Telegram Web Link
ንግድ ባንክ 7 ቢሊዮን ብር አልተዘረፍኩም አለ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በትናንትናው ዕለት ከባንኩ አካውንት ውስጥ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ ተዘረፈ በሚል በተለያዩ ሚዲያዎች የተሰራጨው ዘገባ ሐሰተኛ መሆኑን አስታወቀ።

ባንኩ ባወጣው መግለጫ፤ ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሚዲያ አገልግሎት (EMS) በተሰኘ የዜና ማሰራጫ “በኢትዮጵያንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በሚል እንደ ሰበር ዜና የተላለፈው መልዕክት የሐሰት ዘገባ ነው ሲል አስተብሏል።

በሚዲያዎቹ ከተዘገበው በተቃራኒ ከባንኩ ምንም የተዘረፈ ገንዘብ አለመኖሩንና ይልቁንም ከፍተኛ ገንዘብ ለመዝረፍ የተደረገ ሙከራ እንደነበር የጠቀሰው ባንኩ፤ ሙከራው በተደረገ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ በጠንካራው የውስጥ ቁጥጥር ስርአት አጠራጣሪ ግብይት መፈፀሙን ስለደረሰበት ምንም ዓይነት ገንዘብ ወጪ ሳይደረግ ሙከራው እንዲከሽፍ ማድረጉን ጠቁሟል፡፡ ከንግድ ባንክ የተሰጠው መግለጫ ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ቀርቧል፡፡


⬇️⬇️

ግንቦት 19 ቀን 2017 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ሚዲያ አገልግሎት በተሰኘ የዜና ማሰራጫ እንደ ሰበር ዜና የተላለፈ መልእክት “በኢትዮጵያ ንግድ ባንከ የውስጥ አካውንት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ከ7 ቢሊየን ብር በላይ መዘረፉ ተገለፀ” በማለት ባንካችን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተዘረፈ፣ ዘራፊዎቹ እንዳልተያዙና ባንካችንም ጉዳዩን አድበስብሶ እንዳለፈው የሚገልጽ የሐሰት ዜና ስለተዘገበ በጉዳዩ ላይ አጭር መግለጫ ለመስጠት ተገድደናል።

ከላይ የተጠቀሰው ሚዲያና ሌሎችም ይህንኑ ሚዲያ ያጣቀሱ ሚዲያዎች ከባንካችን ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ እንደተዘረፈ የሚገልጽ ዜና ቢዘግቡም፣ እውነታው ግን፡-

➢ በሚዲያዎቹ ከተዘገበው በተቃራኒ ከባንካችን ምንም የተዘረፈ ገንዘብ አለመኖሩን፣ ይልቁንም ከፍተኛ ገንዘብ ለመዝረፍ የተደረገ ሙከራ መሆኑን፣

➢ ባንካችን ሙከራው በተደረገ በጥቂት ደቂቃዎች ዉስጥ በጠንካራው የውስጥ ቁጥጥር ስርአታችን አጠራጣሪ ግብይት መፈፀሙን ስለደረሰበት ምንም ዓይነት ገንዘብ ወጪ ሳይደረግ ሙከራው ወዲያውኑ እንዲከሽፍ መደረጉን፣

➢ ሙከራው በጥቂት ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ባሰቡ ተጠርጣሪዎች የተፈፀመ እንጂ የባንካችንን ሲስተም ተላልፎ የተፈፀመ ጥቃት አለመሆኑን፣

➢ ባንካችን ሙከራ የተደረገበትን ገንዘብ ባለው ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓት አማካኝነት ከጥቃት ከተከላከለ በኋላ ጉዳዩን ለሚመለከተው የሕግ አካል በማሳወቅ ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉና የምርመራ ስራውም ተጠናክሮ እየተከናወነ የሚገኝ መሆኑን፣

➢ በማጠቃለያም ባንካችን እንደ ማንኛውም የፋይናንስ ተቋም በተለይም እንደ ግዙፍ የፋይናንስ ተቋምነቱ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት አስበው ለሚንቀሳቀሱ አካላት ኢላማ መሆኑ እሙን ቢሆንም፣ እንዲህ አይነቱን ሕገ ወጥ ተግባር ለመከላከል የሚያስችል ጠንካራ የቁጥጥር ስርዓትና የዘመነ ሲስተም ያለው ለመሆኑ ይህ የሙከራ ድርጊት መክሸፉ አንዱ ማሳያ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅትም ጉዳዩ በሕግ አካላት ተይዞ ጥብቅ ክትትል እየተደረገበት የሚገኝና የምርመራ ሂደቱም ያልተጠናቀቀ መሆኑን እያሳወቅን በቀጣይ የሕግ ሂደቱ ሲጠናቀቅ ዝርዝር መረጃውን የምናሳውቅ መሆኑን ለመግለጽ እንወዳለን፡፡

@YeneTube @FikerAssefa
👍2819😁17👀3
#ከቴምር ሪልስቴት

7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
6
የስራ ማቆም አድማውን ተከትሎ ሲኒየር ሀኪሞች 'ከፍተኛ የስራ ጫና' ውስጥ መግባታቸውንና ህሙማንም አስፈላጊውን አገልግሎት እያገኙ አለመሆኑን ገለጹ!

የደመወዝ ማስተካከያን ጨምሮ ሌሎች ጥያቄዎቻችን ይመለሱልን ሲሉ የጤና ባለሙያዎች በሀገር አቀፍ ደረጃ እያደረጉት ያለው የስራ ማቆም አድማ ሶስተኛ ሳምንቱን በያዘበት በአሁኑ ወቅት፤ በተለያዩ የሀገሪቱ አከባቢዎች በሚገኙ ሆስፒታሎች የሚሰሩ ሲኒየር ሀኪሞች "ከፍተኛ የስራ ጫና" ውስጥ መግባታቸውንና "ህሙማንም አስፈላጊውን አገልግሎት እያገኙ አለመሆኑን" ገልጸዋል።

ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ በጥቁር አንበሣ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሚሰሩ አንድ ሲኒየር ሀኪም፤ አሁን ላይ ብቻቸውን በርካታ የድንገተኛ ክፍል ታካሚዎችን ለመከታተል መገደዳቸውንና ይህም የስራ ጫናውን እንዳበረታባቸው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

"ህሙማንን ብቻዬን ነው ሳይ የነበረው። አንድ ዶክተር ብቻዬን ስለሆንኩ ቀድመው ቢታዩ ትልቅ ለውጥ ሊያመጡ የሚችሉ ህሙማን ሲሰቃዩ እያየሁ ነው" ብለዋል።

በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ንግስት እሌኒ መሀመድ መታሰቢያ ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ሲኒየር አድማን ተከትሎ ክፍተቱን ለመሙላት በስራ ላይ ቢሆኑም ሁኔታዎች አስቸጋሪ መሆናቸውን ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል። “በዚህ ሁኔታ መቀጠል አይቻልም" ብለዋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
39😭6👍1
ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ለሚሰነዘርባት ዘለፋ ምላሽ የመስጠት ፍላጎት የላትም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ!

ኢትዮጵያ በተለያዩ ጊዜያት ከጎረቤት ሀገራት ለሚሰነዘርባት ዘለፋዎች ምላሽ የመስጠት ፍላጎት የላትም ሲል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።ሚኒስቴሩ ዛሬ ግንቦት 21 2017 ዓ.ም በወቅታዊና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮረውን ሳምንታዊ መግለጫ፤ በቃል አቀባዩ አምባሳደር ነብያት ጌታቸው በኩል ሰጥቷል።

ቃል አቀባዩ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ሁልጊዜም የተሻለ ግንኙነት ለመፍጠር እንደምትሰራ ቃል አቀባዩ ተናግረዋል።ከሰሞኑ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የኤርትራን የነፃነት ቀን ግንቦት 16 ባከበሩበት ወቅት ባደረጉት ንግግር፤ ኢትዮጵያን በተመለከተ ሰፋ ያለ ንግግር አድርገዋል።ይህ ንግግራቸው በርካታ ኢትዮጵያዊያንን ያስቆጣ ሲሆን፤ የተለያዩ ሀሳቦችም እየተሰነዘሩበት ቆይተዋል።

ይህንን በተመለከት ጥያቄ የቀረበለት የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ በቃል አቀባዩ በኩል ምላሽ የሰጠ ሲሆን፤ ቃል አቀባዩ "ኢትይዮጵያ ለሚሰነዘሩባት ዘለፋዋች ምላሽ የምስጠት ፍላጎት የላትም" ብለዋል።ኢትዮጵያ የተረጋጋ አካሄድን የምተከተል ሀገር መሆኗን የገለጹት አምባሳደር ነብያት፤ "ከዚህ ቀደምም ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት በመሪዎቹ ደረጃ ተገቢ ያልሆኑ ክሶችና ዘለፋዋች ደርሶባት ያውቃል" ሲሉ ገልጸዋል።

"ኢትይጵያ ግን እንደዚህ ያለ እንካ ሰላምትያ ዉስጥ ሳተገባ በሰከነ ዲፕሎማሲ መንገድ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የምትቀጥል ነው የሚሆነው" ብለዋል።በሌላ በኩል የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሥም በመጠቀም 'ወደ ውጪ እንልካለን' የሚሉ አካላት መኖራቸውንም የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል

ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ ጋር በተያያዘ ከማይናማር ከ700 በላይ ዜጎችን መመለስ መቻሉንም አምባሳደሩ በሳምንታዊ መግለጫቸው ተናግረዋል።ይሁን እንጂ መንግሥት በዚሁ ሁሉ ጥረት እያደረገ ባለበት በዚህም ወቅት፤ ይህንን የሕገ-ወጥ መንገድ ተከትሎ የሚሄዱ ዜጎች አሁንም መኖራቸውን እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

'ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሕጋዊ ፍቃድ አለኝ' በማለትና የቀድሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሥም በመጠቀም ሀሰተኛ ማስረጃ በማስራጨት 'ወደ ውጪ እልካለሁ' የሚሉ ሐሰተኛ ግለሰቦች መኖራቸውን ሕዝብ ሊረዳ ይገባል ብለዋል።ይህ ሀሰተኛ ማስረጃ በተለያየ ማህበራዊ ሚዲዎች እየተሰራጨ መሆኑን የገለጹት አምባሳደሩ፤ ስህተት መሆኑን ሕዝብ ሊረዳ እንደሚገባም አሳስበዋል።"የሕገ-ወጥ መንገድ የሚወስዱ ደላሎች ሰንሰለታቸው ረጅም ርቀት ያለው ቢሆንም፤ ርምጃ ለመውሰድ ሥራዎች ቢሰሩም አሁንም ችግሩ አልተቀረፈም" ሲሉም ገልጸዋል።

Via Ahadu
@YeneTube @FikerAssefa
😁3432👎3👍1🔥1
Ethiopian Building Codes Standards
Private Sector Engagement in Building Code Revision


The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.

Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.

📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here

#EthiopianBuildingCodeStandards
Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector
9👍2
የአለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ለተረጂዎች እየሰጠ ያለው የሰብአዊ እርዳታ በሰኔ ወር ሊቆም እንደሚችል አስታወቀ!

- የገንዘብ ድጋፍ ባለማግኘቱ ለተረጂዎች እያከፋፈለ የሚገኘውን እርዳታ በከፍተኛ መጠን መቀነሱንም አመላክቷል

የተባበሩት መንግስታት የአለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) “ባጋጠመው የገንዘብ ድጋፍ እጥረት ሳቢያ በተያዘው አመት ሰኔ ወር ላይ በኢትዮጵያ በማካሄድ ላይ ያለውን የእርዳታ አቅርቦቱ ሊቋረጥ እንደሚችል አስጠነቀቀ፤ በመሆኑም በአሁኑ ወቅት የሚሰጠውን ለምግብ እርዳታ መጠን በከፍተኛ መጠን መቀነሱን አመላክቷል።

ባሳለፍነው ወር በኢትዮጵያ ያከናወናቸውን ተግባራት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ያጋጠመው የገንዘብ ድጋፍ እጥረት አስገድዶት “ለተረጂዎች የሚያከፋፍለው የምግብ እርዳታ መጠን በስታንዳርዱ መሰረት አንድ ተረጂ እንዲያገኝ ከሚጠበቃው በታች 65% ብቻ መሆኑን አመላክቷል”፣ በየካቲት ወር ለተረጂዎች ያከፋፍል የነበረው መጠን ከስታንዳርዱ ባነሰ መጠን ግን ደግሞ 80 % እንደነበር አስታውቋል።

የሚያከፋፍለው የምግብ እርዳታ መጠን ቅነሳ በተመሳሳይ በስደተኞች ላይ ተግባራዊ መደረጉን ገልጿል።

“በኢትዮጵያ አሁንም የቀጠሉት ግጭቶች፣ ድርቅ፣ ጎርፍ እና የዋጋ ግሽበት በሀገሪቱ ያለውን የምግብ ዋስትና ችግር እያባባሱት ነው”ብሏል፤ “በትግራይ ክልል ሲካሄድ የነበረውን ጦርነት የሰላም ስምምነቱ ቢያስቆመውም በሌሎቹ የሀገሪቱ ክልሎች በተለይም በአማራ እና ኦሮምያ ክልል በመካሄድ ላይ ያሉ በትጥቅ የተደገፉ ግጭቶች ኤጀንሲው ተጨማሪ ወጭ እያስወጣው፣ ለከፍተኛ አደጋ እያጋለጠው መሆኑን አስታውቋል።

@Yenetube @Fikerassefa
16👍8😭3
ከኢትዮጵያ ከተሞች መካከል በውሃ አቅርቦት “በጣም ትልቅ ችግር” ያለው በሻሸመኔ እንደሆነ የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ገለጹ

በኢትዮጵያ ካሉ ከተሞች ውስጥ በንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት “በጣም ትልቅ ችግር ያለበት” የሻሸመኔ ከተማ መሆኑን የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ሀብታሙ ኢተፋ ተናገሩ። በሀገሪቱ ያለውን የውሃ ሽፋን በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት መቶ በመቶ ለማድረስ ይቻል ዘንድ፤ ክልሎች እና ከተሞች “የኮብል ስቶን” መንገዶችን ለመስራት “ቅድሚያ እንደሚሰጡት” ሁሉ ለውሃ አቅርቦትም ተመሳሳዩን እንዲያደርጉ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል። 

ዶ/ር ሀብታሙ ይህን ያሉት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 19፣ 2017 በተካሄደው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። በዛሬው ስብሰባ ለሚኒስትሩ ጥያቄ ካቀረቡ ሰባት የፓርላማ አባላት መካከል አምስቱ በተመረጡባቸው አካባቢዎች ያለውን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር አንስተዋል።

ይህ ችግር የመረጣቸው ህዝብን በሚያነጋግሩበት ጊዜ በተደጋጋሚ የሚነሳ እና እነርሱም በአካል የተመለከቷቸው እንደሆነ ገልጸዋል። በገዢው እና በተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ተመራጮች በተመሳሳይ መልኩ የተነሳው ይህ ጉዳይ፤ ይበልጡኑ ተደጋግሞ የቀረበው በአማራ ክልል ተወካዮች ነው።

🔴 ዝርዝሩን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/16025/

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
26😁8👍2👎2👀2😭1
#ከቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
6😁2
Ethiopian Building Codes Standards
Private Sector Engagement in Building Code Revision


The Ethiopian Construction Authority, in collaboration with the College of Technology and Built Environment (formerly AAiT) and The Urban Center, is organizing a series of technical sessions in June 2025 to support the ongoing revision of the Ethiopian Building Code Standards.

Designed for professionals in the construction industry, the 14 expert-led sessions of EBCS will address key themes such as structural design, fire and earthquake safety, mechanical and electrical systems, and emerging building technologies. These sessions aim to highlight the building codes and gather input from the private sector, ensuring that industry experience is reflected in the revised codes, making them both inclusive and grounded in practice.

📍Venue: The Urban Center
📅 Participation by registration only
🔗 Register here

#EthiopianBuildingCodeStandards
Open to professionals, engineers, architects, and others in the construction sector
5
ሥራ ፈላጊ ነዎት
መልካም ዕድል‼️
1
በአማራ ክልል ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ከ30 በላይ አሽከርካሪዎች መታገታቸው ተገለጸ

                - በክልሉ ያለው የጸጥታ ችግር የአሽከርካሪዎችን ደህንነት አደጋ ላይ ጥሎታል ተብሏል

በአማራ ክልል ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ከ30 በላይ አሽከርካሪዎች "ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች" መታገታቸውን ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቀ።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ የማኅበሩ አመራር የአሽከርካሪዎች እገታ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ መኖሩን ገልጸው ሆኖም አሁን ላይ በክልሉ ካለው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል።

ከጨጨሆ በጋይንት: ደብረ ታቦር እስከ ወረታ መገንጠያ ድረስ ያለው መስመር የስጋት ቀጠና መሆኑን የገለጹት እኚሁ የማኅበሩ አመራር አያይዘውም ከጎንደር ጭልጋ እስከ መተማ ያለው መንገድ ለሁለት ወራት ያህል አገልግሎት አቋርጦ እንደነበረ ጠቁመዋል።

እንደ እሳቸው ገለጻ: ከዚህ በፊት በክልሉ በስፋት የሚስተዋለው የሾፌሮች ሞት የቀነሰ ሲሆን ይህም የሆነው ሾፌሮች በማታ የሚያደርጉትን ጉዞ በመቀነሳቸው መሆኑን አስረድተዋል፤ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከ50 ሺህ እስከ ሚሊዮን ብሮች ድረስ እንደሚጠይቁ ገልጸው ጉዳዩ አስቸኳይ እልባት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

ተጨማሪ ለማንበብ

https://addisstandard.com/Amharic/?p=7941
15😭6🔥1👀1
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በይፋዊ የ X ገፁ ላይ በትግርኛ ካሰራጨው በቀጥታ ተተርጉሞ የተወሰደ ነው።

"ኢትዮጵያ ካላት ጂኦ-ፖለቲካዊ እና ስልታዊ ጠቀሜታ፣ የህዝብ ብዛት እና ተፅዕኖ የተነሳ በአፍሪካ ቀንድ ጠቃሚ ሀገር መሆኗ ጥርጥር የለውም።

እስካሁን ኢትዮጵያ የምትመራው ከአፄ ምኒልክ ጀምሮ በአምስተኛው መንግሥት ነው።
ይሁን እንጂ በተለይ በብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ ሥር ከወደቀች በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ትርምስ ውስጥ ገብታለች።

ስለሆነም የኢትዮጵያ ዜጎች የሀገራቸው ሉዓላዊነት ሲደፈርስ እና አንድነታቸው መደፍረሱ በእጅጉ ያሳስባቸዋል።

በአሁኑ ወቅት የችግሩ ብቸኛ መፍትሄ ሁከት ነው ብለው በማመን በትጥቅ ትግል የሚካፈሉ ወገኖች በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች አሉ።
ከ2020-2022 ከባድ ጦርነት በኋላ ኢትዮጵያዊነቱ ወደ ኋላ የቀረ የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ አካል በመሆንም ሆነ በሌላ መንገድ ሰላምና ደህንነትን ይናፍቃል።

በአማራ ክልል ህዝቡ በመንግስታቸው ላይ እምነት አጥቶ ሰብአዊ መብቱንና ሀገራዊ ክብሩን ማስከበር ብቸኛ አማራጭ አድርጎታል፣የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲም ከጥይት ድምጽ አልወጣም።
የብልፅግና መንግስት በዋና ከተማው (በአዲስ አበባ) ብቻ ተወስኖ በህገ መንግስቱ ስም እየዘፈነ ያሉትን ችግሮች ችላ ማለትን የመረጠ ይመስላል።

እንደውም በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ለመፍታት ብስለትና ብቃት ያለው አይመስልም። ኢትዮጵያውያን በመንግስታቸው ጅልነት እንዲህ ያለ ያልተረጋጋ አካባቢ መጋፈጣቸው በእውነት ያሳዝናል። በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ በተፈጥሮው ለዜጎቿ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአፍሪካ ህዝብ እና ከዚያ እስከ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ድረስ አሳሳቢ ነው።

በአራት መንግስታት (በምኒልክ፣ በሃይለስላሴ፣ በደርግ እና በኢህአዴግ) ሉዓላዊነቷን እና አንድነቷን ያስጠበቀችው የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካል ቅርፅ አሁን ላይ ያለው ሁኔታ ብዙዎችን ያሳስባቸዋል" ይላል።

የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በተመለከተ ተመሳሳይ ትንተና እንደሚያቀርብ እና ቀጣይነት እንዳለው ገልጿል።
መንግሥት ሰሞኑን ኤርትራ እያራመደችሁ ያለውን ተከታታይ ዘለፉን በተመለከተ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል።


@Yenetube @Fikerassefa
81👍23👎10😁6
በአማራ ክልል ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ከ30 በላይ አሽከርካሪዎች መታገታቸው ተገለጸ!

በአማራ ክልል ባለፉት 15 ቀናት ብቻ ከ30 በላይ አሽከርካሪዎች "ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች" መታገታቸውን ጣና የከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር ለአዲስ ስታንዳርድ አስታወቀ።

ለደህንነታቸው በመስጋት ስማቸውን እንዳንጠቅስ የጠየቁ የማኅበሩ አመራር የአሽከርካሪዎች እገታ ከ2009 ዓ.ም ጀምሮ መኖሩን ገልጸው ሆኖም አሁን ላይ በክልሉ ካለው የጸጥታ ችግር ጋር በተያያዘ እየተባባሰ መምጣቱን ተናግረዋል።

ከጨጨሆ በጋይንት: ደብረ ታቦር እስከ ወረታ መገንጠያ ድረስ ያለው መስመር የስጋት ቀጠና መሆኑን የገለጹት እኚሁ የማኅበሩ አመራር አያይዘውም ከጎንደር ጭልጋ እስከ መተማ ያለው መንገድ ለሁለት ወራት ያህል አገልግሎት አቋርጦ እንደነበረ ጠቁመዋል።

እንደ እሳቸው ገለጻ: ከዚህ በፊት በክልሉ በስፋት የሚስተዋለው የሾፌሮች ሞት የቀነሰ ሲሆን ይህም የሆነው ሾፌሮች በማታ የሚያደርጉትን ጉዞ በመቀነሳቸው መሆኑን አስረድተዋል፤ ታጋቾችን ለማስለቀቅ ከ50 ሺህ እስከ ሚሊዮን ብሮች ድረስ እንደሚጠይቁ ገልጸው ጉዳዩ አስቸኳይ እልባት ሊሰጠው ይገባል ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
18
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7 በመቶ ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል – የአፍሪካ ልማት ባንክ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ባወጣው ሪፖርት፣ በተያዘው የአውሮፓ ዓመት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በ7 በመቶ እንደሚያድግ የሚጠብቅ መሆኑን አስታውቋል። ይህ ዕድገት ለሀገሪቱ የድህነት ቅነሳ እና የመዋቅራዊ ሽግግር ሂደት ወሳኝ ምዕራፍ እንደሆነ ባንኩ ገልጿል።

ከኢትዮጵያ በተጨማሪ፣ በዚህ ዓመት ኢኮኖሚያቸው በ7 በመቶ ያድጋል ተብለው ከሚጠበቁ የአፍሪካ ሀገራት መካከል ሴኔጋል፣ ሩዋንዳ እና ኒዠር ይገኙበታል።

ሪፖርቱ የምስራቅ አፍሪካ ቀጠና በ5.9 በመቶ ዕድገት ከአህጉሪቱ ቀዳሚውን ስፍራ እንደሚይዝም አመልክቷል። ይህም የሚሆነው ኢትዮጵያ፣ ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ያስመዘግባሉ ተብሎ ስለሚጠበቅ እንደሆነ የአፍሪካ ልማት ባንክ አክሎ ገልጿል።

[KGEthiopia]
@YeneTube @FikerAssefa
😁9611👍11😭2
ወደ ትግራይ ይጓዙ የነበሩ እና በአፋር ክልል ቆመው የሚገኙ የጭነት መኪኖች እንዲለቀቁ የክልሉ መንግስት ጠየቀ!

የሸቀጥ ጭነት ይዘው በአፋር ክልል በኩል ወደ ትግራይ ይጓዙ የነበሩ መኪኖች ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአፋር ክልል እንዳይንቀሳቀሱ መደረጋቸውን የትግራይ ክልል መንግስት አስታወቀ፤ የፌደራል መንግስት መፍትሔ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የንግድ እና ሰነድ ኤጀንሲ ለንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚንስቴር ለዶ/ር ካሳሁን ጎፌ በጻፈው ደበዳቤ ወደ ትግራይ ክልል ጭነት ይዘው የሚጓጓዙ ተሽከርካሪዎች መከልከላቸውን አስታውቆ ማብራሪያ ጠይቋል።

የክልሉ ቴሌቪዥን በበኩሉ ሁሉም የጭነት መኪኖች ህጋዊ መሆናቸውን የሚገልጽ ሰነድ ያላቸው ቢሆንም እንዳይጓዙ የተደረገበት ምክንያት እንዳልተገለጸላቸው አስታውቋል፤ በጭነት መኪኖቹ ክልከላ ዙሪያ ከፌደራል መንግስቱም ይሁን ከአፋር ክልል በኩል የተባለ ነገር አለመኖሩን አመላክቷል።

በአፋር ክልል ወደ ትግራይ በሚወስደው መንገድ ብቻ ሳይሆን በአማራ ክልል በወልድያ በኩል ወደ መቀለ የሚወስደው መንገድ ላይ የጭነት መኪኖቹ እንዳያልፉ መከላከልቸውን ቢቢሲ ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
21😁5👀3👍2😭1
አይ ኤም ኤፍ ለኢትዮጵያ ከሚሰጠው ብድር ውስጥ 260 ሚሊዮን ዶላር ሊለቅ ነው!

ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ) ባለሙያዎች፤ በተራዘመ የብድር አቅርቦት ሶስተኛ ግምገማ ላይ ከስምምነት ደረሱ። ግምገማው በአይ ኤም ኤፍ ስራ አስፈጻሚ ቦርድ ሲጸድቅ፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከዓለም አቀፉ ተቋም ከሚበደረው 3.4 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 260 ሚሊዮን ዶላር ይለቀቅለታል።

የአይ ኤም ኤፍ ቦርድ ግምገማውን ከማጽደቁ በፊት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ከይፋዊ አበዳሪዎች ጋር የመግባቢያ ስምምነት ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል። ይህንን ዛሬ አርብ ግንቦት 22፤ 2017 ይፋ ያደረጉት፤ ከሁለት ወር ገደማ በፊት ወደ አዲስ አበባ መጥቶ የነበረውን የአይ ኤም ኤፍ የባለሙያዎች ቡድን የመሩት አልቫሮ ፒሪስ ናቸው።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
👎3711👍5🔥1
የገንዘብ ሚኒስቴር አዲስ የታክስ ኦዲት መመሪያ አወጣ!

የገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ ኦዲት አፈጻጸምን እና የታክስ ስሌት ማስታወቂያ አወጣጥን የሚመራ አዲስ መመሪያ ቁጥር 1063/2017 አውጥቷል። መመሪያው በትላንትናው ዕለት ግንቦት 21 ቀን 2017 ዓ.ም. የወጣ ሲሆን፣ የታክስ አስተዳደር ሥርዓቱን ውጤታማ፣ ቀልጣፋና ግልጽ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።

ይህ አዲስ መመሪያ የታክስ ባለሥልጣን ባለሙያዎችንና ታክስ ከፋዮችን ኃላፊነት የሚደነግግ ሲሆን፣ በተለያዩ የታክስ ኦዲት ዓይነቶች ላይ፣ እንደ የተመላሽ ኦዲት፣ የዴስክ ኦዲት፣ ጭብጥ ተኮር ኦዲት፣ አጠቃላይ ኦዲት እና የማጭበርበር ምርመራን ጨምሮ ተፈጻሚ እንደሚሆን ይደነግጋል።

መመሪያው የፌዴራል መንግስትን የታክስ አዋጅ ድንጋጌዎች ተግባራዊ ለማድረግ የተሟላ ማዕቀፍ እንደሚሰጥ፣ እንዲሁም የኦዲት ሂደቱ ወጥነት ያለው፣ ግልጽነት የሰፈነበት እና የታክስ ከፋዮች መብት የሚጠበቅበት መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ተመላክቷል።

የታክስ ስሌት ማስታወቂያ የሚላከው ታክስ ባልተከፈለበት፣ ተጨማሪ ታክስ እንዳለ ሲረጋገጥ፣ ወይም ታክስ ማጭበርበር ጥርጣሬ ሲኖር የተባለ ሲሆን የመስክ ኦዲት ከመጀመሩ አስር የስራ ቀናት በፊት ለታክስ ከፋዩ የጽሁፍ ማስታወቂያ መሰጠት እንዳለበት ካፒታል ከመመሪያው ለመረዳት ችሏል።

ኦዲት በሚደረግበት ጊዜ ታክስ ከፋዮች ለኦዲተሮች ምቹ ሁኔታዎችን የማመቻቸትና የሚጠየቁ ሰነዶችን የማቅረብ ግዴታ እንዳለባቸው ያሳስባል።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
34👎9😁1
Forwarded from YeneTube
#ከቴምር ሪልስቴት
‼️7ሳይቶችን ስርተን አስረክበናል አሁን ላይ ደግሞ መሀል ሣር ቤት አፓርትመንት እና ሱቅ ፒያሳ ለሽያጭ ያወጣነው 

🎯የክፍያ አማራጮች 40/60 ለሚከፍል

👉1መኝታ 75ካሬ 4,815,000ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 94ካሬ 6,034,800ብር ሙሉ ክፍያ
👉2መኝታ 103ካሬ 6,612,600ብርሙሉክፍያ
👉3መኝታ 132ካሬ 8,474,400ብር ሙሉ ክፍያ
👉3መኝታ 146ካሬ 9,373,200ብር ሙሉ ክፍያ 9,373,000ብር 

‼️ፒያሳ ሱቅ ሽያጭ 
👉3.9ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ900,000ብር 4ተኛ እና 5ተኛ
👉4.2ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.2ሚሊዮን 3ተኛ
👉4.8ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 1.5ሚሊዮን 2ተኛ
👉5.5ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2ሚሊዮን 1ኛ
👉 7ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 2.8ሚሊዮን ግራውንድ በውስጥ በኩል
👉10ሚሊዮን 20ካሬ ቅድመ ክፍያ 4ሚሊዮን ግራውንድ በውጪ
ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251939770177
     +251996856273
https://www.tg-me.com/TemerRealEstateSalesConsultant
WhatsApp. https://wa.me/251939770177
8👎1😁1
2025/07/14 17:08:00
Back to Top
HTML Embed Code: