Telegram Web Link
Forwarded from YeneTube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ቴምርሪልስቴት
ከዚህ በፊት 7 ሳይቶችን ጥንቅቅ አርጎ ያስረከበዉ ቴምር ፕሮፐርቲስ አሁን
‼️ፒያሳ ሊሴ ገ/ማርያም ትምህርት ቤት ፊት ለፊት ያለውን ሳይት ለሽያጭ አውጥተናል

10% ቅድመ ክፍያ
ሰፊ የጋራ መገልገያ
ቢያከራዩት,ቢሸጡት ወይም ቢኖሩበት አዋጭ
ተመጣጣኝ ዋጋ

🏡  ሊሴ ገ/ማርያም አጠገብ
       👉1 መኝታ 63ካሬ=
     10% ቅድመ ክፍያ 693,000 ብር
        ሙሉ ክፍያ 6,930,000 ብር

         👉2 መኝታ 86 ካሬ
        10%ቅድመ ክፍያ 946,000 ብር
        ሙሉ ክፍያ 9,460,000 ብር

        👉3 መኝታ 114 ካሬ
      10%ቅድመ ክፍያ 1,219,800 ብር
      ሙሉ ክፍያ 12,198,000 ብር
       
👉ቀሪውን 90% በ16ዙር ብር ያለምንም
ጭማሪ በብር ከፍለው የሚጨርሱት

👉Other locations include
📌 ሳር ቤት
📌  አያት
👉30% እና ከዛ በላይ ለሚከፍል ከከፈሉት ላይ 25% ደረስ የሚደርስ ቅናሽ

⚠️በተጨማሪም ሱቅ በ900ሺ ብር ቅድመ ክፍያ እዛው ፒያሳ ሚኒሊክ አደባባይእየሸጥን እንገኛለን::

ለበለጠ መረጃ ይደውሉ
       👇👇👇👇👇👇
     +251976195835

WhatsApp
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835

Telegram user
@Ruthtemersales

TEMER PROPERTIES
Create | Construct | Deliver
#TemerProperties #Temerrealestate
Forwarded from YeneTube
🎨 Graphic Design Course Registration Now Open!
Unlock your creativity and learn the skills to design stunning visuals for social media, branding, and more.
Beginner-friendly
Hands-on projects
Certificate included

📅 Limited seats – Register today!

Call us:
          ☎️
0989747878
0799331774

@merahyan
Forwarded from YeneTube
አቅመ ደካማወችን ሀረጋውያኖችን በነፃ

https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN

በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
  44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
  አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ
Forwarded from YeneTube
Ethiopian Building Code Standards
Private Sector Engagement in Code Revision: Final Week – Week 4 Sessions


We're closing out our 14-part expert-led workshop series with two crucial technical sessions in Week 4:

🧱 Concrete Design & Specifications
📏 Technical Specs & Measurement Methods


📅 Tuesday, June 24, 2025
📍 The Urban Center, Addis Ababa
🖥 Live on TUC Facebook page & Google Meet (link shared 30 min before each session)
☕️ Free sessions with refreshments

📲 Register now: https://forms.gle/NewtRdbnasiUFW6r7

🔗 Let’s finish strong, join the conversation, contribute your perspective, and help shape Ethiopia’s future building code.

Many thanks to all our incredible partners for making this journey possible!

#EBCS #CodeRevision #BuiltEnvironment #ECA #CoTBE #TUC #EngineeringEthiopia #ConstructionStandards #UrbanDevelopment #ProfessionalEngagement
ኢትዮጲያ በቅርቡ የጋዛ ምርት ታቀርባለች አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለተነሱላቸው ጥያቄዎች ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው።

ኢትዮጲያ ጋዝ ምርትን ወደ ገበያ ልታቀርብ መሆኑን ያነሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፡፡ ሱማሌ ክልል ላይ ይህ ፕሮጀክት እውን መሆኑን በዛሬው እለት ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጲያ የራሷን ጋዝ ለማምረት ጥረት ስታደርግ መቆየቷን አስታውሰው ፡፡ ይህ የጋዝ ምርትም በመጪው መስከረም የ 2018 ዓ/ም አዲስ አመት ላይ ወደ ገበያ ሊቀርብ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የነበሩ በመንግስት ደረጃ ሲደረጉ የቆዩ ንግግሮች አልተሳኩም ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አዳዲስ ኩባንያዎችን በማስገባት አሁን ላይ ይህንን ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የዘንድሮው ዓመት ለኢትዮጵያ የማንሰራራት ዓመት ሆኗል ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ዘንድሮ ታላላቅ ውጤቶች የተመዘገቡበት፤ አመሪቂ ውጤቶች የታዩበት እና በኢትዮጵያ ታሪክ ታይተው የማያውቁ ድሎች የተጎናጸፍንበት ዓመት ነው” ብለዋል።

ለዚህ ድል መሳካት የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላት ቁጥጥር እና ድጋፍ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሕዝብ ላሳየው ድጋፍ በእኔ እና በኢፌዴሪ መንግስት ስም ምስጋናዬን አቀርባለሁም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡

@Yenetube
🇪🇹 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ ከምክር ቤቱ አባላት ለተነሱላቸው ጥናያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ነው

የሀገሪቱ መሪ እስካሁን ያነሷቸው ቁልፍ ጉዳዮች፦

◻️ ኢትዮጵያ በዘንድሮ የበጀት ዓመት 8.4% የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ አቅዳለች፣

◻️ በግብርናው ዘርፍ 6.1% እድገት ለማስመዝገብ ታቅዷል፣

◻️ 23 ሚሊየን ኢትዮጵያውያን ከሴፍቲኔት ተረጂነት ወጥተዋል፣

◻️ ዘንድሮ 1.5 ቢሊየን ኩንታል ምርት ተሰብስሷል፣

◻️ 85 ሄክታር መሬት ማልማት የሚችሉ 6 ከፍተኛ ግድቦች በቅርቡ ይመረቃሉ፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
የሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች ዲያጎ ጆታ ሕይወቱ ማለፉ ተሰማ!

የመርሲሳይዱ ክለብ ሊቨርፑል የፊት መስመር ተጫዋች የሆነው ፖርቹጋላዊው ዲያጎ ጆታ ንጋት አካባቢ ባጋጠመው የመኪና አደጋ ሕይወቱ ማለፉን ማርካ አስነብቧል።

ዛሞራ በተባለ አካባቢ በተከሠተው የመኪና አደጋ ህይወቱ እንዳለፈ የተገለጸው ዲያጎ ጆታ፤ አብሮት የነበረው ወንድሙም ሕይወቱ ማለፉ ተገልጿል።

የ26 ዓመቱ የጆታ ታናሽ ወንድም አንድሬ ሲልቫም ልክ እንደ ወንድሙ ሁሉ ፕሮፌሽናል እግር ኳስ ተጫዋች የነበረ ሲሆን፤ በፖርቱጋል ሁለተኛ ሊግ ለሚሳተፈው ፔናፌል በመጫወት ላይ ይገኝ ነበር።

የ26 እና የ29 ዓመት እድሜ ያላቸው ወንድማማቾቹ በጉዞ ላይ እንዳሉ አደጋ የገጠማቸው ሲሆን፤ መኪናውም በእሳት የተያያዘ መሆኑ ሲገለፅ አደጋውም ከበድ ያለ ነው ተብሏል።የሊቨርፑሉ ኮከብ ከአምስት ቀን በፊት የሠርግ ሥነ-ስርዓቱን በእስፔን ማከናወኑ ይታወሳል።

@YeneTube @FikerAssefa
በዝቋላ አንድ አባት መገደላቸውን ጠ/ሚኒስትሩ አመኑ፣ ግድያው በማን እንደየፈጸመ እየተጣራ ነው ብለዋል!

ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ (ዶ/ር) ዛሬ ሰኔ 26 ቀን 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርበው ከምክር ቤቱ ለተነሱ ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ “በዝቋላ አንደ የሐይማኖት አባት መገደላቸውን አስታውቀው ግድያው እየተጣራ ነው” ብለዋል።አንድ አባት ተገድለዋል፣ እየተጣራ ነው ማን እንደገደላቸው ተጣርቶ ምላሽ እንደሚያገኝ ተስፋ አደርጋለሁ” ብለዋል።

የሀይማኖት ተቋማት የታጠቁ ሀይሎች መሸሸጊያ ከሆኑ እንደዚህ አይነት አደጋ ሊያጋጥም ይችላል፣ የሀይማኖት ቦታ የሀይማኖት ብቻ መሆን አለበት፤ ሲሸሹ የሚደበቁበት ከሆነ ሲከፋቸው ገድለው ሊሄዱ ስለሚችሉ ሲሉ” ገልጸዋል።

በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን በሚገኘው በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ገዳም ሰኔ 13 ቀን 2017 ዓ.ም “የሸኔ ታጣቂዎች” ናቸው ተብለው የጠሩት የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት አባላት ፈጸሙት በተባለ ጥቃት አንድ ባሕታዊ አባት “በአሰቃቂ” ሁኔታ መገደላቸውን የገዳሙ አባቶችን ዋቢ በማድረግ መዘገ ይታወሳል።

በተመሳሳይ በሌላ ዘገባ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሰ) በበኩሉ በተፈጸመው ጥቃት ላይ እጁ አለበት መባሉን ማስተባበሉ የታወሳል።

ጠ/ሚኒስትሩ “12 አመት ተምሮ ለፈተና ወደ ትምህርት ቤት የሚሄድ ተማሪ ላይ የሚተኩሱ ሰዎች የሀይማኖት አባት ቢገድሉ ምን ይገርማል” ሲሉ ገልጸው፣ “ማዳበሪያ ለእርሻው ለመውሰድ የሚንቀሳቀስ ገበሬ ለምን ትወስዳለህ ተብሎም የሚገደልበት” ሁኔታ አለ ብለዋል።

በታጣቂዎቹ የተገደሉት ባሕታዊ ሀይለ ሚካኤል የተባሉ አባትን መሆናቸውን ምንጦቻችን መግለጻቸውን እና “በዱላ ቀጥቅጠው በጥይት ረሽነዋቸዋል” ሲሉ መናገራቸውን በዘገባው ተካቷል።

ይሁን እንጂ ከአዲስ ስታንዳርድ ጋር ቆይታ ያደረጉ እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነሰ) ከፌዴራል መንግስት ጋር ባካሄዳቸው በሁለቱም የሰላም ንግግሮች ላይ የተሳተፉ አንድ ከፍተኛ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አመራር፣ "አባላቱ በጥቃቱ ላይ ምንም አይነት ተሳትፎ የላቸውም" ሲሉ አስተባብለዋል።

Via AS
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ጦርነት እንዳይቀሰቀስ ኤምባሲዎችን ጨምሮ ጉዳዩ የሚመለከታቸው “በፍጥነት” ሚናቸውን እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ!

የትግራይ ክልል “ወደ ጦርነት እንዳይገባ” የሃይማኖት አባቶች፣ ባለሃብቶች፣ ምሁራን እና ኤምባሲዎች ሚናቸውን “በፍጥነት” እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ጥሪ አቀረቡ። በትግራይ ውጊያ ከተጀመረ፤ ከዚህ በፊት ከነበረው የተለየ እንደሚሆን ጠቅላይ ሚኒስትሩ አስጠንቅቀዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ያሉት ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 26፤ 2017 ዓ.ም በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው። በሁለት ክፍል የቀረበው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ቅድሚያውን እና ሰፊውን ጊዜ የሰጠው፤ የኢኮኖሚ ጉዳዮችን በተመለከተ ለቀረቡ ጥያቄዎች ነበር።

ሶስት ሰዓት ገደማ ከፈጀው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ውስጥ የሰላም እና ጸጥታ ጉዳይ የተመደበለት አንድ ሰዓት ያልሞላ ጊዜ ነበር። በዚህኛው የማብራሪያ ክፍል ከተነሱ ጉዳዮች ውስጥ ትግራይ እና ኤርትራን የተመለከቱት ይገኙበታል።

“የትግራይ ህዝብ መቶ ፐርሰንት ጦርነት አይፈልግም” ያሉት አብይ፤ ከህዝብ ፍላጎት እና አሁን ካለው ዓለም አቀፋዊ ነባራዊ ሁኔታ ውጭ በክልሉ ውጊያ ቢቀሰቀስ “ዓለም ደንታ የለውም” ብለዋል። “[ዓለም] ብዙ ውጊያ እያስተናገደ ስለሆነ፤ ጆሮም የለውም፣ ጊዜም የለውም። ዓለም ጊዜ ቢኖረው ኖሮ ሱዳንን ያዳምጥ ነበር” ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተደምጠዋል።

Via Ethiopia Insider
@YeneTube @FikerAssefa
በትግራይ ኃይሎች እና በ'ነጻ መሬት' ታጣቂዎች መካከል የተፈጠረው ምንድን ነው?

በትግራይ ክልል ወጀራት በተባለው ወረዳ በትግራይ ኃይሎች እና በሌሎች ታጣቂዎች መካከል ግጭት መፈጠሩን ቢቢሲ አረጋገጠ።ግጭቱ የተከሰተው በትግራይ ክልል ደቡባዊ ዞን ሰንዓለ የዞኑ አካባቢ በሁለቱ የታጠቁ ኃይሎች መካከል ማክሰኞ ሰኔ 24/2017 ዓ.ም. አመሻሽ ከ10 አስከ 11 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።

ግጭቱ በአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ስጋት እና ፍራቻ የፈጠረ ሲሆን፣ የአካባቢው የአገር ሽማግሌዎች በሁለቱ ታጣቂዎች መካከል ገብተው ለማሸማገል መሞከራቸውን የቢቢሲ ምንጮች ገልጸዋል።ከትግራይ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ የገቡት ታጣቂዎች እስካሁን ድረስ ይፋዊ ስም ባይኖራቸውም በተለምዶ 'የነጻ መሬት ተዋጊዎች' በመባል ይታወቃሉ።በሁለቱ ታጣቂ ኃይሎች መካከል የተፈጠረውን ፍጥጫ እና ተኩስ በተመለከተ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር አስካሁን ያለው ነገር የለም።

ተጨማሪ፡
https://www.bbc.com/amharic/articles/cp3l709w34go?fbclid=IwZXh0bgNhZW0CMTEAAR4J_ElBBYE-nKVQ0CK6wxtiTpYthE1C3RfFsIakvHcHRNaYQvhK65Y_1bWjzQ_aem_eRCCi6e2D1aWVp0slm07Ww

@YeneTube @FikerAssefa
2025/07/04 06:24:56
Back to Top
HTML Embed Code: