲህ በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፣ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ። ነፍሴ በቅቤና በስብ እንደሚጠግቡ ትጠግባለች ፤  ከንፈሮቼም ስምህን በደስታ ያመሰግናሉ፡፡” መዝ ፷፪፥፬ - ፭። “እህል መብላት ተረስቶኛልና"መዝ ፻፩፥፬። ነፍስ በእግዚአብሔር በአምላኳ በጠገበችና በረካች መጠን የሥጋ ፈቃዳትን ለማስተናገድ ጊዜ  አይኖረውም፤ ከይፈቃዳቱ በላይ ይሆናልና። ሥጋም ከነፍስ ጋራ በመንፈሳዊ ምግባር ይተባበራል፤ መሻቶቹንም ሁሉ ይተዋቸዋል። ለዚህም ነው  “የጠገበች ነፍስ የማር ወለላ ትረግጣለች፤ የተራበች ነፍስ ግን የመረረ ነገር ሁሉ ይጣፍጣታል፡፡'' ያለው። መጽሐፈ ተግሣጽ ፫ ፥ ፯። ነፍስ ስትጠግብ ሥጋም ይጠግባል፣ ይህም የሚነግረን  መጾም  (ከምግብ መከልከል) ነፍስንና ሥጋን በአንድነት። መንፈሳዊ ምግብን መመገብ እንደሆነ ነው። ግዘፍ ያለው ሥጋ መንፈሳዊ ምግብ መመገቡ አስደናቂ ነው። ሥጋውን የማያጾም ለነፍሱ መለኮታዊውን ምግብ (ቃለ እግዚአብሔርን...) የማይሰጥ ሰው ድሀ ነው። ቅዱስ ያሬድ "ቀድሱ ጾመ፣ ጾምን ቀድሱ" እያለ በጾመ ድጓው ማዜሙ ለዚህ
👉የጾም ጊዜ የጸጸትና የልብ ንጽሕና ጊዜ ነው:: “ወደ እኔ ተመለሱ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እኔም ወደ እናንተ እመለሳለሁ”  ( ትንቢተ ዘካርያስ ፩ ፥ ፫ ) እንዲል ጾም እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ሥራን የሚሠሩበት ፤ በኀጢአት የጎሰቆለች ነፍስንም በንስሓ አጥቦ ቀድሶ በቅዱስ ሥጋውና በክቡር ደሙ የሚያነጹበት ጊዜ ነው፡፡
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
ውበቱን አድንቀን የማንጨርሰውን ዓለማት በፈጠረ አምላክ ፊት እንኳ ፥ ቅዱሳን ሲናገሩ የሰማነው “በታላቅ ድምፅም እየጮኹ፦ ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም?” ሲሉ እንጂ ፥ እፁብ ድንቅ ስለሆነው ውብ ዓለማት ከሚፈሰው ደም በፊት የአድናቆት መዝሙር ሲዘምሩ አይደለም።(ዮሐ ራዕ 6፥10)።

በደም በጨቀየ ሀገር ውስጥ ፥ ንጹሐን እንደ በግ ከሚታረዱበት የተሰበሰቡ አባቶች ስለአንድ ሙዚየም በሀገር መሪ ፊት እንዲህ መናገር ምንኛ ያሳፍራል! ለመንጋው ጠባቂ የተባሉት እረኞች ፥ የልጆቻቸው ስቃይ ሳይሆን በከተማ መኃል ስላዩት ውበት ተናግሮ ዝም ማለት እንደምን አስቻላቸው?! ለመሪውስ መስማት የሚወደውን የሚነግሩት ወይስ እውነትን የሚያጋፍጡት እንደ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የበለጠ ወዳጆቹ ናቸው?

©ሙሉዓለም ጌታቸው
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
📓#አንድጥያቄ
✟ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ለአብርሃም ድንኳን ለኖህ መርከብ ለያዕቆብ መሰላል ለአዳም ምኑ ናት? ✟
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋሕዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
✥የዓብይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት✥

            ✥ቅድስት✥

በመባል የታወቃል ።

በዚህ ቀን እግዚያአብሔር አምላክ ቅዱስ ነውና እኛም ቅዱስ እንድንሆን ይፈልጋል ሁሉም የተቀደሰ ህይወት እንዲኖረው ይሻል። እኛም እርሱን መስለን በሮሜ 8÷28 የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቅድሞ ወሰነ ይላልና። እግዚያአብሔር አምላክ በቅድስና እንዲመራን የርሱ መልካም ፍቃድ ይህውንልን።

ሌላው ግን በዚህ ጊዜ ቅድስት ተብሎ በሚታወቀው ሳምንት ውስጥ የምናስበው ምንድነው? ስንል ሰንበትን ነው። እግዚያአብሔር አምላክ ሰንበትን እንደቀደሳት ሰንበትን ቀድሶ ለኛ ቅድስት አድርጎ እንደሰጠን የሚያሳይ ነው።

ሰንበት ስናከብር ሁለት ሰንበት እናከብራለን።
በኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን።
1ኛ ቀዳሚ ሰንበት
2ኛ ሰንበተ ክርስቲያን
የክርስቲያን ሰንበት ቀዳሚ ሰንበት የተባለቺው #ቅዳሜ ነው። ለምሳሌ ውዳሴ ማርያም በንደግምበት ሰዓት ውዳሴሃ ለእግዝተነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ። ይላል።

የቀደመች ሰንበት የአይውድ ሰንበት ወይም በብሉይ ዘመን የምትከበር ሰንበት ሁሉም ሰው ሊያከብራት የምትገባ ሰንበት። ዘፍጥረት 2÷3 እግዚያአብሔር አምላክ ሁሉን በስድስት ቀን ከፈጠረ በዋላ በሰባተኛው ቀን አረፈ የሰባተኛው ቀንም ቀደሰው።
አከበረው ሰንበት አለው። ዘጸአት 20 ላይ ስንመለከት ከአስርቱ ትዛዛት አንዱ ሰንበቴን አክብር ነው። ወይም ሰንበትን አክብር ነው።

እዚህ ሰንበት ቅዳሜ ላይ ጌታ ከፈጠረው ፍጥረት ሁሉ አረፈ ። ለምን አረፈ?
ደክሞት በፍፁም አይስማማውም።
ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባው።
ከምንሰራው ስራ አርፈን እግዚያአብሔርን እናመሰግነው ዘንድ ነው።
ስለዚህ ቅዳሜ የስጋ እረፍት ነው።

2ኛ ሰንበት እውድ ነው።
እውድን ሰንበት እንደውም የቀኖች ሁሉ ንግስት ነው የሚላት አትናቲዮስ ሲጠራት ። የእለታት ሁሉ ንግስት አባይ ታላቅ እለት ይላታል።

ለምን ?
በዚህ ቀን ደሞ ነብሳችን አርፋለች።
እንዴት ? አለምን በስድስተኛው  ቀን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን ያረፈው የሁሉ ፈጣሪ እግዚያአብሔር አለምን ለማዳን በጀመሪያውስንመለከት ትምህርት ዘወረደ እንደተመለከትነው ወርዶ ወደዚህ መቶ ነብሳችን በህለተ ሰንበት እውድ አሳረፋት። ማቴ 28÷1 ዮሐ 20÷1  በመቃብሩ ስፍራ በህለተ ሰንበት ወይም ደግሞ የሰንበቱ መጨረሻ በመጀመሪያው የሰንበት ቀንእነሆ ወደ መቃብሩ ስፍራ ኤዶ መቃብሩ ግን ባዶ ነበር። ነብሳችን ያረፈችበት ሰንበት እለተ ሰንበት እውድ ነበር ። እውድ ደግሞ ሰንበት ተብሎ ይጠራል።

1 ቀዳሚት ሰንበት ።
2 እውድ ሰንበት ።
ይኤንን እነሆ ሰንበታቴን አክብሩ ብሎ እንደተናገረ እነዚህን እናከብራለን ።

ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ በፍጥሞ ደሴት ሳለው ይላል ። ራይ 1÷10 ላይ በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርኹ አለ። የጌታ ቀን የሚላት እውድነው። ሐዋሪያት የጌታ ቀን ብለው ይጠርዋታል ።
ቅዳሜ ሥጋችን ያረፈበት የሚያርፍበት
እውድ ደግሞ ነፍሳችን የሚያርፍበት ልዩ ቀን ነው።  ቅድስት ሲል እግዚያአብሔር ቅዳሜን እግዚያአብሔር እውድን ለውላችን ቅድሶ ሰጠን ።

በዚህ ቀን አርፈን የታመመን እንድንጠይቅ ድውያን እድንጠይቅ እግዚያአብሔር ይፈልጋል።

ለስጋ ብቻ መሮጥ አይደለም ወገኖቼ ለዓለማዊ ነገር ብቻ መክነፍ አይደለም።
እግዚያአብሔር ዛሬ ይጠይቀናል ።
በዚህ ቀን ችግረኞችን እንድንጠይቅ እግዚያአብሔር ይሻል።

                   ✥

የህለተ ሰንበ በረከት እረድኤት ከኛጋር ይኑር።

ሼር በማድረግ ቴሌግራም ቻናላችን ይቀላቀሉ።

👇👇👇👇👇👇👇
╔═✟✞════🇨🇬    ════✟✞═╗
         @dmse_tewado                       @orthodoxswi_eywet
╚═✟✞════🇨🇬    ════✟✞═╝
2025/06/28 13:35:46
Back to Top
HTML Embed Code: