Telegram Web Link
አቅመ ደካማወችን ሀረጋውያኖችን በነፃ

https://vm.tiktok.com/ZMSayMdXa
በተለያየ የጤና ችግር የሚሰቃዩትን እየ ፈወሰ
ደስታቸውን እየመለሰ የሚገኘውን የህክምና ተቋም https://vm.tiktok.com/ZMSay8eV2/
ሰወች እንዴት እንደተፈወሱ ሲመሰክሩ እንስማ እንይ ቻናሉን እንቀላቀል
https://vm.tiktok.com/ZMSaDEhoN

በስጋውይም ሆነ በመንፈስ ደውየ ከተቸገሩ መተው በመመርመር ይታከሙ ይፈወሱ
  44ት አይነት በሽታወችን እየፈወስን እንገኛለን
  አድራሻ አዲስ አበባ አየርጤና ወደካራ ናትራን ኩፓንያ ፊት ለፊት
ቁጥር ሁለት ባህርዳር ዲያስፖራ በአሮጌው አስፓልት መስጊዱ ፊት ለፊት
☎️ 0917040506
☎️0912718883
ይደውሉ ይምጡ ይታከሙ ይፈወሱ ይመስክሩ
ዜና: "የኃይሌ ኃይሎች" የተሰኘና በአንጋፋው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የስኬት ሚስጥሮች ዙርያ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለምርቃት ሊበቃ ነው

"የኃይሌ ኃይሎች" ወይም 'Dissecting Haile' የተሰኘና በአንጋፋው አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የህይወት ስኬት ሚስጥሮች ዙርያ የሚያጠነጥን መጽሐፍ ለምርቃት ሊበቃ መሆኑ ተገለጸ።

የመጽሐፉን ምረቃ ቅድመ ዝግጅት አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ መርሀግብር ዛሬ ቅዳሜ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም በኃይሌ ግራንድ ሆቴል ተካሄዷል።

በመርሀግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የመጽሐፉ ደራሲ እና የአትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ ልጅ ሜላት ኃይሌ መጽሐፉ ስለ አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ የህይወት ፍልስፍናዎች የሚዳስስ መሆኑን አንስተዋል።

አክለውም መከራን ወደ ተጽዕኖ ለመለወጥ ለሚፈልጉ ሰዎች ምሳሌ የሚሆን እና ከሀይሌ ገብረስላሴ የህይወት ስኬቶች ጀርባ ያሉ ሚስጥሮችን ያካተተ መጽሐፍ መሆኑን ተናግረዋል።

አትሌት ሻለቃ ኃይሌ ገብረስላሴ በመርሀግብሩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉ ሲሆን "ብቻን ሆኖ ጀግና መሆን አይቻልም: እኔም ከቤተሰብ ጀምሮ የማህበረሰቤ ውጤት ነኝ" ብለዋል።

አክለውም በመጽሐፉ ላይ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ሰዎች ምስጋና አቅርበዋል።

"የኃይሌ ኃይሎች" /Dissecting Haile/ በ12 ምዕራፎች ተከፋፍሎ በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋዎች እንዲሁም በብሬል የተሰናዳ እንደሆነም ተገልጿል።

መጽሐፉ የፊታችን ነሐሴ 2017 ዓ.ም በኤሌክትሮኒክስ እና በሀርድ ኮፒ አማራጮች በይፋ ለአንባቢያን ይቀርባል ተብሏል።
ኦፌኮ ከተመድ የውጭ መረጃ አሰባሳቢ ልዑክ ጋር በ2018 ሀገራዊ ምርጫ ዙሪያ ተወያየ፤ የምርጫ ቦርድ እንደገና ማዋቀርን ጨምሮ ቁልፍ ጥያቄዎችን አቀረበ!

የኦሮሞ ፌዴራላሲት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ጋር በ2018 ዓ.ም. በሚካሄደው 7ኛው ዙር አጠቃላይ ምርጫ ዙርያ ውይይት ማድረጉን አስታወቀ።

በኦፌኮ ዋና ጽ/ቤት በተካሄደው ስብሰባ ላይ የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እና የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሱልጣን ቃሲም የተገኙ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ህብረት ቢሮ (UNOAU) የምርጫ ድጋፍ ክፍል ዋና ኦፊሰር የሆኑት አኪንየሚ ኦ. አዴግባላን ጨምሮ አራት አባላትን የያዘ ልዑክ መገኘቱን ከፓርቲው ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ኦፌኮ በስብሰባው ላይ ነጻ፣ ፍትሃዊ እና ተአማኒነት ያለው የምርጫ ሂደት እንዲረጋገጥ መንግስት ሊያሟላቸው የሚገቡ "መሰረታዊ" ጥያቄዎችን ማቅረቡ ተጠቁሟል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ኦፌኮ በ2018 ምርጫ ላይ መሳተፉ ሙሉ በሙሉ "በመሠረታዊ እና በተጨባጭ ለውጦች" ላይ የተመሰረተ መሆኑን ለልዑካን ቡድኑ አስረድተዋል።

"ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ቴክኒካዊ ሂደት ብቻ አይደለም፤ የዲሞክራሲያዊ ሂደት ውጤት ነው" ያሉት ፕሮፌሰር መረራ፣ "ይህ ሂደት ዛሬ በኢትዮጵያ የለም። በጦርነት እና በፖለቲካ ስደት ውስጥ ተአማኒነት ያለው ምርጫ ማካሄድ አይቻልም" ሲሉ አክለዋል።

ኦፌኮ በ2018 ዓ.ም አጠቃላይ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ መሠረታዊ ተቋማዊ እና ህጋዊ ማሻሻያዎች እንዲደረጉ የጠየቀ ሲሆን የምርጫ ቦርድን እንደገና ማዋቀርን ጨምሮ የምርጫ ስርዓት ማሻሸያ እንዲደረግ እና ከምርጫ በፊት በገዢው ፓርቲ እና በተቃዋሚ ፓርቲዎች መካከል ግልጽ የሆነ ፍኖተ ካርታ ላይ ለመስማማት የሚያስችል ውይይት እንዲካሄድ ጥሪ አቅርቧል።

በተጨማሪም በኦሮሚያና በመላ ኢትዮጵያ ያለው ግጭት እንዲቆም፣ የኦፌኮ አባላት፣ አመራሮችንና ደጋፊዎችን ጨምሮ በመላ አገሪቱ የታሰሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች፣ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ በተቃዋሚዎች ላይ የሚደርሰው ማስፈራራት፣ ወከባና እስራት እንዲቆም እና የጸጥታ ሀይሎች በፖለቲካው ሂደት ውስጥ ገለልተኛ የሚሆኑበት ስምምነት እንዲፈረም ጠይቋል።

@YeneTube @FikerAssefa
የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ለአርቲስት አንዱአለም ጎሳ ሰጥቶት የነበረውን ሽልማት ሰረዘ፤ ይቅርታም ጠይቋል!

የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ስሞኑን በተካሄደው አራተኛው የሀጫሉ ሁንዴሳ የሽልማት ፕሮግራም ላይ ለአርቲስት አንዱአለም ጎሳ ሽልማት መስጠቱ "ስህተት" እንደሆነ ገልፆ ሽልማቱን በይፋ መሰረዙን አስታወቀ።

በእጮኛው ቃናኒ አዱኛ ሞት ጋር በተያያዘ ተጠርጥሮ ለሶስት ወራት ታስሮ ከቆየ በኃላ በዋስ የተለቀቀው አርቲስት አንዱአለም ጎሳ ሰሞኑን የሀጫሉ ሁንዴሳ ሽልማት መሸለሙን ተከትለው የተለያዩ አካላት በማህበራዊ ሚድያ ተቃውሞዋቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል።

በተለይም ከሽልማት ፕሮግራሙ በኃላ በቀኔኒ አዱኛ ላይ የደረሱ አካላዊ ጉዳቶችን የሚያሳዩ ምስሎች በማህበራዊ ሚድያ በስፋት መሰራጨታቸውን ተከትሎ ፋውንዴሽኑ የሰጠውን ሽልማት እንዲሰርዝ የማህበራዊ ሚድያ ዘመቻ ሲደረግ ነበር።

ይህንን ተከትሎ የሀጫሉ ሁንዴሳ ፋውንዴሽን ዛሬ ሰኔ 28 ቀን 2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ ሽልማቱን ከማበርከቱ በፊት ጉዳዩን ሲከታተል መቆየቱን ገልፆ፤ ሽልማቱ ምርመራ እያደረገ ካለው የሚመለከተው አካል ባገኘው ደብዳቤ ላይ በመመስረት የተበረከተ መሆኑን ገልጿል።

ይሁን እንጂ "ሽልማቱን ተከትሎ ከህዝብ በደረሰን ሀሳብ እና ቅሬታ ላይ በመመስረት ውሳኔያችን ስህተት እንደ ነበር በፋውንዴሽኑ ቦርድ ተረጋግጧል "ብሏል። ፋውንዴሽኑ ለተፈጠረው ስህተት ህዝቡን ይቅርታ እየጠየቀ ለአርቲስት አንዱአለም ጎሳ ተሰጥቶ የነበረው ሽልማት መሰረዙን ገልጿል። ፋውንዴሽኑ የሰውን ልጅ መብት ከሚጥሱ እና ፍትህ ከሚያዛቡ አካላት ጋር አብሮ እንደማይቆም አረጋግጧል።

@YeneTube @FikerAssefa
ህወኃት ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ ለሰጡት ሃሳብ ምን አለ?

ጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ተገኝተው ትግራይን በተለይም የተከፋፈሉትን የህወሓት አመራሮች አስመልክቶ ለሰጡት ሃሳብ ህወኃት ባለ 3 ነጥብ መግለጫ አውጥቷል፡፡ በመግለጫው ምን አለ?

@YeneTube @FikerAssefa
በአሜሪካ ቴክሳስ የጎርፍ አደጋ 15 ሕፃናትን ጨምሮ የ51 ሰዎች ሕይወት አለፈ!

በማዕከላዊ ቴክሳስ በደራሽ ጎርፍ አደጋ 15 ሕፃናትን ጨምሮ 51 ሰዎች ከሞቱ በኋላ በመቶዎች የሚቆጠሩ የነፍስ አድን ሠራተኞች የጠፉ ሰዎችን ፍለጋ ተሰማሩ።በጣም የተጎዳው ኪር የተባለው አካባቢ ሲሆን 43 ሰዎች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ በጓዳሉፔ ወንዝ አጠገብ በሚገኘው የክርስቲያን ወጣቶች ካምፕ የነበሩ 27 ሕፃናት ደግሞ ጠፍተዋል።

የአካባቢው የፖሊስ አዛዥ ላሪ ሊታ "ፍለጋው ይቀጥላል። ሁሉም ሰው እስኪገኝ ድረስ ሥራው ይቀጥላል" ሲል ቃል ገብቷል።ትራቨስ እና ቶም ግሪን የተባሉ አካባቢዎችን ጨምሮ በሌሎች የግዛቱ ክፍሎች ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል።

በማዕከላዊ ቴክሳስ በሳምንቱ መጨረሻ ላይ በርካታ የደራሽ ጎርፍ ማስጠንቀቂያዎች ወጥተዋል።እስካሁን 850 የሚሆኑ ሰዎች በሕይወት መትረፍ ችለዋል።የቴክሳስ ገዥ ግሬግ አቦት ቅዳሜ ከሰዓት በኋላ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የፍለጋ ጥረቶችን ለማስፋፋት የአደጋ ጊዜ አዋጅ መፈራረማቸውን ተናግረዋል።የአካባቢው ባለስልጣናት "በዚህ ክስተት ሰለባ የሆኑትን እያንዳንዱን ሰው ፈልገው እንዲያገኙ ለማድረግ ሌት ከቀን እንሰራለን" ብለዋል።

የፍለጋ እና በሕይወት የማዳን ተልዕኮው እንደሚቀጥል የተናገሩት ባለስልጣናቱ፤ ይሁን እንጂ ጥረቱ በሕይወት የማዳን ጥረት አይደለም ብለዋል።በጎርፉ ተጠርገው የተወሰዱ ሰዎችን ለማግኘት የነፍስ አድን ሠራተኞች ወደ ጓዳሉፔ ወንዝ እየወረዱ መሆኑንም ተናግረዋል።

@YeneTube @FikerAssefa
ከባህር ኃይል ትልቅነት መለኪያዎች አንዱ የሆነው የተዋጊ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ (Aircraft Carrier) ነው።

እነዚህ ተንሳፋፊ የአየር ማረፊያዎች ጄቶችንና ሄሊኮፕተሮችን በምድር ላይ ወዳለ ማንኛውም ቦታ ያስነሳሉ።የተዋጊ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ በአየር ላይ የተመሰረቱ አውሮፕላኖችን ለመደገፍ እና ለማሰማራት የተነደፈ፣ በባህር ላይ የሚንቀሳቀስ የአየር ማረፊያ ሆኖ የሚያገለግል የጦር መርከብ ነው።

እነዚህ ግዙፍ መርከቦች ያሏቸው ሃገራትን እና አሜሪካ ከተቀረው አለም ያላትን የባህር እና አየር ሃይል ልዩነት የዳሰስንበትን ዝግጅት በዩትዩብ ገጻችን ላይ ይከታተሉ። ዝግጅታችን ከተመችዎ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ።

https://youtu.be/CeI0EpJQeGw
የእስራኤል እና የሃማስ  ድርድር ዛሬ  በዶሃ ለጋዛ ስምምነት እና ታጋቾችን ለመልቀቅ እንደገና ሊጀመር ነው

ይህ የሚሆነው ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ዋይት ሀውስ ከመጎብኘታቸው በፊት ነው።

ኔታንያሁ ቀደም ሲል የጦርነቱ ቁልፍ አስታራቂ ወደሆነችው ኳታር ቡድን እየላኩ መሆኑን አስታውቀው ነበር፤ ምንም እንኳን የሃማስ ምላሽ ለአሜሪካ ደጀንነት የተደረገው የተኩስ አቁም ረቂቅ ስምምነት “ተቀባይነት የሌላቸው” ፍላጎቶችን እንደያዘ ገልጸው ነበር።

አሁን ወደ 22ኛው ወር እየተቃረበ ያለውን ጦርነት ለማስቆም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ግፊት ተከትሎ ኔታንያሁ ሰኞ ዕለት ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ለመገናኘት ቀጠሮ ይዘዋል። ዶናልድ ትራምፕ ውጊያውን ለማቆም አዲስ ጥረት እያደረጉ ነው።

ከድርድሩ ጋር በቅርበት የሚያውቁ እና ከሃማስ ጋር ቅርበት ያላቸው የፍልስጤም ባለስልጣን ለአኤፍፒ እንደተናገሩት አለም አቀፍ አስታራቂዎች ለቡድኑ “አዲስ ዙር ተዘዋዋሪ ድርድር...ዛሬ በዶሃ ይጀምራል” ሲሉ አሳውቀዋል።

በዋናው ተደራዳሪው ካሊል አል-ሃያ የሚመራው የቡድኑ ልዑክ በኳታር ዋና ከተማ ደርሷል ሲሉ ባለስልጣኑ አክለዋል።

አርብ ዕለት ሃማስ በድርድሩ “ወዲያውኑ እና በቁም ነገር ለመሳተፍ” ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

የእስራኤል ተደራዳሪዎችም በመንገድ ላይ መሆናቸውን ያረጋገጡት ኔታንያሁ፣ “ሃማስ በኳታር የቀረበው ሃሳብ ላይ ሊያደርጋቸው የሚፈልጋቸው ለውጦች... ለእስራኤል ተቀባይነት የላቸውም” ብለዋል።

@Yenetube @Fikerassefa
ኢሎን መስክ የፖለቲካ ፓርቲ አቋቋመ

ኢሎን መስክ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ጋር ያለው የቅርብ ወዳጅነት በአለመግባባት ከተጠናቀቀ ከሳምንታት በኋላ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁሜያለሁ አለ።

ቢሊየነሩ የፖለቲካ ፓርቲን ማቋቋሙን ለሪፐብሊካን እና ዲሞክራቲክ የሁለት ፓርቲ ስርዓት ፈተና እንደሆነ በመግለጽ በማህበራዊ ሚዲያው ኤክስ ገጹ ላይ አስታውቋል።
ሆኖም ፓርቲው በይፋ በአሜሪካ የምርጫ ባለሥልጣን መመዝገቡ ግልፅ አይደለም
ከአሜሪካ ውጭ በመወለዱ ለአሜሪካ ፕሬዝዳንትነት ለመወዳደር ብቁ ያልሆነው መስክ ፓርቲውን ማን እንደሚመራው አልተናገረም።
መጀመሪያ ከትራምፕ ጋር በነበረው አለመግባባት ወቅት ፓርቲ የመመስረት ሃሳብን አንስቶ የነበረው መስክ፣ አለመግባባቱ እየተካረረ መጥቶ በአስተዳደሩ ውስጥ የነበረውን ኃላፊነት ለቅቆ ከቀድሞ የቅርብ ወዳጁ ጋር የተካረረ አለመግባባት ውስጥ መግባቱ የአደባባይ ሚስጥር ነበር።

መስክ ከፕሬዚደንት ትራምፕ ጋር የተካረረ አለመግባባት ውስጥ በነበረበት ወቅት የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን በአሜሪካ ውስጥ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ መኖር ይኖርበት እንደሆን የሚጠይቅ አስተያየት ለጥፏል።
መስክ በቅዳሜው ልጥፍ ላይ ያንን የሕዝብ አስተያየት በመጥቀስ "2 ለ 1 በሆነ ውጤት፣ አዲስ የፖለቲካ ፓርቲ እንዲኖር ፍላጎታችሁን አሳይታችኋል! አገራችንን በቆሻሻና በሌብነት ወደ ኪሳራ ስለመውሰድ ስንነጋገር የምንኖረው በአንድ ፓርቲ ስርዓት እንጂ በዲሞክራሲ አይደለም።" ሲል ጽፏል።

አክሎም "ዛሬ የአሜሪካ ፓርቲ የተመሰረተው ነፃነታችሁን ሊመልስላችሁ ነው" ብሏል።
ከቅዳሜ ጀምሮ የፌዴራል ምርጫ ኮሚሽን ፓርቲው በይፋ መመዝገቡን የሚጠቁሙ ሠነዶችን ይፋ አላደረገም።

በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ከተለምዷዊው የሁለት ፓርቲ ስርዓት ውጪ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችም ቢኖሩም፣ እውነተኛ ጫና ለመፍጠር በአገር አቀፍ ደረጃ ጠንካራ ተቀባይነት ማግኘት አዳጋች ነው።

ባለፈው ዓመት በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ እንደ ሊብሪተያን ፓርቲ፣ ግሪን ፓርቲ እና ፒፕልስ ፓርቲ ያሉ እጩዎች ትራምፕን ወይም የዴሞክራቲክ ተቀናቃኛቸውን ካማላ ሃሪስን እንዳያሸንፉ ለማድረግ ያልተሳካ ሙከራ አድርገዋል ።

መስክ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የትራምፕ ዋና ደጋፊ ነበር።

ባለፈው ዓመት በተደረጉ የምርጫ ቅስቀሳዎች ወቅት ከፕሬዚደንቱ ጎን በአጋፋሪነት የነበረው መስክ ሥልጣን ከያዙ በኋላም የአራት ዓመት ልጁ ትራምፕን እንዲያገኝ ኦቫል ኦፊስ ድረስ ይዞት መጥቷል።

መስክ የትራምፕን የምርጫ ቅስቀሳ በገንዘብ ከደገፉ ባለሀብቶች መካከል ዋነኛው ነው። ፕሬዚደንቱ ዳግም ሥልጣናቸውን እንዲይዙ 250 ሚሊዮን ዶላር አውጥቷል።

ከምርጫው በኋላም በፌዴራል በጀት ውስጥ የሚታዩ ወጪዎች ላይ ቅነሳዎችን የመለየት ኃላፊነት የተሰጠውን የመንግስት ቅልጥፍና (ዶጅ) ተብሎ የሚጠራውን ተቋም እንዲመራ ተሾመ።
ከትራምፕ ጋር የነበራቸው ውዝግብ የጀመረው በግንቦት ወር አስተዳደሩን ለቅቆ በወጣበት ጊዜ እና የትራምፕን ግብር እና የወጪ ዕቅዶችን በይፋ መተቸት ሲጀምር ነው።

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ "ትልቅ ቆንጆ" ሲሉ በይፋ የሰየሙት ረቂቅ በጀታቸው በአገሪቱ በምክር ቤት ጸድቋል።

ሕጉ ከፍተኛ ወጪን እና የግብር ቅነሳን ያካተተ ሲሆን በአሜሪካ በጀት ላይ በሚቀጥሉት አስርት ዓመታት ውስጥ ከሦስት ትሪሊየን ዶላር በላይ ጉድለት እንደሚያስከትል ተገምቷል።

በኤሌክትሪክ የሚንቀሳቀሱ መኪኖችን የሚያመርተው ግዙፉ ቴስላ ባለቤት የሆነው መስክ የትራምፕ ሕግ በአረንጓዴ ሽግግር ላይ ወይም እንደ ቴስላ ላሉ ምርቶች ድጎማ ማድረግ ላይ አያተኩርም ሲል ይተቻል።

ትራምፕ በዚህ ሳምንት በማኅበራዊ ድረ ገጻቸው ትሩዝ ሶሻል ላይ "ኤሎን በታሪክ ውስጥ ከየትኛውም የሰው ልጅ የበለጠ ድጎማ ሊያገኝ ይችላል" ሲሉ ጽፈዋል። "ያለ ድጎማ ኤለን ምናልባት ሱቁን ዘግቶ ወደ አገሩ ደቡብ አፍሪካ መመለስ ይኖርበታል።"

ትራምፕ የቢሊየነሩን ሌሎች ንግዶችን በመጥቀስ ለመስክ ኩባንያዎች የሚደረጉ ድጎማዎችን እንዲመለከት የቅልጥፍና ቢሮውን እንደሚያዙ ዝተዋል።

በተጨማሪም መስክ ለአሜሪካ መንግሥት ሮኬቶችን የሚያመጥቀውን ስፔስ ኤክስ እና ለአሜሪካ እና አውሮፓ የመከላከያ ኃይሎች የሳተላይት አገልግሎት የሚሰጠውን ስታርሊንክ ባለቤት ነው።

Via:- BBC
@Yenetube @Fikerassefa
የሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ገበያ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋዊ ግብይት ሊጀምር ነው

ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረው የኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋዮች ( ስቶክ ገበያ) በሚቀጥለው ሳምንት ሥራ ሊጀምር መሆኑ ተሰምቷል። ይህ እርምጃ ለአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ ታውቋል።

ገበያዉ በኖቬምበር 2023 በተደረገ የካፒታል ማሰባሰቢያ ዘመቻ 1.5 ቢሊዮን ብር በማሰባሰብ ከታሰበው ግብ በ631% በልጧል። ይህ ገንዘብ ከ48 የአገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ተቋማት የተገኘ መሆኑ ይታወቃል።

በሕዝብና በግል ሽርክና የሚሰራው አዲሱ የበይነመረብ ንግድ ልዉዉጥ መድረክን መንግሥት 25%፣ የግል ዘርፍ ደግሞ 75% ድርሻ አላቸዉ። አሁን ላይ ገዳ ባንክ አ.ማ. እና ወጋገን ካፒታል ኢንቨስትመንት ባንክ አ.ማ. በገበያው ላይ ከተመዘገቡት ኩባንያዎች መካከል ይጠቀሳሉ።

የሰነደ መዋዕለ ንዋይ በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ውስጥ እስከ 50 ኩባንያዎችን፣ በአሥር ዓመታት ውስጥ ደግሞ ከ90 በላይ ንግዶችን ለማካተት አቅዷል። ይህ ልውውጥ የኢትዮጵያን የፋይናንስ ዘርፍ ለማዘመን፣ ግልጽነትን ለማሳደግ እና ለንግዶች ካፒታል ማሰባሰቢያ አዳዲስ አማራጮችን ለመስጠት ያለመ ሲሆን፣ የኢኮኖሚ ዕድገትን እንደሚያነቃቃም ይጠበቃል።

ዝርዝሩን ያንብቡ
@Yenetube @Fikerassefa
አል-ፋሽጋ ዳግም በኢትዮጵያውያን እጅ ገባ

ለዘመናት የኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች የእርሻና የኑሮ መሰረት የነበረው ለም መሬት፣ አል-ፋሽጋ፣ ዳግም ወደ ህጋዊ ባለቤቶቹ ተመልሷል።

የሱዳን ጦር የኢትዮጵያን የውስጥ ችግር እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር፣ በአማራ ክልል፣ ምዕራብ ጎንደር ዞን የሚገኙትን የመተማና የቋራ ወረዳ ለም መሬቶችን በኃይል ተቆጣጥሮ ነበር።

በወቅቱ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በቅርብ ርቀት ላይ ሆኖ ሁኔታውን በትዕግስት ሲከታተል የነበረ ሲሆን፣ መንግሥትም ችግሩን በዲፕሎማሲና በውይይት ለመፍታት ያለውን ፍላጎት በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል፡፡

በዚህ የሱዳን ወረራ ወቅት ኢትዮጵያውያን ገበሬዎች ከእርሻቸው ከመፈናቀላቸውም በላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብልና የንብረት ውድመት እንደደረሰባቸው አይዘነጋም፡፡

የሱዳን ባለሥልጣናት ከሰሞኑ የኢትዮጵያ ታጣቂዎች በአገሪቱ መከላከያ ሠራዊት በመታገዝ የአማራ ክልል አዋሳኝ ወደኾኑ የሱዳን ለም መሬቶች በመስፋፋት ላይ ናቸው ሲሉ መክሰሳቸው ተዘግቦ ነበር፡፡

@Yenetube @Fikerassefa
2025/07/06 18:00:36
Back to Top
HTML Embed Code: