በጉርሱም ወረዳ በትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ!
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ጉርሱም ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ሕይወት አለፈ።አደጋው ከጉርሱም ወረዳ ወደ ጅግጅጋ ከተማ ሲጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ከባጃጅ ጋር በመጋጨቱ ነው የተከሰተው፡፡
በአደጋውም ባጃጁ ውስጥ የነበሩ የ6 ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ማለፉን በወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት የወንጀል መከላከል መምሪያ ም/ሃላፊ ኢንስፔክተር ቱሪ ድሪባ ለፋና ሚዲያ ኮርፖሬሽን ተናግረዋል።የተከሰተው አደጋ መንስኤ በፍጥነት ማሽከርከር መሆኑንም አብራርተዋል፡፡
Via FBC
@YeneTube @FikerAssefa

😭29❤9
አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ በአዲስ መዋቅር ስር ሆኖ እንደሚቀጥል አስታወቀች!
የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ኤጀንሲ (USAID) ቢዘጋም ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የተፈጸሙ “የሁለትዮሽ የእርዳታ ስምምነቶች” በሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስር በተዘረጋው አዲስ መዋር እንደሚቀጥሉ የአሜሪካ ኤምባሲ አስታወቀ። ኤምባሲው ዋነኛ ናቸው ያላቸው የሰብአዊ እርዳታ፣ ዓለም አቀፍ ጤና እና የምግብ ዋስትና መርሃ ግብሮች በአዲሱ መዋቅር እንደሚቀጥሉ ዛሬው ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል።
አሜሪካ በእነዚህ ዘርፎች ለኢትዮጵያ የምትሰጠው እርዳታ እንደሚቀጥል ኤምባሲው ማረጋገጫ የሰጠው፤ የሀገሪቱ ተራድኦ ደርጅት የሆነው USAID ባለፈው ምንት በይፋ መዘጋቱን ተከትሎ ነው። ላለፉት 64 ዓመታት በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሰብአዊ እና የልማት እርዳታ ሲያቀርብ የቆየው ይህ ተቋም የተዘጋው፤ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር ድርጅቱን ቀስ በቀስ ሲያዳክመው ከቆየ በኋላ ነው።
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት፤ ድርጅቱ የነበሩትን ኃላፊነቶች ካለፈው ሰኞ ሰኔ 24፤ 2017 ጀምሮ በይፋ ተረክቧል። ሽግግሩ “ድግግሞሽን ለመቀነስ”፣ “ተጠያቂነትን ለማጠናከር” እና የእርዳታ መርሃ ግብሮችን ከዩናይትድ ስቴትስ “የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ እና የብሔራዊ ደህንነት ዓላማዎች ጋር ለማጣጣም የሚያስችል” ሆኖ እንደተቀረጸ የአሜሪካ ኤምባሲ በዛሬው መግለጫ ጠቁሟል።
Via Ethiopia Insider

❤43😁12👍4🔥3👀2
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለንግድ ሱቅ ፈላጊዎች በሙሉ
📍 ፒያሳ ከሚኒልክ አደባባይ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር የሚወስደው መንገድ ላይ የንግድ ሱቆችን መሸጥ ጀምረናል።
👉 2 ቤዝመንት ያለው
👉ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉በ1 ዓመት ተኩል የምትረከቡት
👉ምድር ቤት
20 ካሬ= 7ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2.8ሚሊዮን ብር
👉1ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 5.5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2 ሚሊዮን ብር
👉2ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.8 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.5 ሚሊዮን ብር
👉3ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.2 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.2 ሚሊዮን ብር
👉4ኛ እና 5ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 3.9 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 900 ሺ ብር
👉ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፈል።
ለበለጠ መረጃ
09-76-19-58-35
Telegram username
@Ruthtemersales
Whats app
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835

❤8
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ፔንታጎን የመከላከያ መሳሪያዎችን በቅርቡ ወደ ዩክሬን እንደሚልክ አስታወቀ
የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ቀደም ሲል ለዩክሬን ተጨማሪ መሳሪያዎችን እንደሚልኩ ቃል ገብተው የነበረ ሲሆን ይህም በዋነኛነት "የመከላከያ" መሳሪያዎችን እንደሚመለከት አጽንኦት ሰጥተዋል።
የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ የያዘ ማንኛውም ጭነት የሩሲያ ሕጋዊ ኢላማ እንደሚሆን ተናግረዋል።
👉 ሚኒስትሩ የኔቶ አባል ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ በማቅረብ "በእሳት እየተጫወቱ ነው" ሲሉ አስረግጠዋል። ክሬምሊን ዩክሬንን በምዕራባውያን የጦር መሳሪያዎች ማጨናነቅ በሩሲያ-ዩክሬን ድርድር ስኬት ላይ አስተዋፅኦ እንደማያደርግ እና አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው በአበክሮ አስታውቋል።
@Yenetube @Fikerassefa

❤13👍3🔥3😁3👀3
የኦሞ ወንዝ መሙላትን ተከትሎ በደረሰ አደጋ ከ65 ሺሕ በላይ ዜጎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ!
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በዳሰነች ወረዳ የኦሞ ወንዝ መሙላቱን ተከትሎ ከ65 ሺሕ በላይ ዜጎች ከቀዬአቸው መፈናቀላቸው ተገልጿል፡፡በዚህም ከ15 ሚሊዮን በላይ የዋጋ ግምት ያላቸው የሰብአዊ እርዳታዎችን ለተፈናቀሉ ዜጎች ማቅረብ መቻሉን በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማሕበር የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ለአሐዱ አስታውቋል።
የኦሞ ወንዝ በከፍተኛ ሁኔታ በመሙላቱ በርካታ አርብቶ አደሮችን ከቀዬያቸው ማፈናቀሉን ለአሐዱ የገለጹት፤ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ተስፋዬ ዱንዳ ናቸው።ተፈናቃዮች በጊዜያዊ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ መደረጉን የገለጹት ኃላፊው፤ የምግብ እህልና መጠጦች፣ የሕክምና መገልገያዎች እና ሌሎች ግብዓቶች እንደቀረቡላቸው አስታውቀዋል።
በአሁኑ ወቅት የውሃው መጠን ከተለመደው ውጪ እየጨመረና ሰፊ ቦታ እየያዘ ከመምጣቱ የተነሳ ለኦሞራቴ ከተማ ማህበረሰብም አደጋው እንደሚያሰጋ ተናግረዋል።ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ በመቀናጀት ውሃው ወደ ከተማውና መንደሮች ዘልቆ እንዳይገባ የግድብ ሥራ በመስራት ጊዜያዊ መፍትሄ የመስጠት እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የውሃውን አቅጣጫ የማስቀየርና የማፋሰስ ሥራዎች ከዚህ ቀደም የተጀመሩ ቢሆንም፤ በባለሃብቶች እርሻ ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያስከተለ በመሆኑ በጅምር መቆሙን አስታውሰዋል። በቀጣይ ዘላቂ መፍትሄ ለመስጠት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተማከሩ መሆኑንም ኃላፊው ጠቁመዋል፡፡አያይዘውም፤ በተደጋጋሚ የሚከሰተውን የጎርፍ አደጋ በዘላቂነት መፍትሔ ለመስጠት ጥናት መጀመሩን ገልጸዋል።
ችግሩን ለመፍታት የምክክር መድረኮች ተዘጋጅተው በወንዙ አቅራቢያ የሚኖሩ ነዋሪዎችን ወደ ሌሎች አካባቢዎች እንዲሰፍሩ እና የተወሰኑ የሕብረተሰብ ክፍሎችን እንዲነሱ መደረጉን ተናግረዋል።
ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ከኦሞ ወንዝ ሙላት ጋር ተያይዞ በአካባቢው በተደጋጋሚ የጎርፍ ማጥለቅለቅ አደጋ ሲከሰት እንደነበር የተናገሩት ኃላፊው፤ አምና ከ79 ሺሕ በላይ አርብቶ አደሮች በወንዙ ሙላት መጥለቅለቅ ከመኖሪያ ቀዬአቸው በመፈናቀላቸው እስከ ዛሬ በጊዜያዊ ማቆያ ስፍራ እንዲቆዩ መደረጉን አንስተዋል፡፡
ቢሆንም ለእርሻ ሥራ በሚል ወደ ቀድሞ ቀዬአቸው በተመለሱት ዜጎች ላይ የአሁን የውሃ ሙላት መጠነኛ ጉዳት ማስከተሉን ገልጸዋል፡፡በወረዳው ባለፉት 8 ዓመታት በተደጋጋሚ የጎርፍ አደጋ ተከስቶ በ34 ቀበሌዎች የሚኖሩ ከ79 ሺሕ 828 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው መፈናቀላቸው አይዘነጋም።የጎርፍ አደጋው ከነዋሪዎች መፈናቀል ባለፈ፣ የእንስሳት ሞትን ጨምሮ በእርሻ መሬት እና በንብረት ላይ ጉዳት ማስከተሉም የሚታወስ ነው።
Via Ahadu

❤5😭1
አሜሪካ የጣለችውን ከፍተኛ ታሪፍ ተፈፃሚነት በማዘግየት በአንዳንድ አገሮች ላይ አዲስ የታሪፍ ምጣኔ አስተዋወቀች!
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ አሜሪካ በሚገቡ ምርቶች ላይ ጥለውት የነበውን ከፍተኛ ታሪፍ ተፈፃሚነት አዘገዩ።ፕሬዝዳንቱ ጃፓን እና ደቡብ ኮሪያን ጨምሮ ለ14 አገራት የተጣለባቸውን አዲስ ቀረጥ የያዘ ደብዳቤ ልከዋል።
ይህ የታወጀው በገቢ ምርቶች ላይ ተጥሎ የነበረው ታሪፍ የ90 ቀናት የእፎይታ ጊዜው ከመጠናቀቁ ከቀናት አስቀድሞ ነው።ፕሬዝዳንት ትራምፕ ማስፈራሪያቸውን ቀጥለው ከጃፓን እና ደቡብ ኮሪያ በሚገቡ ምርቶች ላይ ከነሐሴ 1/2025 ጀምሮ ተፈፃሚ የሚሆን የ25 በመቶ ታሪፍ የጣሉበትን ደብዳቤ ይፋ አድርገዋል።
የዋይት ሐውስ ባለሥልጣናት የንግድ ድርድር ለማድረግ ሲባል ገታ አድርገውት የነበረው ከፍተኛ ታሪፍ እ.አ.አ ሐምሌ 9 ጀምሮ እንዲተገበር ቀን ተቆርጦለት ነበር።

❤16👎2😁1
ሳዑዲ አረብያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በሞት የምትቀጣቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ነው - አምነስቲ
አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናል ያወጣው አዲስ ሪፖርት እንደሚያሳየው በሳዑዲ አረብያ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የሞት ቅጣት የሚተላለፍባቸው የውጭ ሀገር ዜጎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል።አብዘሃኛዎቹ የሞት ቅጣት የተፈጸመባቸው እኒሁ ዜጎች ፈጸሙት ከተባሉት ወንጀሎች መካከል ከፍተኛ ቁጥሩን የሚይዘው የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውር መሆኑን ሪፖርቱ አመላክቷል።
የአደንዛዥ ዕጽ ዝውውር ወንጀል በአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ህግ እና መለኪያ የሞት ቅጣት የሚያስወስን አይደለም ያለው አምነስቲ ባሳለፍነው የሰኔ ወር ብቻ ሳዑዲ አረብያ 46 ሰዎች በሞት የቀጣች ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 37ቱ ከአደንዛዥ እጽ ጋር በተያያዘ መሆኑን ጠቁሟል፤ ከነዚህ ውስጥ 34ቱ ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ የውጭ ሀገር ዜጎች ናቸው ብሏል።
ለአምነስቲ ኢንተርናሽናል አናገርኩት ያለው አንድ የሞት ፍርድ የተላለፈበት ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ “የፍርድ ቤት ዶክመንታቸውን መያዝ አለመያዛቸውን አናውቅም… ምንም አይነት ህጋዊ ሰነድ ማግኘት አልቻልንም፣ ምክንያቱም በሃገር ውስጥ ጉዳዩን የሚከታተልልን ሰው ስለሌለን፣ ህጋዊ ተወካይ ስለሌለን፣ የቋንቋ ችግርም አለ” ሲል መግለጹን ሪፖርቱ አካቷል።

❤27😭16😁1👀1
በአለም አቀፍ ደረጃ ለሰብአዊ እርዳታ የሚሰበሰበው ገንዘብ ቀነሰ!
የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው አመት በዚህ ጊዜ 9 ቢሊዮን ዶላር በአለም አቀፍ ደረጃ ለሰብአዊ ጉዳዮች የተሰበሰበ ሲሆን በዚህ አመት ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ሊል ችሏል።
@YeneTube @FikerAssefa
የኖርዌይ የስደተኞች ካውንስል ያወጣው መረጃ እንደሚያሳየው ባለፈው አመት በዚህ ጊዜ 9 ቢሊዮን ዶላር በአለም አቀፍ ደረጃ ለሰብአዊ ጉዳዮች የተሰበሰበ ሲሆን በዚህ አመት ወደ 6 ቢሊዮን ዶላር ዝቅ ሊል ችሏል።
@YeneTube @FikerAssefa
❤14😭6👀1
ግብጽ በድጋሚ የቀይ ባህር ደህንነት ላይ ትኩረት አደርጋለች፣ ከሶማሊያ ጋር ጠንካራ ወታደራዊ ግንኙነት ለመመስረት ቃል ገብታለች!
የግብፅ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ ኤል ሲሲ አሁንም በድጋሚ በቀይ ባህር ደህንነት ላይ ያተኮረ መልዕክት ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም አስተላልፈዋል፤ የቀይ ባህርን ደህንነት ለማስጠበቅ እንደሚሰሩ ገልጸዋል። ግብጽ ለሶማሊያ የምታደርገውን ወታደራዊ ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉም ቃል ገብተዋል።
ፕሬዝዳንቱ ይህንን መልዕክት በድጋሚ ያስተላለፉት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድን በግብፅ የባህር ጠረፍ ከተማ ኤል አላሜይን ሰኔ 29 ቀን 2017 ዓ.ም ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው፤ በአፍሪካ ቀንድ ውጥረት እየጨመረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሁለቱ መሪዎች በውይይታቸው ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል ተብሏል።
ሁለቱ መሪዎች ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ በግብጽ በኩል የወጣው መግለጫ አንደሚያትተው መሪዎቹ የሁለቱን ሀገራት ሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል፣ በተለይም በሶማሊያ ደህንነት እና መረጋጋት ዙሪያ በዝርዝር ተነጋግረዋል ብሏል።
ፕሬዝዳንት አልሲሲ በተደጋጋሚ በአፍሪካ ቀንድ እንዲሁም በቀይ ባህር ደህንነት እና መረጋጋት ዙሪያ አስተያየት ሰጡ ወይንም ተወያዩ የሚሉ አገላለጾች መሰማት የጀመሩት ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ. በ2024 መጀመሪያ ላይ ከሶማሌላንድ ጋር የመግባቢያ ስምምነት ከተፈራረመች በኋላ ነው።
በኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ዙሪያ ከሁለቱም ወገኖች ምንም አይነት ድምጽ እየተሰማ ባይሆንም ኢትዮጵያውያ በቀጥታ የባህር በር ለማግኘት የምታደርገው ጥረት አሁንም ከግብፅም ሆነ ከሶማሊያ በኩል በጥርጣሬ እና በስጋት የሚታይ ነው።
Via AS

❤47😁11👎8😭3
Forwarded from YeneTube
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለንግድ ሱቅ ፈላጊዎች በሙሉ
📍 ፒያሳ ከሚኒልክ አደባባይ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር የሚወስደው መንገድ ላይ የንግድ ሱቆችን መሸጥ ጀምረናል።
👉 2 ቤዝመንት ያለው
👉ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉በ1 ዓመት ተኩል የምትረከቡት
👉ምድር ቤት
20 ካሬ= 7ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2.8ሚሊዮን ብር
👉1ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 5.5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2 ሚሊዮን ብር
👉2ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.8 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.5 ሚሊዮን ብር
👉3ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.2 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.2 ሚሊዮን ብር
👉4ኛ እና 5ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 3.9 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 900 ሺ ብር
👉ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፈል።
ለበለጠ መረጃ
09-76-19-58-35
Telegram username
@Ruthtemersales
Whats app
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835
📍 ፒያሳ ከሚኒልክ አደባባይ ወደ ሀገር ፍቅር ቲያትር የሚወስደው መንገድ ላይ የንግድ ሱቆችን መሸጥ ጀምረናል።
👉 2 ቤዝመንት ያለው
👉ከ 900,000 ብር ቅድመ ክፍያ ጀምሮ
👉በ1 ዓመት ተኩል የምትረከቡት
👉ምድር ቤት
20 ካሬ= 7ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2.8ሚሊዮን ብር
👉1ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 5.5 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 2 ሚሊዮን ብር
👉2ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.8 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.5 ሚሊዮን ብር
👉3ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 4.2 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 1.2 ሚሊዮን ብር
👉4ኛ እና 5ኛ ፎቅ
20 ካሬ= 3.9 ሚሊዮን ብር
ቅድመ ክፍያ= 900 ሺ ብር
👉ቀሪው በግንባታ ሂደት የሚከፈል።
ለበለጠ መረጃ
09-76-19-58-35
Telegram username
@Ruthtemersales
Whats app
Message Temer properties on WhatsApp. https://wa.me/251976195835
❤4
Forwarded from YeneTube
በሩን ይክፈቱ ችግረወን
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
ይፍቱ ህመምወን ይዳኑ
ዐሊንኩን ይጫኑ ይቀላቀሉ
https://vm.tiktok.com/ZMSqDLvo7/
https://vm.tiktok.com/ZMSqD4rLk/
ሙሉ አድራሻ አዲስ አበባ ባሕርዳር
0912718883
0917040506
👎5❤2
በኦሮሚያ ክልል በውጪ ዜጎች አንድ የደጋ አጋዘን በ15 ሺህ ዶላር እየታደነ መሆኑን ባለስልጣኑ ገለፀ!
በኦሮሚያ ክልል የውጪ ዜጎች በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኘውን የደጋ አጋዘንን በ15 ሺህ ዶላር እያደኑ መሆኑን ክልሉ አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።የኦሮሚያ ክልል አካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ቦና ያዴሳ፤ “የውጪ ዜጎች አንድ አጋዘን ለማደን 15 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ይከፍላሉ፤ ያደኑትንም አጋዘን ከአንገት በላይ ያለው አካል ይዘው መሄድ ይችላሉ” ብለዋል።
ዋና ዳይሬክተሩ፤ የደጋ አጋዘን በአርሲ እና ባሌ ተራራማ ስፍራዎች እንዲሁም በምዕራብ ሀረርጌ በስፋት የሚገኝ መሆኑን ጠቅሰው የውጪ ሀገር ዜጎችም ለስፖርታዊ አደን የሚመርጡት ብርቅዬ እንስሳ መሆኑን ተናግረዋል።አሁን ላይ በአዳባ እና ዶዶላ አካባቢዎች ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ለውጪ ዜጎች የደጋ አጋዘንን ለአደንነት እንዲያቀርቡ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
አደኑን የሚያደርጉት የውጪ ዜጎች ፈቃድ የሚሰጣቸው ሲሆን፤ በአካባቢው ከተደራጁ ኢንተርፕራይዞች ጋር በመሆን ያረጀ ወንድ የደጋ አጋዘን ተመርጦ እንዲያድኑ ይደረጋል ሲሉ ለኢፕድ ተናግረዋል። ማንኛውንም የደጋ አጋዘን ማደን ፈጽሞ የተከለከለ መሆኑንም አክለዋል፡፡ከአደኑ የሚገኘው ገቢ 70 በመቶ ለኢንተርፕራዞች የሚገባ መሆኑና 30 በመቶውን መንግስት እንደሚወሰድም አቶ ቦና ተናግረዋል፡፡
በዚህም ኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ የሚገኘውን የደጋ አጋዘን ለውጪ ሀገር ዜጎች ለሕጋዊ አደን በማቅረብ የህብረተሰቡን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ከፍ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡

😭38❤19😁5👀2👍1
የአሜሪካ አየር ማረፊያዎች በደህንነት ፍተሻዎች ወቅት ጫማ ማውለቅን ሊያስቀሩ ነው!
የዩናይትድ ስቴትስ አየር ማረፊያዎች በትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር (TSA) በሚካሄዱ የደህንነት ፍተሻዎች ወቅት ተሳፋሪዎች ጫማቸውን እንዲያወልቁ የሚያስገድደውን እና ከ20 ዓመታት በፊት ገደማ የተጀመረውን ብዙም ተቀባይነት የሌለውን ፖሊሲ ሊያስቆሙ ነው።
የሃገር ውስጥ ደህንነት ኃላፊ ክሪስቲ ኖውም ምንም እንኳን "ተከታታይ" የፍትሻ ሂደቱ እንዳለ ቢቆይም ለውጡ በመላው የአሜሪካ አየር ማረፊያዎች ላይ ወዲያውኑ ተግባራዊ ሆኗል ብለዋል ።
መንገደኞች አሁንም ቀበቶዎችን እና ካፖርቶችን ማውለቅ እንዲሁም ላፕቶፖችን እና ፈሳሾችን ከቦርሳ ማውጣት አለባቸው፣ ነገር ግን እነዚህም ሂደቶች እየተገመገሙ ናቸው ሲሉ ኖውም ተናግረዋል።
አየር መንገድ ተሳፋሪዎች ለምርመራ ጫማ እንዲያወልቁ የሚጠይቀው መስፈርት በአገር አቀፍ ደረጃ ተግባራዊ መሆን የጀመረው እ.አ.አ ከ2006 ጀምሮ አንድ እንግሊዛዊ ወደ ማያሚ በሚጓዝ በረራ ላይ በአንዱ ጫማው ውስጥ ቦምብ ከደበቀ በኋላ ነበር።
ኖውም ማክሰኞ ዕለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ "የእኛ የደህንነት ቴክኖሎጂ በከፍተኛ ሁኔታ ተቀይሯል፣ ተሻሽሏል። የትራንስፖርት ደህንነት አስተዳደር ተለውጧል" ብለዋል።

❤11👍4
ስኳር በእርግጥ ልጆችን ሃይፐርአክቲቭ(ከመጠን በላይ የነቁ) ረባሾች ያደርጋል?
https://www.tiktok.com/@sociosaga/video/7524997823616584965

❤1😁1
የሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ የኢትዮጵያ ብር ከሩብል ጋር ያለውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ሊወስን መሆኑ ታወቀ!
ባንኩ በተጨማሪ የ11 ሀገራት ገንዘቦች ከሩሲያ ማዕከላዊ ባንክ ጋር ያላቸውን ይፋዊ የምንዛሪ ተመን ለማስቀመጥ ውሳኔ ላይ መድረሱ ታውቋል።
እነርሱም የባንግላዴሽ ታካ፣ የባህሬን ዲናር፣ የቦሊቪያ ቦሊቪያኖ፣ የኩባ ፔሶ፣ የአልጄሪያ ዲናር፣የኢራን ሪያል፣ የሚያንማር ኪያት፣ የሞንጎሊያ ቱግሪክ፣ የናይጄሪያ ናይራ፣ የኦማን ሪያል እናየሳዑዲ ሪያል ናቸው።ባንኩ የምንዛሪ ተመኑን ከሀምሌ 3 ጀምሮ ይፋ እንደሚያደርግ ኢንተርፋክስ ዘግቧል፡፡

😁8❤5